EPS (Ethio-Parents' school) @epsnow Channel on Telegram

EPS (Ethio-Parents' school)

@epsnow


Ethio-Parent's School Student Resource Center

EPS (Ethio-Parents' school) (English)

Welcome to EPS (Ethio-Parents' School), also known as epsnow on Telegram! EPS is a student resource center dedicated to helping Ethiopian parents navigate the educational system and provide support for their children's academic success. Whether you're a parent looking for tips on how to help your child excel in school or a student seeking additional resources to enhance your learning, EPS is here to assist you every step of the way

Who is EPS? EPS is a community-driven initiative created by a group of passionate educators and parents who understand the challenges that Ethiopian families face when it comes to education. Our goal is to empower parents with the knowledge and tools they need to support their children's learning journey and foster a culture of academic excellence within the Ethiopian community

What is EPS? EPS is more than just a school; it is a hub of resources, information, and support for Ethiopian parents and students. From study tips and exam preparation strategies to information on college admissions and career guidance, EPS offers a wide range of services to help families navigate the complexities of the education system

At EPS, we believe that every child has the potential to succeed academically, and we are committed to providing parents and students with the resources they need to unlock that potential. Join us on Telegram at epsnow to access our wealth of educational resources, connect with other like-minded parents and students, and embark on a journey towards academic success with EPS by your side.

EPS (Ethio-Parents' school)

14 Feb, 09:09


We are sharing what we have..schools are being hosted by us

EPS (Ethio-Parents' school)

14 Feb, 08:02


Experience Sharing at EPS

EPS (Ethio-Parents' school)

09 Feb, 17:01


These all apply to the high school students as well.

EPS (Ethio-Parents' school)

09 Feb, 16:12


ውድ የኢትዮ- ፓረንትሰ የተማሪዎች ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች በሙሉ
የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን  እንደሚታወቀው
የሁለተኛው  ወሰነ ትምህርት  የካቲት 3/2017 ዓ.ም ይጀመራል። የመማር ማስተማሩን ሂደት ይበልጥ የተሳለጠ ለማድረግ የሚከተሉትን  የተማሪዎች ስነስርአት ክትትል እና ቁጥጥር ደንብ እና መመሪያዎች  በደንብ  በማጤንና ልጅዎን በቤት  በማስረዳትም ለተግባራዊነቱ ሀላፊነትዎን
እንድትወጡልን በጥብቅ እያሳስብን በቀጣዮቹ ወሰነ ትምህርት በጋራ ጠንክሮ በመስራት  ተማሪዎቻችንን በእውቀትና በስነምግባር የምንቀርፅበት እንደሆን ተስፋ አደርጋለሁ ።
   
