ዘ ተዋህዶ @tewhodox Channel on Telegram

ዘ ተዋህዶ

@tewhodox


ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን ናቹሁ ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየንና በዚህ ቻናል የተዋህዶ ፎቶችን ስለ ሚያገኙበ ተቀላቀሉበትበየቀኑ አዳዲስ ፎቶ ያገኙበታል


ጥያቄ ወይንም አስተያየት ካለ
👉 @DagiN19

ሼር በማድረግ የቤተክርስቲያን እና የቅዱሳን ምስእል ያስፋፉ!
--join--
👇👇👇👇
@tewhodox
@tewhodox

ዘ ተዋህዶ (Amharic)

ዘ ተዋህዶ ከለውጥ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ለመከላከል እና ለልዩ ቀን በሰማይ ታምጣሎችን እና ተመልከቱን በሚያገኙ መረጃዎች ላይ የታለለ፣ ሚዳቋ አዳዲስ ፎቶች በየቀኑ ያገኙበታል። እባኮታ አስተያየትን ከትልቅ በኃይል ሊያወጣ ነው፡፡ አባቶችን እና ቤተክርስቲያንን እንዴት ማድረግ የሚችያለት፣ ለመልስ የሚከበረውን ምስእል ለመዘንጋት ማቅረብ በመጠቀም ቤተሰብን እና ምርጥ ፎቶችን ለመታወቅ መረጃዎች ይሆናሉ። በዚህ ቻናል መረጃ ለመታወቅ ለመጠን ፓስተፋሳትዎን ለመሸጥ እና ሉኡል ፎቶችን ለማምዋል የተቆረጡ ፎቶች በምሳሌ ይደሰቱ። ከዚህ በታች ከትክክለኛ ትረካከል እና ለአስተማሪም ለመመልከት ቤተሰብ፣ ብቻ ምስእልን ያስፋፉ።

ዘ ተዋህዶ

21 Jun, 04:16


Channel photo removed

ዘ ተዋህዶ

22 Aug, 06:30


ኪዳነ ምህረት ሆይ ባንቺ የተፈጸመው ድንቅ ነገር ለማንም ያልተደረገ እረቂቅ ነገር ነው ኅብስት ህይወት ጌታን ያስገኘሽልን ድንግል ሆይ እናመሰግንሻለን።

ኢየሱስ ክርስቶስ ስጋዬን የበላ ደሜንም የጠጣ የዘላለም ሕይወትን ይወርሳል በማለት ያስተማረን ከአንቺ የነሳውን ሥጋ እና ደሙን እንበላ እና እንጠጣ ዘንድ ነው።

በሄዋን ምክንያት የተዘጋ ገነት በአንቺ የተከፈተብሽ ድንግል ሆይ በአንቺ ድንቅ ነገር እረቂቅ ሚስጥር ተደረገልን።

ከአንቺ የተዋሐደውን ሥጋና ደም ተቀበልን። ገነት መንግስተ ሰማያት የምንወርስብሽ ድንግል ሆይ እናመሰግንሻለን።

ከድቅድቅ ጨለማ ሳለን ብርሃን የተመለከትንብሽ የብርሃን እናቱ ድንግል ማርያም ሆይ እናመሰግንሻለን በማህጸን የፈጠርሽን አምላክ በማህጽንሽ የተሸከምሽው ድንግል ሆይ እናከብርሻለን።

የእመቤታችን ኪዳነ ምህረት በረከቷ ፍቅራ በሁላችን ላይ ይደርብን።

እንኳን ለእመቤታችን እርገት ትንሳኤዋ በአል በሰላም አደረሳችሁ

👉 @tewhodox
👉 @tewhodox
👉 @tewhodox

ዘ ተዋህዶ

21 Aug, 16:35


#ቅድስት_ሥላሴ

"ሥላሴን " "ቅድስት ሥላሴ እያልን የመጥራታችን ምስጢር ምንድን ነው?

