አንጾኪያ ሚድያ @antsokia77 Channel on Telegram

አንጾኪያ ሚድያ

@antsokia77


አንጾኪያ ሚድያ (Amharic)

አንጾኪያ ሚድያ የቴሌግራም ኮርፖሽን ነው ከሚለው በፊት የእንደሚያወቅን መንገዶችን ይጠቀመ. እናቴላግራም እየጠቃላይ ከዚህ በፊት ላይ የተወደደ ሆኖ ማፍረስበት በርካታ ትችላለች. nnለምን አንጾኪያ ሚድያ ይህን ባለሙያ ይጠቀሙ። አንጾኪያ ሚድያ ከዚህ በፊት ላይ የሚያደርጉ መረጃዎችን እንቀጣበል። የቴሌግራም ኮርፖሽንን በመጫን ማዋቀር ወይም ማውጣት ጠቃላይ ነው። ስለዚህ ይህ ቻና ማለት ነባብ ይሰጠጣል። nnአንጾኪያ ሚድያ ለመመለስ ቅንጅት መሣሪያዎችን ለመቆጣጠር ይጠቀሙ. እኛም የሚመዝገበው መርሃ ግባዊ እና ኢንፒሲዝም መረጃለው። ጠቀላይ ችግርን ለማግኘት እባኮትን ከቴሌግራም ኮርፖሽን ጋር በመጫን ላይ መሆን ይገባል።

አንጾኪያ ሚድያ

25 Nov, 12:32


https://vt.tiktok.com/ZSjXJmu84/

አንጾኪያ ሚድያ

11 Nov, 15:42


https://youtu.be/qjaYR-0snnc?si=kj9kqucVkAgL0DOS

አንጾኪያ ሚድያ

04 Nov, 17:12


https://vt.tiktok.com/ZSjrxsJm2/

አንጾኪያ ሚድያ

28 Oct, 14:54


https://youtu.be/zNqdtQBhDms?si=8I2l6JIS53dy3dKN

አንጾኪያ ሚድያ

25 Oct, 01:18


https://youtu.be/gBVLd114cY0?si=nXbHossnDIp0lz74

አንጾኪያ ሚድያ

23 Oct, 05:06


https://youtu.be/1nJs8LG-WAY?si=MFz72fJwvJndbRry

አንጾኪያ ሚድያ

22 Oct, 23:30


https://youtu.be/VgocIBeb9G8?si=_cMgweowibJu2Gti

አንጾኪያ ሚድያ

19 Oct, 15:59


https://youtu.be/JR0Lzrn66ms?si=OAZOXAjcoGwQHS7n

አንጾኪያ ሚድያ

19 Oct, 01:08


ህይወት አዙሪት ናት።ረጅም ርቀት የተጓዝክ ቢመስልህ የምትጨርሰው ከጀመርክበት ነው።ራቁትክን ትወለዳለህ እርቃንህን ወደ መቃብር ትወርዳለህ።በጥርስ ዐልባው ድድህ እየጋጥክ ትጀምራለህ ጥርሱን ባረገፈው ድድህ እያልጎጠጎጥክ ትጨርሳለህ።የህይወት ትግል እየዳህ ትጀምራለህ አጎንብሰህ ትጨርሳለህ።ዘመንም ተምኔታዊ ነው።መስከረም ጥቅምት ብሎ ያስጀምርህና መስከረም ብሎ ይመጣብሀል።ሰኞ ማክሰኞ ብለህ ተጉዘህ እንደገና ሰኞ ትላለህ።ሕይወት አዙሪት ናት!መጀመሪያህ መጨረሻህ ነው።የጀመርክበትን አትርሳ መጨረሻህ ነውና።የጀመርክበትን አትናቀው ትጨርስበታለህና።ተራ ሰው ሆነህ ትጀምራለህ ተምረህ እውቀት ብትጨምር ነግደህ ሀብት ብታገኝ ተሹመህ በህዝብ ላይ ብትሰለጥን ክቡረ ክቡራን ሆነህ የወርቅ ካባ ብትለብስ የምትጨርሰው እንደ ተራ ሰው አፈር ለብሰህ ነው።
ባለማወቅ ትጀምራለህ በመዘንጋት ትጨርሳለህ ዕውቀት አላመጣህምና ዕውቀትም ይዘህ አትሄድም።በለቅሶ ትጀምራለህ በጭንቅ ትጨርሳለህ።በሰው እቅፍ ትጀምራለህ በሰው ሸክም ትጨርሳለህ።
ገፅ 314_315
ከመርበብት
በዶ/ር አለማየሁ ዋሴ