   ገርጂ  አንደኛ ደረጃ ት/ቤት



የተማሪዎችስነስርአት ክትትል እና ቁጥጥር ደንብ እና መመሪያዎች
1. የትምህርት ሰዓትን በተመለከተ
ጊዜ አላቂ ሀብት ነው ስለዚህ በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ ማርፈድ የትምህርት ሰዓትን መስረቅ ነው፡፡ ደግሞም የስንፍና ምልክት ነው፡፡
ተማሪዎች በትምህርት ቀናት ጠዋት እስከ 2፡15 በት/ቤት ግቢ ውስጥ መገኘት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ደወል ሲደወል ወዲያውኑ መሰለፍ አለባቸው፡፡ ከ 2፡20 ጀምሮ ባለው ጊዜ የሚመጡ ተማሪዎች አርፋጆች ይሆናሉ፡፡
2. አለባበስን በተመለከተ
ተማሪዎች የት/ቤቱን የተማሪ የደንብ ልብስ በአግባቡ ለብሶ መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡
ተማሪዎች ሁልጊዜ ወደ ት/ቤት ሲመጡ ንፁህ የተማሪ የደንብ ልብስ ማድረግ አለባቸው፡፡ የደንብ ልብስን አግባብ ባልሆነ መልኩ ማሰፋት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
የፀጉርና የግል ንጽህናን መጠበቅ ተገቢ ነው፡፡
ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ጥፍራቸውን በየጊዜው በአግባቡ መቁረጥ አለባቸው፡፡
ወንዶች ፀጉራቸው አጠር ብሎ በአግባቡ የተስተካከለ መሆን አለበት፡፡ ጆሮን መበሳትና የጆሮ ጉትቻ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
ሴቶች በት/ቤት ውስጥ የጥፍር ቀለም፣ ትልልቅ የጆሮ ጉትቻ፣ የአንገት ሀብል፣ የእግር አልቦ፣ የእጅ አንባር፣ የፀጉር ጌጥ እና ማንኛውም የመዋቢያ ነገሮችን መጠቀም አይፈቀድላቸውም፡፡
3. መታወቂያ መያዝን በተመለከተ
ተማሪዎች መታወቂያቸውን ት/ቤት ሲመጡ ይዘው መምጣት ይኖርባቸዋል፡፡
ተማሪዎች በጥበቃና እንዲሁም በግቢ ውስጥ ማንኛውንም ሰራተኛ መታወቂያ እንዲያሣዩ ሲጠይቁ ወዲያውኑ የማሳየት ግዴታ አለባቸው፡፡
4 - የሰልፍ ሥነ-ስርዓትን በተመለከተ
ማንኛውም ተማሪ በሰልፍ ሥነ-ስርዓት ላይ ተገኝቶ የሚተላለፈውን መልዕክት መከታተልና ብሔራዊ መዝሙር ሀገራዊ ፍቅርን በሚያሳይ መልኩ መዘመር አለበት፡፡
5. የት/ትን ሰዓት በአግባቡ መጠቀምን በተመለከተ
በት/ት ሰዓት ከክፍል መውጣት የሚቻለው የመምህሩን ፈቃድ ሲያገኙ ብቻ ነው፡፡
6. ከት/ቤት መውጣትን በተመለከተ
ተማሪዎች ወደ ት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ከገቡ በኃላ የጤና ችግርን ጨምሮ አስገዳጅ የሚያስወጣ ሁኔታ ከተፈጠረ በር/መ/ሩ ወይም በዪኒት መሪ ፈቃድ ወላጅ እንዲወስድ ይደረጋል ፡፡
7. መቅረትን በተመለከተ
ተማሪዎች በተለያዩ  ከአቅም በላይ በሆኑ ችግሮች ከት/ት ሲቀሩ ወደ ት/ቤቱ በመደወል ፈቃድመጠየቅ አለባቸው፡፡
የክፍል ኃላፊ መምህር ለበላይ ኃላፊ እያስተላለፈና መረጃን በመያዝ እስከ አንድ ቀን ፈቃድ ሊሰጥ ይችላል፡፡ ከዚያ በላይ ላሉት የት/ትቀናት ፈቃድ መስጠት የሚችለው ር/መ/ሩ ወይም ም/ር/መ/ሩ ይሆናል፡፡
8. የአመጋገብ ስርአትን በተመለከተ
ተማሪዎች የእረፍት ሰዓት ቁርስና ምሳ በስርአቱ መመገብ ይኖርባቸዋል፡፡ 
በት/ቤት ግቢ ውስጥ ማስቲካ ማኘክ የተከለከለ ነው፡፡
ከረሜላና ቸኮላት የመሳሰሉ ጣፋጭ ነገሮችን ወደ ት/ቤት ይዞ መምጣት አይፈቀድም፡፡
9. የት/ቤቱን ንብረት አጠቃቀምን በተመለከተ
ተማሪዎች በክፍል ውስጥም ሆነ ከክፍል ውጪ የት/ቤቱን ንብረት በአግባቡ በመጠቀም የየዕለት ት/ታቸውን መከታተል ይኖርባቸዋል፡፡
በዴስክ፤ በጠረጴዛ፤ በግድግዳና በጥቁር ሰሌዳ፤ እንዲሁም በሽንት ቤት ግድግዳ፣ በርና  በመፅሀፍት ላይ መፃፍ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
10 - የተማሪዎች እርስ በርስ ግንኙነትን በተመለከተ
 ተማሪዎች በት/ቤቱ ውስጥ ከማንኛውም ተማሪ ጋር መልካም ግንኙነት     ሊኖራቸው ይገባል፡፡
መሳደብ (መዝለፍ)፣ መደባደብ፣ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
ሴት ተማሪዎችን ከማንኛውም ጥቃት መከላከል ይገባል፡፡
11 - ሙሉ ትኩረት ለትምህርት መስጠትን በተመለከተ
ትምህርት የተማሪውን መሉ ትኩረት የሚጠይቅ ሂደት ነው፡፡ ስለሆነም ተማሪዎች  የተቃራኒ ፆታ የፍቅር ጓደኝነት በት/ቤት ውስጥም ሆነ ከት/ቤት ውጪ እንዲመሰርቱ አይፈቀድም፡፡
12 - በት/ቤት ውስጥ የተለጠፉ ማስታወቂያዎችንና የተለያዩ ጽሁፎችን በተመለከተ
በት/ቤት ውስጥ የተለጠፈ ማንኛውም ማስታወቂያ ማንበብ ተገቢ ሲሆን በላዩ ላይ መፃፍና መገንጠል ግን በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
13 - በግል ጥረትና ንብረት ብቻ መጠቀምን በተመለከተ
ሀ)ኩረጃ የጥገኝነት መገለጫ ነው፡፡ ተማሪዎች ባላቸው እውቀትና ክህሎት ሊተማመኑና ከትጋታቸው ብቻ በሚገኝ ውጤት ላይ ሊደገፉ ይገባል።
ማንኛውም ተማሪ ፈተና ሲኮርጅ በፈታኝ መምህሩ ቢያዝና ቢፈረምበት እንደጥፋቱ ሁኔታ ከፈተና ውጤቱ ላይ  ከመቀነስ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ውጤት እስከመሰረዝ በሚያደርስ ቅጣት ሊቀጣ ይችላል።
ለ) ስርቆት አስፀያፊ ተግባር ነው፡፡
የሌላን ተማሪ ወይንም የት/ቤቱን ንብረት ሳያስፈቅድ መውሰደ የስርቆት ተግባር እንደሆነ ይቆጠራል፡፡
14 - ለመምህራን የሚገባውን ክብር መስጠትን በተመለከተ
ተማሪዎች የዕውቀት አባት/እናት የሆኑ መምህራንን ማክበር መታዘዝና  በሚያሳዩአቸው መንገድ መመራት ይኖርባቸዋል፡፡ ከመ/ራን ጋር የሚፈጠር ማንኛውም አለመግባባት ከመምህሩ ጋር በመወያየት፣ በዚህም ካልተፈታ ለት/ቤቱ  አስተዳደር በማሳወቅ መፍታት ይቻላል፡፡
15 - ከሱስ የጸዳ ህይወትን በተመለከተ
ተማሪዎች በት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥም ሆነ ከት/ቤት ቅጥር ግቢ ውጪ ከሱስ አምጪ ነገሮች የፀዳ ህይወት ሊኖራቸው ይገባል፡፡
16 - የተማሪዎች አካላዊ ደህንነትን በተመለከተ
የተማሪዎች ደህንነት ላይ ስጋት ሊፈጥሩ የሚችሉ አደገኛና ስለታም መሳሪያዎችን በት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይዞ መገኘት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡


17. የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችንና ገንዘብን በተመለከተ
እንደሞባይል፣ I-pod, Lap top, Palm top, mp3 player, Walkaman, ሬድዮ የመሳሰሉትን የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በት/ቤት ውስጥ ይዞ መገኘት አይፈቀድም፡፡
ተማሪዎች ከላይ የተጠቀሱትን ቁሳቁሶች በት/ቤቱ ውስጥ ይዘው ቢገኙ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃው በት/ቤቱ ይያዝና ወላጅ እንዲያመጡ ይደረጋል፡፡ ንብረቱ በትምህርት ቤቱ መመሪያ መሰረት የት/ት ዘመኑ እሰከሚያልቅ ድረስ በት/ቤቱ ተይዞ ይቆያል፡፡
ተማሪዎች ለትራንስፖርት ከሚሆን መጠን ያለፈ ገንዘብ ይዘው ወደ ት/ቤት መምጣት አይፈቀድላቸውም፡፡
ማሳሰቢያ
በክፍልም ሆነ በውጭ የሚፈጸሙ ጥፋቶች የግቢውን ማህበረሰብ ሁሉ የሚመለከተው ሲሆን ለአፈጻጸም ከተማሪው የክፍል መ/ር ጀምሮ ወደ ላይ በሚኖሩት የኃላፊነት እርከኖች  ሪፖርት ይደረጋል፡፡
ምርመራን የሚያካትት ድርጊቶች ሲከሰቱ በዲሲፕሊን ኮሚቴ የሚታይና የውሳኔ ሀሳብ የሚሰጠው ይሆናል፡፡
ከባድ የድሲፕሊን ጉድለት/ግድፈት/ ሲፈጸም በአንድ ጊዜም ቢሆን ከት/ቤት እስከመባረር ድረስ የሚያደርስ እርምጃ ሊወሰድ ይችላል፡፡