◉አንዲት ሴት ወይም እናት ልጆቿን አልወለደችም ተብላ አትጠረጠርም ፤ ሥላሴም ይህንን
ዓለም ፈጥረዋል እናም አልፈጠሩም ተብለው አይጠራጠሩም ።

◉አንዲት ሴት በባሕሪይዋ ልጅን ታስገኛለች ፤ ሥላሴም ይህንን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር
አምጥተው ስለፈጠሩት በሴት አንጻር # ቅድስት ተብለው ይጠራሉ ።

◉አንድም ሴት አዛኝ ናት ፤ ለታናሹም ይሁን ለታላቁ ትራራለች ሥላሴም እንደዚሁ ለፍጥረት
ሁሉ ያዝናሉ ፥ ይራራሉ ፥ ምህረት ይሰጣሉ ። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንዲህ ይላል ።
ምህረታችሁ ከልክም በላይ የበዛ በሴት አንቀጽ ቅድስት ተብላችሁ የተጠራችሁ ሥላሴ " በማለት ያመሰጥራል።
ስለዚህ ቅድስት ለምን ተባሉ ቢባል በረከታቸው ፥ ርህራሄያቸውና ፥
ይቅር ባይነታቸው መሆኑን ማወቅ አለብን ።

◉አንድም ሴት ልጇ ቢታመምባት አትወድም ፤ ሥላሴም አንድም ልጅ በዲያብሎስ እጅ ተይዞ
በኃጢአት እንዲታመሙ አይወዱም ፥ አይፈቅዱም በመሆኑም
#ቅድስት ይባላሉ ።

◎አንድም ሴት ልጅ የልጇን ነውር አትጠየፍም ልጄ ቆሽሿል ፥ ተበላሽቷል ብላ ፊቷን አታዞርም ።
ሥላሴም የሰውን በኃጢአት መቆሸሽ ሳይፀየፉ በቸርነታቸው ጎቦኝተው ለንስሐ ያደርሱታል ።

◎ይህንን የፅድቅ አየር የምንምገው ያማረውንም ብርሃን የለበስነው ስለ ፅድቃችን ሳይሆን
በሥላሴ ቸርነት ነውና ስለዚህም ሥላሴን በሴት አንቀፅ # ቅድስት እንላቸዋለን ።

◉አኔድም ሴት ልጆቿን ፈጭታና ጋግራ ትመግባቸዋለች ሥላሴም እንደዛው ናቸው ። በዝናብ
አብቅለው በፀሐይ አብሥልው ፍጥረታትን ሁሉ ይመግባሉ ። ስለዚህ ሥላሴ እንደ እናት
ሁሉንም ይመግባሉና በሴት አንቀጽ #ቅድስት ይባላሉ ።


----- Share---&---Join

👇👇👇👇
@tewhodox
@tewhodox
👆👆👆👆

ዘ ተዋህዶ

03 Apr, 19:00


🌿ሆሳዕና_ማለት_ምን_ማለት_ነው ??
🌿በሆሳዕና_ለምን_ቀለበት_እናስራለን ?
🌿በሆሳዕና_ጌታችን_ለምን_በአህያ_ላይ_ተቀመጠ .
🌿በሆሳዕና_ለምን_ዘንባባ_አነጠፉ ?
................................................................
እና ሌሎች በደንብ ይነበብ ሼር!
=> ሆሳዕና ማለት ምን ማለት ነው??
ሆሳዕና ማለት፦ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ ‹‹እባክህ አሁን አድን አሁን ባርከን›› ማለት ነው፡፡በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሃት ጸሎተ አስተስርዮ ስለማይፈጸም ጸሎተ ፍትሃትና አስተስርዮ
የሚደረገው በዚሁ ዕለት ነው::

=> በሆሣዕና ዕለት በእጃችን እደ ቀለበት ማሰራችን የምን ምሳሌ ነው??
1.ጌታ ለአዳም የሰጠው ቃል ኪዳን ለማስታወስ፡-ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድነሃለሁ ያለውን የተስፋ ቃል ለማስታወስ፡፡
2.ጌታ ለእመቤታችን የገባላትን ቃል ኪዳን ተምሳሌት ነው።
3.ጌታ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ቃል ኪዳን ተምሳሌት ነው።
4.ጌታ ለአዳም ከሰይጣን ግዛት ነጻ እንዳወጣው ሁሉ እኛም ከሰይጣን ግዛት ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ከክፋት ከኃጢአት አውጣን ማረን ለንስኃ ሞት አብቃን ከቤትህ አትለየን እንደ ቸርነትህ ይቅር በለን ስንል ለጌታ ዳግም ላናጠፋ ቃል የምንገባበት ነው፡፡

=> ጌታችን በዕለተ ሆሳዕና ለምን በፈረስ ላይ አልተቀመጠም??
ትንቢቱንና ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፡፡ "
አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ
ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።(ትንቢተ ዘካርያስ 9:9)
=> በአህያ መቀመጡ፦

