Kolfe P.P - ብልፅግና @kolfepp Channel on Telegram

Kolfe P.P - ብልፅግና

@kolfepp


Kolfe P.P - ብልፅግና (Amharic)

ክልፈ ፓ.ፓ - ብልፅግና, አዲስ ቡቬት ከተደረገ እና በተለይነቱ እባኮት በአንድ አማራ ነበር ። ከዚህ በላይ አብሮ ከፒክኬንክ ውስጥ የባለዉን መረጃ ይዟል ። አንዴ ላይ በልፅፍግና ላይ በተለይ ነበር። እንደkolfepp ተስፋ ውስጥ ነበር ። እና አ ውስጥ በፉትር ላይ ሀሰቻሆሎች እና በተለይ ነበር። ከkolfepp በፉትሮ ያቀረቡ እንቅስቃሴ አለኝ ይለናል ።

Kolfe P.P - ብልፅግና

09 Nov, 19:57


#የሃሳብ_ልዕልና_ለሁለንተናዊ_ብልጽግና!!

የብልፅግና ፓርቲ 5ተኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክኒያት በማድረግ የኮልፌ ቀራንዮ አስተዳደር "የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለሁለንተናዊ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል እሁድ ህዳር 1/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ ቤተል እሳት አደጋ አከባቢ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያካሂዳል።

#aa_prosperity
#Kolfe
Prospertiy Party Kolfe Keraniyo Sc Branch - ብልፅግና

Kolfe P.P - ብልፅግና

01 Jul, 08:16


አረንጓዴ አሻራ የኢትዮጵያ ህዝብ ለችግሮች በቀላሉ እጅ የማይሰጥና ጠንካራ መሆኑን ማሳያ ነው !!

ኢትዮጵያ የበለፀገ ታሪክ፣ ባህልና ብዝሃነት ያላቸው ህዝቦች በጋራ የሚኖሩባት ሀገር ናት። እንደ ሀገር ድህነት፣ ድርቅ፣ ግጭትና የአየር ንብረት ለውጥ የመሳሰሉ ብዙ ፈተናዎች ገጥመዋታል። የሀገራችን ግብርና የኢኮኖሚው ዋና ምሶሶ ቢሆንም በዝናብ የዝናብ፣ የውሃ ሃብት እና የተፈጥሮ ስነ-ምህዳር ላይ ከፍተኛ ጥገኛ በመሆኑ ለአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ እጅግ ተጋላጭ ነው። የአየር ንብረት ለውጥ የኢትዮጵያን የልማት ግቦች ፈተና ላይ የሚጥል እና የሚሊዮን ህዝብ መተዳደሪያ የሆነውን ግብርና አደጋ ላይ የሚጥል ነው።

ኢትዮጵያ ግን በቀላሉ ተስፋ የምትቆርጥ ሀገር አይደለችም። እድገቷንና ብልፅግናዋን ለመጪዎቹ ትውልዶች ማስቀጠል የሚችል ለአየር ንብረት ለውጥ ተመራጭ የሆነ አረንጓዴ ኢኮኖሚን የመገንባት ራዕይ ያላት ሀገር ናት።

የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ እና ለማላመድ፣ የተራቆተ አካባቢውን ወደነበረበት ለመመለስ እና የተፈጥሮ ካፒታልን ለማሳደግ ደፋርና ትልቅ እርምጃ የወሰደች ሀገር ናት።

መልካም እለተ ሰኞ ተመኘን
#kolfe_prospertiy_party- ብልፅግና
#kolfepp

Kolfe P.P - ብልፅግና

26 Jun, 08:40


የብልጽግና ተምሳሌት የሆነች እንደ ስሟ አዲስ እና አበባ ከተማ በመገንባት ቃል በተግባር እንፈፅማለን !!

አዲስ አበባን እንደ እንደ ስሟ አዲስ እና አበባ የማድረግ ስራው በአመራሮቻችን ቁርጠኝነት እና ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ 7/24 መርህ አድርጎ በመስራት የኢትዮጵያን ብልፅግና አይቀሬነት የታየበት ከመሆኑም በላይ የስራ ባህልን ከአስተሳሰብ ጀምሮ የቀየርንበትም ነው ።

የአዲስ አበባ ስሟን የሚመጥን የቱሪዝም መዳረሻ እና በአለም ተወዳዳሪ ከተማ በማድረግ በአለም ላይ ተወዳዳሪ እና ተመራጭ የማድረግ ስራ በፓርቲያችን ራዕይ በመነሳት ከተማ እና የከተማ ልማትን በማፋጠን እና ከተሜነትን ማስፋፋት መሰረት ያደረገ ነው ።

የኮሊደር ልማት ቃል በተግባር የመፈጸም በተግባር የታየበት ኘሮጀክትን በጥራት እና ፍጥነት ጊዜ መፈጸም የተቻለበት ነው። ይህን ተግባር በሁሉም መስክ አጠናክሮ በመቀጠል የኢትዮጵያን ሁለተናዊ ብልፅግና ማረጋገጥ ይገባል ።

መልካም ቀን ይሁንለዎ!
#Kolfe_Prosperity_Party- ብልፅግና
#kolfepp

Kolfe P.P - ብልፅግና

30 May, 13:55


የረዳን ፈጣሪ ክብርና ምስጋና ይሁንለት!

