JOINT VISION SUCCESS ACADEMY @jointvision Channel on Telegram

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

@jointvision


Grade 1- 8

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY (English)

Are you looking for a comprehensive and innovative educational platform for students in grades 1-8? Look no further than JOINT VISION SUCCESS ACADEMY! As the name suggests, this Telegram channel is dedicated to helping students achieve success through a joint vision of learning and growth

Who is it? JOINT VISION SUCCESS ACADEMY is a specialized educational channel designed for students in grades 1-8. Whether you're a parent looking for additional resources to support your child's learning or a teacher seeking new ways to engage your students, this channel has everything you need to help students succeed.

What is it? JOINT VISION SUCCESS ACADEMY offers a wide range of educational materials, including practice worksheets, interactive quizzes, and informative videos. With a focus on creating a supportive and engaging learning environment, this channel aims to inspire students to reach their full potential and excel academically.

Join JOINT VISION SUCCESS ACADEMY today and be a part of a community dedicated to empowering students and fostering a love of learning. Together, we can help students build a solid foundation for future success and achieve their academic goals. Don't wait any longer - join us on this journey towards academic excellence!

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

17 Feb, 20:30


Believe me this is our season!!

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

17 Feb, 19:52


ሰበር ዜና!
ዘመኑ የዋንጫ ነው!!!
🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆👏👏👏👍👍
ከ የካቲት 04-10/2017 ዓ.ም ሲካሄድ የነበረው 10ኛ ወረዳ አቀፍ የስፖርት ፌስቲቫል የማጠቃለያ ፕሮግራም በድል ተጠናቀቀ ። 👌👌👌👌👌👌👌👌💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
መረብ ኳስ:-
ለዮቶር ት/ቤት 2 ለ 0
ለኢስት አፍሪካ ት/ቤት 2 ለ 0
ለ ብሩህ ተስፋ ት/ቤት 2ለ 1
በማሸነፍ ዋንጫ አግኝተናል።
የሴቶች ተማሪዎች እግር ኳስ ለ ዮቶር ት/ቤት 4 ለ 0 በማሸነፍ ሁለተኛ ዋንጫ አግኝተናል።
ሩጫ በተማሪ በወንድ እና በሴት በሁሉም የተካሄዱት የሩጫ ዘርፎች ማለትም በ100ሜ፣200ሜ እንዲሁም በ 400ሜ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ይዞ የጨረሱት ከ ጆይንት ቪዥን ሰክሰስ አካዳሚ💪💪💪🤙🤙🌿🌿🌾🌾

በአጭሩ ት/ቤታችን እስከ ዛሬ ድረስ በተካሄዱት ልዩ ልዩ ስፖርታዊ ውድድሮች ከፍተኛ ትንንቅ በማድረግ እና የወኔ ልዕልና በመሰነቅ የ2 ዋንጫ እና 6 ሰርተፍኬት ባለቤት በመሆን ውድድሩ በስኬት አጠናቅቀዋል። ውድድሩ በስኬት እንዲጠናቀቅ ከጎናችን በመቆም ስትደግፋን የነበራችሁ ውድ መ/ራን ፣ተማሪዎች፣ወላጆች፣የት/ቤቱ ባለቤት እና አስተዳደር እንዲሁም ስፖርቶኞችን የተቀላጠፈ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት የተባበራችሁን አካላት በሙሉ ምስጋናችን ከልብ ነው።
🙏🙏🙏🙏❤️❤️❤️❤️
ሰናይ ጊዜ!
ት/ቤቱ

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

15 Feb, 17:29


የመረብ ኳስ ድል አሁንም ቀጥለዋል!
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹👍👍👍
የት/ቤታች አምባሳደሮች ዛሬም ድሉ ቀንትዋችዋል ። የት/ቤታችን ዝና እና ክብሩን ለማስጠበቅ በተለያዩ የስፖርት ውድድሮች  በፍፁም ጨዋነት በአንድም በሌላም እየተፋለማችሁ እና እያበረታታችሁ የምትገኙ መ/ራን፣ተማሪዎች፣ወላጆች፣  የት/ቤቱ ባለቤት እና አስተዳደር በሙሉ ታላቅ ክብር እና ምስጋና ለእናንተ ይሁን!🙏🙏🙏👍👍❤️❤️❤️👏👏👏
ወንድማችሁ አጽብሃ ነኝ
   የመረብ ኳስ ውድድር ከዚህ በፊት ለዮቶር ት/ቤት 2-0 በማሸነፍ ለ ግማሽ ፍፃሜ ማለፋችን ይታወቃል ። በዛሬም በከፍተኛ ወኔ እና ትንንቅ ኢስት አፍሪካ ኮሚኒቲ ት/ቤትን 2-0 በማሸነፍ ለሰኞ፣ የካቲት 10/2017 ዓ.ም  ከብሩህ ተስፋ ት/ቤት ጋር ውድድሩ ለማካየድ ለፍፃሚ ጨዋታ በቅተናል!     የኔ ባትሆኑ ይቆጨኝ ነበር ኮርቼባችኋለው 👏👏👏👍👍👍👍 ንስር አሞራ !  አሁንም ንገስገስ  ድሉ የኛ ነው!!! ለቀጣይም በይበልጥ ለመጫወት እና ለማሸነፍ ቆርጠን እንነሳ!
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏❤️❤️👏👏
               መልካም ጊዜ!

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

15 Feb, 16:53


ቀን:-08/06/2017ዓ.ም
ለተማሪ ወላጆች/ህጋዊ አሳዳጊዎች በሙሉ:-
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ነገ የመራ/ን -ወላጆች በ1ኛ ሰሚስተር የተማሪዎች ውጤት እና ስነምግባር ዙሪያ የምክክር እና አዲስ የወተመህ ምርጫ ቀን እንደሆነ ይታወቃል። ስለዚህ ሁሉም ወላጅች/ህጋዊ አሳዳጊዎች ከጥዋቱ 2:30 የት/ቤችን ቤተመፃህፍት እንዲገኙልን በአጽንኦት እናሳስባለን።
ማስታወሻ:-
ውጤት የሚሰጥበት ስዓት በሚመለከት የወተመህ ምርጫ ካለቀ በኋላ እስከ 6:00 ብቻ ይሆናል።
መቅረት ሆነ ማርፈድ ከወላጅ አንጠብቅም። ባለማርፈድ ፣ ባለመቅረት እና የወላጅ ገምቢ ሚና በመጫወት ሐላፍነትዎን እንዲወጡ በአክብሮት እናሳስባለን::
👉 ከልጆቻችን የሚበልጥ ጉዳይ የለምና በስዓታችን ተገኝተን እንመካከር።
             ሰላማችሁ ይብዛ!
                                 