•ትህትናን ለማስተማር
•የሰላም ዘመን ነው ሲል
•ለፈለጉኝ ሁሉ የቅርብ አምላክ ነኝ ሲል በንጽህና በየዋህነት ለሚኖሩ ምዕመናን አድሬባቸው እኖራለሁ ሲል፡፡

•አህያዎች ትሁታን ናቸው ረጋ ብለው ነው
የሚሄዱት፤በቀላሉ ትወጣበታለህ፤በቀላሉ
ትይዘዋለህ፤እንደፈለክም ታዝዋለህ።
ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ዘባባ የመነጠፉ ሚስጢር የምን ምሳሌ ነው???
1.ዝንባባ፡- ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ ደስ ብሎት አብርሃምን ዘንባባ ይዞ እግዚአብሔር አመስግነዋል፡፡
2.ዝንባባ ደርቆ እንደገና ሂይወት ይዘራል፡- የደረቀ የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
3.ዝንባባ የሰላም ምልክት ነው፡- የሰላም አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
4.ዝንባባ የደስታ መግለጫ ነው፡- አንተ ደስ የምታሰኝ ሃዘናችንም የምታርቅልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
5.ዝንባባ እሾሃማ ነው፡- አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
6.ዝንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጂ፡፡ ጌታም አንተ ባህሪህን የማይመረመር ነው ሲሉ ነው፡፡
ህዝቡ ከልብሳቸው ሌላ ስንት አይነት ቅጠንል አነጠፉለት ምን ምን??

ልብሳቸውን ማንጠፋቸው፡-
ለክብሩ መግለጫ ነው፡፡
ሌሎችም ሦስት አይነት ቅጠል አነጠፉለት ዘንባባ፤የቴመር ዛፍ፤የወይራ ዛፍ አነጠፉለት፡፡
ትልቅዋ አህያ በምን ትመሳለለች ውርን ጭለዋስ???
ትልቅዋ አህያ የኦሪት ምሳሌ ነው።
1.ትልቅዋ አህያ ሸክም የለመደች ናት ህገ ኦሪትም የተለመደች ህግ ናትና፡፡
2.የእስራኤል ምሳሌ ነው፡-ትልቅዋ አህያ ሸክም እንደለመደች ሁሉ እስራኤልም ህግ ለመፈጸም በህግ ለመራመድ የለመዱ ናቸው፡፡
3.የአዳም ምሳሌ ነው፡- አዳም ሸክም የበዛበት ነበርና።

ውርጭላዋ
1.በህገ ወንጌል ትመሰላለች፡-ምክንያቱም ወንጌል ኢየሱስ ክርስቶስ የመሰረታት የሰራት አዲስዋ ህግ ናትና፡፡
2.በአህዛብ ትመሰላለች፡-ትንሽዋ አህያ ሸክም የለመደች አይደለችም እንዲሁም አህዛብም ህግህን የመቀበል የመቀበል የለመደ አይደሉም፡፡ ለህግህ አዲስ ናቸውና፡፡
3.የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡- የዓለም ሸክም አቅልላለችና በእመቤታችን ትመሰለላለች፡፡ እመቤታችን ድህነተ ምክንያታችን ጌታን የተሸከመች ንጽህት እንከን የሌላት እናት ናትና፡፡

ወስበሐት_ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ_ድንግል ወለመስቀሉ_ክቡር አሜን አሜን አሜን
🌹ዘተዋህዶ🌹
💐@tewhodox💐
💐@tewhodox💐
💐ለወዳጅ ለዘመድ ለጓደኛ ያጋሩ 💐

ዘ ተዋህዶ

06 Feb, 12:09


የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጠ!

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በዛሬው ዕለት በወቅታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥቷል።

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የተከሰተው ክስተት አየተባባሰና እየተካረረ መሄዱ በእጅጉ እንዳሳሰበው ተቋሙ በመግለጫው አሳውቋል።

የስድስቱ አባል የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች ስለጉዳዩ በመጨነቅ አብዝተው ከመጸለይ ባለፈ ከቤተክርስቲያኒቱ አባቶች ጋር ችግሩ በሰላማዊ ሁኔታ ስለሚፈታበት ሁኔታ መወያየታቸውም ተገልጿል።

