GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH @grace_truth Channel on Telegram

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

@grace_truth

GRACE_TRUTH "My worth to God in pubilc is what I am in private" INTEGRITY

Manifesting church

Exalt the lord
Equip the church
Evangelize the world
Edify the body

የዓላማ ሰው purpose
የቅድስና ሰው Integrity
የኃይል ሰው power
የልዕቀት ሰው Excellence

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry (English)

Are you looking to deepen your understanding of the Bible and connect with others in prayer? Look no further than the GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry on Telegram! Our channel, @GRACE_TRUTH, is dedicated to providing a space for individuals to grow in their faith and relationship with God through studying the Bible and coming together in prayer.

Who are we? We are a community of believers who believe in the power of God's Word and the importance of prayer in our daily lives. Our mission is to manifest the church by exalting the Lord, equipping the church, evangelizing the world, and edifying the body of Christ.

What can you expect from our channel? Daily Bible study resources, prayer prompts, and opportunities to engage with fellow believers in discussions about faith and spirituality. Whether you are a seasoned Bible scholar or just starting your spiritual journey, there is something for everyone at GRACE & TRUTH.

Join us today and experience the transformative power of God's grace and truth in your life. Together, we can grow in our understanding of the Bible, deepen our prayer lives, and strengthen our relationship with God. Let's journey together towards a deeper faith and a closer walk with the Lord. We look forward to welcoming you to our community of believers on @GRACE_TRUTH!

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

27 Jan, 01:35

🔥ለመማር ልባችሁን ክፈቱ🔥

✝️አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፤ ዓይኖቼን በአንተ ላይ አጠናለሁ።”
 — መዝሙር 32፥8

🔥በአንድ ቤተክርስትያን ሥር ለመተከል በመንፈስ መመራት ያስፈልጋል።ሰዎች የቤተክርስትያን አባል የሚሆኑት በተለያየ ምክንያት ቢሆንም ከአካል ብልት መለየት ስለማይችል ተገቢ አይደለም ፤ነገር ግን ዋነኛ የቤተክርስትያን አባል መሆናችንን ሊወስን የሚገባው የመንፈስ ምሪት ነው።

👉በእርግጥ ቤተክርስትያን ልትሰብክና ልታስተምር የሚገባው ወንጌል ብቻ ነው።ትልቁ የቤተክርስትያን አባል ለመሆን ወሳኙ ግን የመንፈስ ምሪት ነው።አባል የምትሆኑበት ቤተክርስትያን መጋቢያችሁ ወይም አረኛችሁ ማን እንደሚሆን ይወስናል።

✝️መጽሐፍ በት ኤር 3፥15 ላይ ሲናገር “እንደ ልቤም በግ ጠባቆችን እሰጣችኋለሁ፥ በእውቀትና በማስተዋልም ይጠብቁአችኋል።”ይላል።

🙏እንደ ልቡ የሆነ መጋቢ የሚሰጣችሁ እግዚአብሔር ነው።ቤተክርስትያናችሁን ወይም መጋቢያችሁን የምትመርጡት እናንተ አይደላችሁም።
እግዚአብሔር በቤተክርስትያን ውስጥ እንድትተከሉ በማድረግ ለሕይወት አስልጥኖ ብቁ የሚያደርጋችሁን ፓስተር ይሰጣችኋል።

✝️በመዝሙር 84፥6 ላይ ሲናገር “በወሰነው ስፍራ የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና።”ይላል።እርሱ በወሰነላችሁ ስፍራ ስትሆኑ ነው፤ከበረከታችሁ ጋር የምትገናኙት።በቃሉ የምትሰለጥኑበት ቦታ ነው እናንተ ለሕይወትና ለአሸናፊነት ብቁ የሚያደርጋችሁ።

🙏ቦታችሁን ስታዉቁ የመንፈስ እረፍትና ሰላም ይሰማችኋል።ከላይ በመግቢያ ላይ ያለውም ክፍል “አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፤ ዓይኖቼን በአንተ ላይ አጠናለሁ።”ይላል።ትሑት ብትሆኑና ጌታ እንዲመራችሁ ብትፈቅዱ በቃሉ ወደምታድጉበትና ወደ ትክክለኛ ቦታ ይመራችኋል።

🔥ጸሎት🔥

ውድ አባት ሆይ በሕይወቴ ስላለው የአንተ ምሪትአመሰግንሃለሁኝ። በቤተክርስትያን ውስጥ በመተከል በቃልህ ሥር ሰድጄ አድጋለሁኝ። በውጫዊ ነገር ላይ ሳይሆን በቤተክርስትያን ውስጥ በሚለቀቀው ቃል ላይ አተኩራለሁኝ።በቃልህ  ውስጥ ስለተተከልኩኝ ሁልጊዜ አፈራለሁኝ።

🔥በኢየሱስ ስም አሜን🔥

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

27 Jan, 01:35

Shalom Shalom

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

27 Jan, 01:18

🔥ዛሬ የምናሰላስለው ቃል🔥

🔥Galatians 4 (KJV)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ And because ye are sons, God hath sent forth the Spirit of his Son into your hearts, crying, Abba, Father.
⁷ Wherefore thou art no more a servant, but a son; and if a son, then an heir of God through Christ.

HAVE A GOOD ONE GOD'S CHILDREN

🔥ገላ 4:6 ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባት ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ።
7 ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፤ ልጅም ከሆንህ ደግሞ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ።

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

26 Jan, 14:00

https://www.facebook.com/share/r/1KUZsYK3dg/?mibextid=wwXIfr

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

26 Jan, 05:07

https://youtu.be/VSzZiwppQ-U?si=FNCUxObu9uFWqzuM

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

26 Jan, 02:02

🔥በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር🔥

🙏1ኛ ጢሞቴዎስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ ፈጥኜ ወደ አንተ እንድመጣ ተስፋ አድርጌ ይህን እጽፍልሃለሁ።
¹⁵ ብዘገይ ግን፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።

🔥
1 ቆሮንቶስ 3፥16
16 aእናንተ ራሳችሁ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ፣ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውስጣችሁ እንደሚኖር አታውቁምን?

🔥
1 ቆሮንቶስ 6፥19
19 aለመሆኑ፣ ሰውነታችሁ በውስጣችሁ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? ይህም መንፈስ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት ነው። እናንተም የራሳችሁ አይደላችሁም፤

🔥
ሕዝቅኤል 37፥27
27 aማደሪያዬ ከእነርሱ ጋር ይሆናል፤ አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

18 Jan, 02:55

Shalom Shalom

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

18 Jan, 02:55

🔥ቃሉን በማድረግ ዕደጉ🔥

✝️ወተት የሚጋት ሁሉ ሕፃን ስለ ሆነ የጽድቅን ቃል አያውቅምና፤ ጠንካራ ምግብ ግን መልካሙንና ክፉውን ለመለየት በስራቸው የለመደ ልቡና ላላቸው ለፍጹማን ሰዎች ነው።“               ዕብራውያን 5፡13-14

👉ብዙ ቅዱሳን ትክክለኛው ቃሉን የመመገብ ዕድል ስናገኝ እንድንኖረው እንዲሁም እንድንገለጥ እና መንፈሳዊ ዕድገት እንድናስመዘግብ ያስፈልገናል

🙏በመንፈሳዊ ሕጻና  የሚሰሙትን ቃል አለማድረግ ነው። መልካም ምግብ ማግኘት አንድ ነገር ሲሆን፤ ያንን ምግብ መመገብ፣ ማዋሃድና ከዚያ ምግብ ተጠቃሚ መሆን  ደግሞ ሌላ ነገር ነው።
በተመሳሳይ መንገድ ቃሉን ሰምታችሁ ከራሳችሁ ጋር ካላዋሃዳችሁት መንፈሳዊ ዕድገት አይታይም።

✍️ቃሉን ስትማሩ ማስታወሻዎችን መያዝ እጅግ መልካም ቢሆንም ቃሉን ወደ መንፈሳችሁ ማስገባት ግን የተለየ ነው። ስለዚህ የጻፍናቸው የማስታዎሻዎቻችን ብዛት  መንፈሳዊ ዕድገቶቻችንን ማሳያ አይደሉም። ቃሉ የሚመጣው እንድንሰማው ብቻ አይደለም። ቃሉ የሚመጣው ከመንፈሳችን ጋር እንድናዋህደውና እንድናደርገው ነው።

✝️መጽሐፍ ቅዱስ በያዕ 1:22 ላይ ሲናገር “ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ።” ይላል።ቃሉን ሰምታችሁ ነገር ግን የማታደርጉት ከሆናችሁ በመንፈሳችሁ አላደጋችሁም ማለት ነው።

የመንፈሳዊ ዕድገት አንዱ መለኪያ ቃሉን ሰምቶ ማድረግ መቻል ነው። በምትሰሙት ቃል ውስጥ ቃሉን የምታደርጉበት አቅም አብሮ ይለቀቅላችኋል። ቃሉን የምታደርጉበት ፀጋ ይበዛላችኃል ያኔ ቃሉን የማታደርጉ ትሆናላችሁ መንፈሳዊ ሕይወታችሁ ይጠነክራል።

✝️በኤፌሶን 3፥16-17 “በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር እንደ ክብሩ ባለ ጠግነት መጠን ይስጣችሁ፤” ይላል።

🙏በውስጣችሁ ባለው የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ስትጠነክሩ ቃሉን ማድረግ ችላችኋል ማለት ነው። የክርስቶስ ቃል በልባችሁ ሲኖርና ሲዋሃድ ቃሉን ማድረግ ትችላላችሁ።
ከላይ ያለውም ክፍል የሚናገረው ይህንን ነው። ጠንካራ ምግብ ግን መልካሙንና ክፉውን ለመለየት የሚችሉ ሰዎች የበሰሉና በመነንፈሳዊ እውቀት ያደጉ ሰዎች ናቸው።

🔑እነዚህ ሰዎች ቃሉን በማድረግ መንፈሳዊ ጡንቻዎቻቸውን ያፈረጠሙ ናቸው። በሳል የምትሆኑት ቃሉን ስትሰሙ ሳይሆን ስታደርጉ ነው።

✝️በራእይ 1፥3 ላይ “የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው።” ይላል። ብፁአን ወይም የተባረኩ ቃሉን የሚሰሙት ብቻ ሳይሆኑ የሚያደርጉት ናቸው። እናንተ ቃሉን የምትሰሙ ብቻ ሳትሆኑ የምታደርጉ ናችሁና ብጹአን ናችሁ።

🔥አዋጅ🔥

አባት ሆይ ዛሬ ቃልህን የማደርግበትን ኃይል በኢየሱስ ስም እቀበላለሁ። ቃልህን እናገራለሁ። በቃልህም እውነት እመላለሳለሁ።ቃልህን በማድረግ ውስጥ ባለው ድል እመላለሳለሁ።

🙏በኢየሱስ ስም አሜን
 
GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

17 Jan, 02:17

https://youtu.be/-bMg3QOyNZc?si=_7FXNyfdBNLnHi7D

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

17 Jan, 02:08

bereket tefsfaye full albums

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

17 Jan, 02:08

🔥🔥🔥የምስጋና ኃይል🔥🔥🔥

👏ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ ስለ ጠላትህ፥ ጠላትንና ቂመኛን ለማጥፋት።”   መዝሙር 8፥2

👉እግዚአብሔር በሕይወታችሁ እንዲገለጥና ጠላቶቻችሁን እንዲያጠፋ ከሚረዳችሁ ነገር ውስጥ ዋነኛው ምስጋና ነው።ምስጋና የእግዚአብሔርን ክብርና ማዳን የምታዩበት ሁነኛ መንገድ ነው። በምስጋና ውስጥ እግዚአብሔር ለእናንተ ያለውን መልካም ሃሳብ ትረዳላችሁ።

🙏መጽሐፍ ሲናገር “ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።”ይላል(ኤርምያስ 29፥11)።

✍️እግዚአብሔር ለእናንተ ያዘጋጀው መልካምና ፍጻሜ ያለውን ሃሳብ የምትረዱት በምስጋና ውስጥ ነው።በማጉረምረም ውስጥ ያለ ሰው የእግዚአብሔር ሃሳብ መረዳት ይሳነዋል።እግዚአብሔርን በእዉነትስታውቁት፤ለእናንተ የሚያስበው ሃሳብ መልካም እንደሆነ ስትረዱ፤እርሱ ስለ እናንተ ክፉ ሃሳብ እንደሌለው ሲገባችሁ ሕይወታችሁ በምስጋና የተሞላ ይሆናል። የእግዚአብሔርን ሃሳብ ለእነርሱ መልካም ብቻ መሆኑን ያልተረዱ ሰዎች፤በምስጋና የተሞላ ሕይወት የላቸውም።
ሁልጊዜ ሕይወታቸው በማጉረምረምና በጥያቄ የተሞላ ነው።መልካም ነገር እንኳ ቢያጋጥማቸው ጥፋት ነው የሚታያቸው።በክርስቶስ ኢየሱስ የተገለጠው እግዚአብሔር የሚያስበው ሃሳብ፤ፍጻሜና ተስፋ ያለው መልካም እንጂ ክፉ አይደለም።ስለዚህ ሃሴት እናደርጋለን።

🙏ስለ እግዚአብሔር በትክክልና በሙላት ሊነግረንና ሊገልጥልን የቻለው ኢየሱስ ብቻ ነው። እግዚአብሔር መልካም እቅድ ያቀደልን ከዘላለም በፊት ነው። መልካምነቱ ከእኛ መልካምነት ጋር፣ከእኛ ጸባይ ጋር የተያያዘ አይደለም።

🔥እግዚአብሔር ለእናንተ ያሰበው ታላቅነትን፣ ስኬትን፣ሕይወትን፣ ጤንነትንና አሸናፊነትን ነው። ይህንን በማወቅ በምስጋና በመሞላት መዋጋት አለባችሁ።ትልቁ ስኬት በሕይወታችሁ የእግዚአብሔር ሃሳብ ምን እንደሆነ መረዳትና ለሃሳቡ መኖር ነው።ምስኪን ሰው የእግዚአብሔርን ሃሳብ ያልተረዳ ሰው ነው።

🙏ምስጉን ሰው ደግሞ የእግዚአብሔር ሃሳብ የተረዳ ነው።እግዚአብሔር ለእናንተ ያሰበው ሁልጊዜ በምስጋናና በፍሰሃ የተሞላ ሕይወት ነው።

እግዚአብሔርን ቃየልን ያለው አንድ ነገር ነው፤በዘፍጥረት 4¯¯⁶ "እግዚአብሔርም ቃየንን አለው፦ ለምን ተናደድህ? ለምንስ ፊትህ ጠቆረ? ⁷መልካም ብታደርግ ፊትህ የሚበራ አይደለምን? መልካም ባታደርግ ግን ኃጢአት በደጅ ታደባለች፤ ፈቃድዋም ወደ አንተ ነው፥ አንተ ግን በእርስዋ ንገሥባት።"፤የእግዚአብሔር ሃሳብ ሰው መልካም እንዲያደርግ ማለትም በክርስቶስ ኢየሱስ እንዲያምንና በደስታና በምስጋና የተሞላ ሕይወት እንዲኖረው ነው።

😇አሁን እግዚአብሔር እናንተን ሲመለከት አይናደድም፤የጠቆረ ማለትም የተኮሳተረ ፊት የለውም።በክርስቶስ ኢየሱስ ከተሰራው ሥራ የተነሳ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሰለሚያያችሁ ፊቱ የፈካና ፈገግታ የተሞላ ነው።ኃይማኖት የሳለብን የእግዚአብሔር ፊት ኮስተር ያለ፣ፈገግታ የራቀውና የሚያስፈራ ነው።ኢየሱስ የገለጠልን የእግዚአብሔር ፊት ግን የሚወደድ፣በርህራሄና ፍቅር የተሞላ ነው።

👉ስለዚህ ይህንን ፊት እየተመለከታችሁ በምስጋናና በውዳሴ ተሞሉ። በሕይወታችሁ ታላቅነት የሌለበትና የእግዚአብሔር ሃሳብ ያልሆነ ነገር ተቃወሙ። አለማግባትን፣ልጅ አለመውለድ፣ አለመስራትን፣በጤንነት አለመመላለስን፣ አለማገልገልንና ውጤታማ አለመሆንን አትቀበሉ።
 
       🔥🙏ምስጋና🙏🔥
አባት ሆይ ለእኔ ያለህ ሃሳብ መልካምና በጎ ብቻ ስለሆነ አመሰግንሃለሁኝ።
በምስጋና ከሸለቆ ወደ ተራራ ወጥቼያለሁኝ። ከዛሬ ጀምሮ ለዘላለም የእግዚአብሔር መልካምነት በምስጋና ውስጥ አያለሁኝ።እኔ አመስጋኝ እንጂ አጉረምራሚ አይደለሁም።
🙏በኢየሱስ ስም አሜን🙏

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

08 Jan, 02:03

Shalom Shalom

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

08 Jan, 02:03

🔥የመንፈስን ሙላት ተለማመዱ🔥

 “✝️መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከንነውና፤”
 — ኤፌሶን 5፥18

🔥መሞላት የሚለው ቃል "ፕሌሮ"ከሚል የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆንሙሉ በሙሉ መዋጥ፣በተሞላነው ነገር ቁጥጥር ሥር መሆን ማለትነው።

የመንፈስ ሙላት የእግዚአብሔር ፈቃድና ዘመኑን የምትዋጁበት ትልቁ መሣሪያ ነው።

✝️ኤፌሶን 5¹:15 እንግዲህ እንደጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴ ትእንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤  ¹⁷ ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምንእንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ።

👌ጥበበኛ ማለትየእግዚአብሔርን ፈቃድ አውቆ በዚያ ውስጥ የሚመላለስ ነው።ጌታእንድናስተውል ፈቃዱ በመንፈስ መሞላታችንን ነው። ጥበበኞችበመንፈስ የሚሞሉ ናቸው። በወይን ጠጅ የሚሰክሩ ግን ሞኞችናቸው። የጌታን ፈቃድ አላወቁምና።

👉እናንተ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ናችሁ(1ቆሮ3:16)ነገር ግን ይህመቅደስ በመንፈስ ቅዱስ እንዲሞላ ይፈልጋል።በዚያ ቤት እየኖረይሆናል ነገር ግን ያንን ቤት በባለቤትነት እያስተዳደረና እየመራ ላይሆን ይችላል።ክብሩ በሙላት በእናንተ እስኪገለጥ ድረስ እናንተን ሊሞላችሁ ይፈልጋል።

✝️በ2ነገ 7:1-3 ሲናገር 2 ዜና 7
¹ ሰሎሞንም ጸሎቱን በፈጸመ ጊዜ እሳት ከሰማይ ወርዶየሚቃጠለውን መሥዋዕትና ሌላ መሥዋዕቱን በላ የእግዚአብሔር ምክብር ቤቱን ሞላ።² የእግዚአብሔርም ክብር የእግዚአብሔርን ቤትሞልቶት ነበርና ካህናቱ ወደ እግዚአብሔር ቤት መግባት አልቻሉም።³ የእስራኤልም ልጆች ሁሉ እሳቱ ሲወርድ የእግዚአብሔርም ክብር በቤቱ ላይ ሲሆን ያዩ ነበር፤ በወለሉም ላይ በግምባራቸው ወደ ምድር ተደፍተው ሰገዱ፦ እርሱ መልካም ነውና፥ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና ብለውም እግዚአብሔርን አመሰገኑ።ይላል።
ሰሎሞን ቤተመቅደሱን ሰርቶ ጨርሶ መሥዋዕት ባቀረበ ጊዜ፣የእግዚአብሔር ክብር መቅደሱን ሞላው ይላል።ከዚህም የተነሳ ካህናት እንኳ ለማገልገል አልቻሉም ይላል።ይህ የሆነው በአሮጌውኪዳን።

🙏አሁን በአዲሱና በተሻለው ኪዳን እንዴት መቅደሱ በተሻለ ሁኔታ መሞላት እንደሚችል አስቡት።ያም መቅደስ እናንተ ናችሁ።

✝️የሰሎሞን ቤተመቅደስ እንደተሞላ እግዚአብሔር በመንፈሱ ሊሞላችሁ ይፈልጋል።ያን ጊዜ መግባት የለለበት ማንኛወም ነገር ወደእናንተ ሰውነት መግባት አይችሉም።በሽታና ሰውነታችሁን የሚጎዳ ነገር ወደ እናንተ የሚገባው በመንፈስ ስላልተሞላችሁነው።

