Ethiopian Embassy in Djibouti @ethiopiaindjibouti Channel on Telegram

Ethiopian Embassy in Djibouti

@ethiopiaindjibouti


Official Telegram Channel for Ethiopian Embassy to Djibouti

Ethiopian Embassy in Djibouti (English)

Are you interested in staying up to date with the latest news, events, and information from the Ethiopian Embassy in Djibouti? Look no further than our official Telegram channel, @ethiopiaindjibouti! As the primary channel for communication between the Embassy and the public, we are dedicated to providing you with timely updates on diplomatic relations, cultural exchanges, and community outreach programs. Who are we? The Ethiopian Embassy in Djibouti serves as the official representation of the Ethiopian government in Djibouti. Our mission is to strengthen the ties between Ethiopia and Djibouti, promote bilateral cooperation, and provide support and assistance to Ethiopian citizens living in Djibouti. What do we do? Through our Telegram channel, we aim to keep you informed about important announcements, events, and initiatives taking place at the Embassy. Whether you are a member of the Ethiopian diaspora in Djibouti, a local resident interested in Ethiopian culture, or a diplomat seeking to engage with our Embassy, this channel is the go-to source for all things related to Ethiopia in Djibouti. Join us on @ethiopiaindjibouti to connect with us, ask questions, and engage in meaningful discussions about the bilateral relations between Ethiopia and Djibouti. Stay informed, stay connected, and be a part of our community! We look forward to sharing our journey with you on this platform. Don't miss out on this opportunity to be a part of the Ethiopian Embassy in Djibouti's official Telegram channel.

Ethiopian Embassy in Djibouti

30 Jan, 18:59


የጅቡቲው ፒፕልስ ሪለይ ፎር ፕሮግረስ (አር ፒ ፒ) ፓርቲ ዋና ጸሀፊ ኢልያስ ሙሳ ዳዋሌህ አዲስ አበባ ገቡ

ዋና ጸሀፊው ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ ከጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

በጉባዔው ከ15 ሀገራት የተውጣጡ የጎረቤት ሀገራት እህት ፓርቲዎች እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች 43 ከፍተኛ አመራሮች እንደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡

Ethiopian Embassy in Djibouti

29 Jan, 08:21


ማስታወቂያ

ታላቁ የረመዳን ጾምን ምክንያት በማድረግ በጅቡቲ የሚገኙ ሬስቶራንቶች/ምግብ ቤቶች ቀን ላይ አገልግሎት አንደማይሰጡ ይታወቃል። ሆኖም በኢትዮ-ጅቡቲ ኮርደር እና አሮጌው ወደብ አካባቢ የሚገኙ የኢትዮጵያ ምግብ ቤቶች በልዩ ሁኔታ ለሾፌሮቻችን፣ ለትራንዚተሮች እና ከወደብ አገልግሎት የተያያዙ ሥራዎች ላይ የተሰማሩ ዜጎቻችን አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ፈቃድ ይጠየቃል። ይህም የወጪ እና ገቢ ምርቶቻችን ሳይስተጓጎሉ ወደ ታለመላቸው መዳረሻዎች እንዲደርሱ ለማድረግ ታልሞ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።

በመሆኑም ይህንኑ ፈቃድ ለመጠየቅ በትንሹ የአንድ ወር ጊዜ ስለሚያስፈልግ በፒኬ 12፣ ፒኬ 13፣ ከመሀል ከተማ ደግሞ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ማህበርን ጨምሮ በአሮጌው ወደብ አካባቢ የምትገኙ የኢትዮጵያ ሬስቶራንት ባለቤቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 7 የስራ ቀናት እስከ ፌብሩዋሪ 6 ቀን 2025 ድረስ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና ፓስፖርት ለሚሲዮኑ የቆንስላ ክፍል ታቀረቡ ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን።

Ethiopian Embassy in Djibouti

25 Jan, 17:06


ውድ የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ደንበኞች፣

የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማህበር ከየካቲት 2017 ጀምሮ በኦንላይን ቦታ በማስያዝ የህዝብ መንገደኞች ትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚጀምር ስንገልጽላችሁ በደስታ ነው።

ጥራት ያለዉና እና ቀልጣፋ የጉዞ አገልግሎት ለመስጠት ሲባል እንዲሁም ትክክለኛ የመንገደኛ መረጃን ለማረጋገጥ እና ከችግር የጸዳ ጉዞን ለማመቻቸት አስፈላጊ በመሆኑ ለሁሉም የሀገር ውስጥ ተሳፋሪዎቻችን ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) በመጠቀም ኦንላይን ቦታ ለመያዝም ሆነ ለመጓዝ መስፈርት መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን።

Dear valued passengers,

We are delighted to inform you that the Ethio Djibouti Railway (EDR) Share Company will be commencing public passenger transport services via train on our online booking platform starting in February 2025.

As part of our commitment to providing a seamless and efficient travel experience, we would like to remind all local passengers that a National ID ( Fayida) is a mandatory requirement for both online booking and travel. This is essential for ensuring accurate passenger information and facilitating a hassle-free journey.

የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር

Ethiopian Embassy in Djibouti

25 Jan, 09:54


በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ማህበር የማህበሩን ሒሳብ የሚያስተዳድርልኝ ልምድ ያለው የሒሳብ ባለሙያ መቅጠር እፈልጋለሁ ብሏል።

ልምድና ፍላጎቱ ያላችሁ መስፈርቱን የምታሟሉ ከታች ያለውን ማስታወቂያ መሰረት በማድረግ እንድትመዘገቡ ይሁን።

መልካም ቀን ይሁንላችሁ!

Ethiopian Embassy in Djibouti

24 Jan, 12:13


ምክትል የሚሲዮን መሪ ከነዳጅ ጫኝ አሽከርካሪዎች ጋር ውይይት አደረጉ፤

(ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም) ምክትል የሚሲዮን መሪ ክቡር ከበደ አበራ ከነዳጅ ጫኝ አሽከርካሪዎች ጋር በኢትዮ-ጂቡቲ ኮሪደር የነዳጅ ጭነት እና ማጓጓዝ ስራ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች ለመቅረፍ ያለመ ውይይት አካሂደዋል።

ውይይቱ በቅርቡ በኤምባሲያችን ከነዳጅ አከፋፋይ ድርጅቶች ጋር በነበረው መድረክ ላይ የተነሱ ችግሮችን በይበልጥ ለመፈተሽ ከነዳጅ ጫኝ አሽከርካሪዎች ጋር ውይይት እንዲደረግ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት ነው።

በመድረኩም አሽከርካሪዎች በኮሪደሩ ስለሚያጋጥማቸው የአገልግሎት ችግሮች፣ በጅቡቲ የሚኖራቸው ረዘም ያለ የፓርኪንግ ቆይታ እና በነዳጅ ጭነት ደህንነት ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

በተያያዘም በነዳጅ ጭነት ተርሚናል ውስጥ ያሉ የአሰራር ክፍተቶች፣ በየጊዜው የሚስተዋሉ የነዳጅ ቅሸባዎች፣ የአሽከርካሪዎች እና የተሽከርካሪ የደህንነት ጥያቄዎች ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል።

ምክትል የሚሲዮኑ መሪም በንግግራቸው የኢትዮጵያ ከባድ ጭነት አሽከርካሪዎች በተለይም ድንበር ተሻጋሪ ከባድ ጭነት አሽከርካሪዎች አጠቃላይ የሀገራችንን የገቢ-ወጪ ንግድን በማሳለጥ ረገድ ለልማትና ለኢኮኖሚያዊ እድገት እያበረከቱ ያሉት አስተዋጽኦ እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ አንስተዋል።

አክለውም በኢትዮጵያ ያሉ የዘርፉ ተቋማትን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የአሽከርካሪውን ደህንነት በመጠበቅ የነዳጅ ምርቱ በተገቢው ጊዜ እና ሁኔታ ወደ ሀገርቤት እንዲገባ በቅንጅት መስራት እንደሚገባቸው ጠቁመዋል። በአሽከርካሪዎች ዘንድ ለተነሱ ጥያቄዎች በየደረጃው በማወያየት ችግሮቸ‍ችን ለመፍታት እንደሚሰራም ከስምምነት ተደርሷል።