EPS (Ethio-Parents' school)

09 Feb, 06:33


የተማሪ ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች የሁለተኛ ሴሜስተር ትምህርት ነገ የካቲት 3/2017 ዓም የሚጀምር ሲሆን የመማር ማስተማሩን ይበልጥ ስኬታማ ለማድረግ የሚከተሉትን የወላጅ ሀላፊነቶች እንድትወጡልን እንጠይቃለን። 1,ተማሪዎች ከጠዋቱ 2:30በፊት ት/ቤት የመገኘት ግዴታ አለባቸው። 2,ዪኒፎርም የት/ቤቱ ባጅ ያለበት መደረግ አለበት 3,የወንዶች ፀጉር በአጭሩ የተቆረጠ በደረጃ ያልተቆረጠ ወይም አንዱ ከአንዱ የማይበላለጥ መሆኑን። ሴቶች ምንም አይነት ጌጣጌጥ የጆሮ የእጅ የጰጉር የማይፈቀድ ሲሆን የከንፈር ቀለም ዊግ ያደገና ቀለም የተቀባ ጥፍር የተከለከለ መሆኑን 4,ማንኛውም ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ ስልክን ጨምሮ በምንም ሰበብና ምክንያት ይዞ መገኘት የተከለከለና ከተገኘም የማይመለስ መሆኑን። ከላይ በዝርዝር የተመለከቱትን ተግባራዊ ያላደረገ ተማሪ ወደ ት/ቤት ግቢ የማይገባ በመሆኑ ወላጆች ተማሪዎች ይህንን ተግባራዊ ማድረጋቸውን እንድታረጋግጡ እያሳሰብን የተጓደሉ ከሆነ ግን ት/ቤቱ ሀላፊነት የማይወስድ መሆኑን ደግመን በጥብቅ እናስታውቃለን። ገርጂ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት

EPS (Ethio-Parents' school)

03 Feb, 06:12


ለገርጂ፤ጉለሌ እና ጉርድሾላ ኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤቶች የተማሪዎች ወላጆች በሙሉ፡፡ የ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ3ኛው ተርም የትምህርት አገልግሎት የመከፈያ ጊዜ ከጥር 27 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ የካቲት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናቶች ውስጥ ክፍያውን እንድታጠናቅቁ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡ኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማህበር

EPS (Ethio-Parents' school)

02 Feb, 08:47


ለኢትዮ- ፖረንትስ ት/ቤት ተማሪ ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች በሙሉ የመጀመሪያ ሴሜስተር ማጠቃለያ የተማሪዎች የፈተና ውጤት ሀሙስ ጥር 29/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30እስከ ቀኑ 6 ሰአት በት/ቤት ተገኝታችሁ እንድትወስዱ እናስታውቃለን። ት/ቤቱ

EPS (Ethio-Parents' school)

31 Jan, 12:22


ለገርጂ፤ጉለሌ እና ጉርድሾላ ኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤቶች የተማሪዎች ወላጆች በሙሉ፡፡ የ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ3ኛው ተርም የትምህርት አገልግሎት የመከፈያ ጊዜ ከጥር 27 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ የካቲት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናቶች ውስጥ ክፍያውን እንድታጠናቅቁ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡ኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማህበር

EPS (Ethio-Parents' school)

17 Jan, 18:12


Few of the Art works by our students

EPS (Ethio-Parents' school)

05 Jan, 15:45


High school students take part in the reading week of our kindergarten..have you seen how they share our responsibilities in bringing up the next generation..wow this is our coordinated effort..thank you high school reading club members.