አንጾኪያ ሚድያ

16 Oct, 15:11


https://youtu.be/ssO4YoTdCw0?si=PHqke7FsSAFZYx92

አንጾኪያ ሚድያ

14 Oct, 14:48


https://youtu.be/CmuG7NNGvvg?si=DlvD_rienJI779tW

አንጾኪያ ሚድያ

08 Oct, 11:56


በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

“አሐቲ ድንግል”

በፈውስ መንፈሳዊ የዩቲዩብ ቻናል የህይወትን ቃል በሚመግቡን በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ ተጽፎ በ628 ገጾችና በ12 ምዕራፎች የተሰነደ
መጽሐፍ ነው፡፡

ከኅሊና አምላክ እስከ ዕርገቷ ድረስ ያለውን የእመቤታችንን ሙሉ የሕይወት ጉዞና በርካታ ምሥጢራት የያዘ ድንቅ መጽሐፍ ነው፡፡

እመቤታችን በነገረ ድኅነት ያላት ድርሻ ምን ይመስላል? ስለ እመቤታችን የሚነሡ ጥያቄዎች በመጽሐፍ ቅዱሳዊ የአበው ትምህርት እንዴት ተዳሰሰ? እንዴትስ በፍቅሯ ማደግና መጽናት ይቻላል? ሌሎችም መልሶችን የያዘው ይህ ግዙፍ መጽሐፍ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ጨምሮ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በተገኙበት የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 2/2017 ዓ.ም ከቀኑ 7 ሰዓት ተኩል ጀምሮ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አዳራሽ ይመረቃል፡፡  ሁላችሁም እንድትገኙ በአክብሮት ተጠርታችኋል።

አንጾኪያ ሚድያ

07 Oct, 23:47


-ሲኖሩ በሰማዕትነት ሲሞቱ በታሪካዊነት፦
በምድር ላይ መኖር የምንችለው ባአጭር ዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ነው።
ከሞት በኋላ ሁለተኛ ለብዙ ዘመናት መኖር የምንችለው ግን በመልካም ታሪካችን ነው።
ታሪክ የሠራ ሰው ዳግም በታሪክ ህልውና ውስጥ ሕያው ሁኖ ሲወሳ መኖር ይችላል።
ህያው አድራጊ ታሪክ ደግሞ ዝም ብሎ በስንፍና አይሠራም።
ራስን ሰጥቶ ሞትን ንቆ አጥቅቶ ነገን አልሞ በመሥራት ነው እንጂ።
ይልቁንም ትንሣኤ ሙታን ያለው ሰው ሁልጋዜም ታሪካዊ ሕያውነትን በህሊናው ማየት ግድ ይለዋል።
ስለሆነም ከሞት በኋላ በታሪክ ህልውና ውስጥ ለመኖር ምን እየሠራን ነው?
ወይስ አሁናዊ ብቻ ሁነን ለመቅረት ነው የምንፈልገው?
ክፉ ሰው ርኩስ መንፈስን አምኖ ምእመናንን ለማጥፋት ለክፉ ታሪክ ከተነሣ እኛ መንፈስ ቅዱስን አምነን ትናንትን ለትውልድ ለማስረከብ የነገ መልካም ታሪክን ለማንበር መነሣሣት ግድ ይለናል።
ምክንያቱም ዛሬ ባለችን በዓላማ በቁርጠኝነት ራሳችንን ሰጥተን ካልሠራን ለነገ ትውልድ ታሪክም ሃይማኖትም አይኖረንም።
በታሪክ ህልውና ውስጥ እንዳናይ የሚያደርገን ገርጋሪያችን ፍርሀት እና አስመሳይነት ነው።
ፈሪ ሰው ደግሞ የክርስቶስ መስቀሉን መሸከም አይችልም።
መስቀልን ያልተሸከመ ሰው ደግሞ መከራ አይንካኝ ሆዴ ይሙላ ደረቴ ይቅላ ሲል የሰማዕትነት ክብር ታመልጠዋለች።
ሲኖሩ በሰማዕትነት ሲሞቱ በታሪካዊነት ለመገለጽ ካሰቡ ፍርሀትን እና አድርባይነትን እንደ ሸረሪት ድር ገፎ መጣል ግድ ይላል።
መስሎ መኖር እና አድርባይነት ለስለላሳ ኑፋቄ ነው።
በምድር ላይ ማን ይፈራል? ሞትን እንዳንፈራው? ትንሣኤ ሙታን አለን።
አግባብስ ያለታሪክ ያለ ሃይማኖት እንዳይቀር የነገውን ትውልድ መፍራት ነው።
ለነገ አለማሰብ የነገውን ትውልድ በግልጽ መበደል ነውና።
ትናንትን እንደሚገባ ከአባቶቻችን እንደተቀበልነ ዛሬም በሰማዕትነት የተቀበልነውን አደራ እየጠበቅነ ለነገው ትውልድ የማስረከብ ሀላፊነት አለብን።
የነገ ታሪክ ሰነፎች ተቀምጠው ሳሉ እንደ ፈጣን ወፍ ማረፊያ አጥቶ በጊዜ ነፋስ ላይ በርሮ መሄዱ አይቀርም።
መሥራት ባይቻል እንኳን ለሚሠሩ ሰዎች እንቅፋት ላለመሆን መጣር ተገቢ ነው።
ከህሊናም ከታሪክም ጋራ መጣላት ትልቅ ድክመት ነው።
መሆን ያለብንን ሳንሆን መሆን ያለበት አይሆንም።

