ጎህ ቴክኖሎጂ / Goh Technology @technology_in_amaharic Channel on Telegram

ጎህ ቴክኖሎጂ / Goh Technology

@technology_in_amaharic


”ከቴክኖሎጂ ጋር መዘመን ብልህነት ነው"

ጎህ ቴክኖሎጂ / Goh Technology (Amharic)

ጎህ ቴክኖሎጂ የቴክኖሎጂ መንገድን ያካትታል እና የመሰረታዊ ዘንግድን ያከታታል። ይህ ቴክኖሎጂ አማርኛ የቴክኖሎጂን ያካትታል፣ የዚህንም ቴክኖሎጂን በመጠቀም እንዲህ ይሆን ያለዎት ነገር ነውu0022 የቴክኖሎጂ የዚህን ድረ-ገጽን ተለያዩ ጉዳይ ገጽታዎችን የቴክኖሎጂን ተከተላቸው። እናም ሌላ ታሪክ እና ደምቢያን መረጃዎችን የቴክኖሎጂን ቀጥታ አስቀድሞ ይጨምሩ።

ጎህ ቴክኖሎጂ / Goh Technology

13 Nov, 12:21


https://youtu.be/GTDH8PykrEw?si=De3x6hoS89oxc7IM

ጎህ ቴክኖሎጂ / Goh Technology

09 Nov, 21:13


https://youtu.be/2r9ebe1f8TA?si=o_etTYBK5WQwNtPg

ጎህ ቴክኖሎጂ / Goh Technology

05 Nov, 18:42


በ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ የዲጂታል አቅምዎን ያሳድጉ! ተጠቃሚነትዎን ያስፉ!

5 #ሚሊዮን_የኢትዮጵያ_ኮደርስ_ለምን?

የ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ በፍጥነት እየተለዋወጠ ባለው ዓለም ዜጎች ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አስፈላጊ የሆኑ የዲጂታል ዘመን ክህሎቶችን ለማስታጠቅ በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ይፋ የተደረገ መርሃ ግብር ነው?

የ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ በዲጂታሉ ዓለም ጊዜውን የዋጀ እውቀትና ክህሎት በመታጠቅ ራሳቸውንና ሀገራቸውን መቀየር የሚፈልግ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ስልጠናውን በነፃ መከታተልና ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ማግኘት ይችላሉ፡፡

#እንዴት_መመዝገብ_ይቻላል?

በ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ የሚሰጠውን ሥልጠና ለመከታተል ከዚህ በታች በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ ተመዝግበው አሁኑኑ ስልጠናዎን መጀመር ይችላሉ፡፡ www.ethiocoders.et

#የዲጂታል_ሥራዎች_እንዴት_ማግኘት_ይቻላል?

በ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ስልጠና የወሰዱትን ጨምሮ በዲጂታል ክህሎት መሰረታዊ እውቀትና ክህሎት ኖሯቸው በኦን ላይን የሚመጡ የሥራ ዕድሎችን ለመጠቀም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት (https://lmis.gov.et)ላይ በመመዝገብ የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን ይችላል፡፡

እስካሁን በስርዓቱ ከመጡ ከ85 ሺህ በላይ የኦን ላየን ሥራ (Remote Job) ዕድሎች ከ26 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።'
👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼
https://www.youtube.com/watch?v=eCbe_y8TYmY

ጎህ ቴክኖሎጂ / Goh Technology

03 Nov, 11:53


https://youtu.be/5IObJurvC2E?si=i05F56AODH3aH4nV

ጎህ ቴክኖሎጂ / Goh Technology

28 Oct, 18:45


https://youtu.be/7puQCbKMjwc?si=wyAcTUu9IVHaJPlX

ጎህ ቴክኖሎጂ / Goh Technology

28 Oct, 05:35


በእንቅልፍ ወቅት የምናያቸውን ሕልሞች እንደፊልም ደግመን ለማየት የሚያስችለን ቴክኖሎጂ ይፋ ሆነ፡፡
_________________________________________

የጃፓን ተመራማሪዎች በእንቅልፍ ወቅት የሚከሰቱ ሕልሞችን በመቅረፅ በፊልም መልክ የሚያጫውት መሣሪያ ይፋ አድርገዋል፡፡ ተመራማሪዎቹ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና የአዕምሮ ምስልን መውሰድ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ሕልምን የሚመዘግብና በፊልም መልክ የሚያሳይ መሣሪያ መፍጠር ችለዋል፡፡ ቴክኖሎጂው ከሕልም ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ የነርቭ እንቅስቃሴዎችን ለመመዝገብ ኤም.አር አይ (magnetic resonance imaging) ይጠቀማል፡፡
ይህ ፈጠራ የአንጎል እንቅስቃሴን በመጠቀም አንዳንድ የሕልም ገጽታዎችን የመግለጽ አቅም አለው። በቴክኖሎጂው ላይ በተደረገ ሙከራ ያለሙትን ሕልም ይዘት ሳይቀይር የመተንተን አቅሙ ከ70 በመቶ በላይ ትክክል ሆኖ መገኘቱን ኒውስ18 የተባለው ድረ ገጽ ዘግቧል፡፡
ቴክኖሎጂው የአዕምሮ ጤናን ለማሻሻል፣ የግለሰቦችን ስብዕና ለመተንተን እና ከሥነ-ልቦና ጋር ተያያዥ በሽታዎችን ለመመርመር ጥቅም ላይ እንደሚውል ተመላክቷል፡፡
መሣሪያው ዕውን መሆን የቻለው በኪዮቶ በሚገኘው የኤ.ቲ.አር (ATR) ኮምፒውቲሽናል ኒውሮሳይንስ ላቦራቶሪዎች ውስጥ በተደረገ ጥናት ነው፡፡

ጎህ ቴክኖሎጂ / Goh Technology

25 Oct, 18:34


https://www.youtube.com/watch?v=gf5G_NmMigs&pp=ygUZc29jaWFsIGR1bGltbWEgIGFtYWhhcmljIA%3D%3D

