"የእናታችን ማርያም ትንሣኤና እርገት"
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በክብር ለምናመሰግንበት #ለእናታችን_ማርያም_ትንሣኤና_ዕርገት መታሰቢያ አመታዊ ክብረ በዐል እንኳን አደረሰን
👉 #የእናታችን_የድንግል_ማርያም እድሜዋ 64 ሲሆን በእናት አባቷ ቤት 3 ዓመት በቤተመቅደስ 12 ዓመት ጌታን ፀንሳ በቤተ ዮሴፍ 9 ወር ከ 5 ቀን ከልጇ ከወዳጇ ጋር 33 ዓመት ከ 3 ወር ከቆየች በኋላ ዓለምን ለማዳን በእለት አርብ ጌታችን በመስቀል በተስቀለም ጊዜ የሚወዳት እናቱን ለሚወደው ደቀመዝሙር ለዮሐንስ እነኋአት እናትህ በማለት የአደራ ልጆቿ እንድንሆን ያደራ እናታችን እንድትሆን በቀራንዮ በእግረ መስቀል ስር ለኛ ለሁላችን ሰጥቶናል
👉ነሐሴ 16 ቀን አስደናቂውን የእመቤታችንን #የዕርገቷን በዓል ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን በታላቅ ድምቀት ታከብራለች የእመቤታችን ማርያምን ሱባኤ በፍጹም በረከት እንድንፈጽም ያደረገን ልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይግባው ጣዕመ ፍቅሯን ያላረቀችብን እመቤታችንን ምስጋና ይግባት የአባቶቻችን #ሐዋርያት በረከትና ረድኤት ለሁላችንም ይድረሰን
👉የእመቤታችን የእረፍቷ ጊዜ ሲደርስ ጥቂት ታመመች እመቤታችን የአምላክ እናት እንደመሆኗ መጠን ሕመም ባይገባትም የሰው ልጅ እንደመሆኗ መጠን ነው የታመመችው አገልጋይዋ ቅዱስ ዮሐንስ በኤፌሶን ወንጌልን እያስተማረ ሳለ #በመንፈስ_ቅዱስ ትዕዛዝ በደመና ተጭኖ ወደ እመቤታችን መጣ ሌሎችም ቅዱሳን ሐዋርያት በጸጋ አውቀው በደመና ተጭነው መጡ ሁሉን የምታጽናና እመቤት ሐዋርያትም ሲያጽናኗት #ልጅሽ_አምላካችን_ነውና ደስ ይበልሽ አሏት
👉እመቤታችንም በአልጋዋ ጠርዝ ተቀምጣ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ወደ ዘላለማዊው ዓለም እንደምሄድ በምን አወቃችሁ አለቻቸው ሐዋርያትም ‹#መንፈስ_ቅዱስ በደመና ጭኖ እንደ ዓይን ጥቅሻ ያመጣን አንቺ ወደ ዘላለማዊ ሕይወት ልትሄጂ ስለሆነ ነው አሏት እመቤታችንም ድምጿን ከፍ አድርጋ ጌታዬ #ፈጣሪዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሆይ ክቡር ምስጉን የሆነ ስምህን ፈጽሜ አመሠግናለሁ የእኔን አገልጋይህን መከራ ተመልክተህ ድንቅ አድርገህልኛልና ከእንግዲህ #ትውልድ ሁሉ ያከብሩኛል ያመሠግኑኛል አለች
👉 #ቅዱሳን_ሐዋርያትም ከእነሱ መለየቷን ሲያውቁ ትባርካቸው ዘንድ እያለቀሱ ጠየቁ ወላዲተ አምላክም እጇንም በላያቸው ላይ ዘርግታ ባረከቻቸው በዚያን ጊዜ የክብር ባለቤት ልጇ እልፍ አእላፍ መላእክት አጅበውት እያመሰገኑት መጥቶ አረጋጋት በሰማይ ያዘጋጀላትን ተድላ ደስታ ነገራት ጌታችንም ከገነት ያመጣውን አፒሊያኖስ የሚባል መዓዛው ለነፍስ የሚጣፍጥ የሚመስጥ አበባ በአፍንጫዋ እያሸተተች በጆሮዋ የመላእክትን ምስጋና እየሰማች ያለ ጣር ያለ ጋር በተመስጦ በደስታ ነፍሷ ከሥጋዋ ተለየ