EPS (Ethio-Parents' school)

05 Jan, 15:36


የጥያቄና መልስ ውድድር

EPS (Ethio-Parents' school)

05 Jan, 15:35


Reading week in EPS kindergarten..we have invited our media icon Alemneh Wassie to read a story for our kids..it was wonderful moment . Imagine to hear a story in that Golden voice..Thank you Alemneh for you are a parent in our school.

EPS (Ethio-Parents' school)

03 Jan, 12:39


የስብሰባ ጥሪ
ለኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማኅበር ባለአክሲዮኖች በሙሉ
የኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማኅበር 23ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ እሁድ ታህሣስ 27 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ጉርድ ሾላ በሚገኘው ኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤት አዳራሽ ይካሄዳል፡፡
ስለሆነም የማኅበሩ ባለአክሲዮኖች በሙሉ በተጠቀሰው ቦታ፣ ቀንና ሰዓት እንድትገኙ የዲሬክተሮች ቦርድ የአክብሮት ጥሪውን እያቀረበ የጉባኤውን አጀንዳዎች በተመለከተ ቅዳሜ ህዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አድማስ ጋዜጣ እና እሁድ ህዳር 29 ቀን 2017ዓ.ም በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ የወጣውን ማስታወቂያ እንድትመለከቱት እናሳስባለን፡፡ ኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማህበር የዲሬክተሮች ቦርድ

EPS (Ethio-Parents' school)

28 Dec, 13:02


የስብሰባ ጥሪ
ለኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማኅበር ባለአክሲዮኖች በሙሉ
የኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማኅበር 23ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ እሁድ ታህሣስ 27 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ጉርድ ሾላ በሚገኘው ኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤት አዳራሽ ይካሄዳል፡፡
ስለሆነም የማኅበሩ ባለአክሲዮኖች በሙሉ በተጠቀሰው ቦታ፣ ቀንና ሰዓት እንድትገኙ የዲሬክተሮች ቦርድ የአክብሮት ጥሪውን እያቀረበ የጉባኤውን አጀንዳዎች በተመለከተ ቅዳሜ ህዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አድማስ ጋዜጣ እና እሁድ ህዳር 29 ቀን 2017ዓ.ም በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ የወጣውን ማስታወቂያ እንድትመለከቱት እናሳስባለን፡፡ ኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማህበር የዲሬክተሮች ቦርድ

EPS (Ethio-Parents' school)

27 Dec, 13:24


🙏

EPS (Ethio-Parents' school)

27 Dec, 11:29


Congrats to all Ethio-parents community

EPS (Ethio-Parents' school)

27 Dec, 11:24


We won the question and answer competition in Bole cluster

EPS (Ethio-Parents' school)

26 Dec, 20:32


📩ማሳሰቢያ

1.ከ4-12ኛ ክፍል የማጠቃለያ ፈተና(6ኛ፣8ኛ እና 12ኛ ሞዴልን ጨምሮ) ወጥ በሆነ table of specification የሚዘጋጅ ስለሆነ ለት/ቤቶች TOS ሰሞኑን የምናወርድ መሆኑን እናሳውቃለን::

2.የ6ኛ እና8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና የሚዘጋጀው የ6ኛክፍል ፈተና( ከ5ኛ እና 6ኛ ክፍል) እንዲሁም የ8ኛ ክፍል(7ኛ እና 8ኛ ክፍል) መሆኑን አውቃችሁ ለተማሪዎቻቹህ አስፈላጊውን እገዛ አድርጉ

3.የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚያካትተው የ9ኛ ክፍል አሮጌው ስርዓተ ትምህርት እና የ11ኛእና 12ኛ ክፍል ከአዳሱ ስርዓተ ትምህርት መሆኑ ታውቆ ለተፈታኝ ለተማሪዎች አስፈላጊው እገዛ ይደረግላቸው!!
10ኛ ክፍል አያካትትም!!

