ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ @prof_biranu_nega_supports Channel on Telegram

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

@prof_biranu_nega_supports


“በፍትሕና በምህረት አውድ ውለን ልናድር ካልሆነ በቀር በኃይልና
በጉልበት በአመፅና በሁከት ሰላምን ብንፈልገውም አናገኘውም”

📝እውነታውን እንዘግባለን፣ Fake news እናወግዛለን

ሰላም ለሀገራችን
ኢትዮጲያ ለዘለአለም ታፍራና ተከብራ ትኑር!

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ (Amharic)

ይህ ብርሃኑ መሣሪያን ጥያቄዎችን ለማግኘት እና እንተባበይባችሁ የምትፈልጉትን የቴሌግራም የቻናላችሁ ቦታ ነው። እንግዲህ ይህ መረጃ ይህ ብርሃኑ መሣሪያን የሚገኙትን ሴራል ዜናዎችን ለመሙላት የሚረዳን መገለጫ ነው። በዚህ መጽሀፍ የሰላም እና እንቅስቃሴ በሚሆንብየተያዘ አልተባርኩም ፅሁፎችን በመሰላበት እና ለሀገርም ሥሩት ለሚለው ይህን መጽሀፍ እና ልማድ ለማድረግ Telegram ላይ ይጫኑና በኤርትራ የአለም ወንድምና የሴቶች በኤርትራያችን ታፍሰሱ።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

02 Nov, 00:47


ሰበር የድል ዜና
---
ጀግናዉ የትግራይ ሰራዊት የትግራይ ህዝብ ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ዋስትና እስኪያገኝ ድረስ በፍሽስት አብይ አሕመድ ሰራዊትና በተሰፋፊዉ የአማራ ትምክሕተኛ ሰራዊት ላይ የጀመረዉ የፀረ-ማጥቃት እርምጃ አጠናክሮ በማሰቀጠል ዛሬ ጥቅምት 22/2014 ዓ.ም በኮምቦልቻ በስተምስራቅ የሚገኙ ገርባ፣ ባቲ ከተማና ቡርቃ በመቆጣጠር ወደ ሚለ አቅጣጫ እየገሰገሰ ይገኛል።

ከኮምቦልቻ በሰተደቡብ የተሰማራዉ ጀግና ሰራዊታችንም ሃብሩን በመቆጣጠር የጠላት ሃይል እያሽመደመደ በከፍተኛ ሞራል ጉዛዉ ወደ ከሚሴ አቅጣጫ በመቀጠል ላይ ይገኛል።

ጀግናዉ የትግራይ ሰራዊት ከተሞቹን ሲቆጣጠር የእነዚህ ከተሞች ኗር ህዝብ ከፍተኛ ህዝባዊነት ለተለበሰዉ ሰራዊታችን እህልና ዉሃ በማቅረብና በዕልልታና በደስታ የተቀበለዉ ሲሆን የደሴና የኮምቦልቻ ከተሞች ህዝብም በተረጋጋ ሁኔታ የዕለተ ተዕለት ኑሮዉን ማካሄድ ጀምራል።

ህልዉናችንና ድህንነታችን በፈርጣማዉ ክንዳችን!!
ትግራይ ታሸንፋለች!!
የትግራይ ሰራዊት ወታደራዊ ኮማንድ
ጥቅምት 22/2014 ዓ.ም

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

29 Jun, 14:37


ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3693 የላብራቶሪ ምርመራ 157 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5846 ደርሷል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

03 May, 10:11


የሚሞቱ ህሙማንን የመጨረሻ ኑዛዜ የምትቀበለው ነርስ‼️

በኮቪድ-19 በጠና ለታመሙ ህሙማን የኦክስጅን መተንፈሻ ማሽን (ቬንትሌተር) ድጋፍ በህይወት እንዲቆዩ ለማድረግ ይረዳል። ምንም እንኳን ቬንትሌተር በህይወት እንዲቆዩ ቢያግዝም፣ በጠና በታመሙት ዘንድ የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት ቢያመጣም ህይወትን መቀጠል አያስችለውም። እናም የመጨረሻዋ ደቂቃ ስትቃረብ፣ በማሽንም መተንፈስ ሲያዳግት፣ ማሽኑ ሊነቀል ግድ ይላል። ወደ ሞት እየሄዱ ላሉ ህሙማን ምን አይነት ስሜት ይኖረው ይሆን? ማሽኑን ለሚነቅሉት የጤና ባለሙያዎችስ?
በለንደን ሮያል ፍሪ ሆስፒታል በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ለምትሰራው ዋና ነርስ ጁዋኒታ ኒትላ በአብዛኛው መተንፈሻ ማሽኖችን መንቀል የሥራዋ አንድ አካል ነው። በብሔራዊ የጤና አገልግሎት በፅኑ ህሙማን ልዩ ነርስ በመሆንም ለአስራ ስድስት ዓመታት ያህል አገልግላለች።






https://telegram.me/prof_biranu_nega_supports

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

03 May, 01:35


#መልካም_ዜና‼️

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 2,016 የላቦራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች አለመኖራቸው ተረጋግጧል

በተጨማሪ ⬇️

በሀገራችን ተጨማሪ 3 ሰው ከኮሮና አገግሟል

በሀገራችን #በአጠቃላይ ያገገሙትን ቁጥር 69 አድርሶታል ።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

03 May, 01:35


#የኢቦላ መድኃኒት ኮሮናቫይረስን ለማከም እንዲውል ተፈቀደ!!