                                      ት/ቤቱ

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

15 Feb, 16:26


ሰበር ዜና!
የፍፃሜ ጨዋታዎች ድልድል👉
የፊታችን ሰኞ👉👉
❖❖❖❖
👉ጠዋት 3:00 ሰዓት የተማሪ ወንድ እግር ኳስ ጨዋታ አቡነ ባስሉዎስ ት/ቤት Vs ብሩህ ተስፋ ት/ቤት
👉ጠዋት 3:00 ሰዓት ላይ የመምህራን መረብ ኳስ ጨዋታ ጆይንት ሰክሰስ Vs ብሩህ ተስፋ ት/ቤት
👉ጠዋት 4:00 ሰዓት ላይ የተማሪ ሴቶች እግር ኳስ ጨዋታ ጆይንት ሰክሰስ Vs ዮቶር አካዳሚ
👉 ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ የመምህራን እግር ኳስ ጨዋታ ብሩህ ተስፋ ት/ቤት Vs አቡነ ባስሊዎስ ት/ቤት
👉ከቀኑ 9:15 ሰዓት ላይ የመምህራን ገመድ ጉተታ ጨዋታ ዮቶር አካዳሚ Vs ጆይንት ሰክሰስ ት/ቤት
👉ከቀኑ 9:30 ሰዓት ላይ በተሳታፊ ት/ቤቶች በተማሪዎች መሉ የአትሌቲክስ ጨዋታዎች ይደረጋሉ::
ማሳሰቢያ:-
⓵ሁሉም ተጋጣሚ ሰዓቱን ጠብቃችሁ ብሩህ ት/ቤት ተገኙ🙏
⓶በእለቱ የመዝጊያ ስነ ስርዓት ስለሆነ ሲሳተፍ የነበረ በአጠቃላይ በሰዓቱና በቦታው እንዲገኝ በጥብቅ እናሳስባለ።
👉👉መልካም እድል🙏

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

12 Feb, 09:02


መጽናናትን ስለመመኘት
የትምህርት ቤታችን የወ.ተ.መ.ህ ሰብሳቢ  የነበሩት ፓስተር ዘመኑ ታደሰ  ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው የካቲት 4/2017 ዓ.ም ወደ ጌታ ሄደዋል።  በሕይወት በነበሩበት ጊዜ ሁሉ  ጊዜያቸውን፣ ጉልበታቸውን እና እውቀታቸውን ሳይሰስቱ  ለወከሉት አጠቃላይ ወላጅ እና ለት/ቤቱ ማህበረሰብ ለግሰዋል ። በህልፈታቸው የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለመላው ቤተሰቡ እና ወዳጆቻቸው ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን ።

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

06 Feb, 13:41


ሰኞ፣የካቲት 03/2017 ዓ.ም የ2ኛ መንፈቀ ዓመት የሙሉ ቀን ት/ት ይጀመራል።

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

06 Feb, 12:46


ለ 8ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና ተፈተኝ ተማሪዎች በሙሉ :-
ይህ የ8ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ሙሉ መረጃ ሲሆን ከላይ በተገለጸው  መረጃ ማነኛውም የስም፣ የጾታ፣ዕድሜ፣የፎቶ፣... ስህተት ካለ በስልክ ቁጥር 0937889375 ደውላችሁ ማስተካከል ትችላላቹ።
ማሳሰቢያ:-
👉 መነኛውም ስህተት ማስተካከል የሚቻለው እስከ ሰኞ፣የካቲት 03/2017 ዓ.ም ብቻ ይሆናል።
                       ት/ቤቱ

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

06 Feb, 10:44


ማስታወሻ!
የተማሪዎች ፎቶ screenshot ስለተደረገ ነው የፎቶ ጥራት ችግር አይደለም። ነገርግን የተማሪ ፎቶ እና ስም መጣጣሙን እንድታረጋግጥሉን በትህትና እንጠይቃለን።
ት/ቤቱ

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

05 Feb, 14:12


ለ 6ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና ተፈተኝ ተማሪዎች በሙሉ :-
ይህ የ6ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ሙሉ መረጃ ሲሆን ከታች በተገለጸው መረጃ ማነኛውም የስም፣ የጾታ፣ዕድሜ፣የፎቶ፣... ስህተት ካለ በስልክ ቁጥር 0937889375 ደውላችሁ ማስተካከል ትችላላቹ።
ማሳሰቢያ:-
👉 መነኛውም ስህተት ማስተካከል የሚቻለው እስከ ሰኞ፣የካቲት 03/2017 ዓ.ም ብቻ ይሆናል።
የ8ኛ ክፍል በተሌግራም በቅርብ ይለቀቃል ተከታተሉ::
ት/ቤቱ

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

05 Feb, 13:57


ቀን:- 28/05/2017 ዓ.ም
ሰላም እና ጤና በያላችሁበት ቦታ እንመኛለን።
ጉዳዩ:- የፈጠራ ስራን ይመለከታል።
የ2017ዓ.ም የፈጠራ አውደርዕይ በት/ቤታች እና በወረዳ ደረጃ በቅርብ ስለምናከይድ ማነኛውም ተማሪ የፈጠራ ስራውን ይዞ የካቲት 03/2017ዓ.ም ወደ ት/ቤት በመምጣት የውድድሩ አካል እንዲሆን በትህትና እንጠይቃለን።
ት/ቤቱ

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

18 Jan, 13:33


ቀን:- 08/05/2017 ዓ.ም
ሽልማት ለውጭ መልካም ገፅታ እና የውሰጥ አቅም ይገነባል!
💫💫💫💫🪷🪷🌺💫💫💫💫💫💫🌴🌳🍀💫💫💫💫💫💫🌻🌸
በ2017 ዓ.ም ከግል እና ከመንግስት ት/ቤቶች በወረዳ እና በክ/ከተማ ደረጃ በተካየደው በ8ኛ ክፍል የጥያቄ እና መልስ ውድድር 1ኛ ደረጃ ይዞ በመውጣት ያሸነፈው ብርቂዬ ተማሪያችን የአብቃል ተስፋዬ የእውቅና ሽልማት እና የ 5000 ብር የማበረታቻ ገንዘብ ከ ት/ቤታችን ባሌቤት እና ዋና ስራ አስኪያጅ ክቡር አቶ በቀለ ጥሩነህ ተበርክቶለታል። እንዲሁም ይህንን ውጤት እንዲመጣ ከጎኑ የቆሙት መ/ራን የምስጋና እና እውቅና ሰርተፍኬት ተሰጥቷል። በቀጣይም ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወክሎ በአዲስ አበባ ደረጃ ከፍተኛ የጥያቄ እና መልስ ውድድር በስኬት እንድናጠናቅቅ የሁላችን ባለድርሻ አካላት የላቀ ተነሳሽነት እና ሁለንተናዊ ቅድመ ዝግጅት የሚጠበቅብን ይሆናል።

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

15 Jan, 17:05


ለ 6ኛ እና 8ኛ ክፍል የተማሪ ወላጆች በሙሉ:-
👉 ለነገ ሐሙስ ፣ ጥር 08/2017 ዓ.ም ተማሪዎች የ ሚኒስትሪ ፎቶ 60 ብር ይዞው እንዲመጡ በትህትና እንጠይቃለን ።
ለ ነገ መላክ የማትችሉ ወላጆች ለ ዓርብ፣ጥር 09/2017ዓ.ም እንድትልኩ።
እስከ ዓርብ የሚኒስትሪ ፎቶ አንስተን ስለምናጠናቅቅ ተማሪ በምንም ዓይነት ከት/ቤት እንዳይቀር እያሳሰብን ተማሪዎች ለፎቶ ዝግጁ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ እና ክፍያ እንድትፈፅሙ።
ማስታወሻ
👉 የቅዳሜ ፣ጥር 10/2017ዓ.ም የከተራ ቀን ስለሆነ እና መንገድ ስለሚዘጋጋ የማጠናከሪያ ት/ት አይኖርም።
ት/ቤቱ

