የዓለምን ጥበብ ልታሳፍር ሞኝን ነገር የመረጥህ
ብርቱውንም ደግሞ ልታሳፍር ደካማውን የፈለግህ
ይደንቀኛል አደራረግህ-የኔን ሕይወት እንዲህ አደረግህ
ይገርመኛል አሰራርህ- የኔን ህይወት እንዲህ ያደረግህ
ቆጠርከኝ ታማኝ አድርገህ
የሾምከኝ ለቤትህ አምነህ
ምን አይነት ፍቅር ነው ያንተስ
ሰው ሰውን እንደሚያይ መቼ ታያለህ
የቆጠርከኝ ታማኝ አድርገህ
የሾምከኝ ለቤትህ አምነህ
ምን አይነት አምላክ ነህ አንተስ
ሰው ሰውን እንደሚያይ መቼ ታያለህ
አይቸግርህም አንተን የሰው ብዛት
የሚያመልክህ በብዙ ትጋት
እኔን ደካማዋን ለየህ ለክብርህ
በፊትህ ልቆም ላጥን በቤትህ
እኔን ደካማዋን ለየህ ለክብርህ
በፊትህ ልቆም ላጥን በቤትህ
ቆጠርከኝ ታማኝ አድርገህ
የሾምከኝ ለቤትህ አምነህ
ምን አይነት ፍቅር ነው ያንተስ
ሰው ሰውን እንደሚያይ መቼ ታያለህ
የቆጠርከኝ ታማኝ አድርገህ
የሾምከኝ ለቤትህ አምነህ
ምን አይነት አምላክ ነህ አንተስ
ሰው ሰውን እንደሚያይ መቼ ታያለህ
በአይኖችህ ታየሁኝ አገኘኝ ሞገስህ
የማልበቃውን ሰው ብቁ አረገኝ ጥበብህ
ይኸው ዝማሬ ላንተ ምስጋና
ያበጃጀኸኝ አንተ ነህና
ይኸው ክብር ይሁን ምስጋና
ለክብር ያረግከኝ አንተ ነህና
ቆጠርከኝ ታማኝ አድርገህ
የሾምከኝ ለቤትህ አምነህ
ምን አይነት ፍቅር ነው ያንተስ
ሰው ሰውን እንደሚያይ መቼ ታያለህ
የቆጠርከኝ ታማኝ አድርገህ
የሾምከኝ ለቤትህ አምነህ
ምን አይነት አምላክ ነህ አንተስ
ሰው ሰውን እንደሚያይ መቼ ታያለህ
ስምህን የሚጠሩትን ያንተን ክፉ አሳዳጅ
በደማስቆ አግኝተህ አደረግከው ሳውልን ወዳጅ
የተመረጠ የክብር እቃ
ይኸው አረግከው ለክብር በቃ
ስምህን የሚሸከም የክብር እቃ
ይኸው አረግከው ለቤትህ በቃ
የዓለምን ጥበብ ልታሳፍር ሞኝን ነገር የመረጥህ
ብርቱውንም ደግሞ ልታሳፍር ደካማውን የፈለግህ
ይደንቀኛል አደራረግህ-የኔን ሕይወት እንዲ አደረግህ
ይገርመኛል አሰራርህ- የኔን ህይወት እንዲህ ያደረግህ
ቆጠርከኝ ታማኝ አድርገህ
የሾምከኝ ለቤትህ አምነህ
ምን አይነት ፍቅር ነው ያንተስ
ሰው ሰውን እንደሚያይ መቼ ታያለህ
የቆጠርከኝ ታማኝ አድርገህ
የሾምከኝ ለቤትህ አምነህ
ምን አይነት አምላክ ነህ አንተስ
ሰው ሰውን እንደሚያይ መቼ ታያለህ