Natinael Mekonnen @natinaelmekonnen17 Channel on Telegram

Natinael Mekonnen

@natinaelmekonnen17


ይህ ቻናል ቴሌግራሜ hacked በተደረገበት ሳት ለግዝያዊነት የከፈትኩት ቻናል ነው ለችግር ጊዜ ይጠቅማል ተቀላቀሉ
በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ከፈለጉ @NatinaelMekonnen1 መረጃዎችን ይላኩልን

Telegram @NatinaelMekonnen1

አጭር መረጃ ቴሌግራም - Natinael Mekonnen (Amharic)

አጭር መረጃ ቴሌግራም - Natinael Mekonnennnእንዴት እንደምትረዳትና አስተያየት የሌሎቹን የቴሌግራሜዎችን ለማከብር እና ኮምሽን ላይ መረጃዎችን እንዴት በማብራሪያ ሊቀንስ ይችላል? ቴሌግራሜቅን መጠን ለማከብርና መረጃዎችን ከመማር ከፈልጉ አይደለም።nn'አጭር መረጃ ቴሌግራም - Natinael Mekonnen' እንዴት እና ምን ለመፈለግ እንደምትወስድ በመረጃዎችና አስተማሪዎች በአባሊያዎ መከላከል እንደመረጃዎችና መዋጮ እንዴት እንደምትልከክል መስከት እንዴት እና ምን እንደምትረዳት መጠን አስተማሪ አልቀረም።nnበዚህ ቴሌግራም እንዴት የተጠቃህነው 'አጭር መረጃ ቴሌግራም - Natinael Mekonnen' ይጠብቃል ምን ይጠብቁ ለሚሉ የሆነው ነገሮችን እና አስተማሪዎችን በማስተማሩ ለችግሩ ላይ መጠን እና እንደምታገኙ በመቀነስ ለመከታተል ይረዳል።nnበቴሌግራም @NatinaelMekonnen1 በተነካው በዚህ ቴሌግራም ላይ በመረጃዎችና አስተማሪዎች እንዴት ርዕስ እና ማግኘት አስተማሪነቷን ይስማል። በዚህ ቴሌግራም እንዴት ለመረጃዎች እና አስተማሪዎች ለመምረጥ እንዴት ይቀንሱታል።nnየቴሌግራሜ ስለ ሚስት ለምስልም፣ ሁኔታን ስለ እድሜ ያተኮነሰው መረፍያ እና መመሪያዎቹን ለችግሩ ወደ ተከሰተ መረጃ እና አስተማሪዎቹ በሞላሁ ቴሌግራሜ ሰዓታችን በመከላክ እና መረጃዎቹን ከፈለጉ።nnለችግራቹ እና አስተማራነቹ ወደ ቴሌግራሜ ሰዓት የሚመጣለውን መረጃ እና አስታወሱት። እስከ ዛሬ አስተማሪነት እና መረጃዎቹ የሚሰበሰቡውን እና አስተማሪዎቷን በመስጠት እና መረጃዎቷን በከተሞች እንዴት መስጠት እና ከፈለጉ ለመከታተል ያሳየናል።nnከሰዓታችን መጠን ይዞ ለአጭር መረጃ ቴሌግራም - Natinael Mekonnen ከመረከብ እና መስክ አሠራር ተጋላጭ።

Natinael Mekonnen

20 Aug, 23:34


The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 8 days, that account will self-destruct and this channel will no longer have an owner.

Natinael Mekonnen

09 Aug, 03:15


The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 20 days, that account will self-destruct and this channel will no longer have an owner.

Natinael Mekonnen

01 Jan, 01:43


የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ የተፈጠሩ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምርመራ ሪፖርትን ነገ ይፋ እንደሚያደርግ አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው በድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ክስተት ጋር በተያያዘ የተፈጠሩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ሲመረምር መቆየቱን ገልጿል።

ሪፖርቱ ከሰኔ 22 አስከ 25 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ባሉ ቀናት ውስጥ የተፈጠሩ ቀውሶችን አስመልክቶ ምርመራ ማካሄዱንም ገልጿል።

ሪፖርቱ 59 ገጽ የያዘ የምርመራ ሪፖርት ሲሆን ነገ ሁሉም መገናኛ ብዙሃን በተገኙበት በአዲስ አበባ ለህዝብ ይፋ እንደሚሆን ኮሚሽኑ ገልጿል።

Natinael Mekonnen

01 Jan, 01:43


በትግራይ አዲስ ሰማይ ነው እየተፈጠረ ያለው

#Ethiopia : ዶ/ር አብርሃም በላይ የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ከመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ከተናገሩት የተወሰደ

