Ibn Yahya Ahmed @ibnyahya777 Channel on Telegram

Ibn Yahya Ahmed

@ibnyahya777


የተለያዩ ዲናዊ ፅሑፎችን ብቻ የማስተላልፍበት ቻናሌ ነው።

Ibn Yahya Ahmed (Amharic)

እንኳን ወደ Ibn Yahya Ahmed ቻናል እናመሰግናለን! ይህ የተለያዩ ዲናዊ ፅሑፎች መከላከያ ያለበት ቻናል ነው የሚለየን። Ibn Yahya Ahmed በትምህርት ለሚገኘው ዲናዊው ፅሑፍ እና ቴሌግራም ፕሮግራም እንዲሁም ሌሎች ተጠቃሚዎች በሚገኘው ፅሑፍ ላይ ይዘው ነው። እባኮትን እንሰምታለን! በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ዲናዊ ፅሑፎች እና ከእናንተ ደግሞ ተጠቃሚዎች ይበልጥ የተለያዩ መድረክዎን እና መማር የምንፈልገውን መልስ ይዘቱ።

Ibn Yahya Ahmed

12 Feb, 03:37


▪️ደበቅ ማለት

🔻ከሰዕድ ኢብን አቢወቃስ - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዓለይሂወሰለም - ይህን ሲሉ ሰምቼያለው ፦ " አሏህ እሱን ፈሪ ፣ ነፍሱ ያብቃቃ(ሀብታም) እና ደበቅ ያለ ባርያን ይወዳል። ". (ሙስሊም ዘግቦታል).

@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

10 Feb, 03:34


▪️የሚያጠራጥርህን ተው

🔻ከሐሰን ቢል ዐሊይ - ረዲየሏሁዐንሁማ - ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ ፡ ከአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዐለይሂ ወሰለም - ይህን ሐፍዤያለው ፦ " የሚያጠራጥርህን ነገር ትተህ ወደ ማያጠራጥርህ ነገር ሂድ። ". (ቲርሚዚይ ፥ 2518 ላይ ዘግበውታል.) ትርጉሙም ፡ የምትጠራጠርበትን ነገር ተውና የማትጠራጠርበትን ነገር ያዝ ማለት ነው በማለት ኢማም አንነዊ አብራርተዋል።

@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

09 Feb, 14:41


▪️ኑዛዜ

🔻ለወራሽ ኑዛዜ ማድረግ አይቻልም። እዳ ካለበት ደግሞ እዳ አለብኝ ብሎ ኑዛዜ ማድረጉ ግዴታ ነው። ከወራሾቹ ውጭ ለሌላ አካል የንበረቱን ሲሶ(1/3ተኛ) ኑዛዜ ማድረግ ይፈቅድለታል። ለምሳሌ መስጂድ ለማሰርያ እና መሰል መልካም ነገራቶች ማለት ነው። ነገር ግን ወራሾቹ በጣም ብር ሚያስፈልጋቸው ከሆነ ይህንን ኑዛዜ ባያደርግ መልካም ነው። ምክንያቱም ነብዩ - ሰለሏሁዓለይሂወሰለም - ይህን ብለዋልና ፡ " ወራሾችህን ደሀ ሆነው ሰዎችን የሚለምኑ አድርገህ ከምትተዋቸው ይልቅ ሀብታም አድርገህ ብትሞት የተሻለ ነው። ". (ቡኻሪ ፥ 4409 / ሙስሊም ፥ 1627)
~~
ኢብኑዑሰይሚን * ሸርሕ ሪያዱሷሊሒን ፥ 2/352-3
@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

05 Feb, 03:52


▪️ችግር ቢደርስባችሁም ሞትን አትመኙ

🔻ከአነስ - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዐለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " ከእናንተ አንድኛችሁ ለደረሰበት ችግር ብሎ ሞትን አይመኝ ፤ መስራቱ የማይቀር ከሆነ እንዲህ ይበል ፡ አሏህ ሆይ! ህይወት መኖሬ ለኔ መልካም ከሆነ አኑረኝ ፤ መሞቴ ለኔ መልካም ከሆነ ውሰደኝ(አሙተኝ)። " (ሙተፈቁን ዐለይህ)

@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

05 Feb, 03:42


▪️ሞትን አትመኙ

🔻ከአቢሁረይራህ - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዐለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " ከእናንተ አንድኛችሁ ሞትን አይመኝ ፤ መልካም ሰሪ ከሆነ ምናልባት ሊጨምር ይችላል ወይም ደግሞ መጥፎ ሰሪ ከሆነ ተውበት ሊያደርግ ይችላልና። " (ሙተፈቁን ዐለይህ * ቃልበቃል ንባቡ የቡኻሪ ነው)

@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

04 Feb, 03:54


▪️ቀብርን መዘየር

🔻ከቡረይደህ - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዐለይሂወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " ቀብርን ከመዘየር ከልክያችሁ ነበር ፤ ዘይሯት " (ሙስሊም ዘግቦታል). በሌላ ዘገባ ላይ አኺራን ታስውሳችኋለች የሚልም አለ።

@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

04 Feb, 03:25


▪️ጥፍጥና ቆራጭ

🔻ከአቢሁረይራህ - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዐለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " ጥፍጥና ቆራጭ የሆነውን (ሞት) ማስታወስን አብዙ። ". (ቲርሚዚይ ፥ 2307)

@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

03 Feb, 03:29


▪️ልክ እንደመንገደኛ

🔻ከኢብኑዑመር - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዓለይሂወሰለም - በትከሻዬ ያዙኝ እና እንዲህ አሉኝ ፦ " ዱንያ ላይ ልክ እንደእንግዳ ሁን ፤ ወይም ልክ እንደ መንገድ የሚያልፍ ሰው ሁን። " ኢብኑዑመር - ረዲየሏሁዐንሁ - ደግሞ ይህን ይሉ ነበር ባመሸህ ጊዜ ንጋትን አትጠባበቅ ፤ ባነጋህ ጊዜ ደግሞ ምሽትን አትጠባበቅ ፤ ከጤንነትህ ለበሽታህ ያዝ ፤ ከህይወትህ ደግሞ ለሞትህ ያዝ። (ቡኻሪ ዘግቦታል።)

@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

29 Jan, 03:32


▪️ምቀኝነት በ2ነገር

🔻ከዐብዲሏህ ቢን መስዑድ - ረዲየሏሁ ዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዐለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " እንደሱ በሆንኩ ብሎ መመኘት በሁለት ነገሮች እንጂ የለም ፤ (1ኛው) አሏህ ገንዘብ የሰጠው ሆኖ በሐቅ ላይ ገንዘቡን በማጥፋት ላይ ያመቻቸው የሆነ ሰው እና ሌላኛው ደግሞ አሏህ እውቀት የሰጠው ሰው ሆኖ በእውቀቱ ፍርድ ይፈርድበታል እውቀቱንም ያስተምርበታል። " (ሙተፈቁን ዐለይህ)

@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

27 Jan, 03:43


▪️የ2ለ3 ፣ የ3ለ4

🔻ከአቢሁረይራህ - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዐለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " የሁለት ሰው ምግብ ለሶስት ሰው ይበቃል ፤ የሶስት ሰው ምግብ ለአራት ሰው ይበቃል። " (ሙተፈቁን ዐለይህ).

@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

23 Jan, 03:47


▪️በደል እና ስስትን ተጠንቀቁ!

🔻ከጃቢር - ረዲየሏሁዓንሁ - ተይዞ እንደተወራው የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " በደልን ተጠንቀቁ ምክንያቱም በደል የቂያማ ቀን ብዙ ጨለማዎች ነውና። ስስትንም ተጠንቀቁ ምክንያቱም #ስስት ከእናንተ በፊት የነበሩ ህዝቦችን ያጠፋው እሱ ነው ፤ ደሞቻቸውን እንዲያፈሱ እና ክልክል የሆኑ ነገሮችን የተፈቀዱ እንዲያደርጉ አነሳሳቸው። ". (ሙስሊም ፥ 2578 ላይ ዘግቦታል).

