Ibnu Ebrahim @ibnuebrahim Channel on Telegram

Ibnu Ebrahim

@ibnuebrahim


"ዝቅ ያለው ከፍ ሊል፣ የረከሰው ሊወደድ ዘንድ እውቀት ግድ ይላል! ለማወቅ ደግሞ ማንበብ!" የንባብ ቤተሰብ ከሆኑ ይቀላቀሉን!

Facebook
👇
https://www.facebook.com/ibnuebrahim2

አስተያየት👉 @ibnu_ebrahim_bot

Ibnu Ebrahim (Amharic)

እንኳን ወደ Ibnu Ebrahim ቤተሰብ እንደሚገኝ በደንበኞች የተሰማው ንባብ ቤተሰብ ነው። እንዴት ነው ይህን ቤተሰብ? ስለሆነ እናመሰግናለን። Ibnu Ebrahim ቤተሰብ ትክክለኛ ልምድ እና ስነስርአባል ብቻ የሚቀላቀል ነው። ከሰብል የእምነት ጋራ እና ከአዕምሮው ግማሽ እንዲመሰክር ታስቦ ነው። Ibnu Ebrahim ከሆነ ስለሆኑ በበሽታም ላይ ያለውን ከፍ የሚመስል የእናት እምነት ነፃነት እና በእነዚህ ርዝመታችን ታስረው ነው። Ibnu Ebrahim ቤተሰብ፣ በራሱ ስለፈረስ አካፈልህ። ከዚህ በታች በእርሱ ላይ የተጻፈረ መለያ ይዘንህ። ከድንገተኛው እና ስብስብ ማህበረሰብ በሰሜቸ ውስጥ መደሰትን ከሚቻል ፅሁፎቹ እንጠቀሙ እና ከቻምፒዮን ተጠናቀቀ። ለማለት የFacebook ገቢዎችዎን ይግቡ። አጋምታ ከፍተኛ አመልካቾችን አገልግሎት ለማለት አስቀድሞ መልዕክት ቀርበር ። በዚህም በተጨማሪ ቦታ መሰረት ነሱ Ethiotelegram ተመልከቱ። እንደምንገኝ ከፍተኛ መረጃ ተጨባጭ ካሉት ሰዎች ጋር ስነስርአባሊ እና ቅንብስን እሳስርናለን።

Ibnu Ebrahim

12 Sep, 06:31


ጥበብ መገለጫዋ ብዙ ነው። ለአንዳንዱ ደግሞ በዚህ መልኩ ትገለፃለች።👆😍
የጥበብ አድናቂ ከሆኑ በዚህ ሊንክ ጎራ በሉና አምሮታችሁን አስታግሱ👇
https://t.me/SA_calligraphy

Ibnu Ebrahim

07 Sep, 16:19


አሏህን መች እናስታውስ?
.
ከላይ ለጠየቅኩት ጥያቄ ምላሽ የሰጣችሁኝ ቤተሰቦቼን አሏህ ያክብርልኝ! እነሆ የናንተንንም የኔንም ሃሳብ ጨምሬ ምላሹ እነሆ!
.
አብዛህኛዎቻችን አሏህን የምናስታውሰው የችግራችን ጊዜ ነው። አሏህን ጠይቄው ሰማኝ፣ በአሏህ ተመክቼ ዳንኩኝ፣ ጠይቄው ሰጠኝ፣ በሱ ተጠብቄ ጠበቀኝ። እንል እንደሆነ እንጂ በተሰጠን ነገር ከማመስገን ባሻገር የሰጠንን ነገር እንዲያዘልቅልን ዱዓ የምናደርገው ጥቂቶች ነን። አብዛህኛው አይደለም ሀጃ ሳይኖረው ዱዓ ሊያደርግ ቀርቶ ለተቸረው ውለታ ምስጋና ማድረሱንም እንጃ! ለዚህም ይመስላል በችግር ሰዓት መፈናፈኛ እስኪታጣ ድረስ በባለ ጉዳዮች የተጨናነቁት መሳጅዶች በአማን ጊዜ ጭር ማለታቸው። አብዛህኛዎቻችን አሏህን ባጣ ቆየኝ አድርገነዋልና!

ዱዓ ልታደርጉ አስባችሁ ምን ብላችሁ ዱዓ ማድረግ እንዳለባችሁ ጠፍቶባችሁ አያውቅም? ምክኒያቱም ዱዓ ሁለት አይነት እንደሆነ አናውቅማ! አዎ! ዱዓ ሁለት አይነት ነው፦ #የአምልኮ_ዱዓ እና #የጥያቄ_ዱዓ። የጥያቄ ዱዓ ሁላችንም ሲቸግረን የምናደርገው የዱዓ አይነት ሲሆን፤ የአምልኮ ዱዓ ደግሞ ምንም ጉዳይ ባይኖረንም እንኳ ከአሏህ ተብቃቂ አለመሆናችንን፣ ከሱ ሀጃ ኖረንም አልኖረን እሱን ችላ አለማለታችንን የምንገልፅበት፣ ከዚህ በፊት ስለሰጠን ፀጋ የምናመሰግንበት፣ የሰጠንን እንዲያዘወትርልን የምንማፀንበት የዱዓ አይነት ነው።

በጥቅሉ #አልሐምዱሊላህም ዱዓ ነው ለማለት ነው። አዎ! ለኛ ለሙስሊሞች የኦክስጅን ያህል ዱዓም ያስፈልገናልና ከርሱ አንዘናጋ! የነብዩላህ ሱለይማንን ፈለግ እንከተል እንዲህ እንበል፦

«ጌታዬ ሆይ! ያቺን በእኔና በወላጆቼ ላይ የለገስካትን ጸጋህን እንዳመሰግን የምትወደውንም በጎ ሥራ እንድሠራ ምራኝ፡፡ በችሮታህም በመልካሞቹ ባሮችህ ውስጥ አግባኝ»[ ሱረቱ አል-ነምል - 19 ]
.
@ibnuebrahim
@ibnu_ebrahim_bot

Ibnu Ebrahim

07 Sep, 07:00


#አህባቢ!

