ቤተ-ግጥም እና ፍቅር

@betagitim


ግጥም '''ስሜቶች ከተደበቁበት ወረቀት ላይ ሰፍረዉ እልፍ ትዝታዎች ከተበተኑበት ተሰብስበዉ የሚቀመጡበት የጸሃፊያን ሀሳብ ማረፊያ የአንባቢያን መጽናኛ ነች''።
በዚ ቻናል @betagitim
ግጥሞች🔥💌
ደብዳቤዎች✍️💌 ያገኛሉ።
ሃሳብ እና አስተያየቶን በዚ 👇👇👇
ያናግሩን @dawit_wegayew

ቤተ-ግጥም እና ፍቅር

21 Oct, 15:09


"ኦሪት ጨርቅ ዘ መጣል"
.
ሃድ ባር
.
.
ከሚወደኝ ጆሮሽ
ከምትወጂው ቧልቴ
ከሳቆችሽ መኃል
"እብድ ነህ" ስትዪኝ
በስሱ በስሱ...ተጀመረ እብደቴ
.
.
ምንም አልገረመኝ!
ላ'ለም ልቡን ዘግቶ..ባንድ ሰው ታዛ ስር ለቆመች ህይወቱ
'እብደት' ማለት ምንም...ጨርቅ መጣል ከንቱ!
.
እኔን መች ደነቀኝ?
"ማበዱ ነው" ሲሉ
..ትናንቴን የሚያውቁ
እርቃን ልብ ላይሸፍን
ወግድ! ብዬ ነበር..
ምን ሊረባኝ ጨርቁ?
.
.
ይኸው!
"አንተ እብድ" ስትዩኝ
አሜን ብዬ እንደኖርኩ..ቅንጣት ሳልከፋ ራሴን ሳልሰስት
ጤናዬን ገብሬሽ..ለደስታሽ ስለፋ
.
ያሳደገኝ ሳቅሽ...
ያሳበደኝ ሳቅሽ...
ለታዛቢ ሰጥቶ...ሳያኖረኝ ጠፋ።
.
.
ያኔ ራሴን አየሁ..!
ከሳቅሽ ባሻገር..ሌላ ዓለም እንዳለ ለፈገግታ ብቻ ጥርስ እንዳልበቀለ
ለመንከስ ..ለመብላት..ለመስበር.. ለማድቀቅ..እንደተተከለ
.
.
ያኔ ራሴን አየሁ!
ሰውኛ ስሜትሽ...ወረት ከወለደ
ቁምነገሬን አጥቶ
ተራማጅ ልቡናሽ እንደተሰደደ
.....ጥሎኝ እንደሄደ
.
.
ይኸው...ከዛን ጊዜ
.
ስክነት እርቃን ወጣ
.....ጤንነት ተነነ
ነገን ማለም ቀረ...ትዝታሽ ገነነ
ናፍቆትሽ ገነነ....ሽንፈቴ ጀገነ!
.
ከብቻነቴ ጋር...ሳቅሽን እያሰብኩ
መሳቅ.... መሳቅ
...መሳቅ...መሳቅ ብቻ ሆነ
.
.
እንኳን ተሳካልሽ!
እንኳን ደስ አላችሁ!
ትንቢት ተፈጸመ
እብደት ምሉዕ ሆነ።

@betagitim
@betagitim

ቤተ-ግጥም እና ፍቅር

20 Oct, 15:26


ሰክን ሀሳብ ስክን ማፍቀር
የሷ አመል የኔም አመል ነበር
ፍቅር ሲስብ የምድር ሰዉ
እሷን ሳበ አምላክ ፍቅርን መስላዉ


ተለየቺዉ አላመነም..ፍቅሩ አልበረረችም
ትመለሳለች የምድሩን ነገር አልጨረሰችም
ትመጣለች ..ታየዋለች ናፍቆቱን ተረድታ
አለዉ ትለዋለች ተመለሳ መጥታ!!!???
 