ጎህ ቴክኖሎጂ / Goh Technology

17 Oct, 19:54


ለምን? አእምሯችን አይፈተንማ፤ አዲስ ነገር ሙከራ አያደርግም፣ አዲስ ክሂሎት አይለምድም። ተመሳሳይ ኑሮ ነው የሚኖረው። ስለዚህ አእምሯችንን እንጎዳዋለን፡፡ ታዲያ ምን ይሻላል? የሚሻለው አዲስ ነገር ለማግኘት መሞከር ነው፡፡ አዲስ ነገር በማድረግ ሕይወትን መቀየር ያስፈልጋል፡፡ ሥራም ከሆነ ትላንት ከሠራነው ዛሬ ጨመር አድርገን መሥራት ነው፡፡ የሚያስደስቱንን ነገር ማድረግ፣ ክሂሎቶችን መልመድ ይገባል። ለምሳሌ ዳንስ የሚወድ ሰው ዳንስ ቢማር፣ የሙዚቃ መሳሪያ መጨዋት የሚወድ ሰው እንዴት እንደሚጫወት ቢማር፣ አዲስ ቋንቋ መልመድ የሚፈልግ ሰው ቋንቋውን ቢማር ብቻ በፊት ከነበርንበት ሁኔታ ሊቀይሩ የሚችሉ ነገሮችን መልመድ ያስፈልጋል፡፡

5ኛ. ዝምታ ማብዛት

ማህበራዊ ሕይወታችን ላይ በጣም ሰነፍ ከሆንን ወይም ደግሞ ከሰዎች ጋር መግባባት የማንፈልግ ከሆነ እንደማሽን ነው የምንንቀሳቀሰው። ለምን? ከሰዎች ጋር አናወራም፡፡ ሃሳብ አንለዋወጥም። መረጃ አንወስድም። አይብዛ እንጂ ጓደኛ መያዝ፣ ከቤተሰብ ጋር ጊዜ ማሳለፍ በጣም ወሳኝ ነው። አእምሯችን ይታደሳል፡፡ አንድ ጥግ ብቻ አይቀመጥም፡፡

አእምሯችን እንደጡንቻ ነው፡፡ እንዳሰለጠነው ነው የሚሆነው፡፡ ካጠነከርነውና ብዙ ነገር ካሰራነው በምላሹ የመሥራት አቅሙን ያሳድጋል፡ ከሰዎች ጋር መግባባት በራሱ የሚሰጠን ጥቅም አለ፡፡ ያነቃቃናል። ጉልበት ይሰጠናል፡፡ ይሁንና ጓደኛ ስንይዝ መምረጥ አለብን፡፡ ‹‹አንድ ዓይነት ቀለም ያላቸው ወፎች አብረው ይበራሉ›› እንደሚባለው ከእኛ ጋር ህልማችንን የሚጋሩ፣ በዓላማ የሚመሳሰሉ፣ ቁምነገረኛ የሆኑ፣ በጎ ነገርን የሚሰብኩ፣ ከእኛ ጋር ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መሆን አለባቸው። ዝምታ የምናበዛ ከሆነ፣ ብቸኝነት የምናበዛ ከሆነ፣ አእምሯችንን እየጎዳነው ነው፡፡

6ኛ. በቂ እረፍት አለማድረግ

ይሄ እንደ ቀላል ልማድ ሊወሰድ ይችላል፡፡ በተለይ አንዳንድ ሰዎች ሥራቸውን በትጋት ይሰሩና ማታ አምሽተው ፊልም ያያሉ፡፡ በቂ እረፍትና እንቅልፍ ሳያገኙ እንደገና በጠዋት ተነስተው ወደ ሥራ ይሄዳሉ። ወይ ደግሞ በቂ እረፍት ሳያደርጉ አሟቸውም ቢሆን በግድ ሥራቸውን የሚሰሩ ሰዎች አሉ፡፡ እንደውም ሳይንሱ ሰዎች እንቅልፋቸው በተመሳሳይ ሰዓት መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል። ይህም በተመሳሳይ ሰዓት መተኛትና በተመሳሳይ ሰዓት መነሳት እንደማለት ነው። ሁሌም አራት ሰዓት የምትተኙ ከሆነ ሰዓቱን ማዛነፍ የለባችሁም። ከዛ አስራ ሁለት ሰዓት የምትነሱ ከሆነ ሰዓቱን ማዛነፍ አያስፈልግም፡፡

የእረፍት ቀን ቅዳሜና እሑድም ቢሆን፣ የበዓል ቀናትም ቢሆን የእንቅልፍና ከእንቅልፍ የመነሻ ሰዓት ማዛነፍ አይገባም፡፡ ለምን? አእምሯችን የማረፋ ፈድን በተለይ ደግሞ እንቅልፍ የመተኛት ሂደት መልመድ አለበት፡፡ ምክንያቱም ይሄ ከሆነለት አእምሯችን እንደ አዲስ ነው የሚነቃው። ለአእምሯችን እረፍት የማንሰጠው ከሆነ ግን አእምሯችንን እንጎዳዋለን፡፡ ስለዚህ ከላይ የተጠቀሱት ምክንያቶች ቀላል መስለው ቢታዩም አእምሯችንን እየጎዱት ነው፡፡ ስለዚህ በፍጥነት ማቆም አለብን፡፡
አስናቀ ፀጋዬ

አዲስ ዘመን ህዳር 8/2016
ቴሌግራም:-https://t.me/technology_in_amaharic
ዩቱብ፦ https://www.youtube.com/@goh-tube

