Halal Profile Pictures|ሀላል ፕሮፋይል ፒክቸርስ @halalpic Channel on Telegram

Halal Profile Pictures|ሀላል ፕሮፋይል ፒክቸርስ

@halalpic


የምንሰራቸው ስራዎች
✍️ፖስተር
✍️ባነር
✍️እስቲከር
✍️ሎጎ ዲዛይን
✍️የሰርግ ካርዶች
✍️ቢዝነስ ካርድ
✍️ፕሮፋይል ፒክቸር
በአጠቃላይ ከዲዛይን ጋር የተያያዙ ማንኛውም ስራዎች እንሰራለን

Halal Profile Pictures|ሀላል ፕሮፋይል ፒክቸርስ (English)

Are you looking for a unique and authentic way to express your faith? Look no further! Introducing Halal Profile Pictures, a Telegram channel dedicated to providing high-quality, Halal-approved profile pictures for all your social media needs. Whether you want to show your love for Islam, celebrate a special religious occasion, or simply showcase your faith in a creative way, Halal Profile Pictures has got you covered

Who is Halal Profile Pictures? Halal Profile Pictures is a community of like-minded individuals who believe in the importance of representing their faith in a positive and respectful manner. Our team of talented designers and artists work tirelessly to create beautiful and inspiring profile pictures that adhere to the principles of Halal

What is Halal Profile Pictures? Halal Profile Pictures is a Telegram channel where you can find a wide range of Halal-approved profile pictures that cater to different preferences and styles. From calligraphy designs to nature-inspired motifs, our collection has something for everyone. By using our profile pictures, you can not only showcase your faith but also connect with others who share your beliefs.

So why wait? Join our Telegram channel @halalpic today and start exploring our collection of Halal profile pictures. Let your faith shine through in a meaningful and artistic way. With Halal Profile Pictures, you can express yourself authentically and proudly. Spread positivity, love, and faith with every profile picture you choose. Join us now and be a part of our growing community of individuals who value faith, creativity, and unity.

Halal Profile Pictures|ሀላል ፕሮፋይል ፒክቸርስ

08 Jan, 11:00


KelalEnglish app

💡 1,000+ ቃላት እና ሀረጎችን የያዘ፡ በየቀኑ በቀላሉ እንግሊዝኛ ይማሩ

🗣️ 100+ ውይይቶች፡ የእውነተኛ በህይወት የሚያጋጥሙ ንግግሮችን (ግዢ፣ ጉዞ፣ ወዘተ) ከአማርኛ ትርጉም ጋር ተለማመዱ።

🎧 የድምጽ ድጋፍ፡ ያዳምጡ እና አነጋገርዎን በቀላሉ ያሻሽሉ።

💰 ገንዘብ ያግኙ፡ KelalEnglish ለጓደኞችዎ ያጋሩ !  ለእያንዳንዱ ስኬታማ ምዝገባ እና ግዥ 100 ብር ያግኙ።

የእንግሊዝኛ ቋንቋዎን ይማሩ እና ያሻሽሉ  🚀


ይቀላቀሉ https://t.me/kelalenglishethiopia

Halal Profile Pictures|ሀላል ፕሮፋይል ፒክቸርስ

28 Oct, 04:10


ዛሬ እኮ ጁመዓ ነው ቀኑ በሰለዋት ይደምቃል ሁላችንም ሰለዋት እናውርድ
‏ﷺ
💞
💞
💞💞
💞💞
💞💞💞
💞💞💞
💞💞💞💞
.

