አስገራሚ አጫጭር ታሪኮች 😲 @asgrami_tarikoche Channel on Telegram

አስገራሚ አጫጭር ታሪኮች 😲

@asgrami_tarikoche


እንኳን ደህና መጡ 🥰🥰🥰

በዝህ ቻናል በእውኑ አለም የተከሰቱ እውነተኛ ታሪኮችን እና ልቦለዳዊ የሆኑ አስገራሚና አስተማሪ አጫጭር  ታሪኮችን እንዲሁም የተለያዩ ምክሮችን ባጭር ባጭሩ እናቀርባለን።

#ይቀላቀሉን_ለወዳጅ_ዘመዶ_ያጋሩ
ለአስታየት @Esku_3i

አስገራሚ አጫጭር ታሪኮች 😲 (Amharic)

የታሪኩ ስም በአስገራሚ አጫጭር ታሪኮች ማለት እናንት የሚበጠሩ እና የሚመጡ ታሪኮችን አቅምንተን ለማከናወን ከፈለጉ። በዚህ ታሪኩ ጋር እዚህ ታሪኮችን ለማከናከና እንደምትችሉ በሚገልጽል የታሪኩ ትምህርቶችን ከፍተኛ በማከናወን ከሆነ በጋራ ማስተላለፋችንን ማሳያ እና ማከናነብ የታሪኩ መሠረት ላይ ምን ያደርጋል ውስጥውና ሁለቱ ትምህርቶች በሚተክላቸው ትምህርቶች የሚቆጠሩ ለማከናወን ይህን ታሪኩን ለመረዳት በትክክለኛ ድርጅቶች እና ገጽ እንድናጋጥሙት ተጠናቋል።

አስገራሚ አጫጭር ታሪኮች 😲

21 Nov, 08:18


😅ለፈገግታ 😜

ልጅ አባቱን " ፕሬዜዳንት ማለት ምን ማለት ነው? " ብሎ ይጠይቃል።
አባት: _ " ፕሬዜዳንት ማለት መሪ ማለት ነው። አሁን
#ለምሳሌ እኔ የዚህ ቤት ፕሬዜዳንት #ነኝ።" ብሎ ይመልስለታል።
ልጅ ጥያቄውን አላቆመም።
ልጅ:_ " እናቴስ ምንድን ናት?"🙂
አባት:_ " እናትህ ገንዘብ ሚኒስቴር ናት።"
ልጅ:_ " አያቴስ?"
አባት:_ " አያትህ
#ሰላይ ናት።"
ልጅ አሁንም ጥያቄውን ቀጠለ " እኔስ ምንድን ነኝ?"
አባት:_ " አንተ
#ህዝብ ነህ።" ብሎ ይመልስለታል።
በሌላ ጊዜ አባት ስራ ሄዶ መኖሪያ ቤታቸው
#ሌላ ሰው ይመጣል። ከዛም
ልጅ
#ተደብቆ አባቱ መስሪያቤት ይደውልና ምን ቢል ጥሩ ነወ?
.
.
.
.
" ሄሎ አባየ! ትሰማኛለህ? እቤታችን
#ሌላ ፕሬዜዳንት መጥቷል🙆‍♂፣ ገንዘብ
ሚኒስቴር
#ሽር_ጉድ እያለ ነው💃፣ ሰላይ ያንቀላፋል፣ ህዝብ ግን #ተጨንቋል👀😧😥


@asgrami_tarikoche
Like,share

አስገራሚ አጫጭር ታሪኮች 😲

18 Nov, 19:34


ባል ጣዕረ-ሞት ይዞት እያጣጣረ ሳለ ሚስቱን ያስጠራና
“እንግዲህ እኔ መሞቴ ነው፤ አንቺ ግን ያለ ባል መቅረት
የለብሽም፤ እንዲያውም ያንን ኩራባቸውን አግቢ” ይላታል።
በዚህ አባባል የተናደደችው ሚስት “አንተን ይማርልኝ እንጂ እኔ
አሁን ስለ ባል አላስብም! ደግሞ ባገባስ እንዴት ያንተን ዋነኛ
ጠላት ኩራባቸውን አግቢ ትለኛለህ?” ስትል ትጠይቀዋለች።
በዚህ ጊዜ ጣር የያዘው ባል እያቃሰተ መለስ ብሎ “አንቺ ደሞ
አይገባሽም እንዴ? ጠላቴ መሆኑንማ መች አጣሁት? ልክ እንደ
እኔ አንገብግበሽ እንድትገድይልኝ ነው እንጂ! አላት ይባላል።😁


@asgrami_tarikoche

አስገራሚ አጫጭር ታሪኮች 😲

17 Nov, 07:37


"በጌታ ፍቅር እወድሀለው!"
በጌታ ፍቅርማ አንዋደድም አናስመስል።  ባልንጀራህን እንደ እራስ እንኳ ውደድ የተባልነው እንደጌታ መውደድ ስለማንችል መሰለኝ🤔 እንደራስህ ልትወደኝ ሳትችል፤ እንደራሴ ልወደህ ሳልችል በጌታ ፍቅር እወድሀለው ብዬ ልሸነግልህ አልፈልግም። በጌታ ፍቅር እንዋደድ ብንል ለኛ ፈተና ነው የሚሆንብን።
እንደ ጌታ መውደድ ቢያቅተን እንደራሳችን እንድንዋደድ ታዘናል እንጂ የማናደርገውን ነገር ለንግግር ማሳመሪያ ተጠቅመን አንሸዋወድ !!