ጎህ ቴክኖሎጂ / Goh Technology

17 Oct, 19:54


አእምሮን እየጎዱ ያሉ ቀላል ልማዶች

አእምሯችን የሰውነታችን ዋነኛ አንቀሳቃሽ ክፍል ነው፡፡ ያለ አእምሯችን ምንም ማድረግ አንችልም። አእምሯችን ሲጎዳ ሃሳብ ማመንጨት የለም፡፡ እንደልባችን ሰውነታችንን ማዘዝ ይሳነናል። ጤናማ ሕይወት አይኖረንም፡፡ ለዛም ነው የአእምሮ ጤና የሁሉም የሰውነት ክፍል ጤና ነው የሚባለው። ከዚህ አንፃር የአእምሯችንን ጤና መጠበቅ ወሳኝ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ ምንም እንኳን አእምሯችን በተለያዩ ከአቅም በላይ በሆኑ ውጫዊና ውስጣዊ ምክንያቶች ጤናው የሚቃወስበት ዕድል ቢኖርም አንዳንዴ ግን ቀላል በሆኑና በራሳችን ቸልተኝነት ምክንያት የሚጎዳበት አጋጣሚ አለ። ይህ ሲባል አእምሯችንን መጠቀም በሚገባን ልክ ካልሰራንበት ምንም ነው፡፡

እነዚህ ቀላል የሆኑ ነገሮች አእምሯችን ከአቅሙ በታች እንዲሰራ የሚያደርጉ ናቸው፡፡ እንድንሰንፍና የተሻለ ሰው እንዳንሆን ያደርጋሉ። ለምሳሌ አንድ ገበሬ ማሳው ላይ ጤፍ ከዘራ ጤፍ ያጭዳል። ስንዴም ከዘራ ስንዴ ያጭዳል። ምንም ባይዘራ ደግሞ ያው አረም ያጭዳል። እኛስ አእምሯችን ላይ ምን እየዘራን ነው? ጥሩ ነገር ከሆነ እንቀጥልበት፡፡ መጥፎ ከሆነ ደግሞ እናስወግደው። ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አእምሯችን እየጎዱ ያሉ ቀላል፣ ነገር ግን መጥፎ የሆኑ ልማዶችን ማስወገድ የግድ ይለናል፡፡

1ኛ. ረጅም ሰዓት ስክሪን ላይ መቆየት

አብዛኛዎቻችን በስልክ፣ ኮምፒዩተርና ላፕቶፕ ስክሪኖች ላይ ረጅም ሰዓት እናጠፋለን። አንዳንዴማ ረጅም ሰዓት እንዳጠፋን ሁሉ አይታወቀንም። ዓይኖቻችን በስልክና ላፕቶፕ ስክሪኖች ላይ ረጅም ሰዓት በቆየ ቁጥር white and gray matter የሚባለው የአእምሮ ክፍል ይጎዳል። እንደውም frontal lob የሚባለውና በጣም ከባድና ጠንካራ ሃሳቦችን የምናመነጭበት የአእምሮ ክፍል ይደክማል። በዚህ ምክንያት ጠንካራ ሃሳቦችን ማሰብ፣ በደንብ ማሰላሰል ይሳነናል፡፡ ደካማ እንሆናለን፡፡ ማንበብ እንድንጠላ፣ በጣም ጥሩ ጥሩ የሆኑና የአእምሮ ጡንቻን የሚያጠነክሩ ሥራዎችን እንዳንሰራና እንዳንለወጥ ያደርገናል። ስለዚህ በላፕ ቶፕ፣ የእጅ ስልክና ኮምፒዩተር ላይ በማፍጠጥ የምናጠፋውን ጊዜ መቀነስ አለብን፡፡

2ኛ. ዜናና ፊልም ማብዛት

ለምሳሌ እቤታችሁ ውስጥ ምግብ እያበሰላችሁ እያለ አንድ ሰው መጥቶ የምታበስሉት ምግብ ላይ የሆነ ቆሻሻ ቢጨምር ትጣሉታላችሁ፡፡ ዝም ብላችሁ አታልፉትም፡፡ ወይ ትሰድቡታላችሁ፤ ወይ ትደበድቡታላችሁ፤ አልያም ሰው ጠርታችሁም ቢሆን ታስደበድቡታላችሁ፡፡ ብቻ ዝም አትሉትም፡፡ ለምን? ወደ ሰውነታችሁ ውስጥ የሚገባ ምግብ ላይ ነው ቆሻሻ የጨመረው፡፡ ምግቡ ጤናማና ንፁህ መሆን አለበት፡፡ ስለዚህ ወደ ሰውነታችን ለሚገባው ነገር እንጨነቃለን ማለት ነው፡፡ ወደ አእምሯችን ለሚገባው ነገርስ ምን ያህል እንጨነቃለን? ዜና ወደ አእምሯችን ሲመጣ ምን ይዞ ነው የሚመጣው? ጥሩ ዜና ነው ወይ የምንሰማው፤ ጥሩ ዘገባ ነው ወ ይ የምናደምጠው?

በርግጠኝነት አምስት ዜና ብትሰሙ ከአምስቱ በጣም ጥሩ ዜና አንድ ወይ ሁለት ነው፡፡ እንትና አሸነፈ፤ እንትን ደግሞ ተመርቆ ተከፈተ የሚል ሊሆን ይችላል። ከዚህ ውጭ ግን አብዛኛው ዜና ወይ ሽብር ነው ወይ የሆነ ማስጠንቀቂያ አልያም ደግሞ አደጋ ነው። እንዲህ ሲባል ዜና አትስሙ ለማለት አይደለም። ነገር ግን በጣም ደጋግሞ አሰቃቂና አስከፊ ዜናዎችን ደጋግሞ መስማት አእምሮን በእጅጉ ይጎዳል። ቀላል ልማድ ይመስላል ግን ዜናው በሀገራችን ተስፋ እንድንቆርጥ ያደርጋል፡፡ ለምሳሌ በገጠር ያለ ሰው እንዲህ ያለ ዜና ሲሰማ ‹‹አዬ! በቃ ይህች ሀገር እንዲህ ሆና ቀረች፤ መጥፊዋ እየቀረበ ነው›› ይላል፡፡ ለመሥራት ያሰበውን ቢዝነስም ይተዋል፡፡ በውጭ ሀገር ያለውም ‹‹እንደው ሀገሬ ላይ ሰላም የለ፤ ምን ላደርግ ነው ሀገሬ የምገባው›› ይላል ያችን ዜና ሰምቶ፡፡ ኢንቨስት ሊያደርግ ያሰበውን ነገርም ይተዋል፡፡ አያቹህ! መጥፎ ዜናዎች ህልማችሁን ሁሉ ይነጥቃችኋል፡፡

