EEN Truth!! @ethiopian_education_news1 Channel on Telegram

EEN Truth!!

@ethiopian_education_news1


እውነት የሀሰት ባህር ብትሰምጥ ትሟሟለች እንጂ አትጥፋም!!! ሰለዚህም ለመኖር ና ለመደሰት እውነተኛ ሁን ሁለ!

ውድ የ @Ethiopian_Education_News1 ቻናል ቤተሰቦች:-
•ያላቹን ሀሳብ,ጥቆማ እና አስተያየት ይላኩልን🙏
👉 @EENhelp
ይህ እዉነተኛ ላይ የተመሰረተና ሀቀኛ ቻናል ነው።

#ETHIOPIAN_EDUCATION_NEWS!!

EEN Truth!! (Amharic)

እውነት የሀሰት ባህር ብትሰምጥ ትሟሟለች እንጂ አትጥፋም፣ ለሁሉም አገልግሎት የተመሰረተና ሀቀኛ ቻናል የተሰማና የተወካዮ እውነተኛ የታወቀ በመሆን እንዴት እንደሚገኝ ለእኛ አገልግሎት ነው።nየ @Ethiopian_Education_News1 ቻናል ቤተሰቦች እና ያላቹን ሀሳብ, ጥቆማ እና አስተያየት የተመሰረተና ሀቀኛ ቻናል ላይ ነው። በቻናሉ ላይ በነጻ ለማሰብና ለማስተዋል፣ እኛ ለምንድን ነንና ምን እንደሚከተለው በማለፈ።nእኛ የተሰማና የተወካዮ እውነተኛ ቻናሎችን በዚህ ቻናሉ እያዘዋጀ ለመምረጥና ለመደረግ ስለእኛ ለማወቅ እና ለማስተካከል በዚህ ቻናል ያስቆጠረና የሚያሳጥሩን አገልግሎት ነው።nበቻናሉ ለመረዳት ተስፋዬ ላይ ለማስተካከል እንዲሰማና እንዲሰማ የሚችል እና በማክበር እንዲሁም ለመረጃና ለመመልከት ለምን ለዚህ የቻናል እውነት ቤተሰብ እንደሚከተለው በማለ።nተጨንቁን ከቻናሉ ሀሳቦች፣ አስተያየቶቻችን፣ የኢትዮጵያ ህብረትና የትምህርት ዜናዎቻችንን በማስገንቆ በቤተሰብዎ ማስተዋወቅ እና ማሰብና ቅምቅምና። #ETHIOPIAN_EDUCATION_NEWS!!

EEN Truth!!

18 May, 17:31


#EEN.
ምድብ ሶስት ✌️

ፈተናው የሚሰጥበት አድረሻ
          👉 https://c4.exam.et ነው።

በዚህ ምድብ ስር የሚገኙ የክልል/ከተማ አስተዳደሮች
            📍 ቤንሻንጉል ክልል
            📍 ሀረሪ ክልል
            📍 አፋር ክልል
             📍 ኦሮሚያ ክልል

በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በዚህ ምድብ የተመደቡ ከተሞች
📌Adama                       📌 Bale
📌 Ambo                        📌 Bishoftu
📌 Agaro                        📌 Borena
📌 Arsi East                   📌 Bule hora
📌 Arsi West                  📌 Buno Badele
📌  Asela                        📌 Dodola
📌 Batu                           📌 East Bale
📌 East Borena              📌 Holeta
📌 Guji                       📌 Horo Guduru
📌 Hararge East       📌 Hararge West                      

እንደሚታወቀው በዚህ ምድብ ወስጥ ያሉ የተመረጡ ተፈታኞች ብቻ በ Online የሚፈተኑ ይሆናል።

በዚህ ምድብ ስር የሚገኙትን በ Online የሚያስፈትኑ ት/ት ቤት ዝርዝር በቅርቡ በዚህ ቻናል👇👇
@Ethiopian_Education_News1
@Ethiopian_Education_News1

EEN Truth!!