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

15 Jan, 16:06


የ8ኛ ክፍል የክ/ከተማ ሞዴል ፈተና በዛሬው ዕለት ረቡዕ፣ጥር 07/2017 ዓ.ም በሰላም የተጠናቀቀ ሲሆን በመጨረሻም በር/መራን እና በተማሪዎች በአጠናን ዘዴ ዙሪያ የምርጥ ተሞክሮ ልውውጥ ተደርጓል።

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

14 Jan, 06:21


በዛሬው ዕለት ማክሰኞ፣ጥር 06/2017 ዓ.ም በጆይንት ቪዥን ሰክሰስ አካዳሚ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል የክ/ከተማ ሞዴል ፈተና እየተሰጠ ይገኛል።

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

13 Jan, 09:32


የ 6ኛ እና 8ኛ ክፍል የሞዴል መፈተኛ ክፍል

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

11 Jan, 18:54


ቀን:-03/05/2017 ዓ.ም
ጉዳዩ:- የት/ቤታች ቀጣይ ክንውኖች ማሳወቅን ይመለከታል።
ሰኞ፣ጥር 05/2017 ዓ.ም ለ 6ኛ፣8ኛ እና 12ኛ  ክፍል ተማሪዎች ብቻ ለሞዴል ፈተና እንዲዘጋጁ ሲባል   ት/ት አይኖርም በቤታቸው ያጠናሉ:: ለሌሎች ተማሪዎች ግን የሙሉ ቀን ት/ት ይኖራል::
ማክሰኞ ፣ጥር 06/2017 ዓ.ም የሙሉ ቀን የክ/ከተማ ሞዴል ፈተና ይሰጣል። ለሌሎች  ተማሪዎች ደግሞ ጎን ለጎን የሙሉ ቀን  ት/ት ይሰጣል::
ረቡዕ፣ጥር 07/2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና 5:00 ስለሚጠናቀቅ  ከፈተና ብኋላ ት/ት ይቀጥላል። 6ኛ ክፍል የሙሉ ቀን ሞዴል ፈተና ይሰጣል::
ሐሙስ፣ጥር 08/2017 ዓ.ም ለ8ኛ ክፍል የሙሉ ቀን ት/ት  ይቀጥላል። 6ኛ ክፍልም ሞዴል ፈተና 4:00 ስለሚጠናቀቅ ከሞዴሉ ብኋላ ት/ት ይቀጥላል::

ማሳሰቢያ:-
👉 የሞዴል ተፈታኝ እና ሌሎች ተማሪዎች መውጫ ስዓት በሚመለከት መደበኛ መውጫ ስዓት ይሆናል።
👉 ሞዴል ተፈታኝ ተማሪዎች በቁርስ ስዓትም ሆነ በምሳ ስዓት ወደ ውጪ መውጣት ስለማይችሉ እንደተለመደው ተማሪዎች ወደ ት/ቤት ሲመጡ ምግባቸውን ይዞው እንዲመጡ ።
👉 ሁሉም የሞዴል ተፈታኝ ተማሪዎች ለፈተና ሲመጡ እርሳስ፣መቅረጫ እና ላጲስ ይዞው እንዲመጡ በትህትና እንጠይቃለን።
መልካም ጊዜ!
🙏🙏🙏
           ት/ቤቱ

         

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

09 Jan, 16:34


ቀን:-01/05/2017 ዓ.ም
ጉዳዩ:- መረጃ መስጠትን ይመለከታል።
በዛሬው ዕለት በት/ቤታችን የሴቶች ልጆገረዶች የማህፀን በር ካንሰር የመከላከያ ክትባት 2ኛ ዙር የግንዛቤ ማስጨበጫ በ ጤና ባለሙያዎች ተሰጠ። በዚህ መሠረት የ2ኛ ዙር የክትባት ዘመቻ ነገ ዓርብ፣ጥር 02/2017 ዓ.ም ለመጨረሻ ጊዜ ይሰጣል። ስለዚህ በዛሬው ዕለት የተላከውን የክትባቱ አጭር ማብራሪያ እና የወላጅ ፈቃድ መጠየቂያ ወረቀት በሚገባ በማንበብ ለነገ ፈጣን ግበረመልስ እንድትሰጡን በትህትና እንጠይቃለን።
          ት/ቤቱ

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

08 Jan, 12:09


ውድ የጆይንት ቤተሰቦች
      ሐሙስ እና አርብ በፈተና ፕሮግራም ላይ እንደተገለጸው መደበኛ ትምህርት ( ከ2:00 - 9 9:15) እተካሄደ ሙከራ 3 የሚሰጥ ይሆናል።

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

04 Jan, 12:30


አንኳን ደስ አለን!🏆🏆🏆🏆🏆
Congratulations!
🌿🌿🌿🏆🏆🌻🌻🌻
በዛሬው ዕለት በክ/ከተማ ደረጃ በ 8ኛ ክፍል የጥያቄ እና መልስ ውድድር ት/ቤታችን እና ወረዳችን ወክሎ የተሳተፎው ብርቅዬ የ8ኛ D ተማሪያችን ጀግናው የአብቃል ተስፋዬ ወረዳቸውን ወክሎ ከ 11 ወረዳ በተወጣጡ እንቁ ተማሪዎች ከፍተኛ ፍክክር እና ትንንቅ አድርጎ ት/ቤታች እና ወረዳችን (ወረዳ 01) 1ኛ ደረጃ ይዘን እንድንወጣ አድርገዋል። ክብር ይገባሃል!! 🙏🙏🙏👏👏🏆🏆🤝🤝🤙🤙
ይህንን ውጤት እንዲመጣ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከታችሁ መ/ራን፣ወላጆች ፣አስተዳደር አካላት ፣የት/ቤቱ ባለቤቶች እንዲሁም የት/ት ባለሙያዎች በድጋሜ እንኳን ደስ አለን!💪💪 🙏🙏🙏

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

04 Jan, 07:06


ተማሪዎች ትምህርት ቤት ለመመዝገብ የፋይዳ  ምዝገባ  አስገዳጅ  ቅድመ ሁኔታ ይሆናል ተባለ


በከተማው ውስጥ ባሉ ትምህርት ቤቶች ሁሉ ለ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የፋይዳ ምዝገባ እንደ ልደት ምዝገባ አስገዳጅ እንደሚሆንም ተገልጿል።


ይህ የተገለፀው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲና የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ከከተማው ትምህርት ቢሮ ጋር በመሆን  የፋይዳ እና የልደት ምዝገባን በተመለከተ ውይይት ባከናወነበት ወቅት ነው።

በዚህም በቀጣይ ግዚያት የፋይዳ ዘመቻ ምዝገባ ስራ በይፋ በግል ትምህርት ቤቶቹ በሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስተባባሪነት ይከናወናል ተብሏል።

የፋይዳ ምዝገባ እንደ ልደት ምዝገባ ለ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ቅበላ የምዘገባ ቅድሙ ሁኔታ እንደሚሆን ተነግሯል