ለሃሳብ እና አስታየት
   👇👇
@Esku_3i

አስገራሚ አጫጭር ታሪኮች 😲

15 Nov, 13:06


👩ልጅቱ ተደወለላት🤳...

"ሔሎ የኔ ቆንጆ...ፍቅረኛ አለሽ ?"
"አዎ አለኝ, ማን ልበል ?"
.
.
"መጣሁልሽ አንቺ ባለጌ...አባትሸ ነኝ" ብሎ ስልኩን ዘጋዉ !
.
.
አሁንም በድጋሚ ተደወለላት..."ሔሎ የኔ ቆንጆ...ፍቅረኛ አለሽ ?"
.
.
"የለኝም ,ማን ልበል ?"
.
"ነዉ አይደል? በቃ ተነቃቃን እሽ...እኔማ ጉዋደኛሽ ተብዬው ሚኪ ነበርኩ" 😔
.
.
"ባክህ ይሄ ገገማ 😒አባቴ ሊያስለፈልፈኝ መስሎኝ ነው...እየደወለ እቃቃ አይጫወትብኝ መሰለህ ? አሁንስ ተጃጃለ..."
.
.
"መጣሁልሽ አንች ወራዳ...አባትሽ ነኝ"
😳😳😳😂😂😂

@asgrami_tarikoche

አስገራሚ አጫጭር ታሪኮች 😲

10 Nov, 20:04


አንድ ወላጅ አባት ከመሞቱ በፊት ለወንድ ልጁ እንዲህ አለው። ይሄን የምትመለከተውን ሰአት የሰጠኝ የኔ አባት ለአንተ ደግሞ አያትህ ነው ይህ ሰአት ከ 200 አመት በላይ ይሆነዋል። ዛሬ ይሄን ሰአት ላንተ መስጠት እፈልጋለሁኝ ነገር ግን ከመስጠቴ በፊት ከመንገዱ ባሻገር ወዳለው የሰአት መሸጫ ሱቅ ሂድና ይሄን ሰአት ለመሸጥ እንደምትፈልግ ንገራቸው ስንት እንደሚያወጣም ጠይቃቸው። አለው!!
.***
ልጁም ወደ ሰአት መሸጫው ሄዶ ሰአቱን አሳይቶ መሸጥ እንደሚፈልግ ለባለ ሰአት ሻጩ እና አዳሹ ነገረው!! ሰአት ሻጩም ሰአቱን ከተመለከተ በኋላ በ 5 ዶላር ብቻ እንደሚገዛው ነገረው!! ምክንያቱም ሰአቱ እጅግ ያረጀ እና ያፈጀ በመሆኑ ምክንያት ከፍተኛ ዋጋው 5 ዶላር ብቻ መሆኑን ደግሞ ነገረው። ልጁም በፍጥነት ይሄንንም መጥቶ ለአባቱ ነገረው!!
.***
አባቱም ልጆንን አሁን ደግሞ ወደ ቡና መሸጫ ሱቅ ሂድ አለው ልጁም ወደ ቡና መሸጫ ሱቅ ሄደ ለቡናም 5 ዶላር ከፈለ ተመልሶም ወደ አባቱ መጣ አባቱ ለልጁ ማስተማር የፈለገው ትልቅ ቁምነገር ስላለ አሁን ደግሞ ይሄን ሰአት ይዘህ ወደ ሙዜም ሂድ አለው!!
.***
ልጁም የአባቱን ትህዛዝ ሰምቶ ሰአቱን ይዞ ወደ ሙዜም ሄደ ሙዜም እንደደረሰም በሙዜሙ የሚገኙ ሰዎች ለአሮጌው ሰአት ሚሊዮን ዶላሮች እንደሚሰጡት ነገሩት!! ልጁም ይሄኔ ወደ አባቱ በአስቸኳይ መጥቶ እንዲህ አለ። ​​​​​​​አባዬ የሙዜሙ ባለቤቶች ለሰአቱ ሚሊዮን ዶላሮች እንደሚሰጡኝ ነገሩኝ አለው!!
.***
አባትየውም ልጁን ጠርቶ ወደ እራሱ እያስጠጋ እንዲህ አለው!! ልጄ ሆይ ዛሬ አንድ ነገር ልነግርህ እወዳለሁኝ የምነግርህን ነገር በልብህ መዝገብ ላይ አኑረው ለህይወትህም መመሪያ ይሁንህ በሄድክበት በገባህበት እና በወጣህበት ሁሉ በህሊናህ አሰላስለው የህይወትህም መመሪያ አደርገው!!
.***
ትክክለኛ ቦታ የተክክለኛ ዋጋ ትክክለኛ ስፍራ ነው!! በየትኛውም ግዜ እና ሰአት ላይ እራስህን በትክክለኛ ቦታ ካስቀመጥቀው እና በትክክለኛ ቦታ ከተገኘህ ዋጋህ በትክክልም የሚመጥንህ ነው!! ያንተን ዋጋ የሚወስነው ትክክለኛው ቦታ ላይ ብቻ መገኘትህ እና መቀመጥህ ነው!!
.***
ስለዚህ ሁሌም እራስህን ባልተገባ ስፍራ ላይ አታስቀምጠው ፤ ባልተገባም ስፍራ ላይ አትዋል ፤ ስፍራው ዋጋህን ያሳንሰዋል ጥቅምህንም ያወርደዋል!! ይህ የምትመለከተው ሰአት እኮ በትክክል ሰአት ነው!! ነገር ግን በሰአት መሸጫ ውስጥ ቢቀመጥ ከዘመኑ ጋር ስለማይሄድ ማንም አይፈልገው ዘመን አልፎበታል አርጅቷል አሮጌ ነው!! ነገር ግን ሙዚየም ቦታው ነው!! ማንም ሊያደርገው የማይፈልገውን ሰአት ብዙ ዶላሮች ከፍሎ ግን ይጎበኘዋል!! እናም ልጄ ስፍራህን እወቅ በትክክለኛው ቦታ ተገኝ!!
.***
ዛሬ ላይ በትክክለኛው ቦታ ላይ ባለመቀመጣችን ዋጋችንን ያሳነስን ሁላችን ከዚህ ትልቅ ነገር ልንማር ይገባል!! የት ነው ያለነው? ዋጋችንን ያሳነሰው እና ያቀለለን ነገር ምንድነው ስፍራው ወይስ እኛ? እራሳችንን እንጠይቅ!! ለራሳችን ክብር እንስጥ እራሳችንንም እናክብር !! ዋጋችንን አናርክሰው

