📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚 @allah_is_the_great Channel on Telegram

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

@allah_is_the_great


የአላህን እዝነት ማግኘት ለምንፈልግ ሁሉ፦
وإذا قرئ القرآن فاستمعوا له وأنصتوا لعلكم
تزكمون
ቁርኣንም በተነበበ ጊዜ እርሱን አዳምጡ ጸጥም በሉ ይታዘንላችኋልና።(ሡራ አል-አዕራፍ 204)

ቁርኣንን ልብ ሰጥተን በማድመጥ ብቻ የአላህንራሕመት እንላበሳለን አላህ ራሕመቱን ያጎናፅፈን።

🔽 ሀሳብ አስተያየት ለመስጠት 🔽

@Astaytemaschaabot

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚 (Amharic)

የአላህን እዝነት ማግኘት ለምንፈልግ ሁሉ:nnቁርኣንም በተነበበ ጊዜ እርሱን አዳምጡ ጸጥም በሉ ይታዘንላችኋልና።(ሡራ አል-አዕራፍ 204)nnቁርኣንን ልብ ሰጥተን በማድመጥ ብቻ የአላህንራሕመት እንላበሳለን አላህ ራሕመቱን ያጎናፅፈን።nnሀሳብ አስተያየት ለመስጠት ከዚህ በታች ከ '@Astaytemaschaabot' አንዱ መስራት የመረጡትን መልቀቂያ ከዚህ እዚህ ተመልከቱ። ይሄ ቻናል ለሁሉም ቁርኣኖችና አጫጭር መልቀቂያዎች ነው እና ማቅረቢያነት የማቆም የቡድን በጣም አለመኳንልን እና ማሰል የሚል ጥሩ ቡድን በደማቸውን በመጠየቅ ማለፊያ ነው። በዚህ በታች የቁርአኖች እና አጫጭሮች ለመሸባትና በጥቅም ላይ እንዲጠቀሙ ማስረጃ ይችላሉ።

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

10 Feb, 05:06


አደገኛው መለያየት‼️


➡️ መለያየትና መበታተን ክፋት ነው። ከመለያየት አይነቶች ውስጥ አደገኛው በዲን ላይ ሲሆን ነው። በዲን ውስጥ ካሉ መለያየቶች ደሞ ይበልጥ አስከፊው ምንጩ ስሜትን መከተል፣ ዱንያዊ ጥቅምና ውጤቱ ድምበር መተላለፍና መጠላላት የሚያስከስተው ነው።

📚【الآثار ٢/ ١٦٢】

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

07 Feb, 10:43


🔖ከቁርአን በላይ መድሀኒት ከቁርአን በላይ ዶክተር ከቁርአን በላይ አስታማሚ ከቁርአን በላይ አፅናኝ ከቶ ማን አለ!

📍قـــال الإمــام إبـن القـيــم رحمـہ اللـہ تعالـى :

فـالقرآن هـو الـشفاء الـتام مـن جميع الأدواء الـقلبية والـبدنية وأدواء الـدنيا والآخـرة

📚【 زاد الـمعـاد (٣٥/٤) 】
=
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

07 Feb, 10:42


በዚህ ቻናል 𝐴𝑑𝑖𝑚𝑛 መሆን ምትፈልጉ ከበፊቱ በቻናሉ ሲለቀቁ የነበሩ ሁሉንም ስትከታተሉ የነበራችሁ መሳተፍ ትችላለችሁ ረመዷንን ለመጠቀም የሚረዱ እና ሀዲስ ና ቁርአንን መሰረት ያደረጉ የተለያዩ ሙሀዳራዎችን እና ትምሀርቶች ለመልቀቅ ዝግጁ የሆናችሁ
@Astaytemaschaabot

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

04 Feb, 19:16


💐Ramadan 2025 22 days left 🌸

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

24 Jan, 06:23


☑️ ክብርህ ለአላህ ስጥ

ለሚቀጥፋብህ፣ ለሚዋሹብህና ባልዋልክበት ለሚያውሉህ ዝም በላቸው መልስ አትስጥ። ለራስህ ስትከላከል ጊዜ አትፍጅ። ክብርህ ለአላህ ስጥ። ዛሬ የጠሉህ መስሏቸው ክብርህ ላይ እንደፈለጉ የሚረማመዱ ሁሉ አላህ ነገ የውመል ቂያማ ደስተኛ እስክትሆን ድረስ ከመልካም ስራቸው እንዲለግሱህ ያደርጋል። ለዚህ ቀን ጥቅም ስትል ዝም በላቸው። ከሰለፎች ውስጥ ለሚያማቸው አካል ለሰጠኸኝ መልካም ስራህ ውለታ ቢሆን በማለት ስጦታ የሚልክ ነበር።

📍አንድ ሰው ወደ ታላቁ ሶሀብይ አቡ ደርዳእ በመምጣት አቡ ደርዳእ ሆይ! በዚያ ላይ አላህ የሚጠቅመኝ የሆነን ንግግር አስተምረኝ አለው። እሱም፦ «ክብርህን ለአላህ ስጥ። የሚሰድብህና የሚያዋርድህን ሰው ለአላህ ስትል ተወው» በማለት መከረው።

📚 الحلية (٢۱٩/۱)

ሁሌም መልካም የሚያስቡልህ ጥቂቶች እንዳሉ ሁሉ በክፋት የሚሹህ ብዙዎች አሉ። አንተ ግን የወዳጆችህ ውዳሴ እንዳይሸውድህ። የጠላቶችህም ማሸማቀቅ ወደ ኋላ እንዳያደርግህ። በጫጫታዎች መሀል ሆነህ አላማህ ላይ ብቻ አትኩር። ሁሉም ያስብልኛል አልያም ይወድልኛል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው። ሰዎችን ሁሉ ማስደሰት የማይቻል ግብ ነውና ከሰዎች ውዴታና ውዳሴ ይልቅ አላህ ዘንድ ያለውን አስቀድም። በአንተና በአላህ መካከል ያለውን አስተካክል የቀረው አላህ ያስተካክለዋል።

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

24 Jan, 06:22


➡️ ሱረቱል ካህፍ

የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል።

➯የጁምዓ ቀን ሱረቱል ከህፍን የቀራ ሰው አላህ በሁለቱ ጁምዓዎች መካከል ብርሃን ያበራለታል።

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

24 Jan, 06:18


የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
"አንዳችሁ ወደ ጁሙዐ ሶላት መምጣት ሲፈልግ ይታጠብ።" [አልቡኻሪይ፡ 877]
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

20 Jan, 17:32


⭕️👉ወደ ሰዎች ፈላጊ አትሁን..!

قال الإمام ابن تيمية:

አቡል አባስ አህመድ ኢብኑ ተይሚያህ እንደዚህ  ይላሉ..

ومتى كنت مُحتاجاً إليهم -أي الناس- نقص الحب والإكرام والتعظيم بِحسب ذلك، وإن قضَوا حاجتك.

▪️ወደ ሰዎች ፈላጊ ሆነህ በተገኘህ ቁጥር ላንተ ያላቸው ውዴታ፣ ከበሬታ፣ ማላቅ የወረደ ይሆናል እነሱን በጠየከው ልክ።

ሀጃህን ( ከነሱ የፈለከውን) ቢፈፅሙልህም

📚الفتاوى (٤١/١)

=
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

20 Jan, 04:12


🎧 - ارح مسمعك بالقــرآن.