🔥በመንፈስ ስትሞሉ ለሌላ ነገር ቦታ እስከማይኖር ድረስ ሁለንተናችሁን ይቆጣጠረዋል።
ከላይ በመግቢያ ክፍል ላይ ጳውሎስ ባለማቋረጥ በመንፈስ እንድንሞላ ይነግረናል።ለጌታ በልባችሁ ስትቀኙ፣🔥ስትዘምሩና እርሱን🔥ስታመሰግኑ በመንፈስ መሞላትይሆንላችኋል።

✍️ትካዜን፣ማጉረምረምን አስወግዱ።

በምስጋናየተሞላችሁ ሁኑ፣ሁልጊዜም በመንፈስ መሞላት ይሆንላችኋል።🙏
🔥ተከናወኑ🔥
 
GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

06 Jan, 21:16

bereket tefsfaye full albums

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

06 Jan, 21:16

🔥🔥🔥የምስጋና ኃይል🔥🔥🔥

👏ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ ስለ ጠላትህ፥ ጠላትንና ቂመኛን ለማጥፋት።”   መዝሙር 8፥2

👉እግዚአብሔር በሕይወታችሁ እንዲገለጥና ጠላቶቻችሁን እንዲያጠፋ ከሚረዳችሁ ነገር ውስጥ ዋነኛው ምስጋና ነው።ምስጋና የእግዚአብሔርን ክብርና ማዳን የምታዩበት ሁነኛ መንገድ ነው። በምስጋና ውስጥ እግዚአብሔር ለእናንተ ያለውን መልካም ሃሳብ ትረዳላችሁ።

🙏መጽሐፍ ሲናገር “ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።”ይላል(ኤርምያስ 29፥11)።

✍️እግዚአብሔር ለእናንተ ያዘጋጀው መልካምና ፍጻሜ ያለውን ሃሳብ የምትረዱት በምስጋና ውስጥ ነው።በማጉረምረም ውስጥ ያለ ሰው የእግዚአብሔር ሃሳብ መረዳት ይሳነዋል።እግዚአብሔርን በእዉነትስታውቁት፤ለእናንተ የሚያስበው ሃሳብ መልካም እንደሆነ ስትረዱ፤እርሱ ስለ እናንተ ክፉ ሃሳብ እንደሌለው ሲገባችሁ ሕይወታችሁ በምስጋና የተሞላ ይሆናል። የእግዚአብሔርን ሃሳብ ለእነርሱ መልካም ብቻ መሆኑን ያልተረዱ ሰዎች፤በምስጋና የተሞላ ሕይወት የላቸውም።
ሁልጊዜ ሕይወታቸው በማጉረምረምና በጥያቄ የተሞላ ነው።መልካም ነገር እንኳ ቢያጋጥማቸው ጥፋት ነው የሚታያቸው።በክርስቶስ ኢየሱስ የተገለጠው እግዚአብሔር የሚያስበው ሃሳብ፤ፍጻሜና ተስፋ ያለው መልካም እንጂ ክፉ አይደለም።ስለዚህ ሃሴት እናደርጋለን።

🙏ስለ እግዚአብሔር በትክክልና በሙላት ሊነግረንና ሊገልጥልን የቻለው ኢየሱስ ብቻ ነው። እግዚአብሔር መልካም እቅድ ያቀደልን ከዘላለም በፊት ነው። መልካምነቱ ከእኛ መልካምነት ጋር፣ከእኛ ጸባይ ጋር የተያያዘ አይደለም።

🔥እግዚአብሔር ለእናንተ ያሰበው ታላቅነትን፣ ስኬትን፣ሕይወትን፣ ጤንነትንና አሸናፊነትን ነው። ይህንን በማወቅ በምስጋና በመሞላት መዋጋት አለባችሁ።ትልቁ ስኬት በሕይወታችሁ የእግዚአብሔር ሃሳብ ምን እንደሆነ መረዳትና ለሃሳቡ መኖር ነው።ምስኪን ሰው የእግዚአብሔርን ሃሳብ ያልተረዳ ሰው ነው።

🙏ምስጉን ሰው ደግሞ የእግዚአብሔር ሃሳብ የተረዳ ነው።እግዚአብሔር ለእናንተ ያሰበው ሁልጊዜ በምስጋናና በፍሰሃ የተሞላ ሕይወት ነው።

እግዚአብሔርን ቃየልን ያለው አንድ ነገር ነው፤በዘፍጥረት 4¯¯⁶ "እግዚአብሔርም ቃየንን አለው፦ ለምን ተናደድህ? ለምንስ ፊትህ ጠቆረ? ⁷መልካም ብታደርግ ፊትህ የሚበራ አይደለምን? መልካም ባታደርግ ግን ኃጢአት በደጅ ታደባለች፤ ፈቃድዋም ወደ አንተ ነው፥ አንተ ግን በእርስዋ ንገሥባት።"፤የእግዚአብሔር ሃሳብ ሰው መልካም እንዲያደርግ ማለትም በክርስቶስ ኢየሱስ እንዲያምንና በደስታና በምስጋና የተሞላ ሕይወት እንዲኖረው ነው።

😇አሁን እግዚአብሔር እናንተን ሲመለከት አይናደድም፤የጠቆረ ማለትም የተኮሳተረ ፊት የለውም።በክርስቶስ ኢየሱስ ከተሰራው ሥራ የተነሳ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሰለሚያያችሁ ፊቱ የፈካና ፈገግታ የተሞላ ነው።ኃይማኖት የሳለብን የእግዚአብሔር ፊት ኮስተር ያለ፣ፈገግታ የራቀውና የሚያስፈራ ነው።ኢየሱስ የገለጠልን የእግዚአብሔር ፊት ግን የሚወደድ፣በርህራሄና ፍቅር የተሞላ ነው።

👉ስለዚህ ይህንን ፊት እየተመለከታችሁ በምስጋናና በውዳሴ ተሞሉ። በሕይወታችሁ ታላቅነት የሌለበትና የእግዚአብሔር ሃሳብ ያልሆነ ነገር ተቃወሙ። አለማግባትን፣ልጅ አለመውለድ፣ አለመስራትን፣በጤንነት አለመመላለስን፣ አለማገልገልንና ውጤታማ አለመሆንን አትቀበሉ።
 
       🔥🙏ምስጋና🙏🔥
አባት ሆይ ለእኔ ያለህ ሃሳብ መልካምና በጎ ብቻ ስለሆነ አመሰግንሃለሁኝ።
በምስጋና ከሸለቆ ወደ ተራራ ወጥቼያለሁኝ። ከዛሬ ጀምሮ ለዘላለም የእግዚአብሔር መልካምነት በምስጋና ውስጥ አያለሁኝ።እኔ አመስጋኝ እንጂ አጉረምራሚ አይደለሁም።
🙏በኢየሱስ ስም አሜን🙏

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

31 Dec, 00:31

Shalom Shalom

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

31 Dec, 00:31

🔥🔥🔥በሁሉ አመስግኑ🔥🔥🔥

"🙏ሁልጊዜ ስለ ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንንና አባታችንን ስለ ሁሉ አመስግኑ።" (ኤፌ 5፡20)

አንዳንዴ ስለተወሰኑ ነገሮች ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜ በሁሉ ስለሁሉ ነገር ማመስገን አለብን፡፡ በእንዳንዱ ገጠመኝ እግዚአብሔርን ማመስገን መልመድ መልካ ነዉ፤ ይህም ለመልካም ነገሮች ብቻ ሳይሆን መልካም መስለዉ ላልታዩንም ገጠመኞች ጭምር ነዉ፤ ምክንያቱም ስናመሰግን መጽሃፍ እንደሚል እግዚአብሔርን ለሚወዱ እንደ ሀሳቡምለተጠሩ ነገር ሁሉ ለበጎ እንደሚደረግ ስለምናዉቅ ነዉ፡፡

ብዙ ሰዎች ነገሮች መልካም ሲሆኑ ማመስገን እና መደሰት ይችላሉ፤ ነገር ግን ነገሮች እንደ አሰቡት ሳይሆኑ ሲቀሩ ከማመስገን ይልቅ ያጉረመርማሉ፡፡ ያ ያላመኑ ሰዎች ልምምድ ነዉ፤ ዳግም የተወለደ ሰዉ እንዲያ ሊሆን አይገባም፡፡ ✍️ምንም አይነት ነገር ዉስጥ ቢያልፍም፤ የትኛዉም ችግር ቢገጥመዉ ለእግዚአብሔር ምስጋና መስጠትን መለማመድ አለብን፤ ምክንያቱም ሁኔታዉን የሚቀየረዉ በማጉረምረም ሳይሆን በምስጋና ነዉ፡፡

🔥1ተሰ 5፡17 "ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።"በሁሉም ማለትም በየትኛዉም ነገር ዉስጥ እግዚአብሔርን እንድናመሰግን ነዉ ፈቃዱ፤ እንድናጉረመርም አይደለም፡፡ ያጉረመረመዉ እስራኤላዉያን ወደ ታየላቸዉ ርስት ሳይገቡ በምድረበዳ ቀርተዋል፡፡

✍️በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔር ካየልን ፈቃድ ጋር የምንገናኘዉም በምስጋና ዉስጥ ስንሆን ነዉ፡፡ ለሚያመሰግን ሰዉ በክርስቶስ ያለዉን የእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ሁሉ ወደ እርሱ ያነጣጠረ በመሆኑነ ይባረክበታል፤ ነገር ግን በሁሉ የማያመሰግን በሁሉ ተሸናፊ ነዉ፡፡

🙏ስለዚህ በየትኛዉም ሁኔታ ብትሆኑ ማመስገን ተለማዱ፡፡ ሁልጊዜ በጌታ ደስ ሊለን እና በመንፈሳችን ልንደሰት ያስፈልጋል፡፡ እግዚብሔር በሰጣችሁ በጥቂቱ ማመስገን ካልቻላችሁ፤ የተሻለና የበለጠ ነገር ወደ እናንተ አይመጣም፡፡

ሁልጊዜ ወዲያዉኑ ለሁሉ ነገር መልስ ታገኙ ብትችሉም ነገር ግን እናንተ ስለሁኔታዉ ያላችሁ እይታ ሊቀየር ይገባል፡፡ የተለየ እይታ ሲኖራችሁም ነገሩ መቀየር ይጀምራል፡፡

🛐በዕንባ 1፡2 ነብዩ ዕንባቆም ሲፀልይ "አቤቱ፥ እኔ ስጮኽ የማትሰማው እስከ መቼ ነው? ስለ ግፍ ወደ አንተ እጮኻለሁ፥ አንተም አታድንም።" በማለት በሃገሩ ያለለዉ ሁኔታ እንዲቀየር ጸለየ፡፡

✝️ምዕራፍ ሁለት ላይ እግዚአብሔር ሲመልስለት ግን ገና ነገሩ እስኪለወጥ የተወሰነ ጊዜ ስላለ የነገሩ መልስ ጠብቅ አለዉ፡፡ ስለዚህ ምዕራፍ ሶስት ላይ መጣና ክርክሩን አቁሞ ማመስገን ጀመረ፡፡

✝️ዕንባቆም 3፡17 ’’17 ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥18 እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።’’  በማለት ሁኔታዉ ከመቀየሩ በፊት ዕንባቆም ስለሁኔታዉ ያለዉ እይታና አመለካከት ሲቀየር እናያለን፡፡

👏እናንተም እርሱን ማመስገንና በእርሱ መደሰት ስትጀምሩ፡- ዕንባቆም 3፡19 እንዳለዉ በመከራ ዉስጥ እግሮቻችሁ እንደ ዋላ እግሮች ተራራዉን የሚወጡና የጠኑ ይሆናሉ፤ ከሁኔታ በላይ ከፍ ብላችሁ ትሄዳላችሁ፣ ሁኔታዉንና ችግሩን ከላይ ሆናችሁ ወደታች ማየት ትጀምራላችሁ፡፡

🛐🔥🔥አዋጅ🛐🔥🔥

ዉድ አባት ሆይ ሁልጊዜ ስለሁሉ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አመሰግንሃለሁ፡፡ በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ስለሆንክ አልፈራም፤ ከህይወቴ ዉስጥ ማጉረምረምን እና ምሬትን አስወግዳለሁኝ፡፡

🛐በኢየሱስ ስም አሜን🔥

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

30 Dec, 07:16

🔥ፈቃዱ የመንፈሱ ሙላት ነው🔥

 “✝️መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤”  — ኤፌሶን 5፥18

ቅድሳን መንፈስ ቅዱስን ሳይሞላ የሚኖረው ሕይወት ጣዕም የሌለውና በትግል የተሞላ ነው።

✝️በአፌ 5 ላይ ሲናገር17 ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ።¹⁸ መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤"ይላል።

✍️የጌታ ፈቃድ ምን እንደሆነ አስተውሉ ካለ በኋላ፤መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይላል።ስለዚህ የጌታ ፈቃድ መንፈስ እንዲሞላባችሁ ነው።አሁን መንፈስህን ስጠን ብለን የምንለምንበት ጊዜ አይደለም። መንፈሱን ሰጥቶናል።አሁን ከእኛ የሚጠበቀው መሞላት ነው።መንፈሴን ጠይቁ ሳይሆን ያለው መንፈስ ይሙላባችሁ ነው ያለው። መንፈሱን አንዴ ብቻ ሳይሆን ይህቺን ምድር ለቀን እስክንሄድ ድረስ በየዕለቱ መሞላት አለብን።

👉ከላይ በመግቢያ ላይ በዋነኛነት ስለ አልኮል መጠጥ ሊያስተምረን ፈልጎ አይደለም። በአልኮል መጠጥ ተጽዕኖ ሥር ስላለና በመንፈስ ሙላት ተጽዕኖ ሥር ስላለ ሰው እያወዳደረ ነው የሚገኘው። በአልኮል መጠጥ ተጽዕኖ ሥር ከመሆን በመንፈስ ሙላት ተጽዕኖ ሥር መሆን እንዳለብን እየነገረን ነው።

👉በወይን ጠጅ መስከር መባከን ነው።በመንፈስ ቅዱስ መስከር ግን መባረክ ና ማትረፍ ነው።አለም የምታቀርብላችሁ ውዱ ነገሯ ወይን ጠጅ ሲሆን እግዚአብሔር ደግሞ ያቀረበላችሁ መንፈሱን ነው።ወይን ጠጅ ገንዘብ አውጥታችሁ ገዝታችሁ ነው የምትጠጡት።መንፈሱን እግዚአብሔር እንድንጠጣ የሰጠን ግን በነጻ ነው።

✝️በኢሳይያስ 55¹ ላይ ሲናገር"እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ፥ ወደ ውኃ ኑ፥ ገንዘብም የሌላችሁ ኑና ግዙ ብሉም፤ ኑ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅና ወተት ግዙ።² ገንዘብን እንጀራ ላይደለ፥ የድካማችሁንም ዋጋ ለማያጠግብ ነገር ለምን ትመዝናላችሁ? አድምጡኝ፥ ።"
ይላል።ገንዘብን ሳታወጡ መጥታችሁ መንፈሱን እንድትጠጡ ተጋብዛችኋል። ከእናንተ የሚጠበቀው መጠማትና መምጣት ብቻ ነው።

🔥ገንዘባችሁን እንጀራ ላይደለ፥ የድካማችሁንም ዋጋ ለማያጠግብ ነገር ማውጣት የለባችሁም።"..በወይን ጠጅ አተስከሩ ይህ ማባከን ነውና" ያለው በዚህ ምክንያት ነው።
ነጻ ምርጥ መጠጥ እያለ ገንዘባችሁን ለወይን ጠጅ ለምን ታወጣላችሁ?ለምን ታባክናላችሁ? መነቃቃትና መሞላት ያለባችሁ በወይን ጠጅ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ነው። ሊቆጣጠራችሁ፣ሊያስደስታችሁ፣ሊገዛችሁና ተጽዕኖ ሊያደርግባችሁ የሚገባው መንፈሱ ነው።በመንፈስ መሞላት አንዴ ብቻ የሚሆን ነገር ሳይሆን ያለማቋረጥ የሚሆን ነገር ነው።ይህም ለስኬታችሁ ቁልፍ ነው።

🔥ጸሎት🔥
አባት ስለ አስደናቅው መንፈስህ አመሰግንሃለሁኝ።በየዕለቱ በመንፈስህ መሞላት ይሁንልኝ።መንፈስህን አስተሳሰቤን፣ንግግሬንና ተግባሬን ሳይቀር ይቆጣጠረው።

🙏በኢየሱስ ስም አሜን🙏

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

30 Dec, 07:16

Shalom Shalom

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

29 Dec, 01:43

Shalom Shalom

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

29 Dec, 01:43

 🔥መንግስቱን አስቀድሙ🔥

“ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።”
 — ማቴዎስ 6፥33

👉እንደ ክርስቲያን በምድር ለምን እንደምትኖሩ ማወቅ አለባችሁ።ጌታን እንደ ግል አዳኝ አድርጋችሁ የተቀበላችሁ ዕለት ፥ወደ ሰማይ ያልሄዳችሁትና በዚህ ምድር ለምን እንግዳ ሆናችሁ እንደምትቆዩ እግዚአብሔር እንደፈለገ ማወቅ አለባችሁ።እንድንማር፣አንድንሰራ፣እንድንጋባና ልጆች ወልደን እንድናሳድግ ብቻ  አይደለም ::

ዋና አላማው።እነዚህ ነገሮች መልካምና የእግዚአብሔር ፈቃድ ቢሆኑም ነገር ግን ከዚህ የላቀ የእግዚአብሔር ዓላማ አለ።

ኢየሱስ በአንድ ክፍል ሲናገር በሉቃስ 17:28"በኖኅ ዘመንም እንደ ሆነ፥ በሰው ልጅ ዘመን ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።²⁷ ኖኅ ወደ መርከብ እስከ ገባበት ቀን ድረስ፥ ይበሉና ይጠጡ ያገቡና ይጋቡም ነበር፥ የጥፋት ውኃም መጣ ሁሉንም አጠፋ"ይላል።መብላት፣መጠጣት ማግባትና መጋባት መጥፎ ነው እያለ አይደለም መጽሐፍ።ነገር ግን የሰው ልጅ በምድር ላይ መኖር ያለበት በዋናነት ለእነዚህ ነገሮች አይደለም እያለ ነው።

👉ሰዎች በውኃ የጠፉት ስለበሉና ስለጠጡ ወይም ስላገቡና ስላላገቡ አይደለም።ነገር ግን ዋናውን የእግዚአብሔር ሃሳብ አልተረዱም፣አካሄዳቸውንም ከእግዚአብሔር ጋር አላደረጉም። ከዚህም የተነሳ በመጣው ጥፋት ተጠቂ ሆኑ።በምድር ስትኖሩ፣ከሚታይ ነገር በላይ  ለሆነ ነገር ኑሩ።ስኬታችሁ ያለው ለእግዚአብሔር ሃሳብ በመኖር ውስጥ ነው።

🙏አስቀድማችሁ መንግስቱን ፈልጉ ማለት ከራሳችሁ ጉዳይ በላይ የእግዚአብሔርን መንግስት ሃሳብ አስቀድሙ ማለት ነው።የእግዚአብሔር መንግስት ሃሳብ ደግሞ የጠፉትን መፈለግ ነው።ለዚያ ነው መጽሐፍ ሲናገር “ከዚያ ዘመን ጀምሮ ኢየሱስ፦ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለ ይሰብክ ጀመር።”የሚለው(  — ማቴዎስ 4፥17)።

🔥የእግዚአብሔር መንግስት መፈለግ ሰዎች ንሰሃ ገብተው እንዲመለሱ መፈለግ ነው።የመንግስቱ ሃሳብ ሰዎችን ማጥፋት ሳይሆን መመለስ ነው።በዚህ ታላቅ በሆነው የመንግስቱ ሥራ ውስጥ፥ የእርሱ ሃሳብ ሃሳባችሁ፣የእርሱ መሻት መሻታችሁ መሆን አለበት።