#join_us_&_shareshare

አስገራሚ አጫጭር ታሪኮች 😲

07 Nov, 08:53


ለፈገግታ 😊

ሰሞኑን ከገጠር የመጣ አጎቴ ጋር ነበርኩ። ትላንት ከቤት ስወጣ እንዳይደብረው ብዬ EBS cinema ከፍቼለት  ወጣሁ። ትንሽ ቆይቼ ስመለስ የሆነ ፊልም እየታየ ነበር ርእሱ ጠፋብኝ። ፊልሙ መካኒሳ በሚል ሰፈር ነው የተሰራው።

እቤት እንደገባሁ አጎቴ ፈጠን ብሎ «እንደው ይሃን ሞላጫ ሌባ እንደው ግሩን ቀጭቶ የሚጥል ይጥፋ?» አለኝ።
«የትኛውን ነው አጎቴ?»
«ያ ጠጉሩን ያሳደገው እንደው የየሰውን ኪስ ሞለጨውኮ ደሞኮ ዛሬ ታስሮ ዛሬ ነው የተፈታ» አለኝ። እሱ ማንበብና መጻፍ ቢችልም የፊልሞች ከሁለት ዓመት በኋላ ከአንድ ወር በኋላ ምናምን የሚሉትን ነገሮች አይገነዘባቸውም። እኔም ላስረዳው ብዬ «ሰውዬውኮ ከሁለት ሳምንት በኋላ ነው የተፈታው» አልኩት።
ዞር ብሎ አየኝና ከት ብሎ ሳቀብኝ
«እዚሁ ሲታሰርና ሲፈታ እያየሁት የምን ከሁለት ሳምንት በኋላ አመጣህሳ? እዚህ ቁጭ ብዬ መሽቶ ሳይነጋ ሁለት ሳምንት ሆነ?» አለኝና ረጅም ሳቅ ሳቀ። ላስረዳው ብልም ስለማይሰማኝ ዝም አልኩት

የሌባው ልጅ ፍቅረኛ አረገዘች ወለደች ፊልሙ ከአራት ዓመታት በኋላ ብሎ ያደገውን ሕጻን አሳየ😁 አጎቴ እንባው እስኪመጣ ሳቀና «መቼስ የማንሰማው ጉድ የለ በቃ በአንድ ቀን ተረግዞ በአንድ ቀን ልጅ መውለድ መጣ? እንዲህ ዓይነት ታምር ሰምቼም አላውቅ

እንዴት ብዬ ላስረዳው? ስለ flash back ስለ flash forward ምን ብዬ ልንገረው?😂 ላስረዳው በሞከርኩ ቁጥር «መችም አያውቅም መሃይም ነው ብለህ ትጫወትብኛለህ አይደል? በል ተጫዎትብኝ!» ይለኛል

ለካ ይሄ ነው generation gap ማለት😁
እና አንድ ነገር ትዝ አለኝ “አውቀዋለሁ የምትለውን ነገር  ለአያትህ ማስረዳት ካልቻልክ ነገሩን ምንም አታውቀውም!”  የሚል አባባል ነዉ

                  ........

😁 like ማድረግ አይረሳ
@asgrami_tarikoche

አስገራሚ አጫጭር ታሪኮች 😲

04 Nov, 14:22


በሐይቅ ዳርቻ አካባቢ የተገደመ ገዳም ነበረ። በዚያ የሚኖሩት መነኮሳት ጓደኛሞች ናቸው እቃ ለመግዛት ወደከተማ ይወጣሉ። እቃ ገዝተው ሲመለሱ
ድንገት ማዕበል ይነሳና በገዳሙ አካባቢ የምትኖር አንዲት ሴት ሐይቁን መሻገር ፈልጋ ነገር ግን መዋኘት ስለማትችል ማዕበሉ አስጨንቋት ዳር ቆማ ይመለከታሉ።

አንደኛው አባት ቀርቦ ምን ልርዳሽ ሲላት መሻገር ፈልጌ ነበር እሚረዳኝ ሰው እየፈለኩ ነው ብትለው በይ እኔ እየዋኘው
አሻግርሻለሁ ጀርባዬ
ላይ ተኚ ብሎ እሷ ከጀርባው ተኝታ እየዋኘ ያሻግራታል።