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

20 Jan, 04:09


كيـف أدخُـل الجنّـة ؟

للشيخ عبد الرزاق البدر حفظه اللّٰه تعالى.

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

17 Jan, 04:18


◾️የጁመዓ ቀን ሱናዎች

➊ الغسل
➋ الطيب
➌ السواك
➍ لبس الجميل
➎ قراءة سورة الكهف
➏ التبكير لصلاة الجمعة
➐الإكثار من والصلاة على النبي


♦️ገላን መታጠብ
♦️ሽቶ መቀባት
♦️ሲዋክ መጠቀም
♦️ጥሩ ልብስ መልበስ
♦️ሱረቱ ከህፍን መቅራት
♦️በጧት ለጁመዓ ሶላት መጣድ
♦️በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማብዛት


اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد


https://t.me/+jncA8fcdMas0MzVk
https://t.me/+jncA8fcdMas0MzVk

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

26 Dec, 17:58


🔖የሚዲያ ሱስ……

የጫት ሱስ አለ። የሲጋራ እንዲሁም የሽሻ። በጉዳቱ ከነዚህ የማይተናነስ አንድ ከባድ ሱስ አለ። እሱም የቲክቶክ የዩቱብና የፌስቡክ ሱስ። ሱስ በባህሪው ይስባል። እንዳትላቀቀው ያደርጋል። ለትንሽ ጊዜ ካልተወሰደ ወይም ካልተገኘ ይጨንቃል። የሚዲያ ሱሰኞችም ባህሪ እንዲሁ ነው። ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ እዛ ላይ ይጣዳሉ። ለአንድ ቀን ከሱ ርቀው መዋል አይችሉም። ገንዘባቸው፣ ጊዜያቸውና አቅላቸው ለማይረባ ነገር መስዋእት ያደርጋሉ። ቁርአን አይቀሩ ቂርአት የላቸው ዚክር ኢባዳ አያደርጉ በቃ አይናቸው እስኪያማቸው እዛ ላይ ያፈጣሉ። እንቅልፋቸው ራሱ ባግባቡ ስለማይተኙ ፋዞ ዝንጉ ተነጫናጭ ሆነው ይውላሉ። ይህ ነገር የጤና እክል ከማስከተሉም ጋር አሔራዊ ኪሳራም አለው። በዛላይ አብዘሀኛው ሰው እዛ ላይ የሚያየው ጤነኛ ነገር አይደለም። ሙዚቃ፣ ፊልም፣ የዘር ወሬ፣ ያማይረባ ዜና፣ የተገላለጡ ሴቶችና ሌሎችም ብዙ ጥፋቶች ይመለከታሉ። ለዛም ነው ድንገት ሰው ሲመጣባቸው ደንግጠው የሚዘጉት። በዚህ ሁሉ አላህ ፊት ተጠያቂ ናቸው።

ወጣትነትህ በኢልም በኢባዳ በሀላል ስራ አሳልፈው። በዋዛ ፈዛዛ በቀልድ በጨዋታ አትግደለው።

ሀራም ነገር የምታይበት ስልክ፣ ለዛ ብለህ የምትሞላው ረሲድ፣ የምታባክነው ጊዜ በዚህ ሁሉ ነገ አላህ ፊት ቆመህ ትጠየቃለህ። የዛኔ መልስህ ምን ይሁን?

=
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

26 Dec, 17:44


👉 ምክር ዐረብ ሀገር ላለሽው እህቴ!

እህቴ ገና ዐረብ ከመሄድሽ በፊት እቅድ ይኑርሽ።በእቅድ ተጓዢ! ይህን ያህል አመት ሰርቼ ወደ ሀገሬ እመለሳለሁ የሚለውንም ወስነሽ መሆን አለበት።

አንድ ሰው መለወጥ መቀየር የሚችለው ዐረብ ሀገር ብዙ አመት ስለቆየም አይደለም።ስንትና ስንት እህቶች አሉ ወደ ዐረብ ሀገር ሄደው ብዙ አመት ቆይተው ግን ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ምንም ተለውጠው ወይም የሆነ ቁም ነገር ይዘው አታገኛቸውም። ይህ ስትመለከት ምስጥሩ ዐረብ ሀገር ሄዶ ብዙ አመት መቆየት አለመሆኑ ይገባሻል። ስንትና ስንት እህቶች ደግሞ አሉ ወደ ዐረብ ሀገር ሄደው በትንሽ ጊዜ ቀይታቸው እራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን የሚለውጡ! የሆነ ቁም ነገር ላይ የሚደርሱ ብዙ ናቸው።

እህቴ ዐረብ ሀገር የሄድሽው ለዓላማና ሰርተሽ እራስሽን ቤተሰቦችሽንም ለመቀየር ነውና አደራሽን ዓላማሽን አትዘንጊ!

ብዙ ውጣ ውረድ አልፈሽ ያገኘሽውን ገንዘብሽን አታባክኚ።በማይረባ ነገር አትጠቀሚ።በሚጠቅሚሽ ነገር ላይ አውይው።ቤተሰቦችሽንም እርጅበት።ቤተሰቦችሽንም ቢሆን ስትረጂ ምክንያታዊ በሆነ ነገር መሆን አለበት።እንዲሁ ቤተሰቦችሽም ቢሆኑ ብር ላኪ ስላሉም ብቻ አትላኪ።ከላክሽም ለምን እንደሆነ በሚገባ ከጠየቅሽ በኋላ ይሁን።ስንትና ስንት ወንድሞች፣ባሎች፣አባቶችና ቤተሰቦች አሉ እህቶቻቸውን፣ ሚስቶቻቸውን፣ልጆቻቸውን ወደ ዐረብ ሀገር ልከው እህቶች ስንትና ስንት ችግር፣መከራና ስቃይ አሳልፈው አግኝተው በሚልኩላቸው ገንዘብ ጫት የሚቅሙ፣ምንም በማይጠቅም ነገር ላይ የሚያውሉ አሉ! በጣም ብዙ ናቸው።ስለዚህ እንዲሁ ላኪ ስለተባልሽ ብቻ መላክ የለብሽም።ከሀገር የወጣሽበትን ዓላማ አትርሺ!ብልጥ ሁኚ።

ሌላው ብር ጓደኛ ምረጪ!በጓደኝነት የቀረበ ሁሉ ጓደኛ አይደለም።አንዳንዱ ጓደኝነቱ ካንቺ የሚያገኘውን ጥቅም እስከሚያገኝ ብቻ ነው።ከዛ በኋላ ጥሎ ነው የሚጠፋው።ብዙ እህቶች ይህን ያህል ለፍቼ ያገኘሁትን ገንዘብ በጓደኛዬ ተበላሁ ሲሉ እንሰማለን።ስለዚህ ገንዘብ ላይ ጥንቃቄ አድርጊ።ብዙ ሰው አማና እየበላ ነውና ከቻልሽ አንቺው ያዢው።