የአሜሪካ ምግብና መድኃኒት አስተዳደር ተቋም የኢቦላ በሽታን ለማከም የሚውለውን ሬምዴሲቪር የተባለውን መድኃኒት ለአስቸኳይ ጊዜ የኮሮናቫይረስ ህክምና እንዲውል ፈቀደ።

በዚህም መሰረት ይህ ጸረ ቫይረስ የሆነው ይህ መድኃኒት በኮሮናቫይረስ በጽኑ ታመው ሆስፒታል የሚገኙ ሰዎችን ለማከም ይውላል።

የአሜሪካ ምግብና መድኃኒት አስተዳደር ኮሚሽነር የሆኑት ስቴፈን ሃን እንዳሉት “ይህ የኮሮናቫይረስን ለማከም ዕውቅና የተሰጠው የመጀመሪያው መድኃኒት ነው” ብለዋል።

በቅርቡ ሬምዴሲቪርን በመጠቀም በተደረገ ሙከራ በኮሮናቫይረስ ክፉኛ ታመው ሆስፒታል የገቡ ሰዎች የሚያገግሙበትን ጊዜ ለማፋጠን እንዳስቻለ ተረጋግጧል።

ነገር ግን ይህ በተቋሙ መድኃኒቱን ለመጠቀም የተሰጠው የአስቸኳይ ጊዜ ፈቃድ ሙሉ ፈቃድ አለመሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ መደበኛ ዕውቅና ለማግኘት ከፍ ያለ ምዘናን ይጠይቃል።

ባለሙያዎች እንደሚሉት ይህ ኢቦላን ለማከም የተሰራው መድኃኒት ኮሮናቫይረስን እንደሚፈውስ ተአምረኛ መፍትሄ መወሰድ የለበትም።

ጊሌድ የተባለው የመድኃኒቱ አምራች ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዋይት ሐውስ ውስጥ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር በነበራቸው ውይይት እንዳሉት ለመድኃኒቱ የተሰጠው ፈቃድ ጠቃሚ እርምጃ መሆኑን አመልከተው፤ ከፍተኛ መጠን ያለው መድኃኒት ጥቅም ላይ እንዲውል እንደሚለግሱ አሳውቀዋል

ምንጭ፡ቢቢሲ አማርኛ

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

03 May, 01:35


በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸዉን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ66ሺ በላይ ሆኗል‼️

በመላዉ አሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 1 ሚሊየን 135 ሺ 984 ሲደርስ የ66,259 ሰዎችን ህይወት ነጥቋል፡፡

የ29 ሚሊየን ሰዎች መኖሪያ የሆነችዉ ቴክሳስ በቤት ዉስጥ ሰዎች እንዲቆዩ የሚያስገድደዉ ህግ እንዲነሳ አድርጋለች፡፡ዋይት ሐውስ በበኩሉ የአሜሪካ መንግሥት ጤና አማካሪ የሆኑት ዶክተር አንቶኒ ፋውቺ ምክር ቤት ቀርበው ምስክርነት እንዳይሰጡ አግዷል። ዶክተር ፋውቺ፤ ትራምፕ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን የመከቱበት መንገድ ትክክል ነው ወይስ አይደለም በሚለው ላይ በቀጣይ ሳምንት ምስክርነት እንደሚሰጡ ይጠበቅ ነበር፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

03 May, 01:35


በኢትዮጵያ ከፍተኛ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዋች ቁጥር እና የከፋ ጉዳት ሊደርስ የሚችለው ሰኔ መጨረሻና ሐምሌ መጀመርያ ቀናት ላይ መሆኑን ጤና ጥበቃ ሚንስቴር አስታወቀ።‼️

መንግስት የኮሮና መከላከያ እርምጃዎችን ባይወስድ ኖሮ ከ27 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በኮሮና ቫይረስ ይጠቁ እንደነበርም ተገልጿል።

ጤና ሚኒስቴር ወረርሽኙ ሊያደርስ የሚችለው የከፋ ውጤት ገና አላለፍነውም፤ እንደ ኮሮና ወረርሽኝ አንድ ሀገር ገብቶ የሚብስበት ጊዜ ገና የሚመጣ ነውና መዘናጋት አደገኛ ነው ብሏል፡፡

በጤና ሚኒስቴር የጤና ነክ አገልግሎት ዳይሬክተር ዶክተር ያዕቆብ ሰማን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ፤ አንድ ወረርሽኝ የስርጭት ጣርያው ላይ ለመድርስ በአማካይ አስር ሳምንት ወይንም 3 ወር ይፈልጋል፤ እኛ አንድ ወር ከ ሁለት ሳምንታችን ስለሆነ አስከፊው ነገር ገና ከፊታችን ነው ብለዋል ፡፡

