አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ @amucampus Channel on Telegram

አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ

@amucampus


Official Arbaminch University ®
ማስታወቂያዎችን እና ወቅታዊ መረጃዎችን በፍጥነትና በጥራት!
ሀሳቦች እና እንዲተላለፍላችሁ የምትፈጉት ነገር ካለ በ
@newneway
@firaK19
@miko1122
@ADA1249
ላይ ያግኙን፡፡
AMU Info ......
እውነተኛ እና ፈጣን መረጃ ይደርሶታል፡፡
።።ከተማሪ ለተማሪ።።:
Arba_Minch_university

አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ (Amharic)

እንቅስቃሴው ለአርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ ተመልከቱ። ይህ ቡድን ከልዩ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ መሆን እንደሚሆን መረጃንና ሰአትን ዛሬው የፍጥነትና የጥራት ስኬት ማሳያ ይከላከሉ። ለተማሪዎቹ ከተሞላችሁ ለአርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ ምን? ዝርዝር ኣለብዛችሁ? ይህ ቡድን የአርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ አስተያየታችሁ ለሚሆን በመሆን አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ በተመሳሳይ መረጃዎችና መልሶ ያለውን የተለያዩ ዜናዎችን ለማየት በሚያነሳን ቦታ ነባር እና ሴትና እና ሴት ቤቶችን እና አካባቢዎችን ጠቀሱ። እውነትና ፈጣን መረጃዎች ከሆነ ደስተኛ ሊሆኑ ይሆናል። የአርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ የተከሰቱ መረጃዎች ናቸው።

አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ

19 Dec, 14:40


የውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሃይድሮሊክ ቤተ ሙከራ

Water Technology Institute: Hydraulic Laboratory
@amucampus
@firak19

አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ

17 Dec, 17:15


በጫሞ ካምፓስ ለተመደቡ የሪሚዲያል ተማሪዎች ኦሬንቴሽን ሰጠ

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጫሞ ካምፓስ በ2017 ዓ.ም ለተመደቡ የሪሚዲያል ተማሪዎች ታኅሣሥ 8/2017 ዓ.ም ኦሬንቴሽን ተሰጥቷል፡፡

የቢዝነስና አኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲንና የካምፓሱ ኃላፊ ዶ/ር መስፍን መንዛ ከዚህ ቀደም በተቋሙ የተመደቡ የሪሚዲያል ተማሪዎች በአብዛኛው አመርቂ ውጤት በማምጣት ማለፍ እንደቻሉ ገልጸው ዕድሉን ያገኙ ተማሪዎች ጊዜያቸውን በአግባቡ በመጠቀም በትምህርታቸው እና በሥነ ምግባር ታንጸው እንዲወጡ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት በማምጣት ወደ መደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር ተሻግረው መቀጠል እንዲችሉ እንደ ካምፓስ አስፈላጊው ጥረት እንደሚደረግም ዲኑ ተናግረዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ የኮሌጁ ዲን፣ የተማሪዎች አገልግሎት ም/ዲን፣ የተለያዩ የሥራ ክፍል ኃላፊዎች እንዲሁም የተማሪዎች ኅብረት እና የሰላም ፎረም አባላት የተገኙ ሲሆን የተማሪዎች የዲሲፕሊን ሕጎች፣ በሁሉም ዘርፎች የሚሰጡ አገልግሎቶች እና  በግቢው የሚኖራቸውን  ቆይታ በሚመለከት ሰፋ ያለ ማብራሪያ ቀርቧል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!



የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት
@amucampus
@firak19

አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ

17 Dec, 09:50


@amucampus

አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ

14 Dec, 14:40


የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ለሪሚዲያል ተማሪዎች ኦሬንቴሽን ሰጠ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በ2017 ዓ.ም በኮሌጁ ለተመደቡ የሪሚዲያል ተማሪዎች ታኅሣሥ 4/2017 ዓ.ም ኦሬንቴሽን ሰጥቷል፡፡ 
                    
የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ቴዎድሮስ ብርሃኑ በመክፈቻ ንግግራቸው ተማሪዎች የተሰጣቸውን መልካም ዕድል ሳያባክኑ በአግባቡ ሊጠቀሙ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ተማሪዎች በኮሌጁ የሚኖራቸው ቆይታ በ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ሲማሩ የቆዩትን ትምህርት የመከለስ ሥራ እንደሚሰራና ቆይታቸው ስኬታማ እንዲሆን ኮሌጁ የሚጠቅበትን እንደሚወጣ እንዲሁም ከተማሪዎቹ የላቀ ትጋት እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል፡፡

የሪሚዲያል ፕሮግራም ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የተሰጠ ሁለተኛ ዕድል መሆኑን የገለጹት የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ም/ዲን ዶ/ር አድማሱ ጣሰው በበኩላቸው ተማሪዎች በሚኖራቸው የግቢ ቆይታ ቤተሰባዊ ግንኙነትን በማዳበር መብትን መጠቀምና ግዴታን መወጣት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲ ብዝሃ ማንነት ያለበት ተቋም በመሆኑ ተባብሮና ተቻችሎ የመኖር ባህልን ማዳበር ከተማሪዎቹ እንደሚጠበቅም ም/ዲኑ አክለዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ ሀገር አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዲሲፕሊን መመሪያዎች እና የተማሪዎች አገልግሎት ዘርፍና እና የተማሪዎች ኅብረት የሚሰጡት አገልግሎት ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ የቀረበ ሲሆን በዕለቱ የኮሌጁን ዲን ጨምሮ ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች፣ የተማሪዎች ኅብረት ፕሬዝደንትና አባላት ተሳትፈዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!


የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት
@amucampus

አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ

13 Dec, 20:48


@amucampus

አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ

13 Dec, 20:44


ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት አዲስ ለተመደቡ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች የተሰጠ የመልካም ምኞት መግለጫ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከቀዳሚ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ሲሆን ገናና ስም ካላቸው ዩኒቨርሲቲዎች ተርታም ይመደባል ፡፡ለዚህም በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የነበረው አመራር ጥንካሬ በመሆኑ ከዚህ ቀደም የነበራችሁ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር ልቆ እንዲወጣ፣ ሰላሙ የተጠበቀና ለሃገሪቱ የሰላም አምባሳደር ምልክት መሆን እንዲችል ለተማሪዎችም እንደመፈክሩ የብሩህ ተስፋ ማዕከል መሆኑ እንዲመሰከርለት ስላደረጋችሁ፣ የዩኒቨርሲቲውን የተማሪዎች ህብረት በሙሉ አቅማችሁ በመደገፍ ላበረከታችሁት አስተዋፅዖ ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን

አዲስ ለተመደባችሁ ለዩኒቨርሲቲያችን ከፍተኛ አመራሮች ይህን ግዙፍ ሃገራዊ ተቋም ለመምራት ዕድል ስላገኛችሁ እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን

እንደተማሪዎች ህብረት  እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ አብረናችሁ ለመስራት እና የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማድረግ ተሰናድተናል። በተማሪዎች እና  በአመራሩ መሀከል ድልድይ በመሆን ፤ የመማር ማስተማር ሂደቱን በማስጠበቅ ፣ የተቋሙን ሰላም በማስቀጠል በበለጠ ለመትጋት እንደተሰናዳን መግለጽ እንሻለን።

በተለይም በአሁኑ ሰዓት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስገዝነት ለሚያደርገው ሽግግር የሁሉም ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ  እንደሚሻ የምንገነዘበው ነው። የትምህርት ዘርፉ ሪፎርምም ይኼንን ተልዕኮ ከግንዛቤ ያስገባ መሆኑን እናምናለን። የተማሪዎች ህብረትም የዩኒቨርስቲው ማህረበሰብ አስኳል እንደመሆኑ መጠን ከትላንት በተሻለ ትጋት ፤ ከአምናው በበለጠ ጥረት መስራት እንደሚገባንና የሚጠበቅብንን ለመከወን ፣ የተሰጠንን ተልዕኮ ለመተግበር እና ከተማሪዎች የሚነሱ ሀሳቦችን ለማስፈፀም ተግተን እንሰራለን፡፡
@amucampus

አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ

20 Dec, 04:30


የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ፈረንሳይ ሀገር ከሚገኝ ‹‹Fund for Innovative Development (FID)›› ድርጅት ጋር በመተባበር በሚያከናውነው ‹‹Adoption of Rhizobium Inoculant Technology (ARIT)›› የተሰኘ የትብብር ፕሮጀክት የተፈጥሮ ማዳበሪያ ‹‹Bio-Fertilizer›› ማምረት ላይ የለውጥ ማሳያ (Progress) ሪፖርትና የመስክ ምልከታ ታኅሣሥ 4/2016 ዓ/ም ተካሂዷል፡፡

የምርምር ዳይሬክቶሬት ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ተስፋዬ ሀብተማርያም በትብብር ፕሮጀክቱ ባቄላ፣ አኩሪ አተር፣ ቦሎቄ፣ ሽምብራ፣ አተርና ሌሎች ጥራጥሬዎች/Leguminous Plants/ ለማምረት የሚያገለግል የተፈጥሮ ማዳበሪያ ለሙከራ የሚመረትበትና ማዳበሪያው በማሳ ላይ በተክሎቹ ላይ የሚሞከርበት የምርምር ማሳያዎች የመስክ ምልከታ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ ምርምሩን በማሳደግ ለአርሶ አደሩ የተፈጥሮ ማዳበሪያን በተለያየ መልኩ ለማቅረብ እንዲሁም መሰል ምርምሮችንና ፕሮጀክቶችን ለማሳደግ እንደሚሠራ ዶ/ር ተስፋዬ ጠቁመዋል፡፡
በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የባዮሎጂ ት/ክፍል መምህርና ተመራማሪ የሆኑት የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዶ/ር አሽናፊ ኃይሉ እንደገለጹት ፕሮጀክቱ በሁለት ዓመታት ቆይታ የደረሰበት የአፈጻጸም ደረጃ፣ የተገኙ ውጤቶች፣ የገጠሙ ችግሮችና ቀጣይ ሥራዎች ላይ ሃሳብ ለመለዋወጥ ብሎም በኮሌጁ ግቢ ውስጥ የተደራጁ የሙከራ ቦታዎችና መስክ ላይ ያሉ ምርቶችን በመመልከት ለቀጣይ ሥራ ግብዓት የሚሆኑ አስተያየቶችን ለማግኘት መርሃ ግብሩ ተዘጋጅቷል፡፡
እንደ ዶ/ር አሸናፊ በጥቂት በጀት ብዙ ተማሪዎችን በተግባር ማስተማር መቻሉና የተፈጥሮ ማዳበሪያን በማምረት ወደ ማኅበረሰቡ ለማድረስ ከሚቻልበት ደረጃ መደረሱ የፕሮጀክቱ መልካም አፈጻጸሞች መሆናቸውን የለውጥ ማሳያ ሪፖርቱና የመስክ ምልከታው ያሳያሉ፡፡ በአፈጻጸሙ እንደ ድክመት የተጠቀሱ ጉዳዮችን ለመቅረፍና በስፋት በማምረት ለማኅበረሰቡ ለማዳረስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የሚሠሩ መሆኑንም ዶ/ር አሸናፊ ተናግረዋል፡፡
የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ቴዎድሮስ ብርሃኑ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ ፈረንሳይ ሀገር ካለ ድርጅት ጋር በጋራ እንደሚሠራና ሙሉ ወጪው በድርጅቱ እንደሚሸፈን ጠቅሰው እንደ ኮሌጅ መሰል የትብብር ሥራዎችን እናበረታታለን ብለዋል፡፡ ፕሮጀክቶችን በየጊዜው የመገምገም ሥራ በዕቅድ ተይዞ የሚሠራ ነው ያሉት ዲኑ በለውጥ ማሳያ ሪፖርቱና በመስክ ምልከታው ለሌሎች ምሳሌ የሚሆኑ ሥራዎች በፕሮጀክቱ እንደተሠሩ ማየት መቻላቸውን ገልጸዋል፡፡
የአርባ ምንጭ ግብርና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተርና ተመራማሪ ቱማ አየለ መሰል ምርምሮችን የማከናወንና የምርምር ውጤቱን በሚገባ በመያዝ አባዝቶ ለተጠቃሚው ማኅበረሰብ የማድረስ ሥራ ተጠናክሮ ቢሠራ ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር ብሎም ማዳበሪያ በውድ ዋጋ መግዛትን ለማስቀረት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡
በኮሌጁ የባዮ ቴክኖሎጂ የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች በሰጡት አስተያየት በምርምር ሥራው ጥሩ ዕውቀትና ጠቃሚ ልምዶችን እንዳገኙ ገልጸው ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ በዘርፉ ማኅበረሰቡን የሚጠቅሙ ሥራዎች ለመሥራት መነሳሳታቸውን ተናግረዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ የጋሞ ዞን ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲና የአርባ ምንጭ ግብርና ምርምር ማዕከል አመራሮች፣ መምህራንና ተመራማሪዎች ተገኝተዋል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