@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

22 Jan, 03:50


▪️ትከሻዋ ሲቀር

🔻ከዓኢሻህ - ረዲየሏሁ ዐንሃ - ተይዞ እንደተወራው እነሱ ፍየል አረዱና (ሰደቃ አደረጉ) እና ነብዩ - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - " ከሷ ምኗ ቀረ?" አሉ ፤ (ዓኢሻም) "ትከሻዋ እንጂ ሌላ የቀረ ነገር የለም" አለች ፤ እሳቸውም " ከትከሻዋ ውጭ ሁሉም ቀርቷል " አሏት. (ቲርሚዚይ ፥ 2470 ላይ ዘግበውታል). ቲርሚዚይ ሐዲሱን ሲያብራሩ ነብያችን ከፍየሏ ትከሻዋ ሲቀር ሁሉንም ሰደቃ አወጡ እና ትከሻዋ ሲቀር ሌላው ሰደቃ የወጣው የፍየሏ ክፍል አኺራችን ላይ ቀርቶልናል አሉ።

@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

21 Jan, 03:48


▪️ገንዘብን አይቀንስም

🔻ከአቢሁረይራህ - ረዲየሏሁዓንሁ - ተይዞ እንደተወራው የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዐለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " ሰደቃ ከገንዘብ ምንም አትቀንስም ፤ አሏህ አንድን ባርያ ይቅርታ በማድረጉ ልቅናን እንጂ አይጨምርለትም ፤ አንድ ሰው ለአሏህ ብሎ አይተናነንስም ከፍ ያደረገው ቢሆን እንጂ። ". (ሙስሊም ፥ 2588).

@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

20 Jan, 03:46


▪️ስጥ

🔻ከአቢሁራይራህ - ረዲየሏሁዓንሁ - ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " አሏሁ - ተዓላ - ይህን አለ ፥ የአደም ልጅ ሆይ! ስጥ ይሰጥሃል። "|| (ሙተፈቁን ዐለይህ)

@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

20 Jan, 03:44


▪️ሁለት መላኢካዎች

🔻ከአቢሁራይራህ - ረዲየሏሁዓንሁ - ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " ባርያዎች በውስጡ የሚያነጉበት አንድም ቀን የለም ሁለት መላኢካዎች የሚወርዱ ቢሆኑ እንጅ ፤ አንድኛው እንዲህ ይላል ፡ አሏህ ሆይ! የሚሰጥን ሰው ምትክን ስጠው ፤ ሌላኛው ደግሞ እንዲህ ይላል ፡ ለሚይዝ ሰው ጥፋትን ስጠው። " (ሙተፈቁን ዐለይህ).

@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

20 Jan, 03:34


▪️የቴምር ቁራጭ

🔻ከዐዲይ ቢን ሓቲም - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " እሳትን በቴምር ግማሽ ቢሆን እንኳ ተጠንቀቁ! ". (ሙተፈቁን ዐለይህ)

@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

20 Jan, 03:28


▪️ያንተ ገንዘብ

🔻ከዐብደሏህ ቢን መስዑድ - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " ከእናንተ ውስጥ የወራሾቹ ገንዘብ ከራሱ ገንዘብ ይልቅ ተወዳጅ የሆነ ማነው? ". የአሏህ መልእክተኛ ሆይ! ገንዘቡ ተወዳጅ የሆነ እንጂ ከኛ ውስጥ ማንም የለም አልናቸው። እሳቸውም እንዲህ አሉ ፦ " የሱ ገንዘብ ማለት (ሰደቃ ሰጥቶ) ያስቀደመው ነው ፤ የወራሾቹ ገንዘብ ደግሞ ያቆየው(የተውከው) ነው። ". (ቡኻሪ ፥ 6442 ላይ ዘግቦታል)

@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

15 Jan, 04:02


ትክክለኛ ሚስኪን ማለት

🔻ከአቢሁረይራህ - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ |" በሰዎች ዘንድ እየዞረ አንድ ወይም ሁለት ጉርሻ የሚመልሰው ሰው እንዲሁም አንድ ወይም ሁለት ቴምር የሚመልሰው ሰው ሚስኪን አይደለም ፤ ሚስኪን ማለት ፍላጎቱን የሚዘጋለት የሚያብቃቃውን ነገር የማያገኝ ነው ፤ ሰዎች ለሱ ሰደቃ እንዳያደርጉለት ደግሞ ስለሁኔታው አያውቁም ፤ ሰዎችን ለመለመንም አይቆምም። "| (ሙተፈቁን ዐለይህ)

@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

15 Jan, 03:26


▪️እሳትን ነው ሚጠይቀው

🔻ከአቢሁረይራህ - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ |" ገንዘብን ለማብዛት ብሎ ሰዎችን የለመነ ሰው የሚጠይቀው የእሳት ፍም ነው ፤ ያሳንስ ወይም ያብዛ። "| (ሙስሊም ዘግቦታል).

@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

14 Jan, 04:40


▪️የተብቃቃ ያብቃቃዋል

🔻ከሐኪም ቢን ሒዛም - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው ነብዩ - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " የላይኛው(ሰደቃ ሰጪ) እጅ ከታችኛው(ከሰደቃ ተቀባይ) እጅ በላጭ ነው ፤ ሰደቃን ከቅርብ ቤተሰብ ጀምር ፤ ከሰደቃ በላጩ ለራስህና ለቤተሰብህ ከተረፈ ከተብቃቃህ በኋላ የምትሰጠው ነው ፤ የተቆጠበ አሏህ ይቆጥበዋል ፤ የተብቃቃ አሏህ ያብቃቃዋል። " (ሙተፈቁን ዐለይህ)

@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

06 Jan, 03:38


▪️ዱንያ እንደተሰበሰበችለት

🔻ከዑበይዲሏህ ቢን ሚሕሰን አልአንሷሪይ አልኸጥሚይ - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ ፦ " ከእናንተ ውስጥ በነፍሱ/በቤተሰቡ ሰላም ሆኖ ያነጋ ፣ በሰውነቱ ጤናማ ከሆነ ፣ እሱ ዘንድ የቀኑ ምግብ ካለው ዱንያ በአጠቃላይ እንደተሰበሰበችለት ይቆጠራል። " (ቲርሚዚይ ፥ 2346 ላይ ዘግበውታል ፤ አልባኒይ ሶሒሑልጃሚዕ ፥ 6042 ላይ ሐሰን ብለውታል)

@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

19 Dec, 03:43


▪️ሰሌን ላይ!

🔻ከአብደሏህ ቢን መስዑድ - ረዲየሏሁዓንሁ ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም - ሰሌን ላይ ተኙና ጀርባቸው ላይ የሰሌኑ ፋና እየታየ ተነሱ ፤ እኛም የአሏህ መልእክተኛ ሆይ! የተመቸ ምንጣፍ ብናዘጋጅሎትስ አልናቸው እሳቸውም እንዲህ አሉ ፦ " እኔና ዱንያ ምን አገናኘን ፤ እኔኮ ዱንያ ውስጥ ልክ ዛፍ ስር እንደተጠለለና ትቷት እንደሄደ መንገደኛ እንጂ ሌላ አይደለሁም " (ቲርሚዚይ ፥ 2377).

@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

19 Dec, 03:18


▪️ገንዘቤ!

🔻ከዐብደሏህ ኢብኒሽሺኪኪር - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ ፡ ነብያችንን - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - { ألهاكم التكاثر } እየቀሩ ወደነሱ መጣው እናም እንዲህ አሉ ፦ " የአደም ልጅ ንብረቴ ንብረቴ ይላል ፤ አንተ የአደም ልጅ ሆይ! ከንብረትህ በልተሀው ያጠፋሀው ወይም ለብሰህ ያበሰበስከው ወይም ደግሞ ሰደቃ አውጥተህ ለአኺራህ ያሳለፍከው ካልሆነ በስተቀር ምን ንብረት አለህ? " (ሙስሊም ዘግቦታል).