ጥያቄ...!!!???
ተነስ አለዉ እግዜር!!??
        ክንፍ ልስጥህ ትበራለህ??
ከሰማይ ወጥትህ ....
         ናፍቆትህን ትወጣለህ!?
ወይስ ዛሬ ማታ
   ነፍስህን ከስጋህ ለይቼ
     ላሳይህ እሷን አንተን ከሰማይ አዉጥቼ!??
  የቱን መረጥክ!!!??
     አንዱን በላ ወይ ስክን በል!?
  በፍቅርህ ዉስጥ እሷን ምስል
  እሷን አፍቅር፣
ከከፍታዉ ከሰማዩ እንድትበር!!!

ተጻፈ ✍️ በዳዊት


🗣ናትናኤል (ያላለቀ ሀሳብ)



@betagitim
@betagitim

ቤተ-ግጥም እና ፍቅር

20 Oct, 14:50


#የዘንድሮ_ፍቅር

አንቺ መቼ ገባሽ…!?
በኔ እንደበረታሽ

ወድሃለው ስትይ እኔም የማልልሽ
አፈቀርኩህ ስትይ መልሱን የማልነግርሽ
የስሜቴን ግለት አፍኜው በውስጤ
እንዳልተነካ ሰው አርፎ መቀመጤ
አይደለም በጭራሽ ሳልወድሽ ቀርቼ
የማልነግርሽማ ነው ገንዘብ አጥቼ
አፌን የለጎምኩት ስሜቴን ያነቅኳት
ላፍ መፍቻ የሚሆን ስለሌለኝ ነው ሀብት
በባዶ ሜዳ ላይ አፈቀርኩሽ ብልሽ
አውቃለው ጠንቅቄ ቅር ይለዋል ልብሽ

ለዚ እኮ ነው ውዴ…
                   ባንቺ መወደዱ ያላረገኝ ዘና
የዘንድሮ ፍቅር…
     ገንዘብ ካልደገፈው ችሎ አይቆምምና።
💔
   
✦✦sʜᴀʀᴇ✦   @betagitim
                           @betagitim

ቤተ-ግጥም እና ፍቅር

20 Oct, 14:48


ገጣሚ አታፍቅሪ

        ገጣሚ

ከሴት መተኛት ምንም
ስሜት አይሰጠው ለእርሱ
ከቃል ነው እንጂ
ከሴት ፍቅር አይዘው እርሱ
        
       ስለዚህ

አፈቀርኩሽ ወደድኩሽ
ብሎ ቢያወራልሽ
ከሺህ ቃላት ወስዶ
እንድ ቃል ቢነግርሽ
እንዳትሰሚው እርሱን
እንዳታደንቂ ቃላት አጠቃቀሙን

       ምክንያቱም

ላንቺ ቃል እምነት ነው
ላንቺ ቃል ፍቅር ነው
ላንቺ ቃል ተስፋ ነው
      
        ግን

ቃል ለእርሱ ቀላል ነው
በቃ ዝም ብሎ
ፊደል መመስረት ነው

      ገጣሚ ስንታየው ታገሰ

@betagitim
@betagitim

ቤተ-ግጥም እና ፍቅር

20 Oct, 14:40


አለኝ
ልብ የለሽም አለኝ
ራሱን ጀግና አድርጎ እኔን ሊኮነነኝ
ልብማ
ልብማ እንደኔ የታደለ
እንደእኔ በፈገግታ ሀዘኑን ሸፍኖ ችሎ ያቻቻለ
ሀዘንን እያጠፋ ደስታን የሚያስነብብ
እየደማም ቢሆን በፈገግታ የሚያብብ
መቼ ተፈጠረ
ልብማ
ልብማ አለኝ
እየሳቀ ሚያለቀስ እያለቀሰ ሚስቅ
እየሞተ ኖሮ ነገን የሚናፍቅ