💞
💞
💞💞
💞💞
💞💞💞
💞💞💞
💞💞💞💞
.
#ﷺ…

💎💦╰⇢💞💞💞⇢⇢╮💦💎
.
💎💦╭⇠⇠💞💞💞⇠╯💦💎
.
.
.
💞💞 صلى الله على محمد💞💞
💞💞 صلى الله على محمد💞💞
💞💞 صلى الله على محمد💞💞
.
.
@halalpic
@halalpic

Halal Profile Pictures|ሀላል ፕሮፋይል ፒክቸርስ

15 Oct, 10:50


#የማለዳ_መልዕክት

«« ህይወት ሚስጥር ናት። ምን እደሚጠብቅህ ፣ምን እንደሚያጋጥምህ አታውቅም። ሁሉንም ነገር ለመቀበል እራስህን ዝግጁ አድርግ። ደግሞ ሲያጋጥምህ አመስግን፣ ክፉም ሲያጋጥምህ ታጋሽና አመስጋኝ ሁን ። ከችግርም ጋር ምቾት አለና እራስህን አፅናና። ይቺ ምድር የፈተና ቦታ መሆኗን ላፍታም አትዘንጋ።

አላህም እንዲህ ይለናል፦📚

كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۗ وَنَبْلُوكُم بِالشَّرِّ وَالْخَيْرِ فِتْنَةً ۖ وَإِلَيْنَا تُرْجَعُونَ

📖 አል-አንቢያ: 35 📖
ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡ ለመፈተንም በክፉም በበጎም እንሞክራችኋለን፡፡ ወደኛም ትመለሳላችሁ፡፡

«አስታውስ! አላህ ከታጋሾች ጋር መሆኑን። አላህን በኸይር ጠርጥረው ኸይር ይሰጥሃል።

@halalpic
.

Halal Profile Pictures|ሀላል ፕሮፋይል ፒክቸርስ

06 Oct, 16:32


#ሀላል profile pictures
@halalpic

Halal Profile Pictures|ሀላል ፕሮፋይል ፒክቸርስ

04 Oct, 18:05


«ቂም መቋጠር ማለት መርዝ ጠጥቶ ሌላኛው ሰው እንደሚሞት ማሰብ ነው !» ይባላል፡፡

ይቅር ብያለሁ ማለት... በመንፈስ የበላይ መሆን ነው። መብለጥ ነው። ገናና የሞራል ከፍታ ላይ መውጣት ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን ደስታን ወደ ህይወታችን የምንጋብዝበት መጥሪያ ካርድ ነው፡፡

@halalpic

Halal Profile Pictures|ሀላል ፕሮፋይል ፒክቸርስ

03 Oct, 17:06


መቼም ቢሆን እጅ አትስጥ
- በወደቅክ ቁጥር ተነስ
- በተሳሳትክ ቁጥር አስተካክል
- ባልተሳካልህ ቁጥር እንደገና ሞክር
- ህይወት ልታሳዝንህ በሞከረች ቁጥር
በግድም ቢሆን ፈገግ በል ።
👉@halalpic

Halal Profile Pictures|ሀላል ፕሮፋይል ፒክቸርስ

02 Oct, 17:57


🤝ለሰው ይቅርታ ማድረግ ያሉት ትሩፋቶች
☞ይቅር ስትል በትክክል መኖር
ትጀምራለህ ይቅር ማለት
የደካማዎች አይደለም።
☞የበደሉህን ይቅር ማለት የመንፈስ
ጥንካሬ እና በራስ የመተማመን
ምልክት ነው።
☞ይቅር ስትል ታድጋለህ።
☞ይቅር ስትል ልብህ ይሽራል።
☞ይቅር ስትል ቀጥ ብለህ ትቆማለህ።
☞ይቅር ስትል አይኖችህ ንፁህ
ይሆናሉ ከዚያም ፊት ለፊትህ ያለውን
መንገድ በግልፅ ታየዋለህ። ብስጩነት
የመንፈስ ህመም ነው።
☞ይቅር ስትል በትክክል መኖር
ትጀምራለህ!
Allah ይቅርታ የሚጠይቅ
አንደበትን
☞ይቅር የሚል ልብን ያድለን💞
@halalpic
@halalpic

Halal Profile Pictures|ሀላል ፕሮፋይል ፒክቸርስ

16 Sep, 05:23


ዛሬ እኮ ጁመዓ ነው ቀኑ በሰለዋት ይደምቃል ሁላችንም ሰለዋት እናውርድ
‏ﷺ
💞
💞
💞💞
💞💞
💞💞💞
💞💞💞
💞💞💞💞
.