በስብሰባው ላይ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር የጅቡቲ ቅ/ጽ/ቤት፣ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት፣ የነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች ተወካዮች፣ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር የሥራ ኃላፊዎች እና በርካታ ቁጥር ያላቸው አሽከርካሪዎች ተሳትፈዋል።

Ethiopian Embassy in Djibouti

24 Jan, 12:12


ምክትል የሚሲዮን መሪ ከነዳጅ ጫኝ አሽከርካሪዎች ጋር ያደረጉት ውይይት

Ethiopian Embassy in Djibouti

22 Jan, 11:04


ክቡር አምባሳደር ከነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች ተወካዮች እና ከከባድ መኪና አሽከርካሪ ማህበራት ተወካዮች ጋር ውይይት አደረጉ፤

ክቡር አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ በጂቡቲ የኢትዮጵያ ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክ ሚንስቴር ፅ/ቤት ተወካይ፣ ከኢትዮጵያ የነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ተወካይ፣ የነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች ተወካዮች እና የከባድ መኪና አሽከርካሪ ማህበራት ተወካዮች ጋር በነዳጅ ዝውውር ሂደት ዙሪያ በኤምባሲው ተገናኝተው ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

በመድረኩም ኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ በመመደብ ከውጪ ከምታስገባቸው ስትራቴጂያዊ ምርቶች መካከል ነዳጅ ቀዳሚውን ድርሻ የሚይዝ እንደመሆኑ መጠን በመንግስት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ችግሮችን ለመፍታት እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህ ረገድ በውይይቱ ከተሳታፊዎች በኩል በጂቡቲ ስለሚያጋጥማቸው የፓርኪንግ ቆይታ፣ የነዳጅ ማሽን ብልሽት፣ የመንገድ ግንባታ ሂደት፣ የነዳጅ ጭነት ቁጥጥር፣ የተሸከርካሪዎች ኮታ ስምሪት እና ካሊብሬሽን ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች እንዳሉ ተነስተዋል።

ክቡር አምባሳደር በበኩላቸው እነዚህ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮች ለመፍታት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር የቅንጅታዊ አሰራር እንደሚያስፈልግ፣ የአሽከርካሪዎች ሴፍቲ እና የፓርኪንግ ቆይታ ላይ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት በተጨባጭ ጥናት የታገዘ አካሄድ ማድረግ እንደሚገባ፣ የነዳጅ ሌብነት እና ሙስናን ለመታገል ይህን መሰል የጋራ ውይይት መድረክ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

አክለውም የመንገድ ግንባታ እና የነዳጅ ተርሚናል አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ ከጂቡቲ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በመጨረሻም በዘርፉ ከነዳጅ ግዥ እስከ ስርጭት የሚታዩ በርካታ ክፍተቶች እና ማነቆዎችን ለመፍታት ሁሉም ባለድርሻ ተቀራርቦ በመነጋገር መስራት እንደሚገባ ተገልጿል።

Ethiopian Embassy in Djibouti

22 Jan, 09:33


ክቡር አምባሳደር ከጅቡቲ ወደቦች እና ነፃ ዞኖች ባለስልጣን ሊቀመንበር ጋር ተወያየ፤

(ጥር 14/2017 ዓ.ም) ክቡር አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ ከጅቡቲ ወደቦች እና ነፃ ዞኖች ባለስልጣን (DPFZA) ሊቀመንበር ሚስተር አቡበከር ኦማር ሃዲ ጋር በወደብ አገልግሎት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

በውይይታቸው እ.ኤ.አ በ2024 የስራ ዘመን በጂቡቲ SGTD ወደብ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ TEU ኮንቴይነሮችን በማስተናገድ ረገድ ውጤታማ አገልግሎት በመስጠቱ የተቋሙ ማኔጅመንት በማመስገን፣ በተያዘው አዲሱ የ2025 የበጀት ዓመት ከጂቡቲ ወደቦች ወደ ኢትዮጵያ ለሚኖረው ከፍተኛ የአፈር ማዳበሪያ ጭነት ዝውውር ይኸው የአገልግሎት ቅልጥፍና መስጠት እንደሚያስፈልግ ተወያይተዋል።

በተጨማሪም የጅቡቲ-ዲኪል -ጋላፊ ዋና መንገድ ግንባታ ያለበት ደረጃ፣ የጣና-ነሽ ጀልባ ወደ አገር ቤት የመጓጓዝ ሂደት እንዲሁም ለረጅም ጊዜ የቆዩ ጭነትዎችን ወደ ኢትዮጵያ በፍጥነትና በብቃት የማጓጓዝ ሂደት እንዲሻሻል መክረዋል ።

Ethiopian Embassy in Djibouti

20 Jan, 06:35


ጥር 12 ቀን 2017 ዓ. ም

ፓስፖርታችሁ እንዲታደስ የሰጣችሁና ስማችሁ ሊስቱ ውስጥ የተጠቀሰ አመልካቾች ፓስፖርታችሁ ታድሶ ስለመጣ ዘወትር በስራ ሰዓት የቀድሞውን/ የመጠቀሚያ ጊዜው ያለፈበትን ፓስፖርት ይዛችሁ በመምጣት ፓስፖርታችሁን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029Va9Yrbs1t90b6eH0Bv06

Ethiopian Embassy in Djibouti

18 Jan, 12:38


የ2017/18 ምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ የማጓጓዝ ሂደት እስከ ዛሬ ጥር 09 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ ባለው መረጃ፤

በ6 መርከቦች 313ሺ 260 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ደርሷል፤ (3ቱ መርከቦች ዩሪያ እና 3ቱ መርከቦች ዳፕ)

ወደብ ከደረሰው ማዳበሪያ ውስጥ

🔹️ 236ሺ 832.2 ሜትሪክ ቶን ወደ ሀገር ውስጥ ገብቷል፤

🔹️ ጅቡቲ ወደብ ላይ 76ሺ 427.8 ሜትሪክ ቶን አፈር ማዳበሪያ አለ፤

🔹️ወደብ የደረሰው የአፈር ማዳበሪያ ተሽከርካሪዎችንና ባቡርን በመጠቀም በፍጥነት ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባ እየተደረገ ሲሆን፣ 27ሺ 930 ሜትሪክ ቶን በባቡር እንዲሁም 178ሺ 314 ሜትሪክ ቶን በከባድ ተሽከርካሪዎች ከ150 በላይ ወደሆኑ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች ተጓጉዟል፤

🚢 56ሺ ሜትሪክ ቶን ዳፕ የአፈር ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ጅብቲ ደርሳ ወደብ ለመግባት በመጠባበቅ ላይ ስትሆን 60 ሺ ሜትሪክ ቶን የጫነችዋ ደግሞ በቀጣዩ ሳምንት ጅቡቲ ትደርሳለች ተብሎ ይጠበቃል።

WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029Va9Yrbs1t90b6eH0Bv06

Ethiopian Embassy in Djibouti

08 Jan, 06:26


የታደሰ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ማህበር መታወቂያ እና 2 ጉርድ ፎቶግራፍ ብቻ ይዞ በመቅረብ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዶላር እና የጅቡቲ ፍራንክ የቁጠባ ሂሳብ መክፈት እንደሚችሉ ያውቃሉ?

Ethiopian Embassy in Djibouti

06 Jan, 14:58


እንኳን ለ2017 ዓ.ም የገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም የገና በዓል

Baga Ayyaana Qillee kan bara 2017 tiif nagaan ittiin isin gahe.
Ayyaana Gaarii

Ethiopian Embassy in Djibouti

06 Jan, 10:49


ኤምባሲያችን በጅቡቲ እንዲሁም በመላው ዓለም ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ እንኳን ለ2017 ዓ.ም የገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን ይገልፃል!🎄🎄🎄

መልካም የገና በዓል🇪🇹

Merry Christmas

Ethiopian Embassy in Djibouti

05 Jan, 14:06


የፓስፖርት ዕድሳት አገልግሎት ለማግኘት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች

1. በእጅዎ ያለውን ወይንም መጠቀሚያ ጊዜው ያለፈበትን ፓስፖርት ዋናውንና አንድ ቅጅ ማቅረብ፣

2. ከ6 ወር ወዲህ የተነሱትን ሶስት ባለ 3X4 cm ፎቶግራፍ፣

3. የአገልግሎት ከፍያ 200 USD (ሁለት መቶ የአሜሪካን ዶላር) ክፍያ በመፈፀም አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ።

WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029Va9Yrbs1t90b6eH0Bv06

Ethiopian Embassy in Djibouti

05 Jan, 12:45


ውድ ዜጎቻችን

ሁላችሁም እንደምታውቁት ፓስፖርት ታትሞ የሚመጣው አዲስ አበባ ከሚገኘው የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ነው። እስካሁን ባለን መረጃ አዲስ ፓስፖርት ማውጣትን በተመለከተ የተለየ ነገር የለም። በኤምባሲያችን በኩልም ለጊዜው እየተሰጠ የሚገኘው የፓስፖርት እድሳት አገልግሎት ብቻ ነው።

በመሆኑም የአዲስ ፓስፖርት አገልግሎት መስጠት እስኪጀመር ድረስ በትዕግስት እንድትጠባበቁ እየገለፅን አገልግሎቱ እንደተጀመረ በዚሁ የቴሌግራም ገፃችን ላይ እንዲሁም በሌሎች የሚሲዮኑ ማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ላይ የምናሳውቅ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

መልካም ቀን ይሁንላችሁ!