በተያያዘም በዚህ ሂደት ተቋሙ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል።

ዘ ተዋህዶ

06 Feb, 09:03


#መሐረነ_አብ #ጸሎተ_ምህላ

ሃሌ ሉያ ዘበእንቲአሃ ለቤተክርስቲያን ተጸፋእከ በውስተ ዐውድ ከመ ትቀድሳ በደምከ ክቡር።

ዘበእንቲአሃ ዝግሐታተ መዋቅሕት ፆረ። ወተዐገሰ ምራቀ ርኩሰ እንዘ አልቦ ዘአበሰ አምላክ ዲበ ዕፀ መስቀል ተሰቅለ።

ሃሌ ሃሌ ሉያ አርእየነ እግዚኦ ሣህልከ፤ ረዳኤ ኩነነ ወኢትግድፈነ፣ መሐረነ መሐከነ እግዚኦ እግዚኦ ተሣሃለነ

✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟

መሐረነ አብ
- ሃሌ ሉያ
ተሣሃለነ ወልድ
- ሃሌ ሉያ
መንፈስ ቅዱስ መሐሪ ተዘከረ በሣህልከ (፫ ጊዜ)

- ለከ ንፌኑ ስብሐተ ወለከ ናዐርግ አኮቴተ።
መሐረነ መሐሪ ኅጢአተነ አስተሥሪ።
- ወአድኅነነ
ወተማኅጸን ነፍሰነ ወሥጋነ
- ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር።
አምላክነ
- ወመድኃኒነ
ኢየሱስ ክርስቶስ ተሣሃለነ።
- በብዝኃ ምሕረትከ
ደምስስ አበሳነ
- ወፈኑ ሣህለከ ላዕሌነ።
እስመ እምኅቤከ
- ውእቱ ሣህል
ሃሌ ሉያ መሐረነ አብ መሐሪ።
- ወተሣሃለነ
ሀብ ሣህለከ መሐሪ
- ኢታጥፋነ ተዘኪረከ ዘትካት።
በምሕረትከ
- እሰመ መሐሪ አንተ
ወብዙኅ ሣህልከ ለኵሎሙ እለ ይጼውዑከ።
- ይጼውዕከ በጽድቅ
ሰማዒ ወትረ
- ከሃሊ ዘውስተ አድኅኖ።
ከሃሊ
- ዘውስተ አድኅኖ
ለአምላክነ ጻድቅ እሰመ ጽድቅ ቃሉ።
- ንስአሎ ለአብ
ይፈኑ ለነ ሣህሎ
- እስመ አብ የአክል ለዘሰአሎ።
ሃሌ ሉያ
- ስብሐት ሎቱ ይደሉ።
ሃሌ ሉያ አኰቴት ሎቱ ይደሉ።
- ሃሌ ሉያ
ለክርስቶስ ለእግዚአ ኵሉ
- ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ።

ወይእዜኒ
- መኑ ተስፋየ
አኮኑ
- እግዚአብሔር
ውስተ እዴከ እግዚኦ አመኀፅን ነፍስየ።

- ኀበ አምላከ ምሕረት
አመኀፅን ነፍስየ።
- ኀበ ንጉሠ ስብሐት
አመኀፅን ነፍስየ።
- በእግዚእየ ወአምላኪየ
አመኀፅን ነፍሰየ።
- እምኵሉ ምግባረ እኩይ አድኅና ለነፍስየ። (፫ ጊዜ በል)

ሀቡ
ንስአሎ
- ንስአሎ
ናስተምሕሮ
- ለአምላክነ ጻድቅ እሰመ ጽድቅ ቃሉ።

ዘይክል ኵሎ ወአልቦ ዘይሰአኖ።
- አምላከ ነዳያን ረዳኤ ምንዱባን።
ንህነ ኀቤከ ተማኅፅነ።

ዘይክል ኵሎ ወአልቦ ዘይሰአኖ።
- አምላከ ነዳያን ናዛዜ ኅዙናን
ንህነ ኀቤከ ተማኅፅነ።

ዘይክል ኵሎ ወአልቦ ዘይሰአኖ።
- አምላከ ነዳያን ወተስፋ ቅቡፃን
ንህነ ኀቤከ ተማኅፅነ።

- ወበከመ ዐቀብከነ እምነግህ እሰከ ሠርክ ዕቀበነ እግዚኦ እምሠርክ እስከ ነግህ። (፫ ጊዜ በል በቅብብል)