18 May, 17:12


#EEN_NEWS.....

Manneen barumsaa qormaata xumura kutaa 12ffaa  kan bara 2016 toora interneetiin qoran ifoomeera.

Qormaanni biyyoolessaa kutaa 12ffaa bara barnootaa 2016 bifa waraqaa fi toora interneetiin akka kennamu ni beekama. Bu’uura kanaan barattoonni qormaata kana karaa interneetii fudhatan magaalota filatamoo kanneeniin qofatti kan fudhatan ta'a.

Haaluma kanaan, qoramtoonni qormaaticha fudhachuun dura  shaakala gahaa gochuun barbaachisaa waan ta'eef, guyyaa har'a Sanbata Caamsaa 10/2016 irraa eegalee naannoolee argamanitti waan ramadaniif shaakaluu ni danda'u jechuun ibsameera.

Qoramtoonni Maqaa Fayyadamaa(username) fi 'Password' manneen barnootaa isaanii irra fudhachuu ni danda'u.

Haaluma kanaan akkuma gara toora shaakala seenaniin jecha icciitii (Passwordii) dhuunfaa isaanii kan hin dagatamnee kan jijjiiran ta'uu ibsameera.

@Ethiopian_Education_News1

EEN Truth!!

18 May, 17:12


#EEN NEWS

#Update

የ2016 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) የበይነ መረብ (Online) ተፈታኞች መፈተኛ ይፋ ሆነ፡፡

የ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በወረቀትና በበይነ መረብ ይሰጣል።

በዚሁ መሠረት በበይነ መረብ ፈተናውን የሚወስዱ ተፈታኞች ከላይ በተገለጸው አድረሻ ብቻ የሚፈተኑ ይሆናል፡፡

ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ሁሉም ተፈታኞች በቂ ልምምድ ማድረጋቸው አስፈላጊ በመሆኑ ከዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በአድራሻው ተፈታኞች በሚገኙበት ክልል የተደለደሉ ስለሆነ ልምምድ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።

ተፈታኞች ልምምድ ለማድረግ ከዚህ በፊት ለክልል / ከተማ አስተዳደር ቀድሞ የተላከውን የይለፍ ቃልና ስም (User Name and Password) ከየትምህርት ቤቶቻቸው ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።

መጀመሪያ ወደ መፈተኛ ሲሰተሙ እንደገቡ የማይረሱትን የግላቸውን የይለፍ ቃል የሚቀይሩ ይሆናል፡፡

ተፈታኞች #ከተደለደሉበት_ክለስተር_ዉጪ ሲሰትሙን መጠቀም #የማይችሉ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

@Ethiopian_Education_News1

EEN Truth!!

07 Oct, 10:19


#EEN

ፈተናው ተሰርቋል!!!

የsocial subject ፈተናዎች እንደተሰረቁ በደረሰን መረጃ ማጣራት ችሌናል!!

በመንግሥት በኩል ምንም የተሰጠ መግለጫ የለም!!!
#Share
@Ethiopian_Education_News1
@Ethiopian_Education_News1
@Ethiopian_Education_News1

EEN Truth!!

01 Oct, 12:28


#EEN
ትምህርት ሚኒስቴር በሁለት ዙር የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል።

ፈተናው ከመስከረም 26 እስከ ጥቅምት 13/2015 ዓ.ም ቆይታ ይኖረዋል።

የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከመስከረም 26 እስከ ጥቅምት 04/2015 ዓ.ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ከጥቅምት 05/2015 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 14/2015 ዓ.ም ፈተናውን ይወስዳሉ።

#Share
@EENofficial @EENofficial
@EENofficial @EENofficial

EEN Truth!!