Ethiopian Embassy in Djibouti

05 Jan, 07:19


ታህሳስ 27 ቀን 2017 ዓ. ም

ፓስፖርታችሁ እንዲታደስ የሰጣችሁና ስማችሁ ሊስቱ ውስጥ የተጠቀሰ አመልካቾች ፓስፖርታችሁ ታድሶ ስለመጣ ዘወትር በስራ ሰዓት የቀድሞውን/ የመጠቀሚያ ጊዜው ያለፈበትን ፓስፖርት ይዛችሁ በመምጣት ፓስፖርታችሁን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029Va9Yrbs1t90b6eH0Bv06

Ethiopian Embassy in Djibouti

04 Jan, 13:51


'ገበታ ለትውልድ' በጅግጅጋ

በክቡር ጠቅላይ ሚንስትራችን ዶክተር ዐብይ አህመድ ተነሳሽነት የተጀመረው ገበታ ለሀገር ዘላቂ ልማትን በማስተዋወቅ የሀገሪቱን የበለፀጉ ባህላዊ፣ ተፈጥሮአዊ እና ታሪካዊ ቅርሶችን በማሳየት የኢትዮጵያን የቱሪዝም ዘርፍ እና ኢኮኖሚ በከፍተኛ ሁኔታ እየለወጠ ነው።

የሸበሌ ፕሮጀክት በሶማሌ ክልል ከሚገኙት መስህቦች ውስጥ አንዱ ሲሆን አካባቢውን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ፣ ስነ-ምህዳሩን በጠበቀ መልኩ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ፣ ለዜጎች የስራ ዕድሎችን ለመፍጠር፣ ማህበረሰቦችን የማብቃት እና በአጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገትን ለማምጣት ያለመ በመሆኑ ይበል የሚያሰኝ ነው።

Ethiopian Embassy in Djibouti

02 Jan, 05:10


የኮሚዩኒቲ የ2025 አዲስ ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት ተደረገ

(ታህሳስ 24/2017) የኮሚዩኒቲ የ2025 አዲስ ዓመት ዕቅድ ምክትል የሚሲዮን መሪ ክቡር ከበደ አበራ ፣ የኮሚዩኒቲው አመራር እና ሠራተኞች በተገኙበት ላይ ውይይት ተካሄዷል።

የ2025 አዲስ ዓመት ዕቅድ በማቅረብ ኮሚዩኒቲው በዚህ ዓመት ትኩረት ማድረግ ያለበት ጉዳዮች ላይ በዝርዝር የተወያዩ ሲሆን፣ ይህን ንድፍ ለማሳካት የማህበሩን አቅም መገንባት ላይ ያለመ የሠራተኞች ማኑዋል እና መመሪያ ስልጠና ተሰጥቷል።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች በተነሱ ሀሳቦች ላይ ምላሽ በመስጠት ተጠናቋል።

Ethiopian Embassy in Djibouti

31 Dec, 12:33


የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ በጂቡቲ ከኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ተወካዮች ጋር ተወያዩ፤

የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ክቡር ዶ/ር ጌድዮን ጢሞትዮስ በጂቡቲ ከኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ተወካዮች ጋር በተለያዩ ርዕሰ-ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

የኮሚዩኒቲ ተወካዮች በጂቡቲ ሊገነባ ስለታቀደው የኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት ድጋፍ፣ ስለ ዜጎች መብት፣ ስለ ሀገራዊ ጥሪዎች እና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ አንስተዋል።

ሚንስትሩ በበኩላቸው ኮሚዩኒቲው እስከአሁን ለሀገራዊ ጥሪዎች ሲያደርጉ ለነበረው ንቁ ተሳትፎ በማመስገን፣ ይህ በጎ ተግባር እንዲቀጥል አበረታተዋል።

አክለውም የትምህርት ቤት ግንባታውን ለመደገፍ ከተዋቀረው ዐብይ ኮሚቴ ጋር እንደሚሰሩ እና በጂቡቲ ያሉ ዜጎች ጥያቄዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመገናኘት እንደሚወያዩ ገልጸዋል።

Ethiopian Embassy in Djibouti

31 Dec, 09:32


የጂቡቲ ቅርንጫፍ የአማራ ልማት ማህበር በቅርቡ ያካሄደውን አስቸኳይ ጉባኤ መነሻ በማድረግ በዕለቱ ከተመረጡት የማህበሩ አዳዲስ አመራሮች ጋር በቀጣይ ሊሰሩ ስለሚገባቸው የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ በሰፊው ተወያይተናል።

የልማት ማህበሩ የህዝብን ማህበራዊ ችግር ከመቅረፍ እና ሀገራዊ የልማት ጥሪዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ ከማድረግ አንጻር አደረጃጀቱን ማጠናከር እንደሚገባው እና ለዚህም ስራ ኤምባሲያችን ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተወያይተናል።

https://x.com/BerhanuTsegaye/status/1874023278416711942?t=MXm9wWpby1RQdvcfme0iTA&s=19

Ethiopian Embassy in Djibouti

01 Dec, 12:07


የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ተጨማሪ ፎቶዎች

Ethiopian Embassy in Djibouti

01 Dec, 12:06


የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አባላትና ደጋፊዎች በተገኙበት በጅቡቲ ተከበረ

የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓል “የሐሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሐሳብ በጅቡቲ የሚኖሩ አባላትና ደጋፊዎች በተገኙበት ተከብሯል።

በመርሐ-ግብሩ ላይ በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የፓርቲው የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምክትል ዘርፍ ኃላፊ ተስፋሁን ጎበዛይ እንዳሉት÷ ብልጽግና ባለፉት አምስት ዓመታት በብዙ ተግዳሮቶች መካከል በጽናት በመሥራት ተከታታይ ድሎችን ማስመዝገቡን ገልጸዋል፡፡

“የህልም ጉልበት ለዕምርታዊ ዕድገት” በሚል የመወያያ ሠነድ በመድረኩ የቀረበ ሲሆን፥ በወቅቱም ያጋጠሙት ተግዳሮቶች፣ ያስመዘገባቸው ድሎች፣ አሁን ያሉ ተስፋዎችን ጨምሮ የወደፊት ራዕዩች ላይ ውይይት ተደርጓል።

ባለፉት አምስት ዓመታትም በግብርና፣ አረንጓዴ ዐሻራ፣ ሌማት ትሩፋት፣ ፕሮጀክት ግንባታ፣ የተቋማት ሪፎርም፣ በቱሪዝም ማስፋፊያ፣ በኢንዱስትሪ ግንባታ እና ሌሎች በርካታ የልማት ሥራዎች መከናወናቸው በመድረኩ ላይ ተብራርቷል፡፡

የሰላም ጥሪ መሠረታዊ የፓርቲው አቋም መሆኑን ገልጸው፥ ሕዝባዊ መድረኮችና ውይይቶች በየደረጃው በማዘጋጀት ብሔራዊ መግግባትን በማምጣት ረገድ በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የወል ትርክቶችን ገዢ በማድረግና ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር አብሮ በመሥራት የአንድነት ተምሳሌት በመሆን የተጀመሩ ተግባራት ይበል የሚያሰኙ መሆናቸውን ተገልጿል፡፡

በመቀጠል የፓርቲው 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን አስመልክቶ በፓርቲው ስም የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር በኤምባሲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ተከናውኗል።

እርስ በእርስ ያለ ወዳጅነትን ለማጠናከር የወዳጅነት እግር ኳስ ግጥሚ ተካሂዷል።

በመጨረሻም የእራት ግብዣ እና የዋንጫ ስነ-ስርዓት ተከናውኗል።

Ethiopian Embassy in Djibouti

01 Dec, 12:05


የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አባላትና ደጋፊዎች በተገኙበት በጅቡቲ ተከበረ

Ethiopian Embassy in Djibouti

25 Nov, 10:19


ሕብር ቀለም፣ ሕብር ቋንቋ፣ ሕብር ባህል፣ ሕብር እምነት፣ ሕብር መልክ እና ሕብር ህዝብ ባለቤት ታላቋ ኢትዮጵያ: የሰው ልጆች መገኛ!