ወደ አሏህ የምትዞሩት(ዱዓ የምታረጉት) በምን ጊዜ(ሁኔታ) ነው?
እስኪ ንገሩኝ!
👇
@ibnu_ebrahim_bot

Ibnu Ebrahim

02 Sep, 18:49


#ኹሹዕ
.
ሶላት ውስጥ ሆኜ በጥሞና(በኹሹዕ) አለመስገዴ አሳስቦኝ ቢያንስ ይህችን ሶላት እንኳን በጥሞና ልስገድ ብዬ ብነሳ፤ በጥሞና ስለ መስገድ እያሰብኩ አንድ ረከዓ እንኳን በጥሞና ሳልሰግድ ኢማሙ አሰላመተ።🤦‍♂

ኧረ ወገን የኹሹዕ ነገር ምን በጀን???🤔
.
@ibnuebrahim
@ibnu_ebrahim_bot

Ibnu Ebrahim

30 Aug, 14:10


#አህባቢ!💕

#ስጦታ በሚል መረሃ ግብር ወደናንተ ሳበረክትላችሁ የነበረው ፕሮግራም መጠናቀቁን ከገለፅኩበት ዕለት አንስቶ ብዙዎቻችሁ ስጦታውን እንዳሳነስኩ ቅሬታችሁን ገልፃችሁልኛል። እርግጥ ነው አንሷል። ቢሆንም ግን በግሌ ወድጄ ከምከታተላቸው ውስጥ በእርግጠኝነት ልጋብዛችሁ የምችለውን ብቻ ነውና ልጋብዛችሁ የተነሳሁት ያንን በሚገባ ማከናወን መቻሌን ተስፋ አደርጋለሁ። ኢንሻ አሏህ ወደፊት ቢኖሯችሁ ብዬ የማስባቸውን የማጋራችሁ ይሆናል።

እስኪ ደግሞ እናንተ በተራችሁ የወደዳችኋቸውን፣ አንተም ብትቀላቀላቸው ትጠቀምባቸዋለህ የምትሏቸውን ቻናሎችን በስጦታ መልክ አበርክቱልኝ! ባይሆን ከዚህ በታች ያሰፈርኳቸውን መስፈርቶችን እንዳትዘነጉ፦

1- ቻናሎቹን ስትጋብዙኝ ጠቃሚ መሆናቸውን እርግጠኛ የሆናችሁባቸውን ይሁኑ። (ምን ተጠቀማችሁባቸው ብትባሉ ቢያንስ አንድ ሁለትት ነገሮችን የምትጠቅሱላቸው መሆን አለባቸው።)

2- ከ ሥስት ያልበለጡ ይሁኑ፣

3- ቻናሎቹ የራሳችሁ መሆን የለባቸውም። (ስለራሳችሁ ሌሎች እንዲመሰክሩላችሁ ተዉላቸው😉)

4- ስጦታዎቻችሁን ከዚህ በታች ባለው አድራሻ ላኩልኝ!
👇
@ibnu_ebrahim_bot

Ibnu Ebrahim

29 Aug, 18:57


..."እስኪ ንገሩልን ሸህ ሙሳ። እኛንም ሰብሰብ አድርገው ሀጅ ቢያስደርጉን ምናለ?" ስትል ጠየቀች ሰዓዳ ወደ ሁለቱ ወንድሞቿ እየተመለከተች።

"እንዲያው ወንድም አለም እንደምንም አንዴ ሂድ እንጅ እዛ ያለው ስሜት በየአመቱ ካልሄድኩ ነው የሚያስብልህ!" አለች ሃላሊ ወደ ታላቅ ወንድሟ እየተመለከተች።

"እንዴ አጓጓሽን እንኮ! አሁንማ ምን አማራጭ አለን። ታናሻችን ሄዳ እኛ ታላቆቿ ብንቀር ነውር ነው። ባይሆን የቀጣዩን ሀጅ እኔና ሸምሴ እንሄድና ከዛ ቀጥሎ ያለውን ደግሞ ሰዓዲ እና ሀውሊ ትሄዳላችሁ።" አለ አክረም የአወንታ ምላሽ ከታላቁ የሚጠብቅ መሆኑን ለማመልከት ወደ ታላቁ እያየ።

"አዎ ኢንሻ አሏህ። ሙኒ እና ሱሚ ከወዲሁ ራሳችሁን አሰናዱ!" አለ ሸምሱ ወደ ባለቤቱ ሙኒራ እና የአክረም ምስት ወደሆነችው ሱመያ እየተመለከተ። ሁለቱ ምስቶች እና ሁለቱ እህቶች በደስታ ተነስተው ተቃቀፉ።

ብቻ ምሽቱ ግሩም ነበር። ከትላልቅ ሰዎች ጋር መቀማመጥ በረከቱ ብዙ ነው። በጣም ብዙ ጉዳዮችን እያነሱ ብዙ ቁም ነገር ሲያስጨብጡን እና ከህይዎታቸው ምዕራፍ እየገለጡ ሲያጫውቱን አምሽተን የምኝታ ሰዓት ሲደርስ ከሰሙ እናት ሰዓዳ በቀር ሁሉም የሃላሊ ወንድም እና እህቶች ከነ ባለቤቶቻቸው በመኪናቸው ተያይዘው ወደየቤታቸው ሲሄዱ የተቀረነው ደግሞ ወደ ማረፊያችን ለመሄድ ተነሳን። ሰሙ እኔ እቅፍ ውስጥ እያለች ተኝታ ስለነበር ቀስ አድርጌ አቅፌ ለእናቷ አስረከብኩና ለማረፊያነት ወደተመደበልን የሃላሊ የድሮ መኝታ ክፍል ዘለቅኩ። ሃላሊ ቀድማኝ ገብታ ስለነበር የሌሊት ልብሷን ቀያይራና የኔንም የሌሊት ልብስ አዘጋጅታ ስትጠብቀኝ አገኘኋት።

"ሀጂት ለይላ! የሌሊት ልብስዎን እንዴት አስውበውታል ባክዎ!" አልኳትና ግንባሯ ላይ ሳም አደረኳት።

"ባህታዊ እርስዎን መፈታተን ከቻልኩ ብዬ ነው ሀጅ ካሊድ!" አለችና የማይነገረው ላይ ሳመችኝ።

"የድሮ መኝታ ክፍልሽ እንዳንች ቆንጆ ናት ልበል?" አልኳት የሌሊት ልብሴን ለብሼ እንደጨረስኩ ቀድሜያት መኝታው ላይ ወጥቼ ጋደም እያልኩ።

