🕋 ISLAMIካ🧐 @islamika_born_muslim789 Channel on Telegram

🕋 ISLAMIካ🧐

@islamika_born_muslim789


በዚህ ቻናል እንባን ከአይን የሚያፈሱ አፍን በእጅ የሚያስይዙ ጥቅሶች በኢስላማዊ ለዛ የተዋዙ ውብ፣ልብ የሚነኩ፣ የተለያዩ ፅሁፎች እና ስራዎች ይለቀቃሉ::
የአኼራ ማስታወሻ
ኢስላማዊ ስነልቦና
ለአስተያየት 👇👇👇
@Usman_mustofa
ለመቀላቀል/join ለማድረግ
👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/ISLAMIKA_BORN_MUSLIM789

🕋 ISLAMIካ🧐 (Amharic)

🕋 ISLAMIካ🧐 is a Telegram channel where born Muslims can find inspirational quotes, motivational speeches, religious teachings, and job opportunities in an Islamic setting. The channel provides a platform for individuals who are looking for uplifting content, career guidance, and job opportunities. Whether you are seeking religious guidance, spiritual motivation, or job prospects, ISLAMIካ🧐 has something for you. Join now to stay connected with like-minded individuals and access valuable resources. Follow @Usman_mustofa to join and be part of this enriching community. Don't miss out on the chance to expand your knowledge and network. Click on the link below to join: https://t.me/ISLAMIKA_BORN_MUSLIM789

🕋 ISLAMIካ🧐

03 Feb, 06:36


መሰናዶ ለረመዳን

ይህ ወር ለረመዳን የምናሟሙቅበት የ10 ወር የወንጀል ሸክማችንን የምንጥልበት በኢባዳ ለመብረር ዱብዱብ የምንልበት ወደ ቅዱሱ ወር ለመክነፍ በኢባዳ የምንንሳፈፍበት መጥፎ ተግባራትን መፈፀም የምናቆምበት ነው።


- በዚህ አይነት በጎ ምግባር ልምምድ የተሳለችው ነፍሳችን በረመዳን መምጠቅ አይከብዳትም የሰማያትን ቅጥር ጥሳ ምልጃዋንም ታሰማለች

እንዘጋጅ! ተዘጋጁ!

አላህ ሆይ ለረመዳን እድርሰን

🕋 ISLAMIካ🧐

02 Feb, 10:30


የረመዳን ኮቴ እየተሰማ ነው

- በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ተሻግረን ዛሬ ከ ሀያ ምናምን ቀናት ርቀት ላይ ረመዳንን እያማተርን ነው

- አዎ ከረመዳን ጋር ከተለያየን እና ጨክኖ ጥሎን ከሄደ 10 ወራት አለፉን

- እኛም በትካዜ እና በጉጉት ውስጥ ሆነን ወደ ሩቅ ሀገር ልጇን እንደሸች እናት የረመዳንን መመለስ በናፍቆት የጊዜ በር ላይ ቆመን እየተጠባበቅን ነበር

አሁን ሻእባን ደረሰ እና የረመዳንን የመምጣት ኮቴ ዳናውን ከሩቅ አሰማን የምስራችም አለን።

- ረመዳን ሆይ ናፍቀንሀል እና ቶሎ ድረስ ሳንጠግብህም ትተኸን አትሂድ ከበረከትህ ፣ ከእዝነት ወርነትህ ብዙ መቋደስ እንሻለንና

💧ሻእባንን በመፆም እና በመልካም ስራ እናሳልፈው የነገውን ሰኞ መፆምን እናስታውሳለን

🕋 ISLAMIካ🧐

01 Feb, 19:33


ማ͟͟ስ͟͟ታ͟͟ወ͟͟ሻ͟͟
ሸ͟ዕ͟ባ͟ን͟ ከ͟መ͟ው͟ጣ͟ቱ͟ በ͟ፊ͟ት͟
:
የቀደመ የረመዳን ቀዷ ያለበት መጪው #ረመዳን ሳይገባበት ቀዷውን አውጥቶ ይጨርስ። ቀዷ ማውጣት እየቻለ ሳያወጣው ተከታዩ ረመዳን የገባበት ሰው: ‐
⚀ ኃጢኣተኛ ይሆናል፤
⚁ ቀዷእ ማውጣቱ አይቀርለትም፤
⚂ ፊድያ (ቤዛ) ማውጣት ግዴታ ይሆንበታል። ፊድያው ለአንድ ቀን አንድ እፍኝ ነው። አመቱ በጨመረ ቁጥርም ፊድያው ለአንድ አመት አንድ እፍኝ እየጨመረ ይመጣል።
:
በህመም፣ በማጥባት፣ በእርግዝና ወይም በሌላ ሸሪዓዊ ምክንያት ቀዷውን መክፈል ያልቻለ ሰው ግን በተመቸው ጊዜ ብቻ ቀዷ ማውጣት ይበቃዋል።
ይህ የሻፊዒዮች እና የአብዝሃኛዎቹ ልሂቃን ሃሳብ ነው!
ረመዷን ሊገባ ነውና እንተዋወስ!
መልካም አዲስ የሥራ ሳምንት ይሁንልን!
https://t.me/fiqshafiyamh

🕋 ISLAMIካ🧐

31 Jan, 05:21


ሰርግዎን በውብ የቀረፃ ጥበብ እናስውባለን

- በአስደማሚ የኤዲቲንግ ጥበብ ከሽነን ሰርግዎን ፊልም አስመስለን በፍጥነት እናሰርክብዎታለን 

0912027023 ወይም በቴሌግራም @Usmanoman ላይ ያናግሩን

"እንኳን ለተቀደሰው የሰርግዎ ቀን አደረስዎ"

#አለም_ፕሮዳክሽን
#wedding_ceremony
#ትዳር_ቅዱስ_ትስስር

🕋 ISLAMIካ🧐

30 Jan, 16:49


~ ዕለተ ሐሙስ፤ረጀብ 30-1446 ዓ.ሂ ላይ ደርሰናል፡፡ለታላቁና ተወዳጁ ረመዷን 30 ወይም 29 ቀን ቀረው፡፡ ሸዕባን ወር ነገ ይገባል።

ሸዕባን - ከረመዷን ቀጥሎ ነቢዩ (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) በብዛት የፆሙት ወር ነበር።ወሩ የዓመት ሥራዎቻችን አላህ ዘንድ የሚቀርቡበት ወር ነው፡፡

• ውዱ ነቢያችንም ለምን እንደሚፆሙት ተጠይቀው በረመዷን እና በረጀብ መካከል ስለሚገኝ ብዙዎች ይዘናጉበታል፣ ፆመኛ ሆኜ ሥራዬ አላህ ዘንድ ቢቀርብ እወዳለሁ ብለዋል፡፡

• ሸዕባን መፆም ለረመዷን ፆም መዘጋጃና አካልንና መንፈስንም ማለማመድ ነው፡፡

• ሸዕባን ላይ ረመዷን በእጅጉ ይናፍቃል፣ ወሬው ሁሉ ስለ ረመዷን ይሆናል፡፡

• አላህ ሆይ ሸዕባንን ባርክልን ለረመዷን በሰላም አድርሰን፡፡
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

🕋 ISLAMIካ🧐

29 Jan, 15:26


https://youtu.be/rtbIh_nu79w?si=ctNwQHxnbKn5VKha

🕋 ISLAMIካ🧐

26 Jan, 10:29


👑የላቀ ምንዳ አለው!

ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿المؤمنُ الَّذي يخالطُ النّاسَ ويصبرُ على أذاهم أعظمُ أجرًا منَ المؤمنِ الَّذي لاَ يخالطُ النّاسَ ولاَ يصبرُ على أذاهم﴾

“ከሰዎች ጋር ተቀላቅሎ በሚያስቆጣው ድርጊታቸው የታገሰ ሙዕሚን የተሻለና የላቀ ምንዳ ይኖረዋል፤ ከሰዎች ጋር ካልተቀላቀለና በድርጊታቸው ከማይታገስ ሰው ይልቅ።”

📚 ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል አልባኒ ሶሂህ ብለውታል፡ 3273

✔️በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

💬፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

💬፦ https://bit.ly/486xnrS

🌐፦ https://bit.ly/41zEZkk

🌐፦ https://bit.ly/4arMbTx

🌐፦ https://bit.ly/41tIUPv

🌐፦ https://bit.ly/3UTTSwh

🕋 ISLAMIካ🧐

26 Jan, 09:27


የአምላኬ ወዳጅነት

ያልተፃፈ የመዋደድ ታሪክ ነው የእኔ አንተ ነገር
ያልተነገረ የፍቅር ገድል

አንተ ስለ እኔ ታውቃለህ
ማንም የማያውቀውን ያህል

እኔ ለአንተ ያለኝ
አንተ ለኔ ያለህ ወዳጅነት

(የኔ እና የጌታዬ አብሮነት)

በጊዜ መስፈሪያ ውስጥ
እስከ ዘላለም የተዘረጋ ሰንሰለት

ጌታዬ እኔ እወድሃለሁ😭

🕋 ISLAMIካ🧐

24 Jan, 03:51


የትራንስፖርት ዋጋ መጨመር ያስከተለው ምስቅልቅል እና ምሬት

(መሠረት ሚድያ)- ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ፣ በተለይ ደግሞ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻ ከተደረገ ወዲህ የኑሮ ውድነት ተባብሶ ቀጥሏል።

የመገበያያ ዋጋቸው እጅግ እየጨመሩ ከመጡ ምርቶች አንዱ ነዳጅ ነው። የዛሬ ሁለት አመት በዚህ ወቅት ቤንዚን በሊትር 61 ብር ነበር፣ ነጭ ናፍጣ በሊትር 67 ይሸጥ ነበር፣ ኬሮሲንም በሊትር 67 ብር ነበር።

አሁን ላይ ቤንዚን 101 ብር ከ47 ሳንቲም ገብቷል፣ ናፍጣ ደግሞ በሊትር 98 ብር ከ98 ሳንቲም ሆኗል፣ በሌሎች የነዳጅ ምርቶች ላይም በትንሹ ከ8 ብር በላይ ተጨምሯል።

ታድያ የዚህ የነዳጅ ዋጋ ማሻቀብ የህዝብ ትራንስፖርቱ ዋጋም በእጅጉ እንዲያሻቅብ ምክንያት ሆኗል። በተለይ በተለይ በአዲስ አበባ ዳርቻ አካባቢዎች በሰፈሮችና በኮንዶሚኒየምዎች የሚኖሩ ዜጎች ለትራንስፖርት የሚያወጡት ወጪ እጅግ በጣም ጨምሮ ኑሮን እንዳከበደባቸው ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል።

ለምሳሌ በኮዬ ፈጬ፣ በአራብሳ፣ በቂሊንጦ፣ በቱሉዲምቱ ወዘተ... የሚኖሩ ዜጎች ከነዚህ መኖሪያ መንደሮች እስከ መገናኛ እንኳን ለመድረስ በአውቶብስ 20 ብር፣ በታክሲ ደግሞ 50 ብር መክፈል ይጠበቅባቸዋል።

"ወቅታዊ ታሪፉ ደርሶ መልስ በአውቶቡስ 40 ብር፣ በታክሲ 100 ብር ነው መገናኛ ድረስ ብቻ። እኛ ግን አልፈን ሄደን መሀል ከተማ ነው የምንሰራው፣ ለትራንስፖርት ብቻ በቀን እስከ 130 ብር በትሹ እናወጣለን" በሚል አስተያየት የሰጡት እነዚህ ዜጎች ይህንንም ለማግኘት ብዙ ተሰልፈው እና ተንገላተው እንደሆነ ያስረዳሉ።

"ይሄ እጅግ በጣም ኑሮአችንን አክብዶብናል፣ ከአቅማችን በላይ ሆኖብናል። አቤቱታችንን በሚዲያችሁ አስተላልፉልን፣ የሚመለከተው አካል መፍትሔ ሊሰጠን ይገባል" የሚሉት እነዚህ ዜጎች የነዳጅ ድጎማ ቀስ በቀስ መነሳት ላልተጠበቀ እና እጅግ አቅምን ለሚፈታተን ከባድ ወጪ እንደዳረጋቸው በምሬት ይናገራሉ።

"በአንድ ቤት ውስጥ ብቻ ስራ ለመሄድ፣ ልጆችን ት/ቤት ለማድረስ እንዲሁም ሌሎች የቤተሰብ አባላትን እንቅስቃሴ ሳይጨምር ለአንድ ሰው  ይሄን ያህል ወጪ በቀን እያወጡ እንዴት መኖር ይቻላል?" በማለት አስተያየታቸውን በጥያቄ ቋጭተዋል።

መረጃን ከመሠረት!

@MeseretMedia

🕋 ISLAMIካ🧐

23 Jan, 16:41


❤️የኛ ነብይ ﷺ
ዝምታቸው ብዙ ሳቃቸው ትንሽ ነበር።

❤️የኛ ነብይ ﷺ በህፃናት ጎን ሲያልፉ ሰላም ይሏቸው ነበር።

❤️የኛ ነብይ ﷺ ለሰው ልጆች ለእንስሳት ሳይቀር ያዝኑ ነበር።

❤️የኛ ነብይ ﷺ ሰዎችን አክባሪና ተናናሽ ኩራት የሚባል ነገር አያውቁም ነበር።

❤️የኛ ነብይ ﷺ ይቅር ባይና ይቅር ማለትን የሚወዱ ነበሩ።

❤️የኛ ነብይ ﷺ የቅርቧ አለም ብልጭልጭ ይልቅ የመጨረሻውን አለም የሚናፍቁ
ዛሂድ ነበሩ።

❤️የኛ ነብይ ﷺ ጌታቸውን አመስጋኝ ሰዎችንም አመስጋኝ ነበሩ።

❤️የኛ ነብይ ﷺ ሷላትን የልቤ እርጋታ እያሉ ለጌታቸው ባጣምም ይሰግዱ ነበር።

❤️የኛ ነብይ ﷺ በፈተናዎች እና በችግሮች ላይ ታጋሽ ነበሩ።

❤️የኛ ነብይ ﷺ ውሸትን በጣም ይጠሉ የነበሩ «ታመኙ-እውነተኛ» ነበሩ።

❤️የኛ ነብይﷺ ስድብንም ሆነ እርግማንን ይጠሉ ነበር።

የኔ ዉድ ነብይ ፤ ሩሔም፣ ገንዘቤም እናቴም፣ አባቴም ለአንቱ ፊዳ ይሁኑሎት..
ሷለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም።

@anbeb_islamic

🕋 ISLAMIካ🧐

23 Jan, 12:08


http://youtube.com/post/UgkxWYzBkdg97clVQrKalUatak4GMVvmDJIS?si=-d7mBnNFAf_VtiCS

🕋 ISLAMIካ🧐

23 Jan, 12:01


ሀላል አርአያ ወጣቶች የወቅፍ እና የበጎ አድራጎት ጀመዓ

ልዩ የረመዳን አስቤዛ ኒያ

(ዝርዝሩን ግራፊክሱ ውስጥ ያገኙታል)

ሁላችንም በመተባበርና በማስተባበር የዚህን ትልቅ የኸይር ስራ ተካፋይ እንሁን !


t.me/HalalArayaWetatochgroup

🕋 ISLAMIካ🧐

23 Jan, 11:20


የሙዕሚን ህይወት በዱኒያ ሀገር!

ከአብደላህ ቢን መስዑድ (📿) ተይዞ፡ እንዲህ ይላል፦

﴿نَامَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَلَى حَصِيرٍ، فَقَامَ وَقَدْ أَثَّرَ فِي جَنْبِهِ، فَقُلْنَا : يَا رَسُولَ اللَّهِ، لَوِ اتَّخَذْنَا لَكَ وِطَاءً. فَقَالَ : " مَا لِي وَلِلدُّنْيَا، مَا أَنَا فِي الدُّنْيَا إِلَّا كَرَاكِبٍ اسْتَظَلَّ تَحْتَ شَجَرَةٍ ثُمَّ رَاحَ وَتَرَكَهَا﴾

“የአላህ መልዕክተኛ (🤍) ሰሌን ላይ ተኙና ጀርባቸው ላይ የሰሌኑ ፋና እየታየ ተነሱ። እኛም የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! የተመቸ ምንጣፍ ብናደርግሎትስ? አልናቸው። እሳቸውም እንዲህ አሉ፦ ‘እኔና ዱንያ ምን አገናኘን። እኔኮ ዱንያ ውስጥ ልክ ዛፍ ስር እንደተጠለለና ትቷት እንደሄደ መንገደኛ እንጂ ሌላ አይደለሁም።’”

📚 ቲርሚዚ ሶሂህ ብለውታል፡ 2377



✔️በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

✈️፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

📞፦ https://bit.ly/486xnrS

👤፦ https://bit.ly/41zEZkk

📸፦ https://bit.ly/4arMbTx

💬፦ https://bit.ly/41tIUPv

🎥፦ https://bit.ly/3UTTSwh

🕋 ISLAMIካ🧐

22 Jan, 16:19


http://youtube.com/post/Ugkx5mq3c1xQyZmze0cy7FF5MH0UEwnm5lgE?si=Z-pNkV9Sn2kTmOoH

🕋 ISLAMIካ🧐

20 Jan, 15:21


የ15 አመቷን ታዳጊ ተማሪ ሐናንን አስታወሳችኋት?!

እስካሁን 1,848,577.06 ያክል ብር ፈጅቶባታል። 1,139,154.00 ያክሉ ብር ተከፍሏል። 709,423.06 ያክል ብር ገና የሆስፒታሉ እዳ አለባት።


ህፃን ሐናን ሕክምናዋ ባይጠናቀቅም የኢትዮ- ጠቢብ ሆስፒታል ሐኪሞች በቤት ዉስጥ የሚሰጡ መድኃኒቶችንና ሌሎች አስፈላጊ አገልግሎቶችን ማመቻቸት ከቻሉ ከሆስፒታል መዉጣት እንደሚችሉ ገልፀዉላቸዋል።

በመሆኑም፦

①.Suction Machine with atleast 2 bottles= 35,000 ብር፣

②.Oxygen cylinder with full accessories= 19,000 ብር፣

③.Patient Bed with Manual Elevator = 72,000 ብር
የሚገመቱ እቃዎችን በቤት ዉስጥ አገልግሎት ከሚሰጥ ነርስ ጋር ማዘጋጀት የግድ ሆኖባቸዋል።


እዛ ሆስፒታል ውስጥ የሚሆኑ ከሆነ ግን በየቀኑ ክፍያውንም አይችሉትም። ምክንያቱም ጉሮሮዋም ቀዶ ጥገና ስለተደረገ የረጅም ጊዜ ሕክምና ነው የሚፈልገው።


ከላይ ከተዘረዘሩት እቃዎች መካከል ቢያንስ ባመጣበት የሚሸጥ ካለ፤ ለአላህ ብሎ የሚሰድቅ ካለ፣ ወይም ቢያንስ የአንዱን መግዣ የሚያግዛቸው ካለ ያናግረኝ።

እስካሁን የታከመችበት ያልተከፈለ እስከ 700 ሺህ ብር ውዝፍ እዳ አለባቸው የሆስፒታሉ። ከዚህ በላይ ከቆየች እዳው እየበዛ ስለሚሄድ እነዚህ ማቴሪያሎች በአስቸኳይ ተሟልተውላቸው ወደ ቤታቸው ይመለሱ።

እንደተለመደው እንረባረብና ለአላህ ብላችሁ የየአቅማችሁን ተቸገሩ ጓዶች።








በእናቷ የተከፈተ አካውንት:
የአካውንት ስም፦ ዙበይዳ ኸድር ዑሥማን:

የአካውንት ቁጥሮች፦
√ ንግድ ባንክ: 1000209696723
√ ዘምዘም ባንክ: 000523020101
√ አዋሽ ባንክ: 01425512687400

ስልክ: +251939905190




የምትሰድቁበትን ደረሰኝ በውስጥ መስመር t.me/Murad_Tadesse ላይ ላኩት። አላህ በምታወጡት እጥፍ ድርብ አድርጎ ይጨምርላችሁ።


በዚሁ አጋጣሚ ኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታሎች ደግሞ በአላህ ዘንድ ታገኙበታላችሁና 709 ሺውን ብትተውላቸው፤ ካልተቸገራችሁ!