Ethiopian Embassy in Djibouti

24 Nov, 13:38


የጋብቻ የምስክር ወረቀት

ቅድመ ሁኔታ

በጅቡቲ ነዋሪ የሆኑና መኖሪያ ፈቃድ ያላቸው:

💍 ተጋቢዎች ከጋብቻው ጊዜ 1 ወር ቀደም ብሎ ማመልከት ይኖርባቸዋል

💍 ማመልከቻውን ተከትሎ የጋብቻ ማመልከቻውን በተመለከተ ለ15 ቀናት የሚቆይ ማስታወቂያ በሚሲዮኑ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ይወጣል

💍 ጋብቻውን ተቃውሞ የሚቀርብ ካለ በማስረጃ ተደግፎ በአካል መቅረብ ይኖርበታል

💍 በቀረበው ተቃውሞ ላይ በአምስት ቀናት ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል

💍 በተጋቢዎች ግራና ቀኝ ሁለት ሁለት የሰው ምስክር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ደጋፊ ማስረጃዎች

💍 ተጋቢዎች ማንነታቸውን የሚገልጽ ጊዜው ያላለፈ ፓስፖርት

💍 ተጋቢዎች ጋብቻ የሌላቸው ወይም የተፋቱ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ

💍 የተጋቢ ምስክሮች ጊዜው ያላለፈ ፓስፖርት

💍 ከስድስት ወር ወዲህ የተነሱት 3X4 የሆነ ተመሳሳይ ሁለት ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ ማቅረብ

💍 በባህላዊ ስርዓት የተፈፀመ ጋብቻ ከሆነ የተጋቢዎች ምስክሮች ወይም በስርዓቱ ላይ የታደሙ ሰዎችን ማቅረብ

💍 የተጋቢዎች የልደት የምስክር ወረቀት ማቅረብ ያስፈልጋል

መረጃዎቻችንን ለሌሎች ሼር በማድረግ ይተባበሩን

Ethiopian Embassy in Djibouti

22 Nov, 14:26


የማህበራዊ ሚዲያዎቻችን በመከተል ቤተሰብ እንዲሆኑ በአክብሮት ተጋብዛችኋል። ብዙዎችን መድረስ እንድንችል ገጾቻችንን ላይክ በማድረግ በማጋራትና ሌሎችን በመጋበዝ ይተባበሩን።

Telegram:
https://t.me/EthiopiaInDjibouti

WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029Va9Yrbs1t90b6eH0Bv06

TikTok
https://www.tiktok.com/@ethioindjibouti?_t=8rbl46v8n5k&_r=1

Website:
https://www.djibouti.mfa.gov.et/

Facebook: https://www.facebook.com/EthiopiaInDjibouti

Twitter:
https://twitter.com/EthioInDjibouti

YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCtCmkpKBg8HMEc_T38BBzxA

LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/ethioindjibouti

Instagram: https://www.instagram.com/ethioindjibouti/

Ethiopian Embassy in Djibouti

21 Nov, 11:23


ዛሬ ኤምባሲያችን ጂቡቲ ከሚገኘው የዓለም አቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት(IOM) ጋር በመተባበር 104 መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞችን በሁለት ዙር ከነጋድ ባቡር ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ አድርጓል።

ህገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ላይ በተጀመረው ክትትል ስራ በየቀኑ በርካታ ዜጎቻችን የህግ ከለላ እንዲያገኙ በማድረግ ከእንግልት እና ከሞት መታደግ ተችሏል። ይህ ተግባር በሚቀጥሉት ጊዜያት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል!

Ethiopian Embassy in Djibouti

21 Nov, 11:11


Ethiopian Embassy in Djibouti pinned «https://t.me/BerhanuTsegayeAbera የሚሲዮናችንን መሪ የክቡር አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ።»

Ethiopian Embassy in Djibouti

21 Nov, 06:14


ህገ-ወጥ የድንበር ተሻጋሪ ንግድ ድህነትን የሚያስፋፋ የኢኮኖሚ ነቀርሳ ነው! የሀገር ግብርን በመቀነስ፣ ህጋዊ የንግድ ስርዓትን የሚቀጭጭ እና ፍትሃዊ የገበያ ውድድርን የሚያጠብ በመሆኑ የአገራችንን የመሰረተ ልማት፣ የጤና፣ የትምህርት እና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች አቅምን ያዳክማል። በመሆኑም በህገ-ወጥ መንገድ የድንበር ንግድ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ለማስቆም ጊዜው አሁን ነው። #ህገወጥንግድይቁም

Illegal cross-border trade is a silent threat to economic growth and poverty alleviation. It siphons off the revenue that could contribute to our nation's development by evading taxes, undercutting legitimate businesses, and hindering fair competition. It weakens our economy and vital resources needed to invest in infrastructure, healthcare, education, and other social services. It's time to #stop the challenges posed by illegal cross-border trade. #StopIllegalTrade

Ethiopian Embassy in Djibouti

20 Nov, 12:16


ሠላም ጤና ይስጥልን፣

ከዚህ ቀደም ከኖቬምበር 12 ቀን 2024 ዓ.ም. ጀምሮ የራፍ ዘመቻ በጅቡቲ የፀጥታ አካላት እንደሚደረግ በመጠቆም፣ ዜጎቻችን ጥንቃቄ እንድታደርጉ ማሳሰባችን ይታወሳል። ሆኖም በአንዳንድ አካባቢዎች ዜጎቻችን ያለሥራ በአውራ መንገዶች ዳር የመቀመጥ እና በቡድን ከተማ ውስጥ የመንቀሳቀስ ሁኔታ አሁንም በስፋት ይታያል።

በመሆኑም ሚሲዮናችን የጅቡቲ መንግሥት የጀመረው የራፍ ዘመቻ አለመጠናቀቁን እየጠቆመ፣ በሥራ ያላችሁ በስራ ሰዓት በሥራችሁ ላይ እንድትሆኑ፣ ስራ የሌላችሁ ደግሞ በቤታችሁ እንድትሆኑ በድጋሚ እያሳሰብን፣ በጉዳዩ ላይ ከጅቡቲ መንግስት ጋር ውይይት በማድረግ መፍትሔ እስኪበጅለት ድረስ ጥንቃቄው ማድረጉ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ በድጋሚ ለማሳሰብ እንወዳለን።

Ethiopian Embassy in Djibouti

20 Nov, 11:57


ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ. ም

ፓስፖርታችሁ እንዲታደስ የሰጣችሁና ስማችሁ ሊስቱ ውስጥ የተጠቀሰ አመልካቾች ፓስፖርታችሁ ታድሶ ስለመጣ ዘወትር በስራ ሰዓት የቀድሞውን/ የመጠቀሚያ ጊዜው ያለፈበትን ፓስፖርት ይዛችሁ በመምጣት ፓስፖርታችሁን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

መረጃውን ሼር በማድረግ መልዕክቱን ለሁሉም በማድረስ ይተባበሩን

WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029Va9Yrbs1t90b6eH0Bv06

Ethiopian Embassy in Djibouti

20 Nov, 10:16


ኤምባሲው ከከባድ ጭነት አሽከርካሪዎች ማህበራት ጋር ውይይት አደረገ

ኤምባሲው ከከባድ ጭነት አሽከርካሪዎች ማህበራት ጋር ከጂቡቲ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ በሚደረገው አጠቃላይ የገቢ-ወጪ ምርት ዝውውር ላይ መሻሻል ባለባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርጓል።