በትግራይ አዲስ ሰማይ ነው እየተፈጠረ ያለው። አዲስ የፖለቲካ ሰማይ፣ አዲስ የሰላም ሰማይ፣ አዲስ የአንድነት ሰማይ። ይሄ ህዝብ የተከበረ ህዝብ ነው፣ ይሄ ህዝብ የሚጨቆን ህዝብ አይደለም። ለዚህ ህዝብ የሚገባው ራሱን የሚፈልገው እንዲያደርግ መፍቀድ ነው፣ ለዚህ ህዝብ የሚያስፈልገው ነፃነት ብቻ ነው። መሪዎቹ እንዴት ይመርጣል፣ ምን መስራት እንዳለበት፣ እንዴት ይደረጋል ልትነግረው አትችልም ራሱ ይነግርሃል እንጂ።

ቀጣይ አካሄዳችን እኛ የምንፈልገው፣ እኛ የምንለው የምንጭንበት ሳይሆን ህዝባችን የሚለን ለማድረግ፣ ህዝባችን የፈለገውን የመረጠው እንዲያስተዳድረው እድሉ እንሰጠዋለን።

ትግራዋይ ተናጋሪ አልነበረም፣ ትግራዋይ በበሬ ወለደ የሚደናገር አልነበረም፣ ህዝባችን ሰራተኛ፣ ሙሁር፣ ተመራማሪ እና በምክንያት የሚያምን ህዝብ ነበር። ህዝባችን ሃይማኖቱ ያከብራል፣ ባህሉ ያከብራል፣ ወላጆቹ የሚያምን፣ የሚመራመር ነበር እንጂ ወላጆች የማይከበሩባት፣ ሃይማኖት የማይከበርበት ትግራይ አልነበረም። ይሄን ለማጥፋት የተንቀሳቀሱ ሃይሎች እድሚያቸው ስላጠረ እንኳን ደስ አለን።

ከትግርኛ ወደ አማርኛ ትርጉም ግዕዝ ሚዲያ

Natinael Mekonnen

30 Dec, 17:34


ጃል መሮ መሞቱን የሚያሳይ ቪዲዮ ፊደል ሚዲያ እጅ ገብቷል https://youtu.be/Ohe-y7t0FBc

Natinael Mekonnen

30 Dec, 15:37


የሕወሓት ጁንታ የመቐለውን የሰሜን ዕዝ ሆስፒታል ማውደሙን በትግራይ ክልል የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት አስታወቀ

#Ethiopia : በትግራይ ክልል የተደነገገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም እየመረመረ ያለው ኮማንድ ፖስት በሕወሓት የጥፋት ቡድን ጉዳት የደረሰበትን የሰሜን ዕዝ ሆስፒታል ተመልክቶ ድርጊቱን አውግዟል።
የጉዳቱን መጠን በተመለከተ በባለሙያዎች ተጠንቶ በቀጣይ የሚገለጽ ቢሆንም በከፍተኛ ወጪ የተገዙ የሕክምና መሣሪያዎች እና መድኃኒቶች በጁንታው ቡድን የተዘረፉ መሆኑን የተቋማቱ ባለሙያዎች ጠቁመዋል።

Natinael Mekonnen

30 Dec, 15:37


'ራይዚንግ ኢትዮጵያ' በሚል የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ተጀመረ

#Ethiopia : ራይዚንግ ኢትዮጵያ' በሚል የተሳሳቱ የመገናኛ ብዙኀን ትርክቶች ለማረቅና የኢትዮጵያን መልካም ጎን ለማስታዋወቅ ያለመ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ዛሬ ተጀምሯል፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ቱሪዝም ኢትዮጵያ እና በሌሎች ኢትዮጵያውያን ትብብር የተዘጋጀው ዘመቻ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎችን እንደሚያስተባብር ተገልጿል፡፡

በዘመቻው ኢትዮጵያ ያላትን የኢንቨስትመንት እምቅ አቅም፣ ባህል፣ የቱሪስት መዳረሻዎችን፣ በጎ አድራጎትን እና ፕሮጀክቶችን ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ያስተዋውቃልም ተብሏል፡፡

የዘመቻው የመጀመሪያ ምዕራፍ በቱሪዝም ላይ የሚያተኩር ሲሆን በዛሬው እለት በሚካሄድ የዌቢናር ውይይት እንደሚጀመርናም ነው የተነገረው።

የማጠቃለያው ምዕራፍ ደግሞ “የኢትዮጵያ የመለገስ ሳምንት” በሚል እንደ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ላሉ አገር አቀፍ ፕሮጀክቶች የሚውል ህዝባዊ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ይካሄዳል ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

Natinael Mekonnen

30 Dec, 15:37


በኢሉ አባቦር ዞን 12 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ ገለጸ!