👉ጌታችንም ንፅህት ነፍሷን የብርሃን መጎናፀፊያ አልብሶ በመላእክት ዝማሬ ጥር 21 ቀን ወደ ሰማይ አሳረጋት ነብዩ ዳዊት ‹"ነፍሴ ሆይ ወደ እረፍትሽ ግቢ እግዚአብሔር መልካም ነገርን አድርጎሻልና›" እንዳለ መዝ.114÷7 #እመቤታችንም በልጇ ደስታ ወደ ሰማይ እረፍቷ ገባች
👉በሌላ ታሪክ #እመቤታችን በእረፍቷ ጊዜ ጌታችን ሲመጣ "ልጄ ወዳጄ እኔ አንተን ወልጄ እንዴት እሞታለሁ በእውኑ ሞት ለእኔ ይገባኛልን ብላ ጠይቃው ነበር "እሱም በሲዖል የሚሰቃዩትን ነፍሳት አሳይቷት እናቴ እነዚህ በሲዖል የሚሰቃዩት ነፍሳት የሚያገኙት እረፍት ባንቺ ሞት ነው ሲላት የሞቷን መልካምነት
በሲዖል ለሚሰቃዩት ነፍሳት ነፃ መውጣት መሆኑን የተረዳችው እመቤታችን "ልጄ ሆይ ለእነዚህስ አይደለም አንዴ ሰባቴ ልሙትላቸው"ብላ በፍቃዷ እዳረፈች ሊቃውንት ይተርካሉ
👉ወዳጆቼ እመቤታችን ለእኛ ለልጆችዋ ሰባቴ ለመሞት በነፍሷ የተወራረደች እናት ሆና ሳለ በዚህም እመቤታችንን በነፍስ ፍቅር አለመውደድ ማለት ከጣዕመ ፍቅሯ መሰደድ በቁም ለሲዖል እሳት መማገድ ነው #እመቤታችን_ማርያምን አለማመስገን ማለት በነፍስ በሥጋ ከፀጋ ፍቅሯ መራቆት ለሰይጣንና ለሠራዊቱ ተላልፎ መሰጠት ነው ከወለላይቱ ከአዛኝቱ ጣዕመ ፍቅር መለየት ማለት ከሞቱት በላይ ከሚኖሩት በታች ሆኖ በቁም መሞት ነው
👉ከዚህ በመቀጠል አብይ ነጥቡ የወላዲተ አምላክ #ማርያም #ትንሣኤና_እርገቷ ነዉ በእለተ እረፍቷ የተፈፀመዉን የመሠወር ሚስጢር ያየ ዮሐንስ ሲሆን የመጨረሻውን ትንሣኤና ዕረፍት ለማየት የታደለዉ #ቶማስ ብቻ ነዉ
👉በወቅቱና በቦታዉ ያልነበረው ቶማስ የትንሣኤዋንና የእርገቷን ምስጢር ተገልፆለት ለሐዋርያት በነገራቸው ጊዜ መቃብሩን ከፍተዉ ቢያዪት ባዶዉን ስላገኙት #ትንሣኤዋንና_እርገቷን ለማየት በአመቱ ነሐሴ አንድ ቀን እንደገና ሌላ ፆመ ሱባኤ በመግባትና ፈጣሪያቸዉን በመለመን በነሐሴ 16ኛዉ ቀን ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ እመቤታችንን መንበር ቅዱስ ጴጥሮስን ረዳት ካህን ቅዱስ እስጢፋኖስን ቀዳሚ ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ አቁሩቧቸዋል ሐዋርያትም የዚህ ድንቅ ሚስጢር ተካፋይ ሆነዋል
👉አባቶቻችን ሐዋርያት የእመቤታችንን እረፍቷን ትንሣኤዋን እርገቷን በፆምና በፀሎት አይተዉ የህሊና እረፍታቸውን የደመደሙት እመቤታችን ለትንሣኤዋ ተጨባጭ ምልክት በእርገቷ ጊዜ #ለቅዱስ_ቶማስ የሰጠችዉን ሰበን ለበረከት ከተካፈሉ በኋላ ነዉ ለኛም የቃል ኪዳን ልጆቿ በረከት ረድኤቷ ለሁላችንም ይድረሰን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️