🕋 ISLAMIካ🧐

19 Jan, 16:50


በጥቂት ቀናት 1 ሺህ እና ከዛ በላይ ሰዎች ስለተከተላችሁኝ ለማመስገን የተፃፈ።[1k subscribers]

በተቆጠሩ ጥቂት ቀናት ውስጥ ከ22 ሺህ በላይ ተመልካች እና ከአንድ ሺህ በላይ ተከታታይ ማፍራቴን ስመለከት ደግነት ዛሬም ዋጋ እንደሚያወጣ እና ሰዎች ልብ ውስጥ ቦታ እንዳለው ዳግም እንዳምን አድርጋችሁኛል።

'የደግነት አለም' ብለን ስንነሳ መተባበርን ፣ መተጋገዝን፣ስራ ፈጠራን (entrepreneur) እና ፈጠራን (innovation ) በማስፋፋት እና በማስተዋወቅ ህዝባችንን ከችግር ከሀዘን እና ከመጠላላት በማውጣት ወደ እድገት ተስፋ እና መረዳዳት ለማምጣት ታልሞ ነው።

ይህንም ጅምር እውቅና ያላቸውን በጎ አድራጊዎችን በማነጋገር እና ድርጅቶቻቸውን በመጎብኘት መጀመራችን ልምድ እና ተሞክሮአቸውን ከማካፈል እና ለኛም ልምድ ከመቅሰም አንፃር ቀላል የማይባል ሚና ተጫውቷል።

ይህ ምኞቴ እንዲሳካ ሀያሉ ጌታዬን አላህ ፀሎቴን ሰምቶ ስላገዘኝ በፍጥረታቱ ብዛት ልክ አመሠግነዋለው።

በመቀጠልም ሀሳቤን ስነግረው በጎ ራእዬን ተረድቶ በቀረፃ ስራው ከጎኔ የሆነውን ወንድሜ እና ባልደረባዬ ያሲን መሀመድ አሚንን እንዲሁም ለመጀመሪያ ቀረፃዬ ፍቃደኛ በመሆን በፍጥነት መልስ የሰጠችንን የባቡል ኸይር መስራቿን (የድሆች እናት) ሀናን አብዱን እንዲሁም የአል አማና መስራች (የየቲሞች አባት) ኡስታዝ አብዱልፈታህን ከልብ ማመስገን እፈልጋለሁ። ምክንያቱም ያለነሱ ይህ ሁሉ የሚታሰብ አልነበረምና።

በቀጣይም ከሀይማኖት እና ከብሄር ወገንተኝነት በነፃ ሰብአዊነት ላይ ባተኮረ መንገድ በጎ አድራጊዎች እና በጎ አድራጎት ድርጅቶች ጋር በመሄድ እና ለጋስ እና ደግ ሰዎችን እየጋበዝን ሌሎችም ተያያዥ የሆኑ መተጋገዝን በሚያንፀባርቁ ሀሳቦች ስራችን በአላህ ፍቃድ እንቀጥላለን።

እናንተም ፕሮግራማችን ብዙ ወጪ ወጥቶበት እናንተ ጋር እንደሚደርስ ተገንዝባችሁ ስፖንሰር በማድረግ ደግነትን ታስቀጥሉ ዘንድ እንጣራለን እኛን ለማግኘት 0912027023 ይደውሉልን

እናመሠግናለሁ🙏

🕋 ISLAMIካ🧐

17 Jan, 09:29


ዝለናል፤ ዱአችን ዝምታ ነው! ከቤትህ ገብተን በአርምሞ ብቻ ቁጭ እንላለን። የእንባ ዘለላዎቻችን ሳናስበው ይወርዳሉ። የመለስክልን ብዙ፣ ያሳካህልን እልፍ ነው። ግን በማይሞላው የፍላጎት አቁማዳችን ደክመናል። በምህረትህ የምኞታችንን ፍፅምና አሳየን።

❤️ጁምአ❤️

🕋 ISLAMIካ🧐

15 Jan, 20:56


ከሰጠህ ስጥ… ካልሰጠህ ደግሞ በፈገግታ አላህ እንዲሰጠው ዱዓ አድርገህ ብቻ እለፍ… አታመናጭቅ፣ “ለማኝ" ብለህ አትሳደብ፣ ጨምዳዳ ፊት አታሳይ…  ህይወት ለሁሉም ሰው ቀላል አይደለችም… የሚለምንህን ሁሉ የሰው ፊት መቆም የቀለለው ቋሚ ስራው አድርገህ አትመልከት… ስለ ችግር ታውቃለህ? … ምናልባት  እየተሳቀቀች የምትጠይቅህ ልጆቿ የራቡባት እናት ትሆናለች… ምናልባት በደጉ ጊዜ ባዶ እጁን  መግባት ያላስለመደ አባት ይሆናል። አትገላምጥ!!
“ለማኝንም አትገላምጥ" [ዱሃ 10]

🕋 ISLAMIካ🧐

15 Jan, 16:38


ከደጉ ሰው ኡስታዝ አብዱልፈታህ ሙስጠፋ ጋር በቅርቡ!
የደግነት አለም ሰዎች
ያለ ሀይማኖት ገደብ ሁሉንም ደግ ሰዎች ወደ እናንተ እናደርሳለን።
አል አማና


http://youtube.com/post/Ugkxf3xUfVBtHmVZ7uFGmUE2PpxwDOv9ooji?si=pxcDlDyQ-4rcqdQd

🕋 ISLAMIካ🧐

15 Jan, 16:16


http://youtube.com/post/Ugkxf3xUfVBtHmVZ7uFGmUE2PpxwDOv9ooji?si=pxcDlDyQ-4rcqdQd

🕋 ISLAMIካ🧐

14 Jan, 09:05


ስለ ሀናን (ባቡል ኸይር)  ትንሽ ለማለት ያህል።

የሀናን ቅንነትን አይቶ አለመፃፍ ፤ የሀናን ደግ ተፈጥሮ ፣ ስስ ፥ ለእንባ የቀረበ የዋህ ማንነት አይቶ አለመገረም ፤ እና  አለመነካት አይቻልም። ከተቻለም ደንዳና ልብ ያለው ወይም ማስተዋል የተሳነው ሰው መሆን ይፈልጋል።

ሀናን ለሰው ስሜት አብዝታ የምትጨነቅ በጣም...ትህትና እና ራስን የማስተናነስን ፀጋ የታደለች (inborn innocent) ከቅንነት ፣ ከአዛኝነት የተሰራች የእንስቶች እና የለጋሶች ሁሉ ቁንጮ እንዲሁም የእናትነት ቀለም ናት።

ሀናንን በፊት ከርቀት እንደሁሉም ሰው አውቃት ነበር። ግን ፀጋዋ እንዲህ የበዛ መሆኑን የተረዳሁት ቀርቤ ኢንተርቪው ሳደርጋት እና ለጉብኝት እንደምንመጣ በስልክ ስጠይቃት 'ከየት ነህ ፣ ማን ናችሁ'? ሳትል ካሳየችኝ ፈጣን ትህትና የተሞላበት የእሺታ ምላሽ ጀምሮ ነው።

'ሀናን መጥተን ልንጎበኝሽ ነው' ስንላት አላቅማማችም ደጅም አላስጠናችንም። የመልካምነቷን ቤት ወለል አድርጋ ከፈተችልን እንጂ

'ይህ ዘመን ፍፁም ደግ ሰው የለውም የምትሉ ፤ በዚህ ዘመን ደግሞ ደህና ሰው አለ ወይ?' ለምትሉ ሂዱና ሀናን እዩ ከዛ ሀሳባችሁን ትለውጣላችሁ።

ሀናን ሳቋም እንባዋም ቅርብ ነው። ስለሚቸገሩ ሰዎች አስባ ታነባለች ፣ ስለተራቡ እና ስለሚሰቃዩ ሰዎች አውስታ ስቅስቅ ብላ ታለቅሳለች ፣ የዚህችን አለም ከንቱነት በጥልቅ ተገንዝባለች። የቀጣዩን አለምም መልካም ቤቷንም ትናፍቃለች።

ሀናን እንደ እንባዋ ሳቋም በጣም ቅርብ ነው።

ሳቋ ከየዋህነቷ እና ከቅንነቷ የተቀዳ ኩልል ያለ የህይወት ምንጭ ነው። ሀናን ጋር ከሆንክ ቅንነት ይጋባብሀል አዛኝነት ይጠናወትሀል በአጠቃላይ ሀናን የደግነት ወገግታ የሰብዓዊነት ፀዳል ነች። 

አሁን በሷ የደግነት ጥላ ስር በፈጣሪ እርዳታ ብዙ ሺ ሰዎች ተቀልበው እና ተደስተው ይኖራሉ። (የአንድ ሰው ቅንነት የብዙ ሺ ስዎችን ህይወት እንዲህ ከለወጠ የሰው ልጆች ቀና ብንሆንስ...?አስቡበት)

ሀናን ማህመድ ለአለም እና ለሰው ልጆች ላሳየሽው ደግነት እናመሠግናለን።

ባቡል ኸይር (የበጎ ነገር በር)
7335 ok ብላቹ በመላክ እንርዳ!

የደግነት አለም
ኡስማን ሙስጠፋ

🕋 ISLAMIካ🧐

12 Jan, 08:04


https://youtu.be/mPtQDrI7C4s?si=yICPHoylKsiMgsx_

🕋 ISLAMIካ🧐

11 Jan, 04:28


በዚህ ቻናል ደግነትን ለአለም እናስተምራለን። ይቅር መባባልን ለሰው ልጆች እንሰብካለን። ያላችሁን ሀሳብ ፣ ገንዘብ ፣ ጉልበት ፣ ፈገግታ ...ለሰው ልጆች እና ለፍጥረታት አጋሩ። ራሳችሁን በብዛት ይቅር በሉ ወላጆቻችሁን እና ታላላቆቻችሁን አክብሩ ለታናሾቻችሁ እዘኑ አምላካችሁን ፍሩ።

ይህ የደግነት አለም ድምፅ ነው።

Through this channel we teach kindness to the world. We preach forgiveness to mankind. Share your thoughts, money, energy, smile...to humans and creatures. Forgive yourselves abundantly, honor your parents and your elders, have compassion on your younger ones, fear your God. This is the voice of the world of kindness.


Join👇👇👇
https://youtube.com/channel/UCzhYSn6zcvVTVlWNYKKoNCg?si=6jpg4O5KlQpD0wWY

🕋 ISLAMIካ🧐

30 Dec, 21:12


መሬቱ ተንቀጥቅጧል

#earthquake

በወንጀላችን እንደንግጥ ለአምላካችን በፍርሀት እንንቀጥቀጥ

🕋 ISLAMIካ🧐

30 Dec, 18:07


إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ
أُو۟لَٰٓئِكَ هُمْ خَيْرُ ٱلْبَرِيَّةِ

🍃እነዚያ ያመኑትና መልካሞችንም የሠሩት፣
እነዚያ እነርሱ ከፍጥረት ሁሉ በላጭ ናቸው፡፡

Al-Bayyinah 98:7

🕋 ISLAMIካ🧐

29 Dec, 09:33


❤️❤️❤️#የእናት_ሐቅ❤️❤️❤️ በጥቂቱ

#ከመሞቷ_በፊት_ተጠቀምባት🥰🥰

1- ☞ድምፅክን ከድምጿ ከፍ አታርግ

2-☞አጉል ክርክር አትከራከራት

3☞-እሷ ሳትጨርስ አትናገር

4-☞በስሟ አትጥራት

5-☞እንቅልፏ ሳትጨርስ አትቀስቅሳት

6-☞ለምክንያት ካልሆነ በቀር ከፊት ተፊቷ አትቅደም

7-☞ባርያ ለጌታው እንደሚተናነስ ሁሉ ተናነስላት

8-☞ጠርታ ሳትጨርስ "አቤት" በላት

9-☞ከቤት ወጥተህ አትዘግይባት

10-☞በእይታህ አታፍጥጥባት

11-☞በንግግርህ አትጋፈጣት

12-☞በንግግሯ አትዘንባት

13-☞መላዋንና ሐሳቧን አታናንቅ

14-☞ሲጨንቃት አማክራት

15-ሲቸግራት እርዳት

16-☞ስትታመም አሳክማት

17-☞ስትታረዝ አልብሳት

18-☞ጉዳይዋ ሁሉ ጉዳዬ ነው በል

19-☞እቅድ ሐሳቧን ተካፈል

20-☞የስጋ ዘመዶቿን ቀጥል

22☞-ወዳጆቿን ውደድላት

23-☞ከእርግማኗ ተጠንቀቅ

24-☞እሷን ከማስከፋት ፈፅሞ ራቅ

25☞-ቀስ ብለህ አስረዳት

26-☞በሚገባት አነጋገርና ቋንቋ አነጋግራት

27-☞ከዱዓዋ ፈልግ

28-☞ለምርቃቷ ተሽቀዳደም

29-☞አላማህን አትደብቃት

30-☞እሷ ሳትቀመጥ አትቀመጥ

አላህ የምንተገብረው ያርገን አንብባችሁ

©

🕋 ISLAMIካ🧐

29 Dec, 06:15


የ 23 አመቱ የሰላም መስጊድ ኢማም እና ኡስታዝ አቶ ሙሀጀር አህመድ (acute leukemia) በደም ካንሰር ህመም በፀና ታሞ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተኝቷል።

ናሙናው ወደ ባንኮክ ተልኮ በተደረገው የመቅኔ ምርመራ ወንድማችን በደም ካንሰር መያዙ ስለተረጋገጠ ጥቁር አንበሳ የህክምና ማእከል ከላይ የተያያዘውን ያያያዝነውን ማረጋገጫ የሰጠው ሲሆን የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት እና የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የእርዳታ ማሰባሰብያ ፍቃድ ደብዳቤ ፅፈውለታል።

እና ሁላችንም ሙስሊሞች ይህን ለጋ የኡማው ሀብት ከሞት የመታደግ ሰበብ በማድረስ ለአኼራ እና ለአዱኒያ የሚሆነንን ስንቅ እንያዝ

ማስታወሻ:- ለመታከሚያ ይሆነው ዘንድ የምንችለውን የገንዘብ መጠን ወደ አካውንቱ ከመላክ ጀምሮ ሄዶ በመጠየቅ ትላልቅ ወጪዎችን በመሸፈን እና በተያያዥ ጉዳዮች ቤተሰቦቹን በማማከር እንሳተፍ። ባረከላህ ፊኩም!

የወንድሙ አብዱል ሰመድ አህመድ ስልክ እና ሂሳብ ቁጥር 0932512569
1000362457468 ንግድ ባንክ

share ማድረግ አትርሱ አደራ
ሚዲያ ካላችሁ እዛ ላይ ይህን ፅሁፍ አጋሩት

ባረከላህ ፊኩም

🕋 ISLAMIካ🧐

27 Dec, 19:16


አላህን ፈሪው ወንድም ለሚወዳት ልጅ የፃፈላት ደብዳቤ!

ውድ እህቴ አንችም አምብቢው ትክክለኛ ከልቡ የሚወድሽ ወንድ ምን አይነት እንደሆነ ተረጅበታለች።

ይላል እንዲህ
📨 እንዲህ እየናፈቅሽኝም ቢሆን ላገኝሽ አልፈልግም ምክንያቱም እኔ ጌታየን ተገናኝ መሆኔን አውቃለሁ አውቃለሁም ላስተዳድርሽ አልችልም እንዲሁም ላገባሽ ሀቅም ስለሌለኝ ውበትሽ መፈተኛየ ነው። ስለዚህ ወዳንቺ እየተሳብኩ አንችን ወደኔ አላቀርብሽም ሀራም በሆነ መልኩ ቀርቤሽ ባገኝሽ ተሸናፊው እኔ ነኝ ታዲያ ለምን እቀርብሻለሁ! እናም ወደ ጌታየ ስደትን ስጀምር ስንቄ ተቅዋ(አላህን ፍራቻ)እንዲሆን ፈላጊ ነኝ። አየሽ አንዳንዱ በገንዘቡ ወዳጆቹን ያቀርባል ሌላው በቁንጅናው ቁንጅናዎችን ይጠራል
እኔ ግን ላንቺ ያለኝን ፍቅር ሰውቼ የጌታየን ፍቅር ማግኜት እፈልጋለሁ። ብቀርብሽ እንደምትጠጊኝ እርግጠኛ ሁኜ ሳለ እርቅሻለሁ ምክንያቱም እኔ ጌታየን የበለጠ በጥሩ ስራ መቅረብ እፈልጋለሁ። አዎ የእርሱ ፍቅር የእርሱ እርዳታ አንችን እንደሚያስረሳኝ አምኜም ደህና ሁኚ እልሻለሁ ደህና ሁኚ እኔ ወደ ጌታየ ሂያጅ ነኝ መንገዴንም ይመራኛል። ሪዝቃችንም ከሆነ በትክክለኛው በሃላሉ መንገድ ዱንያ ላይ እንገናኛለን። የአላህ ፍቃድ ሁኖ ዱንያ ላይ ካልተገናኘን ደግሞ ዘለዓለማዊ በሆነው ሀገር(ጀነት)እድንገናኝ እማፀነዋለሁ።

አላሁ አክበር❗️
አየህ አንተ የአኼራ ጓደኛየ ዱንያ አላታለለችውም፣ ሴት ልጅም አልፈተነችውም። ሴትን ልጅ አታሎ እንደፈለጉ ማድረግ በጣም ተራ ነገር ነው ነፍስያም ምትፈልገው ያንን ነው። ነገር ግን እምነት ሲኖረን ስሜታችንን ሳይሆን የአላህን ትዕዛዝ እናስቀድማለን። እምነት ልባችንጋ ሲጠፋ ደግሞ ስሜታችን እንስሳ ያደርገናል።

አንተም ተማርበት ይሄ ወንድማችን ስሜቱን እንዴት ለአላህ ብሎ መቆጣጠር እንደቻለ ተመልከት። በሃራም መንገድ አሸንፈሃት ልታንበረክካትና የፈለከውን ልታደርጋት ብትችልም የተሸነፍከው ግን አንተው ነህ።! የሷን ህይወት አበላሽተህ ሰላም አታገኝም እየቆየ ህሊናህ በጭንቀት ተቆጣጥሮህ እስረኛ ሲያደርግህ ምን አለ እስር ቤት ገብቸ ቢለቀኝ ብለህ ትመኛለህ።❗️ህሊና አይምርም።

ቶሎ ወደ ትዳር መግባት ካልቻልን እንደዚህ ወንድማችን ከሃራም ፍቅር(መንገድ)መራቅ አለብን። ብዙዎቻችን ምን ችግር አለው ካልተገናኘን ብለን በማሰብ ነው ወደ ዚና እየገባን ነው ያለነው። ከጊዜ በኋላ ከፁሁፍ ወሬ ወደ መደዋወል ከዛም ካፌ ሰው ስላለ ምን ችግር አለው ብሎ በማሰብ መገናኘት ይጀመራል፣ ከዛ በኋላ ለብቻ ወደ መገናኘት ይገባል። ከዛም የምናስበው ከተጋባን ምን ችግር አለው ብንሳሳም፣ ብንተቃቀፍ፣ ከዛም መጨረሻ ላይ ከተጋባን ምን ችግር አለው ዚና ብንሰራ መባባል ይመጣል። ምክንያቱም ወንጀል ልባችንን ስለሚያደርቀው ወደ ወንጀል ነው ሚገፋፋን። ከዛም ያች ሴት ልጅም ዚናን ስትጠየቅ ክብሯ ያስጨንቃትና ያለመፈለግ ስሜት ስታሳይ እሱም ምነው አታምኝኝም እንዴ፣ እወድሻለሁ አፍቅርሻለሁኮ፣ ያላንች ማን አለኝ እናለ የውሸት ቃላቶችን ይደረድራል፣ ያታልላታል። ይሄኔ ያችም ልጅ የነበረችበትን የሃራም መንገድ ልቧን ስላደረቀውና ስለለመደችው ልጁን መለየት ይከብዳትና እሽ ብላ ያንን ቆሻሻ ዚና ትሰራለች። ከዛ በኋላ ውዴታቸውን ከልባቸው አላህ ያወጣባቸዋል። ከዛም ሳይጋቡ ይለያያሉ። ተጨባጩ እውነታ ይሄ ነው።! ካለፉት እንማር!

"የስሜት ጥፍጥናው ሳያልቅ ምሬቱ ያደፈርሰዋል"❗️ማለትም ስሜታችንን ተቆጣጥረን ፈተናውን መወጣት ካልቻልንና በስሜታችን ከተምበረከክን ባጭር ጊዜ አላህ ብቻ የሚረዳው እንቅልፍ የሚያሳጣ ጭንቀትና ቁጭት ይለቅብናል። አላህ ታምፆ ደስታ ከየት ይመጣል።? በጭራሽ አናስተያየው ወደ አላህ እስካልተመለስን፣ ህይወታችንን በአላህ መንገድ መምራት ካልቻልን መቸም አንደሰትም ውስጣችንም አይረጋጋም።

በአላህ ይሁንብኝ ደስታ በሃራም ፍቅር ውስጥ አጭርና ጊዜያዊ ብቻ ነው። እኛ ግን ትልቅ ደስታ እንዳለ ነው ምናስበው። ይሄም የሆነው ኢማናችን ደካማ ስለሆነ ነው። ከግዜ በኋላ ጭንቀትና ቁጭት ነው ሲለቅብን ለምን ይሄን አደረኩ ለምን ለምን እያልን እራሳችንን መውቀስ እንጀምራለን ምክንያቱም የሸይጧን መንገድ ነው። ሸይጧን ደግሞ የእሳት ጓደኞቹ ሊያደርገን ነው የሚፈልገው። የሃራም መንገድ ትርፉ ከኢባዳ መራቅና ጥፍጥናውን ማጣት፣ ልብ ማድረቅ፣ ግዜን መግደል፣ ገንዘብ ማጥፊያ፣ አላህን ማመፅ ብቻ ነው ትርፉ። የሚያሳዝነው ግን ይሄን ፈተና አላህ ካዘነላቸው በስተቀር የሚወድቀት ብዙ ናቸው። መጨረሻም ላይ ሸይጧንም ይስቅባቸዋል። ካለፉት እንማር!

 ስለዚህ ካለፉት እንማር ስሜታችንን ያዝ አድርገን ጀነትን በማሰብ ወጣትነታችንን እንጠቀምበት አላህን የበለጠ ለማወቅና ለመገዛት ጀነትንም ለመውረስ እንቻኮል። ፍቅር ወዳቂ ነው የአላህ ፍቅር ግን ሁሌም ህያው ነው በሁለቱም ሀገር አይወድቅም። አላህም ከወደደን የምንወደውንና የሚጠቅመንን ሁሉ ይሰጠናል። ወላሁ አእለም

🎁 ሼር ማድረግ አንርሳ ሚዲያን ለዲናችን ብቻ! ከኛ የሚጠበቀው ማድረስ ነው አላህ የወደደውን ይመራበታል። ባረከላሁ ፊኩም

አስተያየት ጥያቄ እንዲሁም ተጨማሪ ምክር...
   ወንድማችሁ ሙሂዲን ሰኢድ
          @jezakellah

🎁 ይህ በዝሙት አንዘምን የቴሌግራም ቻናል ነው! የአላህ ፍቃድ ሁኖ በምንለቃቸው ትምህርቶች ብዙዎች እየተማሩበትና ከተኙበትን እንዲነቁ ሰበብ እያደረሰ ይገኛል። ቤተሰብ ካልሆናችሁ ተቀላቀሉን
  ጆይን 👇 &👇 share 👍
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina

🕋 ISLAMIካ🧐

27 Dec, 16:27


ለጸጋዎቹ አመስጋኝ ነበር‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ኢብራሂም (ዓለይሂ ሰላም) ለተሰጡት ፀጋዎች ሁሉ ያለማቋረጥ እውቅና'ና ምስጋናን ይሰጥ ነበር።
-
ለጸጋዎቹ አመስጋኝ ነበር።  ۚشَاكِرًا لِّأَنْعُمِهِ
[አን–ነሕል (121)]

-> ለአላህ ታዛዥ ነበር።
-> በዒባዳ ትጉ ነበር።
-> ወደ ተውሂድ ጠሪ ነበር።
-> ለቤተሰቡ ቸር ነበር።
-> ለእንግዶቹ ለጋሽ ነበር።
-> ለሕዝቦቹ አዛኝ ነበር።
-> በተልዕኮው ቆራጥ ነበር።
-> አላህ ዘንድ ተወዳጅ ነበር።
-> የአላህ ወዳጅ፣ ጀግና ጥበበኛም ነበር።
-> ለጸጋዎቹ አመስጋኝ ነበር።
-> የምስጋና አብነት አደርገው።
-> መመሪያ በረከቱን ሰጠው።
-> የጽናት መሰረት ተምሳሌቱን፤
-> ምስጋና የአማኞች ባሕርይነቱን ገለጸበት።
-> ምስጋናው የአላህን ልዩ ውለታ አስገኝቶታል።
-> ወደ ቀጥተኛው መንገድ መመራትን ሰጥቶታል።

የአላህ ጸጋዎች ስፍርም ቁጥርም የሌላቸው ናቸው፤ ኾኖም አላህ የኢብራሂምን ምስጋና ለሁሉም አማኞች ተምሳሌት አደረጎ አስቀመጠው።

ሙእሚኖች በ'ለት ተዕለት ሕይወታቸው ምስጋናን በማዳበር የአላህን ፀጋዎች እንዲያስታውሱ፣ እንዲገነዘቡ እና አመስጋኞች እንዲሆኑ አዘዘበት።

