Book for all Ethiopia @bookfall Channel on Telegram

Book for all Ethiopia

@bookfall


Book for all Ethiopia (English)

Welcome to 'Book for all Ethiopia'! This Telegram channel is dedicated to all book lovers in Ethiopia who are looking for a place to discover new reads, share their favorite books, and engage in discussions about literature. Whether you're interested in fiction, non-fiction, self-help, or poetry, this channel is the perfect place for you. 'Book for all Ethiopia' aims to create a community of readers who are passionate about expanding their knowledge and exploring new worlds through the pages of a book. From classic novels to contemporary bestsellers, there is something for everyone on this channel. Join us today and be a part of the literary journey with 'Book for all Ethiopia'!

Book for all Ethiopia

19 Dec, 18:11


አብርሆት ቤተ-መጻሕፍት የአባልነት ምዝገባ ተጀምሯል።

ለመመዝገብ ይህን ቅደም ተከተል ይከተሉ :-

1. በ
www.abrehot.org.et/register/ በመግባት የምዝገባ ፎርሙን ይሙሉ

2. ፎርሙን እንደጨረሱ ወደ ክፍያ ገፅ ይወስዳቹሀል ፣ አመታዊ የአባልነት ክፍያ በቴሌብር ወይም በንግድ ባንክ በኩል በቀላሉ መክፈል ይችላሉ።

3. ቅድመ ተከተሉን እንደጨረሱ አባልነቶ አፕሩቭ ይሆናል።

ቅድመ ተከተሉን ከጨረሱ ቡሀላ በ15 ቀን ውስጥ ዲጂታል የአባልነት መታወቂያ በኢሜይል ይደርሶታል።


አባል ሲሆኑ የሚከተለውን ጥቅሞች ያገኛሉ :-

1. መፃህፍትን በነፃ መዋስ።
2.ለ12 ተማሪዎች ነፃ የትምህርት እድል ሙሉ ወጪ በመሸፈን።
3. የጋራ የውይይት ክፍሎችን በኦንላይን ማግኘት።.
4. ከ 1.5 ሚልየን በላይ ጆርናሎች እና የመመረቂያ ፅሁፎች በቀላሉ በኦንላይን ማግኘት።
5.በቶሞካ ትኩስ መጠጦች ላይ  35% ቅናሽ።

ብርሀን ለኢትዮጵያ 🇪🇹

Book for all Ethiopia

20 Apr, 17:59


የሽንታችን መልክ ስለጤናችን ምን ያመላክታል? ↔️

⚪️🟡 🖌 ንፁህ ዉሀማ ወይም ፈዛዛ ቢጫ - በቂ ዉሃ ሰዉነታችን ሲያገኝ, ጤናማ መልክ ነዉ!!

🟧 🖌 ደማቅ ቢጫ - በቀን ዉስጥ የምንጣዉ ዉሃ ሲያንስ!!

🔴 🖌 ቀይ - ደም ሽንት ዉስጥ ሲቀላቀል ፣ የተመገብነው ምግብ (እንደ ቀይ ስር፣ ወይን ፍሬ)፣ የወሰድነዉ መድሀኒት (እንደ ቲቢ መድሀኒት)!!

🟠 🖌 ብርቱካናማ - የጉበት ህመም ሊኖር አንደሚችል ያመላክታል!!

🟢🟣 🖌 አረንጓዴ ወይም ወይነጠጅ - የሽንት ኢንፌክሽን ያመላክታል!!

✒️ የደፈረሰ ሽንት እና ያልተለመደ ሽታ የኢንፌክሽን ምልክቶች ናቸዉ!!

ዶ/ር ፍጹም ሰለሞን

የቴሌግራም ቻነል: https://t.me/drfitsumsolomon

Book for all Ethiopia

18 Apr, 18:54


#ፕሮስቴት

📌 ከሽንት ፊኛ በታች የሚገኝ እጢ ነዉ!!

📌 ወንድ አጥቢ እንስሳት ላይ ብቻ ይገኛል!!

📌 ስራዉም የዘር ፈሳሽ ማመንጨት፣ በግንኙነት ጊዜ የዘር ፈሳሽ ወደ ዉጪ እንዲወጣ መርዳት ነዉ!!