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

03 Jan, 19:15


በዛሬው ቀን(25/042017) በትምህርት ቤታችን የአብሮነት ቀን ውሎአችን በከፊል ይህን ይመስል ነበር፡፡

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

02 Jan, 14:35


ቀን:-24/04/2017 ዓ.ም
ጉዳዩ:- መረጃ መስጠትን ይመለከታል።
ነገ ዓርብ፣ታህሳስ 24/2017 ዓ.ም የሙሉቀን ት/ት መሆኑ።
ሰኞ፣ታህሳስ 28/2017 ዓ.ም ግማሽ  ቀን ማለትም እስከ 5:30 ሙከራ 3 ይሰጣል። 
👉 ዛሬ በት/ቤታችን በተሰጠው የሴቶች ልጆገረዶች የማህፀን በር ካንሰር የመከላከያ ክትባት መውጫ ስዓት ላይ የተማሪዎች ፍርሀት ምክንያት ትንሽ በወላጆች መደናገጥ ስለተፈጠረ ይቅርታ እየጠየቅን የተፈጠረው መደናገጥ የክትባቱ ውጤት እንዳልሆነ ለመግለፅ እንወዳለን።  በዚህ መሠረት ጤና ጣቢያ የገቡ ተማሪዎች ምንም ዓይነት የጤና ችግር እንዳልገጠማቸው እና ተሽልዋቸው ከቤተሰብ ጋር ወደ ቤት በሰላም መሄዳቸውን ለመግለፅ እንወዳለን።
ት/ቤቱ

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

02 Jan, 14:01


ሐሙስ ፣ ታህሳስ 24 ፣ 2017 ዓ/ም
የአንደኛ ሴሚስተር የሙከራ 3 ፕሮግራም

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

26 Dec, 07:24


ሐሙስ ፣ ታህሳስ 17 ፣ 2017 ዓ/ም በጆይንት ቪዥን ሰክሰስ አካዳሚ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ጥሩ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታ ያላቸው ተማሪዎችን ለማበረታታት እውቅና ተሰጠ። በተጨማሪም በእንግሊዘኛ እና ሒሳብ ት/ርት የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ሽልማት ተሰጠ።

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

25 Dec, 15:21


ቀን:-16/04/2017ዓ.ም
ጉዳዩ:- የ8ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተናን ይመለከታል።
የዘንድሮ የ 2017 ዓ.ም የ 8ኛ ክፍል  የሚኒስትሪ ፈተና  የ7ኛ ክፍል ስለሚያጠቃልል ወላጆች ከወዲሁ ልጆቻችን ለፈተናው በሚገባ እንድናዘጋጅ በአፅንኦት እናሳስባለን።
ማሳሰቢያ:-
ተማሪዎች ሚኒስትሪ ፈተና የሚፈተንዋቸው  የት/ት ዓይነቶች የሚከተሉት ናቸው ፦
Math
English
General Science
Social Studies
Citizenship
አማርኛ

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

10 Dec, 04:03


በቀን 30/03/2017 በጆይንት ቪዥን ሰክሰስ አካዳሚ ለሶስቱም ግቢ መምህራን የተማሪ ወላጅ እና የባለ ብዙ ዕውቀትና ልምድ ባለቤት በሆኑት ዶ/ር (PHD) ሺፈራው የተማሪ አያያዝና አመራር ዙሪያ ሳይንሳዊ ዕውቀታቸውና ልምዳቸው በጥልቀት ስልጠና ተሰጠ፡፡ በዚህ አጋጣሚ የተማሪዎቻችን ወላጅ ምሁራን ላደረጋችሁልን ሙያዊ ዕገዛ እጅግ በጣም እያመሰገንን ሌሎቻችሁም ተመሳሳይ አገዛችሁ አይለየን፡፡

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

10 Dec, 02:32


በቀን 29/03/17 ዓ/ም በጆይንት ቪዥን አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተማሪዎች ውጤት፣ ባህሪ እና የመማር ማስተማር ሂደት ዙሪያ የመጀመሪው open house conference ተደረገ።

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

06 Dec, 13:43


በጆይንት ቪዥን ሰክሰስ እካዳሚ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ህዳር 27፣ 2017 ዓ/ም ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን "ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል ህገመንግስቱን መሰረት በደረገ የጥያቄና መልስ ውድድር ታጅቦ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

05 Dec, 15:57


ቀን:- ህዳር 26/2017 ዓ.ም
ማስታወሻ!
ጉዳዩ:- የት/ቤታችን ቀጣይ ክንውኖችን ይመለከታል።

👉 ዓርብ፣ህዳር 27/2017 ዓ.ም ''የኢትዮጵያ  ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን '' ባዓል ለ ግማሽ ቀን (እስከ 5:30) በድምቀት ይከበራል።
👉 ቅዳሜ፣ህዳር 28/2017 ዓ.ም መደበኛ የቅዳሜ ጥናት ይቀጥላል።
👉 እሁድ፣ህዳር 29/2017 ዓ.ም የወላጅ-ት/ቤት በተማሪዎች ውጤት እና ባህሪ ዙሪያ የምክክር ቀን ( Open House Conference)  ለግማሽ ቀን ብቻ ይኖራል። በዕለቱ አሁናዊ የተማሪዎች ውጤት መግለጫ/ ''Progress Report'' ለወላጅ/ህጋዊ አሳዳጊ ይሰጣል::
👉 ሰኞ፣ህዳር 30/2017 ዓ.ም የመ/ራን የስልጠና ቀን ይሆናል:: በዚህ ቀን ት/ት አይኖርም::
👉 ማክሰኞ፣ ታህሳስ 1/2017 ዓ.ም የሙሉ ቀን ት/ት ይቀጥላል።

                  ት/ቤቱ

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

29 Nov, 15:41


የቅዳሜ ትምህርትን ይመለከታል
ከ5ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ያላችሁ የጆይንት ቪዥን ሰክሰስ አካዳሚ ተማሪዎች ዛሬ ዓርብ፣ ህዳር 20፣ 2017 ዓ.ም አጋማሽ ወይም ሚድ ፈተና በጥሩ ሁኔታ ስለጨረስን እያመሰገንን ለነገ የቅዳሜ ትምህርት ተዠጋጅታችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን።
ፈተና ጨርሰናል በሚል ሰበብ መቅረትም ሆነ ማርፈድ የማይቻል መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።
የሚያረፍዱ እና ዩኒፎርም በአግባቡ ሳይለብሱ የሚመጡ ተማሪዎችን ት/ቤት የማናስገባ መሆኑን በአጽንኦት እንገልፃለን።
ት/ቤቱ