@amucampus
@amucampus

አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ

05 Dec, 20:50


🙏Sawla Campus

Academic Programs

Regular under Graduate Degree Programs
A.College of Engineering & Technology
1.Civil Engineering
2.Automotive Engineering
3.Electromechanical Engineering
4.Food Technology and Processing Engineering
B.College of Commerce and Business Administration
1.Logistics and Supply Chain Management
2.Finance and Development Economics
3.Business Administration and Information Systems
4.Marketing Management
5.Cooperative Accounting and Auditing
C.School of Communications
a.Communication and Media Studies
b.Public Relation and Advertising

Regular Post Graduate Degree Programs
1.Logistics and supply Chain Management

Weekend under Graduate Degree Programs
1.Economics
2.Accounting and Finance
3.Civil Engineering
4.Management

Summer Undergraduate Degree Programs
1.English Language and Literature

Weekend Post Graduate Degree programs
1.Business Administration (MBA)
2.Accounting and Finance

@amucampus
@amucampus

አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ

05 Dec, 20:46


👉Sawla Campus

Sawla Campus is located at 196kms to the South West of Arba Minch town in Gofa Zone via Arba Minch to Bonke, Bonke to Kamba and then Kamba to Sawla or 260kms through Arba Minch to Wolayta Sodo and then Wolaita Sodo to Sawla.

Sawla Campus was built on an area of about 45.3hectar in June 2014 and inaugurated in November 2015 by admitting 191 students (M = 98, F = 93) in four departments with 7 academic and 38 administrative staffs.

Sawla campus is working hard to the parameters to produce citizens which are knowledgeable, skilled and with good characters of citizens who work for the development of the country. It is also working to become teaching and research institute in the coming years. It is a multi-disciplinary campus.

@amucampus
@amucampus

አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ

01 Dec, 14:24


Arba Minch University

The University is sited in five campuses based around Arba Minch town, with the Arba Minch Institute of Technology, and primary administrative units based on the Main Campus site, and the Colleges sited according to infrastructure and facilities, number of students, and proximity to field and institutional attachment and laboratories. The College of Medicine and Health Sciences, for example, is sited nearby Arba Minch Hospital.

1.Main Campus

👉Arba Minch Institute of Technology
The 'Mother Campus' is located at about 5km north of Arba Minch town on the road to Addis Ababa.

2.Abaya Campus

👉College of Natural Sciences

Located in Secha Kifle Ketema of Arba Minch town overseeing Lakes Abaya to the left and Chamo to the right.

3.Chamo Campus

👉College of Business and Economics

👉College of Social Sciences and Humanities
Located at the southern end of Arba Minch in Secha Kifle Ketema overseeing Lake Chamo.