ሌላው ቂርኣት ላይ አደራሽን።በርትተሽ ቅሪ።ቴክኖሎጂው ብዙ ነገር አመቻችቷልና ተጠቀሚበት።ከተመቸ እዛው አመቻችተሽ ቅሪ።ካልሆነ ኦን ላይን በሚያስተምሩ ኡስታዞች ዘንድ ተማሪ።ባይሆን ስትማሪ ስለሚያስተምረው ኡስታዝ ማንነት ጠንቅቀሽ እወቂ።ኦን ላይን ላይ የሚያስተምር ሁሉ ጤነኛ ነው ማለት አይደለምና።

በመልካም ነገሮች ላይ ተባበሪ!አሻራሽን አሳርፊ።ለመስጅድ ግንባታዎች፣ለመድረሳዎች፣ለታመሙ ሰዎችና ለተቸገሩ ሰዎች በሚደረገው እርዳታ ላይ ተሳተፊ።ስትተባበሪ ግን አጣርተሽ እርግጠኛ ሆነሽ መሆን አለበት።

ሌላው የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምሽን አስተካክይ።ማህበራዊ ሚዲያ ስትጠቀሚ ለኸይር ስራ ብቻ ይሁን።ለወሬ፣ለጫወታና እርባና ቢስ ለሆኑ ነገሮች አትጠቀሚ!ቁርኣንና ሐዲስ ጠቃሚ ምክሮችን፣የኡስታዞችን ዳዕዋ፣አሰራጪ! በርቺ አላህ ያግዝሽ!


ከወንድምሽ አቡ መርየም

ይቀላቀሉ።ሼር በማድረግ ሌሎችንም ይጋብዙ።!

የቴሌግራም ቻናል=
👉
t.me/AbuMeryemNeja 👈

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

26 Dec, 16:39


⛔️ብዙሃኑ በሚያየው ሚዲያ ላይ ልንጠነቀቀው የሚገባ ጉዳይ❗️

«አሕነፍ ኢብኑ ቀይስ ረሂመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦»

«ውሎዋችንን ከሰው ጋር ስናደርግ፤ ሴትን(ስለተቃራኒ ጾታ ስሜት በሚቀሰቅስ መልኩ ማውራት) እና ምግብን ማውሳት አርቁልን። ሰውየው ስለብልቱ እና ስለ ሆዱ ተናጋሪ የሆነ ሲሆን እኔ አልወደውም(እጠለዋለሁ)።

"ሲየሩ አዕላሚ አኑበላእ (4/94)"

( جَنِّبُوا مَجالِسَنَا ذِكْرَ النساءِ والطعامِ ، إني أَبْغَضُ الرجلَ يكونُ وَصَّافًا لفَرْجِه وبَطْنِه )
[الأَحْنَفِ بنِ قَيْسٍ]


|

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

17 Dec, 19:50


በጊዜ መተኛት ያለው ጥቅም↲

ሌሊት ቁጭ ብሎ ማደር
⇘ የፈጅር ሶላት ማስመለጥ
⇘የጠዋት ስራ በረካ አለው
⇘ከኢሻ በኋላ በወሬ ማሳለፍ

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ


=
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

12 Dec, 18:40


«ዐይኑ አን ናስ »ሐቅ ነው። ይሁንና አጉል ጥርጣሬ እና ከሚገባው በላይ ልትፈራ እና ልትጨናነቅ አይገባም። እለታዊ አዝካር አዘውትር፤ በአላህ ተመካ።

=

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

01 Dec, 19:46


◾️ሸህ ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ አሉ።

አንድ ሰው እውቀት የሚሰጥበት ቦታ ከመሄድ ሊዘናጋና ወደ ኋላ ማለት አይፈቀድለትም። ምክንያቱም ጀነት ለመግባት ሰበብ የሚሆነው አንዲት ጥቅም ሊያገኝ ይችላልና።

📝[ المنتقى (جزء 1 ، ص39)]

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

26 Nov, 21:03


♦️ تلاوة من سورة سبأ
♦️ القارئ: #إلياس_فطاني
•••━══❁✿❁══━•••

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

26 Nov, 11:45


የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ (እርሷም) አላህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣ በርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፤ በላቸው፡፡ እምቢ ቢሉም፡- እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው፡፡ [ቁርዓን 3፥64]

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

24 Nov, 14:54


አደገኛው መለያየት‼️


➡️ መለያየትና መበታተን ክፋት ነው። ከመለያየት አይነቶች ውስጥ አደገኛው በዲን ላይ ሲሆን ነው። በዲን ውስጥ ካሉ መለያየቶች ደሞ ይበልጥ አስከፊው ምንጩ ስሜትን መከተል፣ ዱንያዊ ጥቅምና ውጤቱ ድምበር መተላለፍና መጠላላት የሚያስከስተው ነው።

📚【الآثار ٢/ ١٦٢】

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

20 Nov, 07:35


➡️ አቡ ዘር ሆይ "ከጀነት ድልቦች ውስጥ የሆነ ነገር ልጠቁምህ?" «لَا حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إلَّا بِاللهِ» በል። (ውዱ ነብያችን)

https://t.me/+jncA8fcdMas0MzVk
https://t.me/+jncA8fcdMas0MzVk

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

19 Nov, 14:05


የኡስታዞችን ደዕዋ፣ትምህርቶቻቸውን፣የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶቻቸውን ማለትም የቴሌግራም ቻናሎችን፣የዋቲሳፕ ግሩፖችን፣የፌስቡክ አካውንቶችን፣የዩትዩብ አካውንቶችንና ሌሎችንም የኡስታዞች ትምህርቶች የሚተላለፉባቸውን የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮችን ህዝቡ ዘንድ እንዲደርሱ በማስተዋወቅ፣ኣድ በማድረግ፣ሼር በማድረግ እና ለመስጂዶች ግንባታና ማስፋፍያ፣ለመድረሳ፣ ለታመሙ ሰዎች ለህክምናና ለመሳሰሉት የእርዳታ ጥሪ በሚደረግ ጊዜ ቀድመው የሚሰለፉት  እህቶቻችን ናቸው ።በተለይ በተለይ ዐረብ ሀገር ያሉ እህቶቻችን በጣም በጣም ትልቅ አስተዋፅኦና አሻራ አላቸው። ትልቅ ባለ ውለታዎቻችን ናቸው። ሀገር ውስጥ ያሉትንም ውጭ ሀገር ያሉትንም አላህ ይጠብቃቸው። አላህ የዱኒያም የአኼራም ሓጃቸውን ገር ያድርግላቸው። ያሳቡትን ሁሉ ያሳካላቸው። ውጭ ሀገር ያሉትንም በሰላም ወደ ሀገራቸውና ቤተሰቦቻቸው ይመልሳቸው። አላህ ይጨምርላችሁ። በዚህ ቀጥሉ!