ሌላው ቀላል ነገር ግን ደግሞ አእምሮን የሚጎዳው ነገር ፊልም ማየት ነው፡፡ በነገራችን ላይ ፊልም ማየት ካበዛን በጣም መጥፎ ነው፡፡ ለምን መሰላችሁ? አብዛኛዎቹ ፊልም ላይ የሚሰሩ ሰዎች ከእኛ በብዙ የተሻሉ ናቸው፤ ለፊልሙ ሲባል፡፡ ለዛም ነው እየደጋገምን የምናያቸው፡፡ እናም እነሱን ስናይ የበታችነት ስሜት ሊሰማን ይችላል፡፡ እንደውም በአሜሪካን ሀገር በአፍላ የወጣትነት እድሜ ላይ በሚገኙ ወጣቶች ላይ በተደረገ ጥናት 85 ከመቶ ያህሉ አሁን ያላቸውን ሰውነታቸውን እንደማይወዱት ተረጋግጧል፡፡ ሰውነታቸውን መቀየር ይፈልጋሉ። ወይ ቀዶ ሕክምና መሰራት፣ ቦርጭ ካላቸው ማስወገድ፣ ውፍረት ካላቸው መቀነስ፣ ብቻ የሆነ ነገር ማድረግ ይፈልጋሉ፡፡

ለምንድን ነው? ሲባል ለካ በመዝናኛው ኢንዱስትሪው ላይ በተለይ በፊልም፣ ሙዚቃ ክሊፖችና ሌሎችም የመዝናኛ ዘርፎች ላይ የሚያዩዋቸው ሰዎች በሙሉ በጣም ቀጭን፣ የተስተካከለ የሰውነት ቅርጽ ያላቸው በመሆኑ እነሱን ለመምሰል የሚደረግ ጥረት መሆኑ ነው። ያ ማለት በፊልምና በሙዚቃ ክሊፕ ውስጥ በሚያዩዋቸው ተዋንያን ምክንያት የራሳቸውን ሰውነት እንዲጠሉ ተደርጓል፡፡ ስለዚህ የበታችነት ስሜት ይሰማቸዋል፡፡ እኛም አንዳንድ ጊዜ የምናያቸው ነገሮች በራሳችን ላይ የሚፈጥሩት ተጽዕኖ አለ፡፡ አእምሯችን ላይ በጣም ከባድ ጉዳት አላቸው፡፡ ስለዚህ ዜና መስማት መቀነስ አለብን፡፡ ፊልም ማየት ማብዛት የለብንም፡፡ ማየት አለብን፤ ግን በልኩ መሆን አለበት፡፡

3ኛ. ብዙ ሥራ በአንዴ መሥራት

በአንድ ጊዜ ብዙ ሥራ ስለ ሠራን ጥሩ ነገር ያደረግን ሊመስለን ይችላል፡፡ ለምሳሌ እየበላን ይሆናል አልያም ደግሞ ሥራ እየሠራን ይሆናል፡፡ ዘፈን እንከፍታለን፡፡ ዜና ካለም እንከፍታለን፡፡ ምናልባት ተንቀሳቃሽ ስልካችን ላይ አጭር የጽሑፍ መልዕክት ከገባ እንመልሳለን፤ እንላላካለን፡፡ እያጠናንም ሊሆን ይችላል፡፡ ሥራም እየሠራን ሊሆን ይችላል፡፡ በአንድ ጊዜ የተለያዩ ሥራዎችን እንድንሰራ አድርጎናልና በዚህ ጊዜ አእምሯችን ጥምር ሥራዎችን ወደ መሥራት ውስጥ ይገባል፡፡

ስለዚህ የሆነ ጊዜ ደግሞ አንድ ሥራ ብቻ መሥራት ያለብን ሰዓት አለ፡፡ ለምሳሌ ጸሎት ማድረግ ሊኖርብን ይችላል፡፡ ያኔ አእምሯችን ስንት ቦታ ሊሆን ይችላል? ለምን? አልሰበሰብነውማ፤ ጎድተነዋል፡፡ ብዙ ሥራ እሠራነው፡፡ ስለዚህ አእምሯችን ትኩረት እንዳያጣ፤ ሃሳቡን መሰብሰብ እንዲችል በተቻለ አቅም አንድ ነገር ብቻ መሥራትን ማስለመድ አለብን፡፡ ብዙ ሥራ በአንዴ መሥራት አእምሯችንን ይጎዳዋል፡፡

4ኛ. ሁሌም ተመሳሳይ ሥራ መሥራት

አዲስ ነገር አለመሞከርና ሁሌም አንድ ዓይነት ሥራ መሥራት ቀላልና አእምሮን የሚጎዳ ሌላኛው ምክንያት ነው፡፡ ሕይወታችን የተለመደና ተመሳሳይ ነው። ጠዋት ወደ ሥራ ከሥራ ወደ ቤት እንመላለሳለን። ጋደም ብለን ቲቪ እናያለን። ቀኑ ያልፋል፤ ይመሻል፤ ይነጋልም። ቅዳሜና እሁድ ይመጣል፡፡ እቤት እናርፋለን፤ ወይስ ሥራ እንሠራለን። እሱም ያልፋል፡፡ አዲስ ነገር አንሞክርም፡፡ በዚህ ምክንያት አእምሯችን መሰልቸት ውስጥ ይገባል፡፡

ጎህ ቴክኖሎጂ / Goh Technology

11 Oct, 07:07


በማሰብ ብቻ ኮምፒውተርና ስልኮችን ማዘዝ የሚያስችለው ቺፕ

ቺፑ ሰውነታቸው የማይታዘዝላቸውና አይነ ስውራን ኮምፒውተር እና ስልክ በቀላሉ እንዲጠቀሙ ያግዛል ተብሏል

የአለማችን ቁጥር አንድ ቱጃር ኤለን መስክ ኩባንያ ኒውራሊንክ ገመድ አልባ ቺፕ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው ልጅ አዕምሮ ውስጥ መግጠሙን አስታወቀ።