4.የ6ኛ ፣8ኛ እና 12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና በክፍለ ከተማ ደረጃ የሚዘጋጅ ይሆናል!!

5.contnous assessment እስከ ት/ቤት ድረስ ውይይት ተደርጎና ጸድቆ ከከተማ እስኪመጣ ድረስ በጀመራቹህት አግባብ ቀጥሉ

6.ሁሉም የመንግስት እና የግል ት/ቤቶች አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ምዘና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 3/2016 ረቂቅ መመሪያ መሰረት መስራት ይጠበቅባቸዋል!!

EPS (Ethio-Parents' school)

24 Dec, 06:19


የስብሰባ ጥሪ
ለኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማኅበር ባለአክሲዮኖች በሙሉ
የኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማኅበር 23ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ እሁድ ታህሣስ 27 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ጉርድ ሾላ በሚገኘው ኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤት አዳራሽ ይካሄዳል፡፡
ስለሆነም የማኅበሩ ባለአክሲዮኖች በሙሉ በተጠቀሰው ቦታ፣ ቀንና ሰዓት እንድትገኙ የዲሬክተሮች ቦርድ የአክብሮት ጥሪውን እያቀረበ የጉባኤውን አጀንዳዎች በተመለከተ ቅዳሜ ህዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አድማስ ጋዜጣ እና እሁድ ህዳር 29 ቀን 2017ዓ.ም በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ የወጣውን ማስታወቂያ እንድትመለከቱት እናሳስባለን፡፡ ኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማህበር የዲሬክተሮች ቦርድ

EPS (Ethio-Parents' school)

19 Dec, 08:22


ለገርጂ ቅርንጫፍ የ12ተኛ ክፍል ተማሪ ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች በሙሉ በ2017 ዓ,ም ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሰራር መሠረት የፈተና መፈተኛ ብር ሰባት መቶ ሀምሳ ብር(750)የሚከፈል ስለሆነ በወጋገን ባንክ ሆህተ ጥበብ አ.ማ የሂሳብ ቁጥር 0747242010101 ገርጂ ቅርንጫፍ ገቢ እንድታደርጉ እያሳሰብን transfer ማድረግ የማይቻል መሆኑንም ለማሳወቅ እንወዳለን።ትምህርት ቤቱ

EPS (Ethio-Parents' school)

18 Dec, 10:53


የስብሰባ ጥሪ
ለኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማኅበር ባለአክሲዮኖች በሙሉ
የኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማኅበር 23ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ እሁድ ታህሣስ 27 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ጉርድ ሾላ በሚገኘው ኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤት አዳራሽ ይካሄዳል፡፡
ስለሆነም የማኅበሩ ባለአክሲዮኖች በሙሉ በተጠቀሰው ቦታ፣ ቀንና ሰዓት እንድትገኙ የዲሬክተሮች ቦርድ የአክብሮት ጥሪውን እያቀረበ የጉባኤውን አጀንዳዎች በተመለከተ ቅዳሜ ህዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አድማስ ጋዜጣ እና እሁድ ህዳር 29 ቀን 2017ዓ.ም በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ የወጣውን ማስታወቂያ እንድትመለከቱት እናሳስባለን፡፡ ኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማህበር የዲሬክተሮች ቦርድ

EPS (Ethio-Parents' school)

14 Dec, 08:53


Discussion with parents of grade twelve students who are due to take 2017 Ay. National exam..we had a wonderful time with parents the Discussion was really constructive. We have agreed to carry out our roles regarding students results and academic achievements.