🔑ሰዎችን ከሞት ወደ ሕየወት ለማምጣት የትኛውንም አይነት ዋጋ መክፈል አለባችሁ።የምትኖሩት ለወንጌል ነው።ያላችሁ ነገር ሁሉ ለወንጌል መሆን አለበት።የትም ሁኑ፣በምንም አይነት ቦታ ሁኑ ፥ወንጌልን አስቀድሙ።

🔑ስለ ንግስት አስቴር የተነገረ አንድ ታሪክ አለ፥በንጉሱ ፊት ሞገስ አግኝታ ወደ ቤተመንግስት ገብታ፥የንጉሱ ሚስት ሆነች።ነገር ግን ቤተመንግስት መግባትዋ፣ለንጉሱ ሚስት ከመሆን ያለፈ የእግዚአብሔር ዓላማ በእርሷ ላይ ነበረ።በአይሁድ ላይ አንድ ክፉ አዋጅ በታወጀ ጊዜ፣መርዶክዮስ ለአስቴር የሚከተለውን አላት፦“

በዚህ ጊዜ ቸል ብትዪ ዕረፍትና መዳን ለአይሁድ ከሌላ ስፍራ ይሆንላቸዋል፥ አንቺና የአባትሽ ቤት ግን ትጠፋላችሁ፤ ደግሞስ ወደ መንግሥት የመጣሽው እንደዚህ ላለው ጊዜ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?”  — አስቴር 4፥14።

✍️መርኮድዮስ ለአስቴር እየነገራት ያለው፥አስቴር ቤተመንግስት የገባቺውና እግዚአብሔር በዚያ ያስቀመጣት፥ ሚስት ለመሆን፣ጥሩ ኑሮ ለመኖር ሳይሆን የእግዚአብሔር ሃሳብ ለመፈጸም እንደሆነ እየነገራት ነው።የተሰጣትን ዕድል እግዚአብሔር ለማገልገልና ሃሳቡን ለፈመጸም እንድትጠቀም እያሳሰባት ነው።በራስዋ ጉዳይ ተይዛ የአይሁድን መዳን ቸል እንዳትል፤

✍️አስቀድማ የእግዚአብሔርን መንግስት ጉዳይ እንድታስቀድም ነገራት።"ደግሞስ ወደ መንግሥት የመጣሽው እንደዚህ ላለው ጊዜ እንደ ሆነ ማን ያውቃል"ሲላት፥በዚያ ቤተመንግስት የተቀመጠቺው የእግዚአብሔር ሃሳብ በእርሷ እንዲፈጸም፣ለሕዝቡ እንድትማልድና ሕዝቡን ከጥፋት እንድታድን እንዳስቀመጣት እየነገራት ነው።

ብዙዎች እግዚአብሔር በተለያየ የከበረ ሥፍራ ቢያስቀምጣቸውም፣ዕድሉን ወንጌል ለመስበክ፣የእግዚአብሔር ሃሳብ ለመፈጸም ተጠቀሙበት።

👉 እናንተ እግዚአብሔር በሰጣችሁ የትኛውም ዕድል፣እግዚአብሔር ባስቀመጣችሁ በየትኛውም ቦታ ላይ ብትሆኑ የእግዚአብሔር ሥራ እርሱም ነፍሰትን የማዳንን፣ወንጌል የመስበክንና ወንጌል እንዲስፋፋ አስተዋጽኦ ማድረግን መዘንጋት የለባችሁም።
                   🔥አዋጅ🔥
አባት ሆይ  ከአንተ ጋር የወንጌል አብሮ ሰራተኛ ስላደረከኝ አመሰግንሃለሁኝ። በሄድኩበት ሥፍራ ሁሉ፥ በተቀመጥኩበት ቦታ ሁሉ ከግል  አላማዬ ይልቅ የአንተን አላማ መፈጸም የምችልበት ጸጋ ይብዛልኝ።አስቴር ሕዝቡን ለማዳን ዋጋ ለመክፈል እንደ ወሰነች እንዲሁ እኔም ወንጌል እንዲሮጥና ሰዎች ከጥፋት እንዲድኑ የሰጠኸኝን ዕድል ሁሉ ለመልካም ሥራ እንድጠቀም እርዳኝ።

🙏በኢየሱስ ስም ከሜን

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

22 Dec, 19:32

🔥መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማሰላሰል🔥

✝️የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም።” — ኢያሱ 1፥8

✍️በዚህ ክፍል የምንነጋገረው ስለ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማሰላሰል ነው። ማሰላሰል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው። ልባችሁ ውሰጥ ሞልቶ የተጥለቀለቀ ነገር አዕምሮአችሁን የመቆጣጠር አቅም አለው።

✍️የምታስቡት ሃሳብ ትልቅ ኃይል አለው። አዕምሮችሁ ትክክለኛውን ነገር ማሰብ እንዲችል፣ መንፈሳችሁን በቃሉ ልትሞሉ ይገባል። በሕይወታችሁ ስኬታማ መሆን ከፈለጋችሁና በክርስቶስ ባላችሁ ሕይወት መደሰት ከፈለጋችሁ ትክክለኛ ሃሳቦችን ማሰብ መቻል አለባችሁ።

✍️አዕምሮችሁና መንፈሳችሁ ትክክለኛ ሃሳብ እንዲያስብ ማድረግ የምትችሉት ደግሞ በውጤታማ፣ ቀጣይነት ያለው ያልተቆራረጠ የመጽሐፍ ቅዱሳዊውን የማሰላሰል ሂደትን በመከተል ነው።

🔑ማሰላሰል ማለት አዕምሮአችሁ የእግዚአብሔር ቃል ላይ እንዲያተኩር በማድረግ፥ መንፈሳችሁን በቃሉ የምትመግቡበት ሂደት ነው። ይህ ቋሚ የሆነ ጊዜ ሰጥታችሁት በቀኑ ውስጥ ልታደርጉት የሚገባ ነው።

✝️መጽሐፍ በፊል 4፥8 ላይ ሲናገር “በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤”ይላል።"

🔑ማሰብ የሚለው ቃል "ሎጊዞማኢ" ከሚል የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን በትኩረት ማሰብ የሚል ሃሳብ ያመለክታል።

✍️ይህ ማለት ማሰላሰል ነው።
ከላይ በመግቢያ ላይ ያለው ክፍል እግዚአብሔር ለኢያሱ ለተሰጠው ትልቅ  ኃላፊነት ብቁ ማድረግ የሚችልውን ምስጢር ነገረው።

የጠላቶችህን ግዝፈት ወይም የተመሸጉ የኢያርኮን ግንቦች ሳይሆን ቃሉን አሰላስል አለው። ቃሉ ከአፍህ አይለይ ካለ በኋላ በቀንም በሌሊትም አሰላስለው አለው። ይህ ነው የስኬት ቁልፍ።

በመዝሙር 1:2-3 ላይ ሲናገር "ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል። እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።" ይላል።

በቃሉ የምትደሰቱ ከሆነ ቃሉን ማሰላሰል አለባችሁ። ቃሉን መውደዳችሁ የሚታወቀው ቃሉን በቀንም በሌሊትም በማሰብ ነው። ሌላ ነገር እያሰባችሁ የምወደው ቃሉን ነው ማለት አትችሉም። ቃሉን በቀንም በሌሊትም ስታስቡ፥ ሕይወታችሁ እንደተጻፈው በውሃ ፈሳሽ ዳር እንደተተከለ፥ ፍሬዋን በጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል። ሃሌሉያ!

🔥አዋጅ🔥

አዕምሮዬ ያለማቋረጥ ቃልህን ያስባል። ከዚህም የተነሳ መንፈሴ በብርሃን የተጥለቀለቀ ነው። የእኔ ሃሳቦች የእግዚአብሔር ሃሳቦች ናቸው። ቃሉን ስለማሰላስል መንገዴ የስኬትና የልምላሜ ነው።

🙏በኢየሱስ ስም አሜን🙏

https://t.me/GRACE_TRUTH

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

22 Dec, 19:32

Shalom Shalom

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

21 Dec, 23:14

Shalom Shalom

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

21 Dec, 23:14

🔥ቃሉ በእናንተ ይኑር🔥

✝️በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል።” — ዮሐንስ 15፥7

ክርስትና የትግል ሕይወት አይደለም። በእግዚአብሔር ጸጋና በቃሉ ተደግፋችሁ ስትኖሩ፥ ሕይወታችሁ ወደ ፊትና ወደላይ ብቻ የሚሄድ ይሆናል።

🔑የእግዚአብሔር ቃል ለሕይወታችሁ እጅግ መሠረታዊ ነገር ነው፤ ምክንያቱም ፍጥረት ሁሉ በእርሱ ነው የተፈጠሩት።

መጽሐፍ በዮሐ 1፥3 ላይ ሲናገር “ሁሉ በእርሱ (በቃሉ) ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።” ይላል። ሆነ ማለት ተፈጠረ ማለት ነው። እርሱ ደግሞ የፈጠረው መልካም ብቻ ነው።

በ1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥4 ላይ መጽሐፍ ሲናገር “እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም ነውና፥” ይላል።
🙏ቃሉን በልባችሁ ማኖር አለባችሁ ምክንያቱም አለምን የፈጠረውን ቃሉ ሁሉን ነገር ማድረግ የምትችሉበትን አቅም ይሰጣችኋል። ብዙ ሰዎች ለማግኘት የሚጓጉለትና የሚጸልዩለት ነገር በቃሉ ውስጥ ታጭቆ ይገኛል።

✍️ማድረግ የሚያስፈልጋችሁ በቃሉ መሙላት ብቻ ነው።

✝️በዕብ 1፥3 ላይ ሲናገር “ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥” ይላል። በተጨማሪም ደግሞ በዕብ 11፥3 ላይ “ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን።” ይላል።

አለማትን በሙሉ ውብ አድርጎ ያዘጋጀው ቃሉ ነው።

✝️መጽሐፍ በዕብራውያን 3፥4 ላይ “ሁሉን ያዘጋጀ ግን እግዚአብሔር ነው።” ይላል። እግዚአብሔር ደግሞ ሁሉን ያዘጋጀው በቃሉ ነው። ቃሉን ሁሉን ውብ አድርጎ ያዘጋጃል።

"በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል።" አለ። ቃሉ በመንፈሳችሁ ሲቀመጥ፥ የምትወዱትን ሁሉ ጠይቃችሁ ትቀበላላችሁ።

🙏እንደ ቃሉ ትናገራላችሁ፥ የተናገራችሁት ይፈጸማል። ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን! ከምንም በላይ ቃሉ በልባችሁ እንዲሞላ ፍቀዱ። ያለማቋረጥ በቃሉ ሙሉት። ከቃሉ ውጪ ለሌላ ነገር ሥፍራን አትስጡ። ያን የክብርን ሕይወት መምራት ትጀምራለችሁ። ሃሌሉያ!

🔥ጸሎት🔥
ውድ አባት ሆይ ለቃልህ ትኩረት መስጠት የምችልበት ጸጋ በኢየሱስ ስም ይለቅቅልኝ። ከቀድሞ ይልቅ የቃልህ ርሃብ ይሙላብኝ። በኢየሱስ ስም የቃልህ ሙላት በኃይል ይኑርብኝ።

🙏በኢየሱስ ስም አሜን🙏

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

20 Dec, 02:32

Shalom Shalom

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

20 Dec, 02:32

                ✝️ቃሉን ተመገቡ🛐

✝️እርሱም መልሶ፦ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው።”
 — ማቴዎስ 4፥4

✍️ለጤናማ አካላዊ ዕድገት ጥሩ አመጋገብ ወይም የተመጣጠነ ምግብ መመገብ ያስፈልጋል።"ሰው የሚመገበውን ይመስላል" ይባላል።በተለያየ አጋጣሚ የተበከለ ምግብ በልተው የታመሙ ሰዎች ሰምታችሁ ይሆናል።ሥጋችሁ ጤናማ ምግብ እንደሚፈልግ እንዲሁ መንፈሳችሁም ጤናማ ምግብ ይፈልጋል። ለሰውነታችሁ ጤናማ ምግብ ለመመገብ እንደምትጠነቀቁ እንዲሁ፥ለመንፈሳችሁም ትክክለኛ ቃል ለመመገብ መምረጥ አለባችሁ።

🙏ለመንፈሳችን ትክክለኛው ምግብ ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል ነው።ቃሉ እምነታችሁን የሚያሳድግ ምግብ ነው።ከቃሉ የሚቃረን ድምፅ ስትቀበሉ ደግሞ ፍርሃትን እየመገባችሁ ነው።

ይበልጥ ደፋር ከመሆን ይልቅ ፈሪ ትሆናላችሁ።ትክክለኛ ማንነታችሁ መንፈሳችሁ ነው።መንፈሳችሁን የምትመግቡት ነገር መምረጥ አለባችሁ።

ሰው ሥጋ ብቻ አይደለም።ሥጋ ብቻ ቢሆን በእንጀራ ብቻ መኖር ይችል ነበር።እርሱ ደግሞ ጊዜያዊ የሚታይ ነው

👉ከእግዚአብሔር አፍ የሚወጣ መንፈስ የሆነ ቃል ያስፈለገው እውነተኛ ማንነቱ መንፈሱ በመሆኑ ነው።ሰው መንፈስ ነው፣ነፍስ አለው ፣በሥጋ ውስጥ ያድራል።አካላችሁ ምግብ ካልተመገበ እየደከመ እንደሚሄድ እንዲሁ መንፈሳችሁም ዕለት ዕለት ቃሉን ካልተመገበ ደካማ ይሆናል።ያልጠነከረ ይሆናል።

🔑ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ሲናገር በሉቃስ 1፥80 ላይ “ሕፃኑም አደገ በመንፈስም ጠነከረ፥።”ይላል።በመንፈስ የጠነከረው መንፈሳዊ ምግብ የሆነውን ቃሉን ስለሚመገብ ነው።በቀን ሦስት ጊዜ አንድ አንዴም ከዚያ ላለፈ ጊዜ እንደምትመገቡ እንዲሁ መንፈሳችሁን ዕለት ዕለት በቃሉ መግቡ።ያኔ ስኬትና መልካም ነገሮች ሁሉ ከእናንተ ይወጣሉ።ሃሌሉያ

🔥ጸሎት🔥

አባት ሆይ እውነተኛ ማንነቴ መንፈሴ ስለሆነ፥የሥጋዬን ጤንነት እንደምጠብቀው እንዲሁ የመንፈሴን ጤንነት እጠብቃለሁኝ።ዕለት ዕለት ቃልህን በመመገብ እምነቴን እገነባለሁኝ።

🙏በኢየሱስ ስም አሜን🙏

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

18 Dec, 02:33

🔥እንደሚገባ መጸለይ🔥

እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤”— ሮሜ 8፥26

🙏ውጤታማ የጸሎት ሕይወት ቀጣይነት ላለው የድልና የአሸናፊነት ሕይወት መሠረት ነው። እንደሚገባ መጸለይ በየዕለቱ ለብዙ ሰዓታት ያለማቋረጥ መጸለይ ብቻ አይደለም። ዋናው ነገር በየዕለቱ ለምን ያህል ሰዓት ጸልያለሁ? የሚለው ብቻ ሳይሆን ከጸለዩኩት ጸሎት ምን ያህሉ ውጤታማና መልስን ያገኘሁበት ነው ብሎ መጠየቅ ነው። ጸሎት ኃይማኖታዊ ሥርዐትና እንቅስቃሴ ሳይሆን የእግዚአብሔር ፍቃድ በሕይወታችሁ፣ በቤተሰባችሁ፣ በአገልግሎታችሁና በሀገራችሁ ጭምር ተጽዕኖ አምጪ ኃይል የምትገልጡበት ትልቅ መሣሪያ ነው።

መጽሐፍ በዮሐ 16፥24 ላይ ለደቀመዛሙርቱ ሲናገር “እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ ትቀበሉማላችሁ።” አላቸው።

🔑ጸሎት የኢየሱስን የስሙን ኃይል ሥልጣን የምትለማመዱበት፤ ከእግዚአብሔር ጋር ያልቋረጠ ሕብረት በማድረግ ለጥያቄዎቻችሁ መልስን የምትቀበሉበት፤ በመንፈስ የምትታደሱበትና ኃይልን የምትሞሉበት መንፈሳዊ መርሃ ግብር ነው።
ውጤታማ ጸሎትን እውን ማድረግ የምትችሉት በመንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው። እርሱ በጸሎት ጊዜ ረዳታችሁ ነው። ብዙዎች ይህንን ህይወት መለማመድ ይሁንልን።

🙏ለውጤታማ ጸሎት የሚሆን ኃይል የሚለቀቀው ከመንፈስ ቅዱስ ነው። ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስን ጸሎትን አስተምረን ብለው ጠየቁት። ኢየሱስም በተለምዶ "የአባታችን ሆይ ጸሎት" ብለን የምንጠራውን አስተማራቸው። ሆኖም ቀደመዛሙርቱ ውጤታማና ተጽዕኖ አምጪ ጸሎት መጸለይ የጀመሩት መንፈስ ቅዱስ ከወረደና ከተቀበሉ በኋላ ነው።

በሐዋሪያት ሥራ ላይ የካህናት አለቆችና ሽማግሌዎች ወንጌል እንዳይሰብኩ በአስጠነቀቁአቸው ወቅት ተሰብስበው በአንድ ልብ እንደጸለዩ መጽሐፍ ይናገራል (ሐዋ4፥24)። ወረድ ብሎ ከጸለዩ በኋላ የሆነውን ሲናገር

🛐ሐዋርያት 4፥31 “ከጸለዩም በኋላ ተሰብስበው የነበሩበት ስፍራ ተናወጠ፥ በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ የእግዚአብሔርንም ቃል በግልጥ ተናገሩ።” ይላል።

✍️ውጤታማና በመንፈስ ቅዱስ የታገዘ ጸሎት ስትጸልዩ እንዲህ ነው የሚሆነው። ስፍራው ተናወጠ (አከባቢያችሁ ላይ ለውጥን ታመጣላችሁ) በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው (በእናንተ ላይ የሚሆን ለውጥ አለ) እና የእግዚአብሔርን ቃል በግልጥ ተናገሩ (የምትፈሩ ደፋር ከመሆናችሁ በላይ ለሌሎች በረከት ትሆናላችሁ)።

✝️መጽሐፍ በዘካ 4፥6 ላይ ሲናገር “መልሶም፦ ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።” ይላል።

✍️እግዚአብሔር እያለ ያለው ነገሮች ውጤታማና እውን የሚሆኑት በእኔ ኃይልና ብርታት (በመንፈሴ) እንጂ በእናንተ ኃይልና ብርታት አይደለም ነው። በመንፈሱ ጸልዩ በኃይልና በብርታታችሁ አትጸልዩ። በመንፈስ ቅዱስ ላይ ስትደገፉ ኃይል አልባ አትሆኑም። ደካማ አትሆኑም። ቀጣይነት ያለውና ውጤታማ ጸሎት ለመጸለይ ትግል ላይ ከሆናችሁ በመንፈስ ቅዱስ አቅም ላይ ተደገፉ!እርሱ ለጸሎትም ይሁን ለየትኛውም ጉዳይ የሚሆን ኃይል ይለቅላችኋል።

🔥ጸሎት🔥
ውድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ለውጤታማ ጸሎት የሚሆን ጸጋ በኢየሱስ ስም አሁን እቀበላለሁ። የጸሎት ሰዓቴ የተወደደና የማጣጥመው እንጂ አሰልቺ ነገር አይሆንብኝም። የጸሎት ሕይወቴ አስደናቂ ውስጤቶችን የማይበት ልዩ ጊዜ በመሆኑ አሳንሼ አላየውም። ሁልጊዜ በመንፈስ በመጸለይ እነዳለሁኝ! እቀጣጠላለሁኝ!

🙏በኢየሱስ ስም አሜን።🙏

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

08 Dec, 18:24

🔥በእግዚአብሔር ተከባችኋል🔥

አንድ ደስ የሚል መዝሙር ሰምቻለሁ። እንዲህ ይላል "በዚህ ስል በረከቱ፣ በዚያ ስል ጸጋው፣ በዚህ ስል ሰላሙ፣ በዚያ ስል በጎነቱ፤ከበበኝ! ከበበኝ! ከበበኝ!" ሃሌሉያ!