4.Nech Sar Campus

👉College of Medicine and Health Sciences
Located on the main road from Sikela to Secha, close to Arba Minch Hospital.

5.Kulfo Campus

👉College of Agriculture
Located on the main road from Main campus to Sikela, close to Kulfo River.

Sawla campus @more info contact
@amucampus
@amucampus

አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ

01 Dec, 14:10


የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች መግቢያ ጥሪ ማስታወቂያ
በ 2015 የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ውጤት በማምጣት በ2016 የትምህርት ዘመን አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ መደበኛ ተማሪዎች እና በ2015 የትምህርት ዘመን አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ (Remdial) ፕሮግራም ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች መግቢያ እሁድ ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም፣ የአቀባበልና የጋራ መግለጫ የሚሰጠው ሰኞ ታኅሣሥ 1 ቀን 2016 ዓ.ም፣ ምዝገባ ማክሰኞ ታኅሣሥ 2 ቀን 2016 ዓ.ም፣ ትምህርት የሚጀመረው ረቡዕ ታኅሣሥ 3 ቀን 2016 ዓ.ም እንዲሆን ተወስኗል፡፡
ስለሆነም ተማሪዎች በተጠቀሰው ቀን ወደ ዩኒቨርሲቲው በምትመጡበት ጊዜ፡-
የ8ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ኦርጂናልና ሁለት የማይመለስ ኮፒ፣
ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ኦርጂናልና ሁለት የማይመለስ ኮፒ፣
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ኦርጂናልና ሁለት የማይመለስ ኮፒ፣
የፓስፖርት መጠን (Passport Size) የሆኑ ሁለት ጉርድ ፎቶግራፎች እና
አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ
በመያዝ ሁሉም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው ዓባያ ካምፓስ፣ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የስም ዝርዝራችሁ ከፍደል ተራ “A” እስከ “S” የሚጀምሩ በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው በጫሞ ካምፓስ እና የስም ዝርዝራችሁ ከፍደል ተራ “T” እስከ “Z” የሚጀምሩ በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በሚገኘው በሳውላ ካምፓስ በአካል  ቀርባችሁ እንዲትመዘገቡ እናሳውቃለን፡፡
 ማሳሰቢያ፡- ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን በጥብቅ ያሳውቃል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት
ማሳሰቢያ :-
አዲስ ተማሪዎች ቀለል ያለ አንሶላ ብትይዙ ይመረጣል 🙏@amucampus

@amucampus
@amucampus

አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ

01 Dec, 14:06


የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች መግቢያ ጥሪ ማስታወቂያ

በ2016 የትምህርት ዘመን የድኅረ ምረቃ ትምህርት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ለመማር አመልክታችሁ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን ብሔራዊ የድኅረ ምረቃ ቅበላ ፈተና (National Graduate Admission Test – NGAT) ወስዳችሁ የማለፍያ ነጥብ ያመጣችሁና የተመዘገባችሁ አዲስ አመልካች ተማሪዎች ፡-
👉የዩኒቨርሲቲ አቀፍ መግቢያ ፈተና የሚሰጠው  ኅዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ለመማር ባመለከታችሁበት ኢንስቲትዩት ወይም  ኮሌጅ ወይም ትምህርት ቤት፤
በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን ብሔራዊ የድኅረ ምረቃ ቅበላ ፈተና (National Graduate Admission Test – NGAT) ወስዳችሁ በተለያየ ምክንያት                              ያልተመዘገባችሁ እና አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለመማር የሚትፈልጉ ኅዳር 24 እና 25 ቀን 2016 ዓ.ም ሬጅስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 210 እና 211 ቀርባችሁ መመዝገብና ኅዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም የሚሰጠውን ፈተና በመቀበል መማር የሚትቸሉ፤

👉ከፈተና በኋላ የሬጅስትራር ምዝገባ የሚካሄደው ኅዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም እና

