🏷አል-በያን / البــيان @al_beyann Channel on Telegram

🏷አል-በያን / البــيان

@al_beyann


የዚህ ቻናል አላማ ፦ በሀገራችንም ሆነ ከሀገራችን ውጭ ያሉ የተለያዩ አጥፊና አውዳሚ አንጃዎች እስልምናንና ሙስሊሞችን እንዳያጠሙ ቁርአንና ሀዲስን በሰለፎች ግንዛቤ በማስተማር መከላከልና የአናጃዎቹን ማንነት መገለፅ ነው።

◌አል- በያን ( البــيان)

⏳https://t.me/Al_Beyann

አል-በያን البــيان (Amharic)

አል-በያን ( البــيان) የተኽፊርዮች ሹብሀና አስከፊነታቸው የሚገለፅበት እና የሚዳሰስበት ልዩ ቻናላችን ነው። ይህ ቻናል ታዳጊ ቢሆን፣ ሥራዊት ባገኘ ቦታ ምንጮቸን እና የሚደረግ እድሉን ያልተጠቀሱትን መረጃዎች ለማስተካዉ የሚያዘንብ የምርምር ቻናል ነው። በሚመለከት ላይ የሚባሉት ከቻናላችን የሚተላለፍ ጥቅምት ነህዋ? ለምን ነዉ በመኝታ ከወይም ከፍቅር በተለይም ስለ ዋጋ፣ ሰላም እና ለሌሎች ቻናሎች ትምህርት የሚመስሉ መረጃዎች የለም። በዚህ በላይ ስለ እኛ የምንሄድለት ለመሆኑ ይህን ቻናልን አብራክራት በእንቅስቃሴው ለማስተላለፍ እና የተከፈተ መረጃ ለማግኘት የምንረዳለት ለማደም የሚከተለው እና በተጨማሪም መረጃ ቻናል።

🏷አል-በያን / البــيان

16 Nov, 08:55


#በያን
--------
🔖አጠር ያለች  በያን   ሙስጦፋ ተክፊሪዩ ከኢኽዋን ጋር ስለተሻሸበት አስገራሚ ንግግሩ ይዳሰስበታል።

⬇️⬇️

🩸በጭፍን አትከተሉ ይቅርባችሁ ሙስጦፋ እቀብር አብሯችሁ አይገባም እንደማይሳሳት አርጋችሁ አትያዙ ።

🎙ከወንድማችን :አቡ ዓብዲላህ  ዘይኑ ገነቴ/ አላህ ይጠብቀው።

💠💠

🔑ወደ ቻናሉ ለመቀላቀል⬇️
🔗https://t.me/al_beyann/1313

🏷አል-በያን / البــيان

16 Nov, 07:24


💥አዲስ ነገር💥 جديد جديد💥

بسم الله الرحمن الرحيم

♻️ታላቅ የዳዕዋና የዚያራ ፕሮግራም  ወደ ሰሜን ወሎ♨️

📅ዛሬ በዕለተ ቅዳሜ ህዳር 07/2017 E.C


🌎ከደሴ ወደ ሰሜን ወሎ ወዳሉት ከተሞች   ከታላላቅ ኡስታዞቻችን እና ወንድሞቻችን ጋር  ከትመናል‼️

🔺============🔸============🔺

① ኡስታዝ አቡ ዙምሩድ ነቢል ዐሊ ደሴ

② ኡስታዝ አቡ አብደረህማን  ሼይኽ ሀሰን ደማጅ

③ ኡስታዝ አቡ ሙቅቢል አወል  ዳውድ

④ ኡስታዝ አቡ ሃቲም ሰኢድ ሼይኽ ሀሰን

⑤ ኡስታዝ አቡ ኢብራሂም  አንዋር ሙሀመድ

⑥ኡስታዝ አቡ ሙጃሂድ ኡመር አደም

እና ሌሎችም ታላላቅ ወንድሞች ይገኙበታል



{ وَمَا بِكُم مِّن نِّعْمَةٍ فَمِنَ اللَّهِ}


📢ፕሮግራሙ  🛜በቀጥታ ስርጭት🛜  ይተላለፋል

┈┉┅━❀🍃🌸🍃❀━┅┉┈

📲 አጠቃላይ ፕሮግራሞቻችን በሶሻል
ሚዲያ ለመከታተል:

