Ethio unverstye @habshamusi Channel on Telegram

Ethio unverstye

@habshamusi


Ethio unverstye ይህ chanal
ኢትዮጵያ ውስጥ ስላሉ ዩኒቨርስቲዎች መረጃ
የሜቀርብ chanal

ዋና አላማውም ለተማሪዎች በቀላሉ የትምህርት መረጃዎችን, ኖቶችን, Test, ና,EUEE ጥያቄያዎችን ለማድረስ ነው።
Grade 12 &11 text book
Teacher guide
Short Notes each subjects
@ethioUniversity

Ethio unverstye (Amharic)

ኢትዮ ዩኒቨርስቲ የመረጃችንን ዝርዝር ለተጠቃሚዎች! ይህ አመት ምሳሌ ኖት, መረጃዎች, ለተማሪዎች በቀላሉ ትምህርት መረጃዎች, ለኖቶች የመረጃዎችንና EUEE ጥያቄያዎችን ለመሰራት ይህን አዲስ አገልግሎት ለማድረስ ያሰባሰቡ ስራዎችን ለጥሩነቷ ትምህርት እና ትምህርት ወሳኝ መረጃዎች, ሴትና ወንድ አቀባብሎችን ያጋሩት! አሁን እስከ ትምህርት እንደምትታዘዙ ፔስኮ እምነትና ፣ ሰአት ጽፎባችሁ, እና ማናዳት ሰጋን ጋር ለሚታይ ወሳኝ መረጃዎች እንደምንሰማም እናደርሳለን! አብደሻል! @ethioUniversity

Ethio unverstye

31 Jan, 10:36


ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የሬሚዲያል ፈተና መዘጋጀቱ ተማሪዎቹን ሊያዘናጋ እንደሚችል ተገለጸ።

የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈታናን ማለፍ ላልቻሉ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሬሚዲያል ፈተና መዘጋጀቱ ተማሪዎች አማራጭ እንዳላቸው እንዲያስቡ እንደሚያደርጋቸው እና እንደሚያዘናጋቸው የትምህርት ባለሙያዎች ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቀዋል፡፡

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈታናን ወስደው ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ማምጣት ላልቻሉ ተማሪዎች በዩንቨርስቲዎቹ ውስጥ የሬሚዲያል ፈተና መዘጋጀቱ ተማሪዎቹን እንደሚያዘናጋቸው የትምህርት ባለሙያው አቶ ቢኒያም ገ/እየሱስ ተናግረዋል፡፡

ሌላኛው የትምህርት ባለሙያ ዶ/ር አለማየሁ ከበደ የአቶ ቢንያምን ሃሳብ በማጠናከር ተማሪዎቹ አሁን ላይ #ባናልፍም ሬሚዲያል እንወስዳለን በሚል ተስፋ ትምህርታቸው ላይ ትኩረት አያደርጉም ብለዋል፡፡

በድጋሚ ለመፈተን በዩንቨርስቲዎች ውስጥ የሚቆዩት አንድ አመት ቢሆንም መንግስትን ላልተገባ ወጪ የሚዳርግ በመሆኑ ትኩረት ተደርጎበት ከስር ከመሰረቱ ሊሰራ እንደሚገባ ባለሞያዎቹ አመላክተዋል፡፡


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

Ethio unverstye

28 Jul, 18:32


#MoE

ከ2016 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ይሰጣል።

ትምህርት ሚኒስቴር ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች ቅበላን በተመለከተ በላከው ደብዳቤ እንዳሳወቀው፥ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና (Graduate Admission Test) ይሰጣል።

ሚኒስቴር ባደረገው ክትትልና ግምገማ "ጥቂት በማይባሉ የመንግሥትና የግል ትምህርት ተቋማት የድህረ ምረቃ ለመማር የሚያመልክቱ ተማሪዎች ምንም አይነት የመመዘኛና የመግቢያ ፈተና እንዳማይወስዱ" ለማወቅ መቻሉን ገልጿል፡፡