01 Oct, 12:12


#EEN
#ብሔራዊ_ፈተና

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከቀናት በኃላ መሰጠት ይጀምራል።

ፈተናው በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ ይታወቃል። ተማሪዎች መብታቸው ፣ ግዴታቸው፣ ወደ ዩኒቨርሲቲ ይዘው መሄድ የሚችሉት እና የተከለከሏቸው ነገሮችን ከላይ በምስሉ በዝርዝር ተቀምጧል።

በተጨማሪም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ እንደሚከተለው ቀርቧል።

➤ የመጀመሪያ ዙር (የሶሻል ሳይንስ) ፦

🗓 ከመስከረም 26 - 28 (ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ)

🗓 መስከረም 29 (ኦረንቴሽን ይሰጣል)

🗓 ከመስከረም 30 - ጥቅምት 2 (ፈተና ይሰጣል)

🗓 ከጥቅምት 3 - ጥቅምት 4 (ተፈታኞች ወደየአካባቢያቸው ይመለሳሉ)

➤ ሁለተኛ ዙር (የተፈጥሮ ሳይንስ) ፦

🗓 ከጥቅምት 5 - ጥቅምት 6 (ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ)

🗓 ጥቅምት 7 (ኦረንቴሽን ይሰጣል)

🗓 ከጥቅምት 8 - ጥቅምት 11 (ፈተና ይሰጣል)

🗓 ከጥቅምት 12 - ጥቅምት 13 (ተፈታኞች ወደየአከባቢያቸው ይመለሳሉ)

(ትምህርት ሚኒስቴር / የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት)

#Share
@EENofficial @EENofficial
@EENofficial @EENofficial

EEN Truth!!

28 Sep, 17:33


#EEN
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 30 ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይሰጣል።

የተፈታኝ ተማሪዎች መብቶች፦

➭ ከፈተና ጥያቄ ውጪ ማንኛውንም ያልተረዳውን ነገር ጠይቆ የመረዳት መብት አላቸው።

➭ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የምግብ፣ የህክምና አገልግሎት፣ የማደሪያ ክፍል፣ ፍራሽ እና ትራስ የማግኘት መብት አላቸው።

➭ ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ያለውን የቤተ መፅሐፍት፣ የመጸዳጃ ቤቶች፣ የሻወር፣ የካፍቴሪያዎች፣ የሚኒ ሱፐር ማርኬቶች፣ የተለያዩ ሱቆች እንዲሁም የመናፈሻና መዝናኛ አገልግሎቶችን የመጠቀም መብት አላቸው።

➭ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የጋራ የደህንነት ጥበቃ የማግኘት መብት አላቸው።

➭ በፈተና ሰዓት መፈተኛ ክፍል ገብቶ ብርሃናማ የመፈተኛ ቦታ፣ ወንበርና መፃፊያ ጠረጴዛ የማግኘት መብት አላቸው።

➭ ፈተና ከመጀመሩ አንድ ቀን ቀድሞ ስለፈተናው ገለጻ (ኦሬንቴሽን) የማግኘት መብት አላቸው።

የተፈታኝ ተማሪዎች ግዴታዎች፡-

➤ ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከልና መፈተኛ ክፍል አድሚሽን ካርድ ይዞ የመገኘት ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ የትምህርት ቤት ወይም የነዋሪነት መታወቂያ ይዞ መገኘት አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ግቢ ከመግባቱ በፊትና ወደ መፈተኛ ክፍል ከመግባቱ በፊት ሙሉ አካላዊ ፍተሻ የመፈተሽ ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢና በመፈተኛ ክፍል የተከለከሉ ዕቃዎችን መያዝ የለበትም።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ እርሳስ፣ ላጲስና የእርሳስ መቅረጫ ይዞ መገኘት አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብን የማክበር ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከል/በመፈተኛ ክፍል ውስጥ የፈተና አስፈጻሚዎች የፈተና አስተዳደር ሥራን ውጤታማ ለማድረግና ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የሚያደርጉትን ጥረት የመተባበር ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ፈተና ከመጀመሩ በፊት መፈተኛ ክፍል የመገኘት ግዴታ አለበት።