♦️ይህ የሰለፍዮች ልሳን የሆነው
"ሁድሁድ ስቱድዮ"
            ነው‼️

🗞️ በ Telegram~Channel 👇
🌐https://t.me/Hudhud_Studio

🗞️ በFacebook page👇👇
https://www.facebook.com/Hudhud.wello

🏷አል-በያን / البــيان

14 Nov, 20:00


📮ኡለማዖችና ሙስጦፍ ክደቱ
በሚል ርዕስ የተዘጋጀ በያን።

----------------------------------------------
#ቁጥር ❶

💠💠

🩸በድምፁ የተካተቱ ነጥቦች

🔖ባጠቃላይ ኡለማወች ትልቅ ደረጃ እንዳላቸው ከቀደምቶች የተወሰኑ ብርቅየ ኡለሞችንም ጠቅሷል።

🔖በተለየ መልኩ የየመን ኡለሞችን እስከነ መርከዛቸው በዝርዝር በትኖ ገልፇል።
-------------------------------

🎙በወንድማችን: አቡ ሀቲም ሰኢድ ገነቴ/አላህ ይጠብቀው።
---------------⬇️⬇️-------------
🔗https://t.me/al_beyann/1310

🏷አል-በያን / البــيان

13 Nov, 12:26


🔖ስለ ሙስጦፋ እና ስለ ተክፊርዮች የተዳሰሰበት በያን

#ቁጥር -2

💠💠

🕌በመስጂደ ሱና

🎙በኡስታዝ አቡ ሃቲም ሰኢድ ሼይኽ ሐሰን حفظه الله

----------------⬇️⬇️---------------
🎙ድምፁን ለማግኘት👇
🔗https://t.me/al_beyann/1309

🏷አል-በያን / البــيان

13 Nov, 12:17


🔖ስለ ኡለማዎች ክብር

#ቁጥር-1
💠💠💠

🔑ከኡለማዎችላይ መከላከል

🔑እውን ሼኽ አቡ ቢላል እደሚሉት ነውን

🔑ሙስጦፋ ተ*ክ*ፊ*ሪ*ው ስለ ቀበዣዠራቸው ነጥቦች በስሱ ተዳሶበታል

📌እና ሌሎች አንገብጋቢ የሆኑ ነጥቦች ተጠቅሷል። ይደመጥ ሼር!!

----------------⬇️⬇️------------

🎙️️በኡስታዝ አቡ ሃቲም ሰዒድ ሼኽ ሃሰን حفظه الل


---------------
🎙ድምፁን ለማግኘት👇

https://t.me/al_beyann/1307

🏷አል-በያን / البــيان

13 Nov, 12:08


#በያን ቁጥር -01

🏷ከወንድሞቻችን ጋር የተግባባንባቸው ነጥቦች

💠💠

🏷እሰዎች ላይ ሳያጣሩ ከመውደቅ አላህ ይጠብቀን።

💠💠

🎙ወንድማችን; አቡ ዓብደላህ ዘይኑ ገነቴ/አላህ ይጠብቀው።
--------------⬇️⬇️-------------
🔗https://t.me/al_beyann/1306

🏷አል-በያን / البــيان

13 Nov, 12:05


🔖 በድጋሜ የተለቀቀ

📌 ስለመጅሊስ ማብራሪያ ?

💠💠

ለምን ገባችሁ ለምትሉ እና ነገሩን ለምትደጋግሙ ሰዎች!?

🎙በኡስታዝ ;አቡ ዙምሩድ
ነቢል /አላህ ይጠብቀው።

📁 ድምፁን ለማግኘት👇
-------------⬇️⬇️--------------
https://t.me/al_beyann/1305

🏷አል-በያን / البــيان

13 Nov, 12:03


🔖«ሙስጦፍ ክደቱ በኡለማዎች ላይ ያለው ድንበር ማለፍ እና የተክፊሪ አመለካከቱ..

 
#ቁጥር(2)
 💠💠

🩸 በሚል ርዕስ የተደረገ መደመጥ ያለበት ገሳጭ እና መካሪ የሆነ  በያን ።

🎙በታላቁና ወደ الله ተጣሪ በሆነው በኡስታዝ አቡ ዙምሩድ  ነቢል  ዐሊ ደሴ  حفظه الله

((مَنْ يُرِدِ اللَّهُ بِهِ خَيْرًا يُفَقِّهْهُ فِي الدِّينِ، وَإِنَّمَا الْعِلْمُ بِالتَّعَلُّمِ)).

