ፈተናውን ተፈተንኩ.... ታርሞ መጣ ያን ግዜ ግን ፈራው በቃ ዛሬ የሞተ ውጤት ማምጣቴ ነው አላየውም አልኩ... ግን አላመንኩም ውጤቴን ሳየው ፈተናውን የሰቀለው ልጅ በ 1 ነጥብ ነው የበለጠኝ😋 በደቂቃዎች ልዩነት ልቤ የደስታ ጮቤ ረገጠች....... በዋላ ወደልማዴ ተመልኩ ቁዋሚ ደንበኛ ያረገኝ ጭንቀቴ መጣ ማሰብ ጀመርኩ ተነግሮ በማያልቀው መጥፎ ልማዴ ምወዳቸውን ብቻ ሳይሆን ሚወዱኝንም አጣው አልኩ ቆዘምኩ... ይሄ ያለፈ ታሪኬ ነው አሁን አልፉዋል ብዬ ዞር ልል ስል ልሎች ጥፋቶቼ እንዴ menu ተዘረዘሩልኝ ለእናቴ ጥሩ አልነበርኩም... ምናልባት ከ7-8 ባለው እድሜዬ ሳየው የነበረው ፊልም animation ሳይሆን horror movie ነበር ያ አድጎ አድጎ ፊልም ሳስጭን ራሱ ሙሉውን ሌላ ሳልቀላቅል ብዙ horror ፊልም ይዞ መግባት ልማዴ ሆነ በኔ ቤት horror ፊልም ማዬቴ ሌሎች ሚፈሩትን መድፈር አለፍ ሲል ሌሊት 8 ሰዓት ላይ ተነስቶ ማየት ጀግንነት መስሎ ተሰማኝ በዋላ ግን የ ሰውነቴን ትርጉም አስረሳኝ ጨካኝ ሆንኩ ስሜት አልባ 😔 ድፍረት የመሰለኝ ማስተዋል ሲጀመር የፈሪዎች ፈሪ አድርጎ ሽምድምድ አርጎ ጣለኝ.........
ሚያስጨንቀኝ ክፉ ልማዴ ምን ይሄ ብቻ በተንኮል professor ከተኮነማ ረዳት ሳይሆን ዋና ማዕረግ ነበር ማገኘው በተላይ ወደ ጭንቅላቴ ሚመጡት ሃሳቦች የሚያስቀስፉ በኖህ ዘመን በጥፋት ውሃ ያለቁ ሰዎች ራሱ ሚያስቡት አይመስለኝም ላለፉት 2-3 ዓመት ማለትም ከ 1000 በላይ ቀናትን ጨለማ ወስጥ ነበርኩ 1000 ቀናት ያልኩት 2-3 ዓመት ሲባል ቀላል ስለሚመስል ነው! ሊዘርዝረው ካልኩ ተንኮሌን የማቱ ሳላ እድሜ አይበቃኝም..... ቢሆንም ተስፋ መቁረጥ እና መቀየር አለመፈለግ 1ድም ቀን አስቤ አላቅም ወድቃለው እነሳለው ወድቃለው እነሳለው..... የተውኩት አመል እና ልማዴ ልተወኝ አልቻለም ነበር.... ግን ዋናው ቁም ነገር መውደቄን ሳይሆን መነሳቴን መጥፋቴን ሳይሆን መመለሴን ሚፈልገው ፈጣሪዬ ለኔ ምርጥ ጉዋደኛ ሰጠኝ ሁሌም positive thinker ነው ጨለማውን እስክሻገር እጄን አለቀቀውም ስለሱም ተናግሬ ማቆም ይከብዳል...
ይቀጥላል ....
የተቀደሰ ቀን ተመኘን🙏
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ😊