@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

17 Dec, 03:23


▪️ዱንያ!!

🔻ከአቢዘር - ረዲየሏሁዓንሁ ተይዞ እንደተወራው ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " ዱንያ የሙእሚን እስር ቤት ነው ፤ የካ*ፊ*ር ደግሞ ጀነት ነው። " (ሙስሊም ዘግቦታል).

@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

17 Dec, 03:12


▪️የበላያችሁን አትመልከቱ!!

🔻ከአቢዘር - ረዲየሏሁዓንሁ ተይዞ እንደተወራው ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " ከናንተ የበታች ወደሆኑት ተመልከቱ ፤ ከናንተ የበላይ ወደሆነ አካል አትመልከቱ ፤ ይህ አሏህ በናንተ ላይ የዋለውን ፀጋ እንዳታሳንሱ የተገባ ነው። " (ሙስሊም)

@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

12 Dec, 03:33


▪️ዱንያ ላይ በጣም ችግርተኛ የነበረ ሌላው ደግሞ በጣም ባለፀጋ የነበረ

🔻ከአነስ ቢን ማሊክ - ረዲየሏሁዓንሁ ተይዞ እንደተወራው ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " የቂያማ ቀን ከእሳት ሰዎች ውስጥ ዱንያ ላይ በጣም ባለፀጋ የነበረ ሰው እንዲመጣ ይደረጋል ከዛም እሳት ውስጥ አንዲትን መነከርን ይነከራል ፤ ከዛም አንተ የአደም ልጅ ሆይ! በእድሜህ መልካም ነገር አይተህ ታውቃለህን? በእድሜህ ፀጋ አልፎብህ ያውቃልን? ወላሂ ጌታዬ ሆይ አላየሁም ይላል ፤ ከጀነት ሰዎች ውስጥ ደግሞ በዱንያ ላይ በጣም ችግርተኛ የሆነ ሰው እንዲመጣ ይደረግና ጀነት ውስጥ አንዲት መነከርን ይነከራል ፤ ከዛም አንተ የአደም ልጅ ሆይ! በእድሜህ ችግርን አይተህ ታውቃለህን? በእድሜህ መከራን አልፎብህ ያውቃልን? አይ ወላሂ ምንም ችግር አልፎብኝ አያውቅም ፤ ምንም አይነት መከራንም አይቼ አላውቅም። ይላል። " (ሙስሊም ዘግቦታል)

@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

12 Dec, 03:16


▪️ሟችን 3ነገሮች ይከተሉታል

🔻ከአነስ ቢን ማሊክ - ረዲየሏሁዓንሁ ተይዞ እንደተወራው ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " የሞተን አካል ሶስት ነገሮች ይከተሉታል። ቤተሰቡ ፣ ንብረቱና ስራው ፤ ሁለቱ ይመለሱና አንዱ ብቻ ይቀራል ፤ ቤተሰቡና ንብረቱ ይመለሳሉ ፤ ስራው ይቀራል። " (ሙተፈቁን ዐለይህ)

@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

12 Dec, 03:05


▪️ዱንያና ሴትን ተጠንቀቁ!!

🔻ከአቢሰዒድ አልኹድሪይ - ረዲየሏሁዓንሁ ተይዞ እንደተወራው ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " ዱንያ ጣፋጭ እና አረንጓዴ ናት። አሏህን በሷ ላይ ተክቷችኋል እናም ምን እንደንትሰሩ ይመለከታል ፤ ዱንያን ተጠንቀቁ ፣ ሴትንም ተጠንቀቁ። " (ሙስሊም ዘግቦታል)

@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

09 Dec, 03:17


▪️እኔ ማውቀውን ብታውቁ

🔻ከአነስ - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ ፦ | የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - የሷን አምሳያ ኹጥባ ሰምቼ ማላውቀውን አይነት ኹጥባ አደረጉ እናም ይህን አሉ ፦ " እኔ ማውቀውን ብታውቁ ኖሮ ጥቂትን ስቃችሁ ብዙን ባለቀሳችሁ ነበር። " አነስም እንዲህ አለ ፡ የረሱሉሏህ ሶሓባዎች የለቅሶ ድምፅ ያላቸው ሲሆኑ ፊቶቻቸውን ሸፈኑ። |. (ሙተፈቁን ዐለይህ)

@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

05 Dec, 03:25


▪️#ጀናዛ_በተቀመጠች_ጊዜ

🔻ከአቢ ሰዒዲኒል ኹድሪይ - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዐለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " ጀናዛን ባስቀመጧት እና ወንዶች በትከሻቸው ላይ በተሸከሟት ጊዜ ፤ መልካም ከሆነች አስቀድሙኝ አስቀድሙኝ ትላለች ፤ መልካም ያልሆነች ከሆነች ዋይ ጥፋቴ! ወዴት ነው ይዛችሁኝ ምትሄዱት? ትላለች ፤ ድምፁዋን የሰው ልጅ ሲቀር ሁሉም ነገር ይሰሙታል ፤ የሰው ልጅ ቢሰማው ኖሮ በድንጋጤ ይወድቅ ነበር። " (ቡኻሪ ፥ 1314 ላይ ዘግቦታል)

@t.me/ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

22 Oct, 05:46


🔻በመጀመርያ መርካቶ በነበረው የእሳት አደጋ ንብረታችሁን ላጣችሁ ወንድሞቻችን አሏህ በተሻለ ይተካችሁ። ሶብሩንም ይስጣችሁ።

🔻በመቀጠል መርካቶም ሆነ ሌላም የንግድ ቦታዎች ላይ ያለን ሰዎች የትናንቱ እሳት ካለንበት የማጭበርበር ወንጀል ወደአሏህ እንድንመለስ ማንቅያ ደውል ነው። ሰዎችን ሸውደን ያልሆነ እቃ ሽጠን ምናካብተው ሀብት በደቂቃ እንደሚጠፋ ማሳያ ነው። ወደአሏህ እንመለስ!

@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

19 Oct, 17:47


በወለድ ብድር ሚያበድሩ እና ከሚበደሩ እንደምሳሌ ቴሌን ከመሰሉ ድርጅቶች አክስዮን መግዛት ክልክል ነው።
ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ
ለበለጠ ፦ https://t.me/ustazilyas/1279

Ibn Yahya Ahmed

19 Sep, 08:12


▪️የዒባዳ መሰረቶች

🔻አሏህን የምናመልከው ስለምንወደው ፤ ጀነትን ስለምንከጅል እና ቅጣቱንም ስለምንፈራ ነው። ሶስቱ የዒባዳ መሰረቶች ይባላሉ። ከሶስቱ አንዱ መጉደል የለበትም።
@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

17 Sep, 06:50


▪️ለአሏህ መተናነስ

🔻ለአሏህ የተናነሰ አሏህ ከፍ ያደርገዋል። የአሏህ መልእክተኛ ﷺ ይህን ብለዋል ፦ [ አንድም ሰው ለአሏህ አይተናነስም አሏህ ከፍ ቢያደርገው እንጂ ] ሙስሊም ዘግቦታል።
@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

14 Sep, 06:17


▪️እውነት ይህ አንቀጵ መውሊድን ለማክበር ማስረጃ ይሆናልን?