ሕይወትን በሙሉ የማይቋረጥ ምስጋና!
وَإِن تَعُدُّوا نِعْمَةَ اللَّهِ لَا تُحْصُوهَا ۗ አን-ነሕል (18)
«ጸጋዬንም ብትቆጥሩ አትዘልቋትም!» ባለበት ምዕራፍ ላይ ኢብራሂም ያለማቋረጥ እኔን አመስጋኝ ነበር፤ ብሎ አወደሰው።

ምስጋና ሁሉን አቀፍ፣ ቁሳዊ፣ መንፈሳዊ እና ስሜታዊ ሞገስን ሲሸፍን፤ የአላህን ሚታዩና ማይታዩ ፀጋዎችን ሁሉ እውቅና መስጠትን ሲያካትት ምስጋና ይሰኛል።
--
የአላህ መልክተኛም (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) አሉ፦
«አላህ እንደ ምስጋና የሚወደው ነገር የለውም።»
[ሲልሲለቱ ሶሒሐህ (4-404)]
والحمد لِلّه تملأُ الميزان
አልሓምዱሊላህ ('ምስጋና ለአላህ ነው' ማለት)
ሚዛን ትሞላለች። [ሶሒሁል ጃሚዕ (3957)]

ክብርና ምስጋና የዓለማት ጌታ ለኾነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም፣ የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን፡፡
||

🕋 ISLAMIካ🧐

26 Dec, 08:54


አንድ ሙስሊም ያልሆነ blogger ስለ አክሱም ሙስሊሞች እያወራ የሰራውን ቪዲዮ እያየው ነበርና ከስር የሚሰጡ ኮሜንቶችን ስታዮ የአክሱም ሙስሊሞች ጉዳይ ሲሪየስ የሆነ ትግል እንዲሚፈልግና ጉዳዮ እንደሌሎች አካባባዎች የውስን ግለሰቦች ጥጋበኝነት ሳይሆን ህዝባዊና ኃይማኖታዊ መሰረት እንዳለው ትረዳላቹ ። ይሄን ነገር ከኛ በላይ የከተማው ሙስሊሞች ያውቁታል ብዬ አስባለው ። የኃይማኖትህን መሰረታዊ ድንጋጌዎች መተግበር የማትችለበት ከተማ ውስጥ የሚከፈለውን ከፍለህ ካልታገልክ ምንም ለውጥ አታመጣም ። አክሱም ያላቹ ሙስሊም ወንድምና እህቶች እንዲሁም ከከተማው ውጪ ምትኖሩ የአካባቢው ተወላጆች ተናባቹ የሆነ ነገር ፍጠሩ ፣ መብት በልመና አይገኝም ።

#ፍትሕ_ለአክሱም_ሙስሊሞች

🕋 ISLAMIካ🧐

25 Dec, 13:41


በወንጀሌ ብዛት ምክንያት ካንተ እዝነት መባረርን በኔ ላይ አትወስን አምላኬ ሆይ!!🥹

ወደ ምህረትህ ቅጥር ነፍሴን አስገባት
ያ ረሂም😭

🕋 ISLAMIካ🧐

25 Dec, 12:14


እንደ ሀገር አሳፋሪ ታሪክ ነው።

የ12ኛ ክፍል ማትሪክ መፍፈተኛ ፎርም የሚምሞላበት የመጨረሻው ቀን ዛሬ ነው።

በአክሱም ከተማ ያሉ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ከዩኒፎርማችን ጋር ተመሳሳይ የሆነ ሂጃብ ለብሰን እንማር ሲሉ፡

አይ ፀጉራችሁን ካልከፈታችሁ መማር አትችሉም ተብለው ፎርም እንዳይሞሉ ትምህርታቸውንም እንዳይማሩ ተከለከሉ።

አስቡት!
ጅልባብ እንልበስ አላሉም! ኒቃብ እንልበስ አላሉም!

የጠየቁት ጥያቄ ከዩኒፎርማችን ጋር ተመሳሳይ በሆነ ሂጃብ ፀጉራችን ሸፍነን እንማር ነው ያሉት!

ታዲያ ይህንን ከከለከለ አመራር የበለጠ አፓርታይድ ማን አልለ?

🕋 ISLAMIካ🧐

24 Dec, 14:32


(ካስለቀሰኝ🥹)

ዘመኑ. . . 
 
:ወላጆች ለልጃቸው ዲን እና ባህሪ የማይጨነቁትን ያህል ስለ ልብስ እና ምግባቸው አብዝተው ይጨነቃሉ

:ጎረምሦች ቀኑን ሙሉ ሲዝናኑና ሲዘሉ ዉለው ሦስት ረከዓ መግሪብ ለመስገድ ኢማሙ አረዘመብን ይላሉ ৲


#ይገርማል . . .


:ጠዋት ላይ ሠራተኞች ወደ መንግሥት ሥራ ሲሄዱ ወደ ሞት የሚጓዙ ነው የሚመስሉት ৲

:አውቶቡስ ዉስጥ ለደከሙና በዕድሜ ለገፉ እናት አባቶች የሚነሳ ወጣት እየጠፋ ነው ৲

:በመንገድ ይሁን በመስጊድ የሃይማኖት ሰው ጊዜ ወስዶ የሚማከር አታገኝም ৲

:መንገደኞች የጉዞ ሰዓት እንዳያልፋቸው አላርም ይሞላሉ ለሱብሒ ሶላት ግን ችላ ይላሉ ৲

:ተጠቃሚዎች ለአስተናጋጅ ወፍራም ቲፕ ይሠጣሉ፣  ለነጋዴ መልሱን ይተዋሉ ፤ የተቸገረ ለማኝ ግን አይተው እንዳላየ ያልፋሉ ৲

:ዳዒዎች ለደዕዋ ሥራ አበል ይጠይቃሉ ፣ ዑለሞች የአላህን ዲን በትንሽ ጥቅም ይቸበችባሉ ৲

:ኡስታዞች ራሣቸው የማይተገብሩትን ለሌሎች ይመክራሉ ৲

:መንገደኞች አደጋ በዛ ይላሉ ፤ የጉዞን ህግ አያከብሩም ፣ የጉዞን ዱዓ አያውቁም ৲

:መስጊድ እንሂድ ሲባል ወደ ሰማይ እንውጣ የተባለ ያህል ዳገት ሆኖበት ትንፋሽ የሚያጥረው በዛ ৲

:ተው ሐራም ነው ይቅርብን ሲባል “ሁሉም እየሠራው እኛ ብቻ ለምን ይቅርብን” የሚል በረከተ ৲

:ጉቦን “የሻይ” እኮ ነው ብለው ይወስዳሉ ৲

:ወለድን “ፐርሰንት” ነው” ብለው ይበላሉ ৲

:ሙዚቃን “ነሺዳ” ነው ብለው ይጨፍራሉ ৲

:ኢኽቲላጥን ወንድም እህትማማችነት ብለው ያጠናክራል ብለው አደረጉ ৲

:ሲመክሩት ተቆጪውና ገንፋዩ በዛ ৲

:ሲያስታውሱት አትምከረኝ አውቃለሁ ባይ እንደ አሸን ፈላ ৲

:የሚያውቁ አይሰሩበትም ፤ የማያውቁ ደግሞ አናውቅም አይሉም፡፡

:አቀማመጣችን ተፋልሷል፤ ከፊት መሆን የነበረበት ከኋላ ፤ ከኋላ መሆን ያለበት ከፊት ሆኗል ৲

ታዲያ ምን ይሻለናል ?

╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤ᢀ


©️

🕋 ISLAMIካ🧐

24 Dec, 09:17


Someone: why you not married yet?

Me: the same reason you're "not dead yet. It's not my time.


😅😳

🕋 ISLAMIካ🧐

23 Dec, 08:46


- ሀሳብ ኖርዎት እንዴት ወደ ዩቲዩብ ወይም ማንኛውም ኮንቴንት (ይዘት) መቀየር እንደሚችሉ ግራ ተጋብተዋል?

- ወይም ድርጅትዎን እንዴት በራስዎት ሚዲያ ማስተዋወቅ እንደሚችሉ በማሰብ ተጨንቀዋል?

- እኛ ጭንቀትዎን ለማቅለል ተዘጋጅተናል

ማለትም በሚከተሉት

- በኮንቴንት አዘገጃጀት (content creation methodology and strategy)
- በፕሮፌሽናል ስቱዲዮ እና ካሜራ ውስጥ ለድርጅትዎ ስክሪፕት ፅፈን የቲክቶክ ማስታወቂያ ቪዲዮ በመስራት
- ዩቲዩብ መሠረታዊያን basics (uploading techniques,hook, thumbnail,etc..) እናማክራለን
- ለቴሌግራም ደረጃቸውን የጠበቁ ፅሁፎችን ለድርጅትዎ እና ለስራዎ እናዘጋጃለን

በአጭሩ ሶሻል ሚዲያዎት የተቀላጠፈ ሰው ጋር ተደራሽነት ያለው እና የድርጅትዎን ገቢ የሚያሳድግ እንዲሆን ካወሰኑ እኛን ያማክሩን

"ጥርሳችንን በነቀልንበት በዚህ ሙያ ከአለም ጋር እናስተሳስሮታለን"

ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን ወይም ቴሌግራም ላይ በዚሁ ቁጥር ይፃፉልን
0912027023

የ startup ቅናሽ ላይ ስለሆንን እድሉን ይጠቀሙበት

🕋 ISLAMIካ🧐

22 Dec, 06:26


5 ትናንሽ ታሪኮች…

  1  በአንድ ወቅት በአንድ መንደር የሚኖሩ ሰዎች ዝናብ በመጥፋቱ ምክንያት ዱዓ ሊያደርጉ ወሰኑ፡፡ በዛ ቀን ሁሉም የመንደሩ ሰዎች ተሰባሰቡ፣አንድ ትንሽ ልጅ ብቻ ዣንጥላ ይዞ ተገኘ፡፡

(ይህ እምነት ይባላል፡፡)

፣፣፣፣፣፣፣፣፣

2 ህጻን ልጅህን ወደላይ እየወረወርህ ስታጫውታት በደስታ ትፍነከነካች እንጂ አታለቅስም ፡፡ምክንያቱም መልሰህ እንደምትቀልባት ታውቃለችና!!

ይህም እርግጠኝንት ይባላል፡፡

፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣

3 በእያንዳንዱ ምሽት ወደ አልጋችን ስንሄድ በነገው ማለዳ በህይወት እንደምንቆይ ምንም ዓይነት ማረጋገጫ ባይኖረንም አላርም(የማንቂያ ደወል) ሞልተን እንተኛለን!!

ይህም ተስፋ ይባላል፡፡

፣፣፣፣፣፣፣፣፣

4 ወደ ፊት ምን እንደምንሆን (እንደሚሆን)እውቀት ሳይኖረን ታላላቅ እቅዶችን እንነድፋለን!!!

ይህ ደሞ በራስ *,መተማማን ይባላል፡፡**


5 አንድ ሽማግሌ በለበሰው ቲሸርት ላይ እንዲህ የምትል አንዲት  ዐረፍተ ነገር ተጽፋለች

“እኔ የስድሳ አመት ሽማግሌ አይደለሁም ፣የአርባ አራት አመታት የሕይወት ልምድ ያለኝ የአስራ ስድሰት አመት ወጣት እንጂ”

ይህ ለራሳችን ያለንን አመለካከት ያሳያል፡፡


እምነት ፣እርግጠኝነት ፣ተስፋ ፣በራስ መተማማን  ለራሳችሁ ጥሩ አመለካካት ሳይለያችሁ ኑሩ !!!

🕋 ISLAMIካ🧐

21 Dec, 11:44


🔺የሆነ ነገር ሲረሳ ለማስታወስ ተብሎ
አሏሁመ ሶሌ አላ ሙሀመድ ማለት..

#ጥያቄ
ብዙ ጊዜ ሰዎች እቃም ይሁን የሆነ ነገር ሲጠፋቸው
#ለማስታወስና ትዝ እንዲላቸው ብለው "#አሏሁመ_ሶሌ_አላ_ሙሀመድ" ይላሉ ለዚህም ደግሞ #ሀዲስ አለ ይላሉ ይህ እንዴት ነው⁉️

#መልስ
መርሳት አላህ በቁርአኑ እንደጠቀሰው ከሸይጧን የሚመጣ ጉትጎታ ነውና አንድ ሰው የሆነ ነገርን ለማስታወስ ሲቸገርና
#ሲረሳው ማድረግ ያለበት #አላህን ማስታወስና አላህ ትዝ እንዲያስብለው አላህን #ዱዓ ማድረግ ነው።ለዚህም አላህ እንዲህ ይላል፦"በረሳህም ጊዜ ጌታህን አውሳ"
📚ሱረቱል ከህፍ ፣ 24

ነገር ግን በዚህ ፈንታ
#ሶላዋት [አሏሁመ_ሶሌ_አላ_ሙሀመዲን] ማለት በሸሪዓችን መሰረት #የሌለው ተግባር ነው። በዚህ ዙሪያ የመጣውም #ሀዲስ በጣም ዶዒፍና #ቅጥፈት ነው።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
♻️ ምንጭ :— 📚ተፍሲሩል ቁርጡቢ ፣ 10/386 ፣ 📚ኢብኑል ጀውዚይ ፣ ኪታብ ዛዱል ሙየሰር ፣ 5/128 ፣ 📚ኢብኑ ኡሰይሚን ፣ ፈትዋ ኑሩን አለደርብ

🕋 ISLAMIካ🧐

20 Dec, 06:17


የመለከል መውት ትዝብት‼️
==================

  "ከቀናቶች ውስጥ አንዲትም ቀን የለችም መለከል መውት ወደ ሁሉም ቤት በቀን 3ጊዜ እየመጣ ቢጎበኛቸው እንጂ። ከቤተሰቦቹ መሃል
👉ሪዝቁን የጨረሰና
👉እድሜውን ያለቀ ካገኘ ሩሑን ይዞ ይሄዳል።

ልክ ሩሑን ይዞ ሲሄድ ቤተሰቦች መጮህና ማልቀስ ይጀምራሉ። በዚህ ጊዜ መለከል መውት የቤቱን መቃን ይዝና……
«ወላሂ እኔ እንደ ሆነ ምንም ሪዝቁን አልወሰድኩበትም፤ እድሜውም አልቀነስኩበትም። ባይሆን ወደ እናንተም መመለሴ ስለ ማይቀር ተራ በተራ ሁላችሁም እወስዳችኋለሁ» ይላቸዋል።

መለከል መውት ትዝቡቱ ይቀጥልና……
«ወላሂ እነዚህ ሰዎች ሟቹን ያለበት ሁኔታ ቢያዩ ኖሮ እሱን ይረሱትና ስለ ራሳቸው ማልቀስ ይጀምሩ ነበር።» ይላል።
     [ሐሰኑል በስሪ]

   🤲አላህ መጨረሻችን ያሳምርልን🤲
               መልካም ጁምአ

🕋 ISLAMIካ🧐

19 Dec, 10:24


ወደ ረመዳን የምናደርገውን ጉዞ እያጋመስን ቢሆንም
ዝግጅታችን ግን ቀጥሏል

"ጉዞ ወደ ላቀው ረመዳን" ያልነው ለረመዳን መሠናዶ ያዘጋጀነው የሀሳብ ድግስ 5ተኛው ክፍል ላይ ደርሷል

ኡስታዝ አህመድም ከአስደማሚ ሀሳቦቹ እና አዲስ እይታው ጋር ጉዟችንን የተዋበ አድርጎታል

ታዳሚዎችም ዘወትር ሀሙስ የረመዳን ስንቃቸውን ለመቋጠር ከአዳራሹ በሰአቱ መሠየሙን መልካም ልማድ አድርገውታል። ብዙዎች በነዚህ ምሽቶች ህይወታቸውን አድሰዋል ፤ ከኢስላም ጋር እንደ አዲስ ተዋውቀዋል።

በዋኒያ መድረክ በኡስታዝ አህመድ አዘጋጅነት ዘውትር ሀሙስ የሚቀርበውን ይህን መድረክ በነፃ ታድማችሁ ብዙ አትርፉ

ዛሬ ከ 11:30 ጀምሮ በቢላሉል ሀበሺ አዳራሽ እንገናኝ።

ለበለጠ በዚህ ይደውሉልን +251935608888

🕋 ISLAMIካ🧐

07 Dec, 05:56


(185) 💔ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡ ምንዳዎቻችሁንም የምትሞሉት በትንሣኤ ቀን ብቻ ነው፡፡ ከእሳትም የተራቀና ገነትን የተገባ ሰው በእርግጥ ምኞቱን አገኘ፡፡ ቅርቢቱም ሕይወት የመታለያ መሳሪያ እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡

(190) 🌓ሰማያትንና ምድርን በመፍጠር ሌሊትና ቀንንም በመተካካት ለባለ አእምሮዎች በእርግጥ ምልክቶች አሉ፡፡

(191)🌍 (እነርሱም) እነዚያ ቆመው፣ ተቀምጠውም፣ በጎኖቻቸው ተጋድመውም አላህን የሚያወሱ በሰማያትና በምድር አፈጣጠርም የሚያስተነትኑ፡- «ጌታችን ሆይ! ይኸን በከንቱ አልፈጠርከውም፤ ጥራት ይገባህ፤ ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን» የሚሉ ናቸው፡፡

(192) 🔥«ጌታችን ሆይ! አንተ እሳት የምታገባውን ሰው በእርግጥ አዋረድከው፤ ለበደለኞችም ምንም ረዳቶች የሉዋቸውም፡፡»

(193) 💙«ጌታችን ሆይ! እኛ በጌታችሁ እመኑ በማለት ወደ እምነት የሚጠራን ጠሪ ሰማን፡፡ አመንም፡፡ ጌታችን ሆይ! ኃጢአቶቻችንንም ለኛ ማር፡፡ ክፉ ሥራዎቻችንንም ከኛ አብስ፡፡ ከንጹሖቹም ሰዎች ጋር ግደለን፤»

(194) 💙«ጌታችን ሆይ! በመልክተኞችህም ላይ ተስፋ ቃል ያደረግክልንን ስጠን፡፡ በትንሣኤ ቀንም አታዋርደን፡፡ አንተ ቀጠሮን አታፈርስምና» (የሚሉ ናቸው)፡፡

(195) 💚ጌታቸውም «እኔ ከእናንተ ከወንድ ወይም ከሴት የሠሪን ሥራ አላጠፋም፡፡ ከፊላችሁ ከከፊሉ ነው፤ በማለት ለነርሱ ልመናቸውን ተቀበለ፡፡ እነዚያም የተሰደዱ ከአገሮቻቸውም የተባረሩ በመንገዴም የተጠቁ የተጋደሉም የተገደሉም ክፉ ሥራዎቻቸውን ከእነርሱ በእርግጥ አብሳለሁ፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በእርግጥ አገባቸዋለሁ፡፡ ከአላህ ዘንድ የኾነን ምንዳ (ይመነዳሉ)፡፡ አላህም እርሱ ዘንድ መልካም ምንዳ አልለ፡፡ »

(198) 💙ግን እነዚያ ጌታቸውን የፈሩ ለእነሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች በውስጧ ዘውታሪዎች ሲኾኑ ከአላህ ዘንድ (የተሰጡ) መስተንግዶዎች አሏቸው፡፡ አላህም ዘንድ ያለው (ምንዳ) ለበጎ ሠሪዎች በላጭ ነው፡፡

(200)💙 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ታገሱ ተበራቱም፡፡  ተሰለፉም፡፡ ትድኑም ዘንድ አላህን ፍሩ፡፡ 3:165 - 200

🕋 ISLAMIካ🧐

05 Dec, 17:27


ልቀቋቸው!!!

ምንም ነገር ብታደርጉ መለወጥ የማትችሏቸውን ነገሮች ልቀቋቸው!

ምንም ብትታገሉ የራሳችሁ ልታደርጓቸው የማትችሏቸውን ሰዎች ልቀቋቸው!

ምንም ብታሰላስሏቸው እንደገና የማትመልሷቸውን ያለፉ ሁኔታዎች ልቀቋቸው!

በቃ ልቀቋቸው! ለፈጣሪ ስጧቸው!

መልካም ምሽትና የእረፍት እንቅልፍ ለሃገሬ ሰዎች!!!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

🕋 ISLAMIካ🧐

03 Dec, 14:48


በመልካም ምግባርህ ዳእዋ አድርግ/ ወደ ኢስላም ተጣራ።

🕋 ISLAMIካ🧐

03 Dec, 14:16


አምላኬ ስነምግባሬን አሳምረው።

🕋 ISLAMIካ🧐

03 Dec, 10:54


🛬 ቀናት በሰአታት አክናፍ ተጭነው ወደ ረመዳን በር አፋፍ እያደረሱን ነው

ጊዜ በማይሰማ ኮቴው ወደ ተቆጠሩት ቀናት አዘናግቶ እየወሰደን ነው

-ዛሬም ዝግጅታችንን እና መሰናዷችንን ወደ ረመዳን አቀጣጭተን በዋኒያ አጋፋሪነት በ ኡስታዝ አህመድ አዘጋጅነት ስለ ተናፋቂው እና የችሮታው ፀጋ ስለሞላበት ወር ልንዘክር ቀጥሮ ይዘናል

እናንተስ የት ናችሁ?

🏢 ከ 11:30 ጀምሮ መሀል መካኒሳ የሚገኘው የቢላሉል ሀበሺ አዳራሽ በሮች ተከፍተው እርስዎን ይጠባበቃሉ።

አድራሻ ከጠፋዎት ወይ ለማንኛውም መረጃ ☎️+251935608888 ላይ ለመደወል አያመንቱ ኦፕሬተራችን በትህትና ታስተናግድዎታለች።

ኢንሻአላህ!

🕋 ISLAMIካ🧐

02 Dec, 17:41


« ህመማችን ሁሉንም አያሳምም። ስቃያችን ለሁሉም አይሰማም። በእኛ ህመም እና ስቃይ እስትንፋሳቸውን ለመቀጠል ሰርክ የእኛን ስቃይ እና ህመም የሚፈልጉ ሰዎች አሉ። ከእኛ ደህንነት የበለጠ የእኛ መታወክ ሰላም የሚሰጣቸው አሉ።
እንባሽን ሪዝቁ ያደረገ፣ ለቅሶህን ጥም መቁረጫ አድርጎ የያዘ አለ። ባንቺ ሀዘን የሚፈረጥሙ ሰላሉ በርታ በይ! ስብራትህ የሚያፈረጥማቸው አሉና ጠንከር በል። ህመማችሁ ይህን ለመረዳት ከጋረዳችሁ የዓለምን ፖለቲካ በጥልቀት መርምሩ። እነማን በስብራቶቻችን እንደፈረጠሙ። እነማን በስቃያችን እንደ ደለቡ ልብ በሉ! ሰላም ለእነዝያ በህመም ስቃያቸው እስትንፋስ ለተቀጠለባቸው! »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:

🕋 ISLAMIካ🧐

02 Dec, 14:12


የደስታ ግማሹ እናት ነች
ቀሪው ግማሽ ደሞ የእናት ዱዓ ነው!