---------------⬇️⬇️----------------
🕌 ወሎ ኮምቦልቻ
____
🎙ድምፁን ለማግኘት👇

🔗https://t.me/al_beyann/1304

🏷አል-በያን / البــيان

13 Nov, 12:00


🔖«በያን ስለ አዲሶቹ ተ*ክ*ፊ*ሪ*ዎች

#ቁጥር(1)
 💠💠

🩸 በሚል ርዕስ የተደረገ መደመጥ ያለበት ገሳጭ እና መካሪ የሆነ  በያን ።

🎙በታላቁና ወደ الله ተጣሪ በሆነው በኡስታዝ አቡ ዙምሩድ ነቢል ዐሊ ደሴ حفظه الله

((مَنْ يُرِدِ اللَّهُ بِهِ خَيْرًا يُفَقِّهْهُ فِي الدِّينِ، وَإِنَّمَا الْعِلْمُ بِالتَّعَلُّمِ)).

---------------⬇️⬇️----------------
🕌 ወሎ ኮምቦልቻ
____
🎙ድምፁን ለማግኘት👇
https://t.me/al_beyann/1303

🏷አል-በያን / البــيان

13 Nov, 11:48


🔖በሙስሊሞች ላይ የተሰለጠው ከባድ የተክፊሪ ቡድን በሚል ርዕስ ;-

#ቁጥር-7
💠💠💠

🩸ስለ
#ተ*ክ*ፊ*ሪዮች ባህሪና ድርቀት ቆንጆ የሆነ ተከታታይ ምክር

🕌ፉርቃን መስጂድ

فماذا بعد الحق إلا الضلال

-----------⬇️⬇️--------

🎙በሼይኽ አቡ አብደረህማን አብራር አላህ ይጠብቀው።

💠💠

ድምፁን ለማግኘት👇

🔗https://t.me/al_beyann/1302

🏷አል-በያን / البــيان

13 Nov, 11:45


🔖በሙስሊሞች ላይ የተሰለጠው ከባድ የተክፊሪ ቡድን በሚል ርዕስ ;-

#ቁጥር-6
💠💠💠

🩸ስለ
#ተ*ክ*ፊ*ሪዮች ባህሪና ድርቀት ቆንጆ የሆነ ተከታታይ ምክር

🕌ፉርቃን መስጂድ

فماذا بعد الحق إلا الضلال

-----------⬇️⬇️--------

🎙በሼይኽ አቡ አብደረህማን አብራር አላህ ይጠብቀው።

💠💠

ድምፁን ለማግኘት👇
🔗https://t.me/al_beyann/1301

🏷አል-በያን / البــيان

13 Nov, 11:42


🏷 የባጢል ሰዎችን ተጠንቅቅ ከነሱም አስጠንቅቅ...

....ባጢላቸው ግልፅልፅ ብሎ እንዳይወጣ..በዘረኝነት እና መሰል በሆኑ ቆሻሻ ተግባራት...

🚨 የሀቅ ሰዎችን ለመበተን ብዙ ጥረት ይደረጋል ነገር ግን ጠሰንቃቂያችንን እንያዝ።

📌ከዑለማዎችጋር ያለንንም ግንኙነት እናጠንክር እኛን ከነሱ ለማራቅም የተከፈተው ዘመቻ ይብቃ!

--------------⬇️⬇️--------------
🎙 ሸይኽ አቡ ዐብዱረህማን አብራር ቢን ሙሓመድ አላህ ይጠብቀው።

-------------
🔗https://t.me/al_beyann/1300

🏷አል-በያን / البــيان

13 Nov, 11:37


🔖ተንቢህ በቀን 23-11-2016

#ቁጥር-5

💠💠

👉 እውነት ያ ተክፊሪይ ላይ ረድ ሲደረግ ኢልያስ ላይ ረድ ማድረግ ተፈልጎበት ነው ?

📌በተክፊሪ ፊክራ የተለከፈ በመስጂዳችንም በመድረሳችንም ቦታ የለውም...

📌ተክፊሪዮች ሰለፊዮችን ለመነጣጠል የሚያደርጉት ሴራ ተቀባይነት የለውም...

📌ከሰለፊዮች መካከል ለተክፊሪዮች ዲፉአ ለሚየደርጉ ዱዐ አድርጉላቸው
...