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

28 Nov, 15:58


የ 6ኛ ክፍል ተወዳዳሪዎች

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

28 Nov, 15:53


🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆
እንኳን ደስ አለን!!!
Congratulations!!!
🍂🌿🍀🏆🏆💐💐👏👏
በዛሬው ዕለት ህዳር 19/2017 ዓ.ም በወረዳ 01 ት/ጽ/ቤት ደረጃ በተካየደው የሒሳብ እና የኢንግሊዝኛ የት/ት ዓይነቶች በ6ኛ እና 8ኛ ክፍል የጥያቄ እና መልስ ውድድር ት/ቤታችን ውክሎ የተወዳደሩት ተማሪዎች:-
👉 ከ6ኛ ክፍል :
        - ተማሪ አቤኔዘር ብርሃኑ
        - ተማሪ አቢጊያ ፀጋዬ
👉 ከ8ኛ ክፍል:
        - ተማሪ የአብቃል ተስፋዬ
        - ተማሪ ኤልሻዳይ ዘነበ ሲሆኑ በዚህ መሰረት ተማሪ ያአብቃል ተስፋዬ ከ8ኛ ክፍል ተወዳዳሪ ተማሪዎች  1ኛ በመውጣት ያሸነፍን ሲሆን እንደ ትምህርት ቤት ደግሞ 2ኛ ደረጃ ይዘን ውድድሩ በስኬት አጠናቅቀናል።
👉 የ6ኛ ክፍል ተማሪዎቻችን ደግሞ ከፍተኛ ወጤት ውጤት በማስመዝገብ በመጨረሻ ስዓት በመለያያ ጥያቄ ምክንያት የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ማግኘት ችለናል።
ለውድድሩ ስኬት በተለያየ መልኩ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከታችሁ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ፣መምህራን እንዲሁም የአስተዳደር አካላት ከልብ እናመሰግናለን።
                🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
                      
                   ት/ቤቱ

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

26 Nov, 15:06


ዛሬ ህዳር 17/2017 ዓ ም በጆይንት ቪዥን ለቅ/መ/ እና 1ኛ ደረጃ የእንግሊዝኛ መ/ራን የስልጠና ተሰጥቷል ።

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

24 Nov, 00:59


የምስጋና መልእክት!
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

"የስልጠና ችቦ ተለኮሰ"
በዛሬው ዕለት ህዳር 14/2017 ዓ.ም በጆይንት ቪዥን ሰክሰስ አካዳሚ በመጀመሪያ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት  የወተመህ አባልና የቀድሞ የወተመህ ዋና ሰብሳቢ፣በኢትዮጵያ በሎም በአፍሪካ ደረጃ ስመ ገናናው አንጋፋ የምርምር ተቋም አርማወር ሐንሰን /Armauer Hansen Research Institute ( Ahari) ከፍተኛ ተመራማሪ በሆኑት ሜዲካል ማይክሮ ባዮሎጂስት ጌታቸው ተስፋዬ ( PHD)  በተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በማስተማር ሆና በምርምር ባካበቱት ጥልቅ እውቀት እና ተሞኩሮ "የወላጆች ሁለንተናዊ ክትትል በልጆች ( በትምህርት፣ ባህሪ ፣ ጤና ) እንዲሁም ሳይንሳዊ ተማሪዎች በት/ት የማብቃት ዘዴዎች " በሚል የስልጠና ርዕስ ተጋባዥ የተማሪ ወላጆች አስተማሪ የህይወት ተሞኩሮ የታከለበት እጅግ አነቃቂ እና አስተማሪ ስልጠና ተሰጠ፡፡

ጥሪያችን አክብራችሁ በስልጠናው የተሳተፋችሁ የተማሪ ወላጆች/ህጋዊ አሳዳጊዎች እንዲሁም  በከፍተኛ ትጋት እና ያገባኛል ስሜት ስልጠናው በማራኪ ሁኔታ ለሰጡልን ጌታቸው ተስፋዬ (ዶ/ር) ከልብ የመነጨ ክብር እና ምስጋና  በድጋሜ እያቀረብን  የጀመርነውን መልካም ተሞክሮ ቀጣይነት እንዳለው በማረጋገጥ ስልጠና ለእኛ ለወላጆች ፣ለተማሪዎች በሎም እንደሀገር ያለው ዘርፈ ብዙ ፋይዳ በመገንዘብ እና የህይወታችን መስታወት መሆኑን በማመን በቀጣይ  በት/ቤታችን በሚዘጋጁ የስልጠና እና የምክክር መድረኮች ሁላችንም ንቁ ተሳትፎ እንዲኖረን እናሳስባለን።
ማሳሰቢያ :-
- የላቀ የስራ፣የህይወት ተሞክሮ  እና እውቀት ባለቤት ሁናችሁ በተለያዩ የስራ ዘርፎች በመሰማራት ሀገራችሁን በማገልገል የምትገኙ በርካታ የተማሪ ወላጆች እንዳላችሁ ት/ቤቱ በጽኑ ያምናል። ስለዚህ  በማነኛውም ነገር ት/ቤቱ ለማገልገል እና ተምሳሌት የህይወት ልምዳችሁን ለሌሎች ወላጆች ማካፈል የምትችሉ ወላጆች በ አካል/በስልክ 0113694451/0937889375 በመደወል ፕሮግራም ማስያዝ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንጋብዛለን።

👉 መልካም የልምድ ልውውጥ ማድረግ መለያችን ይሁን!
👉 ገንቢ የልምድ ልውውጥ በማድረግ እርስ በእርሳችን እንገነባባ!
        🙏🙏🙏🙏🙏🙏

                      ት/ቤቱ

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

23 Nov, 01:00


በጆይንት ቪዥን ሰክሰስ አካዳሚ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ በቀን 12/0317 ዓ/ም አና 13/03/17ዓ/ም በ6ኛ እና 7ኛ ክፍሎች መካከል የመጀመሪያ ዙር ደማቅ የጥያቄና መልስ ውድድር ተደርጎ በክፍል አሸናፊዎች ተለይተው ታውቀዋል ። በዚህም መሰረት፦ከ6ኛ ከፍል
# 6ለ 1ኛ ወጥቷል
# 6ሐ 2ኛ ወጥቷል
# 6ሀ 3ኛ በመውጣት ውድድራቸውን
አጠናቀዋል።
ከ7ኛ ክፍሎች ደግሞ፦
# 7ሐ እና 7መ ተመሳሳይ ነጥብ
በማምጣት 1ኛ ሲወጡ
# 2ኛ ባለመኖሩ 7ለ 3ኛ በመውጣት
የዕለቱን ውድድር አጠናቀዋል።

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

22 Nov, 11:09


ለተማሪ ወላጆች/ህጋዊ አሳዳጊዎች በሙሉ:-
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ጉዳዩ:- የቅዳሜ የማጠናከሪያ ጥናትን ይመለከታል።
የመ/ራን እና የተማሪዎች  ፍላጎት ግምት ወስጥ በማስገባት ከ ቅዳሜ ፣ህዳር 14/2017 ዓ.ም ጀምሮ የተማሪዎች መውጫ ስዓት 7:40 መሆንን እናሳውቃለን::
ማሳሰቢያ:-
ተማሪዎች እንዳይርባቸው ቁርስ ይዞ እንዲመጡ እንመክራለን::
አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት ከጥናት ገበታ የሚቀሩ ተማሪዎች ተጠያቄ እናደርጋለን::
የጥናት ክፍያ በስዓታችሁ እንድትፈፅሙ እናሳስባለን።
                   ት/ቤቱ

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

22 Nov, 05:10


ለጆይንት ቤተሰቦች በሙሉ:-
ጉዳዩ:- የወላጆች ስልጠናን ይመለከታል።

ከዚህ በፊት የወላጆች ስልጠና ህዳር 14/2017 ዓ.ም እንደሚኖር ማሳወቃችን ይታወሳል። ስለዚህ ነገ ህዳር 14/2017 ዓ.ም ከ3:00 እስከ 5:00 በከፍተኛ በለሙያዎች ስልጠናው ስለሚሰጥ በስዓታችሁ በመጀመሪያ እና መካከለኛ  ደረጃ ት/ቤት ግቢ በቤተመፃህፍት እንድትገኙን በትህትና እንጠይቃለን።