💞
💞
💞💞
💞💞
💞💞💞
💞💞💞
💞💞💞💞
.
#ﷺ…

💎💦╰⇢💞💞💞⇢⇢╮💦💎
.
💎💦╭⇠⇠💞💞💞⇠╯💦💎
.
.
.
💞💞 صلى الله على محمد💞💞
💞💞 صلى الله على محمد💞💞
💞💞 صلى الله على محمد💞💞
.
.
@halalpic
@halalpic

Halal Profile Pictures|ሀላል ፕሮፋይል ፒክቸርስ

12 Sep, 15:41


አንዲት ሴት ወይዘሮ በባቡር ጉዞ ላይ ሳሉ አጠገባቸው ባለው ወንበር ላይ የተቀመጠ ሻንጣ አልተፈቀደምና ስለነበር አንድ ሠራተኛ መጥቶ ይህ ወንበር ለሰው መቀመጫ እንጂ ለዕቃ ማኖሪያ  እባክዎ ያንሱ ሲላቸው ‹‹አላነሳም›› አሉት፡፡

‹‹ቢያነሱ ይሻላል እምቢ ካሉ ላለቃዬ እነግራለሁ›› ቢላቸውም ‹‹ሂድ ንገር›› አሉት፡፡ ሂዶ ሲነግረው አለቅየው መጥቶ "ያንሱ እንጂ ለምን አላነሳም ይላሉ?" ብሎ ቢነግራቸው ‹‹አላነሳም›› በሚለው ሐሳባቸው ጸንተው የማይበገሩ ሆኑበት፡፡

በመጨረሻም ለዋናው ኃላፊ ተነግሮት ይመጣና ‹‹ይህን ሻንጣ ያንሱ›› ሲላቸው ‹‹አላነሳም›› አሉት፡፡ ዋና ኃላፊውም ‹‹ለምን?›› ሲላቸው ‹‹ገና አሁን አዋቂ ሰው መጣ፡፡ እኔ የቸገረኝ እኮ እስካሁን ድረስ ‹‹ለምን›› ብሎ የጠየቀኝ ባለመኖሩ ነበር፡፡ አንተ ‹‹ #ለምን ?›› ስላልከኝ አመሰግንናለሁ፡፡ በመሠረቱ ግን ሻንጣው የእኔ #አይደለም ሲሉት በመደነቅ ይቅርታ ጠየቃቸው፡፡

አብዛኞቻችን በሰዎች ላይ በደፈናው እንፈርዳለን፡፡ ነገር ግን ሁሌም በደፈናው ከመፍረዳችን በፊት "ለምን?" ብሎ መጠየቅም እውቀት ነው፡፡

@halalpic
@halalpic

Halal Profile Pictures|ሀላል ፕሮፋይል ፒክቸርስ

11 Sep, 14:45


❤️ሰዎች ልብህን ሊሰብሩት ሊያስከፉህ ሊያስቀይሙህ ይችላሉ፤ ታግሰህ ካለፍካቸው ፍቅር ገብቶሀል ማለት ነው። ፍቅር የገባውሰው ይቅር ይላል እንጂ እድሉን ሲያገኝ አይበቀልም፤ ከተበቀለ ደግሞ መቼም ሰላም አይሰማውም።

ወዳጄ በፍቅር ካላመንክ ትለፋለህ የትም አትደርስም! ታገኛለህ አትረካም! ትዘራለህ አታጭድም! ብታጭድም አንተ አትበላውም! ፍቅር ሁሌም ያሸንፋል!