{ َقُلْ بِفَضْلَِّ لله وَبِرَحْمَتِهِ فَبِذَٰلِكَ فَلْيَفْرَحُوا هُوَخَيْرٌمِّمَّا يَجْمَعُون }
[| «በአላህ ችሮታና #በእዝነቱ (ይደሰቱ)፡፡ በዚህም ምክንያት ይደሰቱ፡፡ እርሱ ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ነው» በላቸው፡፡ |] (ዩኑስ ፥ 58).
°
🔻በዚህ አንቀጽላይ እዝነቱ ማለት ሙሐመድ - صلى الله عليه وسلم - ናቸው እና በሳቸው እንደሰታለን። ይላሉ ፡ ለዚህ የሚሰጠው መልስ በሁለት መልኩ ነው ፦
°
🔻1ኛ. ቁርአኑ ላይ እዝነቱ የተባለው እንደአብዛኛዎቹ የተፍሲር ሊቃዎንቶች ገለፃ ቁርአን ወይም እስልምና ነው እንጂ ሙሐመድ - صلى الله عليه وسلم - አይደሉም። እንደምሳሌ ተፍሲር አጥ-ጦበሪ , ቁርጡቢ , በገዊ, ኢብኑ- ከሲር, ተፍሲር አስ-ሰዕዲ እና ሌሎችንም መመልከት ይችላል።
°
🔻ቁርአን ወይም እስልምና ተብሎ ለመተርጎሙ ደግሞ ከበፊቱ ያለውን አንቀጽ ስንመለከት የበለጠ ግልፅ ይሆንልናል። አንቀጹ እንዲህ ይላል ፦
يَا أَيُّهَا النَّاسُ قَدْجَاءَتْكُم مَّوْعِظَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ وَشِفَاءٌلِّمَا فِي الصُّدُورِوَهُدًى وَرَحْمَةٌ }
{ َلِّلْمُؤْمِنِين
[| እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ግሳጼ በደረቶች ውስጥም ላለው (የመጠራጠር በሽታ) መድኃኒት ለምእምናንም ብርሃንና #እዝነት በእርግጥ መጣችላችሁ፡፡ |] (ዩኑስ ፥ 57). ስለዚህ አንቀጹ እያወራ ያለው ስለቁርአን ነው ማለት ነው።
°
🔻2ኛ.እንደእነሱ አባባል ሙሐመድ - صلى الله عليه وسلم - ናቸው ብንል ታዲያ ይሄ እንዴት ብሎ ነው በአመት አንድ ጊዜ የተወለዱበትን ቀን ጠብቃችሁ, ተሰባስባችሁ, ምግብ እያበላችሁ አክብሩት እና አሳልፉት ለማለት ማስረጃ የሚሆነው? የተወለዱበትን ቀን ብቻ ገድቦ አመት ጠብቆ መደሰት ከየት የመጣ ነው?? አንዳንዶች መውሊድን ያዘዘን አሏህ ነው ብለውም በድፍረት ሚናገሩና በአሏህ ላይ ሚቀጥፉ አሉ .. ይህ በጣም ስህተት ነውና ልንጠቀቅ ይገባናል። .

✍️አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ @ Ibn yahya Ahmed
ሶፈር 29/1440ሂ. # ጥቅምት 28/2011. ላይ የተፃፈ
https://t.me/ibnyahya7

Ibn Yahya Ahmed

12 Sep, 15:12


🔻አንዳንዶች ራሳቸውን ገለልተኛ ለማድረግ ከሚጠቀሙበት ዘዴያቸው ውስጥ ቅርንጫፋዊ ነጥቦች ላይ አትከራከሩ የሚለው ማምታቻ ነው።ከዛ ኺላፍ አለበት ብለው ሚያስቡትን ነጥብበሙሉ ቅርንጫፍ ውስጥ ይከቱትና ዝምጭጭ!!
@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

10 Sep, 11:53


▪️ቢድዓ ለሁለት ይከፈላል የሚሉ ሰዎች ሚያመጧቸው ማምታቻዎች እና ምላሹ የመጨረሻው ክፍል 4.

🔻#አራተኛ_ማምታቻ ፡ በሶሓባዎች ጊዜ እና ከዛም በኋላ የተሰሩ አንዳንድ ነገሮችን እያመጡ ለምሳሌ ቁርአን መሰብሰብ ፤ መርከዝ ማቋቋም ፤ ትምርህርቶችን በየዘርፉ ከፋፍሎ ማስተማርን የመሰሉ ስራዎችን እነዚህ መልካም ቢድዓ ስለሆኑ እኛም አዲስ ቢድዓ ማምጣት እንችላለን የሚል ነው።
°
🔻ለዚህ የሚሰጠው መልስ ቁርአንን መሰብሰብ እና ሌሎች ከላይ የተጠቀሱ ነገሮች ከመሷሊሕ አልሙርሰላህ ውስጥ እንጂ ከቢድዓ ውስጥ አይካተቱም የሚል ነው። ይህንንም ለመረዳት እንዲያስችለን የመሷሊሕ አልሙርሰላህን ትርጉም እንደዚሁም በቢድዓ እና በመሷሊሕ አልሙርሰላህ መካከል ያለውን ልይኑት መመልከት ያስፈልጋል።
°
🔻#መሷሊሕ_አልሙርሰላህ ማለት ፡ ግልፅ በሆነ መልኩ በዝርዝር የሚደግፈው መረጃ ባይኖርም ጥቅል የሆኑ የሸሪዓ ህግጋት እና መርሆዎች ውስጥ ሊከታት የሚችል ፤ እናም #እንደመረማመጃ_እና_መዳረሻ_ተደርጎ_የሚወሰድ_ተግባር ነው። ይህም ሸሪዓህ የሚያሟላቸው እና የሸሪዓ ህግጋት እንዲደነገጉ ምክንያት የሆኑትን አላማዎች የሚያሟላ መዳረሻ ነው። ቢድዓ ማለት ግን ከዚህ ቀደም እንዳየነው ቁርአናዊም ሆነ ሐዲሳዊ ወይም በእስልምና ቦታ ካላቸው እንደኢጅማዕ አይነት ማስረጃዎች ውስጥ አንዱ የማይደግፉት #የዲን_ተደርጎ_የሚታሰብ ተግባር ወይም እምነት ነው።
°
🔻የሁለቱን ልይኑቶች ግልፅ ለማድረግ ያክል ፦
1..#ቢድዓ_በራሱ "መቅሱድ" ነው ፤ ማለትም ለራሱ ተብሎ የሚሰራ ነገር ነው። አንድ ሰው ቢድዓ ሲሰራ ለራስነቱ አስቦ, ዒባዳ ነው, ወደአላህ እቃረብበታለሁ ብሎ ነው የሚሰራው ; #መሷሊሕ_ግን_ለራስነቱ_ታስቦ_አይደለም_የሚሰራው ፤ ማለትም የሚገባው መዳረሻ ቦታዎች ላይ ነው እንጂ "መቃሲድ" ወይም ዋና አላማ ላይ አይደለም ማለት ነው።
°
🔻ለምሳሌ ማይክራፎንን ብንወስድ ሩቅ ያሉ ሰዎች እንዲያዳምጡበት የተሰራ ነገር ነው ፤ እኛም የምንጠቀምበት ለዚህ አላማ ነው እንጂ በራስነቱ ማይክራፎንን መጠቀም ዒባዳ ነው ብለን አይደለም። "መቅሱዱ" የተፈለገው ራሱ ማይክራፎኑ ላይ አይደለም ማለት ነው።
°
2..#ቢድዓ_የሚካተተው_ዒባዳ_ተብለው_ወደሚሰሩ_ዘርፎች_ውስጥ_ነው ፤ ዒባዳ ላይ ደግሞ በመሰረቱ
#የሚሰራበት_ምክንያት_አይታወቅም ፤ ማለትም ለምን ይሄ ነገር ሆነብለህ ብትጠይቅ ከበስተኋላው ያለውን ምክንያት አታውቅም ፤ ለምሳሌ ለምን ዙህር 4ረከዓ ሆነ ፣ ለምን ጀናባ ስሆን ሙሉ ሰውነቴንእታጠባለሁ ፣ ለምን መግሪብ ላይ ይጮሃል? ዙህርስ ላይ አይጮህም .. የመሳሰሉት ነገሮች ግልፅ የሆነ ምክንያታቸው አያታወቅም።