                            ት/ቤቱ

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

19 Nov, 14:57


የተቀየረ የቅዳሜ ተማሪዎች መክፈያ ኮድ፡፡

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

18 Nov, 14:03


በጆይንት ቪዥን ሰክሰስ አካዳሚ
የመጀመሪያ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ህዳር 09/2017 ዓ.ም በተግባር የተደገፈ ት/ት ተሰጠ።

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

18 Nov, 14:03


ለተማሪ ወላጆች/ህጋዊ አሳዳጊዎች በሙሉ:-
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ጉዳዩ:- የቅዳሜ የማጠናከሪያ ጥናትን ይመለከታል።
የመ/ራን እና የተማሪዎች ፍላጎት ግምት ወ
                   ት/ቤቱ

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

13 Nov, 15:01


ለጆይንት ቤተሰቦች በሙሉ:-
ጉዳዩ:- ሃገራዊ የድጋፍ ጥሪን ይመለከታል።

ለታላቁ የህዳሴ ግድብ የብር መዋጮ የመሰባሰቢያ የመጨረሻ ቀን ነገ ሐሙስ፣ ህዳር 05/2017 ዓ.ም ስለሆነ እስከ አሁን ድጋፋችሁን ያልገለፃችሁ ወላጆች ለነገ ከ 50 ብር ጀምሮ ወደ ት/ቤት በመላክ / በአካል መጥታችሁ በመክፈል ሃገራዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ በትህትና እንጠይቃለን።

ት/ቤቱ

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

13 Nov, 13:47


በጆይንት ቪዥን ሰክሰስ አካዳሚ
የመጀመሪያ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ህዳር 04/2017 ዓ.ም በተግባር የተደገፈ ት/ት ተሰጠ።

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

13 Nov, 02:08


በጆይንት ቪዥን ሰክሰስ አካዳሚ
የመጀመሪያ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ህዳር 03/2017 ዓ.ም በተግባር የተደገፈ ት/ት ተሰጠ።

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

11 Nov, 00:27


ለተማሪ ወላጆች/ህጋዊ አሳዳጊዎች በሙሉ:-
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ጉዳዩ:- የቀጣይ ክንውኖችን ይመለከታል።
በት/ቤታችን በህዳር ወር ውስጥ ከሚከናወኑ ዓበይት ክንውኖች መካከል:-
👉 ከሰኞ፣ህዳር 02 እስከ  ሐሙስ ህዳር 05/2017 ዓ.ም ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ማጠናቀቂያ የሚሆን ብር ከ ነፍስወከፍ ተማሪ 50 ብር የምናሰባስብበት ሳምንት ይሆናል።
👉 ቅዳሜ፣ህዳር 14 /2017 ዓ.ም ለሁሉም ወላጆች የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ለግማሽ ቀን ይሰጣል።
👉 ሰኞ፣ህዳር 16 /2017 ዓ.ም የ1ኛ መንፈቀ ዓመት አጋማሽ ፈተና ( First Semister Mid Exam) ይኖራል።
ማሳሰቢያ:-
  የ 6ኛ እና 8ኛ ክፍል የቅዳሜ ማጠናከሪያ ት/ት ክፊያ ያለ ቅጣት መክፈል የሚቻለው ወር በገባ ከ 1 እስከ 10 ባሉት ቀናት ብቻ ሲሆን ከ 10 ቀን በኋላ በቀን 10 ብር ቅጣት እየቆጠረ ይሄዳል።

የጥናቱ ክፍያ  በስልክ ወይም በባንክ መክፈል ይቻላል።


 
                   ት/ቤቱ

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

10 Nov, 13:24


ለተማሪ ወላጆች/ህጋዊ አሳዳጊዎች በሙሉ:-
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ጉዳዩ:- ከ1ኛ -4ኛ ክፍል የከስዓት ጥናት ስለማቋረጥ።

ከ ት/ቢሮ በወረደልን  መመሪያ መሰረት  የከስዓት ጥናት  ማለትም ከ1ኛ-4ኛ ክፍል ከሰኞ፣ህዳር 02/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለጊዜው  እንደሚቋረጥ በደብዳቤ ማሳወቃችን የሚታወስ ሲሆን በቀጣይ ጥናቱ እንዲሰጥ ከተፈቀደ የምናሳውቅ ይሆናል።
ማሳሰቢያ:-
👉 ከዚህ በፊት ጥናቱ ያጠኑ የነበሩ ተማሪዎች ወደ ቤት መውጫ ስዓት (9:00) ስለሚሆን ልጆቻችሁ በጊዜ እንድትወስዱ።
👉 የ5ኛ እና የ7ኛ ክፍል ጥናት ከህዳር ወር ጀምሮ ወደ ቅዳሜ ቀን የሚዘዋወር ሲሆን በቀጣይ ዓመት የሚኒስትሪ ፈተና የ 5ኛ እና የ7ኛ ክፍል ት/ት ጭምር ስለሚያካትት  ተማሪዎች ከወዲሁ በቂ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ያግዛቸው ዘንድ የጥናቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ እናሳስባለን።  


                   ት/ቤቱ

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

08 Nov, 07:58


ለተማሪ ወላጆች/ህጋዊ አሳዳጊዎች በሙሉ:-
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ጉዳዩ:- የ6ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ውጤትን ይመለከታል።
የ 2016 ዓ.ም የ 6ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ዋናው ደኩመንት በሃርድ ኮፒ ስለመጣ ከ ዛሬ፣ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም ጀምራችሁ በስራ ስዓት ከ 1ኛ - 8ኛ ግቢ ከ ማህደር ክፍል መውሰድ ትችላላችሁ።
ማሳሰቢያ:-
👉 ውጤት መውሰድ የሚችለው ወላጅ/ ህጋዊ አሳዳጊ ብቻ ነው።

                   ት/ቤቱ

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

07 Nov, 08:50


በጆይንት ቪዥን ሰክሰስ አካዳሚ በመጀመሪያ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የመጀመሪያ ዙር በ8ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል የጥያቄ እና መልስ ውድድር ተካየደ።

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

05 Nov, 10:45


Test-2 schedule for 1-8 students.