@halalpic
@halalpic

Halal Profile Pictures|ሀላል ፕሮፋይል ፒክቸርስ

11 Sep, 14:36


#ሀላል profile pictures
@halalpic

Halal Profile Pictures|ሀላል ፕሮፋይል ፒክቸርስ

10 Sep, 13:29


#ሀላል profile pictures
@halalpic

Halal Profile Pictures|ሀላል ፕሮፋይል ፒክቸርስ

12 Aug, 05:59


ዛሬ እኮ ጁመዓ ነው ቀኑ በሰለዋት ይደምቃል ሁላችንም ሰለዋት እናውርድ
‏ﷺ
💞
💞
💞💞
💞💞
💞💞💞
💞💞💞
💞💞💞💞
.

💞
💞
💞💞
💞💞
💞💞💞
💞💞💞
💞💞💞💞
.
#ﷺ…

💎💦╰⇢💞💞💞⇢⇢╮💦💎
.
💎💦╭⇠⇠💞💞💞⇠╯💦💎
.
.
.
💞💞 صلى الله على محمد💞💞
💞💞 صلى الله على محمد💞💞
💞💞 صلى الله على محمد💞💞
.
.
@halalpic
@halalpic

Halal Profile Pictures|ሀላል ፕሮፋይል ፒክቸርስ

08 Aug, 17:28


ከጥሩ ጋር ዋል ጥሩ ትሆናለህ..!

አንድ አባት ከስራ ቦታው ሲመለስ ልጁን ከቦዘኔ ልጆች ጋር ሲጫወት ያየዋል ልጁን ጠራውና ልጄ ተው ከነሱ ጋር አትዋል ያበላሹሀል አለው። ''ኧረ አባቴ እኔ ከነሱ ጋር ጨዋታ ብቻ ነው ምጫወተው እነሱ ሚሰሩትን መጥፎ ስራ አልሰራም'' ሲል መለሰለት እና በተደጋጋሚ ቢመክረውም እንቢታውን ቀጠለበት። አባት ከቀናት ቡሀላ ከስራ ሲመለስ በካኪ ወረቀት የሆነ ነገር ይዞ መጣ እና እንካ ሳጥን ላይ አስቀምጠው ብሎ ሰጠው።

ልጁም አባቱ ያመጣውን ለማየት ጓጓና ከፍቷ አየው ልጁ ተደሰተ ያለበሰለ ፖም ነበር በዛ ላይ አንዷ ፍሬ ተበላሽታለች አና ላውጣት ተበላሽታለች ሲል አባቱን ጠየቀው አይ ተወው ዝም ብለህ አስቀምጠው አለው። እናም ከሳምንት በኋላ እስቲ ያንን ያስቀመጥከውን ነገር አምጣው አለው እናም ልጁ በጉጉት ይጠብቅ ስለነበር ደስ አለው ፖም እንደሚወድም ስለሚያቅ ልጁም ተስፈንጥሮ ተነስቷ አመጣና በጉጉት እና በተስፋ ካኪውን ከፈተው።

ነገር ግን ሁሉም የፖም ፍሬዎች ተበላሽተው ነበር ልጁ በጣም ተናደደና አየሀ አባዬ ያኔ የተበላሸውን የፖም ፍሬ ላውጣው ስለህ እሺ ብትለኝ ኖሮ ሁሉም አይበላሽም አለው አባትም ሌላ ካኪ ወረቀት አመጣና ሰጠው አሁንም ደስ ብሎት ከፍቶ ሲያይ ፖም ነበር ነገር ግን አባቱ አሁንም ያመጣው አልበሰለም እና ልጅ አልበሰለም እኳ ሲል ጠየቀው አባትም አዎ ሂድ ሳጥኑ ላይ አስቀምጠው አለው ልጅም እሺ ብሎ ከማስቀመጡ በፊት የተበላሸ እንደሌለው አረጋግጦ አስቀመጠው።