ወዳጁም ብቻውን ይሻገርና ገዳማቸው ይገባሉ። አበምኔቱ መነኮሳትን የሚሰበስቡበት ጊዜ ነበራቸውና መነኮሳቱን በሰበሰቡበት ወቅት ብቻውን የተሻገረው መነኩሴ እጁን በማውጣት አባታችን ጓደኛዬ ገዳሙን አርክሶታል አለ። አበምኔቱም ተገርመው በምን ምክንያት ልጄ ቢሉት ያኔ
ለገዳሙ እቃ ልንገዛ ወተን ከከተማ ስንመለስ ሴት ልጅን በጀርባው አዝሎ ሓይቁን አሻግሯል አለ። አብምኔቱም ልጅቷን ያሻገረውን
መነኩሴ የሚለው እውነት ነው ቢሉት። አዎ አባቴ እኔ ሴትየዋን የተሸከምኳት የዛኔ ነው በጀርባዬ
አዝዬ አሻግሬ እዛው አውርጃታለሁ ወዳጄ ግን እስከ አሁን
በአዕምሮው ተሸክሟታል አለ።

እስቲ ስንቶቻችን እንሆን ከሳሽ
ሆነን የራሳችንን ሳይሆን የሰውን በደል በአዕምሮዋችን ተሸክመን የምንኖር?

@asgrami_tarikoche

አስገራሚ አጫጭር ታሪኮች 😲

30 Oct, 19:17


በተሳፋሪዎች የተሞላዉ አዉቶብስ ጉዞ ላይ ነዉ ወዲያዉ የአካባቢዉ የአየር ሁኔታ ተቀያየረና አስፈሪ የነጎድጓድ ድምፅ የመብረቅ ብልጭታ መታየት ጀመረ፡፡
ተሳፋሪዎቹ አዉቶብሱ ከአሁን አሁን በመብረቅ ተመታ እያሉ መጨነቅ ጀመሩ መብረቁ ግን መኪናዉን እያለፈ ይወድቅ ነበር፡፡
እንዲህ አይነቱ አጋጣሚ ሁለት ሶስቴ እንደቀጠለ ሾፌሩ አዉቶብሱን ከአንድ ዛፍ ሃምሳ ጫማ ርቀት ሲቀረዉ አቆመና ተሳፋሪወቹን "ከእናንተ መሃል ዛሬ መሞቱ ግዴታ የሆነ ሰዉ አለ ከአሁን በኋላ አብሮን ከተጓዘ በእሱ ምክንያት ሌሎቻችንም አብረን ልንጠፋ እንችላለን።
ስለዚህ ሁላችሁም በየተራ እየወጣችሁ ያንን ዛፍ እየነካችሁ እንድትመለሱ እፈልጋለሁ መሞት ያለበት ሰዉ ካለም ዛፉን የነካ ጊዜ በመብረቅ ይመታል ሌሎቻችን ግን እንተርፍለን ማለት ነዉ!!" አለ ሁሉም የመጀመሪያዉን ተሳፋሪ ሄዶ ዛፍን እንዲነካ መጎትጎት ጀመሩ እሱም እየጨነቀዉና በፍርሃት ተዉጦ ሄዶ ዛፍን ነክቶ በሰላም ተመለሰ ምንም ሳይሆን በመመለሱም ልቡ በደስታ ጮቤ ረገጠች፡፡ መጨረሻ ላይ የነበረዉ ተሣፋሪ ተራ እንደደረሰ ሁሉም ሟቹ እሱ እንደሆነ በማሰብ ዐይኑን እያዩት እንዲሄድ ገፋፉት እሱም በመሞት ፍራቻ ተዉጦ ከአዉቶብሱ ወረደ። ከዛፉ ደርሶ እንደነካዉም ኃይለኛ ድምፅ ተሠማ አስፈሪ የመብረቅ ብልጭታም ሆነ...
መብረቁ ግን የመታዉ አዉቶብሱን ነበር። ውስጡ የነበሩት ተሳፋሪዎችም ሞቱ፡፡ እነዚያ ቀደም ብሎ አዉቶብሱን ያለፉት አደጋዎች ሁሉ ያለፉትም ለመጨረሻዉ ተሣፋሪ ንጽህና ነበር፡፡

ራሳችንን ሁልጊዜ እንደ ንጹህ እናያለን ግን ለምን?


@asgrami_tarikoche

አስገራሚ አጫጭር ታሪኮች 😲

26 Oct, 17:15


ማግባት እንደማልፈልግ ብነግረዉም ጭቅጭቁን ያልቻልኩት እንድ ሽማግሌ ጎረቤቴ የሆነ ሰርግ ላይ ተጠርተን ‹ቀጣዩ ሙሽራ አንተ ትሆናለህ ›ብሎ  አናደደኝ…በሌላ ጊዜ ሰዉ ሞቶ የቀብር ስነስርአት ላይ አግኝሁትና ‹ቀጣዩ ሰዉ አንተ ነህ›አልኩት፡፡ ~ዘቶፕ ቴንስ~


@asgrami_tarikoche

አስገራሚ አጫጭር ታሪኮች 😲

23 Oct, 09:42


#ኔልሰን_ማንዴላ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የህግ ትምህርት በሚማሩበት ጊዜ ነጭ ፕሮፌሰር አስተማሪ ነበራቸው። ስሙም ፒተር ይባላል።