📌እድለኛ ሰው ማለት ከፊትና የራቀ ሰው ነው በሚል የተሰጠ መደመጥ ያለበት ወቅታዊ ተንቢህ።

----------------⬇️⬇️--------------
🎙 በሸይኽ አቡ ዐብዱረህማን አብራር ቢን ሙሓመድ አላህ ይጠብቀው።

https://t.me/al_beyann/1299

🏷አል-በያን / البــيان

13 Nov, 11:34


🔖 ደርስ ላይ የተሰጠ ተንቢህ

#ቁጥር 4

💠💠

📌ተክፊሪዮች እና ሰለፊዮች አንድ እንዳልሆኑ...

📌 አንድን ነጥብ አንስተው ችክ ሚሉት ለምንድነው?...

📌መለክያው ቁርዓን ሀዲስ በሰለፎች ግንዛቤ እና በዑለማዎች ካልሆነ ውድቀቱ የቀረበ ነው...

-----------------⬇️⬇️---------------
🎙 ሸይኽ አቡ ዐብዱረህማን አብራር ቢን ሙሓመድ አላህ ይጠብቀው።
-------
https://t.me/al_beyann/1298

🏷አል-በያን / البــيان

13 Nov, 11:26


🔖ተክፊርነቱ ገሀድ የወጣው ሙስጠፋ ክደቱ

#ቁ.03
💠💠

📌የጠማማውና የተክፊሪው ሙስጠፋ አብደላህጥመትና ድንበር አላፊነት...

📌 ከዚህ ተክፊሪይ ሚከላከል እና ለሱ ሚከራከርን ሰው መራቅ እና መጠንቀቅ...

📌 የዚህ አካል ጥመት የተደበቀበት እና ግልፅ ያልሆነለት አካል መቶ መጠየቅ እንደሚችል...

⚠️ አነዚህ እና ሌላም ወሳኝ ነጥቦች የተብራራበት ረድ {ተንቢህ}።

---------------⬇️⬇️---------------
🎙 በሸይኻችን አቡ ዐብዱረህማን አብራር ቢን ሙሓመድ

🕌 በፉርቃን መስጂድ

🔗https://t.me/al_beyann/1297

🏷አል-በያን / البــيان

13 Nov, 11:22


🔖ተክፊርነቱ ገሀድ የወጣው ሙስጠፋ ክደቱ

#ቁ.02

የጠማማውና የተክፊሪው ሙስጠፋ አብደላህጥመትና ድንበር አላፊነት...

ከዚህ ተክፊሪይ ሚከላከል እና ለሱ ሚከራከርን ሰው መራቅ እና መጠንቀቅ...

⚠️ አነዚህ እና ሌላም ወሳኝ ነጥቦች የተብራራበት ረድ {ተንቢህ}።
----------------⬇️⬇️-------------
🎙 በሸይኻችን አቡ ዐብዱረህማን አብራር ቢን ሙሓመድ አላህ ይጠብቀው።

🕌 በፉርቃን መስጂድ አላህ ይጠብቃት።

💠💠

🔗https://t.me/al_beyann/1296

🏷አል-በያን / البــيان

13 Nov, 10:46


🔖 ተክፊርነቱ ገሀድ የወጣው ሙስጠፋ ክደቱ

#ቁ.01
-----------
የጠማማውና የተክፊሪው ሙስጠፋ አብደላህ...

...ጥመትና ድንበር አላፊነት የተብራራበት ረድ {ተንቢህ}።

-----------------⬇️⬇️---------------

🎙 በሸይኻችን; አቡ ዐብዱረህማን አብራር ቢን ሙሓመድ አላህ ይጠብቀው።

🕌 በፉርቃን መስጂድ አላህ ይጠብቃት።

https://t.me/al_beyann/1295

🏷አል-በያን / البــيان

08 Nov, 13:51


‼️#አዲስ_አዲስ      #ክፍል_04

🔖كلام نفيس حول تكفير المعين

💠💠💠
🏷መረጃ ሳይደርሰው እና ሳይገለፅለት በተናጠል አንድን አካል ካፊር ነህ ማለት ;-

🔖ተመሳሳይነት ያለዉ ጥያቄ ለታላቁ ሸይኽ አሸይኽ ሙሀመድ አማን አል–ጃሚይ رحمه الله
 
🎙لفضيلة الشيخ العلامة  محمد أمان الجامي  رحمه الله تعالى

🔷🔶🔷
https://t.me/al_beyann/1293
https://t.me/al_beyann/1293

🏷አል-በያን / البــيان

08 Nov, 12:13


‼️#አዲስ_አዲስ #ክፍል_03 ⬇️⬇️

🏷በተናጠል አንድን አካል ካፊር ማለት‼️

-----------------💠💠--------------
📌አይደለም አፍሪካ ላይ የአረብ ደሴት ላይ ሆነው ጅህልና ያለቀቃቸው አሉ።

#تكفير_المعين


🎙الشيخ محمد أمان الجامي/رحمه الله.