➤ ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ለፈታኙ የማሰረከብ ግዴታ አለበት።

➤ ማንኛውም ተፈታኝ ወደተመደበበት ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ጨርቅ ይዞ የመምጣት ግዴታ አለበት።

ለተፈታኝ ተማሪዎች የተፈቀዱ ነገሮች፦

➣ አዲስ ወይም ቀድሞ ለመማር እና ለማጥናት ሲጠቀሙበት የነበሩ ማስተወሻ ደብተር፣ የትምህርት መፅሐፍ፣ መንፈሳዊ/ኃይማኖታዊ መፅሐፍት፣ ባዶ ወረቀት

➣ ደረቅ ምግቦች (ጩኮ፣ በሶ፣ ዳቦ ቆሎ፣ ቆሎ….)

➣ ገንዘብ (ብር)

➣ የልብስ ወይም የእጅ ቦርሳ፣ የግል ልብስ፣ ጫማ

➣ የግል ንጽህና መጠበቂያዎች (ሳሙና፣ ሞዴስ፣ የጥርስ ብሩሽ፣ የጥርስ ሳሙና፣ ፎጣ፣ ሶፍት፣ ሻምፖ፣ ኮንዲሽነር፣ ሎሽን፣ ቻፕስቲክ፣ የጸጉር ቅባት፣ የፊት ቅባት)

ለተፈታኝ ተማሪዎች የተከለከሉ ነገሮች፦

➣ ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡

➣ ማንኛውንም ዓይነት ስለት እና ሹልነት ያላቸውን ብረታ ብረቶችና ጠንካራ ፕላስትኮች ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው።

➣ ማንኛውም ድምጽ የሚቀዳ፣ ፎቶ የሚያነሳ፣ ቪዲዮ የሚቀርጽ፣ ከቴሌ መስመርም ሆነ ከቴሌ መስመር ውጭ መልዕክት በዲጂታል መንገድ የሚሰጥ ወይም የሚቀበል የግል ዕቃ/መሳሪያ/የቴክኖሎጂ ውጤት፣ ስልክ፣ አይ-ፓድ፣ ታብሌት፣ ኮምፕዩተር፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ሰዓት፣ ማጂክ ብዕር/እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት/ጃኬት እና ሌሎች ማንኛቸውም ፎቶ፣ ምስል እና ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኖክስ መሣሪያዎችን በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥም ሆነ ግቢ ዙሪያ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

➣ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት የግል ፍላሽ ዲስክ፣ ሃርድ ዲስክ፣ ሲዲ፣ ሚሞሪ፣ ሚሞሪ ሪደር፣ ኦ-ቲጂ ኮንቨርተርና መሰል ዕቃዎችን ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

➣ ማንኛውም አደንዛዥ እጾች (ጫት፣ ሲጋራ፣ በሐኪም ማዘዣ የሌለው መድኃኒት)፣ ህክምና መስጫ መርፌ መያዝ ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

➣ ማንኛውም ዓይነት የአልኮል መጠጥ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

➣ ማንኛውም ዓይነት የአንገት ሐብል፣ የጸጉር ጌጥ፣ የጆሮ ጌጥ፣ የጣት ቀለበት፣ የእጅ አንባር፣ አድርጎ ወይም ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡ (ከልሙጥ የጋብቻ ቀለበት በስተቀር)

➣ ፈተና ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት እና ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል መውጣት የተከለከለ ነው፡፡

➣ ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ይዞ መውጣት ተከለከለ ነው፡፡

➣ በፈተና ሰዓት በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ማስቲካ መያዝም ሆነ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡

➣ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በግልም ሆነ በቡድን መጮህ ወይም በጣም ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው፡፡
Via MoE

#Share
@EENofficial @EENofficial
@EENofficial @EENofficial

EEN Truth!!