👉መደበኛ ትምህርት የሚጀመርበት ታኅሣሥ 01 ቀን 2016 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡ -
HB- የማስተርስ ዲግሪ አመልካቾች የመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም የፒ.ኤች.ዲ ዲግሪ አመልካቾች የመጀመሪያና የሁለተኛ ዲግሪ ኦፍሻል ትራንስክሪፕት በፖስታ   
ሳጥን ቁጥር 21 ወይም በተቋማዊ ኢሜይል አድራሻዎች፡- [email protected] ወይም [email protected] በኩል በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ማስላክ ይጠበቅባቸዋል፡፡

👉የማታ እና የሳምንት መጨረሻ ፕሮግራም አመልካቾች በቂ ተማሪ ባልተገኘባቸው ፕሮግራሞች ከመደበኛ ተማሪዎች ጋር መማር የሚትችሉበት ሁኔታ ማመቻቸት ይጠበቅባቸዋል፡፡


የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት

@amucampus
@amucampus

አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ

28 Nov, 10:22


ሱፐርቫይዘሮች በተማሪዎች የጥናት ሥራዎች ላይ በሚሰጡት አስተያየት ላይ የእንግሊዝኛ ቋንቋ አጠቃቀማቸውን ለማሻሻል የሚያስችል ግራንድ ምርምር ፕሮጀክት ይፋ ሆነ
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች የመመረቂያ ጽሑፍ ላይ ሱፐርቫይዘሮች በሚሰጧቸው አስተያየቶች ላይ የእንግሊዝኛ ቋንቋ አጠቃቀማቸውን ለማሻሻል የሚያስችል ግራንድ የምርምር ፕሮጀክት ኅዳር 15/2016 ዓ/ም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ይፋ አድርጓል፡፡
በመርሃ ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የማኅበራዊ ሳይንስና ሥነሰብ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ሙሉጌታ ደበሌ የምርምር ሥራ ዋና ዓላማው ለተለያዩ ችግሮች መፍትሄ ለማምጣት መሆኑን ገልጸው ምርምር ሁል ጊዜም ጥራት ያለው፣ ሊተገበር የሚችልና አዲስ ዕውቀት ሊፈልቅበት ይገባል ብለዋል፡፡ የባህልና ቋንቋ ጥናት ኢንስቲትዩት ከምሥረታው ጀምሮ የተለያዩ መደበኛና ግራንድ ምርምሮችን እያከናወነ እንደሚገኝ የጠቀሱት ዲኑ በዕለቱ ይፋ የተደረገው የምርምር ፕሮጀክትም በዘርፉ ያሉ ችግሮችን ለመለየት እንዲሁም በዘርፉ የሚከናወኑ የምርምር ሥራዎችን ከማሻሻል አንጻር የጎላ ሚና እንደሚያበረክት ገልጸዋል፡፡
የባህልና ቋንቋ ምርምር ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ዶ/ር ሰኢድ አሕመድ እንደገለጹት ኢንስቲትዩቱ በቋንቋና ባህል ብዝሃነት ላይ በማተኮር የተለያዩ የምርምር ሥራዎችን የሚያከናውን ሲሆን አሁን ላይ በኢንስቲትዩቱ 48 መደበኛና አዲሱን ፕሮጀክት ጨምሮ ሦስት ግራንድ የምርምር ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ በዕለቱ ይፋ የተደረገው ፕሮጀክት የትምህርት ጥራት ላይ ያተኮረ መሆኑን የገለጹት ዳይሬክተሩ ይህንን እንደ ጅማሬ በመውሰድ በቀጣይ መሰል ግራንድ የምርምር ፕሮጀክቶችን ለመሥራት ጥረት ሊደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በእንግሊዝኛ ቋንቋና ሥነ-ጽሑፍ ትምህርት ክፍል መምህርና  የፕሮጀክቱ ዋና ተመራማሪ  ዶ/ር አባተ ደምሴ የፕሮጀክቱን ዓላማ ለማስተዋወቅ መርሃ ግብሩ መሠናዳቱን ገልጸው ጥናቱ ሱፐርቫይዘሮች ለተማሪዎቻቸው የሚሰጡት አስተያየት የሚፈጥረውን አዎንታዊና አሉታዊ ተጽእኖ መለየት በዋናነት የቋንቋ አጠቃቀማቸውን ለመዳሰስ የሚሠራ ነው፡፡ እንደ ተመራማሪው ገለጻ ለተማሪዎች የሚሰጡት ግብረ መልሶች የቋንቋ አጠቃቀም ስሜትንና ሞራላቸውን የሚነካ ከሆነ ስሜታቸው ተጎድቶ ተስፋ ሊያስቆርጣቸውና ወደ ኋላ ሊዘገዩ ስለሚችሉ ሱፐርቫይዘሮች ግብረ መልስ ሲሰጡ የሚጠቀሙበት ቋንቋ ምን እንደሚመስል መዳሰስና ከኋላም ግንዛቤ መፍጠር የፕሮጀክቱ ዋነኛ ትኩረት ነው፡፡
