👍 የወይራ ትምህርት ቤት በቢታኒ ክርስቲያን ሰርቪስ ተሰርቶ የተበረከተ የምግብ ማብሰያ እና የተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ የማቴሪያል አቅርቦት በደማቅ ሁኔታ አስመርቆ ተረክቧል።
👍በዚህም መሠረት ቢታኒ ክርስቲያን ሰርቪስ ለትምህርት ቤታችን ቤቱን ከመስራት በተጨማሪ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ከፍተኛ መዋእለ ነዋይ በማፍሰስ ለትምህርት ቤታችን አስረክቧል።
1. ደረጃውን የጠበቀ፣ የልብስ መቀየርያ እና ማረፍያ ክፍል ያለው 120 ካሬ ስኩዌር ሜትር የሚሰፋ የማብሰያ እና የመመገቢያ አዳራሽ።
2. 10 የኤሌክትሪክ ምጣድ
3. 10 ትልቁ የኤሌክትሪክ ስቶቭ
4. 5 ባለ 48 ሊትር ጎላ ድስት
5. 5 ባለ 42 ሊትር ጎላ ድስት
6. 600 የሻይ መጠጫ ኩባያ
7. 600 የመመገቢያ ሰሀን
8. 600 ማንኪያ
9. 100 ሜትር የውሃ ቱቦ
10. 10 ትልቁ ወጥ መጨለፊያ ጭልፋ፤ 10 ትልቁ ቢለዋ፤ 10 ትልቁ ማማሰያ፤ 10 ትልቁ መክተፊያ፤ 10 ትልቁ ሳፋ፤ 7 መጥረጊያ፤ 7 መወልወያ፤ 5 ማንቆርቆሪያ በድምሩ ሶስት ሚሊዮን ብር የሚገመት ወጪ ተረክበናል።
✍በመርሀ ግብሩ ላይ የኮ/ቀ/ክ/ከ/ት/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ገነነ፤ የወረዳ 06 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሸናፊ የወረዳ 06 ፅ/ቤት አቶ አንበሴ፣ የቢታኒ ክርስቲያን ሰርቪስ አመራሮች እና የተለያዮ እንግዶች ታዳሚ ሆነዋል።
✍የወይራ ትምህርት ቤት ለዚህ ስራ መሳካት ታላቅ አስተዋፅኦ ላደረገው ለቢታኒ ክርስቲያን ሰርቪስ ድርጅትና ተሳታፊዎች የምስክር ወረቀትና ስጦታ ከላቀ ምስጋና ጋር አበርክቷል።
Unity is power!!