01 Sep, 14:28


#OEN
#Oromia_Education_News

Bara kana barsiisota kutaa 12 xumuranii leenjii barsiisummaa
waggaa sadii xumuran eebbisiisuullee kaasaniiru.
''Barsiisoonni ammaan booda akkuma eebbifamaniin hojii
barsiisutti kan bobba'an osoo hin taane qormaata gahumsa
ogummaatu isaaniif kennama. Qormaanni gahumsa ogummaa
kun mirkaneeffannoo qulqullinaaf yoo ta'u, nama qormaata
kana daruu danda'e qofatu hojiitti bobba'a,'' jedhan Dr.
Galaanaan.
Sirna barnootaa haaraa amma hojiirra ooluuf jedhu kana
keessatti gosoonni barnootaa jijjiiraman yoo jiraateef kan
gaafataman Itti-aanaan Biiroo Barnoota Oromiyaa kun, gosti
barnoota haaraan jalqabaman akka jiran dubbatu.

#Share
@EENofficial @EENofficial
@EENofficial @EENofficial

EEN Truth!!

01 Sep, 14:23


#AFAAN_OROMOO

For Afaan Oromo join ours channel

@EENofficial
@EENofficial

EEN Truth!!

01 Sep, 14:19


Channel photo updated

EEN Truth!!

31 Aug, 18:01


#EEN

የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የ8ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከዛሬ ጀምሮ በኢንተርኔት ላይ ማየት እንደሚቻል አስታወቀ።

ቢሮው የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት መውጣቱን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ በክልሉ 451 ሺሕ 21 ተማሪዎች ለፈተና የተመዘገቡ ሲሆን 98 ነጥብ 3 በመቶ የሚሆኑት ፈተና መውሰዳቸውን ገልጿል።

በዚህም የ9ኛ ክፍል የማለፊያ ውጤት ለወንዶች 50 በመቶ እና ለሴቶች 47 በመቶ ነው ብሏል።

በአርብቶ አደሩ አካባቢ የ9ኛ ክፍል ማለፊያ ውጤት በመቶኛ ለወንዶች 47% ለሴቶች 44% ሲሆን ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ደግሞ ለወንዶች 44% እና ለሴቶች 41% መሆኑም ተገልጿል።

ማለፊያው ውጤት በአገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ እና በትምህርት ጥራት ላይ ተመስርቶ መወሰኑን የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ግርማ ባይሳ ገልጸዋል::

ሴት ተማሪዎች የተሻለ የፈተና ውጤት በማምጣት ለውጥ አምጥተዋልም ነው ያሉት።

ተማሪዎች ውጤታቸውን በኢንተርኔት ላይ ‘https://oromia.ministry.et/#/home ላይ መመልከት ይችላሉም ነው የተባለው።

#Share
@Ethiopian_Education_News1
@Ethiopian_Education_News1
@Ethiopian_Education_News1

EEN Truth!!

02 May, 16:03


#BoranaUniversity

ቦረና ዩኒቨርሲቲ #የሁለተኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ግንቦት 02 እና 03/2014 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ተማሪዎች በተገለጹት ቀናት ምዝገባ እንዲያደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

የአንደኛ ዓመት አዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወንበት ጊዜ በቅርቡ እንደሚያሳውቅ ተቋሙ ገልጿል።

https://t.me/Ethiopian_Education_News1

@Ethiopian_Education_News1
Stay Safe!

For campus info join @Ethiopian_Education_News1

EEN Truth!!

02 May, 16:01


ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ አዲስ በከፈተው CMC ካምፖስ ምዝገባ ጀምሯል።

ለ2014 ዓ.ም ዕውቅና ያገኘባቸው የትምህርት መስኮች፦

- አካውንቲንግ እና ፋይናንስ
- ማኔጅመንት
- ማርኬቲንግ ማኔጅመንት
- ኮምፒውተር ሳይንስ

አድራሻ፦ ከሰሚት አደባባይ ወደ CMC ሚካኤል በሚወስደው ዋና መንገድ ላይ 500 ሜትር አለፍ ብሎ

ለበለጠ መረጃ፦

0116298163/54/55

#Unity_University
@Ethiopian_EDUCATION_News1

@Ethiopian_EDUCATION_News1

Stay Safe!