በመሆኑም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ በ2016 ዓ.ም ተማሪ የሚቀበሉባቸውን የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች (የፀደቁና ፈቃድ የተሰጣቸው) ዝርዝር እስከ ነሐሴ 20/2015 ዓ.ም እንዲያሳውቁ ተብሏል።

ተቋማቱ የተልዕኮና ትኩረት ልየታን መሰረት በማድረግ ለድህረ ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች ማስታወቂያ በማውጣትና በመመዝገብ ዕጩ ተማሪዎቻቸውን እስከ መስከረም 10/2016 ዓ.ም ሚኒስቴሩ ማሳወቅ እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል።

የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና (Graduate Admission Test) ለተቀራራቢና ተመሳሳይ ፕረግራሞች በጋራ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፈተና ማዕከል ከመስከረም 20 እስከ 28/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

(ሚኒስቴሩ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የጻፈው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል።)

More : @tikvahuniversity

Ethio unverstye

24 Jul, 17:53


# *የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መርሃ ግብርን ይፋ አድርጓል።*

Ethio unverstye

19 Jun, 18:05


ባህርዳር ዩኒቨርስቲ Exit Exam ያለለፈ ተማሪ አይመረቅም ብሏል።😢
👇👇👇👇👇

ከውይይቶች መረዳት እንደተቻለው አንዳንድ አካዳሚክ ክፍል ሬጅስትራሮች በስርዓተ ትምህርቱ የተቀመጡ ሁሉንም ኮርሶች አጠናቀው ሳይመዘገቡ ወይም “F” ያላቸውና ቀጣይ ሴሚስተር መመዝገበ የሚያስፈልጋቸው ጥቂት ተማሪዎች ስማቸውን ስመውጫ ፈተና ጨምረው መላካቸውን ተረድተናል፡፡

ስለሆነም ትምህርት ሚኒስቴር በሰጠው አቅጣጫ መሰረት👇

1ኛ:- ኮርስ አጠናቀው ያልተመዘገቡ እንዲሁም ያልተመዘገቡትና ያልፋቁት "F" ያላቸው ተማሪዎች በስህተት ለመውጫ ፈተና ዝርዝራቸው የተላኩ ካሉ የመውጫ ፈተና እንደማይፈተኑ ከወዲሁ እንዲነገራቸውና የመውጫ ፈተና ኮርስም እንዳይመዘገቡ፤

2ኛ:- ከላይ በተራ ቁጥር 1ኛ በተገስፀው መሰረት የመውጫ ፈተና መመዝገብ የሚችሉት ብቻ ኮርሱን እንዲመዘገቡና የምዝገባ ስሊፕ ለመውጫ ፈተና መግቢያ እንዲያገለግላቸው ከወዲሁ ለተማሪዎች እንዲሰጣቸው፤

3ኛ:- ለምረቃ መሟላት ከሚገባቸው መመዘኛዎች በተጨማሪ የመውጫ ፈተና ያለፉ (50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ) ብቻ ለምረቃ እንዲቀርቡ፤

4ኛ:- የምረቃ መስፈርቱን ያሟሉና የመውጫ ፈተና ያስፉ ብቻ የመመረቂያ ጋዎን አንዲሰጣቸው በጥብቅ አሳስባለሁ ብሏል።

መቻል ነው እንግዲህ🥺🥺🥺

ምንም አይነት እንከን ያለበት አካል እንዳልተማረ ነው የሚቆጠረው።

ለማንኛውም Exit-Exam ተፈታኞች ጠንክራችሁ አንብቡ።

በትምህርታችሁ ላይ እየቀለዳችሁ ያላችሁና ግቢ Life ምናምን የምትሉ ተማሪዎች ደግሞ ከወዲሁ እራሳችሁን አዘጋጁ።

መመረቅ የሚፈልግ ምንም እንከን አይኑርበት ያለበትም ከወዲሁ ያስተካክል🙏🙏

#Share_Share

Join Us
👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 @Ethio_Universty 👈
👉 @Ethio_Universty 👈
👉 @Ethio_Universty 👈
👆👆👆👆👆👆👆👆