ጥናታችን እንደሚያሳየው በሀገር አቀፍ ደረጃ አሁን የምናደርገውን ጥንቃቄ ባናደርግ ከ 27 ሚሊዬን በላይ ህዝብ ኮሮና ያጠቃብን ነበር የሚሉት ዶ/ር ያዕቆብ በደንብ ከተጠነቀቅን ደግሞ የዚህን ቁጥር 60 በመቶ ወይንም 13 ሚሊዮን መቀነስ ይቻላል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እንደ ዶ/ር ያዕቆብ ኮሮና ቫይረስ በሀገራችን ሊያደርስ የሚችለው ከፍተኛውን ጉዳት የሚያደርስበት ወቅት ሰኔ መጨረሻና ሀምሌ መጀመርያ ላይ ነው፡፡

በታሪክ የተከሰቱ ወረርሽኞችም ለምሳሌ የህዳር በሽታ የዝናብና የብርድ ወቅት መውጣትን ተከትሎ ነው የስርጭታቸው ከፍታ ላይ የደረሱት ያሉ ሲሆን ከቅርብ አመታት ወዲህ ዝናብ ቀደም ብሎ ሚያዚያ፣ግንቦት ላይ እየጀመረ ስለሆነ የሰኔ የመጨረሻ ሳምንትና የሀምሌ የመጀመርያ ሳምንት ሊከፋ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

እኛም እየሰራን ያለነው ከዚያ አንፃር ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ኮሮና ሀገራችን ገባ ሲባል ድንጋጤው ህዝቡም ላይ ብቻ ሳይሆን ፌደራል መንግስትም ክልል መንግስታትም ላይ እንደነበር የምታውቀው የተወሰዱት እርምጃዎችን ስታስታውስ ነው የሚሉት ዶ/ር ያዕቆብ አሁን በኮሮና የሚያዘው ቁጥር ሲያድግ ህዝቡ ብቻ ሳይሆን መንግስትም በቁጥጥር ላላ እያለ እንደሆነ ነው የምታስተውለው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አንዳንድ መፍትሄዎች ቀድመህ በማድረግህ ብቻ ላይሰሩልህ ይችላሉ፤ የወረርሽኙ የከፍታ ወቅት ላይ (እንደ ግምታችን ሰኔ መጨረሻና ሀምሌ መጀርመያ ላይ) ፤ ህዝቡ በጣም እንዲጠነቀቅ ብትፈልግ፤ ሊዳከምና ሊሰላችብህ ይችላል፣ ስለሆነም መቼ በምን ያህል መጠን ነው እንቅስቃሴ የምገድበው፣ እርምጃዎቼን የማጠብቀው የሚለውን ሲወስን መንግስት ባለሙያዎችን ሁሌም ማማከር አለበት ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

©Ethio fm

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

03 May, 01:35


የኮሮና ቫይረስ አፍሪካዊ መረጃ!‼️

እስከዚህ ሰዓት ድረስ፦⬇️
- 53 የእፍሪካ ሀገራት ቫይረሱን ሪፖርት አድርገዋል።

- 42,704 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

- 1,722 ሰዎች ተይዘው ሞተዋል።

- 14,308 ሰዎች አገግመዋል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

01 Mar, 14:00


ኢዜማ የአሜሪካን መግለጫ «ኢትዮጵያ ሳትሳተፍበት የተፈጸሙ የቅኝ ግዛት ጊዜ ስምምነቶችን የሚያስታውስ» ሲል አብን በበኩሉ «ያልተጠበቀና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የተዳፈረ» ብሎታል። አቶ ጀዋር መሐመድ ድርድሩ ነሐሴ 23 ቀጠሮ ከተያዘለት ምርጫ በኋላ እንዲቀጥል ጠይቀዋል። እስካለፈው ታኅሳስ 2011 ዓ.ም. ድረስ ብቻ 98 ቢሊዮን ብር ገደማ የወጣበት ግድብ ድርድር መቼ እንደሚቀጥል አልታወቀም https://p.dw.com/p/3YgwO?maca=amh-RED-Telegram-dwcom


https://telegram.me/prof_biranu_nega_supportsi

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

01 Mar, 13:53


‹‹ምናልባትም በትዕግስት ለዘመናት የጠበቁት ኢትዮጵያውያን ከዓባይ ወንዝ የትዕግስታቸውን ጥፍጥና የሚቀምሱበት ጊዜ ሩቅ አይሆን ይሆናል፡፡››‼️©ጋዜጠኛ ሙሐመድ ቫል⬇️

በዓባይ ወንዝ ዙሪያ ዛሬን በትናንት ሚዛን እየለኩ ኢትዮጵያን ለመሞገት የሚሞክሩ ሁሉ ሁለት የዘነጓቸው ነጥቦች አሉ፡፡ የመጀመሪያው ጉዳይ በኢትዮጵያ ዓይናቸውን በእንጨት ጭስ እያጨናበሱ እና እያለቀሱ በትዕግስት የሚጠብቁ እናቶች መኖራቸውን መዘንጋታቸው ነው፡፡ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ የምትገነባው ግድብ ቅንጦት ሳይሆን መሠረታዊ ፍላጎት ነው፡፡ በዚህ በሰለጠነ ዘመን ዳገት ወጥተው እና ቁልቁለትን ወርደው ሕይወታቸውን ለአደጋ እያጋለጡ ጭራሮ ለቅመው እንጨት ሰብረው በእሳት ጭስ እየተፈተኑ ‹‹እራት እና መብራት›› የሚሹ እናቶች ቁጥር የትየለሌ ነው፡፡