🕋 ISLAMIካ🧐

02 Dec, 12:08


☀️ ለነሱ ብለን ሁሉን ነገር
እናጣና በስተመጨረሻም
እነሱንም እናጣለን ።

#ግን.....

🕋 ISLAMIካ🧐

02 Dec, 09:26


ወደ ረመዳን ለምናደርገው ጉዞ ስንቅ የምንቋጥርበት 4ተኛ ምእራፍ ላይ ደርሰናል

ማስታወሻ [ዘውትር ሀሙስ እለት ይዘጋጅ የነበረው የረመዳን ዝግጅታችን ለዚህኛው ሳምንት ለነገ ማክሰኞ ተሸጋሽጓል። በቢላሉል ሀበሺ አዳራሽ ነገ ከ11:30 ጀምሮ እንገናኝ ]

በሶስቱ ምሽቶች ነፍሳችንን በኢማን አጥምቀናል ፣ ስብእናችንን በኢስላም ከፍ አድርገናል ፣ ወደ ልቅናችንም ብዙ እርምጃዎች ተጉዘናል።ነገም እንቀጥላለን።

ኢንሻአላህ
┈┈┈┈┈•❈••✦✾✦••❈•┈┈┈┈┈•

ረመዳን ምንድነው ?

🕸ረመዳን ወር ብቻ አይደለም ረመዳን የሰው ልጆች የሚሰደዱበት የመስከን የመለወጥ እና የመታደስ ሀገር ነው።

🕸ረመዳን የልቦች መርጊያ የሰው ልጆች ማረፊያ ደሴት ነው

🕸ረመዳን ለሰው ልጆች ብርንን ያዘለው መለኮታዊ መገለጥ (ቁርአን) የወረደበት ተአምራዊ ወቅት ነው

🏩ኡስታዝ አህመድ ሙስጠፋ ከዚህ በፊት ባልተለመደ (የስልጠና ይዘት ባለው) ለረመዳን ቀድሞ የመዘጋጀትን ጭብጥ ረቂቅ እና ውብ በሆነ ሀሳቦቹ ጥልቅ በሆኑ እይታዎቹ ያመላልሰናል ሀሳቦቹንም ያጋራናል።

#ዋኒያ_የረመዳን_መዳረሻ_ስንቅ
#ኡስታዝ_አህመድ_ሙስጠፋ
#ጉዞ_ወደ_ለቀው_ረመዳን_2
#ክፍል_4
#7ተኛ_ዙር_ስልጠና_ጀምረናል

🕋 ISLAMIካ🧐

01 Dec, 18:29


የአመሻሽ ተማፅኖ/ ያረብ

- አምላካችን ሆይ despite ወንጀላችን ወደ አንተ መቅረብ እንናፍቃለን ፣ እንከጅላለን የህይወታች ማእከላዊ ጉጉት እና ምኞት ወደ ላክልን ነቢይ የአኗኗር ዘይቤ መሰደድ ነው። ጉዳያችንን አሳምርልን ፤ ወንጀላችንን ማርልን።🥹

🕋 ISLAMIካ🧐

30 Nov, 17:49


🛣️ ጉዞ ወደ ላቀው ረመዳን ሁለት
🍕ክፍል ሁለት
የድምፅ ቅጂ 🔊

"ለሰው ልጆች ሁሉ መመሪያ የሆነውን ቁርአን እኛ ልንጠቀምበት ያልቻልነው ለምንድነው ?

አለም ላይ ዳኛ ያጡ ሀሳቦች አሉ ።ማን ነዉ የሚዳኛቸው ?

ኸይር ምንድነው በቁርአን ?

'ጥያቄ' የሚባለው ነገር ቁርአን ውስጥ ያለው ቦታ ምንድነው" ?


👤 ኡስታዝ አህመድ ሙስጠፋ ጉዞ ወደ ላቀው ረመዳን ዝግጅት መድረክ ላይ ከተናገሩት የተወሰደ

👂ሙሉውን ታደምጡት ዘንድ ያያዝነውን የድምፅ ቅጂ እንጋብዛለን።

(ዩቲዩብም ላይ ይህን የረመዳን ተከታታይ ዝግጅት ከምስል ጋር ለመከታተል ይህን ሊንክ👇 ይጠቀሙ) https://youtu.be/DYe_xthK1z4?si=UHcBwfLAC_qkkuvo-)

#ዋኒያ_የረመዳን_መዳረሻ_ስንቅ
#ኡስታዝ_አህመድ_ሙስጠፋ

🕋 ISLAMIካ🧐

30 Nov, 16:03


የእለቱ ዱአ/ፀሎት 🤲

ያ ረበና! የብዙ ትንቢቶች ማህደር የሆነችውን ሀገረ - ፍልስጤምና ህዝቦቿን ስቃይ በቃ በላቸው

ሀገራችንንም የሰላም ሰገነት የልምላሜ ደሴት አድርግልን

አዛኝ የሆንከው አምላካችን ሆይ ወንጀላችንን ማር ምልጃችንን ስማ 🥹

🕋 ISLAMIካ🧐

30 Nov, 12:24


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሙስሊም አግላይነት መቼ ይሆን የሚሻሻለው?

ባወጣው የሥራ ማስታወቂያ ላይ ሴት አመልካቾች አጭር ቀሚስና እጅጌ ጉርድ ሸሚዝ ለብሰው እንዲመጡ፣ ጸጉራቸውም ተገልጦ ወደ ኋላ ታስሮ እንዲመጡ (MINI SKIRT, SHORT SLEEVED SHIRT & TIE THEIR HAIR TO THE BACK) ይላል። ወንዶች ደግሞ ጺማቸውን መላጨት ብቻ ሳይሆን የሚለው ሙሉ በሙሉ ሙልጭ አድርገው ላጭተው (FULLY SHAVED BEARD ሆነው) መምጣት አለባቸው ይላል።

በአጭር አገላለፅ በእምነቱ ሙስሊም የሆነና ለዲኑ ቅድሚያ የሚሰጥ ሰው ዓይናችንን መሳተፍ አይችልም እንደማለት ነው።

ታዲያ እንደት ነው አየር መንገዱ «የኢትዮጵያ» የሚል የጋራ ስያሜ የሚሰጠው? ምክንያቱም የኢትዮጵያ ህዝብ ከግማሽ በላይ ሙስሊም ሆኖ ሳለ ሙስሊሙን ያጋለለ ተቋም በጋራ ስያሜ መጠራት የለበትም።

ይህ የአየር መንገዱ ድርጊት አዲስ አይደለም። ግን መቼ ነው የሚቀየረው ለማለት ነው። ምናልባት ዘመኑ ሲለወጥ ይህ እነ ኃይለ ሥራላሴ ጋር የተቸነከረ አስተሳሰብ ከተቀየረ!

አሁን ጺምና ሒጃብ በምን መልኩ ከሥራ ዘርፉ ጋር የሚጋጨው? አንዳንዶች ይህ ፕሮቶኮል ነው ይላሉ። ማነው ፕሮቶኮሉን ያወጣው? ከሰማይ የወረደ መሻሻል የማይችል ህግ ነው እንደ? ሰው እንዳዘጋጀው ሁሉ ሰው አካታች በሆነ መልኩ ያሻሽለዋል። ተቋሙ ይስተካከል! ይህን የአካታችነት ጉዳይ ሳይፈቱ ስለ ስኬቱ ማውራት አጥጋቢ አይሆንም።



Cc:
===
Ethiopian Airlines

||
t.me/MuradTadesse

🕋 ISLAMIካ🧐

28 Nov, 10:26


ወልይ ማለት : አሏህንና ባህሪያቶቹን የሚያውቅ ፣ የአሏህ ትእዛዛት ላይ የሚዘወትር ፣ ከወንጀሎች የሚርቅ ፣ ጣፋጭና ለስሜት የሚመቹ ነገራቶች ላይ ከመስሰማራት የተቆጠበ ነው ።

   ሸርህ ዐቂደት አልውስጣ

🕋 ISLAMIካ🧐

27 Nov, 18:11


የምሽቱ ዱአ

አምላኬ ሆይ! ልሳኔን ከሀሜት ልቤን ከምቀኝነት ሰውርልኝ

አይኔን የከለከልከውን ከማየት ጆሮዬ ያገድከውን ከመስማት አርቅልኝ።

ያ!ሰታር ነውሬን ደብቅልኝ

🕋 ISLAMIካ🧐

27 Nov, 10:21


ጉዞ ወደ ላቀው ወር ረመዳን 2|
ክፍል አንድ
የድምፅ ቅጂ 🔊

ረመዳን (የከውኑ) የፍጥረተ - አለሙ አሰራር የሚታደስበት ፣ የሰማያት በር የሚከፈትበት ፣ የሰው ልጆች ልቅና የሚገለጥበት ፣ የአላህ ጠቢብነት እና ሀያልነት የሚታይበት ተአምራዊ እና ረቂቅ ወር ነው።

"ለረመዳን በህዝብ ደረጃ እንደ ሀገር ወይም በአለም ደረጃ እኛ ሙስሊሞች ዝግጅት ብናካሂድ ምድር ላይ ለሁሉም ፍጥረታት እና ለሰው ልጆች በሙሉ ልናመጣ የምንችለውን ለውጥ አስቡት።

"በ 4 አመት አንድ ጊዜ ለሚካሄደው የአለም ዋንጫ ምን ያህል ነው ዝግጅት የሚደረገው?..."

"ልቦቻችን ውስጥ የላቁ ብዙ ነገሮች አሉ፤ አንዳንድ ሰው ልቡ ውስጥ ኳስ በጣም ልቋል ፣ ሌላው ሰው ልብ ላይ ደግሞ ስልጣን በጣም ልቋል፣ ሌላው ሰው ላይ ደግሞ ገንዘብ በጣም ልቋል


አላህ ደግሞ ልቦቻችን ላይ የእሱ ምልክቶች (ሸኣኢረ - ዲን) እንዲልቁ ይፈልጋል።እነዚህን ምልክቶች ማላቅ አላህ ከመፍራት ምልክት ነው።

🔬አላህ ከእኛ ጥረት ይፈልጋል። በጣርን ልክ ከረመዳን የመጠቀም አቅማችንን ከፍ ያደርገዋል

🔬ለዚህ ረመዳን ዝግጅት አድርገን ባንደርስ እንኳ አላህ በኒያችን ልክ እንደፆምን ቆጥሮ ይመነዳናል"


👤 ኡስታዝ አህመድ ሙስጠፋ ወደ ላቀው ረመዳን ዝግጅት መድረክ ላይ ከተናገሩት የተወሰደ

👂ሙሉውን ታደምጡት ዘንድ ያያዝነውን የድምፅ ቅጂ እንጋብዛለን።

(ዩቲዩብም ላይ ይህን ቅጂ ከምስል ጋር ለመከታተል ይህን ሊንክ👇 ይጠቀሙ https://youtu.be/DYe_xthK1z4?si=UHcBwfLAC_qkkuvo-)

#ዋኒያ_የረመዳን_መዳረሻ_ስንቅ
#ኡስታዝ_አህመድ_ሙስጠፋ

🕋 ISLAMIካ🧐

26 Nov, 14:36


ኢብኑ ወሕብ አሏህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል፡

እኔ ሁሌም ሰውን ካማሁ አንድ ዲርሃም ሶደቃ ላደርግ/ልሰጥ ነየትኩኝ።

ዲርሃምን ከመውደድ የተነሳ ሀሜትን ተውኩኝ።


📌 قال ابن وهب (توفي۱٩٧هــ) :

نوﻳﺖ ﺃﻧﻲ ﻛﻠﻤﺎ اﻏﺘﺒﺖ ﺇﻧﺴﺎناً ﺃﻥ ﺃﺗﺼﺪﻕ ﺑﺪﺭﻫﻢ ﻓﻤﻦ ﺣﺐ اﻟﺪﺭاﻫﻢ ﺗﺮﻛﺖ اﻟﻐﻴﺒﺔ.

📖 ترتيب المدارك [٢٤۰/٣].

🕋 ISLAMIካ🧐

26 Nov, 13:33


እስከ መጨረሻው አንብቡት‼️

ማክሰኞ በሪያድ ከተማ የተከሰተው አደጋ

የ Mercedes እና Lexus መኪና ፊት ለ ፊት ተጋጭተው ነበር..

"አምቡላንስ አየሁ ከዛም የተሰበሰበ ህዝብ፣

አንድ ወጣትን ልጅ እድሜው 26 አካባቢ የሆነን ከመኪናው ሲያወጡት አየው፡፡

ሰውነቱ በደም ተሸፍኗል አካላቱ ተቆርጠዋል፣ እግሩም ጭምር ተቆርጧል እና እሱም እየጮኸ ነው"፡፡ ይለናል የታሪኩ ዘጋቢ

ልጁም ወደ ወንድሙ እየተመለከተ ምናልባትም የቅርብ ቤተሰቡ ይሆናል

"መሞት አልፈልግም፣በጣም ፈርቻለሁ ፣ እሳት ነው ምገባው እኮ" ይለዋል

እዛው ተኝቶም እየጮኸ "ሙሀመድ እኔኮ አልሰግድም ነበር ምናልባትም አካል ጉዳተኛ እሆን ይሆናል መሞት ግን አልፈልግም፣ ከዚህ ቡሃላ እሰግዳለሁ፣ ወላሂ እሰግዳለሁ ብቻ ግን መሞት አልፈልግም" ይላል

ሰወችም ተሰበሰቡ፣ እኔም ሁሉንም ክስተት እየተመለከትኩ አዛው ቆምኩ፣ በጣምም ፈርቻለሁ፡፡

በቦታው ላይ የሚታየው በሙሉ እጅግ በጣም ይዘገንናል፣ ያስፈራል

የልጁም መድማት እየጨመረ መጣ ጩኸቱም _ ቀጠለ ሰውነቱም ወደ ሰማያዊ እየጠቆረ ሄደ፡፡

ሊያድኑት ግን አልቻሉም

አብሮት የነበረውም ልጅ እያለቀሰ “እሺ ሸሀዳ በል ከሊማዉን በል…በል” ይለዋል ልጁ ግን እየጮኸ ነበር ምላሱም ከሊማውን ልትል አልቻለችም

አላሁ አክበር፣ በጣም ፈርቶ ነበር፣ ግን ነፍሱም ተወሰደች ድምፁም ተሰወረ

ግን....ግን ሸሀዳውን ማለት አልቻለም ነበር

ከዚያም አልተንቀሳቀሰም፣ ሰውነቱም ደርቆ ቀረ

ዶክተሮቹም ያላቸውን መሳሪያ ሁሉ አወጡ ልጁንም ቃሬዛ ላይ አስቀመጡትና ጭንቅላቱን ሸፈኑት

ወደ ወንድሙም በመዞር “አለቀ” - “ወንድምህ የለም ዱዓ አድርግለት ልናድነው አልቻልንም ምክንያቱም ከጭንቅላቱ እና ከሰውነቱ ብዙ ደም ፈሷል” አሉት፡፡

ዘጋቢውም ይለናል፦" በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ከፊት ለፊቴ እያየሁት ግን ሸሀዳን ለማለት ሳይችል ሞተ እህት ወንድሞቼ ሞት ድንገት ነው የሚመጣው፣ ሰላታችሁን ግን ጠብቁ፣ በፍፁም ከነገ ጀምሮ እሰግዳለሁ አትበሉ፡፡

የመጨረሻ ቀናችሁ መቼ እንደሆነ ማንም አያውቅም እኔም ከዚህ ክስተት ቡሃላ መተኛት አልቻልኩም እንደ ህፃን ሳለቅስ ነበር ልጁን ባላውቀውም ቃላቶቹን ግን በደንብ አስታዉስ ነበር...” እሰግዳለሁ፣ ወላሂ ከዚህ ቡሃላ እሰግዳለሁ፣ መሞት ግን አልፈልግም..….”🥹🥹

ያ አላህ መጨረሻችንን አሳምርልን ከመጥፎ አሟሟትም ጠብቀን

አንብባችሁ ለሌሎችም ሼር አድርጉ ምናልባትም በዚህ ታሪክ የ1 ሰውን ህይወት ማቃናት እንችል ይሆናል፡፡

🕋 ISLAMIካ🧐

26 Nov, 08:14


እልም ባለ ገጠር ምድረ በዳ በሆነ መንደር በአፍሪካ በረሐ በጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ ከምታገለግል አንዲት ሴት ጋር ተገናኘሁ በማለት ገጠመኛቸውን ያወጉናል። ዶክተር ዐብዱረህማን ሱመይጢ ናቸው። ከሩቅ ስታየን ወደኛ እየቀረበች በመልካም ሰላምታ ተቀበለችን። ፈገግ እያለች እንኳን ደህና መጣችሁ አለችን።
"ሉብናናዊ ነሽ?" አልኳት በቅላፄዋ ታስታውቅ ስለነበር። "አዎ" አለችኝ።
"እዚህ ምን ትሰርያለሽ"
"የበጎ አድራጎት ድርጅት አገልጋይ ነኝ" መልኳ ድሎት አቀማጥሎ ያሳደጋት ግና ችግር ያቦሳቆላት መሆኑ ያሳብቃል
"ማነው የላከሽ" ስል ጠየቅኳት
"ቤተ ክርስቲያን ናት በልዩ ትዕዛዟ በዚህ ስፍራ እንዳገለግል የላከችኝ" ስትለኝ በአግራሞት አፌ እየተከፈተ
"ከመቼ ጀምሮ" አልኳት
"ከ25 ዓመት በፊት" አለችኝ።

ኻሊድ አርራሺድ ይህን ታሪክ ተናግሮ እንዳበቃ
  "ለህይወት የሚያስፈልጉ ነገሮች በሌሉበት ገጠር፣ ውሀ እንኳ በቅጡ በማይገኝበት፣ ያለ ምንም ደመወዝ ሉብናን የነበራትን የተድላ ህይወት ትታ የቤተክርስቲያንን ትዕዛዝ ልታስፈፅም መቸገር መራብን መርጣ ከበረሀው መሐል ተሰየመች።

ለምንድነው በዘመናችን ሙስሊሞች ለዳዕዋ መስዋዕትነት ሲከፍሉ የማናየው?!
እነርሱ ለክርስትናቸው ፊዳ ሲሆኑ እኛ ለእስልምናችን ዋጋ የማንከፍለው ለምንድነው?! እኛ ልንቀድም አይገባም?! ዲናችን አሸናፊና የበላይ አልነበረምን?!

የታል ብርታታችን
የታል ቆራጥነታችን
የታል ችግሮችን መሸከምና መቻላችን"

ተራሮች ነበርን እንዲያውም ከዚያ የበለጠ ጠንካሮች! በሞት ባህር ዘልቀን በመሐሉ የተጓዝን!

ምንጭ
ሪህለቱል ኸይር ፊ አፍሪቂያ

🕋 ISLAMIካ🧐

26 Nov, 06:54


➩የቀኑ ➌ቱ ሐዲሶች‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
ክፍል:- 283

➊) «አላህ በእናቶቻችሁ ላይ አደራ ይላችኋል። ከዚያም በአባቶቻችሁ፣ ከዚያም በጣም ቅርብ በሆኑት፣ ከዚያም በጣም ቅርብ የሆኑትን (ዘመዶቻችሁን) አደራ ይላችኋል።»
ረሱል (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ፦📒(1580/فتح الغفار (3
«إنَّ اللهَ يُوصيكم بأمَّهاتِكم، ثم يُوصيكم بآبائِكم، ثم بالأقربِ فالأقربِ.»
*
➋) «አንድ ሰው ወደ ነብዩ (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) መጥቶ የአላህ መልክተኛ ሆይ! ከሰዎች መካከል ከማንም በላይ መልካም ልውልለት የሚገባ ሰው ማን ነው? ብሎ ጠየቃቸው ረሱልም እናትህ አሉት፣ ከዚያስ አላቸው እናትህ፣ ከዚያስ አላቸው እናትህ፣ ከዚያስ አላቸው፤ አራተኛው አባትህ አሉት።»
ምንጭ:-📒ሶሒህ ሙስሊም (2548)
«...يا رَسولَ اللَّهِ، مَن أحَقُّ النَّاسِ بحُسْنِ صَحَابَتِي؟ قالَ: أُمُّكَ قالَ: ثُمَّ مَنْ؟ قالَ: ثُمَّ أُمُّكَ قالَ: ثُمَّ مَنْ؟ قالَ: ثُمَّ أُمُّكَ قالَ: ثُمَّ مَنْ؟ قالَ: ثُمَّ أبُوكَ.»
*
❸) «ዝምድና በዓርሽ ላይ ተንጠልጥላለች። እኔን የቀጠለ አላህ ይቀጥለው እኔን የቆረጠኝን አላህ ይቁረጠው ትላለች።»
ረሱል (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ፦📒ሶሒህ ሙስሊም (406)
«الرَّحِمُ معلَّقةٌ بالعرشِ تقولُ: مَن وَصَلني وصلَه اللهُ ومَن قطعني قطعه اللهُ.»

🕋 ISLAMIካ🧐

25 Nov, 19:33


🥹

🕋 ISLAMIካ🧐

25 Nov, 17:28


ባሏ ከዚህ አለም በሞት ተለየና ሚስትየዋም የሱን ልብስ ጓዳ ውስጥ አንጠልጥላው ትታዋለች። ለአመታት በሟቹ ኪስ ውስጥ ገንዘብ ታስቀምጥም ነበር፣ ከልጆቿ አንዱ ለግል ጉዳዩ ገንዘብ በጠየቀ ቁጥር ሂድ ከአባትህ ኪስ ውስጥ ውሰድ ትላለች። ይሄንን ያደረገችውም ልጆቹ ዘንድ የአባታቸው ትውስታ እንዳይቋረጥ ዘንድ መታሰቢያ አደረገችላቸው።
.
.
የህይወት መዓዛ፣ ታማኝነትና መልካም የፍቅር ቆይታ፣ የመልካም ስነምግባር ጫፍ ...ይሉታል። በሌላ አገላለፅ ‘እናት’ ..መምህርት (ት/ቤት) ስትሆን እንለዋለን።

'ሚስት'
'የትዳር አጋር'
'የፍቅር ጓደኛ' የሚለው 'ስም' ቦታውን ሲያገኝ!
ገራኢብ ወአጃኢብ🥰

ትርጉም በእኔ #ዒታብ_አይደለም !😊

🕋 ISLAMIካ🧐

25 Nov, 11:09


አላህ ያድለን
~ ~
ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

" أفضل الإيمان الصبر و السماحة."
{በላጩ ኢማን ትእግስትና ደግነት ነው።}
---------•
📚 [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 1097]

🕋 ISLAMIካ🧐

25 Nov, 06:55


የእናቶቻችንን ነገር አደራ ብለውናል ውዱ ነብይ ‼️ የዝምድናንም ነገር እንዲሁ
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬

➊) «አላህ በእናቶቻችሁ ላይ አደራ ይላችኋል። ከዚያም በአባቶቻችሁ፣ ከዚያም በጣም ቅርብ በሆኑት፣ ከዚያም በጣም ቅርብ የሆኑትን (ዘመዶቻችሁን) አደራ ይላችኋል።»
ረሱል (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ፦📒(1580/فتح الغفار (3
«إنَّ اللهَ يُوصيكم بأمَّهاتِكم، ثم يُوصيكم بآبائِكم، ثم بالأقربِ فالأقربِ.»
*
➋) «አንድ ሰው ወደ ነብዩ (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) መጥቶ የአላህ መልክተኛ ሆይ! ከሰዎች መካከል ከማንም በላይ መልካም ልውልለት የሚገባ ሰው ማን ነው? ብሎ ጠየቃቸው ረሱልም እናትህ አሉት፣ ከዚያስ አላቸው እናትህ፣ ከዚያስ አላቸው እናትህ፣ ከዚያስ አላቸው፤ አራተኛው አባትህ አሉት።»
ምንጭ:-📒ሶሒህ ሙስሊም (2548)
«...يا رَسولَ اللَّهِ، مَن أحَقُّ النَّاسِ بحُسْنِ صَحَابَتِي؟ قالَ: أُمُّكَ قالَ: ثُمَّ مَنْ؟ قالَ: ثُمَّ أُمُّكَ قالَ: ثُمَّ مَنْ؟ قالَ: ثُمَّ أُمُّكَ قالَ: ثُمَّ مَنْ؟ قالَ: ثُمَّ أبُوكَ.»
*
❸) «ዝምድና በዓርሽ ላይ ተንጠልጥላለች። እኔን የቀጠለ አላህ ይቀጥለው እኔን የቆረጠኝን አላህ ይቁረጠው ትላለች።»
ረሱል (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ፦📒ሶሒህ ሙስሊም (406)
«الرَّحِمُ معلَّقةٌ بالعرشِ تقولُ: مَن وَصَلني وصلَه اللهُ ومَن قطعني قطعه اللهُ.»