አሁን በምድራችን እየተገለጠ ካለው የአዲስ ፍጥረት እውነት የተነሳ፣ ዘማሪዎቻችን በሚዘምሩት መዝሙር ላይ ብዙ ለውጦችን እየተመለከትን ነው። አንዳንድ በጠላት፣ በችግር፣ በጨለማ እንደተከበብን የሚነግሩን መዝሙሮች፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የሌላቸውና ሊታረሙ የሚገባቸው ናቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ ሰይጣን እንደከበበን፣ ጨለማ እንደከበበን አይነግረንም። ሁልጊዜ በጠላትና በጨለማ እንደተከበቡ የሚያስቡ ሰዎች ጸሎታቸው በሙሉ የከበባቸውን ጠላት ለመበተን በሚያደርጉት ግብ ግብና ትግል የተሞላ ነው።

🙏በ 2ኛ ነገሥት 6፥15-16 ላይ ሲናገር "የእግዚአብሔር ሰው ሎሌ ማለዳ ተነሥቶ በወጣ ጊዜ፥ እነሆ፥ በከተማይቱ ዙሪያ ጭፍራና ፈረሶች ሰረገሎችም ነበሩ። ሎሌውም፦ ጌታዬ ሆይ፥ ወዮ! ምን እናደርጋለን? አለው። እርሱም፦ ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ አለው።"ይላል።

የእግዚአብሔር ሰው ሎሌ በማለዳ ተነስቶ "ጠላቴ ከበበኝ"የሚለውን መዝሙር ጀመረ። ወዮ!ምን እናደርጋለን? አለ። ይህ ሰው በእምነት ሳይሆን በማየት የሚመላለስ ሎሌ ነው። ወዮ! አበቃልን ብለው ፍርሃትን በሌሎች ላይ ለማስተጋባት የሚጥሩ ሰዎች 👉አይናቸው ያልተገለጠላቸው ናቸው።
የእግዚአብሔር ሰው ኤልሳዕ አይኑ የተገለጠለት ነበርና ወዮልን ሳይሆን "ተረጋጋ! ከእነርሱ ጋር ካሉት ከእኛ ጋር ያሉት ይበልጣሉ"አለው።

🙏ኤልሳዕ እንዲረጋጋ ያደረገው በእግዚአብሔር መከበቡን ማወቁ ነው። በእግዚአብሔር የተከበበ ሰው አደጋ ውስጥ ሊሆን አይችልም።

👉በዘካሪያስ 2፥5 ላይ ሲናገር “እኔ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ፥ በውስጥዋም ክብርን እሆናለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።” ሃሌሉያ። ዙሪያችሁ በእሳት ቅጥር ተቀጥሯል።በውስጣችሁ ክብር ሆኖላችኋል። ስለዚህ በውስጥም ከውጭም በሚመጣ ጠላት ተጠብቃችኋል።

✝️የጻድቅ ሰው አንዱ በረከት መለኮታዊ ጥበቃ ነው። እንደተጠበቅን ራሱ ጠላት እንኳ ኢዮብን በተመለከተ በሰጠው ምስክርነት ውስጥ እንመለከታለን። ሰይጣን የሰጠው ምስክርነት (ኢዮብ 1፥10) “እርሱንና ቤቱን በዙሪያውም ያሉትን ሁሉ አላጠርህለትምን? የእጁን ሥራ ባርከህለታል፥ ከብቱም በምድር ላይ በዝቶአል።” የሚል ነው።

👉እናንተና የእናንተ የሆነው ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም በእሳት ታጥሯል! የጠላት ፍላጻና አደጋ ሊያገኛችሁ አይችልም። እናንተ በሰይጣን ሳይሆን በመላዕክት ተከባችኋል! በእርግማን ሳይሆን በበረከት ተከባችኋል!በጨለማ ሳይሆን በብርሃን ተከባችኋል! በበሽታ ሳይሆን በጤንነት ተከባችኋል! ሃሌሉያ

🔥አዋጅ🔥
በክርስቶስ ኢየሱስ ጻድቅ በመሆኔ እኔና የእኔ የሆነ ነገር በሙሉ በእሳት የታጠረ ነው። ከእኔ ጋር ያለው ከእነርሱ ጋር ካለው ይበልጣል።በእኔ ውስጥ ያለው በእነርሱ ውስጥ ካለው ይበልጣል። ከዚህ የተነሳ ወዮልኝ! ጠፋሁ! ሳልል ያለሥጋት እመላለሳለሁ። በኢየሱስ ስም አሜን

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

08 Dec, 13:27

_*Who hath delivered us from the power of darkness, and hath translated us into the kingdom of his dear Son (Colossians 1:13).*_

Our opening scripture says God has transferred us from the domain of darkness into the Kingdom of His Love-Son. That's where you are now. The transfer wasn't a process; it's not something that happens from time to time; it's already been effectuated, and it was a permanent transfer. Your present and permanent place of domicile is the Kingdom of God's Love-Son.

The question is: do you realize you're in His Kingdom? It's important to know this because it means you're not under the dominion of Satan. You're seated together with Christ, _*"Far above all principality, and power, and might, and dominion, and every name that is named, not only in this world, but also in that which is to come"*_ (Ephesians 1:21).

Recall what the Bible says about our Lord Jesus Christ in 1 Timothy 6:15-16: He's the _*"...blessed and only Potentate, the King of kings, and Lord of lords; Who only hath immortality, dwelling in the light which no man can approach unto...."*_ In other words, He only has immortality (life, "deathlessness") and dwells in unapproachable light. He is light, and in Him is no darkness at all (1 John 1:5), and you're in Him.

That means in you, there's no darkness, no sickness, disease or infirmity, nothing of Satan because you were born into God's Kingdom of light—His marvellous light: _*"But ye are a chosen generation, a royal priesthood, an holy nation, a peculiar people; that ye should shew forth the praises of him who hath called you out of darkness into his marvellous light"*_ (1 Peter 2:9).

If this is true, and thank God it is, how can you have cancer? Where will diabetes, hypertension, heart condition, migraine headache, etc., come from since you presently and permanently dwell in the Kingdom of God's Love-Son where there's no darkness but light; where life and immortality reign? How can the devil oppress you when you're not under his jurisdiction?

In Luke 10:19, the Lord said, _*"Behold, I give unto you power to tread on serpents and scorpions, and over all the power of the enemy: and nothing shall by any means hurt you."*_ It's the reason you can say, "In the Name of Jesus, I refuse to accommodate Satan and anything from him; I belong in the Kingdom of God's Love-Son, Jesus Christ, with dominion over Satan, sickness, disease, death and the demons of darkness." Hallelujah!

*CONFESSION*

*I'm in the Kingdom of God's Love-Son, where there's no darkness, disease, failure or death. I'm seated with Christ, far above all principality, power, might, dominion and everything that's named, not only in this world, but also in that which is to come. Amen.*

*FURTHER STUDY:* *||* *Ephesians 2:4-6* But God, who is rich in mercy, for his great love wherewith he loved us, 5 Even when we were dead in sins, hath quickened us together with Christ, (by grace ye are saved;) 6 And hath raised [us] up together, and made [us] sit together in heavenly [places] in Christ Jesus: *||*

*||* *1 John 5:4* For whatsoever is born of God overcometh the world: and this is the victory that overcometh the world, [even] our faith. *||*

*||* *Colossians 1:12-13* Giving thanks unto the Father, which hath made us meet to be partakers of the inheritance of the saints in light: 13 Who hath delivered us from the power of darkness, and hath translated [us] into the kingdom of his dear Son: *||*
*DAILY SCRIPTURE READING*

*1-Year Bible Reading Plan=>* 2 John & Daniel 5-6

*2-Year Bible Reading Plan=>* Revelation 7:11-17 & Amos 3-4

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

08 Dec, 04:36

https://t.me/bookstore2014

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

07 Dec, 04:07

🔥ብቁ አገልጋዮች ናችሁ🔥

✝️2ኛ ቆሮ 3
⁵ ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን እንደሚሆንአንዳችን እንኳ ልናስብ ራሳችን የበቃን አይደለንም፤⁶ እርሱም ደግሞበመንፈስ እንጂ በፊደል ለማይሆን ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንሆንዘንድ አበቃን፤ ፊደል ይገድላልና መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል።

ቅዱሳን ብዙ ጊዜ ከሚቸገሩበት ጉዳይ አንዱ በሄዱበት ቦታ ሁሉወንጌልን መስበክና የተሰጣቸውን የማስታረቅን አገልግሎት መፈጸምነው።

ብዙዎች ወንጌልን ለሌሎች ለማካፈል ብቁ እንዳልሆኑይሰማቸዋል። በዚህ ምክንያት ነው ብዙዎች ለወንጌል አገልገሎትናሥራ ለመውጣት የተወሰነ ጊዜ መጠበቅ እንዳለባቸው የሚሰማቸው ምክንያቱም በትምህርት ቤት፣በሥራ ቦታ፣በመኪና ውስጥናበየመንገዱ ወንጌልን ለሌሎች ለማካፈል በቂ ዝግድት የለንም ይላሉ።

👉ስለተቀበልነው የማስታረቅ አገልግሎት አስደናቂው ነገር የእኛንችሎታ፣ብቃትና ልምድ እንደሚጠይቅ እንደ ሙያ ሥራ አለመሆኑነው።የማስታረቅ አገልገሎት ስለንግግር ችሎታ ወይም ተናግሮየማሳመን ብቃት አይደለም።እነዚህ ነገሮች የተወሰነ አስተዋዕጾያደርጉ ይሆናል እንጂ ዋና ነገሮች አይደሉም።

🙏ሉቃስ 4¹⁷-¹⁹ የነቢዩንም የኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት፥ መጽሐፉንምበተረተረ ጊዜ፦ የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትንእሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንምየጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራአገኘ።²⁰ መጽሐፉንም ጠቅልሎ ለአገልጋዩ ሰጠውና ተቀመጠ፤ በምኵራብም የነበሩት ሁሉ ትኵር ብለው ይመለከቱት ነበር።

👉ኢየሱስ መጽሐፉን ከፍቶ በማንበብ ብቻ የሁሉንም ትኩረትአገኘ።የተለየ መገለጥ አልሰበከም ቀድሞኑ የሚያውቁትና ሲያነቡየነበረውን የመጽሐፍ ክፍል ነው ያነበበው። መልዕክቱ ውስብስብናለመረዳት አስቸጋሪ አልነበረም።

👉የመጣበትን አላማ የሚገልጥ ቀላልግን በኃይል የተሞላ ነበረ።“ሁሉም ይመሰክሩለት ነበር ከአፉምከሚወጣው ከጸጋው ቃል የተነሣ እየተደነቁ፦ ይህ የዮሴፍ ልጅአይደለምን? ይሉ ነበር።”  — ሉቃስ 4፥22 ይላል።

ዋናው ነገር የመልዕክታችሁ የሚያድን ውስብስብነትየሌለው ነው። ለወንጌል አገልግሎት ራስን ማዘጋጀትና ማስታጠቅመልካም ነው።ነገር ግን ከላይ በመግቢያ ላይ ያለው ክፍል" ብቃታችንከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን እንደሚሆን አንዳችንእንኳ ልናስብ ራሳችን የበቃን አይደለንም" ይላል። ይህ ማለት የእኛብቃት ከእኛ ሳይሆን ከእርሱ ዘንድ ነው።

🙏እግዚአብሔር ለሰጠንየማስታረቅ አገልግሎት ብቁ አድርጎናል።እኔ ዝምተኛና ብዙ ከሰውጋር መነጋገር የማልፈልግ ሰው ነኝ ትሉ ይሆናል።

👉መንፈስ ቅዱስበእናንተ እንዲሰራና እንዲናገር ከፈቀዳችሁለት ብዙ ማውራትሳይጠብቃችሁ የምትናገሩት ጥቂት ቃል በሰዎች ልብ ውስጥ ተጽዕኖበመፍጠር ደንዳናውን ልብ ለወንጌል እንዲንበረከክ ያደርገዋል።
እናንተ ስትናገሩ መንፈስ ለሰዎች ሕይወትን ይሰጣል።ለዚህምአገልግሎት እግዚአብሔር ብቁ አድርጓችኋል። ስለዚህ ለሰዎችወንጌልን ለመናገር እፈራለሁኝ፣አልችልም የሚለውን አመለካከትአስወግዱ።

👉እናንተ መኪና እየነዳችሁ ራይድ ስትሰጡ በታክሲ ስትሄዱ በስራ ቦታ በመንደር አጠገባችሁ የተቀመጠው ሰውየመዳን ተስፋ ናችሁ።ለዚያ ሰው ወንጌል ሳትናገሩ ሌላ ስለ ፖለቲካወይም ማህበረዊ ጉዳይ አውርታችሁ ወንጌልን ሳትነግሩት ፈጽሞአትውረዱ አትሂድ ።እርሱ በመንፈስ እንጂ በፊደል ለማይሆን መንፈስንለሚያካፍል አገልግሎት ብቁ አድርጓችኋልና ለወንጌል አንደበታችሁንክፈቱ እርሱ ይሞላዋል።ለብዙዎችም በረከት ተደርጋችኃል።

🔥አዋጅ🔖
እኔ መንፈስንና ሕይወትን ለማካፈል ብቁ የአዲስ ኪዳን አገልጋይተደርጌያለሁኝ።እያንዳንዱን እድል ወንጌልን ለማካፈልእጠቀማለሁኝ።የተሰጠኝን የማስታረቅ አገልግሎት በትጋትናበታማኝነት እወጣለሁኝ።

🙏በኢየሱስ ስም አሜን

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

06 Dec, 02:10

🔥በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር🔥

🙏1ኛ ጢሞቴዎስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ ፈጥኜ ወደ አንተ እንድመጣ ተስፋ አድርጌ ይህን እጽፍልሃለሁ።
¹⁵ ብዘገይ ግን፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው።

🔥
1 ቆሮንቶስ 3፥16
16 aእናንተ ራሳችሁ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ፣ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውስጣችሁ እንደሚኖር አታውቁምን?

🔥
1 ቆሮንቶስ 6፥19
19 aለመሆኑ፣ ሰውነታችሁ በውስጣችሁ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? ይህም መንፈስ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት ነው። እናንተም የራሳችሁ አይደላችሁም፤

🔥
ሕዝቅኤል 37፥27
27 aማደሪያዬ ከእነርሱ ጋር ይሆናል፤ አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

06 Dec, 02:10

Shalom Shalom

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

05 Dec, 04:54

    🔥ታላቅ  ተልዕኮ ላይ ነን🔥

🛐እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።” ማቴዎስ 28፥19-20

ዳግም የተወለዳችሁት ከዚህ አለም ሳይሆን ከላይ ነው። ለዚያ ነው መጽሐፍ ቅዱስ ዮሐንስ 1 (አዲሱ መ.ት) ላይ ¹² ለተቀበሉትና በስሙ ላመኑት ሁሉ ግን የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን መብት ሰጣቸው።¹³ እነዚህም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ፣ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም" የሚለው።

🙏ከእግዚአብሔር መወለድ ከላይ መወለድ ነው፤ የተለየ ሕይወትና ተልዕኮ ይዘን ከላይ ተወልደናል። ታላቁ ተልዕኮ ከላይ የመጣ ተልዕኮ በመሆኑ በምድር ካለ ከየትኛውም ተልዕኮ የላቀ ትኩረትና ትጋት የሚጠይቅ ነው። እርሱ ተልዕኮውን ሰጥቶን ብቻችንን አልተወንም። እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ ብሏል።

ወንጌል ለመስበክ መፍራት የሌለብን በዚህ ምክንያት ነው።
የወንጌልን ተልዕኮ ለመፈጸም በምንሄድበት ሥፍራ ሁሉ እርሱ አብሮን አለ። የተልዕኮው ጌታ ሰዎችን በምናስተምረበትና በምንሰብክበት ሥፍራ ሁሉ አብሮን በመሆን ተአምራቱን ይገልጣል።

🙏ኢየሱስ ለሐዋሪያቱ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ ሲል ባዶ ተስፋ እየሰጣቸው አልነበረም። አብሮአቸው መሆኑን በድንቅና በተአምራት አሳይቷል። አንዳንዶች በወንጌል ስለሚያፍሩ ይህንን የተቀበሉትን አላማ ሕይወትና ተልዕኮ ለመፈጸም መነሳሳት ይጎድላቸዋል። ኢየሱስ የጠራን በወንጌል እንዳናፍርና በድፍረት እንድንሰብክ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ በዕብ12:2 ላይ ሲናገር “የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።” ይላል።

🛐ሁኔታውን ከተመለከትን እናፍራለን እንዲሁም እንፈራለን፤ኢየሱስን ከተመለከትን ግን ወንጌልን በመስበካችን ምክንያት የሚደርስብንን ነውር ንቀን እናልፋለን።
ኢየሱስ ኃጢአትን በመሸከም ነውርን ሁሉ ንቋል።ለኃጢአትኞች ለመሞት አላፈረም። የደረሰበትን ነውር ሳይሆን ከፊቱ ያለውን የክብርና ደስታ ተመለከተ። ያለ ሃፍረት የመስቀልን ሞት ታግሶ፤ ለአለም ሞተ።

በማቴ16:24 ላይ ሲናገር “በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።” አለ ይላል። የኢየሱስ ተከታይ መባልን ታፍራላችሁን? ከእርሱ ጋራ በእርሱ ስም መጠራትን ታፍራላችሁን? ወንጌልን ለመስበክ አትፈሩ። በክርስቶስ የተቀበላችሁትን ሕይወት ለመግለጥ አትፈሩ። ለኢየሱስ ለመቆም አትፈሩ። ኢየሱስን በግልጥ ስበኩ።

✝️መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሐዋሪያት ጉባኤ ሲናገር “ዕለት ዕለትም በመቅደስና በቤታቸው ስለ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ማስተማርንና መስበክን አይተዉም ነበር።” ይላል  —ሐዋርያት 5፥42።

👉ስለ ኢየሱስ እንዳታወሩ የሚያደርግ ሁኔታ ወይም ሕግ እንኳ ቢኖር ስለ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ መስበክ አትተው። ሰለ ኢየሱስ የሚሰብኩት ዕለት ዕለት እንጂ የሆነ የወንጌል ስርጭት ቀን ሲባል አልነበረም። ወንጌል መስበክና ስለ ኢየሱስ ማውራት የዕለት ተዕለት ሥራቸው ነው። ስለ ኢየሱስ ለማውራት ጊዜና ቦታ መምረጥ የለባችሁም፤ ሐዋሪያት  ቦታ ሳይመርጡ በቤትም በመቅደስም ስለ ኢየሱስ ይሰብኩ ስለ ነበረ እናንተም ቦታ ሳትመርጡ በቤትም፣ በሰፈርም ሁሉ ስለ ኢየሱስ መስበካችሁን አታቋርጡ።

🙏የዚህንም ውጤት መጽሐፍ ሲናገር “ ጌታም የሚድኑትን ዕለት ዕለት በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር።” ይላል(ሐዋርያት 2፥47)። ወንጌልን መናገር ካላቋረጣችሁ፤ የሚድኑ ዕለት ዕለት ይጨምራሉ። ሃሌሉያ!