ቺፑ የተገጠመለት የነርቭ ችግር ያለበት ግለሰብ ከህመሙ ማገገም መጀመሩንም ነው ኩባንያው የገለጸው።

ኒውራሊንክ ኩባንያ ያመረተው ገመድ አልባ ቺፕ ዋነኛ ተግባር የሰው ልጅ አዕምሮን ከኮምፒውተር ጋር ማገናኘት ነው።

ኩባንያው ቺፑን በሰው ልጅ አዕምሮ ላይ እንዲቀብር በአሜሪካ የምግብና መድሃኒት አስተዳደር ባለስልጣን በግንቦት ወር ፈቃድ ያገኘ ሲሆን፥ ሙከራው ሰውነታቸው ለማይታዘዛቸው(ፓራላይዝ) እና ዐይነ ስውራን ትልቅ ብስራት ነው ተብሏል።
የአካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎች ኮምፒውተር እና ተንቀሳቃሽ ስልካቸውን በቀላሉ እንዲጠቀሙ ይረዳል የተባለው ቺፕ፥ የአዕምሮን የእንቅስቃሴ ሃሳብ በ64 ከጸጉር የቀጠኑ ገመዶች እየተከታተለ ለኮምፒውተር በብሉቱዝ መረጃ ይልካል።

ቺፑ የተገጠመላቸው ሰዎች ሊያደርጉት ያሰቡትን ነገርም የሮቦት ቴክኖሎጂው ወዲያውኑ አንብቦ ለኮምፒውተሩ መረጃ ስለሚሰጥ በቅጽበት የፈቀዱት ይፈጸማል ተብሏል።

ኒውራሊንክ ለስድስት አመት የተመራመረበት ገመድ አልባ ቺፕ “ቴሌፓቲ” እንደሚሰኝ የቴክኖሎጂ ኩባንያው ባለቤት ኤለን መስክ በኤክስ (ትዊተር) ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

ቴሌፓቲ “ስልክም ሆነ ኮምፒውተራችን በአዕምሯችን በማሰብ ብቻ መቆጣጠር ያስችላል” ያሉት መስክ፥ የመጀመሪያዎቹ የቺፑ ተጠቃሚዎች እጃቸውን ያጡና ማዘዝ የማይችሉ ሰዎች ይሆናሉ ብለዋል።

መስክ ይህ ቴክኖሎጂ ለቀድሞው ብሪታንያዊ ተመራማሪ ስቴፈን ሃውኪንግ ቢደርስ ሊፈጥረው የሚችለውን ተዐምር መገመት አይከብድም ባይ ናቸው።

በሰው ልጅ አዕምሮ ውስጥ ቺፕ መግጠም በመጀመር የኤለን መስኩ ኒውራሊንክ የመጀምሪያው አይደለም።
የአሜሪካው ብላክሮክ ኒውሮቴክ በፈረንጆቹ 2004 ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ የሰው ልጅ አዕምሮን ከኮምፒውተር ጋር የሚያገናኝ መሳሪያ መግጠም የጀመረው።

በአሜሪካ የተደረጉ ሁለት ጥናቶች በአዕምሮ ውስጥ የሚቀበሩ ጥቃቅን ቺፖች መንቀሳቀስ ለማይችሉ (ፓራላይዝ) ሰዎች ተስፋ ሰጪ ውጤት ማሳየታቸውን አመላክተዋል ብሏል ቢቢሲ በዘገባው።

የስዊትዘርላንድ አጥኚዎችም ባለፈው አመት አዕምሮ ላይ በተሳካ ሁኔታ ኮምፒውተር መቅበራቸውን መግለጻቸው ይታወሳል።

በዚህም ሰውነቱ የማይታዘዝለት አንድ የኔዘርላንድስ ዜጋ ጭንቅላቱ ውስጥ በተቀበረለት ቴክኖሎጂ አማካይነት ስለመራመድ በማሰብ ብቻ መራመድ መቻሉ መነገሩ አይዘነጋም።
ምንጭ፦ALIAN አማርኛ
ቴሌግራም:-https://t.me/technology_in_amaharic
ዩቱብ፦ https://www.youtube.com/@goh-tube

ጎህ ቴክኖሎጂ / Goh Technology

11 Oct, 06:58


ማሽን ለርኒንግ ምንድን ነው?
ሰው ሠራሽ ልኅቀት (አርቴፍሻል ኢንተለጀንስ) በውስጡ ከያዛቸው ዘርፎች አንዱ ማሽን ለርኒንግ (Machine Learning) ነው።

“. . .ማሽን ለርኒንግ ስንል፣ ስማርት አልጎሪዝም በመጠቀም፣ የሚገባውን ዳታ በመጠቀም [ማሽን] ጥሩ ሥራ እንዲሠራ ማድረግ ነው” ሲሉ ዶ/ር ዳኛቸው ይገልጹታል።

ከማሽን ለርኒንግ ጋር ከሚገናኙ አልጎሪዝሞች አንዱና ዋነኛ ሆኖ የሚታወቀው ዲፕ ለርኒንግ (Deep Learning) ነው።

ባለሙያው ምሳሌ የሚሰጡት ምሥል፣ ተንቀሳቃሽ ምሥል እና ንግግርን ማብላላትን (Processing) ነው።

መጀመሪያ ማሽን ብዙ መረጃ (Data) ይገባበታል። ከዚያም ምሥሎችን ዐይቶ ምን እንደሆኑ እንዲያውቅ ይሠለጥናል ማለት ነው።

Image Recognition በመባል በሚታወቀው ሂደት ማሽን በሚሊዮኖች ከሚቆጠሩ ምሥሎች መካከል ‘ይሄ ቤት ነው፣ ያኛው ውሻ ነው፣ ይህኛው ኮምፒውተር ነው’ ብሎ ይለያል።