"በጣም እንጅ! እንዲያውም የረሳሁትን ነገር አስታወስከኝ። አንድ ነገር ላሳይህማ!" አለችኝና ከአልጋው ስር አንዳች ነገር አወጣች።

"ይህች ሳጥን ምን እንደሆነች ታውቃለህ? ለመጀመሪያ ጊዜ ለሀጅ ገንዘብ ሳጠራቅም የገዛኋት ባንከር ናት።" አለችና የደስታ እንባዋን እያዘነበች ባንከሯን ወደ ደረቷ አስጠግታ ጭምቅ አድርጋ አቀፈቻት።

"ማሻ አሏህ ይሄማ እኮ ትልቅ ቅርስ ነው። የኔ ውድ ባንከሯን ስታቅፊ እኮ ቅናት ቢጤ ተሰማኝ!" አልኳትና ተነስቼ ባንከሯን ከሷ ተቀብዬ ጠረዼዛው ላይ አደረኩና ወደ ደረቴ አስጠግቼ በእንባ የራሱት ጉንጮቿን ሳምኳቸው።

"እውነትህን ነው ቅርስ ናት ወደ ቤት ስንሄድ እንወስዳታለን።" አለችን ወደ ላይ ቀና ብላ እየተመለከተችኝ።

"አይ አንወስዳትም። ለሰሙ እንሰጣትና ሳንቲም ታጠራቅመበታለች።" አልኳት ይዣት ወደ መኝታው እየገባሁ።

"ሰሙ ደግሞ ምን ሊያደርግላት ነው ገንዘብ የምታጠራቅመው?" ስትል ተደንቃ ጠየቀችኝ። አሁን አልጋችን ላይ ጋደም ብለን አንዳችን ወደ አንዳች ዙረን ተኝተን ነው እያወራን ያለነው።

"ዛሬ እሷም እንደ አንቺ ከባሏ ጋር ሀጅ ማድረግ እንደምትፈልግ ነግራኛለች። ስገምት ህልምሽን ወራሽ ሳታገኚ አልቀረሽም።"

"ወላሂ በል የምርህን ነው?" ስትል ጠየቀችኝ በደስታ ከተጋደመችበት ተስፈንጥራ ተነስታ ቁጭ እያለች።

"አዎ! ምን አስዋሸኝ? ባይሆን ለዚያራ በመጣን ቁጥር ትንሽ ትንሽ ገንዘብ እየሰጠን እንድታጠራቅም እናደርጋታለን። ለአጎቶቿም ነግረን ገንዘብ እንዲሰጧት ብናደርግ የተወሰነ ገንዘብ ማጠራቀም ትችላለች።" አልኳት ከተጋደምኩበት ሽቅብ እየተመለከትኳት።

"ሱብሃነላህ! ምናለ በኔ ጊዜ እንዳንተ ሃሳቤን የሚደግፍ ወዳጅ በኖረኝ ኖሮ!" አለችና መብራቱን አጥፍታ ተጠመጠመችብኝ።
.
.
"ጨለምተኛነትን ተጠንቀቅ! ጨለምተኛነት ሽህ ጊዜ ሲገልህ፤ ተስፈኝነት ደግሞ ሽህ ህይዎት ይሰጥሃል!"
.
@ibnuebrahim
@ibnu_ebrahim_bot

Ibnu Ebrahim

29 Aug, 18:57


#ሃላሊ...21 C 👿
(Ibnu Ebrahim)
.
ሚና ገበያ በህይዎቴ ካየኋቸው ገበያዎች ውስጥ ሰፊውና አስደናቂው ነበር። የሌለ የእቃ አይነት የለም። በረካውም በዛው ልክ ነው። ከተለያዩ አህጉራት የመጡት ነጋዴዎች በጣም ብዙ አይነት አልባሳት፣ ቁሳቁሶች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ብቻ ምን ልበላችሁ ሁሉም ሙሉ ነበር። እኔና ሃላሊ ለአንዳድ እቃዎች መሸመቺያ የሚሆን ጥቂት ገንዘብ ይዘን ስለነበር ወደዚህ በረከተ ሰፊ የገበያ መዓከል ጎራ የማለቱን እድል አግኝተን ነበር። ቤት ውስጥ የጎደሉንን አንዳንድ የቤት እቃዎችን እና ለወዳጅ ዘመዶቻችን እንዲሁም ለወላጆቻችን ስጦታወችን ሸምተናል።
*
ሰሙ ለጠየቀችኝ ጥያቄ ምላሽ ሳልሰጣት ለነ አባቢ እና ለነ ቶፋ የገዛሁላቸውን ስጦታ በትንሽዬ የጀርባ ቦርሳ ውስጥ አድርጌ ከክፍሉ ወጣሁ። አሁንም ድረስ እማማ ፋጤ እልልታቸውን እያቀለጡት ነው።

"ጎሽ! ጎሽ! ጎሽ! እማማ ሀሊማ አንቺ ነሽ ልጅ የወለድሽው። እንዲህ ነው እንጂ ልጅ ማለት! ነይ እስኪ ዘይሪኝ ልጄ ነይ!" የሚለው ንግግራቸው እነ ሃላሊ ያሉበት ክፍል ውስጥ ጥርት ብሎ ይሰማኛል። ሃላሊን እየዘየሩ መሆናቸው ነው። እማማ ፋጤ ሁሌም እንዲህ ናቸው። አንድን ነገር ለማጠልሸትም ሆነ ካጠለሹ በኋላ አይናቸውን አጥበው ለማወደስ የሚቀድማቸው የለም። አስታውሳለሁ ሃላሊን ላገባ እንደሆነ የሰሙ ዕለት፤

"ወይ የዘንድሮ ልጅ! ገና ንፍጡን በስርዓት ሳይናፈጥ ለትዳር ምን አሮጠው? ደሞ ለመቃጠል! ፋጤ ምናለች በሉኝ! ተንገብግቦ እንደገባው ተንገብግቦ ሲወጣ ልናይ አይደል?" ብለው አሟርተውብኝ ነበር።😁 በኋላ ላይ ግን የሰርጋችን ቀን እንደሳቸው ሰርጉን ሰርግ ያስመሰለ ወዳጅ አልነበረም!😂 እልልታቸውን፣ ሽር ጉድ፤ ላይ ታች ማለታቸውን ላየ ሁሉ የሙሽራው እናት መስለው ነበር።