🔻#መሳሊሕ_ግን_ምክንያትነቱ_ለምን_እንደሆነ_በግልፅ_የሚታወቅ_ነገር_ነው ፤ ምክንያቱም መዳረሻ ስለሆነ ማለት ነው። ለምሳሌ ቁርአንን መሰብሰብ ብናይ ምክንያቱ የታወቀ ነው ፤ እሱም ቁርአን እንዳይጠፋ ነው። እንደዚሁ ትምህርቶችን በየዘርፉ እየከፋፈሉ ማስቀመጥ ፤ ማለትም ኡስሉልፊቅህ , ነሕው ምናምን እያሉ ከፋፍሎ ማስቀመጥ አላማው የታወቀ ነው ፤ ቀለል ተደርጎ ሰዎች እንዲገባቸው ነው ፤ እንጂ በራሱ መከፋፈሉ ዒባዳ ነው ተብሎ አይደለም የሚሰራው።

🔻እንደዚሁም መርከዝ ማቋቋም, ወይም በየጊዜው እየገደቡ ለምሳሌ በ4አመት ጃሚዓ ላይ ማስተማር .. እና የመሳሰሉት ምክንያትነታቸውይሄ ነው ተብሎ በግልፅ ይነገራል ፤ ማለትም ሰዎች ት/ቱን በ4አመት ውስጥ ይጨርሱታል ስለዚህም ተማሪዎቹ እንዲቀላቸው እና እንዲገባቸው ይሆናል, ምናምን ተብሎ ምክንያቱ በግልፅ ይታወቃል ፤ ከቢድዓ በተቃራኒ ማለት ነው። #ቢድዓ_ግን_ምክንያትነቱ_አያታወቅም።
°
3..#ቢድዓ_ሁልጊዜ_ሰዎች_ላይ_ጫና_ነው_የሚፈጥረው ምክንያቱም ያልታዘዙትን መስራት ስለሆነ ማለት ነው ;#መሳሊሕ_ግን_ከሰዎች_ላይ_ጫናን_ያቀላል ፤ ምክንያቱም ነገራቶችን ያቃልላል, ያልተመቻቹ ወይንም_መሷሊሕ_የሚባለው_ምክንያቱ_ኖሮ_ከመስራት_የሚከልክላቸው_ነገር_የተገኘበት_ነገር_ሊሆን_ይችላል። ለምሳሌ ቁርአን በዛ ጊዜ ይሰብሰብ ከተባለ ገና ወሕይ እየወረደ ስለሆነ ያለው አዲስ አንቀጽ ወይም ምዕራፍ በሚመጣ ሰአት እሱን ማስገባት, ሌላውም ሲወርድ እሱንም ማስገባት ችግር ይፈጠራል። ስለዚህ ከልካይ ነገር ሥለነበረ ሳይሰበስብ ቀርቷል። ነገር ግን ከሳቸው ሞት በኋላ እንዳይሰበሰብ ያገደው ከልካይ ነገር ስለተወገደ ሊሰበስብ ችሏል።ስለዚህ ቁርአን መሰብሰ መሷሊሕ አልሙርሰላህ ውስጥ እንጂ ቢድዓ ውስጥ አይካተትም ማለት ነው።.
°
🔻በመሆኑም እስካሁን ድረስ እንደተመለከትነው የቢድዓ መልካም የለውም። ቢድዓ ሁሉም ጥሜት ነው ፤ ይህንንም በደንብ ተገንዝበንዒባዳችን አላህ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ለአላህ ብቻ ጥርት አድርገን እና መልእክተኛውን - صلى الله عليه وسلم - ሳንጨምር እና ሳንቀንስ በመታዘዝመስራት ይኖርብናል።
____
✍️አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ @ Ibn yahya Ahmed
ሰኞ ሶፈር 27/1440ሂ. # ጥቅምት 26/2011.ላይ የተፃፈ
https://telegram.me/ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

09 Sep, 05:03


▪️ቢድዓ ለሁለት ይከፈላል የሚሉ ሰዎች ሚያመጧቸው ማምታቻዎች እና ምላሹ ክፍል 3.

🔻#ሶስተኛው_ማምታቻ ፡ كل بدعة ضلالة" የሚለው ሐዲስ ላይ "كل" የምትለዋ ቃል ሁሉም ማለትን አትጠቅምም ፤ ለዚህም ቁርአን ውስጥለምሳሌ አላህ የሑድ ህዝቦችን ለማጥፋት የተላከችውን ንፋስ
በጌታዋ ትዕዛዝ አንዳቹን ሁሉ ] { تُدَمِّرُكُلَّ شَيْءٍبِأَمْرِرَبِّهَا } አስመልክቶታጠፋለች ] (አሕቃፍ ፥ 25) ብሏል ፤ ነገር ግን ሁሉም ነገሮች አልጠፉም ፤ እናም "كل" የሚለው ቃል ሁሉንም የሚለውን ስለማያመላክት ሐዲሱ ላይ ሁሉም ቢድዓ ጥሜት ነው ተብሎ አይተረጎምም ፤ ስለዚህ መልካም እና መጥፎ ቢድዓ አለ በማለት መከራከሪያ ያቀርባሉ።
°
🔻ለዚህ ማምታቻ በአራት መልኩ መልስ መስጠት ይቻላል ፦
1⃣ኛ."كل" የሚለው ቃል ሁሉን አካታች መሆኑን ያስጠቅማል። ይህንንም ከተናገሩ ዑለማዎች ውስጥ እንደምሳሌ አስነዊ (አት-ተምሂድ ሊልአስነዊ ፥ 302) ላይ የጠቀሱትን ንግግር መመላከት ይቻላል። ፤ ነገር ግን ይህን ቃል ሁሉን ነገር ለማለት እንዳያመላክት የሚገድበው ነገር ከተገኘ በዛ ነገር ይገደባል። በቁርአን ውስጥም ሆነ በሐዲስ ላይ "كل" የሚለውን ቃል ሌላ ነገር የሚገድበው መልእክት እስካልመጣ ድረስ በዛው ሁሉን ነገር ለማለት ነው የሚጠቁመው።
°
2⃣ኛ.ነብዩ - صلى الله عليه وسلم - በሐዲሳቸው ላይ "كل بدعة ضلالة " [ ቢድዓ ሁሉ ጥሜት ነው ] በማለት የተናገሩትን ጠቅላይ የሆነን ንግግር ጠቅላይነቱን የሚገድበው ሌላ ንግግር ስላልመጣ በዛው በጠቅላይነቱ ነው የሚተረጎመው። ይህን አስመልክቶ (አሪ-ረሳለቱ - ሻፍዒያ ፥ 295) ላይ የኢማሙ ሻፊዒይን ንግግር ይመልከቱ።
°
3⃣ኛ. ይህ ሐዲስ ሁሉንም ቢድዓ ለማለት እንደተፈለገበት ደግሞ የሚያመላክቱ ነጥቦች አሉ ፦ ከነዚህም ውስጥ ፡ 1.ነብዩ - صلى الله عليه وسلم - በተደጋጋሚ በየጁሙዓ ኹጥባቸው ላይ ሳይገድቡ መናገራቸው ፤ 2. ከሱ ቀጥለው [ ሁሉም ጥሜት እሳት ውስጥ ነው ] በማለትማጠናከራቸው ፤ 3.በተጨማሪም "كل" የምትለዋ ቃል በ"ነኪራ" ወይም ያልታወቀ ስም ላይ ስትገባ ጠቅላይነትን እንደምታመላክትሁሉም የኡሱሉል-ፊቅህ ሊቃውንት መስማመታቸው ነው(ሸርሕ ከዋኪቡል ሙኒር ፥ 3/123-125 * በሕሩል ሙሒጥ ፥ 4/84). ላይ ይመልከቱ። ስለዚህ ሐዲሱ ላይ ቢድዓ ሁሉም ጥሜት እንደሆነ
ይጠቁመናል።
°
⃣4ኛ.ቁርአኑ ላይ ሁሉንም ታጠፋለች የተባለችው ንፋስ ሁሉንም አላጠፋችም ለሚለው ሐሳብ የሚሰጠው መልስ ሁለት አይነት ነው ፡
1.ንፋሷ ሁሉንም ነገር አጥፍታለች ፤ ነገር ግን ያጠፋችው እንድታጠፋ የታዘዘችበትን ሁሉንም ነገር ነው። የቁርአኑ ትርጉም ለማጥፋት በታዘዝችበት ሁሉንም ነገር ታጠፋለች ለማለት እንደሆነ የተፍሲሮችኢማም የሆኑት አብኑ ጀሪር አጥ-ጦበሪ ተፍሲራቸው (26/27) ላይ ተናግረዋል።
°
🔻የታዘዘችበትን ነገር በሙሉ አጥፍታለች ተብሎ እንዲተረጎም ያደረገው ደግሞ አመላካች ነገር ስላለ ነው። አመላካች ነገሩንም አሏሁ - ተዓላ - በሌላም አንቀጽ ላይ እንዲህ ሲል ይገልፃል ፦
{َِمَا تَذَرُمِن شَيْءٍأَتَتْ عَلَيْهِ إِلاَّجَعَلَتْهُ كَالرَّمِيم }
°
[| በላዩ ላይ #የመጣችበትን_ማንኛውንም_ነገር እንደ በሰበሰ አጥንትያደረገችው ብትሆን እንጂ አትተወውም፡፡ |] (አዝ-ዛሪያት ፥ 42). ስለዚህ "كل" የሚለው ቃል ጠቅላይነቱን ይዞ ይተረጎማል ማለት ነው። 2.ወይም ደግሞ "كل" የሚለው ቃል የሚገድበው ነገር ከመጣ ተገድቦይተረጎማል ባልነው መሰረት ከሆነ እዚህም አንቀጽ ላይ ተገድቦሊተረጎም ይችላል። ምክንያቱም እዛው አንቀጽ ላይ መገደቡን የሚያመላክት ቃል ስላለ ማለት ነው ፡ እሱም
{ .. ْۚفَأَصْبَحُوا لاَيُرَى إِلاَّمَسَاكِنُهُم ..}
[| .. #ከመኖሪያዎቻቸውም_በስተቀር ምንም የማይታዩ ሆኑ፡፡ .. |] (አሕቃፍ ፥ 25).
°
🔻አሏሁ - ተዓላ - ሁሉንም ነገር ታጠፋለች ብሎ እዛው ቀጥሎ ከመኖሪያዎቻቸውም በስተቀር በማለት መኖሪያዎቻቸው እንዳልጠፉ ተናግሯል። ስለዚህ "كل" የሚለው ቃል የሚገድበው ነገር ስለመጣ ተገድቦ ይተረጎማል ማለት ነው።
°
🔻ሌሎች የቁርአን አንቀጾች እና ሒዲሶች ላይም እንደዚሁ "كل" የሚለው ቃል ከጠቅላይነቱ እንዲገደብ የሚያደርገው "ቀራኢን" ወይም አመላካች ነገር ከመጣ በዛ ምክንያት ተገድቦ ይተረጎማል ፤ ካልሆነ ግን ጠቅላይነቱን ይዞ ይተረጎማል። ሐዲሱ ላይ ግን ከላይ እንዳየነው "كل" የሚለው ቃል የሚገድበው ነገር ምንም ስለሌለ ሁሉም ቢድዓ ተብሎ ነው የሚተረጎመው ማለት ነው። በመሆኑም ይህን እና መሰል ማስረጃዋች ላይ ተመርኩዘው የሚያመጧቸው ማምታቻዎች ላይመልስ መስጠት ይቻላል። ነገር ግን ፅሑፉ እንዳይረዝም ሲባል በዚሁእንብቃቃለን።
____
✍️አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ @ Ibn yahya Ahmed
ሰኞ ሶፈር 27/1440ሂ. # ጥቅምት 26/2011.ላይ የተፃፈ.
https://telegram.me/ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