ይህን የሚያሳልጡ መተግበሪያዎች (Applications) አሉ።

ማሽኑ ቤት አይቶ ‘ውሻ ነው’ ካለ፣ መሳሳቱ ይነገረውና ቤት እንደሆነ ይገለጽለታል። በዚህ መንገድ በቀጣይ ስህተቱን ያርማል።

“. . .ግሬድየንት ዲሰንት አልጎሪዝም [Gradient Descent Algorithm] በሚባል መንገድ ነው ማሽንን ማሠልጠን የሚቻለው። እራሱን በእራሱም ያሠለጥናል። ሚሊዮን ጊዜ [መረጃ] ይገባል፣ ስሌት ይሠራል፣ ይሠለጥናል። ሠልጥኖ ሲጨርስ ብዙ ነገር ለይቶ ማወቅ ይቻላል።”

ምሥል፣ ተንቀሳቃሽ ምሥልና ንግግር ለይቶ የሚያውቀው ዲፕ ለርኒንግ እያደገና ውስጡ ያሉት ለመማር የሚያገለግሉ ፓራሜትሮች እያደጉ እንደመጡ ባለሙያው ያስረዳሉ።

በጊዜ ሂደት በሺዎች እና በሚሊዮኖች የሚቆጠረው ግብዓት አሁን በቢሊዮኖች ደርሷል።

ማሽን የሚመገበው መረጃ በጨመረ ቁጥር፣ ውስብስብነቱ ከፍ ባለም ቁጥር፣ የማሽኑ የመረዳት አቅምም ይጨምራል ማለት ነው።

“ብዙ ዳታ ገብቶ [ማሽን] ሲሠለጥን በጣም የተራቀቀ ውጤት ያለው ማሽን ይታያል። በዚህ መንገድ ሞዴሉ ብዙ ነገር ይረዳል። ይህም ዲፕ ለርኒንግ ነው።” ሲሉ ዶ/ር ዳኛቸው ያብራራሉ።

ፌስቡክ የተጠቃሚዎቹን የግል መረጃዎች አብላልቶ ስለ ተጠቃሚዎቹ ማንነትና ፍላጎት መረዳቱ በዚህ ሊካተት ይችላል።

ከአማዞን እቃ ሲገዛ ድርጅቱ ምርት የሚጠቁምበት ሂደትም በዚህ ዘርፍ ይጠቃለላል።

ጎህ ቴክኖሎጂ / Goh Technology

07 Oct, 06:25


በየቀኑ በስልካችን የምንጭነው ፎቶና ቪድዮ የት ነው የሚቀመጠው?
በቀን ስንት ጊዜ ስልክዎን ይመለከታሉ?


ዘንድሮ የተሠራ ጥናት አንድ ሰው በአማካይ 58 ጊዜ ስልኩን ይመለከታል ይላል። ከ58ቱ ጊዜ 30ው በሥራ ቦታ ነው የሚከናወነው።

ጥናቱ በ47 አገራት ነው የተሠራው። ሰዎች በየቀኑ በአማካይ ሦስት ሰዓት ከሩብ ስልካቸው ላይ እንደሚያጠፉ ይጠቁማል።

ስልካችን ላይ ከምናጠፋው ሰዓት አብላጫውን የሚይዙት ማኅበራዊ ሚዲያ መከታተል እንዲሁም ፎቶ እና ቪድዮ ማንሳት ናቸው።

ሌላ ጥናት እንደሚለው፣ በየሰከንዱ 45 ሺህ ፎቶዎች፣ በየሰዓቱ 196 ሚሊዮን ፎቶዎች፣ በየቀኑ ደግሞ 4.7 ቢሊዮን ፎቶዎች ይነሳሉ።

ይሄ ሁሉ ፎቶ የሚከማቸው በማይታየው፣ በማይዳሰሰው ክላውድ (cloud) ነው።

ክላውድ ፎቶ ብቻ ሳይሆን ማንኛውንም ስልካችን ላይ የምንመዘግበውን መረጃ ያከማችልናል።

በ1960ዎቹ እንደተፈጠረ የሚነገርለት ክላውድ፣ በዋናነት አገልግሎት የሚሰጡት አፕል (አይ ክላውድ)፣ አማዞን (አማዞን ዌብ) ድሮፕቦክስ እና ጉግል ናቸው።

ክላውድ የመረጃ ክምችትን በምን መንገድ ለወጠ? የሚሠራውስ እንዴት ነው? ስንል የሰው ሠራሽ አስተውሎት (አርቴፍሻል ኢንተለጀንስ ወይም ኤአይ) ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ዳኛቸው ብሩን ጠይቀናል። በኳንቲፊ የቴክኖሎጂ ተቋም የዓለም አቀፍ ጥናት እና ምርምር ዘርፍ መሪ ናቸው።

ክላውድ ምንድን ነው? ምንስ ይጠቅማል?
ዶ/ር ዳኛቸው እንደሚሉት፣ ክላውድ ከመፈጠሩ በፊት መሥሪያ ቤቶች በራሳቸው ማዕከላዊ የመረጃ ቋት (central server) ነበር መረጃ የሚያከማቹት። ይህ ማለት ሥራ የሚከናወነው፣ መረጃም የሚቀመጠው በመሥሪያ ቤት ኮምፒውተር ላይ ነው።

ግለሰቦችም መረጃ የሚያከማቹት በስልካቸው ወይም በላፕቶፓቸው ከፍ ሲልም ሀርድ ዲስክ ላይ ነበር።

እነዚህ ኤሌክትሮኒክሶች ይሞላሉ። ለመረጃ ምዝበራም ይጋለጣሉ።

እንደ አማዞን ያሉ ግዙፍ ተቋሞች ለሥራቸው የኮምፒውተር ስሌት (computation) ይፈልጋሉ።

ሰዎች በበይነ መረብ የሚያዙትን ምርት ለመከታተል፣ በቀጣይ ምን መግዛት እንዳለባቸው ለመጠቆምም ኮምፒውቴሽን ያስፈልጋቸዋል።

“. . .ብዙ ዳታ ሴንተር (የመረጃ ማዕከል) ዲስትሪብዩት አድርገው ማዘጋጀት ጀመሩ። ይሄንን የሚጠቀሙት ለበይነ መረብ ግብይት ነው። ከዚያ አዲስ የንግድ ሐሳብ አምጥተው [ሰርቨሩን] ለደንበኞቻቸው ማከራየት ጀመሩ” ሲሉ ባለሙያው ያስረዳሉ።

