Deborah School @deborahschool Channel on Telegram

Deborah School

@deborahschool


Shaping the Next Generation with Wisdom and Character!

Promotional Article for Deborah School Telegram Channel (English)

Welcome to Deborah School, where we focus on shaping the next generation with wisdom and character! Deborah School is a Telegram channel dedicated to providing valuable resources and guidance for parents, teachers, and students who are looking to instill important values and skills in young minds. Who is Deborah School? Deborah School is a community of like-minded individuals who believe in the power of education and character development. Our goal is to create a supportive and inspiring environment where children can learn, grow, and thrive. What is Deborah School? Deborah School offers a wide range of educational content, including tips for raising resilient and responsible children, strategies for teaching important life skills, and resources for fostering creativity and critical thinking. Whether you're a parent looking for ways to support your child's learning journey or a teacher seeking new ideas for the classroom, Deborah School has something for everyone. At Deborah School, we believe that education goes beyond academics. It's about instilling values like empathy, integrity, and perseverance in the next generation. By teaching children to be compassionate, ethical, and resilient individuals, we are helping to create a brighter future for all. Join us at Deborah School and be a part of a community that is dedicated to shaping the next generation with wisdom and character. Together, we can inspire and empower young minds to reach their full potential. Start your journey with Deborah School today and help make a difference in the lives of tomorrow's leaders!

Deborah School

13 Nov, 10:10


ለተከበራችሁ ውድ ወላጆች

የ2ተኛው ሩብ ዓመት የትምህርት ክፍያ ስለተጀመረ፣ በብርሃን ባንክ በልጆቻችሁ አካውንት ክፍያውን እንድታስገቡ እንጠይቃለን።
                          
ትምህርት ቤቱ።

Deborah School

18 Oct, 16:23


ውድ ወላጆች/አሳዳጊዎች

የማጠናከሪያ ትምህርት (After School Program) በነገው እለት ለ6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ተጠናክሮ እንደሚሰጥ እናሳውቃለን።

ትምህርት ቤቱ።

Deborah School

18 Oct, 11:13


ውድ የ12ኛ ክፍል ወላጅ እና ተማሪዎች

ነገ ጥቅምት 9:2016 ዓም በ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ ስለ መማር ማስተማሩ ሂደት እና ውጤት ማሻሻል ዙሪያ አጠቃላይ ስብሰባ ከወላጆች ጋር ከጠዋቱ 3 ሰዐት ላይ ስለሚኖር በስብሰባው እንድትገኙ እናሳስባለን።

ነገር ግን በስብሰባው ላይ ያልተገኛችሁ ወላጆች ሰኞ ጥቅምት 11 ከልጆቻችሁ ጋር በመምጣት ምክንያታችሁን እንድታሳውቁን እንጠይቃለን።

ትምህርት ቤቱ።

Deborah School

12 Oct, 16:29


Dear 2016 E.C. Grade 12 students,

Please note that your university choices need to be submitted to the office no later than 12 PM on Monday, October 14, 2024. You can submit your university preferences either electronically or in printed form.

Note: When filling out your preferences, make sure that all universities are selected without repetitions of choice numbers.

Deborah School

12 Oct, 08:23


For Grade 12 (2016 E.C) University Choice Form. Please download the file and put your university preferences accordingly.

Deborah School

09 Oct, 18:20


ቀን:- መስከረም 29/2017ዓ.ም

በ 2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን  12 ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛ  እና በ መልሶ ማሻሸያ መርሃግብር(Remedial program) ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች ትላንት ትምህርት ሚኒስቴር በተለያዩ ድረገፆች ላይ ባስተላለፈው ማሳሰቢያ በየትምህርት ቤቶቻችሁ ተገኝታችሁ የተቋም እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ አስሞልታችሁ እንድትልኩ መግለፁ ይታወቃል ነገር ግን ይህንን ጉዳይ ለማጣራት ወደ ተለያዩ የትምህርት አመራር ተቋማት ደውለን ባገኘነው መረጃ ምርጫችሁን ለማስሞላት እና ለመላክ የሚያስችል እንዲሁም የትኞቹ ዩኒቨርስቲዎች ናቸው ለምርጫ የቀረቡት የሚለውን ግልፅ እና ተጨማሪ መመሪያ ከትምህርት ሚኒስቴር በኩል ይመጣል  ተብሎ እየተጠበቀ እንደሆነ ስለተገለፀልን ይህንን ተገንዝባችሁ በትእግስት እንድትጠብቁና መረጃውም እንደደረሰን በአፋጣኝ በዚህ በትምህርት ቤቱ ቴሌግራም ቻነል የምናሳውቃችሁ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