📌 ፕሮስቴት ላይ ሊያጋጥም የሚችል ህመም ኢንፌክሽን፣ መጠኑ መጨመር ወይም ካንሰር ነዉ!!

📌 ምልክቶቹም የሽንት ጉልበት መቀነስ ፣ የሽንት መቆራረጥ፣ ለሊት ከእንቅልፍ ደጋግሞ ለሽንት መነሳት፣ ቀንም የሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት ናቸዉ!!

📌 እነዚህ ምልክቶች ካሎት ሐኪም ያማክሩ!!

📌 ህክምናዉም በሚዋጥ መድሀኒት ወይም ቀዶ ህክምና ነዉ!

ስለፕሮስቴት ተጨማሪ መረጃ ወደፊት ይቀጥላል!! ➡️➡️➡️➡️

https://t.me/drfitsumsolomon

ዶ/ር ፍጹም ሰሎሞን

Book for all Ethiopia

03 Apr, 05:46


*ስለምንታይ አብዚ ዝረከብካኒ ይመስለካ?- ለምን እዚህ ያገኘኸኝ ይመስልሃል?
-----------------------------------------

ማስታዎሻ: "የሰው የነፍስ ዋጋው ስንት ነው?" ለማለት ማስታዎሻ ትሁንልኝ፡፡ ዛሬ ላይ ቁጥር የሆነብን የአንድ ሰው ሞት በጀርባው የብዙ ሰዎችን የነፍስ ኩርፊያ ተሸክሟል፡፡ ከእናንተ አንደኛችሁን ባስቀይም ቢያንስ እናታችሁ/አባታችሁ እንደማሳዝናቸው እርግጥ ነው፡፡ ከአንድ ሰው ጋር ለማውራት ጊዜ ከተገኘ ብዙ ነገሮችን እንሰማለን፡፡

ዮሐንስ በላይ

Book for all Ethiopia

03 Apr, 05:46


ሺ ሰማኒያ [1080]

አንድ ቅዳሜ ቀን ጫማዬን ለማስጠረግ የሆነ ቦታ ቆሜ ሳለሁ አንድ መበለት እኔ ወዳለሁበት መጥተው ስባሪ ሣንቲም እንድጥልላቸው እጃቸውን ዘረጉልኝ፡፡

"ይቅርታዎትን? እዛች ቤት ይግቡና ቁርስ ይዘዙ፤ አብረን እንበላለን" አልኳቸው፡፡

እጃቸውን አየር ላይ እንደዘረጉ ዝም ብለው አዩኝ፡፡

"ጫማዬን አስጠርጌ እስክጨርስ የሚፈልጉትን አዘው ይጠብቁኝ" አልኳቸው፡፡

"ኧረ ብሩ ይበቃኛል" አሉ የሆነ አይነት ሳቅ እና መሽኮርመም እያሳዩኝ፡፡

ብሩን ብቻ የፈለጉ አይመስልም፡፡ ሳይጠራጠሩ፤ ምናልባት እረስቶት ባይመጣ ብለው የፈሩ ይመስለኛል፡፡

ለመሄድ ከተስማሙ በኋላ ዘወር እያሉ አንድ ሁለት ጊዜ ተመለከቱኝ፡፡

"ይቅርታ ትንሽ አፍጥንልኝ" አልኩ ጎንበስ ብዬ፡፡

ቀይር ብሎ ቆርቆረውን ከመምታቱ በፊት ጫማዬን ለመቀየር እግሬን ወደ ላይ ብድግ አደረግሁለት፡፡

"እሺ" አለና ቆርቆሮውን ኳ! አደረገው፡፡

ቁርስ የምበላበት ቤት እንደገባሁ ወደዚህ የላኳቸውን እናት በዐይኔ ፈለኳቸው፡፡ በእጃቸው ይዘውት የነበረውን ጥቁር ፌስታል ጭናቸው ላይ እንዳደረጉ በሩ አጠገብ ጭብጭ ብለው አየኋቸው፡፡

"ለምን ይሸከማሉ?" አንደኛውን ወንበር ወደእሳቸው ሳብ አደረኩና፤

"እዚህ ላይ ማስቀመጥ ይችላሉ" አልኳቸው፡፡

እቃውን እስቀምጠው ወደኔ ለማየት እንዲመቻቸው ትንሽ ዘወር አሉ፡፡

"ምን አዘዙ?"