የክላውድ ሐሳብ ከዚህ በፊትም ቢኖርም አማዞን የበለጠ ታዋቂ አድርጎታል።

ግለሰቦችና ተቋማትም በcloud computing አማካይነት መጠነ ሰፊ መረጃ፣ ዘለግ ላለ ጊዜ ያስቀምጣሉ።

በክላውድ መረጃ የሚከማቸው ኢንተርኔት በመጠቀም ሲሆን፣ መረጃው ከየትኛውም ቦታ፣ በየትኛውም ዓይነት ኤሌክትሮኒክስ፣ በማንኛው ጊዜ ይገኛል።

ክላውድ፣ መረጃ እንዳይጠፋ ወይም መረጃው የተመዘገበበት ኤሌክትሮኒክስ ቢጠፋ እንኳን መረጃውን በሌላ ኤሌክትሮኒክስ ለማግኘት ይጠቅማል።

ለምሳሌ ስልክ ስንቀይር በቀድሞ ስልካችን የነበሩት ምሥሎች፣ ጽሑፎች፣ ቪድዮዎች፣ አጭር የጽሑፍ መልዕክት ልውውጦች፣ ስልክ ቁጥሮች እና ሌሎችም ጠቃሚ መረጃዎች ወደ አዲሱ ስልካችን ይሸጋገራሉ።

እንዲህ አይነቱን አገለግሎት በነጻ ከሚሰጡ መካከል ጉግል ድራይቭ፣ ድሮፕቦክስ እና ቦክስ ይገኙበታል። የሚያከማቹት መረጃ መጠን ከፍተኛ ነው። የመረጃ ምዝበራን ለመከላከል፣ መረጃ ደኅንነቱ ተጠብቆ ዘለግ ላለ ጊዜ እንዲቀመጥም ይረዳል።

“ክላውድ የሚባለው መረጃው ፊዚካሊ (በተጨባጭ) የት እንዳለ ስለማይታወቅ ነው። መረጃው የተቀመጠው ቴክሳስ ነው ወይስ ናይሮቢ ዳታ ሴንተር የሚለው አይታወቅም። መረጃው ብዙ ቦታ ይቀመጣል” ሲሉ ነው ዶ/ር ዳኛቸው የሚገልጹት።
ቪድዮ፣ ድምጽ፣ ሰነድ እና ሌላም መረጃ ክላውድ ላይ እንዲከማች እንደ ማይክሮሶፍት እና ጉግል ያሉ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋሞች ይመክራሉ።

ዶ/ር ዳኛቸው እንደሚሉት ከመረጃ ክምችት ባሻገር ለኮምፒውቲንግ ሲባልም ክላውድ ጥቅም ላይ ይውላል።

“. . .ኤአይ የኮምፒውቲንግ ፓወር ማግኘት ነው። ሞዴሎችን ለማስተዋወቅና ለማሠልጠን የሚያስፈልገው የኮምፒውቲንግ ሪሶርስ ብዙ ነው። ለዚህም [መረጃውን ለማብላላት] የሚያስፈልገው ሪሶርስ ክላውድ ላይ ስላለ፣ ተከራይቶ መጠቀም ይቻላል። ክላውድ ላይ ዳታውም ኮምፒውቲንግ ሪሶርሱም አለ። ክላውድ እንዲሁ የተበተነ ነገር አይደለም። ሴንተሮች (ማዕከሎች) አሉት። ኮምፒውት የሚደረገው፣ እነዚያ ማዕከላት ላይ በኢንተርኔት አማካይነት ነው።”

ተቋሞች የራሳቸው የክምችት ማዕከል ማቋቋም እና ማስተዳደር የሚጠይቃቸውን ወጪ ለመቆጠብ ሲሉ ክላውድ ይከራያሉ።

መረጃ የሚቀመጠው አንድ ቋት ወይም ማዕከል ውስጥ ብቻ አይደለም። ኢንተርኔት እስካለ ድረስ፣ በማንኛውም ሰዓት፣ ከአንድ በላይ በሆኑ ኤሌክትሮኒክሶች ጭምር ማግኘት ይቻላል።

የተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች እና የበይነ መረብ አገልግሎት ሰጪዎችም በተሻለ ፍጥነት እንዲሠሩ ክላውድ አስተዋጽኦ አድርጓል።

ዶ/ር ዳኛቸው እንደሚሉትም፣ እነ ዩቲዩብ እና ፌስቡክ የመጡት ክላውድ በመኖሩ ነው።

መረጃ ከተለያየ ቦታ እንዲገኝ ማስቻሉ የቴክኖሎጂ ፍጥነት እየጨመረ እንዲሄድ ማገዙን ባለሙያው ያክላሉ።
ቴሌግራም
https://t.me/technology_in_amaharic
ዩቱብ፦ https://www.youtube.com/@goh-tube

ጎህ ቴክኖሎጂ / Goh Technology

29 Sep, 08:47


https://youtu.be/9TY_tBcjrkI

ጎህ ቴክኖሎጂ / Goh Technology

20 Sep, 19:47


https://youtu.be/mQTUh87bbqE?si=OyR2pnLw_P02oZ9g

ጎህ ቴክኖሎጂ / Goh Technology

19 Sep, 06:39


ማህበራዊ ሚዲያ ምንድን ነው?
የማህበራዊ ሚዲያ መገለጫዎች?
የማህበራዊ ሚዲያ ተግዳሮት
የማህበራዊ ሚዲያ ጥቅሞች
ማህበራዊ ሚዲያን እንዴት እንጠቀም?
ስለ ማህበራዊ ሚዲያ ምን እናድርግ?
በጎህ ዩቱብ ይጠብቁን
👇🏼👇🏼👇🏼👇🏼
https://youtu.be/xRhEB6yuORI?si=0X6DGa2eRK86vQH9