ትምህርት ቤቱ

Deborah School

04 Oct, 13:47


ውድ ወላጆች/አሳዳጊዎች

የሚከተሉትነት ነጥቦች ትኩረት እንዲደረግባቸው እናሳስባለን

1ኛ በነገው እለት የቅዳሜ ትምህርት የማይሰጥ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን

2ኛ የተማሪውን የመማሪያ መጽሐፍ እስከአሁን ያልገዛችሁ ወላጆች እንድትገዙ እየጠየቅን፣ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት በሚመጡበት ወቅት የተሟላ የትምህርት መሣሪያዎችን ማለትም ደብተር  እና መጽሃፍ ይዘው እንዲመጡ  እንድታግዟቸው እንጠይቃለን።

3ተኛ ከመዋዕለ ህፃናት አንስቶ እስከ አስረኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የስፖርት መስሪያ ልብስ ስለተዘጋጀ ወላጆች ከትምህርት ቤት ለልጆቻችሁ የስፖርት መስሪያ ልብስ መግዛት የምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

ትምህርት ቤቱ
---
Dear Parents/Guardians,

We would like to draw your attention to the following points:

1. We would like to clarify that there will be no Saturday classes tomorrow.

2. We request that parents who have not yet purchased the students' textbooks, do so. We encourage students to come to school prepared with these essential educational books.

3. Since sports uniforms have been prepared for students from Kindergarten to grade ten, we would like to inform and encourage parents that they can purchase sports uniforms for their children from the school.

The School.

Deborah School

03 Oct, 08:17


ውድ ወላጆች/አሳዳጊዎች

👉ዛሬ ከትምህርት ቢሮ በደረሰን መልእክት መሰረት ነገ አርብ ማለትም በቀን 24/01/2017 ዓ/ም በመላው አዲስ አበባ ባሉ ትምህርት ቤቶች ትምህርት ለግማሽ ቀን ብቻ መሆኑን ትምህርት ቢሮ በመግለፁ፣ ትምህርት በነገው እለት እስከ ቀን 6ሰዐት ድረስ ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን፣

ትምህርት ቤቱ።

Deborah School

01 Oct, 15:24


ውድ ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች

ከብርሃን ባንክ በመጣ ጥያቄ መሠረት
የልጆቻችሁን የትምህርት ወይም ሌሎች ክፍያ በምትከፍሉበት ወቅት ቀጥታ በብርሃን ባንክ ወደ ብርሃን ባንክ ብቻ ትራንስፈር እንድትጠቀሙ እየጠየቅን በቴሌብር ወይም ከሌላ ባንክ ወደ ብርሃን ባንክ ማስተላለፍ ችግር እየፈጠረ በመሆኑ ከዛሬ ጀምሮ የልጆቻችሁን የተመለከተ ማንኛውንም ክፍያ በከብርሃን ባንክ ወደ ብርሃን ባንክ ብቻ ትራንስፈር ወይም በቀጥታ በአካል እንድትከፍሉ በትህትና እንጠይቃለን።

Deborah School

26 Sep, 11:00


ውድ ወላጆች/አሳዳጊዎች

የማጠናከሪያ ትምህርት (After School Program) ይመልከታል።

የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የማጠናከሪያ ትምህርት ፕሮግራም (After School Program)  ቅዳሜ መስከረም 18 ቀን 2017 ዓ.ም ለ6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ባሉ ተማሪዎች ይጀምራል። በተለይም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች እንዲሁም ደግሞ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለክልላዊና ብሔራዊ ፈተናዎች በሚገባ እንዲዘጋጁና የ6ተኛ  የ8ኛ  እና የ12ኛ ክፍል የትምህርት ፖሊሲ ጋር ተያይዞ ሊፈጠሩ የሚችሉ ክፍተቶችን ሙሉ ለሙሉ ለመቅረፍ በማጠናከሪያ ትምህርት ፕሮግራሙ ላይ መሳተፍ ይኖርባቸዋል።

በቅዳሜ ቀን የሚሰጠው የጥናት ፕሮግራም የ6ኛ፣ የ 8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሲሆን ፕሮግራሙ እስከ ከጠዋት 2 ሰዐት እስከ ቀን 7:30 ሰዐት ድረስ የማጠናከሪያ ትምህርት ይሰጣል።

ከ2:10 ቦሃላ የመጣ ተማሪ አርፋጅ እና የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እንገልፃለን