Ethio unverstye

17 Dec, 10:43


የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የ2ኛ እና የ3ኛ ዓመት ተማሪዎች አድማ በመምታት ትምህርት ማቋረጣቸውን ሰምተናል።

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የሁለተኛ እና ሶስተኛ ዓመት ተማሪዎች ያለ አግባብ የምንመረቅበት ጊዜ በተለይም የ2013 ባች ተማሪዎች እስከ ሁለት ሴሚስተር ያህል ማለትም ከመመረቂያ ጊዜያችን አንድ ዓመት ዘግይተን እንድንመረቅ ዩንቨርሲቲው ወስኗል በሚል ምክንያት ተቃውሟቸውን ክፍል ባለመግባት እየገለፁ እንደሆነ ከተማሪዎቹ ያግኘነው መረጃ ያመለክታል።

በጉዳዩ ላይ ግልፅ ውይይት ለማድረግ ኮሚቴ አዋቅረን ጥረት ብናደርግም ዩንቨርሲቲው የኛን ጥያቄ ከመስማት ይልቅ በርካታ ቁጥር ያላቸው የፀጥታ አካላትን በማሰማራት ማስፈራሪያ እያደረሰብን ነው ሲሉ ከሰዋል።

ቤተሰቦቻችን ከኛ ብዙ ነገር ይጠብቃሉ የሚሉት ተማሪዎቹ በሌሎች ዩንቨርሲቲዎች ከሚገኙ ጓደኞቻችን እኩል መመረቅ ባለብን ካላንደር መሰረት ተመርቀን ተወዳዳሪ እንሁን ማለታችን እንደ ስህተት ተወስዶ አግባብነት ያለው ጥያቄያችን በጉልበት ሊታፈን አይገባም ብለዋል።

Ethio unverstye

07 Aug, 09:43


#ትምህርት_ሚኒስቴር

የ2014 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በ12 ኮድ (በጥያቄ አቀማመጥ ስብጥር) ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው።

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከዚህ በፊት እንደነበረው በ4 ኮድ (4 የተለያዩ ፈተናዎች/በጥያቄ አቀማመጥ) ሳይሆን እስከ 12 እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

ይህ የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ከሚሰሩት ስራዎች መካከል አንዱ መሆኑን የሚገልፁት ፕ/ር ብርሃኑ ጎን ለጎን ያሉ ተማሪዎች እርስ በእርስ የሚፈተኑት ፈተና የጥያቄው ዝርዝር (order) በፍፁም የተገናኘ እንዳይሆን እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ፈተናው በዩኒቨርሲቲዎችና በፌዴራል ተቋማት እንደሚሰጥም ገልፀዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢፕድ የሰጡት ቃል፦

" ...የክልል ባለሟሎች፣ የክልል ኃላፊዎችን ከፈተና ጉዳይ ጋር እንለያቸው ፤ ፈተናው እራሱ የፌዴራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ስለሆነ በፌዴራል ተቋማት ውስጥ ብቻ እንስጥ ብለን አሁን በሙሉ ተማሪዎቹን አጓጉዘን ቢቻል ሁሉንም ከክልላቸው ውጭ በሆኑ ክልሎች ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እና የፌዴራል ተቋማት ውስጥ ለመስጠት ነው እየተዘጋጀን ያለነው።

ያ የሚያደርገው ሁለት ነገር ነው። አንደኛ በመንገድ ላይ ሊኖር የሚችለውን የመሰረቅ አደጋ ይቀንሰዋል። ሁለተኛ ክፍል ውስጥ ከተገባ በኃላ ለመስረቅ የሚቻልበትን አደጋ ይቀንሰዋል።