"በጎነት"ብለን በሰየምነው የመኖሪያ መንደር የተገነቡ ሁለት ባለ 9 ወለል ዘመናዊ ሕንጻዎችን እና የስራ ዕድል መፍጠሪያ ማዕከላትን መርቀን ለ140 አቅመ ደካሞች እና አካል ጉዳተኛ ነዋሪዎች አስተላልፈናል።

በልደታ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ቆርቆሮ ሰፈር በሚባለው የተጎሳቆለ የመኖሪያ መንደር ይኖሩ ለነበሩ አቅመ ደካሞች፣ አካል ጉዳተኞች፣ ማየት ለተሳናቸው፣ ለተለያየ ማህበራዊ ችግር ለተጋለጡ እና በልማት ለተነሱ ነዋሪዎች ያስተላለፍናቸው ምቹ የመኖሪያ ቤቶች ሳሎን፣ መኝታ ቤት፣ የማብሰያ እና የመጸዳጃ እንዲሁም የመኝታ ክፍሎች ያላቸው ዘመናዊ ቤቶች ናቸው።
በዚህ የበጎነት መንደር ካስተላለፍናቸው የመኖሪያ ቤቶች ጋር በማቀናጀት የእናቶችን ጫና የሚያቀል የህጻናት ማቆያ፣ ለአካባቢው እናቶች የስራ ዕድል የሚፈጥር ዘመናዊ የእንጀራ መጋገሪያ፣ የሚሰሩ እጆችን ከስራ የሚያገናኙ የወንዶችና የሴቶች የውበት ሳሎኖችን እንዲሁም የልብስ ስፌት ማሽኖችን አዘጋጅተን ለነዋሪዎቹ የስራ እድል ፈጥረናል።

በመኖሪያ መንደሩ ቤት ለሰጠናቸው ማየት የተሳናቸው ነዋሪዎች እንቅስቃሴ እጅግ አስፈላጊ የሆኑ ኬኖች፣ ለአካል ጉዳተኛ ነዋሪዎች ደግሞ ክራንችና ዊልቸሮችን አዳርሰናል።
ሰርቶ ካገኘው ላይ ለወገን በጎ ለመስራት ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመተባበር ቤቶቹን የገነባውን ሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በራሴና በነዋሪዎቹ ስም እያመሰገንኩ፣ በጎነት አያጎድልምና ፈጣሪ ጨምሮ እንዲሰጠው እመኛለሁ።

የሚሰሩ ልማቶች ሁሉ ለሰው ልጆች ተስፋ የሚሰጡ እና የኑሮ ጫናን የሚያቃልሉ ይሆኑ ዘንድ ሰው ተኮርነታችን በተግባር የሚገለጽ ነው።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Kolfe P.P - ብልፅግና

26 May, 09:11


በክፍለ ከተማው የስልጤ ልማት ማህበር (ስልማ) አመታዊ ኮንፈረንስ በአሁኑ ሰዓት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በኮንፈረንሱ አቶ አሊ ከድር የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የስልማ ልማት ማህበር ቦርድ ሰብሳቢ፣የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ንገቱ ዳኛቸው ፤የኢትዮጵያ ኢንተር ፖራይዞች ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አብዱልፈታ የሱፍ፤የክፍለ ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ፅ/ቤት ሃላፊ እንዲሁም የክፍለ ከተማው ስልማ ኮሚቴ አስተባባሪ አቶ ኢብራሂም መሀመድ፣የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የልማት ማህበሩ አባላት እና የክብር እንግዶች ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

በሸወ ከተመ በኮልፌ ጎ/ከተመ የስልጤ ላቶ ሴረ /ስልመ/ አይደኜ ኮንፈረንስ በትረሶት ደር ኢትረከባን።

የዲን አቦትቸ የፌድራል፣የከተመ አትንዳዳሪ ዋ የጎ/ከተማይ ጎትለኜ ዋሻሾ ፣የባድ ባሊቅቸ ፣የላቶ ሴራይ ቆራርቸ ዋ የማልነግዳዶ ዋ ሉላ ሉሌ የፌሩይ አመሠብ በትረከበቢ ኤት ባውጄ አያም ኢትሀበዳን።