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

31 Oct, 16:18


 {{`` መማር`` ማለት በጎ የሆነ የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት ነው``}}
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
 #``በጆይንት ቪዥን 1ኛ ና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
የልምድ ልውውጥ ተካሄደ```
============================
በኮ/ቀ/ክ/ከተማ አሰተዳደር  #የወረዳ 01 ት/ፅ/ቤት  'የ2017 ዓ/ም የ1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ፣የተከለሠ የሒሳብና እንግሊዝኛ እስትራቴጂክ እቅድና የተከናወኑ ተግባራት ግምገማና በጆይንት ቪዥን ሰክሰስ አካዳሚ የልምድ ልውውጥ  ከመንግስትና ከግል ር/መ/ራን፣ቅ/1ኛ አስተባባሪዎች፣የወተመህ አመራሮች፣ ከት/ባለሙያዎቸና ሱፐር ቫይዘሮች ጋር# በ21/02/2017 ዓ/ም
 በአንጋፋው ተቋም በጆይንት ቪዥን ሰክሰስ አካዳሚ ግምገማዊ ውይይቶች ተካሂደዋል::
በወቅቱ ሪፖርት በማቅረብ ልምዳቸውን ያጋሩ ተቋማት
1@.አቶ ሀብታሙ ንጉሴ==ከኢምብሬንሲንግ ሆፕ ኢትዮጵያ ቅ/1ኛ ደረጃ ት/ቤት
2@. አቶ እንዳለው ታዬ==ከዮቶር 1ኛ ደረጃ ት/ቤት
3@.አቶ አፅብሐ ተክሉ==ከጆይንት ቪዥን 1ኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
4@.ፍሬህይወት ጌታነህ==ከቤተሰብ ቅ/1ኛ ደረጃ ት/ቤት
ሲሆኑ በስተመጨረሻም የት/ፅ/ቤት የ1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የተከለሠ የሒሳብና እንግሊዝ እስትራቴጂክ እቅድ ግምገማዊ ውይይት ''በአቶ በቀለ የቀረቡ ሲሆን #በት/ፅ/ቤትና በት/ቤቶች የቀረቡ ሪፖርቶች
አስተማሪና ጥልቅ የሆነ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ከቤቱ ለተነሱ ግልፅነት የሚሹ ጥያቄዎችና አስተያዬቶች በባለሙያዎችና ሱርቫይዘሮች ምላሽና ማብራሪያ መስጠት ተችሏል::ከውይይቱ ማጠቃለያ በኃላ በጆይንት ቪዥን 1ኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የቤተ_ሙከራና  የልዩ ፍላጎት ክፍሎችን በመጎብኘት በተግባር የተደገፈ ት/ት አሠጣጥ ሁኔታ ልምድ መቅሰም ተችሏል::
በአጠቃላይ በዚህ ውጤታማ ልምድ ልውውጥና ውይይቶች ተቋማችሁን በመወከል የተገኛችሁ፣ ሪፖርት ያቀረባችሁና ልምዳችሁን የጋራችሁን ከልብ እያመሠገንን በቀጣይ ይህን አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን እያሳወቅን በዚህ አጋጣሚ ጆይንት ቪዥን ሰክሰስ አካዳሚ ሙሉ  የሻይ ቡና መስተንግዶና የትራንስፖርት አበል ስለሸፈነልን በት/ፅ/ቤት ስም በጣም እናመሠግናለን

================================
               ጥቅምት  21/2017 ዓ/ም

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

29 Oct, 14:56


በቀን15/02/17 በጆይንት ቪዥን የመጀመሪየ ዙር የተማሪዎች ፓርላማ ምርጫ ይህ ሲመስል ሁለተኛ ዙር ሰኞ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

29 Oct, 14:56


ንቁ የክበባት እንቅስቃሴ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የብዙ ውጤታማ ሰዎች መሰረት እና የዜጎች ሀለንተናዊ ንቁ ተሳትፎ መሰረተ ድንጋይ ት/ቤት እንደሆነ ይታመናል። በዚህ መሰረት የ2017 ዓ.ም በጆይንት ቪዥን ሰክሰስ አካዳሚ አንደኛ ደረጃ በ1ኛ እና በ2ኛ ዙር ምዕራፍ የተከናወነ የተማሪዎች ፖርላማ የምርጫ ስነስርዓት እንዲህ ባለ ሁኔታ ተከናውኖ አልፏል ።

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

25 Oct, 15:21


ቀን:- 12/02/2017  ዓ.ም
ለተማሪ ወላጆች/ህጋዊ አሳዳጊዎች በሙሉ:-
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ጉዳዩ:-  የቅዳሜ ጥናትን ይመለከታል።
የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል የጥናት የአከፋፈል ሁኔታ በቅርቡ በባንክ እንድትከፍሉ አሳውቀናችሁ እንደነበረ ይታወቃል ። ነገር ግን አብዛኛዎቹ ተማሪዎች በካሽ ስለከፈሉ እና ለአሰራር እንድያመች ለዚህ ወር ብቻ በካሽ እንድትከፍሉ እናሳስባለን።

ት/ቤቱ


                             

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

22 Oct, 16:12


ቀን:- 12/02/2017  ዓ.ም
ለተማሪ ወላጆች/ህጋዊ አሳዳጊዎች በሙሉ:-
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ጉዳዩ:-  የተማሪ '' Communication  Book'' ይመለከታል።
የተማሪ ''Communication Book'' ለተማሪዎች ሰነ ምግባር እና ውጤት ክትትል ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳለው ሳይታለም የተፈታ ህልም ነው:: ስለዚህ ያልወሰዳቹ ወላጆች እስከ  ዓርብ፣ ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም ድረስ ከት/ቤቱ ግምጃ ቤት (Store) እንድትወስዱ።

                              ት/ቤቱ

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

21 Oct, 16:31


ቀን:- 11/02/2017  ዓ.ም
ለተማሪ ወላጆች/ህጋዊ አሳዳጊዎች በሙሉ:-
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ጉዳዩ:- የከስዓት የማጠናከሪያ ጥናትን ይመለከታል።
የከስዓት የማጠናከሪያ ጥናት በት/ቤታችን መስጠት እንደጀመርን ይታወቃል:: የጥናቱ መርሐ ግብር እንደሚከተለው  የሚሰጥ ሲሆን  ፍላጎት እና አቅም ያላችሁ ወላጆች የጥናቱ ተጠቃሚ እንድትሆኑ የአክብሮት ግብዣችን ነው ።
የሚያጠኑበት ቀን :- ከረቡዕ ውጪ በሳምንት 4 የት/ት ቀናት::
ስዓት ከ 9:40 -  11:00 ( በቀን 2 ስዓት )
ወርሐዊ የጥናት ክፍያ 600 ብር:: ማለትም 18 ብር  ሒሳብ በአንድ ክፍለ ጊዜ።
በጥናቱ ሚሰጡት የት/ት ዓይነት:-
👉ከ 1ኛ -5ኛ ክፍል :-
       🔶ሒሳብ         🔶አ/ሳይንስ
       🔶 English   🔶 አማርኛ
👉 7ኛ ክፍል :-
       🔶 Math       
       🔶 አማርኛ
       🔶 English        
       🔶 Citizenship
       🔶  Gs
       🔶  Social Studies
የጥናቱ አሰጣጥ ስርዓት  ክለሳ፣የአጠናን ዘዴ፣ገላፃ ፣የክፍል ስራ ፣የቤት ሰራ እና እርማት ተጠቃሽ ናቸው።
   
                              ሰናይ ጊዜ!