"ምንም" አንገታቸውን አቀረቀሩ፡፡

"እሺ፡፡ . . . ፍርፍር ነገር ይሁን ወይንስ ቂጣ ነገር? ጨጨብሳ፣ ቅንጬም ከፈለጉ አለ"

"ቅንጬ ይሸጣል?" ገረማቸው፡፡

"አዎ አለ" አሁንም ትንሽ ተሽኮረመሙ፡፡

"ቅንጬ ይሁንለዎት?"

"እሺ!"

አስቸናጋጁን ጠርቼ ቅንጬ እና ጨጨብሳ እንዲያመጣልን ነገርኩት፡፡

"የፈጠነ! አንድ ሌላ ጨጨብሳ እና አንድ ቅንጬ" አለ አስተናጋጁ ድምጹን ከፍ አድርጎ፡፡ ከንግግሩ ጋር አብሮ የተበላባቸውን እቃዎች ለማንሳት ወደጠረጴዛዎቹ ይበራል፡፡

ምን ብዬ ወሬ እንደምጀምር ስለጠፋብኝ፡፡

"ልጅ አለዎት?" በጊዜው የመጣልኝን ጥያቄ አቀረብኩ፡፡

"የለኝም"

ጎንበስ ብለው ያደፈ ነጠላቸውን ማፍተልተል ያዙ፡፡

የማይሆን ርዕስ የመረጥኩ ስለመሰለኝ ቀጥዬ የምጠይቀው ነገር ሁሉ ነውር ሆነብኝ፡፡

"የሚጠጣ ምን ይምጣላችሁ?" አለ አስተናጋጁ አጠገባችን ቆሞ ቁልቁል እያየን፡፡

"ማዘር! የሚጠጣ ምን ይፈልጋሉ?"

"ምንም አልፈልግ፡፡ በልቼ ስጨርስ ቡና ልጠጣና አንድኛዬን በደንብ አድርጌ ልመርቅህ?" ንግግራቸው ውስጥ "እሺ በለኝ?" የሚል ልመና ነበረው፡፡

"አሺ፡፡ . . . ትንሽ ቆይተን ትኩስ ነገር እንጣለን" አልኩኝ፡፡ መጀመሪያ እሳቸውን ቀጥዬ እሱን እየተመለከትኩ፡፡

ወይዘሮ መብራት ርዕሶም ይባላሉ፡፡ ዕድሜአቸው ሰባዎቹ ውስጥ ይገመታል፡፡ ተወልደው ያደጉት ከአሥመራ ወጣ ብላ ያለች ትንሽ መንደር ውስጥ ነው፡፡

በቀይ ኮከብ ዘመቻ አስመራ ያለ አንድ ቡና ቤት ውስጥ ጽዳት ሠራተኛ ሆነው ይሠሩ ነበሩ፡፡ ቤቱ ብዙ የደርግ ወታደሮች ከሚያዘወትሩት እንደነበር በታሪክ ጭምር ይታወቃል፡፡

***
ልክ እንደዛሬው ቅዳሜ እረፋድ ላይ፤ ቤቱን አጽድቼ ቁርሴን ልበላ ቀጭ እንዳልኩ፤ አንድ የደርግ ወታደር በሩን ከፍቶ ወደ ውስጥ ገባ፡፡ ጥግ ላይ ሁለት መኮንኖችን ስለነበሩ ትንሽ ደንገጥ አለ፡፡ ለእነሱ ሰላምታ ካቀረበ በኋላ እጄን ይዞ ወደ ጓዳ ወሰደኝ፡፡
*
አስተናጋጁ አንድ የጀበና ቡና እና አንድ ሻይ ይዞልን መጣ፡፡
*
ወደ ውስጥ እንደገባን፤

"ሻለቃ ባሕሩ ተመቶ ሆስፒታል ገብቷል" አለኝ፡፡

"*ብህይወት አሎ ድዩ ሞይቱ?" አልኩት፡፡

"ደህና ነው፡፡ ወደ አዲስ አበባ ሊሄድ ስለሆነ ሊያገኝሽ ይፈልጋል" አለኝ፡፡ ተያይዘን አሥመራ ሆስፒታል ሄድን፡፡

የሚታከምበት ክፍል ስገባ፤ ገና በር ላይ እንዳለሁ አልጋው ላይ ቁጭ ብሎ አየሁት፡፡ በጣም ደስ አለኝ፡፡ እቅፍ አድርጎ ሳመኝና አልጋው ጠርዝ ላይ አስቀምጦ፡፡