አንድ ቀን ፕሮፌሰር ፒተር በአንድ ምግብ ቤት ምግባቸውን እየበሉ ሳለ ማንዴላ በአጋጣሚ ምግብ ይዘው ከአጠገባቸው ይቀመጣሉ። ዘረኛው ፒተርም "አቶ ማንዴላ! አሳማና 'ርግብ ለመብል አብረው አይቀመጡም!" ሲላቸው ብልሁ ማንዴላም "አይጨነቁ ፕሮፌሰር በርሬ እሄዳለሁ" ብሏቸው ሌላ ወንበር ላይ ይቀመጣሉ።

በዚህ የተናደደው ፒተር በሌላ ቀን ቂሙን
ሊወጣበት ያስባል። አንድ ቀንም ፕሮፌሰሩ ክላስ ውስጥ እያስተማሩ

" ማንዴላ በመንገድ ላይ እየሄድክ ሁለት ቦርሳዎችን ብታገኝና በአንደኛው ቦርሳ 'ገንዘብ' በሌላኛው ቦርሳ ደግሞ 'ጥበብ' ቢኖር የትኛውን ትወስዳለህ?" ብሎ ማንዴላን ሲጠይቀው

ማንዴላም"ገንዘቡን እወስደዋለሁ" …ብሎ መለሰለት። ፕሮፌሰሩም በድል አድራጊነት "አንተ ሞኝ ነህ እኔ አንተን ብሆን ኖሮ ጥበብ ያለበትን ቦርሳ እወስድ ነበር" ሲለው ማንዴላ ፈገግ እያለ "ልክ ነህ ማንም የሌለውን ነው የሚወስደው" አለው።

በዚህ ሁሉ ነገር የተበሳጨው ፕሮፌሰር ፒተር የማንዴላ የፈተና ወረቀት ላይ 'ደደብ' ብሎ ይፅፋል። ሌሎች ተማሪዎች የታረመላቸውን የፈተና ወረቀት ሲያዩ ማንዴላ ደደብ የሚለውን ፅሁፍ ከወረቀቱ ላይ አየና ተገረመ ከዛም ወደ ፕሮፌሰሩ ሄዶ
………
"ይቅርታ ቲቸር ፊርማህን ብቻ ነው ያስቀመጥክልኝ ውጤቴን ረስተኸዋል" ብሎት እርፍ።

ወዳጄ ሁሌም ቢሆን ደስተኛ ወይም ሀዘንተኛ ሊያረግህ የሚችለው አንተ ለነገሮች የሚኖርህ የእራስህ ምላሽ ነው፡፡


@asgrami_tarikoche

አስገራሚ አጫጭር ታሪኮች 😲

18 Oct, 17:50


አንድ ሽማግሌ አርሶ አደር እስር ቤት ላለው ልጁ እንዲህ ሲል ደብዳቤ ላከ ....፤

"ውድ ልጄ ዘንድሮ ድንች መትከል አልችልም ምክንያቱም መስኩን በራሴ መቆፈር ስለማልችል እዚህ ብትሆን ትረዳኝ ነበር"

ልጁ ከእስር ቤት መልሶ እንዲህ ሲል ጽፏል። "አባዬ ሜዳውን ለመቆፈር እንኳ አቅም እንደሌለህ አዉቃለሁ። መሬቱን እንዳታስቆፍር። ከማሳዉ የሚወጣዉን ኩንታል ያክል ድንች እኔ እገዛልሃለሁ። ምክንያቱም የሰረቅኩትን ወርቅ በሙሉ የቀበርኩት እዚያ ነው።"

ደብዳቤውን ለአባትዮዉ ለመስጠት የተቀበለው #ፖሊስ ደብዳቤው ሚስጥር ይኖረዋል ብሎ አነበበዉ። "የሰረቅኩትን ወረቅ የቀበርኩት ማሳ ዉስጥ ስለሆነ እንዳትቆፍር" ይላል። ፖሊሱም በማግስቱ ገንዘቡን ለመፈለግ ማሳዉን በሙሉ አስቆፈረዉ። ነገር ግን #ምንም አልተገኘም።

በማግስቱ ይህን የሰማዉ ልጅ ከእስር ቤት ለአባቱ #እንደገና ደብዳቤ ጻፈ። "አሁን ማሳዉ ተቆፍሯል ድንችህን ትከል። እኔ እዚህ ሆኘ ማድረግ የምችለው  ነገር ይሄን ብቻ ነበር አድርጌዋለሁ።" አለዉ ይባላል ....


@asgrami_tarikoche

አስገራሚ አጫጭር ታሪኮች 😲

15 Oct, 09:16


አዲስ ተች ስልክ የገዛችው አባትዋ ሲያይ >>👨‍🦳አባት "ስልኩን ስገዢ  መጀመሪያ ያደረግሽው ምንድነው? ብሎ ጠየቃት?

👱‍♀ልጅ፦"በመጀመሪያ ያረኩት ስክሪኑ እንዳይጫጫር ሲቲከር ለጠፍኩበት"

👨‍🦳አባት፦እንደዚ እንድታደርጊ የገፋፋሽ ሰው አለ?

👱‍♀ልጅ፦"የለም

👨‍🦳አባት፦"ምርቱን እንደ ማንቋሸሽ አይሆንም ግን……?