*                    *                *
✍️ስመርነሃ

*                   *                 *
@betagitim
@betagitim

ቤተ-ግጥም እና ፍቅር

16 Oct, 19:28


✍️እንደልቡ😂

@betagitim
@betagitim

ቤተ-ግጥም እና ፍቅር

16 Oct, 06:26


(የገጣሚ ክፋቱ)

ገጣሚ ክፉ ነው
ተለየሁኝ ብሎ መች በቋት ይለፋል
ፍቅርን አንቅሮ በብዕር ይተፋል
ብያት ነበር ያኔ
ይሄው ስትለየኝ፣ ቀለም በጠበጥኩኝ
ተለየችኝ የሚል፣ አስር ግጥም ፃፍኩኝ
(ተፋኋት መሰለኝ)
ከልቤ ከረጢት እንባዬ አለቀ
የነከርኩት ቀለም ከእጄ ደረቀ።


(እንግዳዬሁ ዘሪቱ) 🔥🔥🔥🔥

ገጣሚ አይደለሁም👆👆

@betagitim

ቤተ-ግጥም እና ፍቅር

15 Oct, 20:00


#ውሻሽን_እሰሪው

አንችን ስመለከት እንቅፋት መትቶኛል
መምጫሽን ስጠብቅ ፀሐይ አጥቁሮኛል
ባጥር ላይሽ ብዬም ውሻችሁ ነክሶኛል
          ያውም ክፉ ውሻ...
መምጫው ሳይታወቅ አድብቶ ሚያጠቃ
ገዳይ መሬት ጥሎ የሚለውስ ጭቃ
እችን ስንጥር እግሬን ከአፉ አስገብቶ
አንከባሎኝ ሄዷል እመሬት ጎትቶ
      ውሻሽን እሰሪው...
ይህን ሀይለኝነት ከማንስ ተማረ አሳዳጊው አንቺ
አትንኩኝ የምትይ አመል የነፈገሽ ለሰው ማትመቺ
         @betagitim
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
      አቤል ሽመልስ

ቤተ-ግጥም እና ፍቅር

15 Oct, 19:51


(እኔማ ምስኪኑ)

ከእድልሽ ለመኜ ከእድሌ ላይ ጠፋው፤
እየተከተልኩሽ እንድትርቂኝ ለፋው፤
ጀንበርሽን ልጽፍ ዘላለሜን ደፋው፤
ንጹ ናት እንዲሉሽ ራሴ ላይ ተፋው።
ቅሪብኝ እንድልሽ ከየት ይምጣልኝ አፍ፤
ድጌ እያፈቀርኩሽ ስቆም ካንቺ ደጃፍ።
.
ክርስቶስ ጉዴን አላየህ
.
ስላንተ ላስተምር ቆሜ ፥ ደረቷን እያመለኩኝ፤
እንኳንስ ለዛ ገነትህ ፥ ለሲኦል የማልሆን ሆንኩኝ።
.
ክርስቶስ ጉዴን አላየህ
.
ወደሷ እንደምዞር አንተን ልለማምን፤
ብዬ እንደምጠይቅ ፥
ጀነት ወድያ ይቅር እሷ ካለች ለምን?
(ደሞስ)
አላህ ተቆጥቶ ፍጥረታትን ቢያቆም ፥ ተፈጸመ በሚል ቁንጽል ረቂቅ ቃል ፥ እርጋታውን ቆርሶ፤
ለኔ እንደሚቀለኝ ፥ እሷን ይዞ መቆም ፥ ሰማይ ምድር ፈርሶ።
አያውቅም ምዕመን!፤
ረፍት እንደሌለኝ መለኮትን ክዶ እሷን እንደማመን።
ይህን የዘመን ቃል መች ታውቃለች እሷ?፤
ቀልድ እየመሰላት ትስቃለች እሷ፤
አወይ አወይ አወይ አወይ ደሞ ጥርሷ።
ጥርሷ..
ባህር ተሞርክዞ፤
ንፋሳትን አዝዞ፤
ሰማይ ሊኮረኩር ፥ እላይ ታች ይወጣል፤
ስትስቅ ያያት ቀን ፥ ምስጋናውን ትቶ ፥ ሚካኤል ይስቃል።
አወይ አወይ ጥርሷ...
እንደ ባተሌ ሴት ፥ ማድቤትን የሚሞላ፤
እንደ ጌታ መሶብ ፥ ያምስት ገብያ ጉብል ፥ አጥግቦ የሚያበላ፤
ውበትን የሚበልጥ ፥ ሳቋ ግዜን ያዛል፤
ስትስቅ ፥ ያያት ቀን ፥ ሳጥናኤል ይስቃል።
(አወይ አወይ ጥርሷ)