የጥናት ፕሮጀክቱ ተማሪዎች በሰዓት ሥራቸውን አጠቃለው በወቅቱ እንዲመረቁ ለማስቻል ብሎም የመመረቂያ ጽሑፎችን ጥራትና ብቃት ደረጃ ከፍ ከማድረግ አንጻር የጎላ ሚና እንደሚኖረውም ዶ/ር አባተ አመላክተዋል፡፡ የጥናቱ በጀት በዩኒቨርሲቲው እንደሚሸፈን የገለጹት የፕሮጀክቱ ዋና ተመራማሪ ፕሮጀክቱ አንድ ሚሊየን ሰባት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር በጀት የተመደበለት መሆኑንና በአራት ዓመት ቆይታ እንደሚጠናቀቅ ጠቁመዋል፡፡
የምርምር ዳይሬክቶሬት ዋና ዳይሬክተርና የፕሮጀክቱ አባል ዶ/ር ተስፋዬ ሀብተማርያም በመዝጊያ ንግግራቸው መድረኩ የተሳካ የውይይት ቆይታና ለሥራው ጥሩ ግብዓት የተገኘበት እንደነበር ጠቅሰው በጋራ መሥራት ከተቻለ በርካታ ችግሮችን መሻገር እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎችም በሰጡት አስተያየት የጥናቱን ሂደት ለማሳለጥ ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልጸው ለሀገር ያለው ፋይዳ ከፍ ያለ በመሆኑ በሂደቱ የሚያጋጥሙ ተጋዳሮቶችን ተቋቁሞ በሙሉ ኃላፊነት በትብብር በመሥራት የተሟላ መረጃ የሚገኝበትን ሂደት ለመፍጠር እንተጋለን ብለዋል፡፡
የምርምር ሥራው አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ በዋቸሞ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ዲላና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች የሚከናወን ይሆናል፡፡
በመርሃ ግብሩ የማኅበራዊ ሳይንስና ሥነሰብ ኮሌጅ ዲን፣ የምርምር ዳይሬክቶሬት ዋና ዳይሬክተር፣ የባህልና ቋንቋ ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር፣ ለጥናቱ ከተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች የተወጣጡ የእንግሊዝኛ ትምህርት ክፍል ተጠሪዎችና የድኅረ ምረቃ አስተባባሪዎች፣ የፕሮጀክቱ ተመራማሪዎችና በጥናቱ የሚሳተፉ የድኅረ ምረቃ ተማሪዎችን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ታድመዋል፡፡
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

@amucampus
@amucampsu

አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ

27 Nov, 18:58


For All Fresh Students 👉

About AMU
Arba Minch University is based in South-West Ethiopia. The University was initially founded as the Arba Minch Water Technology Institute (AWTI) and it was officially inaugurated as a full -fledged university in June 2004 and started offering both undergraduate and graduate programs in the following institutes, colleges and schools:
1.Arba Minch Institute of water Technology
2.Arba Minch Institute of Technology
3.College of Agriculture
4.College of Business and Economics
5.College of Natural Sciences
6.College of Medicine and Health Sciences
7.College of Social Sciences and Humanities
8.School of behavioral and pedagogical sciences
9.School of law

Sawla Campus (a multi-disciplinary Academic areas campus)
Arba Minch University is currently working as one of National Research Universities and has more than 36,000 registered students in regular, evening, weekend and distance programs in first, second and third degree.