      🖌ወንድማችሁ አቡ መርየም

    👉 
t.me/AbuMeryemNeja 👈

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

18 Nov, 20:00


💢ይህን ሰራሁ ብለህ አትኮፈስ


🔘 قال الشيخ صالح الفوزان - حفظه الله -:
◾️ሸኽ ሷሊህ ቢን ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ አሉ።

🔻【لو قارن الإنسان عمله بِنِعَمِ الله عليه لما بلغت شيئًا يُذكر أمام هذه النعم، فالعمل قليلٌ وإن كَثُر؛ لأنَّ نِعَم الله أكثر وأكثر】
አንድ ሰው የሚሰራው መልካም ስራ አላህ በሱ ላይ ከዋለለት ፀጋ (ኒእማ) አንፃር ሲታይ እንደው ሊጠቀስና ይህ አክል ነው የሚባል አይደለም። ስራችን የፈለገ የበዛ ቢሆንም እንኳ አላህ ለኛ ከሚውለው ውለታ አንፃር በጣም ትንሽ ነው። ምክንያቱም የአላህ ፀጋ ከስራችን እጅግ የበዛና የገዘፈ ነውና።
📚 شرح أصول الإيمان (٢٥٢)

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

08 Nov, 14:40


يَا بُنَيَّ أَقِمِ الصَّلَاةَ وَأْمُرْ بِالْمَعْرُوفِ وَانْهَ عَنِ الْمُنكَرِ وَاصْبِرْ عَلَىٰ مَا أَصَابَكَ ۖ إِنَّ ذَٰلِكَ مِنْ عَزْمِ الْأُمُورِ

«ልጄ ሆይ! ሶላትን አስተካክለህ ስገድ፡፡ በበጎ ነገርም እዘዝ፡፡ ከሚጠላም ሁሉ ከልክል፡፡ በሚያገኝህም መከራ ላይ ታገስ፡፡ ይህ በምር ከሚያዙ ነገሮች ነው፡፡

https://t.me/+jncA8fcdMas0MzVk
https://t.me/+jncA8fcdMas0MzVk

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

05 Nov, 19:36


አማና

---------------------

ኡስታዝ ጅብሪል አክመል

۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩
ሁዳ መልቲሚዲያ

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

05 Nov, 19:34


➡️ ቁርአን ሲቀራ ወደ ቂብላ መዞር⁉️


♦️ለሸኽ ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና ቁርአን ሲቀራ ወደቂብላ መዞር ግዴታ ነውን?

(ቁርን ስንቀራ) ወደ ቂብላ መዞር ይገባል። ምክንያቱም ቁርአን መቅራት ኢባዳ ነው። በኢባዳ ጊዜ ወደ ቂብላ መዞር ይወደዳል። አንድ ሰው ይህን ከገራለትና ከፈፀመው ከማሟያ ይቆጠራል። ነገር ግን ወደ ቂብላ ባይዞር ምንም ችግር የለውም።

📚(المنتقى 2/35)

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

05 Nov, 19:32


▪️ وَلَا يَسۡتَخۡفُونَ مِنَ ٱللَّهِ وَهُوَ مَعَهُمۡ

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

05 Nov, 19:31


◾️ኢማም ሱፍያን ቢን ሰኢድ አሰውርይ "አላህ ይዘንለትና" እንዲህ ብሏል።

ከመልእክተኛው [ﷺ] የትኛውም አይነት ሀዲስ አይደርሰኝም አንዴም እንኳ ቢሆን የሰራሁበት ቢሆን እንጂ።

📚 (السير 2/696)

⭕️👉 አላህ የተግባር ሰው ያድርገን። የምናውቀው ብዙ ነው። የምትንተገብረው ግን በጣም ጥቂቱ ነው። ወደ ምናውቀው መልካም ነገር የምናደርገው ጥሪ ደግሞ እጅግ በጣም ያነሰ ነው። ባወቅነው ነገር የማንሰራ ከሆነ ከመሀይማኖች ጋር ያለን ልዩነት በምንድ ነው? አላህ ያግራልን።

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

30 Oct, 14:42


የሙሉዑ ሰው ባህሪ

➡️ኢብኑል ቀይም ረሂመሁሏህ የአላህ መልእክተኛን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ባህሪ ሲገልጹ እንድህ አሉ፦

➡️የአላህ መልእክተኛ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ለረዥም ጊዜ ዝምታ ያበዙ ነበር። ያለምንም ሀጃ "ጉዳይ" ዝም ብለው አይናገሩም። በማይመለከታቸው ነገር ላይ ገብተው አይናገሩም ነበር። አጅር የሚያስገኝላቸው የሆነን ንግግር እንጂ አይናገሩም። የሆነ ነገር ሲጠሉ በፊታቸው ገፅታ ይታወቅ ነበር።

https://t.me/+jncA8fcdMas0MzVk

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

30 Oct, 04:10


ይድረስ ለሚመለከተው ሁሉ በተለይ ለመስጅድ ኮሚቴዎችና ኻዲሞች!

እንደሚታወቀው በአሁን ሰዓት በየ ቦታው ልመና እጅጉን ተስፋፍቷል። በረግጥ የሚለምኑ ሰዎች ብዙ አይነቶች ናቸው። ከእነዚህም መካከል አንዳንዶቹ እውነትም በተለያዩ ችግሮች የተቸገሩ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ብዙም ያልተቸገሩ ግን አንዴ ቀምሰው ስላዩ ያለ ድካም ስለሚገኝ በዛው ሱስ ሆኖባቸው በልመና የሚቀጥሉ አሉ። አንዳንዶች ደግሞ አላህን ሳይፈሩ እንዲሁ ምንም አደጋ ሳይደርስባቸው እንዲህ አይነት አደጋ ደረሰብን እያሉ ወይም ልጄ ታሞብኝ፣እናቴ ታማብኝ፣አባቴ ታሞብኝ፣እህቴ ወንድሜ  ለህክምና ይህን ያህል ብር ተጠይቀናል እያሉ የተለያዩ ቦታ እየዞሩ በውሸት የሚለምኑ ብዙ ናቸው።

በአጭሩ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት የሚለምኑ እንዳሉ ሁሉ በየ ቦታው የተለያዩ ምክንያቶችን እየፈጠሩ በውሸት በማጨበርበር የሚለምኑ የሰዎችን ገንዘብ የሚበዘብዙም በጣም ብዙ ናቸው።

ሌላው በየ መስጅዶች ሰላት ተሰግዶ እንዳለቀ ወይም ኢማሙ በቀኝ በኩል አሰላምቶ በግራ በኩል ሳያሰላምት ፈጥነው ቆመው ድምፃቸውን ከፍ አድርገው  ጀመዓውን እየረበሹ እየበጠበጡ የሚለምኑም በጣም ብዙ ናቸው። የሚገርመው ፍጥነታቸውን ስታይ ሰላት አልሰገዱም እንዴ! ወይስ ለብቻቸው ነው የሰገዱት ብለህ ትጠራጠራለህ።!ለምሳሌ ዙህር ሰላት ላይ የሆነ መስጅድ ካየሃቸው ዐስር ሰላት ላይ የሆነ መስጅድ ታገኛቸዋለህ።ትላንት  ዲጅታል መታወቂያ ልቀበል ወደ ቤተል ፖስታ ቤት ሄጄ ነበርና በዛው ለዙህር ሰላት ከተቅዋ መስጅድ ወረድ ብሎ ወደ አዲሱ መስጅድ ገባሁ።ሰግጄ ስወጣ ምን አጋጠመኝ ሐሙስ ማታ ዒሻእ ሰላት ላይ አለም ባንክ ሙስዐብ መስጅድ ሲለምን የነበረን ልጅ በር ላይ አገኘሁትና በጣም ገረመኝ።ብቻ በጣም ዐጂብ ነው። አብዛኞቻቸው በሚባል መልኩ እንዲህ ከአንድ መስጅድ ወደ አንድ መስጅድ እየተዟዟሩ ነው ልመናን ስራዬ ብለው የተያያዙት።  አላህ ያስተካክላቸው ቀልብ ይስጣቸው። በእነዚህ ሰዎች ጩሀት
ሰው መስጅድ ገብቶ ሰላቱን በትክክል መስገድ አልቻለም።መስጅድ ገብቶ የቀልብ እረፍት እያገኘ አይደለም።ከሰላት በኋላ በትክክል ዚክር ማድረግ እየቻለ አይደለም። ያመለጠውን ሰላት መስገድ አልቻለም።