@betagitim
🌍 @betagitim

ቤተ-ግጥም እና ፍቅር

15 Oct, 19:25


ተራራዉ የታለ

ፍርሽራሹ እኔን ለማነጽ ለመገንባት
የትላንቱን ፍቄ ዛሬዬን ለመስራት
ግንቡን ለመገርደስ
ትላንቴን ለማፍረስ
እርቃኔን ተጓዝኩኝ
ከሰዉ ተነጠልኩኝ
በጊዜ ሀዲድ
ኦና በሆነዉ መንገድ
ያስጓዘኝን ህልሜን
ጥዬዉ የድሮዉን ስሜን
ቅሉ ግዙፍ
በጊዜ ንጣፍ
ከተሰናዳው ለመጓዝ
በትላንቱ እኔ መዘዝ
ድቅድቁን ሲኦሉ ጨለማ
ተስፋ...ህልሜን ሳይቀማ
ልጓዝ ልሂድና
ከመንገዱ ብዬ ቀና
ሊጥልኝ ያለዉን ልጥል
ከሱ ሀሳብ በመገለል
ከተንሳፋፍኩ
ከኮበለልኩ
ከከፍታዉ ከወጣው
ጥልቁን ደስታ ለማግኘት ስል
እኔነቴ ከማማው ከተስቀለ
ቆም ብዬ ታድያ ተራራው የታለ።

✍️ዳዊት

🤗ጨዋ_ግጥም

@betagitim
@betagitim




[  ]

ቤተ-ግጥም እና ፍቅር

14 Oct, 20:46


#በእንባ_የራሰ_ፍትፍት

ቀበሌ ሂድና ፥ ድህነት አስመስክር
ይላል አሉ ሃብታም ፥ መፅውቶ ሲሰክር

እማኝ ጥራ ይላል ፤ ቀበሌ በተራው
እማኙ ሲመጣ ፤ ይንዛዛል ወረፋው

           አሹቅ ከጨበጠ...
ከነዳይ መዳፋ ላይ ፥ ሹም እየዘገነ
"ድሃ!" መባል እንኳን ፥ ገንዘብ ላለው ሆነ።
         @betagitim
    ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲            
   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ
     በርናባስ ከበደ

ቤተ-ግጥም እና ፍቅር

14 Oct, 20:36


የሴት ልጅ ስህተቷ
         ልቧንና መልኳን አለመለየቷ
ወንድ ልጅ ስህተቱ
       ከልቡ አስቀድሞ ቀበቶ መፍታቱ
ሆኖ ነዉ እዉነቱ
ማታ የተጋቡት ሲነጋ ሚፋቱ