ተሣሃልከ እግዚኦ ምድረከ ሃሌ ሉያ ስማዕ ጸሎተነ ወስእለተነ ወሥረይ ኩሎ ኀጢአተነ ስማዕ ጸሎተነ ወስእለተነ ዘሰማዕኮ ጸሎቶ ወስእለቶ ለዕዝራ ተወከፍ ምህላነ እማዕከሌነ ኢትርኀቅ።

- ወሚጥ መዐተከ እምኔነ ሃሌ ሉያ ንዒ ኀቤየ እንቲአየ ሠናይት ርግብየ መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል ወኵሉ ነገራ በሰላም።

አርእየነ እግዚኦ ሣህለከ ሃሌ ሉያ መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ሚካኤል ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ፤ አዕርግ ጸሎተነ ቅድመ መንበሩ ለንጉሥ ዐቢይ።

- ገብርኤል አብሠራ ለማርያም ወይቤላ ትወልዲ ወልደ፤ ወይነግሥ ለቤተ ያዕቆብ ለዓለም፤ ወአልቦ ማኅለቅት ለሰላሙ።

ሰአል ለነ ጊዮርጊስ ኀበ እግዚአብሔር ወጸሊ በእንቲአነ ሐረድዎ ወገመድዎ ወዘረዉ ሥጋሁ ከመ ሀመድ፣ ወወሰድዎ ኀበ ፸ ነገሥት ረገጸ ምድረ አንሥአ ሙታን አባ ጊዮርጊስ በሰላም ዐደወ መንግሥተ ክብር ወረሰ።

- ባርከኒ አባ እንሣእ በረከተከ በእንተ ሰላማ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን አባ ባርከኒ እንሣእ በረከተከ።

ብፁዕ አባ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዘኤለ ገዳማተ እምኀበ እግዚኡ ይነሣእ እሴተ፤ ቦአ ሀገረ ደብረ ሊባኖስ በፍሥሐ ወበሰላም።

- ማኅደረ ሰላምነ ቅድስት ደብተራ እሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላእክት ንዑ ንስግድ ኵልነ ኀበ ማርያም እምነ።

መስቀል ብርሃን ለኵሉ ዓለም መሠረተ ቤተ ክርስቲያን ወሀቤ ሰላም መድኃኔዓለም ሰላመከ ሀበነ።

- ሰላመ አብ ወሰላመ ወልድ ወሰላመ መንፈስ ቅዱስ የሀሉ ማዕከሌክሙ አኀው።

✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟

ይ.ካ. ሰላመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ወፍቅራ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ሞገሰ መስቀሉ ወሀብተ ረድዔቱ የሃሉ ምስለ ኵልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም።

        እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ
        በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ

ሰአሊ ለነ ማርያም ምሕረተ ወልድኪ የሐውጸነ ማርያም። ሰአሊ ለነ ማርያም ለዕለሰዓቱ ተግባረ እደዊሁ ለወልድኪ ኢንጥፋ በከንቱ። ኲሎ መዓልተ ወኲሎ ሌሊተ ብዙኃ ኃጢአተ ዘገበርነ በእንተ ማርያም እምከ ተማኅጸነ። ሥመር እግዚኦ ከመ ታድኅነነ። ኢታርምም እግዚኦ ወኢትጸመመነ ተዘከር እግዚኦ ከመ መረት ንሕነ።

እግዚኦ ዕቀባ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ።
እግዚኦ አእርፍ ነፈሳተ አግብርቲከ ወአእማቲከ ኲሎሙ ክርስቶሳውያን።
እግዚኦ አድህን ለኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን።
✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟

ዘ ተዋህዶ

04 Feb, 11:59


ቶሎ ቶሎ ሼር እናድር ለሀዋሳ

ዘ ተዋህዶ

04 Feb, 11:58


🌹ዘተዋህዶ🌹
💐@tewhodox💐
💐@tewhodox💐
💐ለወዳጅ ለዘመድ ለጓደኛ ያጋሩ 💐

ዘ ተዋህዶ

04 Feb, 10:12


ቤተክርስቲያን ምዕመኗ ጥቁር ልብስ እንዲለበሱ ጥሪ አቀረበች!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለ3 ቀናት ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን አስተላልፏል። ከጥር 29 እስከ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ለሦስት ቀናት በጾምና በጸሎት በአንድ ልብ ሆነን ወደ ፈጣሪያችንን እንድንጮህ አደራ እንላለን ተብሏል።