አሁንም ከሳምንት ቡሀላ አባት እስቲ ያንን ነገር አምጣው አለው ልጅም በደስታ እና በፍርሀት ስሜት ውስጥ ሆኖ ካኪውን አመጣው የፈራው እንደበፊቱ እንዳይበላሽ በመስጋቱ ሲሆን ደስ ያለው ደሞ ፖም ስለሚወድ ነበር እና ልጅ ካኪውን ከፈተው ማሻአላህ ሁሉም ሳይበላሽ በስለው ነበር ልጅም በጣም ደስ ተሰኘ እና አባት ያኔ ፖም ለምን የተበላሸ ይመስልሀል? ሲል ጠየቀው ልጅም "አንዱ ተበላሽቶ ስለነበር ሁሉንም አበላሻቸው እኔ ላውጣው ስልህ ባወጣው ኖሮ ሁሉም አይበላሽም ነበር" አለው።

አባትም "አየህ እኔም ከመጥፎ ጓደኞች ጋር አትዋል ምልህ ለዚ ነው ልክ እንደ ፖሙ ሁሉ አንተንም በጊዜ ሂደት እንዳያበላሹህ ነው የተበላሸውን ፖም ላውጣው ስትለኝ አውጣው ብልህ ኖሮ ሁሉም አይበላሽም ነበር አንተም ከመጥፎ ጓደኞች ጋር አትዋል ስልህ ካልዋልክ አትበላሽም ነገር ግን የኔን ምክር ችላ ብለህ ከነሱ ጋር ከዋልክ በጊዜ ሂደት እንደነሱ መሆንህ አይቀርም : በሌላ ቀን የመጣሁት ፖም ደግሞ ያልተበላሸው በአጠገቡ የተበላሸ ነገር ሰለሌለ ነው ከጥሩ ነገር ጋር ስላለ ነው ሰለዚህ አንተም ከጥሩ ጋር ከዋልክ ጥሩ ትሆናለህ"። "ከጥሩ ከዋልክ ጥሩ ትሆናለህ: ከመጥፎ ጋር ከዋልክ መጥፎ ትሆናለህ።

@halalpic
@halalpic

Halal Profile Pictures|ሀላል ፕሮፋይል ፒክቸርስ

22 Jul, 12:21


‍ ‍ ❤️በጣም የሚዋደዱ ባልና ሚስቶች በመሀላቸው አለመግባባት ይፈጠርና ይጋጫሉ.
...ባል ይናደድና ይደበድባታል።
ሚስት በጣም ታዝንና ታለቅሳለች
ባል ትቱዋት ወደ መኝታ ቤት ይገባና ይተኛል።
ሚስት ትንሽ ካሰበች ቡዋላ ወደ
መኝታ ቤትዋ ገብታ ትተኛለች።
ሲነጋ ባል ከተኛበት ሲነሳ ደንግጦ
ማልቀስ ይጀምራል።
ሚስት ጥቅልል ብላበት አቅፋው
ተኝታ ነበር....ለቅሶውን ሰምታ
ትነቃለች እንዲህም ትለዋለች....
እንዳስለቀስከኝ አስለቀስኩህ
ብድሬን መለስኩ ብላ እየሳቀች
ትስመዋለች ❤️😍እሱም
በጣም ተደስቶ አቅፎ ይስማታል።
❤️እሳትን በውሀ እንጂ.....
..በእሳት አታጠፋውም❤️
❤️ፍቅር ያሸንፋል❤️

@halalpic
@halalpic

Halal Profile Pictures|ሀላል ፕሮፋይል ፒክቸርስ

22 Jul, 12:16


መልካም ውጤት የሚገኛው ይቅርታ በማድረግ ብቻ ነው ። በተለይ የሰው ልጅ በድክመቱ ሳይሆን ሃይልና ብቃቱ እያለው መበቀል እየቻለ ለአላህ ብሎ ማለፍ ከቻለ እውነተኛ አሸናፊ ይሆናል ። ምክንያቱም ለአላህ ብሎ በይቅርታ ማለፍ የነብያትና የታላላቅ ሰዎች ባህሪ ነውና ።

@halalpic
@halalpic

Halal Profile Pictures|ሀላል ፕሮፋይል ፒክቸርስ

01 Jul, 03:28


ዛሬ እኮ ጁመዓ ነው ቀኑ በሰለዋት ይደምቃል ሁላችንም ሰለዋት እናውርድ
‏ﷺ
💞
💞
💞💞
💞💞
💞💞💞
💞💞💞
💞💞💞💞
.