አጭባርባሪዎች  ከመብዛታቸው  የተነሳ በትክክል ችግር ያለባቸውን  እንኳን ለመርዳት በጣም አስቸጋሪ እየሆነ ነው።ብቻ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ነው ያለው።

በዚሁ አጋጣሚ ኢማሙ እንዳሰላመተ ብድግ ብላችሁ ሰላት እያቋረጣችሁ ከኋላ ፖሊስ እንደሚያባረው ሰው እየሮጣችሁ የምትወጡ ሰዎችም አላህን ፍሩ! ተረጋጉ! የት ለመድረስ ነው? በርግጥ ሓጃ ሊኖርባችሁ ይችላል።ቢሆንም ብያንስ 5 ደቂቃ እንኳን ሰብር አድርጉ። ሰላት ማቋረጥ ምን ያህል ወንጀል እንደሆነም አስታውሱ። ብቻ ሁኔታችሁ ሲታይ ዳግም ወደ መስጅድ የምትመለሱ አትመስሉምና አስቡበት ለማለት ያክል ነው።

ወደ ጉዳዬ ስመለስ እነዚህ መስጅድ ውስጥ ጀመዓውን እየበጠበጡ የሚለምኑ ሰዎችን በተመለከተ መደረግ ያለበት መፍትሔ ምን መሆን አለበት ከተባለ እንደሚከተለው ይሆናል።

_ የመስጅድ ኢማሞችና ኮሚቴዎች በጣም አንገብጋቢና አስፈላጊ ከሆነ ጉዳይ ውጪ መስጅድ ውስጥ መለመን በጣም ክልክል መሆኑን ለጀመዓው ማሳወቅ።መግብያ በር አከባቢዎች መለመን እንደማይቻል የሚገልፁ ወረቀቶችን መለጠፍ።

_ የመስጅድ ኻዲሞች የሚለምኑ ሰዎችን ልክ እንደቆሙ ወዲያው ሄደው ማስቆም እጃቸውን ይዘው ከመስጅድ ውጪ ወጥተው ድምፃቸውን ቀንሰው እንዲለምኑና መስጅድ ውስጥ መለመን እንደማይቻል መንገር። በተደጋጋሚ የሚመጡ ከሆነ ደግም ዳግም እንዳይመጡ ማስጠንቀቅ።

የሚለምኑ ሰዎችን ከየት እንደመጡና ችግራቸው ምን እንደሆነ በደንብ አድርጎ ማረጋገጥና መጠየቅ።የያዙትንም ወረቀት ህጋዊ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን በደንብ ማጣራት።

_ ሌላው መስጅድ ውስጥ ጀመዓውን እየረበሹ ለሚለምኑ ሰዎች ጀመዓው እዛው መስጅድ ውስጥ ብር መስጠት እንደሌለባቸው ለጀመዓው መንገር።

_ ሌላም መስጅድ እየሄዱ ስለሚለምኑ መረጃ እንዲሆን ፎቶ ማንሳትና ቪድዮ መቅረፅ።

_ ጀመዓውም ይህን ጉዳይ ለመስጅድ ኮሚቴዎችና ኻዲሞች ብቻ  መተው የለበትም። ሊለምኑ ሲቆሙ እዛው ከመስጅድ ሳይወጡ ብር አለመስጠት።ጀመዓውን አትረብሽ ብሎ ከመስጅድ እንዲወጣ ማድረግና ይህንኑ አካል ሌላ መስጅድ ሲላምን አይተው ከሆነ በዚህ በዚህ ቦታ ላይ የመስጅድ ስም ጠቅሶ ማጋለጥ።

_  ምንም አይነት ዑዝር የሌላቸውንና ወጣቶችን ህፃናትን በዚህ ወጣትነታቸው የሆነ ስራ ፈጥረው እንዲጠቀሙና ከልመና እንዲወጡ መምከር።

ብቻ ይህ ጉዳይ በደንብ ይታሰብበት ለማለት ያክል ነው። አላህ የሁላችንንም ችግር ያንሳልን።ለሁላችንም ቀልብ ይስጠን ያስተካከለን። ወሏሁ አዕለም!

እስቲ እናንተም በዚህ ጉዳይ ላይ ያላችሁን ሀሳብና ገጠመኞቻችሁን በኮመንት ፃፉልኝ።

ወንድማችሁ፦ አቡ መርየም

           መልዕክቱን ሼር እያደረጋችሁ!
የቴሌግራም ቻናል፦
👉  t.me/AbuMeryemNeja  👈

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

28 Oct, 16:39


ኹጥባ ዱኣ አምልኮ ነው
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

27 Oct, 02:37


እናታችን አኢሻ  በዘገበቺዉ ሓዲስ የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል ትለናለች!
- عن عائشة رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم - قال : ( ركعتا الفجر خير من الدنيا وما فيها )
📚رواه مسلم  
➡️የፈጂር ሁለት ረካዎች  ከዱኒያ እና በዉስጧ ካሉ ነገሮች ሁሉ ይበልጣሉ

  📚[[ሙስሊም ዘግቦታል]]

♦️እኒህ ሁለት ረካአ የተባሉት ከፈጂር ሶላት በፊት የሚሰገዱት ሱናወች ናቸዉ።

▪️ ነብያችን ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም አገርም ዉስጥ ሁነዉ መንገደኛም ሁነዉ አይተዋቸዉም ነበር።

https://t.me/+jncA8fcdMas0MzVk

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

25 Oct, 20:33


➡️ ዱአ ቀደርን ይመልሳል


♦️ኢብኑ ኡሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ።

ዱአ የአላህን ውሳኔ እንደሚቀይር እወቅ። በዲስ ላይ እንደመጣው 【ቀደርን የሚቀይር ነገር የለም ዱአ ቢሆን እንጂ】 ስንትና ስንት የሚላስ የሚቀመስ የሌለው ድህነቱ ሊያጠፋው የቀረበ የነበረ ዱአ አድርጎ አላህ ዱአው የተቀበለው። ስንትና ስንት በሽተኛ ከመኖር ተስፋ የቆረጠ የነበረ ዱአ አድርጎ ዱአው የሰማው አለ። ከ (شرح الأربعون النووية) ላይ የተወሰደ።
https://t.me/+jncA8fcdMas0MzVk