🕋 ISLAMIካ🧐

24 Nov, 20:04


ጎህ የለሊቱን ጨለማ እንደሚያስወግደው ሀሉ፡ የፈጅርን ሶላት በጀመዓ መስገድ የወንጀሎች ተፅዕኖ ከልብ ላይ ያስወግዳል።

ቀንህን በፈጅር ሶላት ጀምር።
በረካ ኑርና ደስታን ታገኛል።

Copy

🕋 ISLAMIካ🧐

22 Nov, 16:33


🔖የመኝታ ሰርዓቶች!!
    〰️〰️〰️〰️
➡️ከመተኛት በፊት በር እቃዎችን መዘጋጋት መከዳደንና እሳት ማጥፋት፣-

#ነብዩ ስለሏሁአለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል እቃዎችን ከዳድኑ ፣ኮዳዎችንም እሰሩ ፣በሮችንም ዝጉ ሰይጣን የታሰረን አይፈታም። የተዘጋን በር አይከፍትም፣ የተከደነንም አይከፍትም።መክደኛ ካጣችሁ እቃችሁ ላይ እንጨት አድርጋችሁ ቢሆን እንኳን የአላህን ስም ጥሩበት ።እሳትንም አጥፉ አይጥ ቤታችሁ ታቃጥላለች ።
📚ሙስሊም ዘግበዉታል

➡️ጀናባ ከሆነ ውዱዕ አድርጎ መተኛት፣-
አኢሻ - ረዲዬሏሁ ዓንሃ - እንድህ ብላለች ነብዩ ስለሏ አለይሂ ወሰለም ጀናባ ሆነው መተኛት ሲፈልጉ ውዱዕ ያደርጉ ነበር።


📚አህመድ ነሳኢይ ኢብኑ ማጃህ ዳርቁጥኒይ ወግበዉታል)

➡️ፍራሹን ጠረግ ማድረህ፣-
ነብዩ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል ለመተኛት ወደ ፍራሻችሁ ስትቀርቡ በሽርጣችሁ ውስጠኛውን ክፍል ሶስት ግዜ ጠረግ አድርጉት።

📚ቡኻሪ ሙስሊም ዘግበዉታል)

➡️ቤት ውስጥ ለብቻ አለመተኛት፣-
አብደላህ ኢብኑ ዑመር እንዳስተላለፉት ነብዩ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም ለብቻ መተኛትና ለብቻ ጉዞ መውጣት ከልክለዋል።

📚አህመድ ዘግበዉታል)

➡️ውዱዕ ማድረግ

ነብዩ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል ወደ መኝታ ስትሄድ ለሰላት የምታደርገውን ውዱዕ አድርግ።

📚ቡኻሪ ሙስሊም ዘግበዉታል)

➡️የመኝታ አዝካሮችንና የተወሰኑ የቁርአን አንቀጾች ማንበብ፣-

🔖ከቁርአን
ፋቲሃ ፣አየተል ኩርሲይ ፣ የበቀራ የመጨረሻ ሁለት አንቀጾች ፣ ሱረት ካፊሩን ፣ሱረት ኢኸላስ ፣ሱረት ፈለቅ፣ ሱረት ናስ፣ ከተቻለ ሌሎችም የአላህ መልእክተኛ ሲተኙ ያነቧቸው እንደነበረ የተዘገቡ አንቀጾችን ማንበብ።

አኢሻ - ረዲዬሏሁ ዓንሃ
እንዳስተላለፈችው፣የአላህ መልእክተኛ ዘወትር ሌሊት ሲተኙ ፣

👈قُلْ هُوَ ٱللَّهُ أَحَدٌ
👈قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ ٱلْفَلَقِ
👈قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ ٱلنَّاسِ
እነዚህን በማንበብ እጃቸው ላይ  ሶስት ሶስት ግዜ ተፍተው ከራሳቸውና ከፊታቸው በመጀመር የደረሱትን ያህል አካላቸውን ያብሱ ነበር።

🔖ከአዝካሮች
👈 بِاسْمِكَ رَبِّ وَضَعْتُ جَنْبِي وَبِكَ أَرْفَعُهُ، إِنْ أَمْسَكْتَ نَفْسِي فَارْحَمْهَا، وَإِنْ أَرْسَلْتَهَا فَاحْفَظْهَا بِمَا تَحْفَظُ بِهِ عِبَادَكَ الصَّالِحِين
▪️ትርጉም ፣- ጌታየ በስምህ ወገቤን አሳረፍኩ በስምህም አነሳዋለው፣ነፍሴን ከያዝካት እዘንላት ፣ከለቀካትም መልካም ባሮችን በምትጠብቅበት ጠብቃት።ሌሎችንም አዝካሮች ማለት--

➡️በቀኝ ጎን መተኛት
ነብዩ ስለሏሁአለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል፣- ወደ መኝታህ ስትሄድ ለሰላት የምታደርገውን ውዱዕ አድርገህ በቀኝ ጎንህ ተኛ።

➡️በሆድ አለመተኛት
ነብዩ ስለሏ ሁአለይሂ ወሰለም በሆዱ ተኝቶ ላዩት ሶሃባ ተነስ ይህ አተኛኝ አላህ የማይወደው ነው ብለውታል።

🔖መተኛትህ ካልቀረ በሱና ላይ ሁነህ ተኛ
👉ሱና የዱንያም የአሔራ ብርሀን ነው።
ህይወት ያለ ሱና ድቅድቅ ጨለማ ነው።

🕋 ISLAMIካ🧐

21 Nov, 21:37


#መልካም_ጥርጣሬ 🦋

:"በጌታችሁ ላይ መልካም ጥርጣሬ ቢኖራችሁ እንጂ አትሙቱ " ብለዋል የአላህ መልዕክተኛ ﷺ። እናም የሙዕሚን አስተሳሰቡ እንዲህ ነው ፦

💡:ብደሀይ ያልፍልኛል*

💡:ብታመም እድናለሁ*

💡:ብፈተን አልፋለሁ*

💡:ባዝን እስቃለሁ*

💡:ብወድቅም እነሳለሁ*

💡:ከርሃብ ቡሀላ ጥጋብ አለ*

💡:ከጥም ቡሀላ እርካታ አለ*

💡:ከእንባ ቡሀላ ሳቅ አለ*

💡:ከድካም ቡሀላ ረፍት አለ*

:አላህም እንዲህ ብሏል ፦

🔸{. . . ﻭَﻣَﻦ ﻳَﻘْﻨَﻂُ ﻣِﻦ ﺭَّﺣْﻤَﺔِ ﺭَﺑِّﻪِ ﺇِﻻَّ اﻟﻀَّﺎﻟُّﻮﻥَ}°

🔹«ከጠማማዎችም በስተቀር ከጌታው እዝነት ተስፋን የሚቆርጥ ማነው?»...*።[#አል_ሂጅር፡56]°

🕋 ISLAMIካ🧐

21 Nov, 08:55


በቀሩት 100 ቀናት ውሰጥ እነዚህን ነገሮች አድርገን ረመዳንን መቀበል እንችላለን።

🗓በቀን 1.14 የቁርአን ሱራ ተፍሲር ብናዳምጥ የሙሉ ቁርአን ትርጉም ሰንቀን ወደ ረመዳን እንዘልቃለን

🗓በቀን አንድ ሀዲስ ብንማር 100 ሀዲስ አውቀን ረመዳንን እንጀምራለን

🗓 ስለ 1 የአላህ ስም በቀን ብናነብ ወይም ብናጠና ረመዳን ሳይገባ 99ኙንም የአላህ ባህሪ ሚስጥራት ተረድተን ረመዳንን እንቀበላለን

🗓በቀን ከኣንድ ሱራ በዛ ያለ ቁርአን ብንቀራ አኽትመን ረመዳንን እንከፍታለን

-እስካሁን የባከነው ጊዜ ባክኗል ዛሬውኑ ከላይ ከተጠቀሱት ምርጫዎች አንዱን መርጠን እንጀምር-

ሌሎችም ለረመዳን ማድረግ ስላለብን ዝግጅት ህይወታችንን መለወጥ ስለምንችልበት የረመዳን አጠቃቀም አስገራሚ እና ጠቃሚ ነጥቦች ኡስታዝ አህመድ ሙስጠፋ በርቱእ አንደበቱ በሰፊው ይነግረናል።

ዛሬ ከ 11:30 ጀምሮ በቢላሉል ሀበሺ አዳራሽ እንገናኝ።

ሁላችሁም ተጋብዛቹሀል

ኢንሻአላህ!

#ዋኒያ_የረመዳን_መዳረሻ_ስንቅ
#ኡስታዝ_አህመድ_ሙስጠፋ

🕋 ISLAMIካ🧐

20 Nov, 13:55


አንድ መቶ (100) ቀናት ብቻ ለቀሩት የረመዳን ጉዞ የምንሰንቅበት የነገው ልዩ ስልጠና

1. የመጀመሪያው ጥያቄ
አምና "ለቀጣይ ረመዳን ይህን አደርገዋለሁ" ብለን ያቀድነው ምን ያህሉን እየተገበርን ነው? ምን ያህሉንስ ፈፅመናል? ምን ያህሉንስ በይደር አቆይተናል?። በስንፍና ፣ ጊዜ በማጣት ፣ ወይስ በመዘንጋት? መልሱን ለራሳችን እንመልስ ፤ ነፍሳችንን እንፈትሽ

-አሁንም 100 የመዳረሻ ቀናት አሉን እንጠቀምባቸው!!-

2.ሁለተኛው ጥያቄ
አምና አብረውን እስከ ቀጣይ ረመዳን "ይህን አደርጋለው "ያን እተዋለው" ብለው እቅድ ያቀዱ ፣ ራእይ የነደፉ የአለም ሙስሊሞች አሁን ምን ያህሎቹ አሉ? እኛስ እስከ ረመዳን እንደርስ ይሆን?

-ይህ ወር የሰማይ በሮች የሚከፈቱበት፣ የአላህ የእዘነት እጆች የሚዘረጉበት፣ ፍጠረታት ከወትሮው በተለየ መልኩ ተፈጥሮአቸው የሚታደስበት ፣ ለምድር ላሉ ህያው ፍጡራን ብቻ የሚለገስ ወርቃማ እድል።

🌅#ሀሙስ_አመሻሽ_በቢላሉል_ሀበሺ_አዳራሽ_
👤ከኡስታዝ_አህመድ_ሙስጠፋ ጋር

🕐#ከ_11_ሰአት_ተኩል_ጀምሮ ነፍሳችንን ፣ ህይወታችንን እና ረመዳንን የምናስተሳስርበት ፣ የምንፈትሽበት አስደናቂ ምሽት ተደግሷል። በነፃም ትታደሙ ዘንድ ጠርተናቹሀል።

ኢንሻአላህ


#ዋኒያ_የረመዳን_መዳረሻ_ስንቅ
#ኡስታዝ_አህመድ_ሙስጠፋ

🕋 ISLAMIካ🧐

20 Nov, 12:07


የእለቱ ዱአ

አምላኬ ሆይ ወንጀሌን ማረኝ ፣ የዚህችን አለም እና የፍጥረታትህን ሁሉ ረቂቅ ሚስጥር ግለጥልኝ።

🕋 ISLAMIካ🧐

20 Nov, 12:01


ጊዜዬ እንዳልባከነ ሚሰማኝ ቁርአንን ሳነብ ነው

🕋 ISLAMIካ🧐

18 Nov, 12:23


የፍጥረታት ሁሉ ነፍስ በእጅህ የሆነች ቀኗ ስትደርስ የምትወስድ 'አል ቃቢድ' ሆይ!

…ሩሐችን ተወስዳ መቃብር የገባን ቀን እዘንልን… በህይወታችን ነፍስ የምትዘራ ሲሳይን የምትዘረጋ 'አል ባሲጥ' ሆይ!
...ኑሯችንን አታጥብብን ሐያታችንን የጭንቅ አታድርግብን የፈለግከውን ዝቅ የምታደርግ 'አል ኻፊድ' ስትሻ ደግሞ ከፍ አድርገህ የምታስቀምጥ 'አር ራፊዕ'
...ከአንተ ውጭ ማንም የለምና ከዘቀጥንበት አውጣን ከወደቅንበት አንሳን የተዋረደን ለክብር የምታበቃ 'አል ሙዒዝ' የተከበረን የምታዋርድ 'አል ሙዚል' ነህና ከተከበርን በኋላ አታዋርደን ነውራችንን ገልጠህ መሳቂያ መሳለቂያ አታድርገን🤲♥️

🕋 ISLAMIካ🧐

18 Nov, 11:37


የእለቱ ዱአ 🤲

አል- ራህማን ነህና በአፅናፈ - አለም ውስጥ ላሉ ፍጡራንህ ሁሉ እዝነትህን ታወርድ ዘንድ እንለምንሀለን።

አል - ረሂም ነህና በአንተ ላመንን አማኒያን በሙሉ ውለታህን ትለግሰን ዘንድ እንጠይቅሀለን።

❤️ያወዱድ ውደደን
፣ ያጀባር ጠግነን❤️

🕋 ISLAMIካ🧐

16 Nov, 16:44


የምሽቱ ዱአ

የቁርአንን መገንዘብ ትለግሰን ዘንድ በልቅናህ እንለምንሃለን።

አሚን።

🕋 ISLAMIካ🧐

15 Nov, 13:48


የእለቱ ዱአ

የላቅከው አምላካ ሆይ! ወንጀላችን ቢበዛም ምልጃችንን ተቀበለን

ሀጥያታችንን ማረን አንተ መሀሪ ነህና
ልመናችንን ስማን

ህልሞቻችንን ሙላልን ሀሳባችንን አሳካልን

🕋 ISLAMIካ🧐

13 Nov, 21:05


ሲደበዝዝ ወይም ሲባክን የምታየውን ወንድም አላህ በርሱ ላይ የዋለውን ኒዕማ እያስታወስክ ልቡ እስኪሰክር ድረስ አሞግሰው። ድብቅ ፈገግታዎቹን በፊቱ መስመሮች ላይ ታነባቸዋለህ። ለቁርጠኝነት ዳዴ ለማለት የሚፈልጉ "ሃፍረቶችንም" ትመለከታለህ። እውነተኛ አሞጋሽ ከሆንክ ሩሑ ዳግም ሲታደስና ህይወቱ ሌላ መልክ ሲይዝም ትመለከታለህ። አንተ ምንም ትልቅ ሁን ማሞገስ ምንህንም አያጎለውም።
“ወንድሜ ሃሩንን እርሱ ከኔ የተሻለ አንደበተ ርቱዕ ነው" ያለው ነብዩላህ ሙሳ ነው።

Copy

🕋 ISLAMIካ🧐

13 Nov, 16:31


የእለቱ ዱአ

አላህ ሆይ በደል ሳንቆጥር ዝምድና ቀጣይ አድርገን

የወንጀላችንን ፋና አዳፍንልን

ተቀባይ ነህ እና መልካም ልመናችንን ተቀበለን።

🕋 ISLAMIካ🧐

13 Nov, 08:51


«ሊቢያ ዳግም በከፍታ ላይ..»💪

በሰሞኑ አለምን እያስደመመ ያለው አድሱ የሊቢያ ህገ-ስርዓት ሊቢያውያን ዳግሞ ወደ ስልጣኔያቸው እየገሰገሱ እንደሆነ ማሳያ ነው ።

ሊቢያ የጀግኖች ምድር....

.ካፌወች ለቤተሰብ ብቻ የተፈቀዱ እንጅ ጓደኛዬ፣ሰራተኛዬ፣ የስራ ባልደረባዬ በሚል ተልካሻ ምክንያት አጅነብይ ጋር መተሻሸት የለም።

②.የሊቢያ ምድር የሊቢያኖች ነች ሊቢያ የሙስሊሞች ናት ሒጃብ ግደታ ነው ሒጃብ ኒቃብ በመልበሱ  ነፃነቴ ተገፈፈ የሚል አካል ካለ ወደ አውሮፓ መጓዝ ይችላል።

.መኪና ይዛ ፀጉሯን ከፍታ ወይም ጠባብ ልብስ ለብሳ የምትሔድ ሴት መኪናዋም ይቀማል እሷም ትታሰራለች።

④.ወንድ ሱሪውን ዝቅ አድርጎ አውረቱን እያሳየ ሲሔድ ከተገኘ ወደ ወንድነቱ እስኪመለስ ታስሮ ይመከራል።

.ፀጉሩን አበላልጦ የቸቆረጠ ሰው ቀጥታ ተይዞ ፀጉሩ ይላጫል።

⑥ከላይ የተዘረዘሩትና መሰል ተያያዥ ድንጋጌወች ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋሉ።

ይህን የተናገሩት የሊቢያ የሀገር ውስጥ ሚኒስተር
👉ኢማድ ትራበልስ ናቸው።
©

🕋 ISLAMIካ🧐

13 Nov, 07:43


ሱብሀነላህ!

🕋 ISLAMIካ🧐

11 Nov, 07:50


ደሞዝ አልፈልግም!

ብዙውን ግዜ ኦሮሚያ መጅሊስ ውስጥ በደሞዝና በሙስና ጉዳይ ችግር እንዳለ ይነገራል። " እኔ የዱንያ ችግር የለብኝም አልሀምዱሊላህ። በስሬ ከሰላሳ በላይ ቋሚ ሰራተኞችን ከፍዬ ነው የማሰራው። ነጌ ጥሩ ሪቮ ይዤ ብታዩኝ አትገረሙ የራሴ ካምፓኒ አለኝና። ነገ "ጋሊ የነዳጅ ማዲያ ከፈተ" ብትባሉ አትደነቁ የራሴ ነዳጅ ማዲያ አለኝና። እኔ በግሌ ከ600 በላይ ደረሶችን ሳቀራ ነበርኩኝ አሁን ግን ያ ስራዬ ተቋርጧል። ስለዚህ የሚከፈለኝ 30 ሺ ብር ደሞዜ ተከፋፍሎ በተለያዩ ዞኖች ውስጥ ለሚያቀሩ ዓሊሞች ይከፈልልኝ። የኔ ዋናው ትኩረቴ የተሰጠኝን አማና በአላህ ዕገዛና በናንተ ትብብር በዚህ ቤት ውስጥ ያሉ ችግሮችን ማስተካከልና መጅሊሱን ወደ ተሻለ ደረጃ ማድረስ ነው። ለዚህ ደግሞ የናንተ ዱዓ እጅጉን ያስፈልገኛል። "

ኡስታዝ ጋሊ ሙክታር  غالي مختار أبو يقين  የ Majlisa Oromiyaa - የኦሮሚያ መጅሊስ - Oromia Mejlis ፕሬዚደንት ተደርጎ ከተመረጡ በኋላ ከተናገሩት!

🕋 ISLAMIካ🧐

11 Nov, 04:55


የእለቱ ዱአ 4#

ድሀ የሚወድ ልብ ለግሰን
የተራበ ማብላትን ፣ የታረዘ ማልበስን አግራልን።

አፉው ነህና ወንጀላችንን ሰርዝልን
ሳቲር ነህና መተላለፋችንን ከፍጡራን አይን ደብቅልን

ያ ሃዩ ያቀዩም ቢረህመቲክ

🕋 ISLAMIካ🧐

10 Nov, 09:05


( وَفِي أَنْفُسِكُمْ أَفَلا تُبْصِرُونَ ) 

"በነፍሶቻችሁ ውስጥ አትመለከቱምን?"

🕋 ISLAMIካ🧐

09 Nov, 15:57


[  ] ድፍን ሙስሊም ማህበረሰብ ውስጥ እየኖርን ሷሊህ ሚስት ፈልጉልኝ ሲባል

[  ] አንድ ሙስሊም ሚስቴ ትካፈለኛለች ብሎ ንብረቱን በእናት በአባት በልጅ ስም ሲያስቀመጥ

[  ] ድፍን ሙስሊም ማህበረሰብ ውስጥ ጫት የማይቅም ባል ፈልጉልኝ ሲባል

እንደ ኡማ ምን ያህል እንደወረድን ምስክር ነው።

©️

🕋 ISLAMIካ🧐

09 Nov, 06:27


እቺን ሴት በመለገስ እርዳን አምላኬ

🕋 ISLAMIካ🧐

08 Nov, 13:53


የእለቱ ዱአ

እኛን ውድ ኑሮውን ርካሽ አድርገው
ያ! ረብ🙏😅

🕋 ISLAMIካ🧐

08 Nov, 07:20


#ከአላህ_የሆነው 🤎

ሁለት ዐይነ-በሲሮች በመንገዳቸው ላይ የአባሲድ ልዕልት በመባል የምትታወቀው የሐሩን አል ረሺድ ሚስት ዙበይዳ አል አባሲያ(ኡሙ ጃዕፈር) ቤት አካባቢ አረፍ ይላሉ። ዙበይዳ በደግነቷ እና በእዝነቷ ትታወቅ ነበር። ከዛም አንደኛቸው ቁጭ ባለበት፡ «አላህ ሆይ! ካንተ የሆነን ችሮታ ለግሰኝ» በማለት ዱዓ አደረገ። አንደኛው ደግሞ፡ «አላህ ሆይ! ከኡሙ ጃዕፈር የሆነውን ችሮታ ለግሰኝ።» በማለት ዱዓ አደረገ! 🤎

ኡሙ ጃዕፈር የሁለቱንም ዐይነ በሲሮች ዱዓ እየሰማች ነበርና በነጋታው የአላህን ችሮታ ለጠየቀው ሁለት ዲርሓም፤ ከእርሷ ችሮታ ለጠየቀው ደግሞ ሙሉ የተጠበሰ ዶሮ(አሩስቶ) ውስጥ 10 የወርቅ ዲናር ወትፋ ላከችለት። 😊

የተጠበሰ ዶሮ የተላከለት ሰው የፈለገው ገንዘብ ስለነበር ሁለት ዲርሓም ለተላከለት ጓደኛው ዶሮውን ይሸጥለታል። ውስጡ የተጠቀጠቀ የወርቅ ዲናር እንደነበር አላወቀም! ከ10 ቀን በኃላ ኡሙ ጃዕፈር ከእርሷ የሆነውን ችሮታ(ሪዝቅ) ወደጠየቀው ዐይነ በሲር ትሄድና: «የኛ ችሮታ(ሐብት) ባለጸጋ አላደረግህም እንዴ?» በማለት ትጠይቀዋለች። ምንም ነገር ያላገኘው ይህ ሰው'ም: «የምን ችሮታ?» አላት!