የመንገድ ችግር፣ የአገልግሎት አሰጣጥ እና የኮንቴነር መጠን መጨመር በማህበራቱ በኩል ከተነሱት ችግሮች መካከል ናቸው።

ኤምባሲውም በባለፈውም ዓመት እንደ ሀገር በተመዘገበው የማዳበሪያ ኦፕሬሽን በድል መጠናቀቅ በትራንስፖርት ዘርፉ ውስጥ የከባድ ጭነት አሽከርካሪዎች ማህበራት ሚና ከፍተኛ መሆኑን በማመስገን በዘንድሮ 2017/18 በተጀመረው የአፈር ማዳበሪያ ኦፕሬሽን ላይ ይህን አኩሪ ተግባር እንዲያስቀጥሉ አበረታቷል።

በዚህ መድረክ የተነሱ ጉዳዮች በቀጣይ ኤምባሲው በጂቡቲ ከሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት የሚደረግ መሆኑ ተገልጿል።

ኤምባሲው ከከባድ ጭነት አሽከርካሪዎች ማህበራት ጋር በወር አንድ ጊዜ መደበኛ የውይይት መድረክ በመፍጠር ተቀራርቦ መስራት የሚቻልበት እና በስራ ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮች ላይ መረጃ በመለዋወጥ መከታተል እንዲቻል ሀሳብ አቅርቧል።

በመጨረሻም የከባድ ጭነት አሽከርካሪዎች የሀገር ኃላፊነት ይዘው በከባድ ሁኔታ እየሰሩ መሆኑን በማንሳት፣ በዘንድሮ ዓመት በተያዘው የአፈር ማዳበሪያ እና አጠቃላይ ገቢ-ወጪ ዝውውር ላይ ይህ ትጋት ማጠናከር እንደሚገባ በአደራ ጭምር አስተላልፏል።

Ethiopian Embassy in Djibouti

18 Nov, 16:09


Hariiroon ltiyoophiyaafi Jibuutii

Hariiroon ltiyoophiyaafì Jibuutii Afrikaa keessatti fakkeenyummaa qaba jedhan,Jibuutiitti
Ambaasaddarri ltiyoophiyaa Ambaasaaddar Birhaanuu Tsaggaayeen.

Misoomawwan bu'uuraan biyyoota walitti hidhuuf hojii hojjetamuufis agarsiiftuudha jedhame.

#OBN

Ethiopian Embassy in Djibouti

18 Nov, 11:25


ዛሬ በጅቡቲ የአልጄሪያ አምባሳደር ከሆኑት አምባሳደር መሀመድ ናስር (ዶ/ር) ጋር ተገናኝተን ተወያይተናል። ኢትዮጵያ እና አልጄሪያ የረዥም ጊዜ ግንኙነት ያላቸው ሀገሮች እንደመሆናቸው መጠን በሁለትዮሽ የንግድ፣ ቢዝነስ እና ቀጣናዊ የትብብር እድሎች ላይ ውይይት አድርገናል።

Ethiopian Embassy in Djibouti

18 Nov, 09:26


ጉዳዩ ለሚመለከታችሁ ውድ ዜጎቻችን በሙሉ

ማንኛውም ዜጋ በአገሩም ሆነ ከአገር ውጪ ሲኖር የሚኖርበትን አገር ህግ እና ደንብ አክብሮ መኖርና መስራት እንደሚጠቅበት ይታወቃል። ይሁን እንጂ አንዳንድ በንግድ ዘርፍ የተሰማሩ በጅቡቲ የምትኖሩ ዜጎቻችን በተለይም ደግሞ በኢትዮ- ጅቡቲ ኮርደር መስመር ላይ የምትገኙ የምግብ ቤት/የሬስቶራንት ባለቤቶች በጅቡቲ መንግሥት የሚጠበቅባችሁን ግብር በወቅቱ ያለመክፈል፣ ተቆጣጣሪዎች ሲመጡ የመዝጋት አልፎ አልፎም አድማ የማድረግ ሁኔታ እንዳለ ተስተውሏል።

በዚህ ምክንያት ፒኬ 12 እና 13 አካባቢ የሚገኙ ምግብ ቤቶች በተቆጣጣሪዎች እንዲሁም በዜጎቻችን አድማ ሰሞኑን ተዘግተው እንደነበሩ ከሕበረተሰቡ ጥቆማ የደረሰን ሲሆን፣ ኤምባሲው ጉዳዩን በመከታተል በልበላ አካባቢ ከሚገኘው የጅቡቲ ገቢዎች ቢሮ (Hotel des Impot) የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት በማድረግና በመደራደር፣ ባለቤቶቹ እንዲከፍሉ ከሚጠበቅባቸው 40% የግብር ቅጣት 30% ተቀንሶላቸው 10% መቀጮ እና የንግድ ፈቃድ እድሳት ክፍያ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚከፍሉ ከስምምነት በመደረሱ ምግብ ቤቶቹ እንዲከፈቱ ተደርገዋል። ኤምባሲያችንም በተደረሰው ስምምነት መሠረት ከላይ በተጠቀሰው አካባቢ የሚገኙ የምግብ ቤት ባለቤቶች የሚጠበቅባቸውን ክፍያ ስለመክፈላቸውም ክትትል እያደረገ ይገኛል።

ከግብር አከፋፈል ጋር ተያይዞ በዜጎቻችን በኩል ያለውን ብዥታ ለማስተካከል እንዲቻል ሚሲዮኑ የምግብ ቤት ባለቤቶች መክፈል የሚጠበቅባቸውን አጠቃላይ ክፍያ ከዚህ በታች ተመላክቷል።

1. ንግድ ፈቃድ(Patente) ለማሳደስ በየዓመቱ የሚጠበቀው ክፍያ= 91,560.00 DJF (ዘጠና አንድ ሺህ አምስት መቶ ስልሳ የጅቡቲ ፍራንክ)

2. አንድ የምግብ ቤት/የሬስቶራንት ባለቤት በአማካይ በወር 80,000.00 DJF (ሰማንያ ሺህ የጅቡቲ ፍራንክ) የተጣራ ገቢ/ደመወዝ ያገኛል በሚል እሳቤ ከገቢው/ደመወዙ በየወሩ የሚከፈል ግብር (IMPOT SUR LES TRAITEMENTS ET SALAIRES) = 7,400.00 DJF (ሰባት ሺህ አራት መቶ የጅቡቲ ፍራንክ) መክፈል እንደሚጠበቅበት፣ ይህም ክፍያ በየወሩ ለገቢዎች ቢሮ መከፈል እንዳሚገባ ለዜጎቻችን መረጃዎችን እንድንሰጥ ተጠይቀናል። በየወሩ በሬስቶራንት ባለቤቶች የሚከፈለው የገቢ ግብር ክፍያ የሬስቶራንት ባለቤቶች ቀጥሯቸው ለሚያሰሯቸው ሠራተኞች ስም የሚከፍሉትን ክፍያ ያስቀራል።

3. በአጠቃላይ አንድ የምግብ ቤት/ሬስቶራንት ባለንብረት ለንግድ ፈቃድ እድሳት መክፈል ከሚጠበቅበት 91,560.00 የጅቡቲ ፍራንክ በተጨማሪ 7,400.00 የጅቡቲ ፍራንክ የገቢ ግብር በወሩ በየአካባቢው በሚገኙ የገቢዎች ቢሮ መሄድ መክፈል ይጠበቅበታል። የሚጠበቅባችሁን ግብር በተቀመጠው የግዜ ሠሌዳ ወይም ገደብ አለመክፈል ደግሞ 40% ተጨምሮ ቅጣት እንድትከፍሉ ሊያስገድድ ይችላል።

በመሆኑም በጅቡቲ የምግብ ቤት/ሬስቶራንት ባለቤት የሆናችሁ በተለይም ደግሞ የአገራችን ወጪ እና ገቢ ምርቶች መተላለፊያ መስመሮች አካባቢ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን በጅቡቲ መንግሥት የሚጠበቅባችሁን የሥራ ግብር በወቅቱ እንድትከፍሉ እና የአገሩን ህግ አክብራችሁ እንድትሰሩ እያሳሰብን፣ የተለየ ችግር ሲያጋጥማችሁ ወደ አድማ ከማምራት እና ቤቶቻችሁን ከመዝጋት ይልቅ ጉዳዩን ለኤምባሲው እንድታሳውቁ እንጠይቃለን።