አሁን ሰሚራ እንደነገረችኝ ከሆነ ወደ ሀጅ ስንሄድ "የምትበላው የላት የምትከናነበው አማራት!" ሲሉ ተርተውብናል። ቢሆንም ግን ዛሬ ደግሞ "በሉ!ይቅናችሁ በሰላም ወጥታችሁ ግቡ!" ብለው የሸኙን ይመስል እልልታቸውን እያስነኩት ይገኛሉ።

እማማ ፋጤ አብዛህኛውን ማህበረሰባችንን የሚወክሉ ይመስሉኛል። ሰው ራዕይ ሲሰንቅ ራዕዩን የሚያኮስሱ፣ በሁለት እግሩ ለመቆም ሲፍጨረጨር እሾህ የሚተክሉ፣ እጆቹን በተስፋ ሲከነዳ የሚቀለጥሙ ጨለምተኞችን 100% የሚወክሉ ጨለምተኛ። አዎ ለእንደነዚህ አይነቶች ነገ ፀሐይ የሚወጣ፣ የዛሬ ተስፋ የሚያብብ፣ የዛሬዋ ችግኝ አጎምርታ የምታፈራ መሆኑ አይታያቸውም። ለእነሱ ከአንድ እርምጃ በኋላ ገደል፣ ከአንድ ዝላይ በኋላ ውድቀት እንጅ ሌላ የለም። ፊት ለፊታቸው ያለ ካለም ጨለማ እና ጨለማ ብቻ ነው።

እማማ ፋጤ ለየት የሚያረጋቸው ነገር ቢኖር ጨለማውን ነግቶ ሲያዩ አይናቸውን በጨው አጥበው የብርሃኑ ተቋዳሽ መሆን መቻላቸው ነው። ቢሆንም ግን አልቀየማቸውም። በዛው ልክ ከልጅነቴ ጀምሮ እንደ እናት ሆነው ሳጠፋም ሳላጠፋም እየቆነጠጡ አሳድገውኛልና!😁

መጀመሪያ ለአባቢ እና ለጋሽ ሐሚድ ያመጣሁላቸውን ሻል፣ መስገጃ እና ሽቶ ጀባኋቸው። እነሱም በአፀፋው ምስጋና እና ምርቃቱን አጎረፉልኝ። ቀጥሎም ለሷሊህ፣ ለሪድዋን፣ ለማሜ እና ለቶፋ ለእያንዳንዳቸው ጀለብያ እና ሽቶ አበረከትኩላቸው። እነሱም ምስጋናቸውን አቀረቡልኝ። ለባለ ትዳሮች ከነ ምስቶቻቸው ቢሆንም ስጦታ ያመጣንላቸው ለሴቶቹ በሃላሊ በኩል እንዲሰጣቸው ነው የተስማማነው። ባይሆን በሀጅ ፕሮሰስ ላይ ሆነን ችላ ላልናቸው ለሪድዋን እና ለአዲሷ ባለቤቱ ለየት ያለ ስጦታ አምጥተንላቸዋል። ኢንሻ አሏህ ግርግሩ ቀለል ብሎ ከተረጋጋን በኋላ ቤታቸው ሄደን የምንዘይራቸው ይሆናል።

ስጦታቸውን ካደረስኩ በኋላ የፕላስቲክ መጠጫ ኩባያ አምጥቼ ለሁሉም የዘምዘም ውሃ አደልኳቸው። ለሁሉም በቅድሚያ ሰጥቼ ሆነ ብዬ ማሜን እና ቶፋን መጨረሻ አደረግኳቸው።

"መቼስ ከላጤ ባለ ትዳር መቅደም ስላለበት እንደሆነ ትረዱኛላችሁ ብዬ አስባለሁ። 'ዘምዘም ውሃ ለተጠጣበት ዓላማ ሁሉ ይሆናል!' ብለዋል ረሱላችን። እስኪ ትዳርን ወፍቀን ብላችሁ ጠጡት!" ብዬ ስሰጣቸው ሁሉም ሳቁባቸው።

"ኧረ ተው ካሊዴ የጓደኛ ገመና መሸፈን ሚባል ነገር አለኮ!" ሲል መለሰልኝ ቶፋ እንደማፈር እያለ። ቶፋ ለብቻችን ስንሆን ካልሆነ በቀር ብዙ ማውራት የማያበዛ አይናፋር ነው።

"ልጆቼ! የላጤነት ገመና ልክ እንደ ግንባር ቁስል ነው። ልትደብቁት አትችሉም። ባይሆን እንደናንተ ያሉትን ሸበላ አግቡና አይባችሁን ይሰትሩላችሁ!" ሲሉ አባቢ መለሱላቸው።

"እውነት ብለዋል ሸህ ሙሳ! ላጤ ሰው ልክ እንደ ነጠላ ነው። በየሄደበት ሁሉ አይን አይሞላም። እስኪ ሪድዋንን ተመልከቱት ግርማ ሞገሱ አያስፈራም? ሃሃሃ" ሲሉ ጋሽ ሀሚድ ስቀው አሳቁን።

"ነጠላማ ነጠላ ነን። አታዩም እንዴ በየሄድንበት ሁሉ እንደ ፈንድሻ ቡና ቁርስ ሲያደርገን!" ማሜ ቀልድም ብሶትም የተቀላቀለበትን ንግግር ተናገረ።

"ታዲያ ሌላ ነጠላ ፈልጎ ጋቢ መሆን ነዋ! ሃሃሃ" ሪድዋን ነበር።

"ጎሽ! 'አዲስ እረኛ ከብት አያስተኛ!' አሉ። እርሶም ወግ ደርሶት እኛን መምከር ጀመሩ? ቶፋ ግድ የለህም እቁብም እድርም ገብተንም ቢሆን ማግባት አለበን!" ሲል ማሜ ሁላችንንም አሳቀን።

"አንተ ደልቶሃል። በሉ ደህና ዋሉ የምንሄድበት ስላለን እኔና ማሜ እንሂድ!" ቶፋ ከመቀመጫው እየተነሳ።

"እድሜ ልክህን ሸሽተህ ትችለዋለህ?" ስል ጠየቅኩት እየሳቅኩበት።

"ሀጂ! እርሱን ተወው እና መኪናህን ለዛሬ እንድንጠቀማት ፍቀድልን ነገ እመልስልሃለው።" ሲል ርዕሱን ለማስቀየር ሞከረ።

"ይቻላል! እነ ሷሊህም መሄድ ሳይፈልጉ አልቀረም እግረ መንገዳችሁን አድርሷቸዋ!" አልኩት። ሷሊህ እና ሪድዋን ለመሄድ መነሳታቸውን እንዳስተዋልኩ።