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

25 Oct, 20:09


👉 የቁርአን ጥፍጥና ከማር የበለጠ ነው
👉 ቁርአን የውመል ቂያማ ወይ ይመሰክርብሀል ወይ ይመሰክርልሀል🌸

http://t.me/+TOuxbrki5gY2iIpt

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

22 Oct, 11:52


በመርካቶው ቃጠሎ ጉዳት ለደረሰባችሁ ወገኖች ሁሉ። ከምንም በፊት ሶብር አድርጉ። አላህ ሰጠ። አላህ ነሳ። ሙስሊም በደስታውም በሀዘኑም ጌታውን ያስባል። ጌታችን እንዲህ ይላል፦

{ وَلَنَبۡلُوَنَّكُم بِشَیۡءࣲ مِّنَ ٱلۡخَوۡفِ وَٱلۡجُوعِ وَنَقۡصࣲ مِّنَ ٱلۡأَمۡوَ ٰ⁠لِ وَٱلۡأَنفُسِ وَٱلثَّمَرَ ٰ⁠تِۗ وَبَشِّرِ ٱلصَّـٰبِرِینَ (155) ٱلَّذِینَ إِذَاۤ أَصَـٰبَتۡهُم مُّصِیبَةࣱ قَالُوۤا۟ إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّاۤ إِلَیۡهِ رَ ٰ⁠جِعُونَ (156) }
"ከፍርሃትና ከረሃብም በጥቂት ነገር፣ ከገንዘቦችና ከነፍሶችም፣ ከፍራፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን፡፡ ታጋሾችንም (በገነት) አብስር። እነዚያን መከራ በነካቻቸው ጊዜ፡ 'እኛ ለአላህ ነን፤ እኛም ወደርሱ ተመላሾች ነን' የሚሉትን።" [አልበቀረህ፡ 155-156]

አልሐምዱ ሊላህ በሉ። የሙእሚን ወጉ ይሄ ነው። በመከራውም በደስታውም ጊዜ ጌታውን አይረሳም። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
عَجَبًا لأَمْرِ المُؤْمِنِ، إنَّ أمْرَهُ كُلَّهُ خَيْرٌ، وليسَ ذاكَ لأَحَدٍ إلَّا لِلْمُؤْمِنِ، إنْ أصابَتْهُ سَرَّاءُ شَكَرَ، فَكانَ خَيْرًا له، وإنْ أصابَتْهُ ضَرَّاءُ، صَبَرَ فَكانَ خَيْرًا له.
"የሙእሚን ነገሩ ይደንቃል። ሁለ ነገሩ መልካም ነው። ይሄ ለሙእሚን እንጂ ለማንም አይደለም። አስደሳች ነገር ቢያገኘው ያመሰግናል። ይሄ ለሱ መልካም ነው። ጉዳት ቢያገኘውም ይታገሳል። ይሄ ለሱ መልካም ነው።" [ሙስሊም፡ 2999]

በማመስገን ታተርፋላችሁ እንጂ አታጡም። በአይነ ህሊናችሁ ቃኘት ቃኘት ብታደርጉ አገር ምድሩ በፈተና ተጥለቅልቆ ታያላችሁ። የባሰ የገጠማቸውን ተመልከቱ። ንብረት ብቻ ሳይሆን ሙሉ ቤተሰብ ያለቀበት ስንት ጉድ አለ። አስቡ። ለመፅናናት ይጠቅማችኋል። ከተስፋ መቁረጥ ይታደጋችኋል። ከባሰ ሁሉ በላይ የባሰ አለ። ከባሰው ያዳናችሁን አመስግኑ። ተስፋ መቁረጥ፣ አጉል ብስጭት ያለፈውን ላይመልስ ከሁለት ያጣ ያደርጋል። ደግሞም እወቁ! አያልፍ የመሰለው ሁሉ ያልፋል። ኢንሻአላህ ነገ ሌላ ቀን ነው።

ከምንም በላይ ግን ዱንያ ነው። ትልቁ ኪሳራ የኣኺራ ኪሳራ ነው። ጌታችን እንዲህ ይላል፦
{ قُلۡ إِنَّ ٱلۡخَـٰسِرِینَ ٱلَّذِینَ خَسِرُوۤا۟ أَنفُسَهُمۡ وَأَهۡلِیهِمۡ یَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِۗ أَلَا ذَ ٰ⁠لِكَ هُوَ ٱلۡخُسۡرَانُ ٱلۡمُبِینُ }
" 'ከሳሪዎች ማለት እነዚያ በቂያማ ቀን ነፍሶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ያከሰሩ ናቸው። ንቁ! ይህ እርሱ ግልጽ ከሳራ ነው' በላቸው።" [አዙመር፡ 15]

አላህ ሶብሩን ይስጣችሁ። በተሻለ ይተካችሁ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

21 Oct, 16:44


የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
ችግር ደርሶበት ችግሩን ሰዎች እንዲቀርፉለት በማሰብ ብሶቱን ለሰው ያሰማ፤ችግሩ አይቀረፍለትም።
በጌታው በመመካት ችግሩን አላህ ላይ ያሳረፈ፤ በፍጥነት አላህ የተብቃቃ ሀብት ይሰጠዋል። ወይ ቅርብ ሀብታም ዘመድ በመሞቱ ይወርሳል። አሊያም በፍጥነት ባለፀጋ ያደርገዋል።”ሰሒህ አቢዳውድ (1645)

=
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

16 Oct, 02:12


ሀቅ ፈላጊ የሆነ ሰው ስህተቱ ሲነገረው አይቆጣም፣ አይሳደብም እንደውም አመስግኖ ይቀበላል


📌قال الشيخ صالح الفوزان حفظه الله
🔘ሸኽ ሷሊህ አልፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና ይህን ብለዋል።

【الذي يريد الحق يفرح بالنصيحة ويفرح بالتنبيه على الخطأ】
♻️ሀቅን የሚፈልግ የሆነ ሰው፦
🔹ሲመክሩትና
🔹ከስህተትህ ተመለስ ተብሎ ሲነገረው ይደሰታል።
شرح كتاب العبودية (252)

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

15 Oct, 10:36


የሃዋሳ ከተማ ከንቲባ ነው እንደ መንግስት ተሿሚ በተገኘበት ቦታ ለተሰብሳቢው ህዝብ ስብከት የሚያከናውነው። እዚች ሃገር ላይ ሴኩላሪዝም የሙስሊሞችን መብት ለማፈን ሲፈላግ ብቻ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

08 Oct, 04:57


Mishary Rashid al Afasy ( 30 juz )

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

07 Oct, 19:27


◾️የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል።

➡️ አላህን የሚፈራ፣ ባለው ነገር ላይ የሚብቃቃና እራሱን የሚደብቅ (ዝቅ የሚያደርግ) ሰው አላህ ይወደዋል።

📚(ሙስሊም ዘግቦታል።)

◾️ሸህ ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ አሉ።

➡️ ነጃ መውጣት (መዳን) የምትፈልግ ከሆነ እነዚህ ሶስት ነገሮች ላይ አደራ፦
①) የአላህን ኪታብ "ቁርአን" አጥብቀህ ያዝ
②) ቅናቻውን "የመልእክተኛው መንገድ" ተከተል
③) ቢድአ "በዲን ላይ ጭማሬ" ተጠንቀቅ።