ጎህ ቴክኖሎጂ / Goh Technology

16 Sep, 18:10


https://youtu.be/2r9ebe1f8TA?si=PyJX_k6uzo732BAG

ጎህ ቴክኖሎጂ / Goh Technology

05 Aug, 21:27


https://youtu.be/eCbe_y8TYmY?si=ia74OGD83dVz7mle

ጎህ ቴክኖሎጂ / Goh Technology

29 Jul, 13:51


#ማስታወቂያ

መንግስት በአጋር አካላት ድጋፍ የጀመረውን “5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮዴርስ” የተሰኘውን አዲስ የonline ስልጠና ስናሳውቃችሁ በደስታ ነው። ይህ አዲሱ የonline ስልጠና በከፍተኛ ጥራት ፣ በፕሮግራሚንግ ፣ በዳታ ሳይንስ ፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና በሌሎችም በሚታወቀው በUdacity መድረክ (platform) በኩል ከአይሲቲ ጋር የተገናኙ ኮርሶችን በነፃ የሚሰጥ ነው።

ተማሪዎች እና አስተማሪዎች ያለምንም ወጪ በእነዚህ ኮርሶች ለመመዝገብ ይህንን ልዩ እድል መጠቀም ይችላሉ፣ ይህንን ስልጠና በራስ ለመሰልጠን ከፈለጉ በUSD ከፍተኛ ውድ በሆነ ክፊያ የሚሰጥ በመሆኑ ይህንን ነፃ ዕድል ተጠቃሚ ይሁኑ።

በዚህ ፕሮግራም ውስጥ በመሳተፍ የትምህርት ማህበረሰባችን ችሎታቸውን በማጎልበት በአለም አቀፍ ገበያ ከፍተኛ ተወዳዳሪ መሆን ይችላል። የዚህ ስልጠና መጨረሻው ግቡ ስልጠና መስጠት ብቻ ሳይሆን በአለም አቀፍ ድርጅቶች እውቅና ያለው እና የስራ እድልን በእጅጉ ሊያሳድግ ከሚችለው Udacity የምስክር ወረቀት መስጠት ነው።

ስልጠናውን በማጠናቀቅ ተወዳዳሪ በዘርፉ አለም አቀፍ በICT ዘርፍ ተወዳዳሪ የሚያደረገውን ሰርቲፊኬት ባለቤት ለመሆን ከፈለጉ በጎፋ ዞን ሳይንስና ኢንፎርመሽን ተክኖሎጂ መምሪያ በመቅረብ መመዝገብ እንደሚችሉ እእንገልፃለን።

የስልጠናው ተሳታፊ መሆን የሚችሉት ከተለያዩ ከታወቁ የትምህርት ተቋማት በICT እና በICT ዘርፍ የተመረቁ አካላት ናቸው።

ምን መማር ይቻላል ?

- Android Kotlin Development Fundamentals
- Data Science Fundamentals
- Programming Fundamentals

ትምህርቱን እንዴት ማግኘት ይቻላል ?

ስልጠናዎቹ በዩዳሲቲ (Udacity) በተሰኘው ኦላይን የትምህርት ፕላትፎርም ተዘጋጅተው የቀረቡ ናቸው።

ሰልጣኞች ያለ አንዳች ክፍያ በነጻ ኮምፒውተራቸውን ወይም ስልካቸውን በመጠቀም መሰልጠን ይችላሉ።

ስልጠናዎቹ 6-7 የሚሆኑ ሳምንታትን የሚፈጁ ሲሆን በማጠቃለያው ላይ ሞያዊ ሰርተፊኬት ይሰጣል።

የስልጠናዎቹን ይዘት እንዲሁም ተጨማሪ መረጃዎች በተዘጋጀው ድረ-ገጽ ( https://ethiocoders.et/ ) ላይ መመልከት ይችላሉ።

ጎህ ቴክኖሎጂ / Goh Technology

27 Jul, 20:45


አዲስ ምዕራፍ
ከ43,500 በላይ የሥራ ዕድል ለዜጎች
በውስጥ አቅም ለምቶ ተግባራዊ በተደረገው የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት (E-LMIS) አማካይነት ከ43,500 በላይ በየትኛውም የሞያ መስክ የመጀመሪያ ዲግሪና ከዛ በላይ የትምህርት ዝግጅት ያላቸው ሥራ ፈላጊ ዜጎችን የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት በመላ ሀገሪቱ ለሚያካሄደው የግብርና ናሙና ቆጠራ ለአንድ ዓመት ቀጥሮ ለማሰራት የሚያስችል ስምምነት ከኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ጋር ተፈራርመናል።
በዚህ ስምምነት ሥራና ክህሎት ሚንስቴር በE-LMIS ስርዓት በአጠረ ጊዜ፣ በአነስተኛ ወጪ እና በዘመነ የሰው ሃይል ቅጥር ስርዓት ብቁ ሰራተኞችን ለኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት የሚያቀርብ ይሆናል።
በመሆኑም የዚህ ዕድል ተጠቃሚ መሆን የምትፈልጉ ዜጎች በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት (E-LMIS) ድህረ-ገጽ https://lmis.gov.et እንድትመዘግቡ እናሳስባለን።
የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌና የሥራ ባልደረቦቻቸው ለሀገራዊ መረጃ ጥራት በሰጡት ትኩረትና ሥራውን በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ለማከናወን እና በትብብር ለመስራት ላሳዩን ቁርጠኝነት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን ለቀርብላቸው እወዳለሁ፡፡
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!
https://t.me/technology_in_amaharic

ጎህ ቴክኖሎጂ / Goh Technology

27 Jul, 20:45


ለመመዝገብ ይህንን ቪዲኦ ይመልከቱ
https://youtu.be/C1KUtFncNlY
https://t.me/technology_in_amaharic

1,088

subscribers

52

photos

1

videos