Ethiopian Embassy in Djibouti

16 Nov, 08:52


በጅቡቲ ቅርንጫፍ የአማራ ልማት ማህበር ጠቅላላ ጉባዔ ለማድረግ ተወያየ፤

በጅቡቲ ቅርንጫፍ የአማራ ልማት ማህበር የሚሲዮናችን ምክትል መሪ ክቡር ከበደ አበራ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣የቀድሞ አመራሮች እና የማህበሩ አባላት በተገኙበት ጠቅላላ ጉባዔ ለማድረግ ውይይት አደረገ።

በውይይቱም በቀጣይ ማህበሩን ለማጠናከር የትኩረት አቅጣጫዎች መሆን ያለባቸው ጉዳዮች ላይ በዝርዝር የተወያዩ ሲሆን፣ ጠቅላላ ጉባኤውን በተመለከተ ለቅድመ-ዝግጅት ስራዎች የጉባዔውን ዐብይ እና ንዑሳን ኮሚቴዎች ሰይመዋል።

ማህበሩ ለጉባኤው ዝግጅት ባቀረበው ዕቅድ ዙሪያ በመወያየት ሁሉም አባላት ለዕቅዱ መሳካት የጋራ ጥረት ማድረግ እንደሚገባው እና አፈፃፀሙም በየሳምንቱ እንደሚገመገም አቅጣጫ ተሰጥቷል።

በመጨረሻም ማህበሩ በጂቡቲ ነዋሪ የሆኑ የክልሉ ተወላጆች አባል እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል ።

Ethiopian Embassy in Djibouti

15 Nov, 09:25


ዛሬ ኤምባሲያችን ከሚያስተባብረው የጂቡቲ የአፈር ማዳበረ‍ያ ኦፕሬሽን ኮሚቴ ጋር በመሆን የ2017/18 አዲስ ዓመት የአፈር ማዳበሪያ ኦፕሬሽን በይፋ አስጀምረናል።

47,250 ሜትሪክ ቶን የዩሪያ አፈር ማዳበሪያ ጭና ጂቡቲ ወደብ የደረሰችውን አባይ II መርከባችን ላይ ተገኝተን የስራ ሂደቱን ጎብኝተናል።

የዘንድሮው የአፈር ማዳበሪያ ዝውውር ከዓምናው ጋር ሲነጻጸር መጠኑ ጭማሪ ያለው በመሆኑ ኢትዮጵያ ያሉ የዘርፉ ተቋማት እና ኮሚቴው በመቀናጀት የሀገርን ኃላፊነት በትጋት እንዲወጣ መክረናል።

Ethiopian Embassy in Djibouti

14 Nov, 13:01


ኤምባሲያችን ጂቡቲ ከሚገኘው የዓለም አቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት(IOM) ጋር በመተባበር በሁለት ዙር 135 መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞችን በአውሮፕላን እና በባቡር ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ አድርጓል።

ይህ ተግባር በሚቀጥሉት ቀናትም ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። ዜጎቻችንን ከህገ-ወጥ ዝውውር መጠበቅ የሁሉም ኃላፊነት ነው!

Ethiopian Embassy in Djibouti

10 Nov, 06:54


https://t.me/BerhanuTsegayeAbera

የሚሲዮናችንን መሪ የክቡር አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ።

Ethiopian Embassy in Djibouti

05 Nov, 16:13


"ስለድህነት ያለንን ስር የሰደደ አመለካከት መፈተሽ ያስፈልጋል። ሳናውቅ ለዓመታት አብሮን የቆየ እና ወደ ኃላ እያስቀረን ያለውን የግል አመለካከታችንን በመጋፈጥ ለለውጥ መዘጋጀት ያስፈልጋል። ኑሮ ካሉ መቃብር አይሞቅም!"

ክቡር ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ አሊ

Ethiopian Embassy in Djibouti

04 Nov, 17:34


የኤምባሲያችን ልዑክ በኦቦክ ውይይት አደረገ፤

የኤምባሲያችን ዲፕሎማቶችን እና ወታደራዊ አታሼዎችን የያዘ ልዑክ ከጅቡቲ ኦቦክ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙሳ አደን ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገዋል።

ስብሰባው ቀዳሚ ትኩረቱ ህገ-ወጥ ስደትን መከላከል እና በየመን መስመር የሚጓዙ መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞችን ለመቀነስ ያለመ ነው።

በውይይቱም ሁለቱ አገራት ህገ-ወጥ ስደትን ለመከላከል የተቀናጀ አካሄድ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። እንዲሁም የድንበር ቁጥጥር መሻሻል አስፈላጊነት ላይ በጋራ ለመስራት መክረዋል።

ከውይይቱ በተጨማሪ የኤምባሲው ልዑክ ለህገ-ወጥ ስደት ቁልፍ ተብለው የተለዩ ቦታዎችን ጎብኝቷል። ይህም በስፍራው ላይ የተደረገው ግምገማ ልዑኩ በስራ ሂደት በሚያጋጥመው እክል የሁኔታዎችን ተለዋዋጭነት እና የህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች መረብ በደንብ እንዲረዳ አስችሎታል።

Ethiopian Embassy in Djibouti

04 Nov, 15:17


ዛሬ በኤምባሲያችን በቅርቡ በተካሄደው የኮሚዩኒቲ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከተመራጡ ከአዲስ የስራ አስፈጻሚ እና የኦዲት ኮሚቴ ጋር በቀጣይ በሚሰሩ ስራዎች ዙሪያ ውይይት አድርገናል።

በውይይታችንም ከነባር አመራሮች ጋር የመወያየት፣ ማህበሩን ዕቅድ የመምራት፣ በየጊዜው የስራ ሂደትን በንዑስ ኮሚቴ መከታተል፣ መተዳደሪያ ደንቡን ማሻሻል እና ነባር ሰነዶችን ለአዲስ ተመራጮች ማስረከብ እንደሚገባ አቅጣጫ ሰጥተናል።

Ethiopian Embassy in Djibouti

03 Nov, 19:12


ከጂቡቲ የቱሪዝም እና የሚዲያ ባለሙያዎች ጋር ውይይት ተደረገ
****

በጂቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በቅርቡ በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገው ከተመለሱ የጂቡቲ የቱሪዝም እና የሚዲያ ባለሙያዎች ጋር መክረዋል።

ኤምባሲያች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በትብብር አዘጋጅቶት በነበረው የ"ፋሚሊያራይዜሽን" ጉብኝት ባለሙያዎቹ አንድነት፣ እንጦጦ እና ወዳጅነት ፓርኮችን እንዲሁም የወንጪ ዳንዲ ኢኮ ቱሪዝም መንደርን ጨምሮ የቱሪስት መዳረሻዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

ከጉብኝቱ መልስ ባለሙያዎቹ በኢትዮጵያ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን በተመለከተ በጂቡቲ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በፈረንይኛ እና በሶሚልኛ ቋንቋዎች የተለያዩ ፕሮግራሞችን ማቅረባቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም በጋዜጦች እና በማህበራዊ ድረ-ገጾች የኢትዮጵያን የቱሪስት መዳረሻዎች አስተዋውቀዋል።

ክቡር አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ከባለሙያዎቹ ጋር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያን በማስተዋወቅ ላከናወኑት መልካም ስራ አመስግነዋቸዋል።

በተጨማሪም ሁለቱ ወገኖች በቀጣይ ተመሳሳይ የኢትዮጵያ ልዑክ ጂቡቲን በሚጎበኝበት እና ሁለቱ አገራት በቱሪዝም ዘርፍ የጋራ ፓኬጆችን በማዘጋጀት በትብብር በሚሰሩበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029Va9Yrbs1t90b6eH0Bv06

Telegram: https://t.me/BerhanuTsegayeAbera

Ethiopian Embassy in Djibouti

03 Nov, 08:46


ትላንት በአምባሲው ቅጥር ግቢ የተካሄደው በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ጠቅላላ ጉባኤው ተጨማሪ ፎቶዎች

Ethiopian Embassy in Djibouti

03 Nov, 08:44


ትላንት በአምባሲው ቅጥር ግቢ የተካሄደው በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ጠቅላላ ጉባኤው ተጨማሪ ፎቶዎች