ሁለተኛው እና ከዓባይ ወንዝ ተጠቃሚነት ጋር ተያይዞ ይህ ትውልድ ለአፍታ ሊደራደርበት የማይፈልገው ጉዳይ ደግሞ ግድቡ የእያንዳንዱን ድሀ ኢትዮጵያዊ ኪስ እና መቀነት ነክቷል፡፡ ግድቡ በብድር ወይም በምዕራባውያን ልግስና የሚገነባ ሳይሆን ነገን ተስፋ አድርጎ ከዛሬ ጠኔ ጋር ትግል በገጠመ ድሀ ኢትዮጵያዊ አንጡራ ሀብት ነው፡፡ ከወታደር እስከ አርሶ አደር፣ ከተማሪ እስከ አስተማሪ፣ ከቀን ሠራተኛ እስከ ጡረተኛ፣ ከሕጻናት እስከ አዛውንት፣ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ዛሬውን እየቀጣ ነገን የተሻለ ለማድረግ አዋጥቷል፤ ኖሮት ሳይሆን ሳይኖረው አምስት አስር ተሰብስቦ እየተገነባ ያለ ግድብ መሆኑን ማስታወስ ቀርቶ ማሰብ የሚፈልጉ አይመስሉም፤ የወቅቱ አደራዳሪዎች ወይም ሞጋቾች፡፡

ከሰሞኑ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ በምትገነባው ግድብ አካባቢ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተዘዋውሮ የተመለከተው የአልጀዚራው ጋዜጠኛ ሙሐመድ ቫል የአገሬዎቹን ኑሮ ተመልክቶ ‹‹አሁንም ኋላቀር በሆነ የኑሮ ዘይቤ ውስጥ የሚኖሩ›› ሲል ይገልፃቸዋል፡፡ ንጹሕ የመጠጥ ውኃ፣ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እና ምቹ የመኖሪያ ቤት የሌላቸው ሕዝቦች፤ ከዚህ አስከፊ የኑሮ ምስቅልቅል ለመውጣት ግድቡን በትዕግስት ይጠብቃሉ፡፡ የትዕግስታቸውን ልክና ወሰንም ‹‹ከአዕምሮ በላይ›› ሲል ይገልጸዋል፡፡
የግድቡን አጠቃላይ ሂደት የመጎብኘት ዕድል ያገኘው ጋዜጠኛ ሙሐመድ ቫል የነዋሪዎቹን ትዕግስት ከግድቡ ሠራተኞች የቀን ከሌት ጥረት ጋር አስናስሎም አንድ ፕሮጀክት ለመጨረስ የሚተጉ ሳይሆን ወገኖቻቸውን ከጨለማ ዘመን ለማሻገር የሚታትሩ መሲሆች ያደርጋቸዋል፡፡ ግድቡ ሦስት የተለያዩ የግንባታ ክፍሎች አሉት፡፡ የእያንዳንዱ ግድብ አፈፃፀም የተለያየ ቢሆንም አጠቃላይ ግንባታው 71 ነጥብ 2 በመቶ መጠናቀቁን ያትታል ጋዜጠኛው፡፡

ግድቡ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ በውኃ ሲሞላ ስድስት ሺህ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም አለው፡፡ ጋዜጠኛ ሙሐመድ ቫል በዘገባው እንደሚለው ይህም ኢትዮጵያ የእነዚያን ታጋሽ ዜጎቿን የኤሌክትሪክ ፍላጎት ከማሟላት ባለፈ ለሰባት የአፍሪካ እና ምዕራብ አውሮፓ ሀገራት የኤሌክትሪክ ኃይል በሽያጭ የማቅረብ አቅም ይኖራታል፡፡ “ከኃይል አቅርቦት ባለፈም የሀገሪቱ መፃኢ ምጣኔ ሀብታዊ ዕድገት ተስፋ ከተጣለባቸው ምሰሶዎች አንዱ ነው” ሲል ዘርፈ ብዙ አስፈላጊነቱን ያትታል ሙሐመድ ቫል በዘገባው።