#መምህር ገብረ መድኅን እንየው

አንጾኪያ ሚድያ

07 Oct, 15:08


https://youtu.be/wyL-ztBQWdk?si=X--EvFfNt_O2b_D9

አንጾኪያ ሚድያ

06 Oct, 11:13


እግዚአብሔር ሁልጊዜ ወደ መከራ እንዳትገባ አያደርግም። አንዳንድ ጊዜ በወጀብ ውስጥ መንገድ ያዘጋጅልሃል። ግፊው በሚበዛበት ዐውሎ ነፋስ እያለፍህ ተፍገምግመህ እንዳትወድቅ ጉልበትህን ያጸናል፤ ኃይልን ያስታጥቅሃል። እንዲህ እያደረገ በመንፈስ ያጎለምስሃል።

እግዚአብሔር ዳንኤልን በአናባስት ጉድጓድ ከመጣል፣ ሠለስቱ ደቂቅን ወደ እቶን እሳት ከመግባት፣ ጳውሎስና ሲላስን ወደ ወኅኒ ከመውረድ ሊያድናቸው ይችል ነበር። ይሁን እንጂ እንዲህ አላደረገም። አምላካችን ፈተና ካለባቸው ቦታዎች ሁሉ ሊያወጣን ቃል አልገባምና። ነገር ግን በመከራ ጊዜያችን ሁሉ ከእኛ እንደማይለይና በእውነት ይዘነውም እንደ ሆነ በድል ነሺነት እናጠናቅቅ ዘንድ እንደሚረዳን ቃሉን ሰጥቶናል።

የጌታ እናት እመቤታችን የተወደደ ልጇን ይዛ በግብጽ በረሃ እንደ ወፍ ከተንከራተተች በኋላ ሕፃኑን የሚፈልገው ክፉ ሄሮድስ ሲሞት ተመልሳ ወደ ገሊላ ገብታለች። እንደ ድንግል ጌታን በመሐል እጅህ ብትታቀፍ እንኳን  ግብጽ መውረድ  አይቀርልህም። ይሁን እንጂ የመጣብህን መከራ ድል ነሥተህ ወደ ገሊላ መመለስህም እርግጥ ነው።

"ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል"
                              1ኛ ቆሮ 10፥13

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

አንጾኪያ ሚድያ

05 Oct, 14:46


http://youtube.com/post/UgkxHhgw15EG8XOI23K0s88rbak4acQDxu7N?si=vjptEVsyjQP3hvbW

አንጾኪያ ሚድያ

03 Oct, 15:20


https://youtu.be/oFnClBt3VXM?si=ugZ7YUor-yEm9CeI

አንጾኪያ ሚድያ

30 Sep, 15:45


https://youtu.be/FCSJGq47IC8?si=kk5c1R8pFIMsmmXZ

አንጾኪያ ሚድያ

30 Sep, 02:00


ድንግል ማርያም በድንጋይ ላይ ትገለጥልኝ ነበር እጅግ ግሩም ቆይታ #ከሰአሊ ቅዱስ ጋር


ዛሬ ምሽት 12:00 ላይ በአንጾኪያ ሚድያ ይጠብቁ


#አንጾኪያ ሚዲያ ሼር ሰብስክራይብ በማድረግ አገልግሎቱን ተደራሽ እናድርግ።

ወደ ቴሌግራም ግሩፓችን ሰዎችን አድ እናድርግ. https://t.me/antsokia77

https://youtube.com/@antiochmedia77?si=2VhwMdVZIA3ib1X3

1,539

subscribers

11

photos

18

videos