👱‍♀ልጅ፦"ኧረ አባዬ!እንደውም ሚመክሩን እንድለጥፍበት ነው

👨‍🦳አባት፦"የሸፈንሽው ግን ርካሽ ስለሆነ ወይም ስለሚያስጠላ ነው"

👱‍♀ልጅ፦"በነገራችን ላይ የሸፈንኩት ……እንዳይበላሽብኝና ብዙ ጊዜ እንዲያገለግለኝ ነው"

👨‍🦳አባት"ስትሸፍኝው……ግን ውበቱ አልቀነሰም"

ልጅ"እንደውም አምሮበታል በዛ ላይ እንዳይበላሽ ይከላከልልኛል"

👨‍🦳አባት፦በአባትነት አይን እያያት……አንድ ጥያቄ ብጠይቅሽ………ከስልክሽ የሚበልጠውን ገላሽን እንድትሸፍኝው እሺ ትይኛለሽ?


@asgrami_tarikoche

አስገራሚ አጫጭር ታሪኮች 😲

08 Oct, 10:41


የጠላትህን ትጥቅ ለማስፈታት የተመረጠ ታማኝነትን ተጠቀም!!


በጥንታዊነቷ ቻይና የቼንግ ግዛት ገዥ ዋ ሐያል እየሆነ የመጣውን የሁ ግዛትን የመውረሪያ ወቅት መድረሱን ወሰነ ። እቅዱንም ለማንም ሳያሳውቅ ለሁ ግዛት ገዢ ሴት ልጁን ዳረ። በመቀጠልም ካብኔውን ሰብስቦ “የትኛውን ሀገር ነው መውረር ያለብን“ ብሎ ጠየቃቸው ። እንደጠበቀወው አንዱ ሚኒስትር የሁ ግዛት ነው መወረር ያለበት ሲል መለሰ ።ዋም የተናደደ መስሎ ሁ አሁን እህት ሀገር ናት ለምን እንድትወረር ሀሳብ አቀረብክ አለ ። ተገቢ ያልሆነ ምክር ሰጥቷል በማለትም ሚኒስትሩ ተገደለ ።የሁ አገር ገዢም ይሄን ነገር ሰማ።የዋም ታማኝነት ከጋብቻው የመነጨ መሆኑን አሰበ። ከዋም ሊሰነዘር ከሚችል ጥቃት ግዛቲቱንም ለመከላከል ምንም አይነት ቅድመ ዝግጅት አላደረገም። ከጥቂት ሳምንታት በኃላም የቼንግ ግዛት ጦር የሁን ግዛት አጥለቀለቀው ግዛቲቱንም ተቆጣጠሩ እስከመጨረሻው ፀና።

አስገራሚ አጫጭር ታሪኮች 😲

29 Aug, 07:46


#አራቱ__ሻማዎች

በአንድ ቤት ውስጥ  አራት ሻማዎች በርተው ይታዩ
ነበር ፡፡ “ እነዚህ አራት ሻማዎች በሹክሹክታ ይጨዋወታሉ፡፡
አንደኛው እንዲህ አለ” እኔ ሰላም(PEACE)
ነኝ ማንም ግን እንዳበራ የሚፈልግ የለም፡፡ስለዚህ
መሄድ አለብኝ “ ወዲያው ነበልባሉ ቀንሶ ሙሉ
ለሙሉ ጠፋ፡፡

👉ሁለተኛው ሻማ “ እኔ እምነት(FAITH) ነኝ
አብዛኛው ጊዜ እታመማለሁ ፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ አላስፈልግም ፡፡ በመሆኑም እየበራሁ መቆየቴ ዋጋ የለውም ፡፡ ” ይህን እንደተናገረ ወዲያው ንፋስ ነፍሶ ጠፋ፡፡

👉በተራው ሶስተኛው ሻማ በሀዘን ይናገራል ። “እኔ ፍቅር(LOVE) ነኝ ፡፡ በርቼ ለመቆየት ብርታቱ
የለኝም ፡፡ ሰዎች እኔን ጠቀሜታ ወደ ጎን ብለውታል ። አጠገባቸው ያሉትን መውደድ ዘንግተውታል፡፡” ብሎ ይጠፋል፡፡

ወዲያው አንድ ልጅ ወደ ቤት ሲገባ ሶስቱ ሻማዎች ጠፍተው ተመለከተ፡፡” ለምን
አልበራችሁም …እስከመጨረሻው መብራት ይጠበቅባችኃል!” አለ፡፡
ይህን ብሎ ልጁ ማልቀስ ጀመረ ፡፡ ይህን ጊዜ አራተኛው ሻማ “ አይዞህ እኔ እየበራሁ
እስካለሁ ድረስ ሌሎቹን ሻማዎች ደግመን ማቀጣጠል እንችላለን ale ፡፡

እኔ ተስፋ(HOPE) ነኝ አለ ፡፡
ልጁ አይኖቹ ብሩህ ሆነው በደስታ ፊቱ ተሞላ ፡፡የተስፋ ሻማውን አንስቶ የጠፉትን ሶስቱን ሻማዎች (አበራቸው) ፡፡
የተስፋ ነበልባል በጭራሽ ከህይወታችን ውስጥ መጥፋት የለበትም ፡፡ እንዲህ ሲሆን

እያንዳንዳችን ተስፋን (HOPE) ፣ እምነትን (FAITH) ሰላምን (PEACE) እና ፍቅርን (LOVE) ማቆየት እንችላለን ። ተስፍ ካጣን ግን ሁሉን ነገር እናጣለን ።
፨ ተስፋ ከማጣት ይሰውረን
 
   
t.me/asgrami_tarikoche

አስገራሚ አጫጭር ታሪኮች 😲

23 Jul, 18:35


ራስህን እየገደልክ ነው...