Ethiopian Embassy in Djibouti

01 Nov, 07:21


በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት አስተባባሪነት ከአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከመጡ ወጣት የበጎ አድራጎት ልዑክ ጋር ጥሩ ጊዜ አሳልፈናል። ልዑኩ በጂቡቲ ቆይታው የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ የሚጠናከርበት እና በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ያለውን ሕገ-ወጥ የድንበር ንግድ በጋራ የምንከላከልበት ሁኔታዎች ላይ ተወያይተናል።

Ethiopian Embassy in Djibouti

31 Oct, 08:10


በዛሬው ዕለት ከክቡር የጅቡቲ ብሔራዊ ፖሊስ አዛዥ Colonel Abdurrahman Akli Kahin ጋር በጽ/ቤታቸው በመገኘት በዜጎቻችን ጉዳይ ላይ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል።

በዜጎቻችን ላይ የሚደርሰውን ህገ-ወጥ ተግባር የሚቀረፍበት እና መብታቸው ተጠብቆ በአገሪቱ የሚኖሩበት እንዲሁም ዜጎቻችንም የጅቡቲን ህግ እና ስርዓት ጠብቀው የሚኖሩበትን ጉዳይ በሚመለከት ተወያይተናል።

https://x.com/BerhanuTsegaye/status/1851898434728657127?t=jNKKJkV2yIQJ0Jv3lwd3og&s=19

Ethiopian Embassy in Djibouti

30 Oct, 14:25


ክቡር አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ከጅቡቲ ሆራይዘን ተርሚናል LTD FZCO ዋና ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ኦማር ካሱ ጋር የነዳጅ ኦፕሬሽን ለማሻሻል በተርሚናሉ አፈጻጸም ላይ የነዳጅ ዝውውር ውጤታማነት አስመልክቶ የተለያዩ ጉዳዮችን በማንሳት ተወያይተዋል።

ነዳጅ ለኢትዮጵያ ዋነኛ የፍጆታ ምርት በመሆኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን ፍላጎት ታሳቢ በማድረግ የባቡር መስመርን ከተርሚናሉ ጋር የማገናኘት እና ኦፕሬሽናል አቅምን የማሳደግ ስራ ይጠበቃል።

WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029Va9Yrbs1t90b6eH0Bv06

Ethiopian Embassy in Djibouti

28 Oct, 06:38


ኤምባሲያችን ከዓለም አቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) ጋር በመተባበር 56 መደበኛ ያልሆኑ ፍልሰተኞችን በአውሮፕላን ወደ ሀገራቸው መልሷል።

የኢትዮ-ጅቡቲ-የመን መንገድ እጅግ አደገኛ ከመሆኑም በላይ በድንበር ተሻጋሪ ሕገ-ወጥ ቡድኖች ምክንያት ዜጎቻችን በየቀኑ ለሞት እየተዳረጉ ይገኛል። ይህንን ተግባር ለመከላከል ሁሉም ወላጅ በየቤቱ ሊሰራ ይገባል።

https://x.com/BerhanuTsegaye/status/1850788600297980267?t=vwizpKKz0gwgDcv2UqhWLA&s=19

Ethiopian Embassy in Djibouti

27 Oct, 09:17


ዛሬ ከኢትዮጵያ ወጣቶች ካውንስል ፕሬዝዳንት ወጣት ፉአድ ገና ጋር ተገናኝተን በካውንስሉ የስራ እንቅስቃሴ ዙሪያ ገለፃ የሰጠን ሲሆን፣ በቀጣይ ከጅቡቲ የወጣት አደረጃጀቶች እና ከኢጋድ ሴክሬታሪያት ጋር በጋራ ተባብሮ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች እና የአገራችንን ወጣቶች በከፍተኛ ሁኔታ ለአደጋ እያጋለጠ የሚገኘውን ህገ-ወጥ ስደት ለመከላከል በአገር ቤት ደረጃ በወጣቶች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ዙሪያ በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ የሃሳብ ልውውጥ አድርገናል።

https://tinyurl.com/y4y5sxwm

Ethiopian Embassy in Djibouti

25 Oct, 17:07


ኤምባሲያችን ከኦፕሬሽን ኮሚቴ ጋር በአዲሱ የ2024/25 ዓመት የአፈር ማዳበሪያ ዝውውር ላይ የቅድመ-ዝግጅት ውይይት አደረገ፤

ኤምባሲያችን ዛሬ ከኦፕሬሽን ኮሚቴ ጋር በመሆን በአዲሱ የ2024/25 ዓመት የአፈር ማዳበሪያ ዝውውር ላይ የቅድመ-ዝግጅት ውይይት አድርጓል።

የጂቡቲ ማዳበሪያ ኦፕሬሽን ኮሚቴ በ2023/24 የስራ ዘመን ከጂቡቲ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዘውን የአፈር ማዳበሪያ ኦፕሬሽን በቅርበት በመከታተል ከጂቡቲ ባለድርሻ እና ኢትዮጵያ ካለው አብይ ኮሚቴ ጋር ተቀናጀቶ በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቁ አንስቷል።

በዚህ ሂደት ውስጥ መሻሻል ያለባቸውን እና ለቀጣይ የ2024/25 ዓመት የአፈር ማዳበሪያ ዝውውር በትኩረት መታየት ያለባቸው ጉዳዮችን በመዳሰስ ኮሚቴው በስፋት ተወያይቷል።

በመጨረሻም ክቡር አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ዘንድሮ ወደ አገር ቤት እንዲገባ የታቀደው የአፈር ማዳበሪያ መጠን ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ጭማሪ የሚያሳይ በመሆኑ የተጀመሩ ጥሩ የክትትል ስራዎችን በማጠናከር በጂቡቲ የሚደረጉ የቅድመ-ዝግጅት ስራዎች እንዲጠናከሩ አሳስበዋል።

በኢትዮጵያ ያለው ዐብይ ኮሚቴም ተመሳሳይ ጥረት ሊያደርግ እንደሚገባ ገልጸዋል።

WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029Va9Yrbs1t90b6eH0Bv06

Ethiopian Embassy in Djibouti

22 Oct, 14:45


ኤምባሲያችን በዜጎች ዲፕሎማሲ ዘርፍ እየሰራ ባለው ስራ ከIOM ጋር በመተባበር በቅርብ በጅቡቲ ባህር ጠረፍ ላይ ከደረሰው የጀልባ አደጋ ለተረፉ ዜጎቻችንን ተገቢውን ክትትል በማድረግ እና የጉዞ ሰነድ በማዘጋጀት ዛሬ 37 መደበኛ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ አድርጓል።

በተከታዮቹ ቀናትም ይህ ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፣ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር የመከላከል ስራ በዋናነት ሀገር ቤት ባሉ ሁሉም ተቋማት እና የጸጥታ አካላት መሆኑን በማወቅ ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል።

Ethiopian Embassy in Djibouti

22 Oct, 09:51


ክብር አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ዛሬ በጅቡቲ ከአዲሷ የአሜሪካ እና የኢጋድ አምባሳደር ክብርት ሲንቲያ ኪርስሽት ጋር የተለያዩ ቀጠናዊ ጉዳዮችን አንስተው ተወያይተዋል።

የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ ሁለትዮሽ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት የሚጠናከርበት እና በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደህንነት ላይ ተቀራርቦ መስራት የሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

https://whatsapp.com/channel/0029Va9Yrbs1t90b6eH0Bv06

Ethiopian Embassy in Djibouti

20 Oct, 09:38


ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ. ም

ፓስፖርታችሁ እንዲታደስ የሰጣችሁና ስማችሁ ሊስቱ ውስጥ የተጠቀሰ አመልካቾች ፓስፖርታችሁ ታድሶ ስለመጣ ዘወትር በስራ ሰዓት የቀድሞውን/ የመጠቀሚያ ጊዜው ያለፈበትን ፓስፖርት ይዛችሁ በመምጣት ፓስፖርታችሁን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

መረጃውን ሼር በማድረግ መልዕክቱን ለሁሉም በማድረስ ይተባበሩን

WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029Va9Yrbs1t90b6eH0Bv06

Ethiopian Embassy in Djibouti

19 Oct, 19:22


Ethiopian Embassy in Djibouti pinned «https://t.me/BerhanuTsegayeAbera የሚሲዮናችንን መሪ የክቡር አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ።»