"ያው እኔና ሪድዋን ተሳቢ ስላለን በባጃጅ ብንሄድ አይሻልም?" አለ ሷሊህ ሞባይሉን አውጥቶ ለባለቤቱ እየደወለ። ማሜ፦
"ዛሬማ ሰው ሁሉ እኛን ለማስቀናት ነው ቆርጦ የተነሳው። ና ባክህ እንሂድ!" ብሎ ቶፋን ቀድሞት ወጣ። እነ ሪድዋንም እየሳቁ ተከተሉት።
*
ዛሬ ቀኑም ማታውም በወዳጅ ዘመድ የደመቀ ነበር። እነ ማሜ እና ሌሎች እንግዶች ከሄዱ በኋላ የተቀሩት ቤተ ዘመድ ተሰባስቦ ስንጫወት ነው ያመሸነው። የሃላሊ ሁለት ወንድሞች ሸምሰዲን እና አክረም በስራ መብዛት የተነሳ ቀን እኛን ቤት ካስገቡን በኋላ ብዙም ባይቆዩም ምሽቱን ከኛ ጋር ሲጫወቱ ለማሳለፍ መጥተዋል።

"እናንተ ስትንቀራፈፉ አጅሪት ቀድማችሁ ቁጭ አለችላም አይደል?" አሉ ጋሽ ሀሚድ አንዴ ወደ ሸምሰዲን እና አክረም፣ አንዴ ደግሞ ወደ ሰዓዳ እና ሀውለት አፈራርቀው እየተመለከቱ። ሰዓዳ ማለት የሃላሊ ሁለተኛ ታላቅ ህት እና የሰሚራ እናት ስትሆን፤ ሀውለት ደግሞ ከሃላሊ በ3 አመት የምትበልጥ ታላቅ እህቷ ናት።

"ከኋላ የመጣ አይን አወጣ አይደል ተረቱስ!" አለ የሁላቸውም ታላቅ የሆነው ሸምሰዲን።

"ወገኛ! ተረቱን ትታችሁ ለበይክ ብትሉ ነው የሚበጃችሁ!" አሉ ወ/ሮ ጦይባ አፋቸውን በማሾፍ መልኩ ጠመም አድርገው።

"አዎ! ወላጆቻችሁ እውነታቸውን ነው። አንድ ሰው አቅሙ ከፈቀደ በህይወቱ አንዴ ሀጅ የማድረግ ግዴታ አለበት። እናንተ ደግሞ ማሻ አላህ እሁድን እንኳን ከቤተሰብ ጋር ለማሳለፍ እስከማትችሉ ድረስ ቢዚ የሚያደርግ ስራ አላችሁ። እንዲያ አላሰባችሁበት እንደሆነ እንጅ አይደለም ለራሳችሁ ለተቀሩት እህቶቻችሁ ጭምር የሚበቃ ሪዝቅ ነው አሏህ የቸራችሁ!" አሉ አባቢ...

Ibnu Ebrahim

28 Aug, 18:18


🎁#ስጦታ_አራት
.
ዛሬ አንድ ትልቅ ደሴት በስጦታ መልክ ላበረክትላችሁ ወደድኩ። የመጨረሻ ስጦታዬ ነውና በሚገባ ተጋበዙልኝ!😊

እንዳልኳችሁ የዛሬው ስጦታዬ አድማሰ ሰፊ የሆነ ውብ ደሴት ነው። የምድርም ይሁን የናንተ ወገብ እስኪንቀጠቀጥ ምድርን ብታስሱ ይሄንን ደሴት የትም አታገኙትም። ምክንያቱ ደሴቱ የምናብ ደሴት ነውና!😉

እውነት ለመናገር ምናባዊ ፅሁፎችን ለሚወድ ጥም ቆራጭ ደሴት ነው። ደሴቱ ያላካተተው መዝናኛ፤ የጎደለው መማሪያ የለም። ወደ ደሴቱ ጎራ ስትሉ ድንቅ ድንቅ አስጎብኚዎች ከሚገርም የማስጎብኘት ክህሎቶቻቸው ጋር እየጠበቋችሁ ታገኛላችሁ። በእነዚህ አስጎብኚዎች የሚቀርብላችሁ የምናብ ጉብኝት ለጉድ ነው። ደሴቱን ካስዋቡት ውስጥ እነዚህ አስጎብኚዎች ናቸው። በቃ ምን ልበላችሁ። ምናባዊ ታሪኮች፣ ምናባዊ ጉዞዎች፣ ምናባዊ የመድረክ ፕሮግራሞች፣ የነብያት፣ የሶሃባ እና የቀደምት ከዋክብቶችን ታሪኮችን ከጎበኛችሁ የዛው ደሴት የመኖሪያ ፍቃድ መጠየቃችሁ አይቀሬ ነው።

የደሴቷ ባለቤቶች አንድነት ይደንቀኛል። ብዙ ሆነው እንደ አንድ፤ አንድ ሆነው እንደ ብዙ መስራትን አስተምረውኛል፣ ከምናብ ደሴቶቻቸው ጥበብን አቅምሰውኛል፣ በእውቀታቸው አስደንቀውኛል፣ የእድሜያቸውን ለጋነት ልብ ስል በራሴ እንዳፍር አድርገውኛል።

እስኪ ለዛሬ በኔ ወጭ ደሴቷን ጎብኙልኝ!
#ትኬቱ_እነሆ!
👇
t.me/Re_ya_zan

Ibnu Ebrahim

26 Aug, 17:47


#ምን_ተይዞ⁉️
.
.
"ለምን አታገባም?"
"ምን ተይዞ?"
.
ይህ የሁሉም ላጤ ምላሽ ነው። እኔ ምለው ግን ለትዳር ሲሆን የያዝነው ነገር የሚያሳስበንን ያህል ለአኼራው ጉዞ ቢያሳስበን ምናለ?
ምናለ "ምን ተይዞ አላህ ፊት ይቀረባል?" ብለን ቢጨንቀን?🤔
.
@ibnuebrahim
@ibnu_ebrahim_bot