09 Sep, 00:49


ለኡዱሂያ እርድ የተቀመጡ የተለያዩ መስፈርቶች ለዐቂቃ እርድ (ከልጆች መወለድ ጋር ተያይዞ የተደነገገ እርድ) ላይ ግን አይደነገጉም።

ለምሳሌ
1) የኡዱሂያን እርድ ስጋውን ለራስ መመገብ፣ ማስቀመጥና ለሚስኪኖች መስጠት ያስፈልጋል። ዐቂቃ ላይ ግን ሙሉ ስጋውን ለራስ ብቻ መመገብ ወይም ሙሉ ስጋውን ለሚስኪኖች ብቻ ማከፋፈል ይቻላል።

2) የኡዱሂያ እርድ የበግና የፈየሏን እድሜ በተመለከተ የተቀመጠ ወሳኝ ገደብ አለ። ለዐቂቃ ግን መታረድ የሚችሉን በየትኛውም እድሜ ላይ ያሉ በጎችንና ፍየሎችን ማረድ ይቻላል።

4) ለኡዱሂያ እርድ የሚቀርቡ እንስሳቶች ከተወሰኑ እንከኖች የነጹ መሆን አለባቸው። ለምሳሌ ግልጽ የማየት ችግር፣ ግልጽ ሽባነት፣ ግልጽ ስብራት እና ግልጽ የሆነ ህመም ያለባቸውን እንስሳት ለኡዱሂያ ማረድ አይቻልም። ለዐቂቃ ግን ይቻላል።

5) የኡዱሂያ እርድ ከፍየል፣ ከበግ፣ ከከብትና ከግመል መሆን ይችላል። የዐቂቃ እርድ ግን ከፍየልና ከበግ ዉጭ ማረድ አይቻል።

6) የኡዱሂያን እርድ በጥቂት ቀናቶች ውስጥ ብቻ ነው ማረድ የሚቻለው። በዒደል አድሃና ቀጣይ ባሉት ሶስት የአያመ ተሽሪቅ ቀናት ብቻ ነው ማረድ የሚቻለው። የዐቂቃ ግን በተወለደ በ7ኛው ቢሆን ሱንና ነው። ይህ ካልተሳካ በ14ኛው ይህም ካልተሳካ በ21ኛው ቀን መታረዱን የሚያበረታቱ የቀደምት አበዎች አስተያየት አለ። በእነዚህ ቀናት ካልተሳካም በየትኛውም በተመቸን ቀንና ጊዜ ዐቂቃን ማውጣት ይቻላል። ከ7ኛው ቀን በፊትም ከ21ኛው ቀን በኋላም በእነዚህ ቀናቶች መካከልም ዐቂቃን ማውጣት ይቻላል።

#ዱረሩል_አልባኒይ

T.me/telkhis

Ibn Yahya Ahmed

08 Sep, 10:31


በፊት በጠንካራ አቋማቸው ምናውቃቸው ኡስታዞች አሁን በከፍተኛ መጅሊስ አመራር ላይ ሆነው ስለመውሊድ ሚያወሩትን ስንሰማ ጌታዬ ሆይ ፈተናዬን በዲኔ ላይ አታድርግብኝ ሚለውን ዱዓ እንድናበዛ ያስታውሰናል።
@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

08 Sep, 05:50


▪️ቢድዓ ለሁለት ይከፈላል የሚሉ ሰዎች ማምታቻቸው እና ምላሹ ክፍል 2.