EPS (Ethio-Parents' school)

06 Dec, 05:34


ለኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤት ጉለሌ ቅርንጫፍ ወላጆች/አሳዳጊዎች በሙሉ። የ2017 ዓ.ም. የአንደኛው ሩብ ዓመት ፈተና ውጤትን በተመለከተና ስለልጆቻችሁ ባህርይ ከመምህራን ጋር ውይይት የሚደረግበት ቀን ቅዳሜ ታህሳስ 5/2017 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2:30 እስከ 6 ሰዓት በመሆኑ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በት/ቤቱ እንዲገኙ እናሳውቃለን።የጉለሌ ቅርንጫፍ አስተዳደር

EPS (Ethio-Parents' school)

04 Dec, 12:45


የ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የሁለተኛው ሩብ ዓመት የትምህርት ቤት ክፍያ እስካሁን ላልከፈላችሁ የተማሪዎች ወላጆች በሙሉ፡፡ የክፍያ ማጠናቀቂያው ቀን ህዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በቀሩት ቀናት ክፍያ እንድታከናውኑ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡ ኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማህበር

EPS (Ethio-Parents' school)

04 Dec, 07:31


ለተከበራችሁ ወላጆች/አሳዳጊዎች /የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን የ2017ዓ,ም የአንደኛው ሩብ አመት ማጠቃለያ ፈተና ውጤት የሚሰጠው ቅዳሜ ህዳር 28/2017 ዓ,ም በመሆኑ ልጅዎ የሚማርበት ቅርንጫፍ ት/ቤት ከጠዋቱ 2:30 እስከ 6 ሰአት በመገኘት የልጅዎን የፈተና ውጤት እንዲወስዱና በውጤቱ ዙሪያ ከመምህራን ጋር እንዲወያዩ እያስገነዘብን የፈተና ውጤት የሚሰጠው ለወላጅ ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን። ት/ቤቱ

EPS (Ethio-Parents' school)

29 Nov, 09:18


ለገርጂ፤ጉለሌ እና ጉረድሾላ ኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤቶች የተማሪዎች ወላጆች በሙሉ፡፡ የ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የሁለተኛው ሩብ ዓመት የትምህርት ቤት ክፍያ ከህዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ህዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት ክፍያ እንድታከናውኑ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡ ኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማህበር(ኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤት)

EPS (Ethio-Parents' school)

24 Nov, 17:34


በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች!🥰🥰
========================
👉ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው::ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምንችለበት መንገድ:-

ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገባን 🥰:-
------------------------------------------------
☝️ ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት።

☝️ ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡

👌ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አይደለም ። 

☝️ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን።

☝️ ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል።

☝️ የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ  መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል

EPS (Ethio-Parents' school)

21 Nov, 05:59


ለገርጂ፤ጉለሌ እና ጉረድሾላ ኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤቶች የተማሪዎች ወላጆች በሙሉ፡፡ የ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የሁለተኛው ሩብ ዓመት የትምርት ቤት ክፍያ ከህዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ህዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት ክፍያ እንድታከናውኑ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡ ኆኅተ ጥበብ አክሲዮን ማህበር(ኢትዮ-ፓረንትስ ት/ቤት)

EPS (Ethio-Parents' school)

16 Nov, 07:03


Congratulations to all HTSC, Ethio-Parents' Schools Community!

EPS (Ethio-Parents' school)

08 Nov, 05:12


Africa leadership college of Higher education has introduced its opportunities for our students..it was nice let us join this pan African University so that you could be an international citizen.

EPS (Ethio-Parents' school)

30 Oct, 16:50


Students who took national exam in 2016 Ec. can come and collect the original certificate as of tomorrow.
Peace.

EPS (Ethio-Parents' school)

29 Oct, 09:11


ለወላጆች ለአፀደ ህፃናትና ለመጀመሪያ ደረጃ (አንደኛ ክፍል)ተማሪዎች የሀሳብ መለዋወጫ ወይም (communication book)ስለመጣ ከመጽሐፍት መሸጫ መጥታችሁ እንድትወስዱ እንጠይቃለን ።

EPS (Ethio-Parents' school)

25 Oct, 15:53


https://youtu.be/Dy7j2zhf-wg?feature=shared

EPS (Ethio-Parents' school)

25 Oct, 15:19


Today our students who have scored above 500 in the national examination in the year 2016 have advised the next year's exam takers and shared their experiences, told them to be planned, be responsible and have confidence..I really appreciate and it was a wonderful occasion..
Thank you our successful students on behalf of your teachers

EPS (Ethio-Parents' school)

24 Oct, 11:00


A training about reproductive health and family planning for members of Red Cross club..Thank you those young Doctors