Ibnu Ebrahim

19 Aug, 16:30


🎁 #ስጦታ ሦስት
.
ዛሬ ሦስተኛ ስጦታዬን ይዤላችሁ መጥቻለሁ። እንደስከዛሬዎቹ የዛሬውንም ስጦታዬን እንደምትወዱልኝ ተስፋ አደርጋለሁ።(ምን ተስፋ ብቻ እርግጠኛም ነኝ እንጅ😊)

የዛሬው ደግሞ ከስያሜው ጀምሮ ማራኪ የሆነ ስጦታ ነው። እንኳንስ ውስጡ ያጨቀውን እንቁ ሀሳቦችን አንብቤ ቀርቶ ገና ስሙን ሳየው ጭምር ነው አንዳች ደስታ የሚሰማኝ። ኢትዮዽያዊነትን ግለፅ ብባል ከዚህ ቤት ውጭ የሚታዬኝ አይኖርም፣ ሚዛናዊነት፣ ቀናነት፣ አወንታዊነት፣ ተስፈኝነት ለሚባሉት ስብዕናዎች በሙሉ ምሳሌ ባደርገው ውሸት አይሆንብኝም። ለነገሩ ስሙ ራሱ 'ስብዕናችን!'ም አይደል? አዎ የዛሬውን ስጦታ ለናንተ ለውድ ቤተሰቦቼ ሳበረክትላችሁ በኩራት ነው! እስኪ ጎራ በሉና ቃኙት! ትወዱታላችሁ!

መግቢያ በሩ እነሆ!
👇
t.me/EthioHumanity

Ibnu Ebrahim

15 Aug, 13:44


ያዘነች እንደሆነች ያሳብቃል።

"ኧረ አይደለም! ማን እንደዛ ሲል ሰምተሽ ነው?"
"እማማ ፋጤ ናቸዋ!" ከማለቷ በጓሮ በኩል ቅልጥ ያለ እልልታ ተሰማ። እልልታውን አውቀዋለሁ። አዎ! የእማማ ፋጤ እልልታ!😁...ይቀጥላል!
.
.
@ibnuebrahim
@ibnu_ebrahim_bot

Ibnu Ebrahim

15 Aug, 13:44


#ሃላሊ...21 B
(Ibnu ebrahim)
.
"እንግዲህ እንደምታውቁት እኔና ጦይባዬ ሃጅ ያደረግነው ለይላዬ የዘጠኝ አመት ልጅ እያለች ነበር። የዛሬ 12 ዓመት ገደማ መሆኑ ነው። የዛኔ ሸሪዓዊ ዕውቀት እስከዚህም ነበር። እናም አብዛህኛው ሃጃጅ ስለ ሀጅ አፈፃፀም እውቀት የሌውም ነበርና ብዙ አስቂኝ ገጠመኞች ይከሰቱ ነበር። እኛ ሀጅ ባደረግንበት ወቅትም ብዙ አስቂኝ ገጠመኞች ገጥመውን ነበር። ያው እርጅና እየመጣም አይደል? ከሁለት ገጠመኞች በቀር አብዛህኛዎቹን ዘንግቻቸዋለሁ።

አንደኛው ገጠመኝ ከእኛ ጋር ሀጅ የሄደ አንድ ሀጃጅ የፈፀመው ተግባር ነበር። ይህ ግለሰብ በመጀመሪያው የሀጅ ቀን ላይ ከፊቱ በቀር መላ ሰውነቱን ተከናንቦ አገኘሁት። ያው ምንም እንኳን አሊም ባልሆንም ሀጅ ከማድረጌ በፊት ስለ ሀጅ አፈፃፀም እና መስፈርቶች አንብቤ ስለነበር፤ ሰውዬውን፤
"ወንድሜ ሆይ! በሀጅ ጊዜ እኮ ጭንቅላት ላይ መጠምጠምም ሆነ ኮፍያ ማድረግ አይፈቀድም። አንተ ደግሞ ጭንቅላትህን በፎጣ ጠቅልለኸዋል።" ስል ነገርኩት።

"አዎ አውቃለሁ። ነገር ግን በዚህ ዙር ሀጅ የማደርገው ለእናቴ ስለሆነ ነው የተከናነብኩት!" ሲል መለሰልኝ ሃሃሃሃ..." ሁላችንንም አንድ ያደረገ ሳቅ ቤቱን ሞላው።

"እና ምን አሉት? የሆነ እውነት የሚመስል ነገር አለው?" ሲል ግራ የተጋባው ማሜ ጠየቀ። በሱ ጥያቄም በድጋሚ ሳቅን።

"ለእናቱ ቢሆንም እንኳን መሸፈን እንደማይጠበቅበት ብነግረው ሊያምነኝ አልቻለም። በኋላ አብረውን ከተጓዙት የኡለማ ቡድን ፈተዋ ከጠየቀ በኋላ ነው ክንብንቡን ያወለቀው።" ብለው ካሉን በኋላ ሁለተኛ ገጠመኛቸውን ጀመሩልን።

"ሁለተኛው ገጠመኜ ደግሞ አንድ ግብፃዊ የተናገረኝ ንግግር ነው።" አሉ እና ሳቅ አቋረጣቸው። እኛም በኋላ ቀልዱን ስንሰማ ከምንስቀው ሳቅ ላይ ተበድረን አብረን ሳቅን!😂

"ይህ ግብፃዊ ወደ ሃጅ ከመምጣቱ በፊት ከምስቱ ጋር ተፋቶ ነበር መሰለኝ፤ ጠጠር የሚወረወርበት ቦታ ላይ ቆሞ
'አንተ ሰይጣን አንተ አይደለህ ከምስቴ ጋር ያጣላህኝ? ይሄው ዛሬ ከአገሬ ድረስ አንተን ልወግር መጥታቸለሁ! እንካ ቅመስ!' እያለ በእልህ የያዛቸውን ሰባት ጠጠሮች ይወረውር ጀመር። ጠጠሮቹን ጨርሶም ንዴቱ አልበርድለት ስላለው ሁለት ጫማዎቹን አውልቆ ተራ በተራ ወረወራቸው። ያው በንግድ ምክንያት አረበኛ ስለምሰማ ወደ ሰውዬው ጠጋ ብዬ፦