                              ት/ቤቱ

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

21 Oct, 15:44


ውድ ወላጆች/አሳዳጊዎች ከላይ የሚደረብ ጃኬት(Old school) በተለያዩ ጊዜያት ስትጠይቁን ለነበራችሁ ምዝገባ ፈፅመን ቶሎ የምናስመጣ ስለሆነ የምትፈልጉ 900 ብር በመክፈል እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

20 Oct, 16:09


ቀን:- 10/02/2017  ዓ.ም
ለተማሪ ወላጆች/ህጋዊ አሳዳጊዎች በሙሉ:-
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ጉዳዩ:-  የ4ዮሽ ውል ስምምነትን ይመለከታል::
የተማሪዎች ውጤት ለማሻሻል፣ ለመገምገም እና የባለድርሻ አካላት አቅም ለማስተሳሰር የአራትዮሽ ውል ስምምነት ተፈጻሚ ለማድረግ የመፈራረሚያ ሰነድ እንደላክን ይታወቃል። በመሆኑም ዝርዝር መረጃውን በሚገባ በማንበብ በተማሪ እና በወላጅ ተፈርሞ ለነገ ሰኞ፣ ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም እንዲላክልን::
ማሳሰቢያ:-
👉 1ኛ ክፍል የ2016 ዓ.ም በቁጥር ገላጭ የሆነ ውጤት ስለሌለው  ምንም ነገር አይሞላም :: ለ2017 ዓ.ም የሚማርዋቸው የት/ት ዓይነት ወጤት ብቻ ይታቀድ።
👉 ከ 2ኛ-8ኛ ክፍል ደግሞ የ2016 ዓ.ም የዓመቱ ውጤት ቀጥታ በመገልበጥ ለ2017 ዓ.ም ዕቅዳቸውን ያስቀምጡ።
                              ት/ቤቱ

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

18 Oct, 15:35


ቀን:- 08/02/2017  ዓ.ም
ለተማሪ ወላጆች/ህጋዊ አሳዳጊዎች በሙሉ:-
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ጉዳዩ:- የቅዳሜ የማጠናከሪያ ትምህርትን ይመለከታል።
የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል የማጠናከሪያ ት/ት ጥቅምት 02 እንደጀመርን ይታወቃል:: ስለዚህ ሁሉም ተማሪዎች መማር ስላለባቸው በስዓታቸው እንዲገኙ በጥብቅ እናሳስባለን።
ማሳሰቢያ:-
መግቢያ እሰከ 2:00 ስዓት
መውጫ 7:00
መቅረት ሆነ ማርፈድ በጥብቅ የተከለከለ ነው::
👉 የክፍያ አከፋፈሉ ሰርዓት የባንክ ሲስተም ሂደቱ ስላልተቋጨ ለነገ ት/ቤት በካሽ መክፈል ተችላላቹ።
👉 የትራንስፖርት ፈላጊ ወላጆች በሚመለከት በቀጣይ መፍትሔ እስኪያገኝ ለነገ የራሳችሁ አማራጭ በመውሰድ ተማሪዎቻችንን የጥናቱ ተጠቃሚ እናድረግ።



                              ት/ቤቱ

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

12 Oct, 14:59


የምስጋና መልዕክት!
🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ጥሪያችን አክብራችሁ በዛሬው ዕለት ጥቅምት 02/2017 ዓ.ም  በልጆቻችን ጉዳይ ለመወያየት የመጣችሁ ወላጆች ከልብ እያመሠገንን የተለዋወጥናቸው ገንቢ ሃሳቦች ደግሞ  የየድርሻችን በመውሰድ እና ወደ መሬት በማውረድ በያዝነው  የት/ት በጀት ዓመት ስኬታማ እንዲሆን የሁላችን ከፍተኛ ርብርብ ይጠይቃል።

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

11 Oct, 18:21


ለማስታወስ፡ ውድ የጆይንት ቪዥን ሰክሰስ አካዳሚ ተማሪ ወላጆች ነገ(02/02/2017) እንድንገናኝ ደብዳቤ መላካችን ይታወቃል ስለዚህ ጠዋት 2:30-6:00 ልጆቻችሁ ባሉበት ግቢ በመገኘት በተማሪዎ ባህሪና ውጤት መሻሻል ላይ ስለምንነጋገር በሰዓቱ እንድትገኙ በአክብሮት ጠርተንዎታል፡፡ መቅረት አይቻልም፡፡

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

09 Oct, 11:18


ቀን:- 29/01/2016 ዓ.ም
ለተማሪ ወላጆች/ህጋዊ አሳዳጊዎች በሙሉ:-
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ጉዳዩ:- የት/ት ክፍያ ኮድን ይመለከታል።
በመጀመሪያ ለእርሶ እና ለቤተሰብዎ ሰላምታ እናቀርባለን፡፡ በመቀጠልም እንደሚታወቀው የተማሪዎች ወርሃዊ ክፍያ የሚከፈለው ወር በገባ ከ1 እስከ 10 ባሉት ቀናቶች ሲሆን ከነዚህ ቀናቶች በኋላ ለክፍያ የሚመጡ ወላጆች በውሉ መሠረት የቅጣት ስርዓት ተግባራዊ እንደሚሆን በምዝገባ ወቅት ተስማምተናል፡፡

በመሆኑም የልጅዎትን የት/ቤት ክፍያ ወር በገባ እስከ1- 10 ካልተከፈለ ከ11 ጀምሮ በየቀኑ ብር 30.00 /ሰላሣ ብር/ ቅጣት እንደሚኖር እያሣወቅን በወቅቱ ክፍያውን እንድትከፍሉ ከወዲሁ ለማሣሰብ እንወዳለን፡፡
የተማሪ መክፈያ ኮድ ከ 1ኛ-8ኛ ክፍል ከዚህ በታች ተልከዋል::

                              ት/ቤቱ

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

04 Oct, 04:12


ፈጣን መልዕክት!
እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !
ነገ ከሰዓት በኋላ በኢሬቻ በዓል ምክንያት ትራንስፖርት ሊኖር ስለማይችል(ስለሚዘጋጋ) ትምህርት ግማሽ ቀን ብቻ ይሆናል፡፡

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

04 Oct, 04:12


ዓርብ፣መስከረም 24 ፣2017 ዓ.ም
ት/ት እስከ 5:30 ስለሆነ በጊዜ መጥታችሁ ልጆቻችሁ እንድትወስዱ።
ት/ቤቱ

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

01 Oct, 16:32


ለተማሪ ወላጆች/ህጋዊ አሳዳጊዎች በሙሉ:-
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ጉዳዩ:- የመንግስት መፅሐፍን ይመለከታል።
👉  የ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ግቢ ከ2ኛ፣7ኛ እና 8ኛ ክፍል ውጪ የመጣው መጽሐፍ ስላለቀ  ያልገዛችሁ ወላጆች የመጽሐፍ ዋጋ ቅድመ ክፍያ ከ መስከረም 24 - ጥቅምት 08/2017 ዓ.ም ድረስ ት/ቤት መጥታችሁ በካሽ ክፍያ እድትፈፅሙ በአክብሮት እንጠይቃለን።


                              ት/ቤቱ

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

30 Sep, 15:37


ጉዳዩ:- የት/ቤት ሰርቪስን ይመለከታል።
በዛሬው ቀን የ አጃምባ መስመር የምትኩ ሰርቪስ ተጠቃሚዎች ተፈጠረው የትራንስፖርት መጉላላት ይቅረታ እየጠየቅን የተፈጠረው ክፍተት በንግግር ስለተፈታ ከነገ ጠዋት ( 21/01/2017) ጀምራቹ በተለመደው ቦታ እና ስዓት በመገኘት የአቶ ምትኩ ሰርቪስ መጠቀም የምትችሉ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።
ት/ቤቱ