ዘ ተዋህዶ

04 Feb, 09:48


የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ፕሮፌሰር ቄስ ዶ/ር ጄሪ ፒላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን  የሚነኩ እና አንድነቷን አደጋ ላይ የሚጥሉ ሁኔታዎች በእጅጉ እንደሚያሳስቧቸው  ገለጹ።

“የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ሐዋርያዊት እና ጥንታዊ ከሆኑ  አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዷ ነች፤ ይህች ቤተ ክርስቲያን ስለሰላምና አንድነት የደም ዋጋ ከፍላለች” ብለዋል።  የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት በአሁኑ ሰዓት ከጥንታዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  የተነጠለውን ቡድንም እንደሚቃወመው ገልጸዋል።

ዋና ጸሐፊው አክለውም "የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕጋዊ እውቅና ያገኘች የሃይማኖት ተቋም  እንደመሆኗ በውስጥ ሕጓና በቀኖናዋ እንድትመራ በመፍቀድ በምእመናን መካከል አንድነትና ሰላም እንዲሰፍን የምታደርገውን ጥረት እንዲደግፉ በኢትዮጵያ ለሚገኙ  የፖለቲካ መሪዎች በሙሉ  እንጠይቃለን።" ሲሉ አሳስበዋል።

የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና ከኢትዮጵያ ጋር በመሆን ለፍትህ፣ ለእርቅ፣ ለአንድነትና ለሀገሪቱ ሰላም  ይጸልያል ብለዋል

ዘ ተዋህዶ

04 Feb, 09:46


በሻሸመኔ ከተማ ሰማዕትነትን የተቀበሉ ኦርቶዶክሳውያን ቁጥር ሁለት ደረሰ!

ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ)

በሻሸመኔ ከተማ ሰማዕትነትን የተቀበሉ ኦርቶዶክሳውያን ቁጥር ሁለት የደረሰ ሲሆን በአራቱ ላይ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገለጸ።

አብያተ  ክርስቲያናት ውስጥ ያሉት ምእመናን እስካሁን ድረስ በቅጽር ግቢ ውስጥ እንዳሉ ናቸው። ነገር ግን አሁን ላይ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጣውን የጸጥታ ኃይል አባላት በዱላ እያባረሩ ይገኛሉ።

የከተማዋ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አካላት ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን ውጪ ላሉት የከተማዋ ነዋሪዎች ነጠላ በማደል ሻሸመኔ ስታዲዮም ተገኝተው ሕገ ወጡን ቡድን እንዲቀበሉ እያስተባበሩ ያሉ ሲሆን በመኪና ከተማውን እየዞሩ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

በዚህ ሰዓት የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ከሻሸመኔ እስከ አርሲ ነገሌ ድረስ ያለውን ቦታ ተቆጣጥሯል

ዘ ተዋህዶ

04 Feb, 09:45


ሰማዕትነትን ከልጆቼ ጋር እቀበላለው በሚል ብጽኡ አቡነ ዮሴፍ ወደ ሻሸመኔ ከተማ ገቡ!

እንግዲህ ሞት የማይፈራ እረኛ ከፊት እየመጣ ነው። እንግዲህ ስንቱን ጨርሳችሁ በምድር ላይ እንደምትኖሩ እናያለን ! ከፊት ሆኜ እቀበላለሁ ሰማዕት እሆናለሁ ብለው ወደ ሻሸመኔ ገብተዋል!


አቡነ ዮሴፍ ከህዝቤ ጋር #እሞታለሁ በማለት በአሁን ሰዐት ሻሸመኔ ናቸዉ!


💚ወስብሐት ለእግዚአብሔር 💚
💛ወለወላዲቱ ድንግል💛
❤️ወለመስቀሉ ክቡር❤️
            ይቆየን!

ዘ ተዋህዶ

04 Feb, 09:42


መረጃ ማግኘት አልቻልንም!