ከዛም በላይ ፈተናዎቹን በማዘጋጀት ደረጃ በፊት በ4 የተለያዩ ፈተናዎች ነበር የምናዘጋጀው እስከ 12 አድርገን Completely scrambled እንዲሆኑና ማንም ጎኑ ያለው ተማሪ የሚፈተነው ፈተና አንተ ከምትፈተነው ፈተና order ጋር በፍፁም ያልተገናኘ እንዲሆን አድርገን እየሰራን ነው።

ይሄ በጣም በብዙ ደረጃ የፈተና ስርቆትን ይቀንሰዋል ብለን ነው ተስፋ የምናደርገው።


@University_Ethiopia_Mereja
@University_Ethiopia_Mereja

Ethio unverstye

07 Aug, 09:43


መንግስት ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተጠናውን JEG ያለምንም ማቅማማት ይተግብርልን!!!
በሀገራችን ታሪክ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በየጊዜው ከሀገራችን እና ከውጭ ሀገር የሚመረቁ እንቁ እና ባለምጡቅ አእምሮ የሆኑ በአካዳሚያዊ ዝግጅት እና ብቃት እንዲሁም ስነምግረባራዊ ባህርይ የተሻሉት ምሁራን የሚገኙበት እና የሚቀጠሩባቸው ተቋማት ናቸው፡፡ ህልጊዜም በሀገራችን በተለይም የከፍተኛ ትምሀርት መስፋፋት ከጀመረባቸው ጊዜያት አንስቶ በሀገሪቱ ካሉ የዩኒቭርስቲ ምሩቃን የተሸሉ እና ውጤታማ የሚባሉት እየተመረጡ የሚሰሩበት፣የሚያስተምሩበት እና የሚመራመሩባቸው ተቋማት ናቸው፡፡
ይሁን እንጂ እኒህ የሀገሪቱ እንቁ አካላት የሚያገኙት ጥቅማጥቅም እና ደመወዝ አሁን ላይ ከቀን ሰራተኛ ያልተሻለ ሆኗል፡፡ ዛሬ ላይ አንድ የቀን ሰራተኛ በጉልበቱ ሰርቶ የሚያገኘው ገቢ በማካኝ ከ250 እስከ 300 ብር ሆኗል፡፡ይህ ግለሰብ በአማካኝ275 ብር ቢያዝ 8250 ብር በወር የተጣራ ገንዘብ ወደ ኪሱ ያስገባል ማለት ነው፡፡ አንድ ከፍተኛ ውጤት አምጥቶ እና የወቅር ተሸላሚ ሆኖ በዩኒቨርስቲ አስተማሪነት የቀረ የዩኒቨርስቲ መምህር በሌክቸረር ማዕረግ በወር የሚያገኘው የተጣራብር 8056 ብር ነው፡፡ ከጉልበት ሰራተኛ ያነሰ ማለት ነው! አቤት ንቀት እና ውርደት፡፡ በነገራችን ላይ ይህ ሆን ተብሎ ሞራላችን ላይ ለመጫወት የተደረገ ሁሉ ይመስላል፡፡ ለምን ቢባል የሚገዙን እና እና እያስተዳደሩን ያሉት በእውቀትእንበልጣቸወው የነበሩ አካላት የበታችነት ስሜት ይመስለኛል እንዲህ ሀገርን ወደኋላ እየወሰዷት ያሉት!!
የትምህርት፣የሲቪል ሰርቪስ እና የገንዘብ ሚኒቴር አሁንም በከፍተኛ ትምሀርት መምህራን እና ተመራማሪዎች ላይ የሚያደርሱትን ቁማር አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡
ወደ ዋናው ነገር ልግባ