📚 شرح المنظومة الحائية (ص٥٦)

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

04 Oct, 18:18


....የገዳ ስርዓት⁉️

እኛ ሙስሊሞች ነን ገዳው አይጠራንም፡
ይህ አይነት ስርዓት አያካትተንም፡
የአምልኮ ተግባር ከአሏህ ውጭ አይሆንም፡

ያኮረፈ ያኩርፍ ርር ይበል ድብን፡
የጌታችን ቁጣ በላዕ እንዳይወርድብን፡
ከገዳ አስተሳሰብ ከመገለል አለብን፡

የኦሮሞ ጀግኖች ኢስላም ያነፃቸው፡
ከሰማያት በላይ አንድ ነው ጌታቸው፡
አሏህን መገዛት ይህ ነው አላማቸው፡
በዚህም ረገድ ውብ ታሪክ አላቸው፡

ጥቁር ቀይና ነጭ ከለር አናመልክም፡
የፀዳ እምነት አለን ዛፍ አንታከክም፡
አሏህ የፀዳ ነው የለም ጥቁር ጌታ፡
የዚህ ተረት አማኝ ያስቡ ቀጥታ፡

ብርሀን ጨለማ ሁሉን የፈጠረው፡
ለሰውም ለጅንም ጥበብ ያስተማረው፡
ሰወችን ከሌሎች መርጦ ያከበረው፡

ብቸኛው ፈጣሪ አሏህ ነው ጌታችን፡
ጉድለት የለበትም ውቡ እስልምናችን፡
ዋቃ እሚባል ኮተት የለም በዐዕምሯችን፡

ግፍ እየተሰራ በዚህ ሁሉ መዓት፡
የአጋንንት አምልኮ የሸይጦን ግብዓት፡
እንደዚህ ነው ለካ የገዳ ስርዓት⁉️

የኦሮሞ ሙስሊሞች ከዚህ ዘግናኝና የሽርክ ተግባር ተጠንቀቁ‼️

ይህ እጅግ ዘግና ለአዕምሮ የሚከብድ ለመናገር የሚቀፍ ከኢስላም የሚያሶጣ አስተሳሰብ ነው።

http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

04 Oct, 08:35


የጁምአ ቀን
~~~~~~~~

ነብዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ)እንዲህ ብለዋል ፡ አርብ(ጁመዓ) ቀን፡ ገላውን ታጥቦ መላ ሰውነቱን አፀዳድቶ ፡ቅባትና ሽቶ ከተቀባ በሗላ ጁመአ ለመስገድ ቀደም ብሎ ወደ መስጊድ ፡በመሔድ ሌሎች ሰዎችን ሳይገፋና ሳይረብሺ በፀጥታ ቦታውን ለሚይዝ ፡ከዚያም የቻለውን ያህል (ነፍል) ከሰገደ በሗላ በፀጥታ ኹጥባን(የኢማሙን ንግግር )ለሚያዳምጥ ሰው ከዚያ ጁመዓ ጀምሮ እስከሚቀጥለው ጁመአ ድረስ በመካከል ያለው ሐጢያቱን አላህ ይተውለታል፡፡ ነብዩ{ሰ,ዐ,ወ} ስለ ጁምአ ቀን ታላቅነት ሲናገሩ የጁምአ ቀን የቀኖች ሁሉ ኑጉስ ነው እነዚህ አምስት ነገሮች በጁምአ ቀን ተከስተዋል ብለዋል። እነሱም
1, አላህ አደምን የፈጠረው በጁመአ ቀን ነው፣
2, አደም ከጀነት የወጡት በጁምአ ቀን ነው፣
3, አደም የሞተውም በጁመአ ቀን ነው፣ 4, ቂያማ የምትቆመውም በጁመአ ቀን ነው፣
5, በጁምአ ቀን የሆነች ሠአት አለች።አንድ የአላህ ባሪያ የጠየቀውን ነገር ይሠጠዋል፣ያቺን ሠአት ካገኛት ሀራም ነገር እስካልሆነ ድረስ አላህ ይቀበለዋል። በሌላ የሀድስ ዘገባ አንድ ሰው ታጥቦ ያለውን ጥሩ ልብስ ለብሶ ሽቶ ተቀብቶ ወደ መስጂድ ሄዶ ማንንም አዛ ሳያደርግ ኢማሙ ቁጥባ ሲያደርጉ ዝም ብሎ ከሠማ ጁማአውን ከሰገደ አላህ ካለፈው ጁምአ እሥከ አሁኑ ጁምአ ያለውን ወንጀሉን ያብስለታል። በሌላ የሀድስ ዘገባ የጁምአ እለት በመጀመሪያ ሠአት ወደ መስጅድ የገባ ግመል ሰደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ የቀንድ ከብት ሠደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ በግ/ፍየል ሰደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ ዶሮ ሰደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታል። ከዚህም አርፍዶ የመጣ እንቁላል ሠደቃ እንዳደረገ ይፃፍለታላ። ኢማሙ ሚንበር ላይ ሲወጡ የሚመዘግቡት መላኢኮች የኢማሙን ኹጥባ ለመስማት መስጂድ ይገባሉ። የአላህ መላእክተኛ(ሰ,ዐ,ወ) እንድህ ብለዋል፦

የጁምአ ቀን በእኔ ላይ ሠላወትን ማውረድ አብዙ፣ማንኛውም ሠው የጁምአ ቀን በእኔ ላይ ሠላዋት አያወርድም ሠላዋቱ ቢቀርብልኝ እንጅ።

{አልባኒ ሶሂህ ብለውታል} ‌"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ። መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነወ።" ‌ "ሶለቲቱም በተፈጸመች ጊዜ በምድር ላይ ተበተኑ። ከአላህም ችሮታ ፈልጉ፡፡ አላህንም በብዙ አውሱ፡፡ ልትድኑ ይከጀላልና፡፡" ((62:9_10)

የጁመአ ቀን ሱናወች ~~~~~~~~~~~~~‌
~ገላን መታጠብ
~ ጥሩ ልብስ መልበስ
~ሽቶ መቀባት ለወንዶች
~ ሲዋክ
~ ማልዶ በግዜ ወደ መስጅድ መሄድ
~ ሱረቱል ካፍን መቅራት ዱአ ማብዛት ~ በረሱል (ሰ፣ዐ፣ወ) ላይ ሰለዋት ማውረድ።

‌ اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد ال

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

26 Sep, 10:18


▪️አዲስ ቆንጆ ምክር


የአላህ ስሞችና መገለጫዎች
የአላህን እውቀት በተመለከተ
የሲህርና የድግምት ሁክም
🔰ሌሎችም ወሳኝ ነጥቦች ተወስቶበታል

🎙الشيخ سلمان العبادي حفظه الله
https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

20 Sep, 20:04


🔹 تلاوة أول سورة الحشر
🔹 القارئ: #عبدالرحمن_الماجد
•••━══❁✿❁══━•••

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

20 Sep, 03:24


◼️የጅሙአ ቀን ሰለዋትን እናብዛ


إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا
↪️ አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ ሶለዋት ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በመልእክተኛው ላይ ሶለዋት አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡
📚(ሱረቱ አል- አሕዛብ - 56)

اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد


http://t.me/+TOuxbrki5gY2iIpt

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

15 Sep, 23:01


▪️ለወላጆች መልካም ማድረግ‼️
                  
አላህ እንድህ ብሏል:-
♦️ وَٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا۟ بِهِۦ شَيْـًۭٔا ۖ وَبِٱلْوَٰلِدَيْنِ إِحْسَٰنًۭا(النساء ٣٦)
➡️አላህንም ተገዙ። በእርሱም ምንንም አታጋሩ። ለወላጆች መልካምን ስሩ።(አል ኒሳዕ)

♦️وَوَصَّيْنَا ٱلْإِنسَٰنَ بِوَٰلِدَيْهِ حَمَلَتْهُ أُمُّهُۥ وَهْنًا عَلَىٰ وَهْنٍۢ وَفِصَٰلُهُۥ فِى عَامَيْنِ أَنِ ٱشْكُرْ لِى وَلِوَٰلِدَيْكَ إِلَىَّ ٱلْمَصِيرُ(لقمان ١٤)

➡️ሰውንም በወላጆቹ (በጎ እንዲያደርግ በጥብቅ አዘዝነው። እናቱ ከድካም በላይ በሆነ ድካም አረገዘችው። ጡት መጣያውም በሁለት አመት ውስጥ ነው። ለእኔም ለወላጆችህም አመስግን በማለት አዘዝነው። መመለሻው ወደኔ ነው። (ሉቅማን 14)

➡️ኢብኑ መስኡድ (ረዲየሏሁ አንሁ)እንዳሉት ለነብዩ ስለሏሁአለይሂ ወሰለም ከስራዎች አላህ ዘንድ ይበልጥ ተወዳጅ ምንድን ነው? ብዬ ጠየኳቸው ፣

♦️እሳቸውም ሰላትን በወቅቱ መስገድ ከዚያስ ቀጥሎ?ስላቸው ለወላጆች መልካም መዋል አሉ። ከዚያስ ቀጥሎ ስላቸው በአላህ መንገድ ላይ ትግል ማድረግ አሉኝ ።

📚(ቡኻሪ ሙስሊም ዘግቦታል።)

http://t.me/+TOuxbrki5gY2iIpt

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

15 Sep, 21:27


እንዲህ ነው ነብዩን ﷺ መውደድi
~
ወደው አይደለም በ734 ሂጅሪያ የሞቱት ታጁዱን ዑመር ኢብኑ ዐሊይ አልፋኪሃኒ እንዲህ ያሉት፡-
“ለዚህ መውሊድ በቁርኣንም በሱናም መሰረት አላውቅለትም። በዲን ላይ ተምሳሌት የሆኑትና የቀደምቶችን ትውፊቶች አጥብቀው የያዙ ከሆኑት የሙስሊሙ ህዝብ ምሁራኖች ከአንዳቸውም ተግባሩ አልተወሰደም። ይልቁንም ቦዘኔዎች የፈጠሩት ቢድዐ ነው። ሆዳ ሞች ያተረፉበት የሆነ የነፍስ ዝንባሌ ነው። ...
ይህ እንግዲህ ነብዩ ﷺ የተወለዱበት ረቢዐል አወል ወር የሞቱበትም ከመሆኑ ጋር ነው። መደሰቱ በሱ ውስጥ ከማዘን ቅድሚያ የሚሰጠው አልነበረም።” [አልመውሪድ ፊ ዐመሊል መውሊድ]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

15 Sep, 04:39


📖ሸይኽ ሷሊህ አል ፈውዛን እንዲህ ብለዋል፡-
«እውነትን የሚፈልግ በምክር ደስ ይሰኛል፣ ስሕተቱን ሲነገረው ደስ ይለዋል «እንጂ አይከፋም»።"

(ሸርሑ ኪታቢ አል – ዑቡዲያህ (252)

=
http://t.me/+TOuxbrki5gY2iIpt

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

14 Sep, 16:06


መውሊድ የሙስሊሞች ኢድ አይደለም።

መውሊድ በዲን ላይ የተጨመረ መጤ በአል ነው።

🎙በአቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ

=
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/13620

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

07 Sep, 19:39


የ ቲክቶክ ትውልድ

🎙ሸይኽ ኤልያስ አሕመድ

ሁዳ መልቲሚዲያ

۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩
http://t.me/+TOuxbrki5gY2iIpt

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

07 Sep, 19:18


📻 መውሊድ መቼ ተጀመረ?
🎙ሸይኽ ሙሐመድ ወሌ ረሒመሁ'ላህ

http://t.me/+TOuxbrki5gY2iIpt

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

07 Sep, 14:57


۞إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ اللَّهِ أَتْقَاكُم۞
۞ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ ۞(ቁርአን 49:13)

ያ አላህ! አንተን ከሚፈሩ ባሮችህ አድርገን።💚


http://t.me/+TOuxbrki5gY2iIpt
http://t.me/+TOuxbrki5gY2iIpt

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

07 Sep, 03:24


ሐራም ነገር ከባዱ የመጀመሪያው ነው። ከዚያ ሲደጋገም እየቀለለ ይሄዳል። ከዚያ እንዲሁ ተራ ነገር ይሆናል። ከዚያ ልማድ ይሆናል። ከዚያ ይጣፍጣል። ከዚያ ልብ ይሸፈናል። ከዚያ ልብ ሌላ ሐራም መፈለግ ይጀምራል።
አንድ ሷሊሕ ሰው እንዲህ ይላል፦ "ነፍስህ ወደ ወንጀል ከጋበዘችህ በዚች አንቀፅ አጭር ቃለ መጠይቅ አድርግላት :-
قُلۡ أَذَ ٰ⁠لِكَ خَیۡرٌ أَمۡ جَنَّةُ ٱلۡخُلۡدِ ٱلَّتِی وُعِدَ ٱلۡمُتَّقُونَۚ 
"እንዲህ) በላቸው፡ 'ይሄ ነው የሚሻለው ወይስ ጥንቁቆቹ ተስፋ የተሰጧት የዘለዓለሟ ጀነት?' " [አልፉርቃን፡ 15]

በዚህ ሐራም ነገሮችን መዳፈር በበዛበት ዘመን ይህቺን አንቀጽ ማስተዋል ምንኛ አንገብጋቢ ነው?!

ከዐረብኛ የተመለሰ @IbnuMunewor

📚ሀዲሦችና አጫጭር የቁርአን አንቀፆች መልቀቂያ ቻናል 📚

06 Sep, 19:51


♦️የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

➡️ ሀሳቡና ጭንቁ ዱንያ ብቻ የሆነ ሰው፣ ጉዳዩን አላህ ይበታትንበታል፣ ድህነቱን በዓይኑ መሀል ያደርግበታል፣ ከዱንያም የተቀደረለት እንጂ አይመጣለትም።

➡️ ሀሳቡና ጭንቀቱ አኼራ የሆነ ሰው አላህ መብቃቃትን በቀልቡ ያደርግለታል። ጉዳዩን ይሰበስብለታል። ዱንያ የግዷ ወደሱ ትመጣለች።

📚(ቲርሚዚይ ዘግቦታል)