🔥🔥🔥ጸሎት🔥🔥🔥
ውድ አባት ሆይ ስለ ቃልህ አመሰግንሃለሁ። አንተን ብቻ እያየሁኝ ያለ ሃፍረትና ፍርሃት ወንጌል እንድሰብክ እርዳኝ።በየዕለቱ በየትኛውም ሥፍራ ወንጌልን ለመስበክ ወስኜያለሁ።ለሰው ልጅ ያለህን ፍቅር በአገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ አውራለሁ።በኢየሱስ ስም ሜን
 
GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

24 Nov, 02:07

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH pinned «🛐በመንፈስ መስከር 🛐 “መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤”— ኤፌሶን 5፥18 🔥በመንፈስ መሞላት ያለ ጥርጥር በእርግጠኝነት የምታውቁትየምትረዱት ነገር ነው።በመንፈስ መሞላታችሁን ለማረጋገጥ የሆነ አይነት ስሜት እንዲሰማችሁ መጠበቅ የለባችሁም። በመንፈስ መሞላት በሁለንተናችሁ ማለትም በመንፈስ፣በነፍስና በሥጋ ላይ የመንፈሱ ተጽዕኖ በኃይል ሲታይ ማለት ነው። 🙏የእግዚአብሐር…»

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

24 Nov, 02:06

24 Nov, 02:05

🛐በመንፈስ መስከር 🛐

“መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤”— ኤፌሶን 5፥18

🔥በመንፈስ መሞላት ያለ ጥርጥር በእርግጠኝነት የምታውቁትየምትረዱት ነገር ነው።በመንፈስ መሞላታችሁን ለማረጋገጥ የሆነ አይነት ስሜት እንዲሰማችሁ መጠበቅ የለባችሁም። በመንፈስ መሞላት በሁለንተናችሁ ማለትም በመንፈስ፣በነፍስና በሥጋ ላይ የመንፈሱ ተጽዕኖ በኃይል ሲታይ ማለት ነው።

🙏የእግዚአብሐር መንፈስ በመንፈሳችሁ ላይ መለኮታዊ ተጽዕኖ አለው። በነፍሳችሁ(በስሜታችሁ፣ፈቃዳችሁና እውቀታችሁ)ላይ ሙሉ ተጽዕኖ አለው።እንዲሁም በሰውነታችሁ ላይ መልካም ተጽዕኖ ያሳድራል።
ሰውነታችሁ እየተንቀጠቀጠ ላይሆን፣ ወድቃችሁ ላይሆን፣የሆነ አይነት ሙቀት ላይሰማችሁ ይችል ይሆናል ነገር ግን ሰውነታችሁ በመንፈሱ ኃይልና ቁጥጥር መሆኑ ይታወቃችኋል።

🔥ከስሜት ያለ እውቀት ነው።ለምሳሌ ወንድ ወይም ሴት እንደሆናችሁ አይሰማችሁም።ጾታችሁን ባይሰማችሁም ታውቁታላችሁ። በመንፈስ መሞላትም ከስሜት ባለፈ እውቀት ነው።በመንፈስ መሞላት ማለት ይህ ነው።ይህ የአንድ ጊዜ ተግባር ሳይሆን በየዕለቱ የምንሞላው ነገር ነው።አንድም ቀን በመንፈስ ሳንሞላ ሊያልፈን አይገባንም።ያለ ማቋረጥ በመንፈስ የምትሞሉ ከሆነ ያለ ማቋረጥ ታሸንፋላችሁ።ሃሌሉያ
 ክርስቲያን ያለ መንፈስ ቅዱስ ሙላት ውጤታማ ሕይወት መኖር አይችልም።እያንዳንዳችን ያለ ማቋረጥ በመንፈስ ያለ ማቋረጥ እንድንሞላ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው።

✍️መንፈሳዊ ፍጥረት እንደመሆናችሁ ያለ መንፈስ ሙላት የምትኖሩት ሕይወት የባከነ ሕይወት ነው።በአልኮል ቁጥጥር ሥር ያለን ሰው፤በመንፈስ ቁጥጥር ሥር ካለ ሰው ጋር ያወዳድረዋል።በአልኮል ቁጥጥር ሥር ከመሆን በመንፈስ ቁጥጥር ሥር መሆን የተሻለና ማትረፍ መሆኑን እየገነረን ነው።በአልኮል ሞቅ ከማለት በመንፈስ ሞቅ ማለት ማትረፍ ነው።የእግዚአብሔር ልጆች ትክክለኛ ሕይወት ይህ ነው። የሚቆጣጠራችሁ፣የሚያነሳሳችሁ፣የሚመራችሁና የምትሆኑትን ሁሉ እንድትሆኑ የሚያደርጋችሁ ምንድነው?

✝️የእግዚአብሔር መንፈስ ነው ወይስ የዚህ አለም ነገር ነው?፤እንደ እግዚአብሔር ልጆች ለዚህ ሁሉ ጥያቄ መልስ የሚሆነው የእግዚአብሔር መንፈስ የሚለው ነው።
እንደ እግዚአብሔር ቃል አስተምህሮ ትክክለኛ ያልሆነው አስተሳሰብ"መንፈስ ቅዱስን የምንሞላው ስለሚጎድለን ወይም ከእኛ ስለሚወጣ ነው"የሚል ነው።ይህ ትክክለኛ አስተሳሰብ አይደለም።የምንሞላው ከውጪ ሳይሆን በውስጣችን ያለው መንፈስ እኛነታችንን እንዲቆጣጠር ስንፈቅድ ነው።በመክፈቻ ላይ ያለውን "መንፈስ ይሙላባችሁ"የሚለውን የግሪኩን ትርጉም ብንመለከት መሞላቱ የአንድ ጊዜ ሳይሆን ያለ ማቋረጥ የሚሆን እንደሆነ ይናገራል።በመንፈስ መሞላት ለስኬትና  ደስተኛ ሕይወት መሠረት ነው።

🔥ጸሎት🔥

አባት ሆይ ስለ መንፈስህ ስጦታ አመሰግንሃለሁኝ።በመንፈስ መሞላት ምን እንደሆነ ስለገባኝ አልወዛገብም። ቃልህን ያለ ማቋረጥ ባጠናሁና በጸልይኩኝ መጠን ያለ ማቋረጥ እለመልማለሁኝ።በኢየሱስ ስም አሜን

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

24 Nov, 02:05

Shalom Shalom

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

22 Nov, 03:03

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH pinned «🔥ሕይወትን ሊሰጠን መጣ🔥            “ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።”  — ዮሐንስ 10፥10 ✍️ክርስትና ከእኛ ርቆ በሚኖር እግዚአብሔር እንድንከተለው የተቀመጠልን ሕግና ሥርዐት አይደለም።በሰማይ ወደሚኖር እግዚአብሔር ለመድረስ የሚደረግ መፍጨርጨርም አይደለም።ክርስትና በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት እግዚአብሔር የተናገረውን…»

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

22 Nov, 02:38

🔥ሕይወትን ሊሰጠን መጣ🔥
         
 “ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።”
 — ዮሐንስ 10፥10

✍️ክርስትና ከእኛ ርቆ በሚኖር እግዚአብሔር እንድንከተለው የተቀመጠልን ሕግና ሥርዐት አይደለም።በሰማይ ወደሚኖር እግዚአብሔር ለመድረስ የሚደረግ መፍጨርጨርም አይደለም።ክርስትና በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት እግዚአብሔር የተናገረውን ለመፈጸም መጣርም አይደለም።

🙏ኢየሱስክርስቶስ በሕይወታችን ሊሰራና ሊፈጸም የመጣው ምን እንደሆነ ማወቅ አለብን።እርሱም ከሙታን በመነሳቱ ማን እንደሆንን እና ምንእንደተሰጠን ማወቅ አለብን።ይህ መረዳት ሲኖራችሁ ክርስትናንበቅጡ ትረዳላችሁ።

ኢየሱስ አዲስ ኃይማኖት ሊመሠርት አይደለም የመጣው።ኢየሱስ የመጣው መለኮታዊውን የእርሱን ሕይወት ሊሰጠን ነው የመጣው። ለአለም የሞተበት አላማ ከኃጢአት ሊያድን እና አለም የእርሱን የማይጠፋ ሕይወት ይካፈል ዘንድ ነው። ታዲይ ይህ ሕይወት ምንድነው?“

✝️አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ደግሞ ለወልድበራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና።”  — ዮሐንስ 5፥26

👉“በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች።”  — ዮሐንስ 1፥4 የሚለው ይህንን ሕይወት ነው።ብዙዎች የሚኖሩት 👉🛐በሮሜ7:15  ጳውሎስ ዳግም ከመወለዱ በፊት የኖረውን ሕይወትነው።“የማደርገውን አላውቅምና፤ የምጠላውን ያን አደርጋለሁና ዳሩግን የምወደውን እርሱን አላደርገውም።”  — ሮሜ 7፥15

🙏የእግዚአብሔርን ሕይወት ካልተካፈላችሁ በእግዚአብሔር መንገድ መጓዝ አትችሉም።ስለዚህ ክርስትና ሰውሕግና ሥርዐትን በመጠበቅ በእግዚአብሔር መንገድ ለመሄድየሚያደርገው ጥረት አይደለም።ክርስትና የእግዚአብሔርን ሕይወትበመካፈልና በመግለጥ ያለ ትግል በእርሱ መንገድ መጓዝ መቻልነው።

🙏ክርስትና የእርሱን ሕይወት በመግለጥ እርሱ ራሱ በምድር እንደኖረና እንደተመላለሰ መመላለስ ነው።ዳግም መወለድ ማለትእንዲህ ነው።በመንፈሳችሁ ውስጥ የእርሱን ሕይወት መሞላትናያንንም ሕይወት መግለጥ ነው።ይህንን ሕይወት ስትካፈሉ ደካማና ተራ ሰው መሆን ታቆማላችሁ።

🔥ምስጋና🔥

አባት ሆይ ዳግም ስለተወለድኩኝ አመሰግንሃለሁኝ። በመንፈሴውስጥ የአንተን ሕይወት ተካፍያለሁኝ።እኔ ተራና ምናምንቴ ሰውአይደለሁኝም። የአንተን ሕይወት ተሞልቼያለሁኝ። ከዚህም የተነሳ በፍቅር፣በጽድቅና በጤንነት እመላለሳለሁኝ።

🙏በኢየሱስ ስም አሜን🙏
 
GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

22 Nov, 02:38

amazing Nazaret coyire yayehut

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

22 Nov, 02:38

Shalom

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

14 Nov, 02:59

Shalom Shalom

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

14 Nov, 02:59

🔥ምድርን በወንጌል ሙሉአት🔥

🙏እንዲህም አላቸው ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ፡፡” ማርቆስ 16፥15

👏እግዚአብሔር ባላችሁበት መሥሪያ ቤት፣ የንግድ ቦታ፣ትምህርት ቤት፣ ሰፈር ውስጥ፣ በቤተሰቦቻችሁ ያስቀመጣችሁ፤ እናንተ ውስጥ ባለው የወንጌል ብርሃን እና ጨውነት ጠላት ሰዎችን እንዳያጠፋ ሰዎችን በእግዚአብሔር ቃል ከጥፋት እንድትጠብቁና እንድታበጁ ነው። እናንተ በዚያ ስፍራ ከመቀመጣችሁ የተነሳ ሰዎች ከክፉ ሊጠበቁ ይገባል። እናንተ የምድር ጨው ናችሁ። የጨው አንዱ ሥራ ምግብ እንዳይበላሽና ለተፈለገው ጊዜ እንዲቆይ ማድረግ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ እስኪመለስ ድረስ ሰዎች ወደ ድህነት እንዲመጡ፤ ከጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን እንዲመጡ የምስራች የሆነውን የክርስቶስን ወንጌል የምትናገሩት እናንተ ናችሁ።

👉መጽሐፍ ሲናገር “በሚመጣው ዘመን ያዕቆብ ሥር ይሰድዳል፥ እስራኤልም ያብባል ይጨበጭብማል፤ በፍሬያቸውም የዓለሙን ፊት ይሞላሉ። ”ይላል ኢሳይያስ 27፥6። ወንጌልን ተምራችሁ ሥር የሰደዳችሁት፤ በወንጌል የዓለሙን ፊት እንድትሞሉ ነው።

🙏ሐዋሪያት በወንጌል ትምህርት ተጽዕኖ በፈጠሩ ጊዜ፤ “ሊቀ ካህናቱም፦ በዚህ ስም እንዳታስተምሩ አጥብቀን አላዘዝናችሁምን? እነሆም፥ ኢየሩሳሌምን በትምህርታችሁ ሞልታችኋል፤ ።” አሉአቸው ይላል
ሐዋርያት 5፥28 ሃሌሉያ!!!

👉እየሩሳሌምን በትምህርታቸው (በወንጌል) እንደሞሉ ይህም የተገለጠ እንደነበረ የሚቃወሟቸው ራሳቸው ሲመሰክሩ እናያለን፡፡ ሐዋሪያት በዘመናቸው ፍሬያቸውን ሁሉ በምድር ላይ አበዙት፣ አስፋፉት እንዲሁም በትምህርታቸው ገዝተው ወደ ጌታቸው ሄደዋል

👉በዚህ ዘመን ተራው የአንተ፣ የአንቺ፣ የእኔ፣ የእኛ ነው!
እግዚአብሔር ባስቀመጠን ስፍራ ለወንጌል መቆም፣የትኛውንም አዋጅ የማንፈራ፣ ለትውልድ የምንማልድ፣ አስታራቂዎች መሆን አለብን። ከሁሉ በፊት ወንጌል ማስቀደማችሁን መርሳት የለባችሁም። በየትኛውም ሥፍራ ብትሆኑ የክርስቶስ ተወካይ፣ እርሱን የምታሳዩና የምታስተዋውቁ መሆናችሁን እወቁ።

🙏ባላችሁበት ስፍራ ራሳችሁን ክርስቶስን ወክሎ እንደተላከ ሰው ተመልከቱ። እናንተ  ጋር የደረሰው ወንጌል ወደ ሌላ ሥፍራ እንዲስፋፋና እንዲሰራጭ አድርጉ። እኛ ውስጥ ያለው የሕይወት ውሃ ኩሬ(የማይፈስ) ሳይሆን የሕይወት ውሃ ወንዝ ነው። ኩሬ ማለት በአንድ ሥፍራ ተወስኖ የሚቀመጥ፣ የማይፈስ የታቆረ ውሃ ነው። ወንዝ ደግሞ በባሕሪው አንድ ቦታ ተወስኖ የሚቀር ሳይሆን ቋንቋ፣ ባሕር፣ የቆዳ ቀለም ሳይል ድንበር ተሻግሮ የሚሄድ ነው። በእናንተ ውስጥ ያለው የወንጌል እውነት እንዲሁ እንደ ወንዝ ውሃ የሚፈስና ብዘዎች ጋር የሚደርስ መሆን አለበት። ሃሌሉያ!!!

🔥🔥🔥ጸሎት🔥🔥💕

ውድ አባት ሆይ፣ በዓለም ዙሪያ ሁሉ የአንተን እውነት እንድሰብክ እና እንዳስፋፋ በወንጌል አገልግሎት ውስጥ አብሮ ሰራተኛ እንድሆን ስለ ሰጠኸኝ ጸጋ አመሰግናለሁ። ስለ ክርስቶስ በመመስከር እና ስለ እርሱ የማዳን ጸጋ በመናገር የወንጌል ወንዝ እንዲፈስ አደርጋለሁ

🙏በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን።🛐

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

12 Nov, 02:34

    🔥ታላቅ  ተልዕኮ ላይ ነን🔥

🛐እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።” ማቴዎስ 28፥19-20

መጽሐፍ ቅዱስ በዕብ12:2 ላይ ሲናገር “የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።” ይላል።

🛐ሁኔታውን ከተመለከትን እናፍራለን እንዲሁም እንፈራለን፤ኢየሱስን ከተመለከትን ግን ወንጌልን በመስበካችን ምክንያት የሚደርስብንን ነውር ንቀን እናልፋለን።
ኢየሱስ ኃጢአትን በመሸከም ነውርን ሁሉ ንቋል።ለኃጢአትኞች ለመሞት አላፈረም። የደረሰበትን ነውር ሳይሆን ከፊቱ ያለውን የክብርና ደስታ ተመለከተ። ያለ ሃፍረት የመስቀልን ሞት ታግሶ፤ ለአለም ሞተ።

በማቴ16:24 ላይ ሲናገር “በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።” አለ ይላል። የኢየሱስ ተከታይ መባልን ታፍራላችሁን? ከእርሱ ጋራ በእርሱ ስም መጠራትን ታፍራላችሁን? ወንጌልን ለመስበክ አትፈሩ። በክርስቶስ የተቀበላችሁትን ሕይወት ለመግለጥ አትፈሩ። ለኢየሱስ ለመቆም አትፈሩ። ኢየሱስን በግልጥ ስበኩ።

✝️መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሐዋሪያት ጉባኤ ሲናገር “ዕለት ዕለትም በመቅደስና በቤታቸው ስለ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ማስተማርንና መስበክን አይተዉም ነበር።” ይላል  —ሐዋርያት 5፥42።

👉ስለ ኢየሱስ እንዳታወሩ የሚያደርግ ሁኔታ ወይም ሕግ እንኳ ቢኖር ስለ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ መስበክ አትተው። ሰለ ኢየሱስ የሚሰብኩት ዕለት ዕለት እንጂ የሆነ የወንጌል ስርጭት ቀን ሲባል አልነበረም። ወንጌል መስበክና ስለ ኢየሱስ ማውራት የዕለት ተዕለት ሥራቸው ነው። ስለ ኢየሱስ ለማውራት ጊዜና ቦታ መምረጥ የለባችሁም፤ ሐዋሪያት  ቦታ ሳይመርጡ በቤትም በመቅደስም ስለ ኢየሱስ ይሰብኩ ስለ ነበረ እናንተም ቦታ ሳትመርጡ በቤትም፣ በሰፈርም ሁሉ ስለ ኢየሱስ መስበካችሁን አታቋርጡ።

🙏የዚህንም ውጤት መጽሐፍ ሲናገር “ ጌታም የሚድኑትን ዕለት ዕለት በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር።” ይላል(ሐዋርያት 2፥47)። ወንጌልን መናገር ካላቋረጣችሁ፤ የሚድኑ ዕለት ዕለት ይጨምራሉ። ሃሌሉያ!

🔥🔥🔥ጸሎት🔥🔥🔥
ውድ አባት ሆይ ስለ ቃልህ አመሰግንሃለሁ። አንተን ብቻ እያየሁኝ ያለ ሃፍረትና ፍርሃት ወንጌል እንድሰብክ እርዳኝ።በየዕለቱ በየትኛውም ሥፍራ ወንጌልን ለመስበክ ወስኜያለሁ።ለሰው ልጅ ያለህን ፍቅር በአገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ አውራለሁ።በኢየሱስ ስም ሜን
 
GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

12 Nov, 00:10

Shalom Shalom

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

10 Nov, 01:02

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH pinned «             🔥ዋጋችሁን ዕወቁ🔥እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤”  — 1ኛ ጴጥሮስ 2፥9 ከልጅነታችን ጀምረን ባለማወቅ ስንዘምራቸው ቆይተናል።ምንኛ ጎስቋላና የማረባ ምስኪን ነኝ እያሉ መዘመር እግዚአብሔርን አያከብርሃም።ዳግም ተወልዳችሁ ከሆነ፤ምናምንቴና ደካማ ሰዎች…»

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

10 Nov, 01:02

             🔥ዋጋችሁን ዕወቁ🔥

እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤”  — 1ኛ ጴጥሮስ 2፥9

ከልጅነታችን ጀምረን ባለማወቅ ስንዘምራቸው ቆይተናል።ምንኛ ጎስቋላና የማረባ ምስኪን ነኝ እያሉ መዘመር እግዚአብሔርን አያከብርሃም።ዳግም ተወልዳችሁ ከሆነ፤ምናምንቴና ደካማ ሰዎች አይደላችሁም።እናንተ ልጆች ናችሁ። ሰማይና ምድርን የፈጠረ ልዑል እግዚአብሔር ልጆች ናችሁ ዮሐ1፥12-13)። ማንነታችሁ በምድራዊ ቤተሰቦቻችሁ፣አካውንት ውስጥ ባላችሁ፣በትምህርት ደረጃችሁና በባለፈው ሕይወታችሁ  የሚወሰን አይደለም።

መጽሐፍ ሲናገር ማቴዎስ 13¯¯¯⁴⁵ "ደግሞ መንግሥተ ሰማያት መልካምን ዕንቁ የሚሻ ነጋዴን ትመስላለች፤⁴⁶ ዋጋዋም እጅግ የበዛ አንዲት ዕንቁ በአገኘ ጊዜ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ገዛት"ይላል።እግዚአብሔር በእናንተ ውስጥ ውድ ዕንቁ አንዳለ ስለተመለከተ ነው ውድና ዕንቁ የሆነውን ልጁን ሰጥቶ የገዛን።

ለምሳሌ ምርጡን  ልብስ ለብሳችሁ እየሄዳችሁ ሳለ ሳንቲም ጭቃ ውስጥ ቢወድቅ ለማውጣት ጭቃ ውስጥ በመግባት ልብሳችሁን አታበላሹም።የሳንቲም ዋጋ ብዙም ስላልሆነ መንገዳቸሁን ትቀጥላላችሁ።ነገር ግን የአንድ ሚሊዬን ብር ቼክ ጭቃ ውስጥ ቢወድቅባችሁ፤የለበሳችሁት ልብስ ምንም ያህል ቢበላሽ ቼኩን ገብታችሁ ታወጡታላችሁ።