በሀገራችን ባሉ የመንግስት ተቋማት እንደ ስራ ጫናው ሁኔታ እና ለሀገር ከሚያበረክቱት አስተዋጽኦ አንጻር የራሳቸው የደመዎዝ እስኬል እና ልዩ ልዩ የማበረታቻ ኬጆች( የቤት አበል፣ የስልክ፣ የነዳጅ/ትራንስፖርት/ ወዘተ) ተጠንቶ በሲቪል ስርቪስ ሚኒስቴር እና ገንዘብ ሚኒስቴር ጸድቆላቸው እየተተገበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ለአብነት ያህልም የክልል እና የፌደራል የህግ ባለሙያዎች፣አቃቢያነ ህግ ዳኞች እና ሹማምንት፣የኢትዮጵያ ግብር እና ምርምር እና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና የምርምር ተቋማትን ማንሳት ይቻላል፡፡( የእነዚህ ድርጅቶች ተልእኮ የተወሰነ እና አንድ እና እንድ ነገር ላይ ብቻ ትኩረት ያደረገ መሆኑን ሊብ ይሏል!)፡፡ ይሁን እንጂ የከፍተኛ ትምሀርት ተቋማት መምህራን ሶስት ተልዕኮዎች(ማስተማር፣ ምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት) ተሰጥቷቸው የሚያገለግሉ ቢሆኑም ቅሉ መንግስት የእነሱን ችግር እና ኢኮኖሚያዊ እና ሙያዊ ጫና ግምት ውስጥ ያላስገባ እና በባለሙያ ተጠንቶ የቀረበለትን ማስተካከያ ወደ ጎን በመተው እና ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት የእራሱን የፌዝ ደብዳቤዎች መጻጻፍ ጀምሯዋል፡፡ በተለይ ደግሞ የከፍተኛ ትምህርትን ያስተባብራሉ ተብለው በልዩ ልዩ የመንግስት የሃላፊነት ደረጃዎች(ሚኒስቴር፣ ዴታዎች፣ እና ዳይሬክተር ጀነራሎች) የተቀመጡ አካላት ከፍተኛ የሆነ ለከፍተኛ ትምህርት መምሀራን ንቀት ያላቸው ፌዘኞች መሆናቸው እና የተጠናላቸውን የሀገሪቱን የመክፈል አቅም እና የስራ ጫና ታሳቢ ያደረገ ጥናት ወደ ጎን በመተው ይራሳቸውን ግላዊ ፍላጎት ለማስፈጸም መጣደፋቸው የግለሰቦችን ግላዊ እና ተቋማዊ ማንነት የሚያሳይ አጉሊ መነጽር ነው፡፡
እነሆ የከፍተኛ ትምርት መምሀራን በዲሞክራሲዊ አካሄድ በተወካዮቻቸው በኩል አቤቱታቸውን ያቀረቡ ቢሆንም ቅሉ ከአንድ ዓመት በኋላ የተሰጣቸው ምላሽ ግን እጅግ ሞራላዊ እና ሰባዊ ስነልቦናቸውን የሚጎዳ ነው፡፡
ስለሆነም አሁንም አልመሸም ፣አልረፈደም እና የሚመለከተቸው አካላት አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጡ እና የተጠናውን የደመወዝ እስኬል እንዲተገብሩ እያሳሰብን ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን ወደ ሌሎች የትግል አማራጮች የሚንሄድ መሆኑን ማስገንዘብ እንወዳለን፡፡
ድምጻችን ይሰማ፤ሳይበላ የሚሰራ የለም!
በጋራ እንችላለን!!
ከመምህራን ተወካዮች አንደበት