EEN Truth!!

29 Apr, 14:57


ሚያዝያ 21ቀን 2014 ዓ.ም

: ማስታወቂያ:

📚 በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለ2014 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ-ግብር ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት አዲስ
ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ ፡

📚 በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለ2014 የትምህርት ዘመን በመደበኛ የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት መርሃ-ግብር በትምህርት ሚ/ር መስፈርት መሠረት አዲስ የተመደባችሁ፤

📌 የተፈጥሮ ሳይንስ/Natural Science/ተማሪዎች በዘንዘልማ ካምፓስ

📌 የማህበራዊ ሳይንስ/Social Science/ተማሪዎች በይባብ ካምፓስ!

📌 የተፈጥሮ ሳይንስ በመምህርነት/Natural Science Teaching እና
📌 የማህበራዊ ሳይንስ በመምህርነት/Social Science Teaching/ተማሪዎች በሰላም ካምፓስ! #ከሚያዚያ 28 - 30 ቀን 2014 ዓ/ም ሪፖርት እንድታደርጉ ያሳውቃል።

📌 ለተጨማሪ መረጃ የዩኒቨርስቲውን ሬጅስትራር ድረ-ገጽ https://bdu.edu.et/registrar/ ማየት ይቻላል፡፡

ማሳሰቢያ
1ኛ ተማሪዎች ለምዝገባ ስትመጡ፣
📌ብርድ ልብስና አንሶላ፣
📌 የስፖርት ትጥቅ፤
📌 የአስራሁለተኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውንና ፎቶኮፒ፣
📌 አራት ጉርድ ፎቶግራፍ ይዛችሁ መምጣት እንዳለባችሁ ያስታውቃል።

2ኛ.በተለያየ ምክንያት ትምህርት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁና የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ ተማሪዎች አዲስ ከተመደቡ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በ2014 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ
ቅበላ ግንቦት 1 እና 2 ቀን 2014 ዓ.ም እንድታመለክቱ እናሳውቃለን፡፡

3ኛ ከተገለጸው ቀን በፊትም ሆነ በኋላ የሚመጡ ተማሪዎች ምንም ዓይነት ዩኒቨርስቲው የማያስተናግድ መሆኑን ያሳውቃል፡፡

https://t.me/Ethiopian_Education_News1
https://t.me/Ethiopian_Education_News1
https://t.me/Ethiopian_Education_News1

EEN Truth!!

21 Mar, 15:40


" ከ13, 862 ተፈታኞች 3,006 ተማሪዎች ብቻ ናቸው ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የመግቢያ ዉጤት ያስመዘገቡት " - የአዊ ብሔ/አሰ ትምህርት መምሪያ

በአማራ ክልል፤ የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ከ13 ሺ 862 ተፈታኞች 3 ሺህ 6 ተማሪዎች ብቻ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የመግቢያ ዉጤት ማስመዝገባቸዉን አሰታወቀ።

የመምሪያዉ ኃላፊ አቶ አለሙ ክህነት ፤ በ2013ዓ.ም በብሔረሰብ አስተዳደሩ በ29 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ 13 ሺህ 862 ተማሪዎች ሀገርአቀፋ ፈተና መፈተናቸውን ገልጸዋል።

ከነዚህም ዉስጥ በብሄረሰቡ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ 3 ሺህ 6 ተማሪዎች ብቻ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የመግቢያ ዉጤት ማምጣታቸውን ነዉ ሀላፊዉ የተናገሩት።

አጠቃላይ የማለፋ ምጣኔም 21.7% ብቻ መሆኑ ተገልጿል።

ከተፈተኑት የተፈጥሮ ሳይንስ 5 ሺህ 745 ተማሪዋች መካከል 1 ሺህ 943 የመግቢያ ዉጤት አምጥተዋል። በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ከተፈተኑት 8 ሺህ 117 ተማሪዎች ዉስጥ 1 ሺህ 63 ወደ የመግቢያ ዉጤት ያመጡ መሆናቸዉን ተገልጿል።