'ወንድሜ! ተረጋጋ መጥፎ ንግግር መናገርም ሆነ ይሄን ያህል መቆጣት የለብህም!' ብዬ ስለው። በቁጣ አይን እያዬኝ፤
'ምነው ይሄን ያህል አሳሰበህ ዘመድህ ነው እንዴ?' ብሎኝ ጥሎኝ ሄደ እላችኋለው" ብለው ድጋሚ አሳቁን። ባይሆን ያሁኑ ከቅድሙ የረዘመና ሞቅ ያለ ሳቅ ነበር።

"አይ ጋሽ ሃሚድ በደንብ አድርገው አሳቁን እኮ! መቼስ ወጣ ካሉ የማይገጥም የለም። እኔም ሀጅ ባደረኩበት ጊዜ አንዱ የደላው የአሜሪካ ሀጃጅ ያለኝን ላጫውታችሁኣ!" ሸህ ሙሳ ነበሩ የተናገሩት።

"ምን ጥያቄ ያስፈልገዋል ይንገሩን እስኪ!" ሷሊህ ከተቀመጠበት ጥግ በኩል ሆኖ መለሰላቸው።

"ያው 'ሸኪ' ነው ምትሉት? ሃሃሃ...አዎ! ሸይኽ ብሆንም እንግሊዘኛ በደንብ አቀላጥፌ መስማትና ማውራት እችላለሁ። አሏህ ይስጣቸውና የተማርኩበት የአዝሃር ዩኒቨርስቲ ከሸሪዓው ጎን ለጎን የእንግሊዘኛ ቋንቋን አስተምረውናል።"

"Are you sure you can speak English?" ማሜ ለማረጋገጥ በሚመስል አንድምታ ጠየቃቸው። ቶፋ በማሜ ፈጣጣነት የተሸማቀቀ ይመስላል።

"Of course! I can. Being able to speak English is not surprising." ሸህ ሙሳ በእንግሊዝኛ መለሱለት።

"ኧረ! ተው ማሜ ሁላችንንም በሚያግባባን ቋንቋ እናውራ! በዚህ አይነት እኮ ገጠመኙንንም በእንግሊዘኛ ልታስደርግብን ነው።" ሪድዋን ወደተነሳንበት ሀሳብ ሊመልሰን ሞከረ።

"መቼም የዘንድሮ ልጆች ከእናንተ ውጭ አዋቂ ያለ አይመስላችሁም። ለማንኛውም ገጠመኙን ልንገራችሁ። እንዳልኳችሁ አረፋ ላይ ቆመን እያለ ከጎኔ የነበረው አሜሪካዊ እንግሊዘኛ አውቅ እንደሆነ ጠየቀኝ። እንደምችል ነግሬው ማውራት ጀመርን። ስለ አረፋ፣ ስለ ሀጅ፣ ስለ ሀገሪቷ ስናወራ ቆይተን በመጨረሻም ስለመጣንበት ሀገር ማውራት ጀመርን።
"ከኢትዮጵያ እዚህ ድረስ ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?" ሲል ጠየቀኝ።
"ወደ ሁለት ሰዓት ገደማ።" ስል መለስኩለት። አጅሬ ምን ቢለኝ ጥሩ ነው?
"ኦው! ለአምስት አውቃት ሶላት ትመላለሳላችኋ!" ብሎኝ አረፈዋ። ሃሃሃ"

"ሃሃሃ የጠገበች እናት ልጇ ይርበው አይመስላትም! አይደል ተረቱ።" አሉ ጋሽ ሀሚድ።

"የደላው! እኛ ኑሮን መግፋት ቸግሮናል እሱ አምስት አውቃት ሶላት ይልልናል እንዴ! አንድ ዙር ሀጅ ማድረግ የህይወት ዘመን ህልማችን እንደሆነ ማን በነገረልን።" ማሜ በስጨት እያለ ተናገረ።

ጨዋታው ደርቷል። በአካል የገጠማቸው ሰዎች ገጠመኞቻቸውን ጨርሰው የተቀሩት ደግሞ የሰሙትን አስቂኝ ገጠመኞችን መናገር ጀምረዋል። በመሃል ያመጣሁላቸውን ስጦታዎች ልሰጣቸው ሻንጣችን ወደተቀመጠበት የሃላሊ የድሮ መኝታ ክፍል አመራሁ። ኮሊደሩ ላይ ሰሚራን አገኘኋት እና አቅፌ ወደ ክፍሉ ይዤያት ገባሁ።

ለቤተሰብ እና ለጓደኞቻችን ያመጣንላቸውን ስጦታዎች የያዘውን ሻንጣ ከፈትኩና ለሰሚራ የገዛሁላትን Educational Tablet ሰጠኋት።

"ይሄ በትምህርትሽ ላይ ጎበዝ እንድትሆኚ የገዛሁልሽ ነው። ወደድሽው?" ስል ጠየቅኳት። በደስታ እያበራ ያለውን ፊቷን እየሳምኩ።

"አዎ ሀጂ አመሰግናለሁ! እኔም ከባሌ ጋር ለሀጅ ስሄድ ጀለብያ እገዛልሃለው እሽ!" አለችኝ በትናንሽ አይኖቿ የነገ ህልሟን አሻግራ ለማየት እየሞከረች።

"አንችም ከባልሽ ጋር ነው እንዴ ሀጅ የምትሄጅው?" ስል ጠየቅኳት። በንግግሯ የተነሳ በደስታ አይኖቼ ሊያነቡ እየዳዳቸው።

"አዋ! እኔም እንዳንተ እና እንደ አክስቴ ለይላ ሳድግ ከባሌ ጋር ነው ሀጅ ማድረግ የምፈልገው!" ስትል መለሰችልኝ። እንዴት ደስ ይላል! የዘጠኝ አመቷ ለይላ ህልም ወደ ስድስት አመቷ ሰሚራ ሲሸጋገር ሳይ እንዴት ደስ አይበለኝ? ለካ ትውልዱን የምንረግመው በራሳችን ጥፋት ነው። አዎ! ተረካቢ ትውልዶቻችን የኛ ግልባጭ ምስሎቻችን ናቸው። የፊታችንን ጉድፍ አሳየን ተብሎ በራሳችን ጉድፍ መስታውቱን እንወቅሳለን እንዴ? ትውልዶቻችንም የኛን መልካምነታችንን እና መጥፎነታችንን የሚያንፀባርቁልን መስታውቶቻችን ናቸው። አጭበርባሪ ማህበረሰብ ውስጥ የተወለዱ ህፃናት አጭበርባሪ፣ ጨካኝ ማህበረሰቦችን እያዩ ያደጉት አረመኔ ቢሆኑ ምኑ ይደንቃል? እውን ከትውልዱ ይልቅ ማህበረሰቡ ሊወቀስ አይገባም? ስምንተኛው ሺህን ከመርገማችን በፊት ሰባተኛውን መፈተሹ ተገቢ አይደለም? አዎ! እንደ ሰሚራ መልካም አርዓያ ያገኙት ትውልዶችማ ይሄው መልካም ራዕይ ለመሰነቅ ታደሉ!