Ethio unverstye

30 Jun, 17:56


የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መቼ ይሰጣል ?

የትምህርት ሚኒስቴር የብሄራዊ ፈተና መሰረቅንና ኩረጃን ለመከላከል ፈተናው በኦንላንይ መስጠት እስኪጀመር ድረስ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንዲሰጥ መወሰኑ ይታወቃል።

የፈተናውን አሰጣጥ ሂደትን በተመለከተ ለጊዜው በዝርዝር የሚታወቅ ነገር የለም።

ከዚህ ቀደም የ2014 ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 20 / 2015 ዓ/ም በኃላ እንደሚሰጥ መገለፁ የሚዘነጋ አይደለም ፤ እስካሁን ድረስ የተቀየረም ሆነ በትምህርት ሚኒስቴር የተገለፀ አዲስ ነገር የለም።

ከትላንት ጀምሮ በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች ፈተናው ሃምሌ እና ነሃሴ ላይ ነው የሚሰጠው እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ምንጩ ያልታወቀና ሀሰተኛ በመሆኑ ተማሪዎች በተረጋጋ መንፈስ በጥናታችሁ ላይ እንድታተኩሩ ወላጆችም ልጆቻችሁ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ እገዛችሁን እንድታጠናክሩ ይሁን።

እጅግ በርካታ ተማሪዎች እንዲሁም ወላጆች የሚከታተሉት የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ጉዳይን በተመለከተ ከትምህርት ሚኒስቴር ውጭ የሚወጡ መረጃዎችን አምናችሁ አትቀበሉ። አንድን መረጃ ስትሰሙ ከትምህርት ሚኒስቴር መሆኑን አረጋግጡ።

@tikvahethiopia

Ethio unverstye

30 Jun, 17:39


የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲዎች ዉስጥ እንደሚሰጥ ተገለፀ።
=============================================
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሆሳዕና ፣ በወራቤና በወልቂጤ ከተሞች የሚገኙ ሁለተኛ ደረጃና ሞዴል ትምህርት ቤቶችን ጎብኝተዋል።

በጉብኚታቸዉ ወቅት ከተማሪዎችና ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ጋር ባደረጉት ቆይታ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በትምህርት ቤቶች ሳይሆን በዩኒቨርስቲ ውስጥ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

እንደሚኒስትሩ ገለጻ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በኤሌክትሮኒክስ /online/ መስጠት እስከሚጀመር ድረስ በዩኒቨርስቲዎች መሰጠቱ ይቀጥላል ።

የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲ እንዲሰጥ የተወሰነው የፈተና ሰርቆትና ማጭበርበርን ለማስቀረት ታስቦ በመሆኑ ተማሪዎች ትምህርት በስራና በታታሪነት የሚገኝ መሆኑን አውቀው በርትተው መማርና ማጥናት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርትን ጥራትን ለማሻሻል በአጠቃላይና ከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፎች ሌሎችንም የተለያዩ እርምጃዎች በመውሰድ ላይ መሆኑንም ፕሮፌሰር ብርሀኑ ጠቁመዋል።

ሚኒስትሩ ሶስቱንም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የጎበኙ ሲሆን የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ ችግኝም ተክለዋል፡፡

🎯 ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ
💥💥💥💥💥💥💥💥

Ethio unverstye

30 Jun, 17:38


💥💥ስኬት

💎አንድ ሰውዬ ሁለት ሴት ልጆቹን የተለያየ ሙያ ላላቸው ሰዎች ዳረ፡፡


አንደኛዋን ለገበሬ
ሁለተኛዋን ደግሞ ለሸክላ ሠሪ ነበር የዳረው፡፡

💥ከዓመት
በኋላም ሊጎበኛቸው ሄደ፡፡ የገበሬው ሚስት ዘንድ ሄደ፡፡ በአባቷ መምጣት
ተደሠተች፡፡ ‹ኑሮ እንዴት ነው?› አላት፡፡ ‹ ባለቤቴ መሬት ተከራይቶ የዘር
እህልም ተበድሮ ነው የዘራው፡፡ ዝናብ ካልጠፋ እናተርፋለን፤ ድርቅ ከሆነ
ግን ችግር ላይ እንወድቃለን፡፡› አለችው፡፡
.
💎ወደ ሁለተኛይቱም ሄደ፤ ተደስታና በፍንደቃ ተቀበለችው፡፡ ‹ኑሮ እንዴት
ነው?› አላት፡፡ ‹ባለቤቴ ለሸክላ የሚሆን አፈር ተበድሮ ነው የገዛው፡፡ አሁን
ብዙ የሸክላ ዕቃዎች ሠርቷል፡፡ ፀሐይ ከሆነ እናተርፋለን፤ ዝናብ የሚሆን
ከሆነ ግን አደጋ ውስጥ ነን› አለችው፡፡