"ቦርድ የምወጣ ይመስለኛል፡፡ አዲስ አበባ አብረን እንሂድ?" አለኝ፡፡

"አዲስ አበባ?!" በጣም ደነገጥኩ፡፡ እሱ ግን ፈገግ እያለ፤

"ከዚህ በኋላ ሚስቴ አድርጌሻለሁ" አለኝ፡፡

*
"አሁን እዚህ ያገኘኸኝ ለምን ይመስልሃል? ታናሽ እኅቴን ይዤ ከእሱ ጋር አዲስ አበባ መጣሁ "

*
ትንሽ ፈገግ ማለት ስጀምር ፊታቸው ጭፍግግ ሲል አየሁት፡፡ የህይወታቸው አሳዛኝ ክፍል ሊጀምር እንደሆነ ስለገባኝ ትንሽ ሰብሰብ ለማለት ሞከርኩ፡፡

"*ዕድል ወድ ሰብ ይገርምዩ" አሉ ጨርሰው ያስቀመጡትን ስኒ እንደገና ፉት እያሉ፡፡

"ይደግማሉ?" አልኳቸው፡፡ በጭንቅላታቸው ብቻ መለሱልኝ፡፡

***
አዲስ አበባ መኖር ከጀመሩ ሠላሳ አንድ ዓመት ሆኗቸዋል፡፡ ባለቤታቸው ከዛሬ አሥራ ሁለት ዓመት በፊት ሲሞቱ ያስቀመጡላቸው ምንም አይነት ጥሪት አልነበረም፡፡ ይባስ ብሎ ይኖሩበት የነበረው ቤት ከባለቤታቸው ወንድም ጋር የፍርድ ቤት ክርክር ገጠመው፡፡

*
ይረዳኛል ብዬ ስላሰብኩ ለባለቤቴ ጓደኛ ነገሩን በዝርዝር አጫወትኩት፡፡ የጠበቃ ብር እንዳይበዛብኝ የቤቱን ዋጋ ዝቅ አድርገሽ ተከራከሪ ብሎ ነገረኝ፡፡ ሰውየው ከባለቤቴ በላይ የወንድምዬው ወዳጅ ነበር፡፡ ተንኮል እንደነገረኝ የገባኝ ነገሩ ካለፈ በኋላ፣ ቆይቶ ነው፡፡ ወንድምዬው ይህንን መሠረት አድርጎ፤ ለዳኞቹ ጉቦ ሰጠና የተባለውን ብር ለእኔ ከፍሎ ቤቱን እንድለቅ ለፍርድ ቤቱ አመለከተ፡፡

*
ትኩሱን ቡና ከሦስት ጊዜ በላይ ፉት አላሉትም፡፡

*
ብሩን ወስጄ ቤቱን እንድለቅ ተፈረደ፡፡ ቤቱ ግን ሚሊዮን ያወጣ ነበር፡፡ ሁለት መቶ ሃምሳ ሺ ብር እና የታመመች እኅቴን ይዤ ከቤት ወጣሁ፡፡ ሦስት ዓመት በትክክል መኖራችንን እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ለህክምና፣ ለኑሮ እያልን ብሩን ጨረስነው፡፡

ለረጅም ጊዜ ዝም ብለው መሬት መሬቱን ሲመለከቱ ቆይተው፤

"*ስለምንታይ አብዚ ዝረከብካኒ ይመስለካ?" አሉኝ፡፡ ዝም አልኳቸው፤

"ልመና ወጣን፡፡ አሁን እስጢፋኖስ በተክርስቲያን የላስቲክ ቤት ሠርተን ነው የምንኖረው"