🙏እግዚአብሔር ከገባችሁት የኃጢአት ጭቃ እናንተን ለማውጣት አንዲያና ምርጡን ልጅ ሰደደው።እናንተ ውድ ባትሆኑ ልጁን ባላከ ነበር።መጽሐፍ ሲናገር “ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።”ይላል  — 1ኛ ጴጥሮስ 1፥18-19።

👉የእናንተ ዋጋ ከብርና ወርቅ ይበልጣል።እግዚአብሔር በብርና ወርቅ አይደለም የገዛችሁ።የእናንተ ዋጋ ከብርና ወርቅ የላቀ ነው።እናንተ በክቡር ደም የተዋጃችሁ ናችሁ።መዋጀት ማለት ዋጋ ከፍሎ መልሶ የራስ ማድረግ ማለት ነው።በከበረ ደም እንደተዋጃችሁ ካወቃችሁ፣የከበራችሁና ልዩ መሆናችሁን ታውቃላችሁ።

🔥ጸሎት🔥

አባት ሆይ የከበረ ዋጋ ስለከፈልክልኝ አመሰግንሃለሁኝ።ዳግም በመወለደ የተለየውና ድንቅ ነኝ።በዋጋ የተገዛሁኝና የተወደድኩኝ ሰው ነኝ።ምናምንቴ ሳልሆን የከበርኩ ልጅ ነኝ።

🙏በኢየሱስ ስም አሜን

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

08 Nov, 03:41

Shalom

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

08 Nov, 03:41

           🔥ከእሳት ተናጠቁ🔥

" 🙏አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፥ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ፥"
(የይሁዳ መልእክት 1: 22)

🛐በምድር ላይ ያለነው በዋናነት ላልዳኑ ሰዎች ብርሃን እንድንሆን ነው ፤የምስራቹን ወንጌል በመስበክ ሰዎችን ከጨለማ ወደ ብርሃን እንድናመጣ ነው፡፡ሰዎችን እግዘዚአብሔር እንደሚወዳቸውና  በክርስቶስ የመስቀል ሥራ ሃጢአታቸውን ይቅር እንዳላቸው ሊንነግራቸው ያስፈልጋል፡፡

🙏ከላይ ባለው ክፍል ወደ ጥፋት እሳት የሚሄዱ ሰዎችን ማዳን የእኛ ሃላፊነት እንደሆነ ይናገራል፡፡ሰዎችን ካሉበት እሳት ነጥቃችሁ  የምታድኑት በምልጃና በእምባ ፀሎታችሁ ነው፡፡

😇ያልዳኑ ጓደኞቻችሁ ወይም የስራ ባልደረቦቻችሁ ወይም ዘመዶቻችሁ ወደ ሲኦል እሳት እንዲገቡ አትፍቀዱ፡፡እናንተ የዳናችሁት ሌሎችን ለማዳን ነው ፥እኔ ከዳንኩ ስለ ሌላው ምን አገባኝ የሚል የራስወዳድነት አስተሳሰብን አስወግዱ ፥እናንተም ጌታን እንድተትቀበሉ በሆነ አጋጣሚ ወንጌል የመስማት ዕድል ስላገኛችሁ ነው ያመለጣችሁት ፥ ለሌሎችም ይህንን ወንጌል የመስማት ዕድል እንዲያገኙ አድርጉ፡፡

በ2ቆሮ 4፥4 ላይ " ለእነርሱም የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ።" ይላል

🙏በምልጃ ፀሎታችሁ  ሰይጣን ያስቀመጠውን ያንን ጨለማና ዕውርነት መግፈፍ ትችላላችሁ፡፡ይህንን የምታደርጉት ሰዎቹ እስኪድኑ ድረስ ነው ፡፡ይህ ሰው የሚድን አይመስልም መድከም መልፋት የለብኝም ብላችሁ በፍፁም ተስፋ አትቁረጡ ምክንያቱም ማንም ይጠፋ ዘንድ  የጌታ ፍቃድ አይደለም በልባቸው የወንጌል ብርሃን ይብራ እያላችሁ ልታውጁ ይገባል፡፡
ከላይ ያለው ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ የሚለው አንዳንዶቹ እንደሚያስቡት ሲዖል ከገቡ ብሁዋላ እንደገና ለማውጣት መጣር ሳይሆን አስቀድሞ ወደዚያ እንዳይገቡ ለእነርሱ በእምባ መፀለይ ነው፡፡

👉እስቲ በቤቻችሁ ፥በአከባቢያችሁ ፥በሥራ ቦታችሁ ስንት ያልዳኑ ሰዎች እንዳሉ አስቡ፡፡ታዲያ ይህን የሚያክሉ ያልዳኑ ሰዎች ዙሪያችሁን ከበው እያለ እንዴት ችላ ትላላችሁ? ፣ወደመዳን እስኪመጡና ክርስቶስን እስኪቀበሉ ድረስ ማረፍ የለባችሁም ፥ለእነርሱ መፀለይ ብቻ አይበቃም ቀርባችሁ ጌታ እንደሚወዳቸው ንገሩዋቸው ፥ካልተቀበሉ አሁንም መፀለያችሁን ቀጥሉ ፥ሌላ ጊዜም ቀርባችሁ  ንገሩዋቸው ፤ሙሉ በሙሉ ልባቸው እስኪሸረሸር አታቁሙ፡፡
አብራችሁ  እየዋላችሁ ፥ እየተጫወታችሁ ፥እየሰራችሁ ወንጌል ያልነገራችሁት ስንት ሰው አለ?

👏በመርከቡ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ጳውሎስ እዚያ በመገኘቱ ምክንያት ከሞት እንደ ዳኑ ፥እናንተ የምትገኙበት ቦታ ሰዎች እንዲጠፉ አትፍቀዱ፡፡በነፍሳት ጉዳይ ላይ አትቀልዱ ፥ሰይጣን ከጉያችሁ ነጥቆ እንዲወስድ አታድርጉ፡፡ኢየሱስ ለአንዲት ነፍስ ገዶት ብዙ ርቀቶችን በእግሩ ሄዷል ፥

👏እናንተም የነፍሳትን ዋጋ እወቁ፡፡የማስታረቅ አገልግሎታችሁን በፍጹም አሳንሳችሁ አትዩ ፥ሰዎችን ወደዚህ ድንቅ ህይወት ጋብዙ ፥ወንጌል የሚታፈርበት አይደለም  ፥ለሰዎች ስለ እርሱ ለማውራት እንዴት ታፍራላችሁ?የሚያጋጥማችሁን እያንዱን ዕድል ወንጌል ለመስበክ ተጠቀሙት፡፡

🔥ጸሎት 🔥

👉ድንቅ አባት ሆይ የወንጌልን እውነት ሰምቼ ከድቅድቅ ጨለማ እንዳመልጥ ስላደረከኝ አመሰግንሃለሁ ፡፡ወንጌለን መስበክ ዋና ሥራዬ በማድረግ ላልዳኑ ነፍሳት ሸክም እንዲሰማኝ እርዳኝ፡፡አንተ የማንንም መጥፋት አትፈልግም ፥ሰይጣን በአከባቢዬ ሰዎችን እንዲያጠፋ አልፈቅድም፡፡ሰዎችን ከእሳት ነጥቀ አወጣለሁኝ ፡፡

🔥በኢየሱስ ስም አሜን🔥
 
GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

06 Nov, 02:51

🔥የአብርሃም በረከት ወደ እናንተ ደርሷል🔥

ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም አከብረዋለሁ፤ ለበረከትም ሁን፤³ የሚባርኩህንም እባርካለሁ፥ የሚረግሙህንም እረግማለሁ፤ የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ ይባረካሉ። ዘፍጥረት 12፡2

🛐ብዙ ቅዱሳን ምንም እንኳ በክርስቶስ ኢየሱስ ሁለንተናዊ በረከት የተባረኩ ቢሆንም ይህ በረከት በሕይወታቸው ተገልጦ የማይታየው የዚህ በረከት አሰተሳሰብ ስለሌላቸው ነው።

✍️መጽሃፍ እንደሚል ሰው በልቡ እንደሚያስበው እንደዚያው ነው። መባረኩን ሁልጊዜ የሚያስብ በዚያ በረከት ይመላለሳል። በክርስቶስ የተባረከ እርግማን የሌለበት ቢሆንም፤ እርግማን እንዳለበት የሚያስብ ከሆነ በሕይወቱ የእግዚአብሔርን በረከት መለማመድ ይሳነዋል። “

🔥ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።” ሮሜ 8፥6።

ሕይወትም ሞትም ያለው በሃሳባችሁ ውስጥ ነው። ስለ ሥጋ (ሽንፈት፣ እርግማን፣ኃጢአት) እያሰባችሁ የሕይወትና የሰላም በረከት አይሆንላችሁም። ስለ መንፈስ ማሰብ ማለት እግዚአብሔር ዳግም በተወለደው መንፈሳችሁ ውስጥ ያስቀመጠውን በረከት ማሰብ ነው።

አብርሃም እግዚአብሔር ሳይጠራው በፊት ይመላለስ የነበረው በአገሩ፣ በዘመዶቹ፣ በአባቱ ቤት በነበረ አይነት ምልልስ ነበር።እግዚአብሔር ተገለጠለትና ከአገሩ፣ ከዘመዶቹ እንዲሁም ከአባቱ ተለይቶ እርሱ ወደሚያሳየው ምድር እንዲወጣ ይህንም ሲያደርግ ታላቅ ሕዝብ እንደሚያደርገው፣ ስሙን እንደሚያከበረውና ለበረከት እንደሚያደርገው ተናገረው።

👉እናንተም በክርስቶስ ኢየሱስ የአብርሃም ዘር ተደርጋቹሃል።ይህንን የአብርሃምን በረከት ለመውረስና ለመግለጥ ተጠርታችኋል። “

🛐እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ፡፡“ ገላትያ 3፡29

🛐በገላትያ 3፥14 ላይ “የመንፈስን ተስፋ በእምነት እንድንቀበል፥ የአብርሃም በረከት ወደ አሕዛብ በእየሱስ ክርስቶስ ይደርስላቸው ዘንድ።” ወደዚህ በረከት በደረስኩ! ማን ወደዚህ በረከት ያደርሰኛል ማለት አያስፈልግም።

🙏በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ወደ እናንተ ደርሷል።እግዚአብሔር የበረከት፣ የሙላት፣ የመትረፍረፍ፣ የሚበዛ ሕይወትን በእምነት ወራሽ አድርጓችኋል።  ታላቅነት የእናንተ ነው!! የከበረ ስም የእናንተ ነው!! ለበረከት መሆን የእናንተ ነው።

የሚባርኩህንም እባርካለሁ፤ የሚረግሙህንም እረግማለሁ፤ የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ ይባረካሉ፡፡“ ዘፍጥረት 12፡3

🔥እናንተ የተባረካችሁ ስለሆናችሁ በማንም ልትረገሙ አትችሉም። እናንተን የሚባርክ በእግዚአብሔር የተባረከ ይሆናል። እናንተን የሚረግም የተረገመ ይሆናል። እናንተ በየትኛው የክፉ ኃይል እርግማን ልትጎዱና ልትቆሙ አትችሉም።የሚጨነግፍ ነገር የላችሁም፡፡

👏እግዚአብሔር ሥራችሁን፣ አገልግሎታችሁን፣ ስማችሁን ሲያከብረው፤ በእናንተ ምክንያት የምድር እርግማን ሲሰበርና ለበረከት ስትሆኑ በእምነትተመልከቱ።
 
🔥ጸሎት🔥
አባት ሆይ እየባረክ ስለባረከኝ አመሰግንሃለሁ። ለበረከት እንድሆን ስለጠራኸኝ አመሰግንሃለሁ። በእኔ ውስጥ ባስቀመጥከው በረከት አከባቢዬን፣ ቤተሰቤን እና ሃገሬን እባርካለሁ። ይህንንም ማድረግ እችል ዘንድ ጸጋህ ስለሚያግዘኝ አመሰግንሃለሁ። ታላቅነትና ክብር የእኔ ነው። በኢየሱስ ስም አሜን!

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

06 Nov, 02:51

Shalom Shalom

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

05 Nov, 03:22

ደስ ብሎይኛል በቤትህ
amazaning live worship

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

05 Nov, 03:22

bereket tefsfaye full albums

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

03 Nov, 03:04

ተከናወኑ

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

03 Nov, 03:04

መዝ 150: 6 እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርንያመስግን።
 
ሃሌ ሉያ።

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

03 Nov, 02:01

🔥በምስጋና እውቅና ስጡ 🔥

የእምነትህም ኅብረት፥ በእኛ ዘንድ ያለውን በጎ ነገር ሁሉ በማወቅ፥ ለክርስቶስ ኢየሱስ ፍሬ እንዲያፈራ እለምናለሁ፤”
 — ፊልሞና 1፥6

ብዙ ቅዱሳን በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔር ለሰራላቸው ሥራ ዋጋ መስጠት አይችሉም።ከዚህም የተነሳ እምነታቸውን ለሌሎች ማካፈል ይሳናቸዋል፤ በመስቀል የተፈጸመውን ሥራ ታላቅነትና ዋጋ መመልከት ይሳናቸዋል።በክርስቶስ ከተፈጸመላቸው ሥራ ይልቅ ይበልጥ የሚያሳስባቸው የዚህ አለም ነገር ነው።ምን እንበላለን፣ምን እንጠጣለን፣ምን እንለብሳለን ብለው አብዝተው ይጨነቃሉ።

👉ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?”የሚለውን ቃል ረስተዋል  — ማቴዎስ 6፥25

ዳግም በመወለዳችሁና የኃጢአት ተፈጥሮ በጽድቅ ተፈጥሮ በመተካቱ በምስጋና መሞላት አለባችሁ።
በመንፈሳችሁ ውስጥ የራሱ የእግዚአብሔር ተፈጥሮና ሕይወት በመሸከማችሁ በሀሴትና ምስጋና መሞላት አለባችሁ።

🙏የእግዚአብሔር ኃይል የሆነው መንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ናችሁ።እርሱ መኖሪያውን በእናንተ አድርጓል።ከእርሱ ጋር አንድ ሆናችሁ ከእርሱ ጋር አብሮ ሰራተኛና አብሮ ወራሽ በመሆናችሁ መደነቅና መገረምን ልትሞሉ ይገባል።

🛐እግዚአብሔር ለሕይወትና እርሱን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለሰጥቶአችኋል 2ጰጥ1:3)።

ይህ ትልቅ ዋጋ ልትሰጡ የሚገባ ነገር ነው።ለገንዘብ፣ለሰጣችሁ መብል፣የሥራ ዕድል፣ጤንነት ማመስገን መልካም ነው ነገር ግን እነዚህ ነገሮች የሌሉ እንኳ ቢመስል አሁን በምስጋና መሞላት ትችላላችሁ።ምክንያቱም ከእነዚህ ነገሮች ያለፈ አስደናቂ ነገሮችን በውስጣችሁ ተሸክማችኋል።

በመንፈሳችሁ ያሉትን መንፈሳዊ በረከቶችን ስታውቁና ስለ እነርሱ ስታመሰግኑ ፤እነዚህ መንፈሳዊ በረከቶች የሚያስፈልጓችሁን ሥጋዊ በረከቶችን ይወልዳሉ።

ኤሳውን ተመልከቱት በሚበልጠው በእግዚአብሔር ነገር ላይ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ ብኩርናውን በምግብ ለወጠ።እግዚአብሔር የሰጠውን ነገር ማድነቅ አልቻለም።

ዕብራውያን 12
¹⁶ ወይም ስለ አንድ መብል በኵርነቱን እንደ ሸጠ እንደ ዔሳው ለዚህ ዓለም የሚመች ሰው እንዳይሆን ተጠንቀቁ።¹⁷

ከዚያ በኋላ እንኳ በረከቱን ሊወርስ በወደደ ጊዜ እንደ ተጣለ ታውቃላችሁና፤ በእንባ ተግቶ ምንም ቢፈልገው ለንስሐ ስፍራ አላገኘምና"።እንደ ኤሳው አትሁኑ።ኤሳው የተሰጠውን ትልቅ ዋጋ ያለውን መንፈሳዊ በረከት ከገጠመው ጊያዊ ሁኔታና የርሃብ ስሜት የተነሳ ማየትና ማመስገን ያልቻለ ሰው ነው።

👉እግዚአብሔር የሰጣችሁን ነገር አድንቁ፣አክብሩት።በክርስቶስ የተቀበላችሁትን የሕይወትና የጽድቅ በረከቶችን አክብሩ።እምነታችሁ ፍሬ የሚያፈራው በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔር በውስጣችሁ ያስቀመጠውን በጎ ነገር እውቅና ሰጥታችሁ ስታመሰግኑ ነው።ዋናው ነገር ላይ በክርስቶስ ኢየሱስ ባላችሁ በረከት ላይ ትኩረት አድርጉ።ያን ጊዜ ተአምራቶችና በረከቶች በሕይወታችሁ ይገለጣሉ።

መዝ 50: 23 የምስጋናን መሥዋዕት የሚሠዋ ያከብረኛል፤መንገዱንም ቀና ለሚያደርግ የእግዚአብሔርን ማዳን አሳየዋለሁ።”አ.መ.ት

🔥ጸሎት🔥

አባት ዛሬ በክርስቶስ ኢየሱስ ስለተሰጡኝ በረከቶችና ጸጋዎች አመሰግንሃለሁኝ።ሕይወትህን እካፈል ዘንድ ልጅህን ስጦታ አድርገህ ስለሰጠሄኝ ከልቤ አመሰግንሃለሁኝ። አንተ መልካም ነህ በሕይወቴም የምታደርገው ሁሉ መልካም ነው።በኢየሱስ ስም አሜን።
 
GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

03 Nov, 02:01

Shalom Shalom

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

02 Nov, 02:43

Shalom Shalom

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

02 Nov, 01:58

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH pinned «በእግዚአብሔር ፊት ብቁ ተደርጋችኋል “🔥ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆንዘንድ በክርስቶስ መረጠን።”  — ኤፌሶን 1፥4 የብዙዎች ትልቁ ችግር የኃጢአትኝነትና የበደለኝነት አስተሳሰብ ነው። የኃጢአተኝነት አስተሳሰብ ብዙዎች እምነታቸውን እንዲጥሉ በእምነት መመላለስ እንዲያቆሙ እና በእግዚአብሔር መልካምነት ማመን እንዲያቆሙ አድርጓቸዋል። ✍️የኃጢአተኝነትአስተሳሰብ በክርስቶስ…»

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

02 Nov, 01:58

በእግዚአብሔር ፊት ብቁ ተደርጋችኋል

🔥ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆንዘንድ በክርስቶስ መረጠን።”
 — ኤፌሶን 1፥4

የብዙዎች ትልቁ ችግር የኃጢአትኝነትና የበደለኝነት አስተሳሰብ ነው። የኃጢአተኝነት አስተሳሰብ ብዙዎች እምነታቸውን እንዲጥሉ በእምነት መመላለስ እንዲያቆሙ እና በእግዚአብሔር መልካምነት ማመን እንዲያቆሙ አድርጓቸዋል።

✍️የኃጢአተኝነትአስተሳሰብ በክርስቶስ ኢየሱስ የተሰጣቸውን እንዳያምኑና እንዳይቀበሉ አድርጓቸዋል። በመሠረታዊነት ብዙ ሰዎችን በኃጢአት ልምምድ ውስጥ እንዲቆዩ የሚያደርጋቸው ይህ የኃጢአተኝነት ናየበደለኝነት አስተሳሰብ ነው።

እንደ እግዚአብሔር ልጆች አንዱ አስረግጠን ማወቅ ካለብን ነገርአንዱ የጸደቅን መሆናችን ነው።ለመጽደቅ እየተጣጣርን ያለን አይደለንም።ዳግም የተወለድን ዕለት ጻድቃን ተደርገናል። ጽድቅ ከጻድቁ እግዚአብሔር በመወለዳችን የተካፈልነው ነጻ ስጦታነው።

✍️ጽድቅ የተካፈላችሁት የእናንተ ተፈጥሮ መሆኑን ስታውቁ ጽድቅን ያለ ትግል ነው የምትኖሩትና የምትገልጡት።

🛐ጻድቅ መሆናችሁን ካላወቃችሁ በእግዚአብሔር ፊት ብቁ እንዳልሆናችሁ እና ጸልያችሁ እንኳ መልስን ለመቀበል እንደሚከብዳችሁ ታስባላችሁ።

🔥እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።”  — 2ኛ ቆሮ 5፥21

🔥ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።”  — ኤፌሶን 4፥24።

🎈ጌታን በተቀበላችሁበት በዚያን ቅጽበት ጻድቅ ልትሆኑ የቻላችሁት እንዴትነው?