ከዓባይ ወንዝ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት አንዷ የሆነችው ሱዳን ኢትዮጵያ የምትገነባው ግድብ የሚያደርስባት ጉዳት አለመኖሩ በባለሙያዎች መረጋገጡን ያወሳል፡፡ ነገር ግን አቋሟ ወጥ አለመሆኑን የሚናገረው የአልጀዚራው ጋዜጠኛ ግብጽን ግን አሁንም የዓባይ ወንዝ ታሪካዊ እና ብቸኛ ተጠቃሚ አድርጋ እንደምትመለከት ያትታል፡፡ ግብጽ ሄሮዳተስ ‹‹የዓባይ ስጦታ ናት›› ትርክት አልወጣችም የሚለው ሙሐመድ ቫል አሁን እንኳን ዘመንን የዋጀ ምክንያት ማቅረብ እንደተሳናት ያብራራል፡፡የግድቡ አጠቃላይ ቅርፅ መልክ እየያዘ ባለበት በዚህ ወቅት ከሚቀጥለው ክረምት ጀምሮ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ውስጥ 74 ቢሊዮን ኪዩ ቢክ ሜትር ውኃ በግድቡ ለመሙላት ኢትዮጵያ ማቀዷን ዘገባው ያትታል፡፡

አሜሪካ እና የዓለም ባንክ ከታዛቢነት ወደ አደራዳሪነት በተሸጋገሩበት የሰሞኑ የዋሽንግተን ውይይት የግብጽ አንዱ መደራደሪያ የውኃው ሙሌት ጊዜ ከሦስት ዓመታት ወደ ሰባት ዓመታት ከፍ ይበል የሚል እንደሆነ ያወሳል፡፡በዚህ ሁሉ የነገሮች ዑደት ውስጥ ግን ይላል ጋዜጠኛው ለዘመናት ከማኅፀኗ እየፈሰሰ የሚነጉደው የዓባይ ወንዝ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ጠብታው የሚገታበት ጊዜ የተቃረበ ይመስላል፡፡ ዝነኛው የዓባይ ወንዝ ለሚሊዮን ዓመታት ከአብራኳ ለምታፈልቀው ሀገረ ኢትዮጵያ ሊገብር የተገደደበት ጊዜ መቃረቡ እውን ይመስላል፡፡ “ምናልባት በትዕግስት ለዘመናት የጠበቁት ኢትዮጵያውያን ከዓባይ ወንዝ የትዕግስታቸውን ጥፍጥና የሚቀምሱበት ጊዜ ሩቅ አይሆን ይሆናል” ይላል፡፡

https://telegram.me/prof_biranu_nega_supports

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

01 Mar, 13:53


ኢትዮጵያ የራሷን ሰነድ ለድርድር ልታቀርብ ነው‼️⬇️

የኢትዮጵያ መንግሥት የታላቁ ህዳሴ ግድብ የውኃ አሞላልና አለቃቀቅን የተመለከተ ሰነድ አዘጋጅቶ ለድርድር እንደሚያቀርብ ተሰማ። አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የሪፖርተር ምንጭ እንደገለጹት፣ በአሜሪካና በዓለም ባንክ አመቻችነት የግድቡን የውኃ አሞላልና አለቃቀቅን በተመለከተ ሲደረግ የቆየው ድርድር ውጤት የኢትዮጵያን ጥቅም የሚጎዳ በመሆኑ፣ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን የአገሪቱን ሉዓላዊነትና ጥቅም የሚያስከብር የድርድር ሰነድ እንዲያዘጋጅ በመንግሥት ታዞ ሰነዱን በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ከተደራዳሪ ቡድኑ በተጨማሪ የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የዓለም አቀፍ ሕግ ስምምነት ባለሙያዎች፣ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሙያዎች፣ ከተለያዩ የአገር ውስጥና የውጭ ዩኒቨርስቲዎች የተወጣጡ ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች ሰነዱን በማዘጋጀት ሒደት ላይ ሌት ተቀን እየሠሩ እንደሚገኙ ማረጋገጥ ተችሏል።

ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ጠንካራ ትስስር ያላት አገር በመሆኗ በድርድሩ መሳተፍ ትክክል ቢሆንም፣ አሜሪካ ያዘጋጀችው የመጨረሻው ሰነድ ውስጥ ያልተፈቱ ጉዳዮች መኖራቸውን ምንጩ ጠቁመዋል፡፡ ታዛቢዎቹ በድርድሮች ወቅት በኢትዮጵያ ላይ ግፊት እያደረጉ እንደነበር ተሰምቷል። ይህ የአገሪቱን ጥቅም የሚፃረር ስለሆነ በቀጣዩ ድርድር ላይ ላለመሳተፍ የተሰጠው ውሳኔ ትክክለኛ መሆኑን አክለዋል።

የታዛቢነት ሚና የተሰጣቸው አሜሪካና ዓለም ባንክ ድርድሩን ወደ ሽምግልና መቀየራቸውና በመጨረሻም ራሳቸው አዘጋጅተው ለስምምነት ያቀረቡት ረቂቅ ሰነድ፣ ኢትዮጵያ እንደማትደራደርባቸው የገለጸቻቸውን በርካታ ነጥቦች ያላካተተና ለታችኞቹ የተፋሰሱ አገሮችም ጥቅም በእጅጉ ያደላ በመሆኑ፣ በኢትዮጵያ ተቀባይነት እንደማይኖረው አቋም መያዙን እኚሁ ምንጭ አስታውቀዋል።