የማይሠራ የሬድዮ ድምጽና የተበላሸ የቴሌቪዥን ምስል፤ መስማትና ማየት ጀመርኩ፡፡

***
-----------------------------------------
* ብህይወት አሎ ድዩ ሞይቱ? - በህይወት አለ ወይንስ ሞቷል?

* ዕድል ወድ ሰብ ይገርምዩ - የሰው ልጅ ዕድል በጣም ይገርማል፡፡

Book for all Ethiopia

27 Mar, 05:28


የመፅሐፍ ሎተሪ

ይህ የመፃህፍት ወዳጆች፣ የንባብ አፍቃሪዎች ቡድን ነው። ይህ ቡድን ከ461,000 በላይ አባላት አሉት። ባለፈው በሰበሰብነው poll ከ2000 በላይ ፍቃደኞች አሉ። ከዚህ ውስጥ ቢያንስ 400 ተሳታፊዎች ብናገኝ እቅዳችን ግብ ይመታል። ይህንኑ እንደሚከተለው አስረዳለሁ፦

400 አባላት እያንዳንዳቸው 50 ብር ቢያዋጡ 20,000 ብር ይኖረናል። በዚህ 20,000 ብር እጣ እያወጣን ለ20 አንባቢዎች ለእያንዳንዳቸው ከ5—8 መፃህፍት እንገዛለን። መርሃግብሩ በየሳምንቱ የሚካሄድ ይሆናል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ እኔን ወይም Fantahun Abie ፋንታሁን አቤን ያነጋግሩ።

በሎተሪው ለመሳተፍ ከዛሬ ጀምሮ ወደዚህ አካውንት 50 ብር እያስገባችሁ ያስገባችሁበትን ስክሪንሻት እያደረጋችሁ በኢንቦክስ ላኩልን።

Tewodros Shewangizaw
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000429953611

Book for all Ethiopia

07 Mar, 19:45


የምስራች ለውድ አንባቢያን!
ሀሁ መጽሐፍት መደብር ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ እንኳን ለታላቁ ዓብይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ እያልን። የፊታችን ሐሙስ በጉጉት የሚጠበቀውን የዲያቆን ሄኖክ ሃይሌን "የብርሃን እናት" መጽሐፍ ቅድሚያ ከፍለው ለሚገዙ 500 አንባቢያን በ260ብር ከፍተኛ ቅናሽ ያደረግን መሆኑን እያሳወቅን ይህ ቅናሽ የሚቆየው እስከ የካቲት 23/06/2014ዓ.ም ብቻ ነው።በዚህ የባንክ አካውንት1000171387808 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፈንታሁን አቤ ብላችሁ ካስገባችሁ በኋላ የሳገባችሁበትን ደረሰኝ +251924408461/@books_of_hahu በዚህ የቴሌግራም አድራሻ ማስቀመጥዎን አይርሱ።

"ነፍሴ ሆይ! የምትድኝበትን እኔ እነግርሻለሁ፥ ከዚህ ሁሉ ይልቅ ወደ ቅድስት ድንግል ጩኺ፣ እንዲህም በይ #የብርሃን_እናት ሆይ! በልጅሽ ፊት በደልሁ ኃጢአቴን አስተስርይልኝ፡፡"
አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ
ሀሁ መጽሐፍት መደብር

አድራሻ፦

ቁ.1. ስታድየም ናሽናል ታወር ግራውንድ ፍሎር ቁ.2 ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ሕንጻ

ስ.ቁ 0911006705

Book for all Ethiopia

07 Mar, 18:11


Channel photo updated

Book for all Ethiopia

07 Mar, 18:10


Channel photo removed

Book for all Ethiopia

12 Nov, 03:56


https://www.linkedin.com/posts/henoke-seyuome-%E1%89%B0%E1%8C%93%E1%8B%A1-%E1%8C%8B%E1%8B%9C%E1%8C%A0%E1%8A%9B-2512b95b_blhblibnz-bqvbkrbpp-blxblhbpmbpcbnz-activity-6862286540635160576-QZtJ

Book for all Ethiopia

17 Oct, 10:55


Surra's Classic Colls
እንኳ ደህና መጡ! ዘመን የማይሽራቸው ሙዚቃዎች በዚህ አሉ።
https://t.me/SuClassicColls