Ethiopian Embassy in Djibouti

19 Oct, 08:48


https://t.me/BerhanuTsegayeAbera

የሚሲዮናችንን መሪ የክቡር አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ።

Ethiopian Embassy in Djibouti

18 Oct, 19:22


በጅቡቲ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደረገ

ቡር አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ነዋሪነታቸው በጅቡቲ ካደረጉ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በወቅታዊ በሆኑ አገራዊ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ላይ በአጠቃላይ ወቅታዊ የሀገራችን ሁኔታ፣ በጅቡቲ ስለሚኖሩ ዜጎቻችን የመብት ጉዳይ፣ ስለህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ሀሰተኛ መረጃን መከላከል ላይ ከእያንዳንዱ የዳያስፖራ አባል የሚጠበቀው ኃላፊነትን በተመለከተ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል።

በመድረኩ ከተሳታፊዎች ለቀረቡ ጥያቄዎች ማብራሪያ በመስጠት ሁሉም የዳያስፖራ አባላት አንድነታቸውን ለሀገራችን የሰላም ዘብ መሆን እንደሚገባ ተገልጿል።

በውይይቱ ላይ የኃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ከተለያዩ የልማት ማህበር አደረጃጀቶች የተውጣጡ የዳያስፖራ አባላት እና በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተሳትፈውበታል።

Ethiopian Embassy in Djibouti

17 Oct, 11:52


በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ግለሰቦች እስከ 25 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ተቀጡ
****

በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ጥፋተኛ ተብለው በ13 መዝገብ የተከሰሱ ግለሰቦች ከአንድ ዓመት እስከ 25 ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣታቸውን ፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በ13 የክስ መዝገብ ተከሰው የፍርድ ውሳኔ የተላለፈባቸው፡-

1ኛ. ተካ ወ/ማርያም 25 ዓመት ጽኑ እስራት እና 28 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፤ በሌላ የክስ መዝገብ ደግሞ 16 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት፣

2ኛ. ለማ ተማሮ 10 ዓመት ጽኑ እስራት፣

3ኛ. መለሰ ካህሳይ 11 ዓመት ጽኑ እስራትና 76 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፣

4ኛ. ደመቀች ማጉጂ 15 ዓመት እስራት እና 30 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፣

5ኛ. ስምኦን ተወልደ 3 ዓመት ከ7 ወር እስራት እና 4 ሺህ 500 ብር የገንዘብ ቅጣት ፣

6ኛ. ዮሃንስ ፍስሃዩ 5 ዓመት ከ7 ወር እስራትና 7 ሺህ 500 ብር የገንዘብ ቅጣት፣

7ኛ. ሀና ዲኖ 3 ዓመት ከ3 ወር እስራትና 2 ሺህ 500 ብር የገንዘብ ቅጣት፣

8ኛ. ረዳት ሳጅን መሀመድ አህመድ 6 ዓመት እና 8 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፣

9ኛ. ገ/ትንሳኤ ሀጎስ በ16 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት እና 80 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፣

10ኛ. አብዱል ሽኩር ይማም 10 ዓመት እና 11 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፣

11ኛ. ሙህዲን አማን መሀመድ 10 ዓመት እና 11 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፣

12ኛ. አብዱላዚዝ ራህመቶ ዳንቴቦ 5 ዓመት እና 6 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፣

13ኛ. ዘላለም ብርሃኑ 5 ዓመት እስራት እና 3 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፣

14ኛ. ናርዶስ ሀብቴ ደበሌ 4 ዓመት ከ5 ወር እስራት እና 3 ሺህ 500 ብር የገንበዘብ ቅጣት፣

15ኛ. ፍሬሕይወት በላይ ግርማ 6 ዓመት እስራት እና 110 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት፣

16ኛ. ቅዱስ ኃ/ሚካኤል ሳምቢ 4 ዓመት ከ5 ወር እስራት እና 3500 ብር የገንዘብ ቅጣት፣

17ኛ. ሚኪያስ ተሾመ ፈጡላ 410 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በ13 የምርመራ መዝገቦች ሲታይ የቆየውን የሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር የወንጀል መዝገብ መርምሮ ጥፋተኞችን ያርማል ሌሎችንም ያስተምራል በሚል ከአንድ ዓመት እስከ 25 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲሁም ከ2 ሺህ ብር እስከ 410 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ መወሰኑን ከፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Ethiopian Embassy in Djibouti

17 Oct, 11:51


በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ጥፋተኛ ተብለው በ13 መዝገብ የተከሰሱ ግለሰቦች ከአንድ ዓመት እስከ 25 ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣታቸውን ፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡

Ethiopian Embassy in Djibouti

16 Oct, 08:40


ህገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በርካታ ዜጎቻችንን በማታለል እና በማጭበርበር በህገ-ወጥ መንገድ ከአገር እንዲወጡ እና በየቦታው ለአካል ጉዳት፣ ለዘረፋ፣ ለከባድ ስቃይ እና ለሞት እንዲዳረጉ እያደረጉ ይገኛል። ህገ-ወጥ ስደት በየትኛውም አገር በጥብቅ የተከለከለ ተግባር ከመሆኑም በላይ ለዜጎች አስፈላጊውን የህግ ከለላ ለማድረግ በህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ምክንያት ውስብስብ ሂደት እየሆነ መጥቷል።

በመሆኑም ዜጎች ለራሳቸው ህይወት ደህንነት ሲባል እነዚህን ግለሰቦች በማጋለጥ እና ህገ-ወጥ ስደትን በመቃወም ሊተባበሩ ይገባል።

https://tinyurl.com/mwc7hca2

Ethiopian Embassy in Djibouti

14 Oct, 08:35


ዛሬ “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችን እና ለብሔራዊ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል የ17ኛ ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን የኃይማኖት አባቶች፣ የመከላከያ አታሼዎች፣ የተቋማት የስራ ኃላፊዎች፣ የኮሚዩኒቲ ማህበር አባላት እና የኤምባሲያችን ሠራተኞች በተገኙበት በደመቀ መልኩ አክብረናል።

የጀግኖች አገር ኢትዮጵያ ዛሬም በማንም ሳትደፈር ተከብራ ትኖራለች። ሰንደቅ ዓላማችን የሉዓላዊነታችን መገለጫ ነው!

Ethiopian Embassy in Djibouti

11 Oct, 10:24


የፓስፖርት የእድሳት ጊዜ ከ5 ዓመት ወደ 10 ዓመት ሊራዘም ነው
*******

እድሜያቸው ከ25 ዓመት በላይ ለሆናቸው ዜጎች የፓስፖርት አገልግሎትን ከ5 ዓመት ወደ 10 ዓመት ከፍ በማድረግ የእድሳት ጊዜውን ለማራዘም እየተሰራ መሆኑን የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አስታውቋል።

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት የተቋማቸውን የሩብ ዓመት አፈፃፀም በተመለከተ ለመገናኛ ብዙኀን ገለፃ አድርገዋል።

የአገልግሎት ሰጪ መስሪያ ቤቱ በተለይ ተቋማዊ ሪፎርም ማድረግ ከጀመረ በኋላ መጠነ ሰፊ ለውጦችን እያስመዘገበ ስለመሆኑ ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም በተለይ በተቋሙ ላይ የሚነሳውን የሙስና ሰንሰለት እና የተገልጋዩች እንግልት ለመቅረፍ እና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው ብለዋል ።

በሩብ ዓመቱ 367 ሺህ ፓስፖርት ለተገልጋዮች ማድረስ መቻሉን ዋና ዳሯይሬክተሯ ገልፀዋል።

ከዚህ ውስጥ 344 ሺህ መደበኛ 22 ሺህ ደግሞ አስቸኳይ ማለትም በአንድ፣ በሁለት እና በአምስት ቀናት ውስጥ የተሰጡ ስለመሆናቸው አብራርተዋል።

ተቋሙ በኦን ላይን (በይነ መረብ) የመቀበል አቅሙን በቀን ወደ 7 ሺህ ያሳደገ ሲሆን ለአቸኳይ ፓስፖርት በቀን 600 ሰዎች ማስተናገድ መቻሉንም ዋና ዳይሬክተሯ ጠቅሰዋል።