አልሀምዱ ሊላሂ ይገባው ምስጋና
ለደነገገልን ዘዋጅን በሱና
አግቡ አትጨነቁ ከላይ ነው እርዚቁ
እንደውም ሰበብ ነው ለሀብት ብታውቁ
እስኪ ይናገሩ ወላጆች በየቤት
ምን ነበር ሲጋቡ የነበራቸው ሀብት
ትንሽ ቆም ብለው ያስታውሱት ለትዝብት
ድህነትን ፈርተህ ድሀ ሆነህ አትኑር
ይልቅ ወንጀል ፍራ ወንድሜ ያዝ ትዳር
አበሰረች ሌራ ~~ ኡስታዟን ሞሽራ
ትዳርህም ያብብ ደዕዋህም ይስፋፋ
ያ አባ አብዲላህ ያ ኡስታዝ ሙሰፋ
አሏህ ያድርግልህ ኢልምህን በረካ
ደግሞም ይወፍቅህ ለሀጅ ወደ መካ
አበሰረች ሌራ ~~ ኡስታዟን ሞሽራ
ብርዱንም ደርሱንም አግኝተሀል አጋዥ
የልብህ ማረፊያ ትሁንልህ ታዛዥ
ጠብ እርግፍ ብለሽ ተንከባከቢያቸው
ባል ብቻ ሳይሆኑ ኡስታዝሽም ናቸው
ሀቃቸው ቢከብድም አደራ ጠብቂ
በለሊት ዱዓቸው እንድትመረቂ
እርሶዎም ሸሆቹ ገና ሳያገቡ
የሴት ልጅን አኽላቅ ቆዪ ካነበቡ
በጀዎት ነው እና ሀዲሱም ኪታቡ
በትግስት ይያዙ ጠበቅ አርገው ሙጭጭ
ቀምሰውታል እና የዚህን ሀገር ውርጭ
እንኳን በነጠላ በስሱ ብርድ ልብስ
ይበርድሀል ሌራ ደራርበህም ብትለብስ
ሻዎር ያለቦይለር
ትራሱ ያለ…… ር
አይቻልም ሌራ
ከጎንህ ከሌለ ብርዱን የሚጋራ
ከንግዲህ ኡስታዜ~~ ለዚህ ቅዝቃዜ
አግኝተሀል ጋሻ~~ብርዱን ማስታገሻ
አሏህ ይጨምርህ አሁንም ሲልድ እሽግ
ማለቴ ስልክ ነው ሀዋዊ ወይ ሳምሰንግ
ግጥም ከሌለበት ቀልድና ነቆራ
በምኑ ይለያል ከስድ ሙሀደራ
ብሎኛል አንድ ወዳጅ
ረሂመሁሏህ በሀያት እያለ
ድሮ ሳይዘወጅ
بارك الله لكما وبارك عليكما وجمع بينكم في خير
عمر
https://t.me/Efadalezd_lebada/5839