ከገባሁበት የሀሳብ ሰመመን የነቃሁት የሰሙን ንግግር ስሰማ ነበር።

"ካሊዴ! የምትበላው የላት ፎጣ አማራት! ማለት ምን ማለት ነው?" ስትል ጠየቀችኝ። በአነጋገሯ ከልቤ ሳቅኩ።

"የምትበላው የላት የምትከናነበው አማራት! ማለትሽ ነው?" ስል አባባሉን አስተካክዬ ጠየቅኳት። ጭንቅላቷን በአወንታ ነቀነቀች።

"ይህ ተረት አንገብጋቢ ጉዳይ እያለው ቅንጦት ነገርን ለሚያስቀድሙ የሚተረት ተረት ነው።" ስል ለማብራራት ሞከርኩ። ተረት፣ ቅኔ ምናምን ላይ እስከዚህም ነኝ። አሁንም ተረቱን በትክክል ልተርጉመው አልተርጉመው እርግጠኛ አልነበርኩም። ኧረ መረዳቷንም እንጃ!😁

"እና እናንተ ምትበሉት ሳይኖራችሁ ነው ሀጅ የሄዳችሁት?" ስትል ጠየቀችኝ። ሁኔታዋ

Ibnu Ebrahim

13 Aug, 18:13


#ልብህን_ጠብቃት!
.
@ibnuebrahim
@ibnu_ebrahim_bot

Ibnu Ebrahim

11 Aug, 18:20


"ብዙ ጣፋጭ ነገሮች ቢኖሩም፤ ከርሃብ በኋላ እንደሚበላ ምግብ፣ ከችግር በኋላ እንደሚገኝ ደስታ፣ ከጭንቅ በኋላ እንሚመጣ ሰላም የሚጣፍጥ ግን ላገኝ አልቻልኩም! እውነት ነው። ችግር ባይኖር የሰላምን ጣዕም ማጣጣም አንችልም።"

(ኢብኑ ኢብራሂም)
.
@ibnuebrahim
@ibnu_ebrahim_bot

Ibnu Ebrahim

09 Aug, 17:51


🎁#ስጦታ_ ሁለት
.
እነሆ ዛሬ ሁለተኛውን ስጦታዬን ይዤላችሁ መጥቻለሁ። የመጀመሪያውን ስጦታ እንደወደዳችሁት የገለፃችሁልኝ ቤተ-ሰቦች አላችሁ። ኢንሻ አላህ የዛሬውንም ስጦታ እንደምትወዱት ተስፋ አደርጋለሁ!

ዛሬ የማበረክትላችሁ ስጦታ አዲስ ነገር ለሚወዱ፣ አንድን ነገር ተርታው ማህበረሰብ ከሚያይበት አንግል ውጭ መመልከት ለሚወዱ፣ ጠንከር ያሉ ሃሳቦች፤ ጠጠር ያሉ ቃላቶች ለሚያስደስታቸው ሰዎች ትልቅ ብስራት ሊሆን የሚችል ግሩም ስጦታ ነው።

እኔ በግሌ ነብስያዬ ከእናንተ በኩል በሚደርሳት የሙገሳ ቃላት ስትኮፈስ ወደዚህ ቤት ጎራ ብዬ ተራነቷን የማሳይበት የኢኽላሴ ውሃ ልክ ነው። እውነቴን ነው። በዚህ ቻናል የሚነሱትን ሃሳቦች ሳይ የሃሳቦቼን ተራነት እረዳለሁ፣ የቃላቶቹን ውበት እና ጥልቀት ስመለከት ቃላቶቼ አንድ የሦስተኛ ክፍል ተማሪ ለመጀመሪያ ጊዜ የሞነጨረው ደብዳቤ ያህል ይቀሉብኛል። ወኔዬ ሲዝል፣ ፅናቴ ሲነጥፍ፣ አቅሜ ሲፈተን ማበርቻዬ ነው። ብቻ ምን አለፋችሁ ግቡና ጎብኙት! በእርግጠኝነት ትወዱታላችሁ፤ ትጠቀሙበታላችሁም!

ይህ ከታች👇 ያሰፈርኩት ሊንክ ወደ ቤቱ መግቢያ በሩ ነው። ግቡና እዩት!
t.me/venuee13

Ibnu Ebrahim

07 Aug, 18:28


💖#ሱብሃነላህ!
.
.
#ሱብሃነላህ! የአፈጣጠር ጥበብህ ምን አማረ!
#ሱብሃነላህ! የማስተናበር ችሎታህ ምን ድንቅ ሆነ!
#ሱብሃነላህ! ፍትህአዊው ግዛትህ ምን ውብ ሆነ!
#ሱብሃነላህ! የትዕግስትህ መጠን ምን ሰፊ ሆነ!
#ሱብሃነላህ! የልቅናህ መጠን ምን ከፍ አለ!
#ሱብሃነላህ! የሀይልና ጉልበትህ አድማስ ምን ጥልቅ ሆነ!
#ሱብሃነላህ! የዝምታህ ደንበር ምን ሰፊ ሆነ!
#ሱብሃነላህ! የጥበብህ ሚስጢር ምን ረቂቅ ሆነ
#ሱብሃነላህ! የአጥሪህ አቅምና እውቀት አንተን ከማጥራት ምን ሰነፈ!
.
.
።።።።።።።። #ጌታዬ_ሆይ! ።።።።።።።።።

~ከተጋሪ መጋራት የፀዳህ ነህ!
~ልጅም ሆነ ምስት ከመያዝ ተብቃቂ ነህ!
~ከእንቅልፍና ማንገላጀት የራቅክ ነህ!
~ከህመምና ሞት የፀዳህ ነህ!
~ከኔ ማጥራት በላይ የጠራህ ነህ!

።።።።። #ሱብሃነከ_ረቢ #ሱብሃነክ! ።።።።።
.
@ibnuebrahim
@ibnu_ebrahim_bot