💞
💞
💞💞
💞💞
💞💞💞
💞💞💞
💞💞💞💞
.
#ﷺ…

💎💦╰⇢💞💞💞⇢⇢╮💦💎
.
💎💦╭⇠⇠💞💞💞⇠╯💦💎
.
.
.
💞💞 صلى الله على محمد💞💞
💞💞 صلى الله على محمد💞💞
💞💞 صلى الله على محمد💞💞
.
.
@halalpic
@halalpic

Halal Profile Pictures|ሀላል ፕሮፋይል ፒክቸርስ

27 Jun, 03:15


በአንድ ዩኒቨርሲቲ የሳይኮሎጂ ዲፓርትመንት ውስጥ መምህሯ ተማሪዎቿን በምታስተምርበት ወቅት አንድ Assignment መስጠት ፈለገች።
ተማሪዎቿን ድንች ይዘዉ እንዲመጡ አዘዘች፡፡ ድንቾቹ ላይም የሚጠሏቸዉን ሰዎች ስም እንዲፅፉ አዘዘቻቸዉ። የሚያመጡት የድንች ብዛትም በሚጠሏቸዉ ሰዎች ብዛት ልክ እንዲሆን አለች፡፡

በሁለተኛዉ ቀን አንዳንዶቹ 3 ሌሎች 5 ቀሪዎቹ ደግሞ 8 ድንቾቹን የሚጠሏቸዉን ሰዎች ስም ፅፈዉ አመጡ። መምህሯ ደግሞ "ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት እኒህን ድንቾች በሻንጣችሁ ይዛችሁ ትዞራላችሁ...ሽንት ቤት ስትሄዱ እንኳ መተዉ አትችሉም!" ብላ አዘዘች፡፡

ቀኑ እየጨመረ ሲሄድ ድንቹ በመበላሸቱ ሽታዉ ይረብሻቸዉ ስለጀመረ ተማሪዎቹ ቅሬታ ማቅረብ ጀመሩ። በተለይም 8 የያዙት ከሽታው በተጨማሪ ክብደቱ እንደበዛባቸው መናገር ጀመሩ፡፡

ከሳምንት በኋላ የ"አሳይመንቱ" ገደብ ስላበቃ ተማሪዎች ድንቹን አዉጥተዉ እንዲጥሉ ተፈቀደላቸዉ::

ከዛም መምህሯ "እህ እንዴት ነበር?" ብላ ጠየቀቻቸው። ሁሉም ማጉረምረም ጀመሩ ..."ኧረረረ ከክብደቱ ሽታዉ...ኧረ በጣም ነዉ የሚያስጠላዉ"...አሉ።

መምህሯም "አያችሁ በልባችሁ የምትሸከሙት ጥላቻም እንዲሁ ነዉ...ጥላቻ ልብን ይመርዛል በምትሄዱበት ሁሉም እየተከተለ ይረብሻችኋል...ለአንድ ሳምንት የተበላሸ ድንችን ሽታ መቋቋም አልቻላችሁም። አስቡት ደግሞ በጥላቻ የተመረዘን ልብ እድሜ ልካችሁን ይዛችሁ ስትኖሩ!!" አለቻቸዉ። ጥላቻን ከዉስጣችሁ አዉጡትና ከእዳ የፀዳችሁ ሁኑ!!

እዉነተኛ ፍቅር እንከን አልባን ሰዉ ማፍቀር ሳይሆን ንፁህ ያልሆነን ሰዉ በንፁህነት መዉደድ ነዉና!!!

@halalpic
@halalpic