ብሎ አንድ ሰው ሊጠይቅ ይችላል። እንዲህ ቅጽበታዊ ሊሆንአይችልም ሊል ይችላል።ጻድቅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ እኛ በእርሱምትክ ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ሆኗል። ብዙዎች ከእግዚአብሔር በረከታቸውን መቀበል የሚከብዳቸው እግዚአብሔርበሰጣቸው ጽድቅ ላይ ከማተኮር ይልቅ በአለመቻላቸውናበድካማቸው ላይ ስለሚያተኩሩ ነው።

✍️በረከትን፣ፈውስን ከመቀበል የሚከለክላቸውን ስህተት እንደሰሩ ሁልጊዜ ይሰማቸዋል።እውነቱ ግን የእግዚአብሔር ጽድቅ በመደረጋችሁ እግዚአብሔር ተስፋ የገባላችሁን የትኛውንም ነገርጠይቃችሁ መቀበል ትችላላችሁ።

ጻድቅ መሆናችሁን አውቃችሁይህንን የጽድቅ አስተሳሰብ ስትይዙ በታላቅነትና በአሸናፊነትከመመላለስ የሚከለክላችሁ የለም።

 “፥ በቅዱሳንም ርስት በብርሃን እንድንካፈል ያበቃንን አብን እያመሰገናችሁ፥ በነገር ሁሉ ደስ ልታሰኙ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱዘንድ እንለምናለን።”  — ቆላስይስ 1፥12።
አሁን ገና እንዲያበቃን እየጸለይን፣ እየተጠባበቅን አይደለም። የርስቱ ብርሃን ተካፋይአድርጎናል።ከእናንተ የሚጠበቀው በፊትህ ብቁ አድርገኝ ሳይሆን ብቁእንደተደረጋችሁ አውቃችሁ ማመስገን ነው።

ብዙዎች እኔ በፊቱጻድቅና ብቁ ተደርጌያለሁኝ ብለው መቀበል ይከብዳቸዋል።በክርስቶስከሆናችሁ ለመጽደቅ፣ለመውረስ፣ለመፈወስ፣እርሱን ለማስደሰት ብቁ ተደርጋችኋል።ትንሽና በእግዚአብሔር ፊት ብቁ እንዳልሆናችሁ በመናገር ጉድለት እንዳለባችሁ የሚናናገርን የኃይማኖት አትቀበሉ።

እናንተንም ነውርና ነቀፋ የሌላችሁና ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊትያቀርባችሁ ዘንድ፥ በፊት የተለያችሁትን ክፉ ሥራችሁንም በማድረግበአሳባችሁ ጠላቶች የነበራችሁትን አሁን በሥጋው ሰውነት በሞቱበኩል አስታረቃችሁ።”— ቆላስይስ 1፥21-22።

🙏ጥሉ በመስቀልተወግዷል።ጠላቶች የነበርን አሁን ተወዳጆችና ወዳጆችተደርገናል።እርሱ ኢየሱስ ኃጢአት ሆኖ የቀረበው እኛን ነውርና ነቀፋየሌለን አድርጎ በእግዚአብሔር ፊት ያቀርብ ዘንድ ነው።

🙏በራሳችሁመልካም ሥራ ቅዱስና ነውር አልባ ለመሆን አትጣሩ።በእርሱ ፊትበክርስቶስ ሆናችሁ ነውርና ነቀፋ አልባ መሆናችሁን ተቀበሉ።

🔥አዋጅ🔥

በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ጻድቅና ነውር አልባ ተደርጌያለሁኝ።ነውርና ነቀፌታ እንዳለብኝ የሚነግረኝን የጠላትንውሸት አልቀበልም። ኢየሱስ እንደ እኔ ኃጢአት ስለሆነ እኔ ደግሞ እንደ እርሱ ጽድቅ ተደርጌያለሁኝ።

🙏በኢየሱስ ስም አሜን🙏

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

25 Oct, 02:29

Live stream finished (12 days)

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

25 Oct, 02:21

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH pinned «    🔥ታላቅ  ተልዕኮ ላይ ነን🔥🛐እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።” ማቴዎስ 28፥19-20 ዳግም የተወለዳችሁት ከዚህ አለም ሳይሆን ከላይ ነው። ለዚያ ነው መጽሐፍ ቅዱስ ዮሐንስ 1 (አዲሱ መ.ት) ላይ ¹²…»

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

25 Oct, 02:21

    🔥ታላቅ  ተልዕኮ ላይ ነን🔥

🛐እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።” ማቴዎስ 28፥19-20

ዳግም የተወለዳችሁት ከዚህ አለም ሳይሆን ከላይ ነው። ለዚያ ነው መጽሐፍ ቅዱስ ዮሐንስ 1 (አዲሱ መ.ት) ላይ ¹² ለተቀበሉትና በስሙ ላመኑት ሁሉ ግን የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን መብት ሰጣቸው።¹³ እነዚህም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ፣ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም" የሚለው።

🙏ከእግዚአብሔር መወለድ ከላይ መወለድ ነው፤ የተለየ ሕይወትና ተልዕኮ ይዘን ከላይ ተወልደናል። ታላቁ ተልዕኮ ከላይ የመጣ ተልዕኮ በመሆኑ በምድር ካለ ከየትኛውም ተልዕኮ የላቀ ትኩረትና ትጋት የሚጠይቅ ነው። እርሱ ተልዕኮውን ሰጥቶን ብቻችንን አልተወንም። እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ ብሏል።

ወንጌል ለመስበክ መፍራት የሌለብን በዚህ ምክንያት ነው።
የወንጌልን ተልዕኮ ለመፈጸም በምንሄድበት ሥፍራ ሁሉ እርሱ አብሮን አለ። የተልዕኮው ጌታ ሰዎችን በምናስተምረበትና በምንሰብክበት ሥፍራ ሁሉ አብሮን በመሆን ተአምራቱን ይገልጣል።

🙏ኢየሱስ ለሐዋሪያቱ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ ሲል ባዶ ተስፋ እየሰጣቸው አልነበረም። አብሮአቸው መሆኑን በድንቅና በተአምራት አሳይቷል። አንዳንዶች በወንጌል ስለሚያፍሩ ይህንን የተቀበሉትን አላማ ሕይወትና ተልዕኮ ለመፈጸም መነሳሳት ይጎድላቸዋል። ኢየሱስ የጠራን በወንጌል እንዳናፍርና በድፍረት እንድንሰብክ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ በዕብ12:2 ላይ ሲናገር “የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።” ይላል።

🛐ሁኔታውን ከተመለከትን እናፍራለን እንዲሁም እንፈራለን፤ኢየሱስን ከተመለከትን ግን ወንጌልን በመስበካችን ምክንያት የሚደርስብንን ነውር ንቀን እናልፋለን።
ኢየሱስ ኃጢአትን በመሸከም ነውርን ሁሉ ንቋል።ለኃጢአትኞች ለመሞት አላፈረም። የደረሰበትን ነውር ሳይሆን ከፊቱ ያለውን የክብርና ደስታ ተመለከተ። ያለ ሃፍረት የመስቀልን ሞት ታግሶ፤ ለአለም ሞተ።

በማቴ16:24 ላይ ሲናገር “በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።” አለ ይላል። የኢየሱስ ተከታይ መባልን ታፍራላችሁን? ከእርሱ ጋራ በእርሱ ስም መጠራትን ታፍራላችሁን? ወንጌልን ለመስበክ አትፈሩ። በክርስቶስ የተቀበላችሁትን ሕይወት ለመግለጥ አትፈሩ። ለኢየሱስ ለመቆም አትፈሩ። ኢየሱስን በግልጥ ስበኩ።

✝️መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሐዋሪያት ጉባኤ ሲናገር “ዕለት ዕለትም በመቅደስና በቤታቸው ስለ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ማስተማርንና መስበክን አይተዉም ነበር።” ይላል  —ሐዋርያት 5፥42።

👉ስለ ኢየሱስ እንዳታወሩ የሚያደርግ ሁኔታ ወይም ሕግ እንኳ ቢኖር ስለ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ መስበክ አትተው። ሰለ ኢየሱስ የሚሰብኩት ዕለት ዕለት እንጂ የሆነ የወንጌል ስርጭት ቀን ሲባል አልነበረም። ወንጌል መስበክና ስለ ኢየሱስ ማውራት የዕለት ተዕለት ሥራቸው ነው። ስለ ኢየሱስ ለማውራት ጊዜና ቦታ መምረጥ የለባችሁም፤ ሐዋሪያት  ቦታ ሳይመርጡ በቤትም በመቅደስም ስለ ኢየሱስ ይሰብኩ ስለ ነበረ እናንተም ቦታ ሳትመርጡ በቤትም፣ በሰፈርም ሁሉ ስለ ኢየሱስ መስበካችሁን አታቋርጡ።

🙏የዚህንም ውጤት መጽሐፍ ሲናገር “ ጌታም የሚድኑትን ዕለት ዕለት በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር።” ይላል(ሐዋርያት 2፥47)። ወንጌልን መናገር ካላቋረጣችሁ፤ የሚድኑ ዕለት ዕለት ይጨምራሉ። ሃሌሉያ!

🔥🔥🔥ጸሎት🔥🔥🔥
ውድ አባት ሆይ ስለ ቃልህ አመሰግንሃለሁ። አንተን ብቻ እያየሁኝ ያለ ሃፍረትና ፍርሃት ወንጌል እንድሰብክ እርዳኝ።በየዕለቱ በየትኛውም ሥፍራ ወንጌልን ለመስበክ ወስኜያለሁ።ለሰው ልጅ ያለህን ፍቅር በአገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ አውራለሁ።በኢየሱስ ስም ሜን
 
GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

25 Oct, 02:21

Shalom Shalom

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

24 Oct, 07:35

https://t.me/bookstore2014

More than 50.000 Books 📚
Invites you relatives family …. Soon. You are blessed

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

24 Oct, 00:30

Shalom Shalom

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

24 Oct, 00:27

        🔥አገልግሎታችሁን ፈጽሙ🔥

🔥“፥ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አድርግ፥ አገልግሎትህን ፈጽም።” 2ኛ ጢሞቴዎስ 4፥5
 
የጌታ ዳግም መምጣት ከየትኛውም ጊዜ ይልቅ እንደቀረበ ታውቃላችሁን?፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ሊወስደን በቅርቡ ዳግም ይመለሳል። ከእኛ የሚጠበቀው ደግሞ የተሰጠንን አገልግሎት መፈጸም ነው። ያም አገልግሎት ላልዳኑ ሰዎች ወንጌልን መመስከርና ወደ ክርስቶስ ማምጣት ነው።

✍️ላልዳኑ በትምህርት ቤት፥ሰፈርና የሥራ ቦታ ለምታገኟቸው ጓደኞቻችሁ፣ የሥራ ባልደረቦቻችሁ እና ቤተሰባችሁ ወንጌልን መስበክ አለባችሁ።ይህ ዋነኛ ሥራችሁ ሲሆን በምድር ያላችሁት ይህንን አገልግሎት ለመፈጸም ነው።
ተማሪ እያላችሁ መምህራኖቻችሁ የቤት ሥራ ሲሰጡአችሁ የቤት ሰራችሁን እንደምትሰሩ፤ የቤት ሥራውን የሰራ ተማሪ ካልሰራው ይልቅ ሽልማት እንደሚቀበል እንዲሁ እግዚአብሔር ሰርተን  በፊቱ እንድንቀርብ የሰጠን የመንግስቱ ሥራ አለ።ይኼንንም ሥራችሁን ስትፈጽሙ፤ ሽልማት ትቀበላላችሁ።ተማሪዎች የቤት ሥራ ሲሰጣቸው፤ አንዳንዱ የቤት ሥራ እንደተሰጠውም የማያስታውስ አለ ሌላው ደግሞ የቤት ሥራ እንደተሰጠው ቢያስታውስም ለመሥራት መነሳሳት የለውም።

✍️ሌላኛው ተማሪ ደግሞ ገና ቤት ገብቶ ከየትኛውም ሥራ በፊት የቤት ሥራውን አስቀድሞ የሚሰራ ንቁና ትጉ ተማሪ አለ።የሚጫወተውና ሚዲያ የሚከታተለው፥የቤት ሥራውን ሰርቶ ከጨረሰ በኋላ ነው።

✝️እንዲሁም ከምንም አስቀድማችሁ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ሥራ ልትሰሩ ይገባል። እርሱም ወንጌልን መስበክ ነው። ይኼ በዚህ ምድር ላይ ሳላችሁ ጌታ የሰጣችሁ "የቤት ሥራ" ነው። ይኼ በዚህ ምድር ላይ የምትሰሩት የመንግስቱ ሥራ ነው። ሰማይ ስትሄዱ የምትሰሩት ሥራ አይደለም። በዚህ ምድር ላይ እግዚአብሔር ያስቀመጣችሁ፥ ከመብላት፣ ከመጠጣት፥ ከመተኛትና ከመነሳት ባለፈ የወንጌልን ሥራ እንድትሰሩ ነው።

መጽሐፍ ሲናገር “እምነታችሁም በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ እንዳይሆን፥ ቃሌም ስብከቴም መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ ነበረ እንጂ፥ በሚያባብል በጥበብ ቃል አልነበረም።”  ይላል— 1ኛ ቆሮንቶስ 2፥4።

👉ወንጌል የሚያምኑትን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ኃይል ነው።የሚያድን መንፈስና ኃይል የሚገለጠው አንድ ሰው በወንጌል ሲያምን ነው። መንፈስና ኃይል የሚገለጠው ክርስቶስ ሲሰበክ ነው። ቃላችሁም ስብከታችሁም ክርስቶስ ሊሆን ይገባል። ሰዋዊ የጥበብ ቃል ሰዎችን ሊያድን አይችልም። ሰዎች የሚድኑት በማባበል ሳይሆን እውነተኛውን ወንጌል ሲሰሙ ነው።

👉ትልቁ ተአምራት ሰዎች ወንጌልን ሰምተው ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሞት ወደ ሕይወት ሲመጡ ነው። ክርስቶስ ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የተገለጠ የእግዚአብሔር ኃይል ነው። ክርስቶስን ብቻ ስትሰብኩ፤የሚያድነውን የእግዚአብሔርን ጥበብና ኃይል እየሰበካችሁ ነው።

🙇እግዚአብሔር የሰጣችሁን የወንጌል ሥራ መስራት አትዘንጉ።ከምንም በላይ የእግዚአብሔር መሻት የመንግስቱ መስፋፋት ነው። የእግዚአብሔር መንግስት በእያንዳንዱ ልብ ውስጥ እንዲሰርጽ ማድረግ አለባችሁ። ይኼንንም የምታደርጉት ለጓደኞቻችሁና ለምታገኟቸው ሰዎች ሁሉ የክርስቶስን ፍቅር በመስበክ ነው።ጌታንም እንደምትወዱት የምታሳዩት ስለ እርሱ ለሰዎች በመናገር ነው።ሃሌሉያ!!

🔥🔥🔥ጸሎት🔥🔥🔥
ውድ አባት ሆይ የአንተን መመለስ ስጠባበቅ፥ላልዳኑ ወንጌል በመስበክና ንቁ በመሆን እንድዘጋጅ እርዳኝ።በእኔ ምክንየት ሰዎች ከጨለማ ወደ ብርሃን፥ከሰይጣን መንግስት ወደ አንተ መንግሰት  ይመለሱ።

🙏በኢየሱስ ስም አሜን🙏

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

23 Oct, 16:32

Hug the Children (HTC)

Hug the Children is an indigenous Christian charity founded with the intention of increasing the participation of the Church in the community by mainly :-
# Addressing the problems of children and youth by enabling them to live for the purpose for which they were created,

# Empowerment in various directions by increasing the participation of women,

# Helping parents to have a job, run their own business and manage their homes well by providing trainings. 

“Let your light so shine before men, that they may see your good works, and glorify your Father which is in heaven." Matthew 5:16

Dr. Gelila Zegeye
📞0947391949/0977497443

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

23 Oct, 02:14

1ጢሞ 1:5 የትእዛዝ ፍጻሜ ግን ከንጹሕ ልብና ከበጎ ሕሊና ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚወጣ ፍቅር ነው፤

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

23 Oct, 01:52

Shalom Shalom

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

23 Oct, 01:28

🔥🔥🔥በፍቅር የሚሰራ እምነት🔥🔥

በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ፥ በፍቅር የሚሠራ እምነት እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና።” ገላትያ 5፥6

እምነታችሁን እንዲሰራ የሚያደርገው ዋነኛው ነገር ፍቅር ነው። ፍቅር የእግዚአብሔር ተፈጥሮና ባሕሪይ ነው። ዳግም ስትወለዱ፤ ፍቅር የእናንተ ባሕሪና ተፈጥሮ ሆኗል። ይህም ማለት ለመውደድና ፍቅርን ለመግለጥ አትታገሉም።

👉እግዚአብሔርም ተጨማሪ ፍቅር እንዲሰጣችሁ መጠየቅ አያስፈልጋችሁም። ተጨማሪ እምነት እንደማያስፈልጋችሁ እንዲሁ፤ ተጨማሪ ፍቅር አያስፈልጋችሁም፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ፍቅር በመንፈሳችሁ በመፍሰሱ፤ የጎደለ ፍቅር የላችሁም።

🛐በሮሜ 5:5 ላይ ሲናገር “በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም።” ይላል።የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችሁ ፈሷል። ዳግም የተወለዳችሁ ከሆነ የእግዚአብሔር ፍቅር አላችሁ።

✍️አንዳንዴ ቅዱሳን" እኔ ይቅር ልል አልችልም ሲሉ "ያስገርማል" እኔ ኢየሱስ አይደለሁም ይህንን ሁሉ ይቅር ማለት አልችልም"ይላሉ።

🙇ቃሉ ግን “፤ እርሱ እንዳለ እኛ ደግሞ እንዲሁ በዚህ ዓለም ነንና። ”ይላል 1ኛ ዮሐንስ 4፥17። እርሱ እንዳለ እንዲሁ እንሆናለን ሳይሆን የሚለው፤ እርሱ እንዳለ እንዲሁ ነን ነው የሚለው። እርሱ ይቅር እንዳላችሁ እንዲሁ እናንተ ይቅር ማለት ትችላላችሁ።

🛐ኢየሱስ በዮሐ 13:34 ላይ “እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ፥ እንደ ወደድኋችሁ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ።”ያለው በከንቱ አይደለም።ሌሎችንም መውደድ የምትችሉበትን አቅም ባይሰጣችሁ፤ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ ባላለ ነበር።

🙏ጠላቶቻችሁንም ውደዱ ሲል፤ የሚጠላችሁንና ብዙ የጎዳችሁን ሰው ይቅር ማለት የምትችሉበትን አቅም ስለሰጣችሁ ነው። ዳግም ስትወለዱ ከፍቅር ተወልዳችኋል። እናንተ የፍቅር ልጆች ናችሁ። ፍቅርን የተሞላችሁ ናችሁ። ፃድቅ እንደመሆናችሁ፤ የተባረካችሁ፣የበለጸጋችሁ፣ መለኮታዊ ጤንነት ያላችሁና በፍቅር  የተወለዳችሁ ናችሁ። የእግዚአብሔር ፍቅር በእናንተ ውስጥ አለ።
✝️ፍቅር ዳግም የተወለደው መንፈሳችሁ ፍሬ ነው። በገላ 5:22 ላይ “የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥... ነው።” ይላል።

👏ፍቅር ከስሜት ያለፈ ነው። ፍቅር እንዳላችሁ ላይሰማችሁ ይችላል፤ ምክንያቱም የሚገኘው በስሜታችሁ ውስጥ ሳይሆን መንፈሳችሁ ውሰጥ ነው። ማንንም መውደድ እንደምትችሉ ለራሳችሁ ንገሩ፤ ምክንያቱም እናንተ የእግዚአብሔር ፍቅር አላችሁ። ለመውደድ የሚያስቸግራችሁ ማንም እንደሌለ እርግጠኛ ሁኑ።

👉ኢየሱስ እናንተን ለመውደድና ነፍሱን ለመስጠት ካልከበደው፤ እናንተም በዚያው ፍቅር መውደድ ትችላላችሁ። አሁን የእርሱን ፍቅር ተቀብላችኋል፤ ያለ ገደብ ሰዎችን መውደድ ትችላላችሁ። እርሱ እንደወደደን፤ እርስ በርሳችን እንድንዋደድ ነግሮናል፤ ይህም ማለት እርሱ እኛን በወደደበት ፍቅር መዋደድ እንችላለን ማለት ነው።""..