@betagitim
@betagitim

ቤተ-ግጥም እና ፍቅር

14 Oct, 20:34


#ሰማዩ_ያንቺ_ነዉ

ሰማይ ክራር ሁኖኝ
   የትዝታ ቅኝት
የልቤን መስመር
   ተስፋዉን ለማየት
የልቤን ዜማ ስልተ ምቱን
ስዉር ፈቺ ቅኔ ቤቱን
ስቃኘዉ ሚታየኝ ጭራሽ ሳላስብሽ
ስማዩን ሳይ ሚታየኝ ያ መልክሽ
ቀና ዋልኩኝ ብዬ ለማመስገን ቀና ስል
ሰማዩ ተዉቧል ባንቺ ገፀ ምስል
ኪዳን ኑሮበት ሲማስን አይኔ ቀና እያለ
ፊትሽ ያይና ንጋትን ከሌት ለሱ ተመሳሰለ
ፍቅር...
የተጻፈለት ..የተባለለት ሁሉ አንዱም መች ገለጸዉ
የቀንን ብረሃን ወደ ሌት የቀየረዉ
ደሞም ሲመጻደቅ
መች ደርሰዉ ይልና
     ልብ ና አፍ አራርቆ
ሲኦል ሲልክ ነፍስን ነጥቆ
ሲያሻዉ የከንፈር ድግስ አስድግሶ
ጽዋ አርጎ ገነት ሲጥል አመንኩሶ
ወደ እሷ በሚል መንፈስ
በመስቀል ተመቶ በጸበል አያስፈዉስ
በአላ በረቢ በዱዓ በእጣን
የማይለቅ ፍቅር ማለት ሰይጣን
ፍቅር ቃሉን ትርጉሙን ሰዉሮ
በቁም ያለ ሰዉን ያሳያል ልብ ዉስጥ ቀብሮ
ነፍስን ጠፍሮ አስሮ ይከርምና
ቃላት ይለግሳል ስለ እርሱ ለሚያጠና
በእንቺነትሽ በኩል በእኔነቴ ግድም
ተሰምሮ አልተቀመጠም የፍቅር ትርጉም
ለአለም አሸን  ሁኖ ፍቅር መገለጫዉ
እኔ ቃል ሳላባክን ልቤ አይጭነቀዉ
ሳልሰጥ ለስቃይ ሃሳቤን ሳልበተን
ፍቅር ማለት የሰማይና የአንቺ አንድ መሆን።


✍️ዳዊት


✌️
@betagitim
@betagitim
@betagitim

ቤተ-ግጥም እና ፍቅር

10 Oct, 20:48


ጎራውን ሙሉ -
የሞት መልኣክ ስለከበበው፤
ውበት ጎደለው፤

ባንዲት አመሻሽ - ወጣት አረጀ፤
የትርጉም እጦት - ብዙ ሰው ፈጀ፤

የሀዘን ሸክም - ልቤን አዛለው፤
የማየው ሁሉ የቁም-ሙታን ነው፤

ከጓደና ጋር እግሬን አዋደድኩ፤
በድን ለመሸሽ ወዴትም ኳተንኩ፤

ይህን ጊዜ ነው፤
አድጦኝ ስወድቅ ሳቅሽ የታየው፤
በከተማዬ ውበት የናኘው፤

ያ'ዛኝ ከንፈር ላይ - ፈገግታ አረፈ፤
ሞት ተቀዘፈ።

ጎራውን ሁሉ - ብርሃን አደነው!!
በድኑን ሁሉ... ሳቅ ወጋገንሽ - ሕይወት አደለው፤

ካ'ይኖችሽ አረፍኩ - ልቤ ሸክሙን ትካዙን አጣ፤
ወትሮም ሲጨልም -
ሙት ፈዋሽ መሲህ... ሆኖ እየመጣ፤
ውበት ብቻ ነው - ነፃ 'ሚያወጣ።

@ጋሻው የኋላሸት (ዘቢደር)
📥

❤️🥰

♡ ㅤ  ⎙ㅤ  ⌲        ✉️   
ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
jᵒⁱⁿ⇝ @betagitim         