በሰሜን አርክትክ ላይ የሚኖሩ እስኪሞ የተባሉ ጎሳዎች ተኩላ ለመግደል ሲሞክሩ የሚዘይዱ ዘዴ አለ። በበረዶው ውስጥ ጫፉ በጥቂቱ የወጣ ቢላ ይደብቃሉ በላዩ ላይ ጥቅት የበግ ደምን ያደርጉበታል ። ተኩላው ደሙን አሽትቶ ይመጣል ። በረዶው ላይ ያለውን ደም መላስ ይጀምራል ።

ደሙ ይጣፍጠዋልና ፍጥነቱን እየጨመረ መላስ ይጀምራል ። በዚህ ፍጥነት ውስጥም እያለ ሳያስበው ደም ደም የተቀባው የተቀባው ቢላዋ ምላሱን ይቆርጠዋል። ነገር ግን ደም መላሱን አያቆምም ። አሁን ላይ ይህ ተኩላ ባለማወቅ ከራሱ ምላስ የሚፈሰውን ደም እየላሰ ነው ሆኖም ጣፍጦታል እና በፍጥነት መላሱን ይቀጥላል ከመጠን በላይም ደም ይፈሰዋልና በነጋታው ተኩላው ሞቶ ይገኛል። የራሱን ደም እየጠጣ እንደነበረም አልታወቀውም ።

ይህ ተኩላ ከእኛ ታርክ ጋር ይቆራኛል። ብዙዎቻችንን ጊዜያችን የምናሳልፈው በስልካችን ላይ አልያም በቴሌቪዥን ላይ ነው ግዜአችንን ሳንጠቀምበት እንዲሁ ያልቃል.....ይጣፍጣልና ጥቂት ብቻ አይበቃንም በፍጥነት እና በሀይልም ሕይወታችንን ግዜአችንን ልሰን እየጨረስን ነው ።

አስገራሚ አጫጭር ታሪኮች 😲

20 Jul, 18:50


🚸You can invite friends and get rewards in TON.

💎For each friend you will receive 0.009 TON.

https://t.me/IncubationRobot?start=03406540410

አስገራሚ አጫጭር ታሪኮች 😲

17 May, 04:46


በአንድ ዩኒቨርሲቲ የሳይኮሎጂ ዲፓርትመንት መምህሯ ተማሪወቿን አንድ
Assignment መስጠት ፈለገች..!! ተማሪወቿን ድንች ይዘዉ እንዲመጡ
አዘዘች፡፡ ድንቾቹ ላይም የሚጠሏቸዉን ሰወች ስም እንዲፅፉ አዘዘቻቸዉ..
የሚያመጡት የድንች ብዛትም በሚጠሏቸዉ ሰወች ብዛት ልክ እንዲሆን
አለች፡፡ በሁለተኛዉ ቀን አንዳንዶቹ 3፡ሌሎች 5 ቀሪወቹ ደግሞ 8 ድንቾቹን
የሚጠሏቸዉን ሰወች ስም ፅፈዉ አመጡ..መምሯ ደግሞ <<ከዛሬ ጀምሮ
ለአንድ ሳምንት እኒህን ድንቾች በሻንጣችሁ ይዛችሁ ትዞራላችሁ...ሽንት
ቤት ስትሄዱ እንኳ መተዉ አትችሉም!>> ብላ አዘዘች . ቀኑ እየጨመረ
ሲሄድ ድንቹ በመበላሸቱ ሽታዉ ይረብሻቸዉ ስለጀመረ ተማሪዎቹ ቅሬታ
ማቅረብ ጀመሩ..በተለይም 8 የያዙት ከሽታው በተጨማሪ ክብደቱ
እንደበዛባቸው መናገር ጀመሩ፡፡ . ከሳምንት በኋላ የአሳይመንቱ ገደብ
ስላበቃ ተማሪወች ድንቹን አዉጥተዉ እንዲጥሉ ተፈቀደላቸዉ:: ከዛም
መምህሯ<<እህ እንዴት ነበር?>> ብላ ጠየቀቻቸዉ...ሁሉም ማጉረምረም
ጀመሩ ..."አረረረ ከክብደቱ ሽታዉ...አረ በጣም ነዉ የሚያስጠላዉ"...አሉ
. . መምህሯ<<አያችሁ በልባችሁ የምትሸከሙት ጥላቻም እንዲሁ
ነዉ...ጥላቻt ልብን ይመርዛል.. በምትሄዱበት ሁሉም እየተከተለ
ይረብሻችኋል...ለአንድ ሳምንት የተበላሸ ድንችን ሽታ መቋቋም
አልቻላችሁም..አስቡት ደሞ በጥላቻ የተመረዘን ልብ እድሜ ልካችሁን
ይዛችሁ ስትኖሩ!!>> አለቻቸዉ . . ጥላቻን ከዉስጣችሁ አዉጡት..ና ከእዳ
የፀዳችሁ ሁኑ!! እዉነተኛ ፍቅር እንከን አልባን ሰዉ ማፍቀር ሳይሆን ንፁህ
ያልሆነን ሰዉ በንፁህነት መዉደድ ነዉና!!!