ኡሙ ጃዕፈርም: «አንድ ሺ ዲናር» አለችው። ዐይነ በሲሩም: «አልደረሰኝም። ይልቅ የላክሽልኝን ሙሉ የተጠበሰ ዶሮ ለጓደኛዬ በሁለት ዲርሓም ሸጥኩለት።» በማለት የተፈጠረውን አስረዳት። እርሷም በአላህ ጥበብ ተገርማ: «ከእኛ ችሮታ የጠየቀውን አላህ ከእርሱ ከሆነው ችሮታው ከለከለው፤ ከጌታው የሆነን ሪዝቅ የጠየቀውን ደግሞ አላህ ባለጸጋ አደረገው፤ ሸለመውም።» በማለት ተናገረች! 🤎

የአላህ ሪዝቅ ከየትኛውም ፈድል የላቀ ነው። አላህ ከእርሱ የሆነን ችሮታ ይለግሰን 😊

#መልካም_ጁመዓ 🤎
Copy

🕋 ISLAMIካ🧐

08 Nov, 05:42


የጁምአ ስጦታ 📦

ይህን ካደረጋችሁ ጭንቀታችሁ ጠፍቶ ፣ ሰላማችሁ በዝቶ ፣ ሀሳባቹህ ተሳክቶ ድል በድል ትሆናላችሁ

🪐ህይወት የሚለውጥ ሀሳብ

ጌታችሁ እናንተ ላይ ሰላም እና እዝነትን ይልካል። ያ ሁሉን የፈጠረው ግዙፍ እና ሀያሉ ፈጣሪ ፥ ስለ እሱ ለመግለፅ ቃላት አቅም የሚያጥራቸው ፣ ቋንቋዎች ብርክ የሚይዛቸው ፣ አይምሮዎች ለመረዳት ጉልበቱ የሌላቸው ፥ ሀያሉ ጌታችሁ ነው እኮ "የሰላም መልእክት ይልካል" ያልኳችሁ።

የነቢዩንም እስትንፋስ መልሶ ሰላምታችሁን ያደርስላቸዋል እኛ አንድ ሰላዋት ስናወርድ ለለጋስነቱ ገደብ የሌለው አላህ በ 10 የእዝነት ብርሀን ያካብበናል

ከዛም መንገዶች በብርሀን ይታደሳሉ ህይወትም ይዋባል።

ዛሬ ጁምአ ነው ሶሉ አላ ሀቢብ/ ውዱን እና ተናፋቂውን ሰው በብዛት አውሱ


💕 «اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى
نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ...

اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى
نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ...

💞اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ...

📦ለሌሎችም በማጋራት ይህን የጁምአ ስጦታ ስጧቸው 🧧


https://t.me/ISLAMIKA_BORN_MUSLIM789

🕋 ISLAMIካ🧐

07 Nov, 17:58


ባል ወደ ሚስቱ በሃዘን ተሞልቶ ሲገባ ሚስት ምን ሆንክብኝ ብላ ጠየቀቺው ::

እሱም:- መሪያችን እያንዳንዱ ሁለተኛ ያላገባ ወንድ እንዲገደል አዘዙ አላት....!!

እሷም" አሏህ በርግጥም ሸሂድ እንድትሆን መርጦሃል ብላው እርፍ 😳

Copy

🕋 ISLAMIካ🧐

07 Nov, 03:30


ለቤተሰብ መልካም መዋል ሀጥያትን ይሰረዛል

🕋 ISLAMIካ🧐

06 Nov, 13:24


የእለቱ ዱአ

አመለ - ሰናይ ታረገኝ ዘንድ እማፀንሀለው፤ ታላላቆችን አክባሪ ፣ ለታናናሾች አዛኝ ፣ ልቦናን ትለግሰኝ ዘንድ እለምንሃለሁ።

ለወላጆች መልካም ውለታ ማድረግን እጠይቅሃለሁ ።

አንተን የሚያስቆጣ ምግባር ከማድረግ የመታቀብ ሀይልን ስጠኝ፤

በመሀሪነትህ  ዳስሰኝ በአዛኝነትህ አውሳኝ።

🕋 ISLAMIካ🧐

06 Nov, 11:36


ረመዳንን ሳይዘጋጁ መጠበቅ ማለት ምን እንደሆነ በሚገባን ቋንቋ ለመረዳት ያህል😉

World Cup(የዓለም ዋንጫ) ላይ የሚሳተፉ ተጫዋቾች ምንም ሳይዘጋጁ ወደ ሜዳው ገብተው እዛው ሜዳው ላይ ነው እንዴ የሚለማመዱት? Never አይደል?! ከዚያ በፊት ዝግጅቱ እንዴት አድካሚ እንደሆነ እና ምን ያህል ጊዜ እንደሚፈጅባቸው we can imagine! በቅድሚያ በደንብ ትሬን አድረገው ፤ ብዙ በጀት የተመደበለት ረዥም ጊዜ የሚፈጅ ዝግጅት አድርገው ብቃታቸውን በሚግገባ አረጋገጠው ሲጨርሱ የዝግጅታቸውን እና የልፋታቸውን ውጤት ለማቅረብ ነው ወደ ዋናው ሜዳ የሚገቡት። ይህ እንግዲህ ተራ ለሆነ የዱንያ ስኬት የሚደረግ ዝግጅት ነው።
ረመዳን በግል እና በህብረት ሆነን ህይወታችንን በሁሉም ዘርፍ አሁን ላይ ካለበት ወደተሻለ የህይወት መስመር የምናሳድግበት ታላቅ አጋጣሚ ሆኖ ሳለ ሳንዘጋጅ ሜዳው ላይ መጣድ አይከብድም?

እመኑኝ ያለ ዝግጅት የበረካውን 0.0000...1 ታህል እንኳ ማግኘት ይቸግረናል። ረመዳን ዱንያዊም ሆነ አኸራዊ ስኬት ላይ የሚያደረሰንን በረካ በውስጡ ይዟልና የረመዳንን ሚስጥር በደንብ እናጥናው ፣ እናስብ ፣ እናስተንትን! ሰሐቦች ረመዳንን አመቱን ሙሉ issue አድርገው ለምን ያዙት? ለምንስ በዚህ ልክ ከህይወታቸው ጋር አስተሳሰሩት? እስኪ በጥልቀት እናስብ!

اللهُم بلغنا رمضان بروح أنقى وقلب أتقى وعمل أرقى🤲

🕋 ISLAMIካ🧐

06 Nov, 10:57


ሰዎችን ድሮ በሰሩት ወንጀል አታነውሩ 😭

🕋 ISLAMIካ🧐

06 Nov, 09:38


ያ! ረህማን የነቢያችንን (ሰ.ወ) ህይወት በ ኸዲጃ (ረ.ዐ) ፍቅር እንዳሰከንከው ፣ እንደባረክከው ፣ በሀሴት እንደሞላሀው። የኛንም የባይተዋርነት ፅልመት በመልካም ሰው አፍካው ።

🕋 ISLAMIካ🧐

05 Nov, 18:46


የአደባባይ ልመና

ብቻችንን አልቻልንም። አምላኬ ሆይ! ለአይን ማረፊያ ለነፍስ መርጊያ የምትሆን መልካም እንስትን ለግሰን

ነፍሳችን የባይተዋርነት ቆፈን ይዟታል እና ከሐዋ ዘር የሠራሀትን አንተን የምናመሰግንባትን ሴት ጀባ በለን


ያሀዩ ያቀዩም😭😭🥹

🕋 ISLAMIካ🧐

05 Nov, 16:37


ዛሬ Channel 12 Hebrew ባወጣው የጀናዛ ምርመራ Report ቃዒዳችን አቡ ኢብራሂም ለ3 ቀናት ለ(72 ሰዓታት) በተከታታይ ሰውነቱ ውስጥ ምግብ እና ውሃ እንዳልገባ 😓እንዲሁም በኪሱ ውስጥ ያገኟት Mentos ማስቲካን እንደ ረሃብ ማስታገሻ እየወሰደ እንደነበር ገልፅዋል።

ثلاثة أيام بدون طعام يا أبا إبراهيم؟💔😭
ህዝቡ እየኖረ የነበረውን ኖሮ በጀግንነት መስዋእት ሆነ
ማረፊያህን ፊርደውስ ያድርግልህ ሰይዲ🤲

🕋 ISLAMIካ🧐

05 Nov, 15:01


ለምንድን ነው ስደውል ያላነሳሽው?
አስተማሪ ታሪክ
~
ለሆነ ጉዳይ ለሶስት ቀናት መንገድ ወጣሁ። ሌላኛው ሃገር እንደደረስኩ ሚስቴንና አንድ ልጄን ደህንነታቸውን ለማስረገጥ ደወልኩ። ከዚህ በፊት ከነሱ ተለይቼ አላውቅም። እነሱም መራቄን አያውቁትም። ካገባሁ ሶስት አመቴ ነው። የሆነ ሆኖ ስልኬ አልተነሳም። ስልኬ ከእጄ ሳይነጠል ሶስት ቀናት አለፉ። ያለ ግነት በየ እሩብ ሰዓቱ ቢበዛ በየ ግማሽ ሰዓት እደውላለሁ። ምላሽ የለም።

በሃይለኛ ተበሳጨሁ። ወንድሜ እና እህቴ ላይ ደወልኩ። የትንሿን ቤተሰቤን ደህንነት እንዲያረጋግጡልኝ ጠየቅኳቸው። ሰላም እንደሆኑ ነገሩኝ። አላመንኳቸውም።

የሚስቴ እናት (አክስቴ) ላይ ደወልኩ። ሰላም እንደሆኑ ነገረችኝ። ስልካቸውን እንደምጠብቅ ነገርኳት። ብጠብቅ ብጠብቅ አንድም የሚደውል የለም።
ሶስቱ ቀናት ረጃጅም ሶስት ወራት ያክል ሆነው አለፉ። አንዳንዴ ቁጣዬ ከውስጥ ሲገነፍል ይሰማኛል። ሌላ ጊዜ በሁኔታው በጣም እየተገረምኩ ምክንያቱን ለማወቅ እሞክራለሁ።

ሸይጧን አስፈሪ ጉትጎታዎችን ደግሞ ደጋግሞ ያመጣብኛል። ቀናቱ አለፉ። ወደ ሃገሬ ተመለስኩ። እግሬ እንደረገጠ ወደ ቤቴ ነበር የበረርኩት። እንደደረስኩ በሩን አንኳኳለሁ። እሱም ሳይበቃኝ ደወሉን ላይ በላይ እደውላለሁ። ባለቤቴ በሩን ከፈተች። ከነ ሙሉ ውበቷ፣ ከነ ሙሉ ድምቀቷ። ባማረ በደመቀ ሁኔታ ተቀበለችኝ። ከባድ አጋጣሚ ነበር። ልጄ ከኋላዋ አለ። አይኖቹ በደስታ ይጨፍራሉ። ሊያቅፈኝ እየሮጠ መጣ። እኔ እንደደነዘዘ ሰው ሆኛለሁ። ሰበቡም ጠፋኝ። በፍጥነት በቁጣዬ ቦታ ግርምት ተተካ።

ባለቤቴን የዚህ ሁሉ ቸልትኝነት ምክንያቱ ምን እንደሆነ ጠየቅኳት። ጉዞዬን አቋርጬ በፍጥነት ልመለስ ተቃርቤ ነበር። አጉል ጥርጣሬ ከያቅጣጫው ወሮኝ ነበር።
ባለቤቴ ተረጋግታ መለሰችልኝ። "ለእናትህ ደውለሃል?" አለችኝ። ለምን እንደጠየቀችኝ ምክንያቷ ባይገባኝም እንዳልደወልኩ ነገርኳት። ንግግሯ ገዳይ ነበር ። እንዲህ አለችኝ፡ "በነዚህ ቀናት ውስጥ ስሜትህ ምን እንደሆነ አየህ አይደል? የእናትህም ስሜት ይሄው ራሱ ነው፣ ለቀናት ሳትደውልላት ስትቆይ። ናፍቆት ለብልቧት፣ ስጋት ገብቷት እሷ ካልደወለች በቀር አንተ ደውለህ ድምጿን አትሰማም። ይሄን ጉዳይ በተደጋጋሚ ላስረዳህ ሞክሬያለሁ። የምትረዳ ግን አልሆንክም። ክቡር ባለቤቴ! ከዚህ የተሻለ መልእክቴን የማደርስበት መንገድ አላገኘሁም።

እድሜዋ ትንሽ ዐቅሏ ግን ትልቅ የሆነችዋን ሚስቴን አፈርኳት። አንገቴን ደፋሁ። ትምህርቱ በሚገባ ነው የደረሰኝ። የመኪናዬን ቁልፍ እያቀበለችኝ ወደ ጀሮዬ ጠጋ ብላ "ጀነትህ እየጠበቀችህ ነው" አለችኝ።

እድሜ ልኬን የማልረሳውን ትምህርት ከጠቢቧ ሚስቴ ተምሬ ወደ መጀመሪያዋ ውዴ ወደ እናቴ ሄድኩኝ። ፀፀት በማይጠቅምበት ቀን ከመፀፀት ነፍሴን ስላተረፈችኝ ውለታዋን መቼም አልረሳም። ለዚች ጠቢብና አስተዋይ ሚስት ምስጋና ይገባታል። አሳምራ ኮትኩታ ላሳደገቻት እናቷ ምስጋና ይገባታል። እሷን ለመረጠችልኝ እናቴ ምስጋና ይገባታል።

እሷን ሰበብ አድርጎ በእዝነቱ ከእንቅልፌ ያነቃኝ ጌታ ምስጋና ይገባዋል።

እናቴ! እናታቶቻችሁ ! በዱንያ ያሉ ጀነቶቻችን ናቸው። ሌላው ቢቀር በየቀኑ በመደወል እንኳ ቢሆን አትርሷቸው። ይሄ ትንሹ ነገር ነው። ልቦቻቸው እኛን ይጠብቃሉ። ለኛ ዱዓእ ያደርጋሉ። በየ ሰዓቱ ስለኛ ይጨነቃሉ። እያሰቡ እየተጨነቁም ደጋግመው በመደወል እንዳይረብሹን በመስጋት ከመደወል ይታቀባሉ። ባሎቻችሁን፣ ሚስቶቻችሁን ወላጆቻቸውን እንዲያስቡ በማስታወስ አግዙ።

ከ0ረብኛ የተመለሰ
የብዙዎቻችን በተለይም የወንዶች ችግር ነውና እንድንማርበት ብታሰራጩት ባረከላሁ ፊኩም።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 26/ 2017)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

🕋 ISLAMIካ🧐

05 Nov, 08:07


የሰው ልጅ እድሜ ሲለካ

የዘመን መስፈሪያ ላይ የሰው ልጅ እድሜ ሲለካ ፥ አመሻሽ ላይ ጀምበር ልትጠልቅ ካለው ወጋገን እስከ ምሽት ድረስ ያለውን ጊዜ ያህል አጭር ነው።

እቺን የብልጭታ ያህል አጭር የሆነች የምድር ቆይታችን፥ ዘላለማዊው ህይወታችን ላይ ትበይናለች እና እያንዳንዷን ሽርፍራፊ ሴኮንድ እንኳ ወደ አላማችን አቀጣጭተን ለማሳለፍ ፤ ከጊዜ ፣ ከምኞት እና ከስሜታችን ጋር ግብግብ እንፍጠር።

🕋 ISLAMIካ🧐

02 Nov, 19:22


ትልቁ ሽማግሌው ሰውየ ስለሂወቱ ምኞት እንዲህ ይገልፃል🥀

➞°✮አላህ ጊዚያችንን ወጣትነታችንን በመልካም ነገር ከሚያሳልፉት ባሮች ያድርገን ከመፀፀታችን በፊት~°✮

رجل كبير في السن يتحدث عن امنياته في الحياه

تمنيت أن أتزوج، و فعلاً تزوجت
ولكن الحياه ليست جميلة بلا أوﻻد

💧ተመኘሁ
➞°✮እንዳገባ ➷ተመኘሁ በርግጥም ➷አገባሁ ነገር ግን ➷ሂወት ያለ ➷ልጆች ➷አታምርም እና~°✮

فتمنيت أن أرزق بالأولاد، وفعلاً رزقت بالأولاد
ولكنني ما لبثت إلا وقد سئمت من جدران البيت !

💧ተመኘሁ
➞°✮አላህ ➷ልጆችን እንዲሰጠኝ ➷ተመኘሁ አላህ ➷በርግጥም ልጆችን ➷ረዘቀኝ ሰጠኝ ➷ነገር ግን ➷ከዛም ቡሀላ ➷ብዙም ➷አልቆየሁም ቤቴን ➷እስከሰለቸሁ~°✮

فتمنيت أن أمتلك منزلاً جميلاً به حديقة
وفعلاً وبعد عناءٍ وجهد امتلكت المنزل والحديقة، ولكن اﻷوﻻد كبروا !

💧ተመኘሁ
➞°✮ሰፊ ➷የሆነ ያማረ ➷ቤት አትክልት ➷ስፍራ ያለው ተመኘሁ ➷ከችግር ከድካም ➷ቡሀላ ሰፊ ➷የሆነ ቤት ➷አትክልት ስፍራ ➷ያለው ቤት አገኘሁ ➷ነገር ግን ➷ልጆች አደጉ~°✮

فتمنيت أن أزوج أولادي
وفعلاً تزوجوا، لكنني سئمت من العمل ومن مشاقه وأصبح يتعبني !

💧ተመኘሁ
➞°✮ልጆቸን ➷ልድራቸው ➷ተመኘሁ በርግጥም ➷አገቡ ነገር ግን ➷በጣም ከስራ ➷ተሰላቸሁ ስራ ➷እያደከመኝ መጣ~°✮

فتمنيت أن أتقاعد لأرتاح
وفعلاً تقاعدت، وأصبحت وحيداً كما كنت بعد تخرجي تماماً !

💧ተመኘሁ
➞°✮እንዳርፍ ➷ጡረታ እንድወጣ ➷ተመኘሁ በርግጥም ➷ጡረታ ወጣሁ ➷ነገር ግን ➷ብቸኛ ሆንኩ ➷ትምርት ጨርሸ ከተመረኩ ➷ቡሀላ ብቻየ ➷እንደነበርኩት ➷አሁንም ብቻየን ➷ሆንኩኝ~°✮

لكن بعد تخرجي كنت مقبلاً على الحياة
أما الآن فأنا مدبرٌ عن  الحياة

➞°✮ነገር ➷ግን ስመረቅ ➷ወደ ሂወት ➷እየገባሁ ነበር ➷አሁን ግን ➷እኔ ከሂወት ➷እየሸሸሁ ነው~°✮

ولكن لا زالت لدي أماني ..

➞°✮ነገር ➷ግን እኔ ➷ዘንድ አሁንም ➷ምኞትን ➷አልተወገደም~°✮

فتمنيت أن أحفظ القرآن .. لكن ذاكرتي خانتني
فتمنيت أن أصوم لله .. لكن صحتي لم تسعفني
فتمنيت أن أقوم الليل .. لكن قدماي لم تعد تقوى على حملي

💧ተመኘሁ
➞°✮ቁርአንን ➷ለመሀፈዝ ተመኘሁ ➷ነገር ግን ➷አእምሮየ ከዳችኝ ➷አልቻልኩም~°✮

💧ተመኘሁ
➞°✮ለአላህ ➷ለመፆም ተመኘሁ ➷ነገር ግን ➷ጤንነቴ ለአላህ ➷እንድፆም ➷አልሰጠችኝም ➷አልቻልኩም~°✮

💧ተመኘሁ
➞°✮ለሊትን ➷ለመስገድ ➷ተመኘሁ ነገር ➷ግን እግሮቸ ➷እኔን መሸከም ➷አይችሉም መቆም ➷አቃተኝ~°✮

فقلت صدق رسول الله ﷺ حينما قال :
إغتنم خمساً قبل خمس :
➊شبابك قبل هرمك
❷وصحتك قبل سقمك
❸وغناك قبل فقرك
❹وفراغك قبل شغلك
❺وحياتك قبل موتك

اللهم أعنا على ذكرك وشكرك
وحسن عبادتك ..

➞°✮የአላህ ➷መልክተኛ ﷺ ያንን ➷በተናገሩ ጊዜ ➷እውነት ተናግረዋል ➷አልኩ ከአምስት ➷ነገሮች በፊት ➷የአምስት ነገሮች ➷እድል እንዳታስመልጥ~°✮

➞°✮➊ወጣትነትህ ➷ከማርጀትህ በፊት ➷ተጠቀምበት~°✮
➞°✮❷ጤንነትህ ➷ከመታመምህ በፊት ➷ተጠቀምበት~°✮
➞°✮❸ሀብትህ ➷ደሀ ከመሆንህ በፊት ➷ተጠቀምበት~°✮
➞°✮❹ክፍት ➷ሰአትህ መሽቁል ➷ከመሆንህ በፊት ➷ተጠቀምበት~°✮
➞°✮❺ሂወትህ ➷ከመሞት በፊት ➷ተጠቀምበት~°✮

إن لم يكن في برنامجك اليومي
​ركعتي الضحى​
  ​وحزب من القرآن​
    ​ووتر من الليل​
     ​وكلمة طيبة​
  ​وصدقة تطفيء غضب الرب​
    ​وخبيئة لايعلمها إلا الله​
    فأي طعم للحياة بقي ..
يا رب نسألك الجنة والنجاة من النار..