በኢሉ አባቦር ዞን 12 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ 34 የጦር መሳሪያዎችና በርካታ ጥይቶች መያዛቸውንም የኢሉ አባቦር ዞን ፖሊስ ጽ/ቤት መግለጹን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

Natinael Mekonnen

30 Dec, 15:36


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው ምርጫ የዕጩዎች የድጋፍ ፊርማ እንዲቀር ፓርላማውን ጠየቀ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ.ም. እንዲከናወን ቀን ለተቆረጠለት ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ፣ ዕጩዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸው የነበረው የድጋፍ ፊርማ እንዲቀርና አገልግሎት ላይ እንዳይውል እንዲደረግ ፓርላማውን ጠየቀ፡፡

በምርጫ ለመወዳደር የሚፈልግ የግልም ሆነ የፖለቲካ ፓርቲን፣ ግንባርን ወይም ቅንጅትን ወክለው በዕጩነት የሚቀርቡ ተወዳዳሪዎች፣ ከ5,000 እስከ 750 የሚደርሱ የድጋፍ ፊርማዎችን ማቅረብ ይጠበቅባቸው ነበረ፡፡ ይሁንና በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ የወረቀት ንክኪን በተቻለ መጠን ለመቀነስና የሚመጡ የድጋፍ ፊርማዎችን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ካለው የጊዜ መጣበብ ጋር በተገናኘ አዳጋች ስለሚሆን፣ ፓርላማው ከግንዛቤ አስገብቶ በአዋጁ ላይ ይኼንን ጉዳይ ማሻሻያ እንዲያደርግበት ጥያቄ መቅረቡን፣ የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ታኅሳስ 16 ቀን 2013 ዓ.ም. ገልጸዋል፡፡

[Reporter]

Natinael Mekonnen

30 Dec, 15:36


በድባጤ 'ዚጊ ቀበሌ' ውስጥ በተፈፀመ ጥቃት ሁለት ንፁሃን ሲገደሉ አንድ ሰው ቆስሏል።

ጥቃቱ በትላንትናው ዕለት ማለዳ ላይ እንደተፈፀመ የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ገልጿል።

የሟቾች የቀብር ስነ ስርዓት ትላንት ተፈፅሟል።

በጥቃቱ ከተገደሉት ውስጥ አንደኛው ባለትዳር እና 5 ልጆች አባት እንደሆኑ ወንድማቸው ትላንት ምሽት በተሰራጨ መደበኛው የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ፕሮግራም ላይ ቀርበው ሲናግሩ ተደምጠዋል።

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ም/ቤት አፈጉባኤ አቶ ታደለ ተረፈ ጥቃቱን አረጋግጠዋል ፥ እሳቸውም በድባጤ ወረዳ ዚጊ ቀበሌ ወደ ማሳቸው በሚሄዱ 3 ሰዎች ላይ ጥቃት ተፈፅሞ 2ቱ መገደላቸውን አንደኛው መቁሰሉን መረጃ እንዳላቸው ተናግረዋል።

ትላንት የመተከል ዋና አስተዳዳሪ እንዲሁም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር በዞኑ ካለው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ እጃቸው እንዳለበት በመጠርጠሩ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል።

Natinael Mekonnen

30 Dec, 03:50


#Ethiopia : የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ም/ኮሚሽነር ኢንስፔክተር ምስጋና እንጂፈታ በመተከል ዞን የጸጥታ ችግር እጃቸው እንዳለበት በመጠርጠራቸው ዛሬ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተገለፀ። ይህን የገለፁት የክልሉ ሰላም ግንባታና ፀጥታ ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ሙሳ ሃሚድ ናቸው።

አቶ ሙሳ ፥ ሌሎችም ከፀጥታ ችግር ጋር እጃቸው ያለባቸውን አመራሮች እና ግለሰቦች የማደኑ ስራ መቀጠሉን ለኢዜአ ተናግረዋል። ዛሬ ረፋድ የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ አትንኩት ሽቱ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መገለፁ ይታወሳል::

Natinael Mekonnen

30 Dec, 03:50


ልዩ መረጃ ‼️

#Ethiopia : በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከመተከል የጸጥታ ችግር ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩ ሁለት ተጨማሪ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ሠላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ሙሳ ሃሚድ ÷ዛሬ በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አትንኩት ሽቱ አንዱ ናቸው፡፡ ሌላው የክልሉ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ኢንስፔክተር ምስጋና እንጂፈታ በመተከል የጸጥታ ችግር እጃቸው እንዳለበት በመጠርጠራቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል፡፡
የዞኑ ሠላም ወደ ቀደመ ሁኔታ እስኪመለስ ከጸጥታ ችግሩ ጋር እጃቸው ያላባቸውን አመራሮች ጨምሮ ሌሎችንም ግለሰቦች የማደን ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን አቶ ሙሳ ጨምረው መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Natinael Mekonnen

30 Dec, 03:35


Channel created