ማሳሰብያ:1. መቅረት የማይቻል ሲሆን የቀረ ተማሪ ሰኞ መስከረም 20 ከወላጅ ጋር ትምህርት ቤት መጥቶ ምክንያቱን ካላስረዳ ትምህርት ቤቱ በቀረው ተማሪ ላይ ቀጣይ እርምጃ እንደሚወስድ እንገልፃለን።

2. ማንኛውም ተማሪ የተሟላ ዩኒፎርም መልበስ ይኖርበታል።

ከጥናት ፕሮግራም በኋላ የሰርቪስ አገልግሎት ለምትፈልጉ ወላጆች 0911203825 በመደወል መረጃ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

ትምህርት ቤቱ።

Deborah School

25 Sep, 15:24


ውድ ወላጆች/አሳዳጊዎች

ነገ ሐሙስ መስከረም 16 ቀን 2017 ዓ.ም የአጠቃላይ የመምህራን ስብሰባ ስለሚኖር ትምህርት ቤት ለተማሪዎች ዝግ ይሆናል፡፡

አርብ መስከረም 17 ቀን 2017ዓ.ም በመስቀል በዐል ምክንያት ትምህርት ዝግ ይሆናል።

ትምህርት ቤቱ

Deborah School

20 Sep, 05:19


ውድ ወላጆች፣

ከመዋዕለ ህፃናት - 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች የመማር ማስተማሩ በሚፈለገው ደረጃ ለማስኬድ የመማሪያ መፅሐፍት ወደ ክፍል ይዘው መምጣት እና መማር ይኖርባቸዋል፣ ስለሆነም ውድ ወላጆች ይህን ተገንዝባችሁ፣ ከዛሬ አርብ መስከረም 10 ጀምሮ ለተማሪዎች የተዘጋጀውን የመማሪያ መፅሐፍትን ከትምህርት ቤት በመግዛት ለልጆቻችሁ በተሰጣቸው የክፍል ፕሮግራም መሰረት በየቀኑ መማሪያ መፅሓፍት መያዛቸውን እንድታረጋግጡ እንጠይቃለን።

ትምህርት ቤቱ

Deborah School

16 Sep, 13:42


ውድ ወላጆች/አሳዳጊዎች!

አሁን ከትምህርት ቢሮ በደረሰን መመሪያ መሰረት  የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን   የመማር ማስተማር በይፋ የሚጀመርበት ቀን ማክሰኞ በ7/01/2017 ዓ.ም መሆኑን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው።

ማሳሰቢያ፣ የመዋዕለ ህፃናት ተማሪዎች ብቻ ለመጀመሪያው ሳምንት ትምህርት ለግማሽ ቀን ብቻ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

ትምህርት ቤቱ።

Deborah School

15 Sep, 06:35


ውድ ወላጆች/አሳዳጊዎች!

1. ሰኞ መስከረም 6: 2017ዓ.ም.
ከቀኑ ፣ 7- 10 ሰዐት ባለው ጊዜ: ወላጆች ከልጆቻችሁ ጋር ትምህርት ቤት በመምጣት Communication Book እና የትምህርት ቤት መታወቂያ እንድትወስዱ፣ እንዲሁም ተማሪዎቹ የተመደቡበትን ደረጃ እና ክፍል እንድታዩ፣

2. ማክሰኞ መስከረም 7: 2017ዓ.ም.
አጠቃላይ የመምህራን ስብሰባ ስለሚኖር፣ ትምህርት በተጠቀሰው ቀን አይኖርም።

3. ረቡዕ መስከረም 8: 2017 ዓ.ም፣2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን   የመማር ማስተማር በይፋ የሚጀመርበት ቀን መሆኑን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው።

ትምህርት ቤቱ።

Deborah School

14 Sep, 11:02


ውድ ወላጆች/አሳዳጊዎች!

2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር በይፋ የሚጀመርበት ቀን ረቡዕ በ8/01/2017 ዓ.ም መሆኑን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው።

ትምህርት ቤቱ።

Deborah School

12 Sep, 03:06


Deborah School pinned «🗓ውድ ወላጆች እንዲሁም ተማሪዎች፣ እንኳን ለ2017 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን! እንደሚታወቀው የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መስከረም 6: 2017 ዓ.ም ይጀምራል። በትምህርት ቀናት ወላጆች ልጆቻችሁን በሰዓቱ ትምህርት ቤት እንድታደርሱ እንዲሁም ወደቤት መሄጃ በሰዐቱ ተገኝታችሁ እንድትወስዱ እንጠይቃለን፡፡  ማሳሰቢያ፣ ለጀማሪ የመዋዕለ ህፃናት ተማሪዎች ብቻ ለመጀመሪያው ሳምንት ብቻ ትምህርት…»