💎ሰውዬው ወደ ቤቱ ተመለሠ፡፡ ሚስቱም ስለ ልጆቿ ሁኔታ ጠየቀችው፡፡
‹ከዘነበም አላህን/ፈጣሪን አመስግኚ፤ ካልዘነበም አላህን/ፈጣሪን አመስግኚ፡፡› አላት፡፡
እሷም ‹በሁሉም ሁኔታ ውስጥ ምስጋና ለአላህ/ፈጣሪን ይሁን፡፡› አለች፡፡
.
🔰ዓለማችን ሁኔታዋ እንዲህ ነው እንግዲህ፡፡ ለኛ የሚያስፈልገን ለሌላው
ላያስፈልግ፣ ለኛ የተመቸን ለሌላው ላይመች፣ ለኛ የሕይወት ጉዳይ የሆነ
ለሌላው ምንም ላይሆን ይችላል፡፡

መልካም ቀን ተመኘሁ❤️❤️

Ethio unverstye

30 Jun, 17:35


#WolkiteUniversity

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት በ2014 ዓ.ም የሚመረቁ ተማሪዎችን አጽድቋል።

ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 53 ተማሪዎች ቅዳሜ ሰኔ 25/2014 ዓ.ም ያስመርቃል።

ከተመራቂዎቹ 64ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት የሦሥት መምህራን የሥራ አፈጻጸም በመገምገም የማዕረግ እድገትም ሰጥቷል።

1. ብርሀኑ አራጌ (ዶ/ር) ~ ከፊዚክስ ት/ት ክፍል ከረዳት ፕሮፌሰርነት ወደ ተባባሪ ፕሮፌሰርነት
2. ሳሙኤል ደሱ ~ ከኅብረተሰብ ጤና ት/ት ክፍል የረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው
3. ሂርፓሳ ተሬሳ ~ ከባዮሎጂ ትምህርት ክፍል
የረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው

🎯 ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️
https://t.me/+5UtUmeE0OYAwOGU8
https://t.me/+5UtUmeE0OYAwOGU8
💥💥💥💥💥

Ethio unverstye

30 Jun, 17:34


Channel photo updated

Ethio unverstye

30 Jun, 17:33


Channel name was changed to «Ethio unverstye»

Ethio unverstye

26 Jun, 11:46


Channel name was changed to «የድሮ ሙዚቃዎች»

Ethio unverstye

14 Jun, 12:02


#ወላጆች_ለልጆች_ጥንቃቄ_እንዲያደርጉ_አሳስቧቸው !

ትናንትና በአዲስ አበባ ከተማ በጣለው ዝናብ አንድ ተማሪ በጎርፍ እንደተወሰደ ተሰምቷል።

የአዲስ አባባ እሳትና ድንገተኛ አደጋ የኮሙኒኬሽን ተማሪው በጉለሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ላዛሪስት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርት ቤት ተማሪ መሆኑን አመልክቷል።

ተማሪው በጎርፍ የተወሰደው ትላንት 9 ሠዓት አካባቢ በጣለው ዝናብ መሆኑን የገለፀው ኮሚኒኬሽኑ በጎርፉ የተወሰደው ተማሪ በትምህርት መውጫ ሠዓት ላይ ከትንሽ ወንድሙ ጋር ወደ ቤት እየሄዱ እንደነበርም አስረድቷል።

እስከዛሬ ጠዋት የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ሠራተኞቹ ከኅብረተስቡ ጋር በመሆን ተማሪውን የመፈለጉን ሥራ ቀጥለዋል ተብሏል፡፡

ወላጆች በክረምቱ ልጆቻቸውን ወደ ት/ቤት ሲልኩ ሆነ ሲቀበሉ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉላቸው የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ማሳሰቡን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

#ኤፍቢሲ

ለተማሪዎች ሼር አርጉላቸው!👇👇

https://t.me/Tmhrt_Minister
https://t.me/Tmhrt_Minister