➞°✮በየቀኑ ➷በፕሮግራምህ ውስጥ ➷እነዚህ ነገር ➷ከለሉ~°✮
➞°✮የዱሀ ➷ሁለት ረከዓ ➷ከለሉበት~°✮
➞°✮ከቁርአን ➷የተወሰነ እምትቀራው ➷ፕሮግራም ከለለህ~°✮
➞°✮ከለሊት ➷ውትር የምትሰግድ ➷ከለለህ~°✮
➞°✮ጥሩንግግር ➷ከለለህ~°✮
➞°✮ሰደቃ ➷የአላህን ቁጣ ➷የምታጠፋ የሆነች ➷ከለለህ~°✮
➞°✮ድብቅ ➷የሆነ ስራ ➷አላህ እንጂ ➷ማንም እማያውቃት ➷ከለለህ~°✮
➞°✮ለሂወት ምን ➷አይነት ጣእም ➷ቀርቶታል እነዚህ ➷ነገር ከለሉ~

Copied

🕋 ISLAMIካ🧐

02 Nov, 17:34


ከፍልስጥኤማውያን የሰው ልጅ ጥልቅ መከራ ውስጥ ሆኖ እንኳ እንዴት አላህን ማመስገን እንደሚችል ተምረናል

ከፍልስጥኤማውያን አላህ ወዳጆቹንም በከባዱ እንደሚፈትን ተምረናል

ከፍልስጥኤማውያን የትኛውም ''ይህማ የህይወቴ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው" ያልከው ነገር እንኳ ሲወሰድብህ ''እኛ የሱ ነን ወደ እሱም ተመላሾች ነን" ማለትን እና (ሪዷ) የአላህን ውሳኔ መውደድን ተምረናል

ከፍልስጥኤማውያን አላህ ለሰው ልጆች ሊያደርሰው የፈለገው ብዙ መልእክት አለ ላዳመጠው ፣ ላስተዋለው ፣ ላስተነተነወ።

አላሁመ- ንሱር - ፊሊስጢን - ወል-ሙስሊሚን

🕋 ISLAMIካ🧐

02 Nov, 14:35


በዩቲዩብ 10ሺ ተከታይ ማፍራታችንን ምክንያት በማድረግ የተፃፈ አጭር ሀተታ

ያለፉት 11 ወራት ገደማ ብዙ ቪዲዮዎችን (ከ50 በላይ) ከዋኒያ የከዋክብት ሰአት እንግዶች እስከ የሰልጣኞች ምርቃት እና ሌሎችም ዝግጅቶቻችንን ለኡማው አጋርተናል። በነዚህም ብዙ ተምረናል አስተምረናል

ጥሩ እይታ ማግኘት ከባድ ከነበረበት የመጀመሪያዎቹ ጊዜያት አንስቶ ብዙ እና ቋሚ ተመልካች እስካፈራንበት አሁን ድረስ የዘለቅንበትን ይህን ጉዞ 10ሺ ተከታይ በማፍራት ደምድመን ወደ ቀጣይ ምእራፍ እየተሻገርን ነው።

ይህ ወቅት አለም አቀፍ እና የሀገር ውስጥ (ኢትዮጵያዊያን) ተመልካቾችን ያገኘንበት እንዲሁም ድክመት እና ብርታታችንን ፣ እድል (opportunity ) እና ተግዳሮቶቻንን ያወቅንበት ጊዜ ነው።

ሁሉም ቪዲዮዎች ከዝግጅት እና ቀረፃ ጀምሮ እስከ ኤዲቲንግ ቀላል የማይበል ስራ ውስጥ አለፈው ነው ለተመልካች የሚደርሱት

የኢስላምን መልእክት እንዲህ የዘመኑን መንፈስ በተረዳ መልኩ የሚቀርብበት የዋኒያ አይነት መድረክ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ተረድተን በአላህ ፍቃድ እስከዚህ ተጉዘናል

ወደፊትም በአረህማን ድጋፍ ዋኒያ
ትውልድ ከ ትውልድ እየተቀባበለ የሚያበራው የኢማን ብርሀን ችቦ ሆኖ ይዘልቃል

ስንጠራቸው አከብረው ሳያሳፍሩን ለተገኙልን የትውልድ እንቁ የኡማው ከዋክብት እንግዶቻችን ታዳሚ ቤተሰቦች ኡስታዞቻችንን የቢላሉ ሀበሺ አስተዳደር በሙሉ ከልብ በመነጨ ስሜት በአላህ ስም በዩቲዩብ 10ሺ ተከታይ ማግኘታችንን ምክንያት በማድረግ እናመሠግናለን።

🖊️ ūśmáň műŝ

🕋 ISLAMIካ🧐

02 Nov, 10:06


🕧 ሰአት

እየቆጠረ ያለው ሰአት እና ሴኮንድ አይደለም እድሜያችን ነው።

🕋 ISLAMIካ🧐

01 Nov, 15:39


❤️‍🩹ወንዶች❤️‍🩹

ተርበው እንደበሉት እህል የጣፈጠች ፣ ተጠምተው እንደጠጡት ውሀ የምታረካ የህይወት ምንጭ የሆነች ሚስት አላህ ይስጣቹህ።

❤️ሴቶች❤️

የአይንሽን ቀለም አይቶ ምኞትሽን የሚያውቅ ፣ ከጌታው ምንዳን ከጅሎ አንቺን ለማስደስት የሚጥር ፥ አንቺን የማፍቀር ፀጋ የተሰጠውን ባል ከሪሙ ይለገስሽ።

💫 ላላገቡት እስኪ ላኩላቸው☺️💫


for more Join
https://t.me/ISLAMIKA_BORN_MUSLIM789

🕋 ISLAMIካ🧐

31 Oct, 10:43


•° ከጨነቀህ… ስገድ
ከፈራህ ስገድ
ካዘንክ ስገድ
ከተስተካከለልህ ስገድ
ስትደሰትም ስገድ… …………¶

قال تعالى:
﴿ولقد نعلم أنك يضيق صدرك بما يقولون فسبح بحمد ربك وكن من الساجدين﴾

🌹
•°
©

🕋 ISLAMIካ🧐

31 Oct, 08:13


🕋 ISLAMIካ🧐 pinned «እኛ በፍጥነት የሚከንፍ ጊዜ የሚባል ምህዋር ላይ የተሳፈርን ተጓዦች ነን ከዘመናት ያለመኖር አለም ወደ ህያውነት ለቅፅበታት ብልጭ ብለን  ወደ ቀጣዩ አለም የምንጠፋ/የምንሸጋገር ፍጡራን ይህን ስውር የጊዜን ዳና ብዙ ሰው አያየውም ጊዜ ግን አካላችን ፣ አለማችን እና ህይወታችን ላይ ሳያቋርጥ ይፈሳል ያልተወለዱትን ወደ ፅንስ ፣ ወጣቶችን ወደ እርጅና ፣ አረጋውያን ወደ ሞት እያተመማቸው ነው። ትውልድ እና…»

🕋 ISLAMIካ🧐

31 Oct, 06:25


አንዳንዴ ነፍሴ ኮምፓሷ የጠፋባት ታንኳ ትሆንብኝ እና የምሄድበት አቅጣጫ ፣ የምራመድበት መንገድ ትክክለኛነት ይሳከርብኛል። አምላኬ ሆይ የልቤ መሪ ፣ የጎዳናዬ ጠቋሚ አንተ ነህ እና መዳረሻዬን ግለጥልኝ።

🕋 ISLAMIካ🧐

30 Oct, 10:01


እኛ በፍጥነት የሚከንፍ ጊዜ የሚባል ምህዋር ላይ የተሳፈርን ተጓዦች ነን ከዘመናት ያለመኖር አለም ወደ ህያውነት ለቅፅበታት ብልጭ ብለን  ወደ ቀጣዩ አለም የምንጠፋ/የምንሸጋገር ፍጡራን

ይህን ስውር የጊዜን ዳና ብዙ ሰው አያየውም ጊዜ ግን አካላችን ፣ አለማችን እና ህይወታችን ላይ ሳያቋርጥ ይፈሳል ያልተወለዱትን ወደ ፅንስ ፣ ወጣቶችን ወደ እርጅና ፣ አረጋውያን ወደ ሞት እያተመማቸው ነው።

ትውልድ እና ዘመን የጊዜ ሀዲድ ላይ ሳያቋርጡ ይነጉዳሉ ስልጣኔዎች በዘመን ተሽረው ኋላቀርነት ይባላሉ
....

🖊️ በ ūśmáň műŝ 📚
'ታሪክህን እንደ አዲስ ፃፈው' 📖

🕋 ISLAMIካ🧐

29 Oct, 10:49


ለሙስሊም ወገኖቼ በህይወታችሁ ማወቅ ያለባችሁ ቁልፎች🔑🔑:

🧎‍♂️🧎 ሰላትህን ዘንግተህ በህይወትህ መልካም እድል አትጠብቅ።

👁️ አይንህን ሳትሰብር የውስጥ ሰላምን አትጠብቅ።

🎤ዘፈን እያዳመጥክ የቁርዓንን ጥፍጥና ለመቅመስ አታስብ።

ብቻህን ስትሆን አላህን እያመፅክ የኢባዳን ጣዕም አታስብ።

🇲🇵በአላህ መንገድ ላይ የታገለ ሁሉ አላህ እንደሚያግዘው እወቅ።

🥰ኸይርን ነገር እስክትለምደው ድረስ በመስራት መታገል አለብህ።

🔨ሃራም ነገርንም እስክትጠላው ድረስ በመራቅ ላይ መታገል አለብህ።

Copied

🕋 ISLAMIካ🧐

28 Oct, 18:56


እኔ ወንጀለኛ ፣ በዳይ ሆኜ ሳለው አምላኬ ሌላ ውለታ እየዋለልኝ ነው። 🥹

🕋 ISLAMIካ🧐

28 Oct, 18:51


ለሴት ልጅ መራቆትን እውቅና የሰጠው የሀገራችን ህግ ነውር አካል መሸፈንን ግልፅ እውቅና መስጠት እንዴት ተሳነው ...!


ኒቃቤን እለብሳለሁ
ትምህርቴን እማራለሁ

🕋 ISLAMIካ🧐

28 Oct, 09:54


እንደዚህ አይነት ሙስሊሞችን የሚጎዳ ህግ በፅኑ እንቃወማለን

🕋 ISLAMIካ🧐

27 Oct, 13:51


ብዙ ሰው ትኩረት ነፍጎታል። በተቃራኒው በማይረባ ነገር ተጠምዷል። መረጃው ያለው ሰው ትንሽ ስለሆነ ይመስለኛል።

አመናችሁም አላመናችሁም ሰሞኑን በበርካታ ትምህርት ቤቶች ኒቃብ ተከልክሏል። የሚደርስላቸው ተቋምም ሆነ ድምፅ የሚሆናቸው ግለሰብ አጥተው በርካታ ኒቃቢስቶች ትምህርት ካቆሙ ሳምንት አልፏቸዋል።

ለማን ቢነገር ይሻላል? መጅሊስ ይህን ጉዳይ ከሚመለከተው አካል ጋር ተነጋግሮ በቋሚነት ለምን አይፈታም? ምን እየተካሄደ ነው? ዛሬስ በምን እናመካኝ?

እህቶቻችንን ስልታዊ በሆነ መልኩ ከትምህርት ገበታ ማገድ እስከ መቼ?

ትኩረት ለኒቃቢስት ተማሪዎች!

ኒቃቧንም ትለብሳለች፣ ትምህርቷንም ትማራለች።


(ይህን መልዕክት በማሰራጨት ቢያንስ ሰዎች ዘንድ እየሆነ ስላለው ነገር መረጃው እንዲኖር እናድርግ። በዱዓችንም እናግዛቸው።

||
t.me/MuradTadesse

🕋 ISLAMIካ🧐

25 Oct, 16:48


በማእከላዊ ጋዛ ሰርጥ በዲር ኤል ባላ የሚኖሩ ፍልስጤማውያን ዳቦ ለማግኘት የሚያደረጉት ትግል!

በጥቅምት ወር የታተመው የሲኤንኤን ዘገባ እንደሚያመለክተው እስራኤል በጋዛ በፈፀመችው ወራራ ምክንያት ቢያንስ 148 ዳቦ ቤቶች በዱቄት እና በነዳጅ እጥረት ከአገልግሎት ውጪ ሆነዋል።

በቅርቡ የወጣው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት እንዳመለከተው ድርጅቱ ከአንዳንድ ዳቦ ቤቶች ጋር በመሆን የስንዴ ዱቄትና እርሾን በማቅረብ ክፍት ሆነው እንዲቆዩ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

እስራኤል በጋዛ እየፈፀመች ባለው ወረራ በርካታ የጋዛ ከተሞችን ያወደመች ሲሆን ፍልስጤማውያንም በከባድ ሰቆቃ ውስጥ እንደሚገኙ ተገልጿል።

🕋 ISLAMIካ🧐

25 Oct, 13:32


ሴቶች በትላልቅ አሰልጣኞች የሚሰጥ ስልጠና ተዘጋጅቶላቿል ብቴዱ ታተርፉበታላቹ

🕋 ISLAMIካ🧐

25 Oct, 07:05


💕 «اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى
نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ...

اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى
نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ...

💞اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ...

🕋 ISLAMIካ🧐

24 Oct, 16:57


ይህን ሰው ምን እንበለው 🤦‍♂😡

#በማሌዥያ የአልጋ ቁራኛ የሆነውን ባለቤቷን ለስድስት ዓመታት ስታስታምም የነበረችው ሚስቱን ከበሽታው ካገገመ በኋላ ፈቷት ሌላ ትዳር መስርቷል

በደረሰበት የመኪና አደጋ ባለቤቷ ምግብ በእጁ ጎርሶ ስለማይወርድለት በናሶጋስቲክ ቱቦ መመገብ፣ ዳይፐር መቀየር እና እንዲታጠብ መርዳት የእርሷ የእለት ከእለት ስራ ነበር።

ይህን ሁሉ አድርጋ እሱ ግን ..

በፌስቡክ ገጿ የቀድሞ ባለቤቷን እና አዲሲቷን ሙሽሪት መብሩክ ብላለች።ለባለቤቴ እንኳን ደስ አለህ ፤ በመረጥከው ህይወት ደስተኛ እንደሆንክ ተስፋ አደርጋለሁ። እባካሽ ልክ እንደ እኔ ተንከባከቢው #አልሃምዱሊለህ እኔ ሃላፊነቴን ጨርሻለሁ አሁን ተራው የአንቺ ነው ስትል መልዕክቷን አጋርታለች።

ምን አይነት ድንቅ #ሴት ናት ሰውየው ትልቅ እንቁ 💎 ነው ያጣው አላህ ላንቺ የተሻለ ይተካልሽ

🕋 ISLAMIካ🧐

24 Oct, 08:00


"በ7 አመቴ ነበር አባቴ የሞተው ፤ እኔም የቲም ሆኜ ነው ያደግኩት ፥ በልጅነቴ ነበር ራሴን የማስተዳደር ሀላፊነት ጫንቃዬ ላይ የወደቀው። በልጅነት አባትን የማጣት ህመምን አውቀዋለሁ፥ ኑሮዬን ለማሸነፍ ማስቲካ እያዞርኩ እሸጥ ነበር። አምስት ብር በወር የትምህርት ቤት ክፍያ አጥቼ ከትምህርት ቤት የተባረርኩ ቀን ነበር 'ወደ ፊት የየቲሞች መርጃ ድርጅት አቋቁማለው' ብዬ በልጅ ልቤ ራእይ የሰነቅኩት"ይላል የዛሬው ኮከብ እንግዳችን ያሳለፈውን የህይወት መንገድ ሲተርክ

📖'የቲምነት' የሚል መፅሀፍ አሳትሟል (ወላጅ በልጅነታቸው ስለሞተባቸው ልጆች እና ባላቸው ስለሞተባቸው ሚስቶች የሚያትት መፅሀፍ ነው)

👤በዘርፈ - ብዙ በጎ አድራጎቱ እና አፍ በሚያስሰፍት ዳእዋው የሚታወቀው ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ ዛሬ የዋኒያ መድረክ ላይ ይነግሳል

የአመታት ተሞከሮ  በነፃ ከሚታፈስበት ከዚህ እልፍኝ ተገኝተው ውድ ጊዜዎን ያሳልፉ ዘንድ ሁላችሁም በክብር ተጠርተዋል ።

🏢 ከ 11:30 ጀምሮ መሀል መካኒሳ የሚገኘው የቢላሉል ሀበሺ አዳራሽ በሮች ተከፍተው እርስዎን ይጠባበቃሉ።


አድራሻ ከጠፋዎት ወይ ለማንኛውም መረጃ ☎️+251935608888 ላይ ለመደወል አያመንቱ ኦፕሬተራችን በትህትና ታስተናግድዎታለች።

ኢንሻአላህ!

🕋 ISLAMIካ🧐

24 Oct, 05:23


ሰሞኑን በአዲስ አበባ በርካታ የመንግስት ት/ቤቶች ማስክ አውልቁ ጭምር እየተባለ ኒቃቢስቶችን ከትምህርት የመከልከል ወንጀል እየተፈጸመ ነው። ከብዙ ት/ቤቶች ጥቆማዎች ደርሰውኛል።

የፌዴራሉና የአዲስ አበባ መጅሊስ ከትምህርት ሚኒስተር እና ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር ተነጋግረው የኒቃቢስቶችን መብት ለምን በቋሚነት አያስከብሩም⁉️

እስከመች ነው በየአመቱ በኒቃብ ምክንያት የእህቶችን እንግልትና ስቃይ የምንሰማው? ይህ ነገር መቋጫው መቼ ነው? እስከ መቼ ሁሌ ሮሮ! አይበቃም ወይ?

ፍትሕ በትውልድ ሃገራቸው እንደ ሁለተኛ ዜጋ እየተቆጠሩ ትምህርት የመማርና ሥራ የመሥራት መብታቸው በተደጋጋሚ ለሚነፈጉት ኒቃቢስት ሴቶች



Cc:
====
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት
Ministry of Education Ethiopia


||
t.me/MuradTadesse

🕋 ISLAMIካ🧐

24 Oct, 05:02


መሪ ጌታ ግን ጌታ ይገስፆት እንጂ በዚህ ከቀጠሉ ቤት ለቤት እያንኳኩ 'መስተፋቅር እንሰራለን' ይላሉ።

አይ መሪጌታ ጉድ እኮ ነዎት 🤣

🕋 ISLAMIካ🧐

23 Oct, 16:18


ኧረ ጭራሽ መሪጌታ በቀጥታ መልእክትም መጡብኝ😅😰😡🤨

አላሁ ሙስተአን!

🕋 ISLAMIካ🧐

23 Oct, 14:25


- አምላኬ ሆይ ቁርአንን የህይወቴ ብርሀን ፣ የመንገዴ መብራት ፣ የትካዜዬ ማርከሻ አርግልኝ።

- አምላኬ ሆይ ቁርአንን ሰምቼው ማልጠግብ ቀርቼው ማልሰለች አድርገኝ።

- አምላኬ ሆይ ቁርአንን የምረዳበት ንፁህ ህሊና ፣ ብሩህ አይምሮ ስጠኝ።

አላሁመ አሚን

አሚን በሉ እስኪ።

🕋 ISLAMIካ🧐

22 Oct, 15:51


እድሉ እንዳያመልጣችሁ

ማንኛውም ሚዲያ ላይ የመስራት የሚፈልግ ወይም የዚህ ዘርፍ ዝንባሌ ያለው ሰው ያናግረኝ

ፆታ አይለይም

ፃፉልኝ በዚህ @Usman_mustofa

🕋 ISLAMIካ🧐

22 Oct, 14:59


የሚያስለቅስ ሀዲስ

የሚገቡበት ክርስቲያኖች ናቸው።"ብሎ ከዘረዘረላቸው በኋላ ሰባተኛውን ለመጥቀስ ፍርሀት ያዘው።
ነቢያችንም(ሰ.ዐ.ወ)፦"ሰባተኛውን በር ለምን አትነግረኝም?" ብለው ሲጠይቁት ጂብሪልም(ዐ.ሰ)፦"በሱ በር የሚገቡት ካንተ ዑመት የሆኑ ትላልቅ ወንጀሎችን ሰርተው ሳይቶብቱ/ሳይፀፀቱ የሞቱ ናቸው" ብሎ ሲመልስላቸው ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) እራሳቸውን ስተው ወደቁ። ከዚያም ጅብሪልም የረሱልን(ሰ.ዐ.ወ)ጭንቅላት ታፋው ላይ አሳረፈ።ልክ ሲነቁ ቀና አሉና፦"አንተ ጅብሪል ችግሬ በዛ ሀዘኔም በረታብኝ ከኔ ኡመት ጀሀነም ሚገባ አለ እንዴ?" ብለው ሲጠይቁት ጅብሪልም(ዐ.ሰ)፦" አዎን ካንተ ኡመት የትላልቅ ወንጀል ባለቤቶች ይገባሉ"ብሎ መለሰላቸው፣ የዐይናችን ማረፊያ ከእናት ከአባት በላይ ለኛ አዛኝ የሆኑትም ነቢይ ይሄን ሲሰሙ ተንሰቅስቀው ማልቀስ ጀመሩ።ጅብሪልም አብሯቸው አለቀሰ።
😭😭😭😭/ፊዳከ አቢ ውኡሚ ያ ረሱለላህ/😭😭😭😭
ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ይህኔ፦"ያጅብሪል አንተም ታለቅሳለክ?" አሉት ።
ጅብሪልም(ዐ.ሰ)፦"እንዴት አላለቅስ የኔንስ መጨረሻ በምን አውቃለሁ?
እብሊስ እኮ ከመላእክት በላይ አላህን ይገዛ ነበር አላቸው 😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭

🕋 ISLAMIካ🧐

22 Oct, 07:29


እነዚህን የጭንቀት ጊዜዎቻችሁን አትጥሏቸው ከነፍሳቹ በመነጨ ጥልቀት ወደ አላህ እንድትዋደቁ ምክንያት ይሆናሉ እና!

ወደ አላህ የተደረገ ህመም ያዘለ ጥሪ ሁሉ ደግሞ ህይወታችችሁን እስከ መጨረሻ የሚቀይር ተአምር ነው

🕋 ISLAMIካ🧐

22 Oct, 05:12


ረመዳን የቀረዉ ቀን ይህን ይመስላል
129 ቀናት ብቻ

አላሁመ በሊጝና ፊ ሸህሪ ረመዷን

🕋 ISLAMIካ🧐

21 Oct, 07:31


አንዴ ቁሙ🛑

😇በረካ ሁኑ

በቃ እሺ እየሄዳችሁ 😅😊

ግን ብታነቡት ይጠቅማችኋል🥹🙏

📰በተለይ የጥናት ነገር አልገራ የትምህርት ነገር አልገባ ያላችሁ ወይ የልጆቻችሁ ወደ ፊት ያሳሰባችሁ!