@asgrami_tarikoche

አስገራሚ አጫጭር ታሪኮች 😲

11 Apr, 17:53


ከውሻ እና ከ አቦሸማኔ የቱ ሊፈጥን ይችላል?" ተብሎ በዓለም ላይ ካሉ ፈጣን የውሻ ዝርያወች ተመርጠው ከአንድ አቦሸማኔ ጋር የውድድር ፕሮግራም ይደረጋል።

ውድድሩ ሲጀመር ውሾቹ ተፈትልከው ሲሮጡ አቦሸማኔው ስንዝር ያህል እንኳ ለመሮጥ ፍላጎት አላሳየም።
በዚህ የተገረሙት ታዳሚዎች የውድድሩን አላፊ "አቦሸማኔው ለምን ሊሮጥ አልሞከረም?" አሉት።

አላፊውም "አንዳንዴ ምርጥነትህን_የማይገባ (የማይመጥንህ) ቦታ ላይ ለማሳየት መሞከር የስድብ ያህል ነው" አላቸው።
Don't prove your self every where' ማንነትህን በማንኛውም ቦታ ላይ ለማሳየት አትሞክር።
ምክንያቱም እንደ አቦሸማኔ የሆነ አቅምህን ከውሾች ጋር አውርደህ አትፎካከር።

     ወዳጄ ሁሉም ነገር ቦታ እና ጊዜ አለው
           በልክ እና የእውነት እንኑር


      @asgrami_tarikoche

አስገራሚ አጫጭር ታሪኮች 😲

02 Mar, 15:03


ሁለት ፈረሶች ጭነት ተጭነው ይጓዙ ነበር ።ፊት ፊት የሚሄደው ብርቱ ሲሆን የኃለኛው ግን ልግመኛ ነበር። ነጂዎቻቸውም የኋለኛውን ፈረስ ጭነት ወደ ቀዳሚው ፈረስ አዛወሩት ። ልግመኛውም የኋለኛ ፈረስ ሸክሙ ስለተራገፈበት ዘና ብሎ እየተጓዘ ለብርቱው ፈረስ እንዲ አለው ። ድካምና ላብ በጣርህ ቁጥር ይበልጥ ትጎዳለህ።ወደ ቤት በደረሱም ግዜ ባለቤቱ "ለምን ሁለት ፈረስ እቀልባለሁ ሁሉንም ጭነት አንዱ ፈረስ ነው የሚሸከመው ።አንድ ፈረስ ሚፈልገውን ምግብ ሁሉ መስጠትና ሌላኛውን ማረድ የተሻለ ነው ። ምክኒያቱም ከልግልመኛው ፈረስ ቢያንስ ቆዳ አገኛለሁ "እናም አደረገ ።

አስገራሚ አጫጭር ታሪኮች 😲

18 Feb, 10:55


የዘንድሮ ተማሪዎች👨‍🎓👨‍🎓


አንድ ለትምህርት ቤቱ አዲስ የሆነ መምህር ክላስ ዉስጥ ገብቶ እራሱን ካስተዋወቀ በኃላ ።

አንድ ተማሪ ጋሸ ስለ ጠቅላላ እዉቀት ጥያቄ አለኝ ብሎ ተነሳ።።።።።።።።።።።።።

ተማሪ👨‍🎓፦ ዝሆንን ፍሪጅ ዉስጥ ለማስገባት ብንፈልግ እንዴት አድርገን እናስገበዋለን?
.
መምህር👨‍🏫፦ አላወኩም
.
ተማሪ፦ ቀላል እኮነዉ ፤ፍሪጁን በመክፈት፥ ሌላም ጥያቄ አለኝ።
.
መምህር👨‍🏫፦ እሽ ቀጥል
.
ተማሪ👨‍🎓፦ አህያንስ ፍሪጅ ዉስጥ ማስገባት ብንፈልግስ እንዴት አድርገን ነዉ የምናስገባት?
.
መምህር👨‍🏫፦ ይችማ ቀላል አይደለች፣ ፍሪጅን በመክፈት
.
ተማሪ👨‍🎓፦ አይደለም ፤መጀመርያ ዝሆኑን ማዉጣት
.
መምህር👨‍🏫፦ ይገርማል
.
ተማሪ👨‍🎓፦ አሁንም ጥያቄ አለኝ
.
መምህር👨‍🏫፦ እሽ
.
ተማሪ👨‍🎓፦ ሁሉም እንስሳ የነብር ልደት ሁኖ ሂደዋል አንድ እንስሳ ብቻ ቀረ ማነዉ እሱ?
.
መምህር👨‍🏫፦ አንበሳ ምክንያቱም ሁሉንም እንስሳት ስለሚበላቸዉ።
.
ተማሪ👨‍🎓፦ አይደለም፣አህያ ነች
ምክንያቱም ከሰሀታት በፊት ፍሪጅ ዉስጥ ስለነበረች።
.
መምህር👨‍🏫፦ እየቀለድክ ነዉ?
.
ተማሪ👨‍🎓፦ አሁን የመጨረሻ ጥያቄ ባህር ተሻግረህ ለማለፍ ፈራህ ምክንያቱም አዞ አለ ብለህ ስለምታስብ።
እንዴት ብለህ መሻገር ትችላለህ?
.
መምህር👨‍🏫፦ በጀልባ ነዋ !
.
ተማሪ፦ አይደለም ፣እየዋኘህ ምክንያቱም አዞ የነብርን ልደት ለማክበር ስለሄደ፥😂😂😂😂

t.me/asgrami_tarikoche