ሻሸመኔ ላይ ኔት ወርክ ሙሉ ለሙሉ ጠፍቷል! መረጃ ማግኘት አልቻልንም! በዚህ ሰዓት ምን ይደረግ ምን ይሁን አናውቅም!  ግን የመጨረሻ የደረሰኝ መረጃ ቢኖር ሕዝቡ ቤተ ክርስቲያን እየጠበቀ እንዳለ እና ሕገ ወጡ ቡድን ሆቴል ውስጥ እንዳለ ነው የሠማነው ከተማውም ላይ በእስታድዪም ቅበላ አድርጉልን እያሉ እየለፈፉ እንዳለ ነበር የሰማነው ከዛ በኋላ ኔት ወርክ ጠፋ!  መረጃ የለም! ቅድም vpn ያዙ ስንል የነበረው ለዚህ ነው!  እግዚአብሔር ሆይ 24 ሰዓት አንተን መጥራት የማታቆመውን ሐገር ፈጽሞ እንደማትተዋት አሳምሬ አውቃለሁ! ድንግል ማርያም የአስራት ሐገርሽን እንደማትተያት ፈጽሜ አውቃለሁ! አቡነ ተክለ ሐይማኖት ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ሐገሬን ብለው እንደሚጠይቁ በሰማይ አምናለሁ! እና ጸልዩ እንጂ ምንም እንዳትፈሩ!

💚ወስብሐት ለእግዚአብሔር 💚
💛ወለወላዲቱ ድንግል💛
❤️ወለመስቀሉ ክቡር❤️
            ይቆየን!

ዘ ተዋህዶ

04 Feb, 09:37


የ ' ፌደራሉ መንግሥት ' በሻሸመኔ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ለሚደረገው ግድያ ኃላፊነቱን ሊወጣና ሊያስቆም ይገባል ስትል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥሪ አቀረበች።

ቤተክርስቲያኗ በሻሸመኔ ከተማ አንድ ሰው በፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት መገደሉን ገለፃለች።

ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጉዳዩን በተመለከተ ፤ " እየሞተ ያለው ሕዝብ ነው ቅጠል አይደለም እየተበጠሰ የሚወድቀው ፤ #ይሄ_ፖለቲካ ነው። የፌደራል መንግሥት በሻሸመኔ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ለሚደረገው ግድያ ኃላፊነቱን ሊወጣና ሊያስቆም ይገባል። " ብለዋል።

በሻሸመኔ ምንድነው የሆነ ?

ተ/ሚ/ማ የተባለው የቤተክርስቲያኗ ሚዲያ " በዛሬው ዕለት ሕገ ወጡ ቡድን ወደ ሻሸመኔ ይመጣል መባሉን ተከትሎ ጠዋት ሁለት (2:00) ሰዓት ላይ ሥርዓተ ቅዳሴ እንደተፈጸመ ሕዝቡን ለመጥራት በከተማዋ ያሉ አድባራት ደወል ደውለዋል " ሲል ገልጿል።

" ጥሪው ሰምቶ ሁሉም ምእመን ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ ይጀምል ፤ በዚህ ጊዜ ወደ ሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የሔዱ ምእመናን የቤተክርስቲያኑ በር በመዘጋቱ ከውጪ ቆመው ነበር።

በእንዲህ ሁኔታ ውስጥ እያለ የከተማው ፖሊስ ሕዝቡን ለመበተን ተኩስ ከፍያል ፤ እስካሁን ድረስ አንድ ኦርቶዶክሳዊ ወጣት ሰማዕትነትን ተቀብሏል፤ በውል ያልታወቀ ሰውም በጥይት ተመቷል " ሲል የነበረውን ሁኔታ አስረድቷል።

በሌላ በኩል ቤተክርስቲያኗ ፤ " ትናንትና ሌሊት ሊቀ ጳጳሷን አስሮ ከከተማ ያባረረው ኃይል   በአርሲ ሀገረ ስብከት መናገሻ አሰላ ኦርቶዶክሳውያንን እያሠረ  ይገኛል " ብላለች።

በቤተ ክርስቲያን ቅጽር ውስጥ ያሉትም እንዲወጡ እየተነገራቸውና ያ የማይሆን ከሆነ የኃይል እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ተዝቶባቸዋል ብላለች።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ያሉት ሁኔታዎች እየከረሩ መጥተው ለሰው ህይወት #መጥፋት ምክንያት እስከመሆን የደረሱ ቢሆንም መንግስት እስካሁን ስለጉዳዩ ምንም ያለው ነገር የለም።

ቤተክርስቲያን በበኩሏ ለዚህ ሁሉ መሆን ህገወጥ ሲመት አከናውነዋል ፤ ተቀብለዋል ባለቻቸው ግለሰቦች እና የመንግስት ተቋማት ላይ ክስ ለመመስረት በሂደት ላይ ነች።