የቀረበው ረቂቅ የስምምነት ሰነድ ከላይ ከተገለጸው በተጨማሪ ከህዳሴ ግድብ አልፎ የዓባይ ውኃ ክፍፍልን የሚመለከቱ አንቀጾች የተካተቱበት በመሆኑ፣ ከድርድር አጀንዳው ያፈነገጠ እንደሆነ ተለይቷል ሲሉ ምንጩ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የግድቡ ባለቤትና በግዛቷ ውስጥ የሚገኝ እንደ መሆኑ መጠን፣ እንዴት መሞላት አለበት የሚለውን ጉዳይ በዓለም አቀፍ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች አጠቃቀም መርሆን መሠረት በማድረግ ለታችኞቹ አገሮች ማሳወቅ፣ አገሮቹ ሊያነሱ የሚችሉት ሥጋትም በዓለም አቀፍ መርሆች ውስጥ የሚወድቅ ከሆነ ለማካተት ድርድር እንደሚደረግበት ያሳወቁት እኚሁ ምንጭ፣ በዚህ አግባብ ሰነዱን የማዘጋጀት ሥራ በመፋጠን ላይ መሆኑን አስረድተዋል። የሰነዱ ዝግጅት ሲጠናቀቅ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለግብፅና ለሱዳን እንደሚላክ ገልጸዋል።

በአሜሪካና ዓለም ባንክ አመቻችነት በሦስቱ አገሮች መካከል ሲደረግ የነበረው ድርድር ባለፈው ሳምንት ይፈረማል ተብሎ ዕቅድ ወጥቶለት የነበረ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ባወጣው መግለጫ ለስምምነት ዝግጁ እንዳልሆነና ልዑካኑንም ወደ አሜሪካ እንደማይልክ በይፋ አስታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ከሳምንት በፊት ለግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ በላኩት መልዕክት፣ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ድርድሩን አስመልክቶ የተረቀቀውን ሰነድ ለማጤን ኢትዮጵያ በቂ ጊዜ እንደምትፈልግ ማስታወቃቸው ይታወሳል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድን መልዕክት ለግብፅ ፕሬዚዳንት ያደረሰው በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የተመራ ልዑክ መሆኑም እንዲሁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በላኩት በዚህ መልዕክት ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ድርድርን በተመለከተ ጊዜ ወስዳ ማጤን እንደምትፈልግ፣ የምትደርሰበትን አቋም እንደምታሳውቅ የሚያስረዳ እንደሆነ መዘገባችን አይዘነጋም። መንግሥት ይህንን አቋሙን ባለፈው ሳምንት ለሕዝብ ይፋ ካደረገ በኋላ፣ በርካታ ኢትዮጵያዊያን የተወሰደውን አቋም በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ሲደግፉ ተስተውለዋል።

https://telegram.me/prof_biranu_nega_supports

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

01 Mar, 13:52


የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት ቅዳሜ የካቲት 21,2012 ባወጣው መግለጫ " በዋሽንግተኑ ወሳኝ በተባለው የህዳሴ ግድብ ድርድር ላይ ኢትዮጵያ ባለመገኘቷ አዝነናል። ጥቅማችንን ለማስጠበቅ ያሉንን ሁሉ አማራጭ እንጠቀማለን ። ከኢትዮጵያ ጋር እያካሄድነው ያለው ድርድር ሚዛናዊና ፍትሀዊ ነው። " ያለው መግለጫው ዝርዝር ነገሮችን ከመናገር ተቆጥቧል።‼️

https://telegram.me/prof_biranu_nega_supports

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

01 Mar, 07:23


ቱርክ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ወደ አውሮፓ ህብረት እንዲገቡ ድንበሯን መክፈቷን አስታወቀች። የሀገሩቱ ፕሬዚዳንት ሬቼፕ ታይፕ ኤርዶሃን «ከትናንት አንስቶ በሮቻችንን ከፍተናል» ሲሉ ዛሬ ኢስታንቡል ላይ ተናግረዋል። ፕሬዚዳንቱ ከአርብ ዕለት አንስቶ 18 000 የሚሆኑ ስደተኞችም የቱርክን ድንበር አልፈው የአውሮፖ ህብረት ገብተዋል ብለዋል። ይህ ቁጥርም ዛሬ 30 000 ሊደርስ እንደሚችል ተዘግቧል። ፕሬዚዳንት ኤርዶሃን ድንበራቸውን የከፈቱበት ምክንያት የአውሮፖ ህብረት የገባውን ቃል ስላልጠበቀ ነው ብለዋል።
ቱርክ ይህንን ሁሉ ስደተኛ ለማስጠለል አቅም እንደሌላት እና ከ 3,6 ሚሊዮን በላይ የሶርያ ስደተኞችን አስጠልላ እንደምትገኝም አስታውቃለች። እኢአ 2016 ቱርክ እና የአውሮፓ ህብረት ያደረጉት ስምምነት ቱርክ በባህር የሚመጡ ስደተኞች ወደ አውሮፓ እንዳይገቡ እንድትከለክል እና ሀገሯ ላይ እንድታስጠልል ሲሆን በምትኩም ከአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ድጋፍ እንደምታገኝ ነበር።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