 
🌍
      

ቤተ-ግጥም እና ፍቅር

10 Oct, 19:44


[••ዕድሜ ለሙዚቃ፥
ዕድሜ ለሙዚቃ፥
ካንድ ክር ዕልፍ ድምጽ እየተወጠነ፥
ብቸኝነት ጠፍቷል ደመና እየኾነ፡፡••]
[ኤፍሬም ሥዩም]

@betagitim

ቤተ-ግጥም እና ፍቅር

10 Oct, 19:33


@betagitim

ቤተ-ግጥም እና ፍቅር

10 Oct, 19:12


ቅማል×ማፍቀር ያማል=😁

@betagitim
@betagitim

ቤተ-ግጥም እና ፍቅር

05 Oct, 15:02


ናፍቀሺኛል ብዬ

ሰማይ እየሰፋዉ
እሳት ከአፌ እየተፋዉ
ምድርን ሳተራምስ
ዝናብ ሁኜ ስፈስ
ናፍቀሺኛል ብዬ...
ሙዚቃ ስሆን የሌለዉ ዜማ
ራቁቴን ሁኜ ስገባ ፖርላማ
ናፍቀሺኛል ብዬ...
ንጣፍ ሁኜ መንገድ እንድትራመጂብኝ
ወንበር ሁኜ እንድትቀመጪብኝ
ተኝቼ እስክስታ ስመታ
በህልሜ ህልምሽን ስፈታ
ካህን ሁኜ እኔዉ ራሴ
ፀበል ረጨዉ አንድን መነኩሴ
በቅዳሴ መሃል ስምሽን ጠርቼ
ኢግዚኦ አስባልኩኝ ቅዳሴዉን ትቼ
ናፍቀሺኛል ብዬ
ባለስልጣን ሁሉ ሰብስቤ ስብሰባ
ስላንቺ እያወራዉ እንባዬን ሳነባ
ናፍቀሺኛል ብዬ...
ኢቲቪን ስላንቺ መግለጫ አስወጣዉ
የቤተ-መንገስቱን በር ቆለፍኩት አዘጋዉ
ናፍቀሺኛል ብዬ..
ከቄሱ ጋር ጠጥተን ሰከርን
ከጠንቋይ ጋር ቅዳሴ አስቀደስን
ባህርን ከፍዬ ስደተኛ አሻገርኩ
ሴይጣንን ከእግዜር አስታረኩ
ናፍቀሺኛል ብዬ..
ራስ ዳሽንን ገፍቼ አመጣዉት ሀረር
ኤርታሌን አደረኩት እጅግ ጥልቅ ባህር
ናፍቀሺኛል ብዬ..
መርካቶ ጥቅጥቅ ጫካ ሆነ
ቴዲ ዮ ቤተ መቅደስ ገብቶ ክህነት ተካነ
ናፍቀሺኛል ብዬ..
ዳይኖሰር ዳግም ተፈጠረ
ሬሳ መቅበር ቀረ
የዛፍ ቅጠል ተቆርጦ
      ይ'በላ ጀመረ
ጆ ባይደን በአብይ አህመድ
   በኢትዮጵያ ታሰረ
ናፍቀሺኛል ብዬ..
መድፍ አስተኩሼ
መንግስትን ሳስቆጣ
በሰይፉ መላጣ ላይ
  ስጫወት ገበጣ
ናፍቀሺኛል ብዬ...
   ጉንዳን ሳክል ማንም እየረገጠኝ
    ከማንም ጫማ ተጣብቆ ያስቀረኝ
ምርጫ ሳይካየድ ምርጫ አሸንፌ
በሬ ሳይታረድ ቆዳዉን ገፍፌ
ናፍቀሺኛል ብዬ...
  አለሁኝ ይህን ሁሉ አልፌ።

✍️ከዳዊት
📥



♡ ㅤ  ⎙ㅤ  ⌲        ✉️   
ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
jᵒⁱⁿ⇝ @betagitim         

 
🌍
      

1,464

subscribers

283

photos

79

videos