🔻#ሁለተኛው_ማምታቻ ፡ ዑመር ኢብኑል ኸጣብ - ረዲየሏሁ ዐንሁ - ለተራዊሕ ሶላት ሰዎችን በአንድ ላይ ሰብስቦ 11 ረከዓ እንዲሰገድ ካደረገ በኋላ በዚህ ምክንያት "هذه البدعة نعمة" / | ምነኛ ያማረች ቢድዓ ነች | (ቡኻሪ ፥ 2012 / ሙስሊም ፥ 761) ብሎ ተናግሯል ፤ ስለዚህ ቢድዓ ሁሉም መጥፎ ነው ከተባለ ለምን ዑመር አዲስ ቢድዓ ፈጥሮ ያንንም ቢድዓ መልካም አለው? የሚል ነው.
°
🔻ለዚህ የሚሰጠው መልስ ዑመር - ረዲሏሁ ዐንሁ - ሰዎችን በአንድ ኢማም በጀመዓ እንዲሰግዱ ማድረጉ አዲስ ቢድዓ ፈጠረ አያስብለውም። ምክንያቱም ይህ ተግባር ማለትም የተራዊሕን ሶላት በጀማዓ መስገድ ሱና እንጂ ቢድዓ አይደለም። መጀመሪያ የጀመሩትም ረሱል - صلى الله عليه وسلم - ናቸው። እሳቸው ሲሰግዱ የመጀመሪያ ቀን ሶሓቦች ተከትለው ሰገዱ ፤ ተከትለዋቸው ሲሰግዱም ዝም አሉ ፤ በቀጣዩም ቀን ቁጥራቸው በዛ ብሎ መጡ እና ተከትለዋቸው ሰገዱ ፤ በሶሥተኛው ወይ በአራተኛው ቀን ላይ ሶሓቦች እንደልማዳቸው የተራዊሕን ሶላት ከነብዩ - صلى الله عليه وسلم - ጋር አብረው ለመስገድ ብዙ ሆነው ተሰባስበው ቢጠባበቁ
ነብዩ - صلى الله عليه وسلم - ከቤታቸው ሳይወጡ ቀሩ ፤ በነጋታውም [ እኔ እኮ ማታ የሰራችሁትን አውቄያለሁ ፤ በእናንተ ላይ ግዴታ እንዳይሆንባችሁ ፈርቼ ነው እንጂ ከመውጣት አልከለከለኝም። ] በማለት ነገሯቸው። (ቡኻሪ ፥ 1129 / ሙስሊም ፥ 761).
°
🔻በመሆኑም የተራዊሕ ሶላት በጀመዓ መሰገድ ሱንና እንጂ ቢድዓ አይደለም ፤ ዑመርም ሰዎችን የሰበሰው በሱንና ላይ እንጂ በቢድዓ ላይ አልነበረም። ከዚህም አልፎ ነብዩ - صلى الله عليه وسلم - የተራዊሕን ሶላት በጀመዓ መሰገድ እንደሚቻል የጠቆሙበት ሐዲስም አለ ፦ [ ኢማሙ እስኪንቀሳቀስ ድረስ ከኢማሙ ጋር አብሮት የቆመ ሰው ሌሊቱን ሙሉ እንደቆመ ይፃፍለታል(ይቆጠርለታል)። ]. (አቡዳውድ ፥ 1375 / ቲርሚዚይ ፥ 806 / ኢብኑ ማጀህ ፥ 1327). ሐዲሱ ሶሒሕ ነው። ስለዚህ የተራዊሕን ሶላት በጀመዓ መስገድ ሱንና እንጂ ቢድዓ አይደለም።
°
🔻#ታዲያ_ዑመር_ለምን_ቢድዓ_አለው_ከተባለ. ፦ ዑመርም ምነኛ ያማረች ቢድዓ ነች ሊል የቻለበት ምክንያት ይህ ተግባር ከላይ እንዳየነው ነብዩ - صلى الله عليه وسلم - ጀምረውት በኡመታቸው ላይ ግዴታ እንዳይሆንባቸው ሲሉ ትተውታል ፤ አቡበከርም ሳይሰሩት አልፈዋል ፤ በዚህ መሀል ወደሁለት አመት ያክል ከተቋረጠ በኋላ ተግባሩን እንደአዲስ መመለሳቸውን ሲያዩ ምነኛ ያማረች አዲስ ፈጠራ አሉ እንጂ ዑመር ከራሳቸው የፈጠሩት አዲስ ቢድዓ ኑሮ አይደለም።
°
🔻በመሆኑም አዲስ ፈጠራ ሊሏት የቻለው በዚህ ክፍት ጊዜ ውስጥ ሳትሰራ በመቅረቷ እና አሁን እንደአዲስ በመሰራቷ ነው ማለት ነው። ስለዚህ የዑመርን ንግግር አዲስ ቢድዓ ለመፍጠር ወይም ቢድዓ መልካም እና መጥፎ አለው ብሎ ለመካከፈል ማስረጃ ሊሆን አይችልም።
°
🔻ከላይ እንደተመለከትነው ሁለቱም ማምታቻዎች አዲስ ቢድዓን ለመፍጠር ማስረጃ መሆን አይችሉም። በሚቀጥለው ክፍል ላይ 3ተኛውን ማምታቻ እናያለን።
____
©ዲን መመካከር ነው
____
✍️አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ @ Ibn yahya Ahmed
እሁድ ሶፈር 26/1440ሂ. # ጥቅምት 25/2011. ላይ የተፃፈ
https://telegram.me/ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

07 Sep, 09:26


▪️ተራዊሕ እና ተሀጁድ

🔻ተራዊሕ እና ተሀጁድን አብራችሁ እየሰገዳችሁ ነብዩ - ﷺ - ያልሰሩትን እየሰራችሁ መውሊድን ትቃወማላችሁ ይሉናል። ይህ አባባል ፍፁም ስህተት ነው ምክንያቱም በረመዷን ለሊት ሶላት ማብዛት የተወደደ ተግባር ነው። ለዚህም ማስረጃው ነብዩ - ﷺ - እንዲህ ማለታቸው ነው ፦ [ የረመዷንን ወር በአላህ አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ አገኛለው ብሎ #በመስገድ_የቆመ_ሰው በፊት ያሳለፈው ወንጀሎች ይማሩለታል ] (ሙተፈቁን ዓለይሂ)
°
🔻የረመዷንን ወር መቆም የመጀመሪያውን ሌሊትም የመጨረሻውንም ሌሊት ያካትታል። ተራዊሕንም ተሐጁንም መስገድ ችግር እንደሌለው ከዚህ ሐዲስ እንረዳለን። ሱና ማለት ደግሞ ነብያችን - ﷺ - የተገበሩት ብቻ ሳይሆን በንግግራቸው የገለፁትም ጭምር ነው። በተግባር ባይሰሩትም በንግግራቸው ለሊቱን በመስገድ የቆመ በማለት ገልፀዋል እና መውሊድን ለማክበር ተራዊሕን እና ተሀጁድን እንደምክንያት ማቅረብ ስህተት ነው!!
__
✍️አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ
https://telegram.me/ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

07 Sep, 03:27


▪️ቢድዓ ለሁለት ይከፈላል የሚሉ ሰዎች ማምታቻቸው እና ምላሹ ክፍል 1.