29 Feb, 17:57


ታላቁ የህዳሴ ግድብ የዓለም አቀፍ ድጋፍና እርዳታን ለማግኘት ማስያዣ መሆን እንደሌለበት አብን አስታወቀ።‼️

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ጣሂር መሃመድ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ግብጽ እስካሁንም የ1929ኙና የ1959ኙ ኢትዮጵያን ያገለለዉ ስምምነት እንዲመለስ ነዉ የምትፈልገዉ ያሉ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ጠንካራ አቋም ሊኖረዉ ይገባል ብለዋል።

ይህ የሉዓላዊነት ጉዳይ በመሆኑ መንግስት ከህዝቡ ጋር መምከርና ቀደም ሲል በነበረበት አቋም ጸንቶ ነዉ መቀጠል ያለበት ብለዋል፡፡

ንቅናቄዉ አሁን ላይ በተለይም ከአረቡ ዓለም ጋር መስመር የሳቱ የሚመስሉ ግንኙነቶች አሉ ብሎ እንደሚያምን ገልጾ በፖለቲካ ዓለም ዉስጥ ፍጹም ታማኝ ወዳጅ ባለመኖሩ ግንኙነታችን ግልጽ መስመር ሊኖረዉ ይገባል

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

29 Feb, 11:19


#እትቱ

እትቱ…እትቱ…በረደኝ፤
እትቱ…በቀን በፀሐይ፤
እትቱ…ናፍቆትሽ ክረምቱን፤
እትቱ…ይዞት ገባ ወይ፤

ዛሬስ እህህህ …ዛሬስ ካይኔ ባጣሽ፤
ዛሬስ እህህህ …ድንገት በማርፈድሽ፤
ዛሬስ እህህህ …ላምባዬን አንስቼ፤
ወጣሁኝ ...ወጣሁ ልፈልግሽ፤
ዛሬስ እህህህ …ወጣሁ ልፈልግሽ፤

እትቱ…እትቱ…በረደኝ፤
እትቱ…በቀን በፀሀይ፤
እትቱ…ናፍቆትሽ ክረምቱን፤
አትቱ…ይዞት ገባ ወይ፤

ዛሬስ እህህህ …ስፍስፍ አልኩኝ ባንቺ፤❤️
ዛሬስ እህህህ …ሰውነቴም ከዳኝ፤
ዛሬስ እህህህ …በልብ ያለ ነገር፤
በሰው... በሰው አፍ ላይዳኝ፤
ዛሬስ በሰው አፍ ላይዳኝ፤

በቀን መብራት ይዤ ተቆጠርኩኝ እንደ ጅል፤
እኔስ ባንቺ ጉዳይ ብልጠትን አልከጅል፤
ሳልምሽ አምሽቼ ሲናፍቅሽ አይኔ፤
አንቺን ካላገኘሁ መንጋቱስ ለምኔ…ዋ፤
የጨዋታሽ ማማር የሳቅሽ ፏፏቴ፤
ውሀዉን አስረሳኝ ሲፈስ ወደ አንጀቴ፤
ወንዙ ዳር አትጥሪኝ መልክሽ ይታየኛል፤
አንቺን አሳስቆ እኔን ይወስደኛል፤ ((②)(×)

በወግ ያልነኩትን ዘራፍ ሲሉት ሸሽቶ፤
ይታገለኝ ጀመር ፍቅርሽ ጦር አንስቶ፤❤️
አንቺዉ ምከሪልኝ ዘንጉን ይመልሰው፤
ጦር ይሰበቃል ወይ ጋሻ በሌለው

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

29 Feb, 11:16


በኅዳሴ ግድብ ድርድር የዩናይትድ ስቴትስ መግለጫ‼️⬇️

በታላቁ የኅዳሴ ግድብ ድርድር ታዛቢ ነች ስትባል የከረመችው ዩናይትድ ስቴትስ የግድቡ ውኃ ሙሌትና የኃይል ማመንጨት ሙከራ ያለስምምነት እንዳይካሄድ ስትል ማስጠንቀቂያ አዘል መግለጫ አወጣች።

ኢትዮጵያ የግድቡን ውኃ ሙሌት በመጪው ሰኔ 2012 ለመጀመርና በ2013 በ2ቱ ተርባይኖች ኃይል ለማመንጨት እቅድ እንዳላት ይታወቃል።
የካቲት 19 በዋሽንግተን የተቀጠረው ድርድር ላይ ኢትዮጵያ "ተደራዳሪዎቼ በአገር ውስጥ የሚያካሂዱትን የባለድርሻ ምክክር ስላልጨረሱ አልሳተፍም ስትል" ማሳወቋን ተከትሎ፤ የዩናይትድ ስቴትስ ግምጃ ቤት ከግብፅና ሱዳን ተደራዳሪ ልዑኮች ጋር መምከሩን አሳውቋል።

ባወጣው መግለጫም ሲባል የነበረውን የታዛቢነት ሚና የተጣረሰ ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክትን ለኢትዮጵያ አስተላልፏል።

የግድቡ አጠቃላይ ሂደት የአውሮፓዊያኑን የ2015 የመርሆች ስምምነት እና በተፋሰሱ ላይ ጉልህ ጉዳት ያለማድረስ እሳቤ መከተል አለበት የሚለው የዋሽንግተን መግለጫ በግብፅ በኩል የታየውን ስምምነቱን ለመፈረም የመዘጋጀት ቁርጠኝነት እንደሚያደንቅም ያክላል።