Book for all Ethiopia

13 May, 11:14


Eid Mubarak

Book for all Ethiopia

03 May, 06:08


🙏🙏 ጣፋጭ ወግ ተጋበዙ
~~~
✍️ ‘ዳ ቬንቺ፣ ከክርስቶስና ከይሁዳ በስተቀር የሌሎቹን ምስል ለመሳል ጊዜ አልፈጀበትም ነበር፡፡ የክርስቶስና የይሁዳን ግን ከየት ያምጣው - ዳ ቬንቺ ቆመ’

የመጨረሻው እራት፣ ዳ ቬንቺ፣ ክርስቶስ እና ይሁዳ

🔹(ግሩም ተበጀ)
~~~~~~~~~~~~
ሊዮናርዶ ዳ ቬንቺ እንዲሁም ሥራ በማዘግየት የሚችለው የለም፤ በተለይ “የመጨረሻው እራት” የሥዕል ሥራውን አዘገየው አይገልፀውም - አደረበት እንጂ፡፡ ሥዕሉን ለመጨረስ ዓመታት ፈጅተውበታል፡፡

እርግጥ በዚህ ማንም ዳ ቬንቺን የሚወቅስ የለም፡፡ እንደእሱ መሳል ካልቻልክ አዘገየህ ብልህ ልትወቅሰው እንዴት ይቻልሃል ! በዳ ቬንቺ ታሪክ ላይ የፃፉ ሁሉ ይሄን የዳ ቬንቺን ሥራን ለነገ የማሳደር ባህሪ ቢጠቅሱም ማንም ሊተቸው አይደፍርም፡፡ ያውም እኮ በዚህ ባህሪው ሳቢያ ሳይጨርሳቸው የቀሩ የሚያስቆጩ የጥበብ ሥራዎች አሉ…

ግን ማን አፍ አውጥቶ ዳ ቬንቺን ሀይ ይላል…
ሃይ… ዝም ነው እንጂ…

በነገራችን ላይ … ተቀናቃኙ እና ሌላው ዘመነኛው (contemporary) ሰዓሊና ቀራፂ ማይክል አንጄሎም ይህቺ አመል ሳትኖርበት አትቀርም፡፡ ለነገሩ የሚያስቡት በጣም ትልቅ ስለሆነ ቀን ከሌት እያሰቡ እየተጨነቁበትም ለመጨረስ ረጅም ጊዜ ይወስድባቸዋል፡፡ እንደዛም ሆኖ በሰሩት መርካታቸውን እግዜር ነው የሚያውቀው - ዓለም በሥራቸው ጉድ ይበል እንጂ እነሱ በእርግጠኝነት በሥራቸው ረክተውበታል ብለን መደምደም አንችልም፡፡

አሁን ወደ ዳ ቬንቺ ድንቅ ሥዕል “የመጨረሻው እራት” የአሳሳል ታሪክ…

በዚህ ሥዕል የአሳሳል ታሪክ ዙሪያ የሚነሳ ትውፊት አለ፡፡ ዳ ቬንቺ ከክርስቶስና ከይሁዳ በስተቀር የሌሎቹን ምስል ለመሳል ጊዜ አልፈጀበትም ነበር፡፡ የክርስቶስና የይሁዳን ግን ከየት ያምጣው፡፡ በየመንገዱ፣ በየገበያው፣ በየመንደሩ እየሄደ የሰው ፊት ያጠና ጀመር - የክርስቶስን እና የይሁዳን ሊመስል ይችላል የሚለው መልክ ግን አጣ…

ከብዙ ጊዜያት በኋላ አንድ ቀን ግን ባልገመተው መልኩ በአንድ ዛፍ አጠገብ ሲያልፍ ከገበያ የሚመለሱ ገጠሬዎች መሃል መልኩ ክርስቶስን ይመስላል ያለውን አንድ ትንሽ ልጅ አገኘ፡፡
በደስታ ዘለለ፡፡

ልጁ መልኩ ክርስቶስን እንደሚመስል ሲነግራቸው ልጁም ዘመዶቹም ደስ አላቸው፡፡ እዛው በዛው የልጁን ወዘና በ‘ስኬች’ ሳል ሳል አደረገው፡፡

በ“የመጨረሻው እራት” የመሃለኛው ቦታ ያለውን የክርስቶስን ምስል ሥሎ ጨረሰ፡፡

የይሁዳ ቀረ…

ይሁዳን የሚመስል ሰው ከየት ይምጣ፡፡ ወንጀለኞች ይበዙበታል የሚላቸው ቦታ ሁሉ ‘ስኬች’ መስሪያ መሳሪያዎቹን ይዞ ተንከራተተ፡፡ ከዚያ በፊት ወንጀለኞች በስቅላት የሚቀጡበት ቦታ ድርሽ ብሎ ባያወቅም - አሁን ግን ይሁዳን የሚመስል እዚያ ቢገኝ በሚል በሞት የሚቀጣ ወንጀለኛ አለ በተባለበት ሁሉ ሄደ፡፡

የለም ይሁዳ….