🙏እንደወደድኋችሁ.."የሚለው ሃሳብ ወሳኝ ነው። ሌሎችን እንድትወዱ አንዱ የሚያነሳሳችሁ ቃል፤ እርሱ ወዶኛል የሚለው ነው። እርሱ እንዴት ወደደን?፤ ገና ሙታን ሳለን፣ ገና ደካሞች ሳለን ነው የወደደን። ስለዚህ ሰዎችን ለመውደድ፣ ብርቱ፣ ስህተት አልባ እስኪሆኑ አትጠብቁ። ከነስህተታቸው፣ ከነድካማቸው ውደዱአቸው።
በእግዚአብሔር እንደተወደዱ የሚያውቁ ሰዎች ሌሎችን ለመውደድ አይታገሉም።

✍️ከላይ በመግቢያ ላይም እምነት አቅም የሚያገኘው፣ የሚበረታውና ጠንካራ የሚሆነውው በፍቅር እንደሆነ ይናገራል። ፍቅር የእግዚአብሔር ኃይል የሚፈስበት ወንዝ  ነው። ወንዙ መፍሰስ ከቆመ፤ የእግዚአብሔር ኃይል መፍሰስ ይቆማል። ለዚያ ነው በጥላቻ፣ በምቀኝነት፣ ይቅር ባለማለት የተሞሉ ሰዎች፤ የሚፈልጉትን ፈውስና ተአምራት መቀበል የሚያቅታቸው። ያልተፈወሱት እግዚአብሐሔር እየቀጣቸው ስለሆነ አይደለም፤ በጥላቻ ምክንያት የእግዚአብሔር የፈውስ ኃይል እንዳይሰራ ስለሚያደርጉ ነው።

✍️እምነታችሁ እንዲሰራ፤ ያለምክንያት እንደተወደዳችሁና፤ ይህንንም ፍቅር ያለምክንያትም የምትገልጡ መሆን አለባችሁ።ጥላቻ፣ ምሬት፣ ይቅር አለማለት ከእናንተ ይወገድ:: ጥላቻ የምትጠሉትን ሰው ሳይሆን ራሳችሁን ነው የሚጎዳችሁ። የእግዚአብሔር ፍቅር በእናንተ አልፎ እንዲፈወስ ፍቀዱ።

🙏🙏🙏ዛሬ የወሰነ አንድ ሰው ካለ የተቀየመውን ይቅር በማለት ምህረትን ይቀበል በኢየሱስ ስም አሜን
 
🔥ጸሎት🔥
ጌታ ሆይ ሁሉንም ነገር ስለሰጠኸኝ አመሰግንሃለሁ። ሌሎችን ለመውደድ የሚያስችል ፍቅር ሰጥተኸኛል። በፍቅር በተመላለስኩ ቁጥር እምነቴ በኃይል መስራት ይችላል። ጥላቻና ይቅር አለማለትን ከእኔ ሕይወት አስወግዳለሁ። በእኔ የአንተ የፍቅር ወንዝ ይፍሰስ።

🙏በኢየሱስ ስም አሜን🙏

ተከናወኑ ቀናችሁ በደስታ ይሞላ
አገልጋይ ዶ/ር ገሊላ
 https://t.me/GRACE_TRUTH

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

22 Oct, 01:54

Shalom Shalom

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

22 Oct, 01:44

🔥በወንጌል ውስጥ የተገለጠ ጽድቅ🔥

"በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና። ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና። (ወደ ሮሜ ሰዎች 1 ፥16-17)

🙏ሰው በመልካም ስነምግባር መዳን ቢችል ኖሮ ፤እግዚአብሔር ኢየሱስን መላክ ባላስፈለገው ነበር። ጨዋ መሆን ጥሩ ቢሆንም የመዳን ዋስትናን ሊሰጥ አይችልም። የመዳን ዋስትና ኢየሱስ ክርስቶስ የሰራው ሥራ ነው።

👏እግዚአብሔር ማንንም የሚቀበለውና የሚያየው ኢየሱስ ክርስቶስ በሰራው ሥራ በኩል ነው። እግዚአብሔር ከሰው ልጆች ጋር ሕብረት ማድረግ የሚፈልገው፤ ክርስቶስ በሰራው የቤዛነት ሥራ በኩል ነው።ማንም ሰው ቢሆን ጽድቅን፣ ቅድስናን፣ የኃጢአትን ይቅርታ በራሱ መንገድ ሊያገኝ አይችልም።

እግዚአብሔር ከሰዎች ጋር መግባባት የሚችልበት ቋንቋ የመስቀሉ ሥራ ነው። ብዙ  ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት በመልካም ሥራቸው ለመፅደቅና በእርሱ ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት ብዙ ነገር ያደርጋሉ፡፡የተለያዩ ፀሎቶችን ይፀልያሉ ለብዙ ቀናት ይጾማሉ ድሆችንም በመመገብ የእግዚአብሔርን ትኩረት ለመሳብና በዚህም እርሱ ቸርነትና ምህረት ያደርግላቸው ዘንድ ይለምናሉ ከዚያም የዘላለምንም ሕይወት ያወርሳቸው ዘንድ ተስፋ ያደርጋሉ፡፡

👉ነገር ግን  ያላወቁት ነገር ቢኖር ለማዳን የሆነ የእግዚአብሔር ፅድቅ ያለው በወንጌል ውስጥ ብቻ መሆኑን ነው፡፡ ከላይ ባለው ክፍል ጳውሎስ በወንጌል የማያፍርበትን ምክንያት ሲናገር ለማዳን የሚሆን የእግዚአብሔር ሃይል ነውና ይላል፡፡

🔥የክርስቶስ ወንጌል የሚያምኑትን ሁሉ የሚያድን እንጂ የሚያጠፋ አይደለም ፡፡
ክርስቶስ ከሰራው ውጪ ጽድቅ የለም። መዳንን የገለጠው የመስቀሉ ሥራ ነው። ሰው የሚጸድቀው የእምነትን ቃል ሰምቶ ሲያምን ብቻ ነው። የእምነት ቃል ማለት ኢየሱስ ከሞት እንደተነሳ በልብ ማመን ፤ጌታ እንደሆነ በአፍ መመስከር ነው።

ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ሃይል ያለው በወንጌሉ ውስጥ ነው፡፡የሚያድን ፅድቅ ማግኘት የሚቻለው የክርስቶስ ኢየሱስን ወንጌል በማመን ብቻ  ነው፡፡

መጽሐፉ ለሚያምን እንጂ ለሚሰራ አይልም፡፡ ሰው የሚያምነው ደግሞ የመስቀሉን ሥራ ነው። የእግዚአብሔር ሃይል የሚሰራው በራሱ ፅድቅ ተማምኖ ወደ እግዚአብሔር ለሚቀርብ ሰው አይደለም፡፡እንዲህ አይነት ሰው ራስ ወደ ሆነው ወደ ክርስቶስ ጽድቅ መቅረብ አይችልም። ማንም ቢሆን ፅድቅን የሚፈልግ ከሆነ ማድረግ ያለበት የማያሳፍረውን ወንጌል መቀበል ነው፡፡

🙇የራስን መልካም ሥራና ጥረት ተማምኖ ለመፅደቅ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ አሳፋሪ ነው፡፡ የሰው ጥረትና ጸድቅ በእግዚአብሔር ዘንድ አጸያፊ ነው።

✍️እርሱ በወንጌል ውስጥ ካስቀመጠው የመዳን መንገድ ውጪ ሌላኛውን የእኛን መንገድ አይቀበልም፡፡ ብዙ መንገድ ሳይሆን አንድ መንገድ ነው ያለው።የእግዚአብሔር ፅድቅ ያለው በወንጌል ውስጥ ሲሆን የሚገለጠው ደግሞ በእምነት ነው፡፡ ይህም እምነት በኢየሱስ የመስቀል ሥራ ላይ ያለን እምነት ነው።

👇ክርስቶስ እንደተሰቀለ ሆኖ ሰዎች ሁሉ ውስጥ እንዲሳል ንጹህ የሆነውን ወንጌል በመስበክ ልንተጋ ይገባል።

🙇ኃይማኖት በሰዎች ልብ ውስጥ የሳለው የክርስቶስን ሥራ የሚሸፍነውን ትምህርትና ሰዋዊ ጥበብነው። የራሳችሁ መልካም ሥራ በፊቱ ያለ ፍርሃት የመቆምን ድፍረት አይሰጣችሁም ነገር ግን በወንጌሉ ውስጥ  ያለው በክርስቶስ የተገለጠው ፅድቅ ይህን ማድረግ ይችላል፡፡ በፊቱ ተቀባይነት በማግኘት እና ከእርሱ ጋር ቀጥተኛ ህብረት በመፍጠር እንደ  አባትና ልጅ የሚያደርገን ይህ እግዚአብሔር ያለ ሕግ ሥራ ለሚያምኑ ሁሉ የገለጠው የእግዚአብሔር ፅድቅ ነው፡፡

👉ሰዎችን  ካሉበት እስራት የሚፈታ ብቸኛው እግዚአብሔር ያዘጋጀው መድሀኒት ወንጌል በመሆኑ በፍጹም ማፈር የለባችሁም፡፡

በዮሐ 14፥16 ላይ  " ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።" ጌታ ከእርሱ ውጪ ሌላ መዳኛ መንገድ እንደሌለ ነግሮናል፡፡ ስለዚህ እናንተም ይህንን በመረዳት ሰዎችን  ወደ እውነትና  ሕይወት መንገድ ልትመሩ ይገባል፡፡ዓለም እግዚአብሔር ያስቀመጠውን መንገድ ትቶ ሌላ መንገድ እየቀየሰ እንዳይባዝን ፤የክርስቶስን ብርሃን በማብራት የሞቱትን አስነሱ የተኙትን አንቁ።

🙏አዋጅ🙏
ኢየሱስ ለሁሉ መድሃኒት ነው። ይህንን መድሃኒት ለሰዎች ሁሉ አስተዋውቃለሁ። የወንጌል ባላደራ ነኝ ለተጨነቁ ሰዎች መፍትሄ የሆነውን ወንጌል እያወጅኩ እቀጥላለሁ፡፡ በወንጌል አላፍርም ምክንያቱም ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ሃይል ነውና፡፡
🔥በኢየሱስ ስም አሜን🔥
 
GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

21 Oct, 02:37

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH pinned «🔥🔥🔥በሚታየው አትናወጡ🔥🔥 “የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው።”  — 2ኛ ቆሮ 4፥17-18 ✍️መንፈሳዊ ዓለም ለሚታየው ነገር ሁሉ መሠረት ነው። በሚታየው ዓለም ለውጥን ማምጣት ከፈለጋችሁ፤ አስቀድማችሁ በመንፈስ ዓለም ነው ለውጥን ማምጣት ያለባችሁ፤…»

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

21 Oct, 02:29

🔥🔥🔥በሚታየው አትናወጡ🔥🔥

“የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው።”  — 2ኛ ቆሮ 4፥17-18

✍️መንፈሳዊ ዓለም ለሚታየው ነገር ሁሉ መሠረት ነው። በሚታየው ዓለም ለውጥን ማምጣት ከፈለጋችሁ፤ አስቀድማችሁ በመንፈስ ዓለም ነው ለውጥን ማምጣት ያለባችሁ፤

የሚታየውን ዓለም የሚቆጣጠረው የማይታየው ዓለም ነው። መጽሐፍ በዕብ11:3 ላይ ሲናገር “ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን።”ይላል።

👉የሚታዩ ነገሮች የተገኙት ከማይታዩ ነገሮች ነው።የሚታዩ ሁኔታዎችና ክስተቶች የመንፈሳዊው አለም ነጸብራቅ ናቸው። ዋናው የሚታየው ሳይሆን የማይታየው ነው።

✍️የሚታየው የጊዜው ወይም ጊዜያዊ ነው ያለው በዚህ ምክንያት ነው። የማይታየው ሲቀየር፤ የሚታየውም ይቀየራል። የሚታየው በራሱ ችሎ አይቆምም። በማይታየው ላይ የተንጠለጠለ ነው።

አንዳንዴ በመኪና እየሄዳችሁ በአስፓልት ላይ በርቀት ስታዩ፤የጸሐይ ነጸብራቅ በአስፓልቱ ላይ ውሃ የተኛ ያስመስላል፤ ጠጋ ስትሉ ግን ውሃ ሳይሆን ነጸብራቅ መሆኑን ትመለከታላችሁ።

👉የሰይጣንን ውሸት ስትቃወሙ፤ ይህም ሕይወታችንን የምንመራውና የምንኖረው  በአምስቱ የስሜት ህዋሳችን አይደለም ማለት ነው። ምክንያቱም የሚታየው ጊዜያዊ ነው። የሚታዩ ቢሆኑም እውነት አይደሉም። ኃላፊና ጠፊ ናቸው።

👉ሕይወታችንን የምንመራው፤ በማይታየው በቃሉ እውነት ነው። የማይቻለውን የማድረግ ምስጢሩ ያለው፤ በማይታየው ዓለም ውስጥ በምናመጣው ተጽዕኖ ውስጥ ነው።

🙏አዋጅ🙏
የሚታየውን ሳይሆን የማይታየውን እመለከታለሁ። ትኩረት የማደርገው በሁኔታ ላይ ሳይሆን በቃሉ ላይ ነው። በሚታየው ነገር መደንገጥና መፍራትን እምቢ እላለሁ። በኢየሱስ ስም አሜን

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

20 Oct, 04:09

ድል በመንሳት ተመላለሱ✝️

"ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን"    2 ቆሮንቶስ 2፥14
      እንደ ክርስቲያን ሁላችንም ሊኖረን የሚገባ የአዕምሮ ቅኝት አለ። በየዕለቱ ለሚያጋጥማችሁ ተግዳሮት የሚኖራችሁ እይታ በሕይወት የሚኖራችሁን ከፍታና ድል ይወስናል። አስተሳሰባችሁ መቃኘት ያለበት በቃሉና እንደ ቃሉ ነው። ቃሉ የድላችሁና የሞገሳችሁ መገኛ ምንጭ ነው።

🛐የአዲሱ ፍጥረት ሕይወት ወደ ፊትና ወደ ላይ ብቻ ነው ። ያለማቋረጥ ብርሃኑ እየጨመረ የሚሄድ፣ የድል፣ የበረከት ሕይወት ነው። ታድያ እውነቱ ይህ ሆኖ እያለ ሕይወታቸው ከላይ ከጠቀስከው በተለየ መልኩ የሽንፈት፣ ያለመከናወን ሕይወት የሚኖሩ ብዙ አማኞችን በዙሪያዬ አውቃለሁኝ ትሉ ይሆናል። ክርስቲያን ሊወድቅና ሊሸነፍ የሚችለው በራሱ ምርጫ፣ ፈቃድ ወይም የተሰጠውን ነገር ባለማወቁ ብቻ ነው።

👉ቤንዚል በሚጠቀም መኪና ውስጥ ሌላ ፈሳሽ ነገር ብትጨምሩ የመኪናው ሞተር አይሰራላችሁም። ሞተሩ ያልሰራው ተበላሽቶ ሳይሆን በቤንዚል ፈንታ ትክክለኛ ያልሆነ ፈሳሽ በመጨመራችሁ ነው። በተመሳሳይ መንገድ የተሳሳቱ እውቀቶች ወይም መረጃዎች ወደ ውስጣችሁ ሲገቡ መንፈሳችሁ ውስጥ ያለው ሕይወትና ኃይል  እንዳይገለጥና እንዳይሰራ ያደርጋል።

   👏ወደ ሥራም፣ ወደ ትዳር ወይም ወደ የትኛውም ሙያ ስትሰማሩ እንደሚሰራላችሁና እንደሚሳካላችሁ አውቃችሁ መግባት አለባችሁ። ከመስራትና ከመሳካት ውጪ ሌላ አማራጭ አይኑራችሁ። እናንተ ከቃሉ በመወለዳችሁ ቃሉ በእናንተ ሕይወት ይሰራል።

✍️በመዝሙረ ዳዊት 1፥3-4 ላይ ስለምስጉን ወይም ስለተባረከ ሰው መዝሙረኛው ሲናገር እንዲህ ይላል" ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል። እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል" ይላል። የእናንተ እድል ፋንታም ይሄ ነው፡፡
     🙏እናንተ በቃሉ የተወለዳችሁ አዲስ ፍጥረት በመሆናችሁ በቃሉ ያለውን አዲሱን ማንነታችሁን በቀንና በማታ ባሰላሰላችሁ ቁጥር የእናንተ ሕይወት የሚሆነው ከላይ እንደተገለጸው ነው። በቃሉ በመወለዳችሁና በእርሱ ውስጥ በመተከላችሁ በዚህ ብዙዎች ፍሬን መስጠት ባቆሙበት፣የብዙዎች ጤንነትና ኢኮኖሚ በወደቀበት ፣ ብዙዎች በኪሣራ ምክንያት ንግዳቸውን በሚዘጉበት ወቅት እናንተ ግን የምትሰሩት ሥራ ሁሉ ይከናወንላችኋል። በሌሎች ላይ የሚሆን ሁሉ በእኔ ላይ መሆኑ አይቀርም አትበሉ! እናንተ በልዩነት መኖር ትችላችሁ።

👉እናንተ ፍሬ የማትሰጡበት ቅጠላችሁ የሚረግፍበት ጊዜ አይኖርም። ሁልጊዜ በቀን 24 ሰዓት በሣምንት ሰባቱንም ቀን ታፈራላችሁ ትለመልማላችሁ!
        በመግቢያችን ላይ ያለው ጥቅስ " ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን"

🙇በ2 ቆሮ 2፥14 እንደሚል ሁልጊዜ በሁሉም ሁኔታ የድል ነሺነትን አስተሳሰብ ያዙ። ችግሮችና ፈተናዎች ቢመጡም የተሸናፊነት ሳይሆን የአሸናፊነት አመለካከት እስካላችሁ ድረስ ሁሉንም ጥሳችሁ ታልፋላችሁ። የእግዚአብሔር ቃል አስተሳሰባችሁንና የአዕምሮ ቅኝታችሁን እንዲቀርፅ መፍቀድ ያለባችሁ በዚህ ምክንያት ነው።
✍️አስተሳሰባችሁ እስከተለወጠ ድረስ ተግዳሮት እያለ እናንተ ከሁኔታው በላይ ሆናችሁ መኖር ትችላላችሁ። በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል የምትነሱበትን የአሸናፊነት ዕውቀትና አስተሳሰብ ያዙ።የቃሉ ዕውቀት ሽታ በእናንተ ሲገለጥ፣ ያን ጊዜ አብሮ ድል ከእናንተ ጋር ይሆናል

🔥አዋጅ🔥
ድል ነሺና አሸናፊ የሚያደርገኝ ዕውቀት ሁልጊዜ በእኔ ይገለጣል። በክርስቶስ ኢየሱስ ድል በመንሳት እመላለሳለሁ። በክብር፣ በጽድቅ፣ በጤንነት እየተገለጥኩኝ እሄዳለሁኝ። በኢየሱስ ስም አሜን!

https://t.me/GRACE_TRUTH

GRACE & TRUTH Bible Study and Prayer Ministry. @ GRACE_TRUTH

19 Oct, 01:34

በሁሉ የመጨመር ህይወት ተቀብለናል፡፡

ኤፌሶን 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴-¹⁵ እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ፥ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፥ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ፤
¹⁶ በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤
¹⁷ የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።
¹⁸ በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፤