ይሁን እንጂ የ3ቱ አገራት የቴክኒክና የሕግ ባለሙያዎች የሚያስማማቸውን የጋራ የሕግ ማዕቀፍ ማውጣት ባልቻሉበት ወቅት ነው ዋሽንግተን አዲስ አበባ ላይ ጫና ለማሳደር እየጣረች የምትገኘው።

ብሔራዊ ጥቅሜን አሳልፎ የሚሰጥን ስምምነት በየትኛውም ኃይል ተፅዕኖ አልፈርምም እያለ ከከረመው የኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ለዋሽንግተን የአሁኑ መግለጫ እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም።

በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የትራምፕ አስተዳደር ለግብፅ ከመወገንና ኢትዮጵያ ላይ ጫና ከማሳደር እንዲቆጠብ የሚጠይቅ የተቃውሞ ትዕይንተ

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

29 Feb, 11:16


አሜሪካ በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ የሰጠቸው ትዕዛዝ ለግብጽ ያላትን ወገንተኝነት በግልጽ ያሳየችበት መሆኑን ዶክተር ያዕቆብ አርሳኖ ተናገሩ።‼️

አሜሪካ በኢትዮጵያ፣ሱዳን እና ግብጽ በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ ከስምምነት ሳይደርሱ ኢትዮጵያ ውሃ መሙላት አትችልም የሚል ትዕዛዝ ማስተላለፉ ይታወሳል።

ኢትዮጵያን ወክለው በግድቡ ዙሪያ ከሚደራደሩ ምሁራን እና ዲፕሎማቶች መካከል አንዱ የሆኑት የዓለም አቀፍ የውሃ ፖለቲካ መምህሩ ዶክተር ያዕቆብ አርሳኖ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የአሜሪካ ውሳኔ በግልጽ ለግብጽ ያላትን ወገንተኝነት ያሳየችበት ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያም አሜሪካ ባስተላለፈቸው ውሳኔ ሃሳብ ዙሪያ እንደ አገር አቋም ለመያዝ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ተደራዳሪ ቡድን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጧል።

ከዘጠኝ ዓመት በፊት የተጀመረው የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ70 በመቶ በላይ የተጠናቀቀ ሲሆን ግድቡ የተጀመረበት ዘጠነኛ ዓመት ከአንድ ወር በኋላ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ይጠበቃል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

29 Feb, 11:16


የኢትዮጲያ አየር መንገድ የዓመቱ ምርጥ ዓለም አቀፍ የአየር ጭነት ገበያ ሽልማት አሸነፈ፡፡‼️

ግዙፉ የአየር ላይ ጭነት ኦፕሬተር እና የባለብዙ ሽልማት አሸናፊው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጭነት እና ሎጅስቲክስ አገልግሎቱ የአውሮፓውያኑ 2020ን አለም አቀፍ የአየር ጭነት ገበያ ሽልማትን ተሸልሟል፡፡

በአየር ጭነት አግግሎት ላይ ከፍተኛ ስኬት ያስመዘገቡ የጭነት አገልገሎት ሰጪዎች በሚሸለሙበት እና በህንድ ሙምባይ ከተማ በተካሄደው የሽልማት ስነስርዓት ላይ የኢትዮጲያ አየር መንገድ ሽልማቱን ተቀብሏል፡፡

አየር መንገዱ በአየር የጭነት አገልግሎት ኢንዱስትሪ ላይ ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋፆ ፣ላሳየው ተወዳዳሪነት እና በዓለም ደረጃ በአየር ጭነት ገበያ ውስጥ ላሳየው ፈጣን እድገት ሽልማቱን ማግኘቱን ለአትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ሽልማቱን አስመልቶ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ሽልማቱን በማሸነፋች ኩራት ይሰማናል ፣ በጭነት አገልግሎትም ቢሆን ከአፍሪካ እንዲሁም ከመላው አለም ቀዳሚ ስለመሆናችን ምስክር ነው በቀጣይም ጠንክረን እንድንሰራ ትልቅ ማበረታቻ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ የጭነት እና ሎጅስቲክስ አገልግሎት በየዓመቱ ወደ 1 ሚሊዮን ቶን የሚጠጋ ጭነትን የማስተናገድ አቅም ያለው በአፍሪካ ትልቁ የሆነውን የጭነት ጣቢያ መገንባቱ የሚታወስ ነው፡፡
ወደ አፍሪካ ፣ ገልፍ ሀገራት፣ መካለኛው ምስራቅ ፣ እስያ፣ ሰሜንና ላቲን አሜሪካ እንዲሁም አውሮፓ በሚገኙ 57 መዳረሻዎቹም የጭነት አገልግሎቱን ተደራሽ ያደርጋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አገልግሎቱን በአጠቃላይ ከ4 መቶ 32 ሚሊየን ኪሌ ግራም በላይ ከፍ ማድረጉን አስታውቋል።