ነገሩን ሊተወው በቋፍ ላይ እያለ የታሰር ጓደኛውን ሊጠይቅ እስር ቤት ሲሄድ ይሁዳን የሚመስል ወጣት እስር ቤት ውስጥ አያይም !!

ዓይኑን ማመን አልቻለም፡፡

የእስር ቤቱን ኃላፊ አስፈቅዶ እስረኛውን አስጠርቶ እሱን የሚመስል ሰው ሲፈልግ ዓመታት እንደተቆጠሩ ሲነግረው እስረኛው ፈገግ አለ…

መልኩ ይሁዳን እንደሚመስል ነግሮት ሊስለው እንደሚፈልግ ሲገልፅለት ግን እስረኛው በንዴት አበደ…

ዳ ቬንቺ ይሁዳን ትመስላለህ ስላለው ተፀፀተ፡፡ እርግጥ ነው ማንም ቢሆን ክስርቶስን የሸጠውን ከሃዲውን ይሁዳን ትመስላለህ ሲሉት ቢናደድ አይገርምም - ምን አይነቱ ደደብ ነኝ አለ ዳ ቬንቺ፡፡

ቢሆንም ግን የእስረኛው ንዴት ከልኩ ያለፈ ሆነበት - ምንድነው ይሄን ያህል - ደግሞም እኮ … መቼም … አለ አይደለ … እስር ቤት ውስጥ አይደለ እንዴ ያገኘው፡፡

ምንድነው ይሄን ያህል…

እስረኛው በንዴት እጆቹን እያወናጨፈ ዳ ቬንቺን፣ “የፈለግከውን ብትሰድበኝ ምንም አልልህም ነበር” አለው፣ “አዎን እኔ የሰው ነፍስ አጥፍቼ የተፈረደብኝ የተረገምኩ ነፍስ ነኝ … ይገባኛል … ግን ቢሆንስ … የዛሬ ስንት ዓመት ልጅ ሳለሁ ክርስቶስን ትመስላለህ ብለህ የሳልከኝን ልጅ ዛሬ ላይ ምንስ ቢሆን … ይሁዳን ትመስላለህ ትለኝ … ይሁዳን … ምን በደልኩ … ምን አጠፋሁ … እርግጥ ነፍሰ ገዳይ ነኝ … ቢሆንስ ግን … ክርስቶስን ትመስላለህ ብለህ እንደገና ደግሞ ቁርጥ ይሁዳን ትመስላለህ ትበለኝ … ምን አለበት ብትገድለኝ … ይሄን ያህል ለዚህ የሚያበቃ ምን ሰራሁ … አዎን የሰው ነፍስ አጥፍቻለሁ … ቢሆንስ ግን”

ዳ ቬንቺ ዓይኖቹ ፈጥጠው ቀረ…

ይሄ ለማመን የሚከብድ ነገር ነው፡፡ ይሄ ምን ማለት ነው - አረ የዚህ ሚስጥሩ ምን ይሆን…
ደግሞ በንዴት ሲንቦገቦግ ቁርጥ ይሁዳን !!

ዳ ቬንቺ በድንጋጤ ክው እንዳለ ከክፍሉ ወጥቶ መቼም ከዓይኑ የማይጠፋውን የ‘ይሁዳ’ን ምስል በስኬች አንስቶ ሄደ…

የጎደለው ሞላ - ይሁዳን ሳለው “የመጨረሻው እራት”ም ሆነ…
ይሄው እስካሁን ድረስ…
ዳ ቬንቺን ግን ድንጋጤው ቢለቀውም - ሚስጥሩ ግን አይለቀውም፡፡
Selam Mulugeta

4,804

subscribers

235

photos

1

videos