#የመጀመሪያው_ማምታቻ ፡ ተከታዩ ሐዲስ ነው ፦
من سن في اْلسلام، سنة حسنة،فله أجراها وأجر من عمل بها من بعده، من غير "]
[" .. أن ينقص من أجورهم شيء، ومن سن في اْلسلام سنة سيئة
[ በእስልምና ውስጥ መልካም ሱናን መንገድ አድርጎ የጀመረ ፤ ለእርሱየሱ ምንዳ አለው ፤ ከእርሱ በኋላ በእርሱ የሰራበት ምንዳም አለው ከምንዳዎቻቸው አንድም ሳይቀንስ። በእስልምና ውስጥ መጥፎን
መንገድ የጀመረ ለሱ ከእርሱ በኋላ በእርሱ የሰራበት ወንጀል ምንም ሳይቀነስ ከወንጀሎቻቸው አለው። .. ] (ሙስሊም ፥ 1017).
°
🔻ይህን ሐዲስ [ በእስልምና ውስጥ መልካም ሱናን መንገድ አድርጎ የጀመረ ሰው ] የሚለውን ትርጉም በእስልምና ውስጥ አዲስን ቢድዓ የፈጠረ ሰው በማለት ይተረጉሙት እና መልካም ቢድዓ ከሆነ መፍጠር
ይቻላል ይላሉ ፤ ለዚህ የሚሰጠው መልስ እንደሚከተለው ይሆናል ፡
°
🔻ይህ ሐዲስ አዲስ ቢድዓን ለመፍጠር ማስረጃ አይሆንም። የማይሆንበትም ምክንያት ሐዲሱ የወረደበትን ሰበብ(ምክንያት) ስንመለከት ግልፅ ይሆንልናል ፤ የወረደበት ምክንያት ከጀሪር ኢብኒዐብዲሏህ - ረዲየሏሁ ዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው ፦ ሶሓባዎች ከነብዩ - صلى الله عليه وسلم - ጋር ተቀምጠው እያለ ከሙደር የሆኑ የገጠር ሰዎች ተቸግረው በመጡ ጊዜ ረሱል - صلى الله عليه وسلم - ሲያዩዋቸው በነሱ ሁኔታ በማዘን ፊታቸው ይቀያየር እና ለነዚህ ሰዎች ሰደቃ እንዲሰጡ ሶሓቦቻቸውን ኹጥባበማድረግ ያነሳሱዋቸዋል ፤ በዚህን ጊዜ ከመካከላቸው አንድ ሶሓባ ተነስቶ ወደቤቱ በመሄድ እጁ እስኪከብደው ድረስ በዘንቢል ሙሉ ሰደቃ ይዞ ይመጣል ፤ ይህንንም ያዩ ሶሓቦዎች የሱን አርአያ በመከተል የአቅማቸውን ያክል ሰደቃ እየያዙ መምጣት ጀመሩ ፤ የተሰበሰበውሰደቃም ነብዩ - صلى الله عليه وسلم - ፊት እንደ ተራራ ተቆለለ። የዚህን ጊዜ ነብዩ - صلى الله عليه وسلم - ይህንን የሰደቃ ሱንና ለከፈተው በመጀመሪያው ሰውዬ ተደስተው ፊታቸው በደስታ አበራ እና [ በእስልምና ውስጥ መልካም ሱና መንገድ አድርጎ የጀመረ ሰው ] የሚለውን ሐዲስ ተናገሩ ማለት ነው።
°
🔻ከላይ እንደምንረዳው ሐዲሱን የተናገሩት በሰደቃ ምክንያት ነው ፤ሰደቃ ደግሞ በቁርአን እና በሐዲስ የተደነገገ መልካም ተግባር እንጂ አዲስ ፈጠራ ወይም ቢድዓ አይደለም። እንደነሱ ትርጉም የምንሄድ ከሆነ እስኪ የትኛው ነው አዲስ ቢድዓ የሆነው? ሰደቃ ቢድዓ ነውን?
°
🔻ስለዚህ [ መልካም ሱንና የጀመረ ] ሲባል ከዚህ በፊት በሸሪዓ ያልተደነገገ አዲስ ቢድዓን ያመጣ ለማለት ሳይሆን ሰዎች ከሱ የተዘናጉበትን ወይም ችላ ያሉትን በሸሪዓ የተደነገገን ሱና እንደአዲስበመስራት የጀመረ እና በሱም ተነሳስሽነት ሌሎች ሰዎች ተከትለውት ከሰሩ ከነሱ ምንዳ ሳይቀነስ ለርሱም ምንዳ አለው ለማለት ነው። በመሆኑም ይህ ሐዲስ ቢድዓን ለሁለት ለመክፈል ማስረጃ መሆንአይችልም ማለት ነው።
°
🔻የሐዲሱ ሁለተኛ ክፍል ማለትም [ በእስልምና ውስጥ መጥፎን መንገድ የጀመረ ] የሚለው ደግሞ ትርጉሙ በመሰረቱ የወንጀሉ ክልከላነት በሸሪዓ ውስጥ የተቀመጠ መጥፎ ተግባር ሆኖ ነገር ግን ሰዎች ያንን ወንጀል ከመስራት ሰላም ሆነው(ታቅበው) ባለበት ወቅት ወንጀሉን እንደአዲስ መንገድ አድርጎ የጀመረ ሰው ከሰሪዎቹ ወንጀል ሳይቀነስ ለርሱም ወንጀል አለው ማለት ይሆናል።

✍️ ____
©ዲን መመካከር ነው
____
✍️አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ @ Ibn yahya Ahmed
እሁድ ሶፈር 26/1440ሂ. # ጥቅምት 25/2011. ላይ የተፃፈ
@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

04 Aug, 08:59


ስለተጨናነቅክ ሪዝቅህ አይመጣም። በጣም ስለለፋህ ደግሞ ሀብታም ትሆናለህ ማለት አይደለም። የሰጠህን ነገር በረካ እንዲያደረግልህ እና በተሰጠህ ነገር መብቃቃትን እንዲሰጥህ ዱዓ አድርግ!
@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

03 Aug, 16:46


▪️ዐይኖቹ የጠፉበት ሰው

🔻ከአነስ - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው የአሏህ መልእክተኛ - ﷺ - እንዲህ ሲሉ ሰምቼያቸዋለው ፦ " አሏሁ - ዐዝዘወጀል - እንዲህ አለ ፡ [ ባርያዬን በሁለት ዐይኖቹ ፈትኜው ከታገሰ በነሱ ምትክ ጀነትን እለውጠዋለው።] " ቡኻሪ ዘግቦታል ፥ 5653
@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

03 Aug, 16:38


▪️የሚወደውን ሰው ከሞተበት
°
🔻ከአቢሁረይራህ - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው የአሏህ መልእክተኛ - ﷺ - እንዲህ አሉ ፦ " አሏሁ - ተዓላ - እንዲህ አለ ፡ [ ለአንድ ባርያዬ ከዱንያ ውስጥ የቅርብ ወዳጁን በወሰድኩበት ጊዜ አጅሩን ከአሏህ ዘንድ አገኛለው ብሎ ከተሳሰበ ለሱ ምንዳው እኔ ዘንድ ጀነት እንጂ ሌላ አይደለም። ] " ቡኻሪ ዘግቦታል።
@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

02 Aug, 10:44


ሙጃሂዶቹ ተሳክቶላቸው ነፃ ቢያወጡት ለዚያራ ሂዶ ሰልፊ ለመነሳት የአለም ሙስሊም ሙሉ ይጓጓል .. ሂዶ ለመታገል ግን ይፈራል .. አንዳንዱ ደግሞ እሱ ሳያንሰው እዛ ሚታገሉትን ቤቱ ቁጭ ብሎ ያብጠለጥላል .. ዐጂብ!!

Ibn Yahya Ahmed

31 Jul, 15:40


🔻ብዙ ነጋዴዎች ጋር ያለ ችግር!
እቃ ተስማምተው ሽጠው ብር በአካውንታቸው ገብቶ እቃ ጨምሯል እና አልሰጥህም ብሎ ቃልን ማፍረስ! ግብይትን ማፍረስ! ክዳት!
@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

26 Jul, 17:12


ረሱል - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ " ሶላት ብርሀን ነው ፤ ሰደቃ ማስረጃ ነው ፤ ትእግስት አንፀባራቂ ብርሀን ነው ፤ ቁርአን ላንተ ወይም ባንተ ላይ ማስረጃ ነው ፤ ሁሉም ሰው ይማልዳል ነፍሱን ነፃ የሚያወጣት አለ ወይም የሚያጠፋት አለ። "
~~~
ሙስሊም ዘግቦታል
@ibnyahya777

Ibn Yahya Ahmed

26 Jul, 16:44


" ጦሃራ የኢማን ግማሽ ነው። ሱብሓነሏህ ሚዛንን ይሞላል ፤ ሱብሓነሏህ እና አልሓምዱሊላህ በሰማያት እና በምድር ያለውን ይሞላሉ ወይም ይሞላል። "
ረሱል - ﷺ -
~~~
ሙስሊም ዘግቦታል
@ibnyahya777

2,231

subscribers

512

photos

2

videos