AMU- Main Campus
@amucampus
@amucampus

አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ

27 Nov, 18:52


እንኳን ደስ አላችሁ 🙏
ባጋጠመን በቴክኒክ ችግር ተቋርጦ የነበረው መረጃ ተመልሷል ለማንኛውም አስተያየት እና መልእክት @newneway ላይ አድርሱን.
አምዩ
Main Campus
@amucampus
@amucampus

አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ

03 Oct, 13:36


nathnael moges:
Yo, yo, yo! We're so excited that you're joining our proactive youth community! We've got a ton of cool stuff planned for you, so get ready to have some fun.
The event will be held at the Gamo Cultural Center near Bekele Mola Hotel. DM us your full name and age, and we'll be sure to hook you up with all the details.
Come early, grab a bite to eat, and meet some new friends. And don't forget to tell your buds to register too!
To become a part of the community, join our Telegram group: t.me/lakechamoyouth.
If you have any questions, you can reach us at any of these numbers on the day of the event: 0969 14 07 38, 0964 89 54 84, or 0923 52 24 28.
And for those of you who attend both events, we'll even give you a certificate of completion!
So what are you waiting for? Sign up today and join the fun!

ዮ፣ ዮ፣ ዮ!  የወጣት ማህበረሰባችንን በመቀላቀልህ/ሽበጣም ደስ ብሎናል! ለእርስዎ የታቀዱ ብዙ ጥሩ ነገሮች አሉን፣ ስለዚህ ለመዝናናት ተዘጋጁ።

በዓሉ በቀለ ሞላ ሆቴል አካባቢ በሚገኘው የጋሞ የባህል ማዕከል ይካሄዳል። ሙሉ ስምዎን እና እድሜዎን ይጻፉልን ::

ቀደም ብለው ይምጡ፣ ሚቀመስ ነገረ አለ እና አንዳንድ አዳዲስ ጓደኞችን ያግኙ። እና ለጓደኞችዎ እንዲሁ እንዲመዘገቡ መንገርዎን አይርሱ!

የማህበረሰቡ አካል ለመሆን የቴሌግራም ቡድናችንን ይቀላቀሉ፡ t.me/lakechamoyouth።

ጥያቄ ካላችሁ በዝግጅቱ ቀን በነዚህ ስልክ ቁጥሮች፡ 0969 14 07 38፣ 0964 89 54 84፣ ወይም 0923 52 24 28 ማግኘት ትችላላችሁ።

እና በሁለቱም ዝግጅቶች ላይ ለምትገኙ፣ የማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት  እንሰጣችኋለን!

ታዲያ ምን እየጠበቁ ነው? ዛሬ ይመዝገቡ ይቀላቀሉ!

አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ

22 Mar, 00:33


#የረመዳን ወር መግቢያ ጨረቃ ዛሬ ባለመታየቷ ምክንያት ታላቁ የረመደን ጾም ሀሙስ መጋቢት 14 ይጀምራል።

እንኳን ለታላቁ የረመዳን ጾም በሰላምና በፍቅር አድረሳችሁ።

ረመዳን የፍቅር፣ የአንድነት፣ የሰላም፣ የመተሳሰብ እና የአብሮነት ወር እንዲሆንልን ከልብ እንመኛለን መልካም የፆም ግዜ።

@amucampus
@amucampus

አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ

06 Jan, 19:28


የገና በዓል መልካም ምኞት መግለጫ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለገና በዓል በሠላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሠላም፣ የጤና፣ የአብሮነትና የመተሳሰብ እንዲሆን ከወዲሁ መልካም ምኞቱን ይገልፃል!!
Merry Christmas!!

@amucampus

@amucampus

Join our group
👇👇👇
https://t.me/+iJrNkGhSr1BiNmI0