የእርማት ጥራት ችግር ማሳያ 140 ያመጣ ተማሪ እንደገና ሲፈተሸ 601 ፣ የሲቪክስ ት/ት ፈተና ችግር በሌለበት አካባቢ መሰረዝ እና የፈተና አስተዳደር ስርዓቱ በአግባቡ የተመሩ ባለመሆናቸዉ ለተመዘገበዉ ዝቅተኛ ዉጤት ተጠቃሽ ሞክንያቶች መሆኑን ትምህርት መምሪያው ገልጿል።

የፈተና ስርዓቱ ስለመታወኩ በተለያዩ ቴክኖሎጂዎች ቼክ ተደርጎ እንደገና መፈተሽ እንዳለበት ከሚመለከተው ጋር እየሰራ መሆኑን መምሪያው አሳውቋል።

እስከአሁንም መምሪያዉ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ጋር የፈተና ሂደቱ እንደገና እንዲታይ ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጾ ተማሪዎች እና የተማሪ ቤተሰቦች በትግስት እንዲጠብቁ አሳስቧል።

#Share
https://t.me/Ethiopian_Education_News1
https://t.me/Ethiopian_Education_News1
https://t.me/Ethiopian_Education_News1

EEN Truth!!

10 Mar, 13:25


#EEN

ከOBN ጋር ቆይታ የነበራቸው የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ቶላ ባሪሶ በ2013/14 በነበረው 12ክፍል ብሔራዊ ፈተና በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ከተፈተኑት 125,180 ተማሪዎች ውስጥ 15% ወይም 19,000 ገደማ የሚጠጋ ተማሪ ብቻ ከ50% በላይ ማስመዝገብ ችሏል ብለዋል።



ከOBN ጋር ቆይታ የነበራቸው የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ቶላ ባሪሶ በ2013/14
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የወሰዱ አጠቃላይ እንደ ኦሮሚያ ክልል 234,433 ተማሪዎች ናቸው።

Natural Science ተማሪዎች
ወንድ ---75,468
ሴት-----52,990
ድምር-----128,458 ተማሪዎች

Social Science ተማሪዎች
ወንድ ---68,243
ሴት-----56,895
ድምር-----125,188 ተማሪዎች

በዘንድሮ አመት የ 12ኛ ክፍል ፈተና የተፈጥሮ ሳይንስ ከ #600 ፣ የማህበራዊ ሳይንስ ከ #500 መያዙንም ገልፀዋል(ለመጀመሪያው ዙር ተፈታኞች)

ከፍተኛ ውጤት ያመጡት በተፈጥሮ ሳይንስ #224 ተማሪዎች ሲሆኑ በማህበራዊ ሳይንስ #3 ተማሪዎች ብቻ ናቸው።

ከ ግማሽ በላይ ያመጡ ተማሪዎች ብዛት
🪧በተፈጥሮ ሳይንስ ከ 300 በላይ----91,933(71.5%) ተማሪዎች

🪧በማህበራዊ ሳይንስ ከ 250 በላይ----19,199(15.3%) ተማሪዎች😳

#Share
https://t.me/Ethiopian_Education_News1
https://t.me/Ethiopian_Education_News1

EEN Truth!!

08 Nov, 13:21


kd 30

1D 2A 3C 4 5B 6C 7D 8B 9D 10B 11C 12A 13B 14A 15D 16C 17D 18B 19B 20A 21B 22D 23A 24C 25A 26D 27B 28D 29B 30 31 32 33D 34D 35A 36B 37C 38B 39C 40C 41D 42B 43D 44A 45B 46A 47C 48B 49A 50A 51A 52! ,53C 54B 55B 56B 57C 58B 59A 60C 61A 62B 63D 64C 65D

.... check it first