- እውቀትን የጠገቡ ፣ በማሰልጠን ልምድ የዳበሩ (እጩ ዶክተሮች) ፤  አስጠኚዎች በተመጣጣኝ ክፍያ ሊያገለግሏቹህ ተዘጋጅተዋል።

ደውላቹህ አማክሯቸው የመፍትሔውን ቁልፍ ይዘዋል 🔑

["በተለይ ለሴት ተማሪዎች ብቁ ሴት አስጠኚ አሰናድተናል" ብለዋል በረካ ይሁኑኑና]

☎️ 0940772235. ደዉላቹህ " 'በረካ Islamic Tutor' ነወ ወይ?" በሏቸው

🕋 ISLAMIካ🧐

21 Oct, 03:25


🦋❝ጀነት ስንገባ አንድም ሰው ከመካከላችን እንዲጎድል አንፈልግም..በሉ ተነሱ ልጆቼ❞ እያለች ልጆቿን ለሱብሒ ሶላት የምትቀሰቅስ አንዲት እናት ነበረች🥰🥰

አሏህ ለልጆቻቹህ ምርጥ ዓርዐያ የምትሆኑ ያድርጋቹህ  ያድርገን🤲🦋

🕋 ISLAMIካ🧐

20 Oct, 21:18


▪️ የጋዛው ሸሂድ የሕያ ሲንዋር ኑዛዜ!
➤ [ የኻን ዩኑስ የዘካ ኮሚሽን ፕሬዚደንት ዶ/ር ጀሚል አቡ ቢላል እንዳስተላለፉት ]
———

እኔ ግዞትን ወደጊዜያዊ እናት አገር፣ ሕልሙንም ወደዳርቻ የለሽ ትግል መለወጥ የቻለ ስደተኛ ልጅ የሕያ (ሲንዋር) ነኝ። እኒህን ቃላት ስደረድር የሕይወቴን ቅፅበቶች በመላ እያስታወስኩ ነው። ያደግኩባቸውን ጠባብ ጎዳናዎች፣ ያሳለፍኩትን ረጅም የወህኒ ኑሮ፣ በፍልስጤም ምድር የፈሰሰችዋን እያንዳንዷን ደም አስታውሳለሁ።

ፍልስጤም አንዲት ቅዳጅ ትውስታ፣ በፖለቲከኞች ጠረጴዛ ላይ የተረሳች ቁራጭ ካርታ በሆነችበት ዘመን በኻን ዩኑስ የስደተኞች መጠለያ በ1962 ተወለድኩ። ሕይወቴ የተፈተለው በእሳት እና አመድ መካከል ነበር። በወረራ ሥር መኖር ዘላለማዊ ወህኒ መሆኑን ገና በልጅ ዕድሜዬ ተረዳሁ። በፍልስጤም ምድር ተርታ የሚባል ሕይወት እንደሌለ በአፍላነቴ ተገነዘብኩ። በዚህች ምድር እኖራለሁ ያለ ሰው ዝናሩ የማይነጥፍ መሣሪያ በልቦናው ይታጠቅ፣ ለረጅሙ የነፃነት ጉዞ መንፈሱን ያዘጋጅ ዘንድ ግድ ይለዋል።

ኑዛዜዬ ከዚህ ይጀምራል…! ወረራውን በመቃወም የመጀመሪያዋን ድንጋይ ከወረወረው ታዳጊ ግዙፍ እውነታን ተረድተናል። የምንወረውራት እያንዳንዷ ድንጋይ ቁስላችንን አይቶ ዝም ላለው ዓለም የምናሰማት ቃላችን ናት። የሰው ማንነት የሚለካው በዕድሜው ሳይሆን ለእናት አገሩ በከፈለው መስዋዕትነት መሆኑን የጋዛ ጎዳናዎች አስተምረውኛል። የእኔም ሕይወት ያለፈው በዚሁ መልክ ነበር… ተደጋጋሚ ወህኒ፣ በርካታ ውጊያ፣ የበዛ ሕመም እና እስከገደፉ በተስፋ የተሞላ ሙቅ ሕይወት…

በ1988 ነበር የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶብኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ወህኒ ቤት የገባሁት። ፍርኃትን ከነጭራሹ አላውቀውም። በጨለማ የእስር ቤት ክፍሎች ሆኜም በግድግዳው ገጽ ላይ ወደሰፊው አድማስ የሚከፈት መስኮት፣ በብረት ፍርግርጎቹ መካከልም የነፃነቱን ጉዞ የሚያበራ ፋኖስ ይታየኝ ነበር። በእስር ቤት ሶብር መልካም ባህሪ ብቻ አለመሆኑን፣ ይልቁንም ባህርን ጠብታ በጠብታ የመጭለፍ ያክል እንደብረት ጠንካራ መሣሪያ መሆኑን ተረዳሁ።

ኑዛዜዬን እንካችሁ…! ወህኒ ቤትን አትፍሩ። ወህኒ ቤት የነፃነት ጉዟችን አንድ ግብዓት ነው። ነፃነት ከተሰረቀ መብት ይልቅ ከህመም ተፀንሶ በትዕግስት የሚቀረጽ ሐሳብ መሆኑን የተማርኩበት መድረሳ ነው።

በ2011 በ"ወፋኡል አሕራር" የእስረኛ ልውውጥ ስምምነት ስፈታ ማንነቴ እጅጉን መቀየሩን ለማስተዋል በቃሁ። የወጣሁት እምነቴ ጠንክሮ ነበር። ትግላችንም ከትግልነት ባለፈ እስከ መጨረሻዋ የደም እንጥፍጣፌያችን ተሸክመነው የምንዘልቅ የአላህ ውሳኔ (ቀደር) መሆኑን ተገንዝቤ ነበር።

ኑዛዜዬን እንካችሁ…! ነፍጣችሁን፣ ለድርድር የማይቀርብ ክብራችሁን፣ መሞት የማያውቅ ሕልማችሁን አጥብቃችሁ ያዙ። ጠላት ትግላችንን ማስቆም ይሻል። ወኔያችንን በማለቂያ የለሽ የድርድር ተስፋ ጠፍሮ ለማኮላሸት ይደክማል። እኔ ግን እላችኋለሁ… በመብታችሁ አትደራደሩ። ትግላችን በተሸከምነው ነፍጥ ብቻ የሚሰፈር አለመሆኑን አትርሱ። ትግላችን ፍልስጤምን መውደዳችን፣ በከበባና በድብደባ የማይፈታ ወኔያችን መሆኑን አስታውሱ።

ኑዛዜዬን እንካችሁ…! ለሸሂዶቻችን ደም ታማኝ ሁኑ። እሾሃማውን መንገድ ያሳየን ትውልድ በደሙ መስዋዕትነት የነፃነትን መንገድ አስጀምሮናልና በፖለቲካ ጨዋታ፣ በዲፕሎማሲ ውስለታ ክብሩን ዝቅ ከማድረግ ተጠንቀቁ። የእኛ መኖር ዓላማ ቀደምቶቻችን የጀመሩትን ትግል ከዳር ማድረስ ነውና የፈለገው ቢሆን ከመንገድ ማፈንገጥ አይገባም። ጋዛ ምንጊዜም የትግሉ ዋና ከተማ፣ የፍልስጤማዊ ወኔ መቀመጫ ልቦና ሆና ኖራለች። ወደፊትም ትኖራለች።

በ2017 የሐማስን የጋዛ ክንፍ አመራር ኃላፊነት ስወስድ ለእኔ ጉዳዩ የአመራር መቀያየር ጉዳይ ብቻ አልነበረም። ይልቁንም ከወንጭፍ ጀምሮ ወደነፍጥ ያደገው ገናና ትግላችን ዕድሜ የቀጣይነት ሠንሠለት ነበር። በእያንዳንዷ ቀናት የሕዝባችንን ዘወትራዊ ፍዳ በዓይኔ በብረቱ ታዝቤያለሁ። የነፃነት ጉዟችን እያንዳንዷ እርምጃም ብዙ መስዋዕትነት የሚከፈልባት መሆኑን ተረድቻለሁ።

አንድ ነገር ግን እርግጠኛ ሆኜ እነግራችኋለሁ…! እጅ መስጠት የባሰ ዋጋ ያስከፍለናል። ግዴለም በጥንካሬያችን እንዝለቅ። ዛፍ በሥሮቹ አፈሩን አንቆ እንደሚረጋ ሁሉ የፍልስጤምን አፈር ሙጭጭ አድርገን እንያዝ። ለመኖር የወሰነን ሕዝብ የትኛውም ንፋስ ከመሬቱ ሊነቅለው ከቶ አይችልም።

የአቅሷ ማዕበል ዘመቻ መሪ መሆን ለእኔ ትልቅ ክብር ነበር። የአንድ ግሩፕ ወይም የአንድ ንቅናቄ መሪ ሳይሆን ነፃነትን የሚያልም ፍልስጤማዊ ሁሉ ድምጽ መሆን እንደቻልኩ ተሰምቶኛል። ትግል ኃላፊነት እንጂ ምርጫ እንዳልሆነ ሁሌም እረዳ ነበር። እናም ይህ ልዩ ዘመቻ በፍልስጤማውያን የትግል መዝገብ አዲስ ገጽ የሚገልጥ፣ የተለያዩ ታጋይ ቡድኖችን በጠላት ፊት በአንድነት የሚያሠልፍ ዘመቻ እንዲሆን ጥልቅ ፍላጎት ነበረኝ፤ ጠላታችን ሕፃን ከሽማግሌ፣ ድንጋይ ከዛፍ ሳይለይ ሁሉንም ያጠቃልና።

ኑዛዜዬ ግለሰባዊ አይደለም…! ይልቁንም ነፃነትን ለሚያልም እያንዳንዱ ፍልስጤማዊ ሁሉ፣ በትከሻዋ ሰማዕት ልጇን ለምትሸከም እናት ሁሉ፣ በዕኩያን ጥይት ልጁ ለተገደለችበት አባት ሁሉ የጋራ ስንቅ የሚሆን ውርስ ነው።

የመጨረሻ ኑዛዜዬን እንካችሁ…! ትግላችን መና እንደማይቀር አትርሱ። የምንከፍለውን ዋጋ ብቻ ሳይሆን በወኔ እና በክቡር ስብዕና ጌጠን የኖርነውን ሕይወት አስታውሱ። የጋዛ የከበባ ኑሮና የወህኒ ውጣ ውረድ ትግሉ ትከሻ የሚያጎብጥ፣ ጉዞውም ሰውነት የሚያዝል መሆኑን አስተምሮኛል። ግና እጅ አልሰጥም ባይ ሕዝብ ብዙ ተዓምር ይሠራል።

ከምድራዊ ሕይወት ፍትህ አትጠብቁ። የዓለም ሕዝብ ሕመማችንን ዓይቶ እንዳላየ መሆን መምረጡን ስረዳ ኖሬያለሁ። እናንተም መረዳታችሁ አይቀርምና ከሌሎች ፍትህ መጠበቁን ትታችሁ ራሳችሁ ፍትህ ሁኑ። የፍልስጤምን ሕልም በልቦናችሁ ያዙ። ከእያንዳንዱ ቁስለት ጥንካሬን፣ ከእያንዳንዷ ዘለላ እንባ ተስፋን መምዘዝ ተማሩ።

ይሃችሁ የእኔ ኑዛዜ ነው…! መሣሪያችሁን በፍጹም አትጣሉ። ወንጭፎቻችሁን አታስቀምጡ። ሸሂዶቻችሁን አትዘንጉ። ሕልማችሁን አትተዉ። እኛ በአፈራችን፣ በልቦናችን፣ በልጆቻችን የወደፊት ተስፋ ውስጥ እንደምንኖር አትዘንጉ።

ኑዛዜዬ ይህ ነው…! እስከሕይወቴ መጨረሻ የታመንኩለትን የፍልስጤም ውዴታ፣ በጫንቃዎቼ የተሸከምኩትን ታላቅ ሕልም ከዳር አድርሱ። እኔ ብወድቅ እናንተ አትውደቁ። ወደመሬት ያልጣልኩትን ሠንደቅ ዓላማ ከፍ አድርጋችሁ አውለውልቡ። መስዋዕትነቴን እንደድልድይ ተጠቅማችሁ ለተተኪው ክንደ ብርቱ ትውልድ መደላድሉን ፍጠሩ። እናት አገር በተግባር የሚኖሩት ተጨባጭ እንጂ የሚተርኩት ተረክ አይደለምና በሚሰዋው እያንዳንዱ ታጋይ እልፍ ተተኪዎች እንደሚፈጠሩ ጥርጣሬ አይግባችሁ።

የእኔ ተራ ደርሶ ከተለየኋችሁ የነፃነቱ ማዕበል የመጀመሪያ ጠብታ እንደነበርኩ፣ ሕይወቴንም ጉዟችሁን ስትፈጽሙ በማየት ጉጉት የገፋሁ መሆኔን አትዘንጉ። በጠላታችሁ ጉሮሮ ውስጥ የተሰካችሁ እሾህ ሁኑ። ዓለም ለሐቃችን መታገላችንን እስኪረዳ፣ ለዕለታዊ ዜና የቁጥር ግብዓት ብቻ እንዳልሆንን እስኪገነዘብ ድረስ ትግላችሁን ቀጥሉ።

የሕያ ኢብራሂም ሲንዋር | ጋዛ

🕋 ISLAMIካ🧐

20 Oct, 21:18


የሸሂዱ ኑዛዜ

🕋 ISLAMIካ🧐

20 Oct, 09:54


💡 ስልክ ሲደወል ሰውዬው በማያውቅበት (ባልፈቀደበት) ሁኔታ ላውድ ስፒከር (ድምፁን ክፍት) ማድርግ አይፈቀድም!

ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿لا يتجالسُ قومٌ إلا بالأمانةِ﴾

“ሰዎች እርስ በርሳቸው አይቀማመጡም (አያወሩም) በእምነት (አንዱ የአንዱን ሚስጥር በመጠበቅ) ቢሆን እንጂ።”

📚 ሶሂህ አልጃሚ፡ 7604

▪️▪️▪️▪️🔸🔸▪️▪️▪️▪️

✔️በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

📱፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

📱፦ https://bit.ly/486xnrS

📱፦ https://bit.ly/41zEZkk

📱፦ https://bit.ly/4arMbTx

📱፦ https://bit.ly/41tIUPv

📱፦ https://bit.ly/3UTTSwh

🕋 ISLAMIካ🧐

17 Oct, 11:28


በዚህች አለም የእኛ ህይወት ዋጋ የሚኖረው የሌሎች ሰዎችን መከራ ለማቅለል ባደረግነው መልካም አስተዋጽኦ ልክ ነው ።

🕋 ISLAMIካ🧐

17 Oct, 11:14


የመሬት መንቀጥቀጥና ተመሣሣይ አደጋዎች በሚያጋጥሙበት ጊዜ የሚደረጉ ዱዓዎች፦

اللهم أعوذ بك من التردي والهدم والغرق والحرق، وأعوذ بك أن يتخطبني الشيطان عند الموت وأعوذ بك أن أموت في سبيلك مدبرا أو أموت لديغا

بسم الله الذي لا يضر مع اسمه شيء في الأرض ولا في السماء وهو السميع العليم

اللهم لا تقتلنا بغضبك، ولا تهلكنا بعذابك، وعافنا قبل ذلك

★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

🕋 ISLAMIካ🧐

16 Oct, 20:13


በርካታ በሮችን አንድ በአንድ ስታንኳኳ አይቶሃል። የሀብታም በር፤ የባለስልጣን በር፤ የባለ ዝና በር፤ የዘመድ በር፤… በየበሩ ስትወድቅ፣ በየመንገዱ ስትሰናከል አይቶሃል። አንዱ ሲያስከፋህ፣ ሌላው ሲያስደነግጥህ፣ ሦስተኛው ሲያሾፍብህ፣ ሌላኛው ሲያሴርብህ… ተመልክቷል።
ቀጥ ብለህ ስትቆም፣ ስትንዳለጥ፣ ስትወድቅ፣ ስትነሳ፣ ስትለፋ፣ ስታለቅስ… በመንገድህ ሁሉ የርሱን ደጃፍ እየዘለልክ ስትባትል አይቶሃል።  የርሱን ደጃፍ የምትረግጥበትን ቀን እየጠበቀ ነው። ከሁሉም ደጃፍ መፍትሄን አጥተህ በተሰበረ ልብ፣ በለቅሶ ተሞልተህ፣ በሀፍረት ተውጠህ፣ ተፀፅተህ በርሱ ግቢ የምትነጠፍበትን ቀን በናፍቆት ይጠብቃል።
:
«ሁሉም ቢገፉህ እኔ ደጋፊህ ነኝ!
ፍጥረት ቢጠሉህም እኔ ወዳጅህ ነኝ!
ቢያቆስሉህ እኔ ሀኪምህ ነኝ!
ከጎናቸው ቢያርቁህም እኔ ቅርብህ ነኝ!
ወደኔ ና!
ወደ እልፍኜ ጎራ በል!
ምንጊዜም ስትፈልገኝ አለሁ!
ከኔ ውጪ ሌላን አትጥራ! ምላሽ ከመስጠት አልታክትም! እኔ እበቃሀለሁ! ችግርህን እቀርፋለሁ! ጭንቀትህን እፈታለሁ! አግዝሃለሁ! እረዳሃለሁ! ስታስበኝ አስብሀለሁ! ስትለምነኝ እሰጥሀለሁ!»
እያለ!…
:
ስለ ''አል‐ወዱድ'' [ﷻ] ነው የማወራው!

©️

🕋 ISLAMIካ🧐

16 Oct, 13:55


በዛሬው ምሽት የቴክኖሎጂ ፕሮግራማችን ላይ መድረኩን የሚሾፍርልን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከ10 አመት በላይ ያስተማረውና እያስተማረ የሚገኘው ኢንጂነር ጂብሪል አክመል ይሆናል።

ተጋባዥ እንግዶቻችንም በሃገራችን ዩኒቨርስቲዎች የብዙ አመት የማስተማር ልምድ ያላቸውና በአሁኑ ወቅት ፒኤችዲያቸውን በአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ እየሠሩ የሚገኙ፣ በአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት የኤአይ ሪሰርቸር የሆኑ ናቸው።
ጥሩ ምሽት ታሳልፋላችሁ ብዬ አስባለሁ። ከወዲሁ ፕሮግራሞቻችሁን አመቻቹና ብትከታተሉ ለራሳችሁም፣ ለልጆቻችሁም፣ ለሃገራችሁም ትጠቅማላችሁ።


ዛሬ ማታ 2:30 ላይ በዚህ ሊንክ እንገናኝ።
https://t.me/MuradTadesse?livestream


ለሌሎችም ጠቁሟቸው።

🕋 ISLAMIካ🧐

16 Oct, 11:46


የሁልግዜም ዱዓህ ይሁን

1. አብደላህ ቢን ዐምሩ (رضي ﷲ عنهما) እንዲህ በማለት አላህን ይማፀኑ ነበር፦

﴿اللهمَّ لا تَنْزعْ منِّي الإمانَ كما أَعْطَيْتَنيه﴾

“አላህ ሆይ! ኢማንን (እምነትን) ከሰጠኽኝ በኋላ ከኔ ላይ አትውሰድብኝ።”

📚 ኢብኑ አቢ ሸይባህ ሙሰነፍ ውስጥ ዘግበውታል፡ 30964


2. ረሱል (ﷺ) እንዲህ በማለት ዱዓእ ያደርጉ ነበር፦ 

﴿اللهمَّ إنِّي أعوذُ بك من منكراتِ الأخلاقِ والأعمالِ والأهواءِ﴾

“አላህ ሆይ! ከመጥፎ ስነምግባር፣ ከመጥፎ ስራና ከስሜት ተከታይነት በአንተ እጠበቃለሁ።”

📚 ቲርሚዚ ዘግበውታል አልባኒ ሶሂህ ብለውታል፡ 3591

🕋 ISLAMIካ🧐

15 Oct, 04:39


ሱጁድ ላይ ስንሆን መዳፋችን መሬት ላይ በምናደርግበት ወቅት ሱናው ጣቶችን መግጠም ነው።

ሩኩዕ ላይ ስንሆን መዳፋችን ጉልበታችን ላይ በሚሆንበት ወቅት ደግሞ፡ ሱናው ጣቶችን መክፈት/መለያየት/ማራራቅ ነው።

ዕንወቅ|ዕናሳውቅ።

ضُمَّ أصابعك وأنت ساجد وفرِّقها وأنت راكع ‌🖐️
سُنةٌ ذكِّر بها غيرك

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

🕋 ISLAMIካ🧐

14 Oct, 17:40


የቂን…

የቂን ማለት ዙርያህ ሁሉ በተስፋ አስቆራጭና ድቅድቅ ጨለማ የተሞላ ቢሆንም አላህ ያሰብኩትን ሁሉ ያሳካልኛል ብሎ ማሰብ ነው።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

🕋 ISLAMIካ🧐

13 Oct, 17:09


ስንቅ ለቀልብዎ
part: ⑭
➪ቁርአን
@alahu_akber1

🕋 ISLAMIካ🧐

13 Oct, 07:30


በአዲስ አበባ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ዳግም መሰማቱ ተገለፀ!

-ሀሩን ሚድያ ጥቅምት 3/2017

በአዲስ አበባ ባለፈው ከተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝርት ቀጥሎ አሁንም ዳግም መከሰቱን ዶክተር ኤሊያስ ሊዌ ለኢቢሲ አረጋግጠዋል።

ዛሬ ጠዋት 1:37 ደቂቃ ከ50 ሰከንድ ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት አዲስ አበባ ድረስ መሰማቱንም ተናግረዋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው ባለፈው በተከሰተበት አዋሽ ፈንታሊ አካባቢ ሲሆን በሬክተር ስኬል 4.6 አካባቢ እነደሆነም ዶክተር ኤሊያስ ሌዊ ለኢቢሲ ሳይበር አረጋግጠዋል።

©ሀሩን ሚድያ

🕋 ISLAMIካ🧐

13 Oct, 06:41


ፍላጎቱን ያገኘ ሰው ማለት ያ ነው። ነፍሱን ከሀጢአት ያጠራት።

🕋 ISLAMIካ🧐

11 Oct, 16:05


ቀን 33/ የቁርአን ዊርድ 🍫
   ከገፅ 322----331☕️
በቁርኣን እንተዎወስ !!
=============
َِይህንን የቁርኣን አያህ በደንብ ያስተነተነ ሰው አላህ በሰጠው ማንኛውም ፀጋ አላህን አያማርም።

ﻭَﺁﺗَﺎﻛُﻢ ﻣِّﻦ ﻛُﻞِّ ﻣَﺎ ﺳَﺄَﻟْﺘُﻤُﻮﻩُ ۚ ﻭَﺇِﻥ ﺗَﻌُﺪُّﻭﺍ ﻧِﻌْﻤَﺖَ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻟَﺎ ﺗُﺤْﺼُﻮﻫَﺎ ۗ ﺇِﻥَّ ﺍﻟْﺈِﻧﺴَﺎﻥَ ﻟَﻈَﻠُﻮﻡٌ ﻛَﻔَّﺎﺭٌٌ۝
ከለመናችሁትም ሁሉ የሰጣችሁ ነው፡፡ የአላህንም ጻጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም፡፡ ሰው በጣም በደለኛ ከሓዲ ነው፡፡

‏( ሱረቱ ኢብራሂም፣ - 34)🍃🍃

1,564

subscribers

650

photos

58

videos