🔷🔶🔷
https://t.me/al_beyann/1292
https://t.me/al_beyann/1292

🏷አል-በያን / البــيان

08 Nov, 12:03


‼️#አዲስ_አዲስ_ይደመጥ።

#ክፍል_02 ⬇️⬇️

🏷ማን ነው ሙዐየን ላይ ሁክም ሚሰጠው ተራ ሰውን እውን ማክፈር ይችላልን ?

🔖من الذي يحكم على المعين
هل يستطيع عن يكفِر  العامي
التكفير شئنه عظم

🏷በኡለምች ና በነዚ ሰዎች መሀል ያለው ልዩነት
📥قول
📌الشيخ حسين با شئيب
📌الشيخ أبو عمرو
📌الشيخ عبد الحميد الحجوري
📌الشيخ الفوزان
📌الشيخ أبو بلال الحضرمي

🔑التكفير التفسيق التبديع ترجع إلى أهل العلم

---------------አል💠በያን-------------
https://t.me/al_beyann/1291
https://t.me/al_beyann/1291

🏷አል-በያን / البــيان

08 Nov, 11:46


‼️#አዲስ_አዲስ_ይደመጥ።

#ክፍል_01⬇️⬇️

📋#تكفير_المعين
------
🔑 ሁጃ ሳይደርሰው ወይም ሳይብራራለት አንድን አካል መተናጠል ካፊር በሚለው ነጥብ ላይ ዑለሞቻችን ምን አሉ?

🔖ما ذا قال العلماء عن تكفير المعين

📌الشيخ با جمال
📌الشيخ عبد الحميد
📌الشيخ الفوزان
📌الشيخ الشمري
📌الشيخ الوادعي

💠التكفير المعين لا بد من إقامة الحجة وانتعاء الموانع
🔑አንድን አካል ለይቶ  ካፊር ለማለት ሁጃ ማቆምና ከልካይ ነገሮች መወገድ  ግዴታ አለባቸው።

💠إذا كان جاهل يبين له يوضح ولا يستعجل في الحكم

🔑አላዋቂ መሀይም ከሆነ ለሱ ይብራራለታል እሱን ካፊር ለማለትም አይቸኮልበትም።

---------------አል💠 በያን ---------------
https://t.me/al_beyann/1288
https://t.me/al_beyann/1288

🏷አል-በያን / البــيان

07 Nov, 16:32


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته.

---------------------💬

📋#የአህሉሱና ኡለማዎች ስለ ኡዝር ቢል ጀህልና ስለ ተ*ክፊርዮ*ች ምን አሉ;- የድምፅ ማስረጃዎችን ይዘን እንቀርባለን። ⬇️⬇️

-------------🔹🔹🔶🔶🔹🔹-------------

🔑ድምፁ ላልደረሳቸው በማድረስ ሙስሊሙን ከተክፊር ጥመት እንታደገው ዘንድ በአላህ ስም እንጠይቃለን።

------------------🎙🎙🎙------------

جزاكم الله خيرا وبارك الله فيكم.

⬇️⬇️ሊንኩን በመጫን ግሩፑን ይቀላቀሉ።
----------------------⬇️⬇️----------------
https://t.me/al_beyann
https://t.me/al_beyann
https://t.me/al_beyann

አል-በያን البــيان

06 Nov, 08:56


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
.
-----------------------📚📚------------------------

📋ከታች የምትመለከቶቸው በክፍል የቀረቡ ርዕሶች የተከፊርዮችን የሹበሀ ወጥመዶችንና ጥመት  ከብዙ በትቂቱ የተዳሰሰበት ቁረዓናዊ ፣ ሀዲሳዊና ቀደምት እና በዘመናችን ያሉ ዑለማዎች ስለ ዑዝር ቢል ጀህል እና ስለ ተክፊርዮች ምን አሉ በሚለው የቀረበ ወቅታዊ መረጃና ትምህርቶችን ይዟል።

⬇️⬇️ሊንኮቹን በመጫን ትምህርቱን ይከታተሉ።


📚📚

🔖ክፍል 1 - ኡዝር ቢል ጀህል ማለት ምን ማለትነው?
🔗https://t.me/al_beyann/1234
🔖ክፍል 2 - ኡዝር ቢልጀህል ቁረዓናዊ ማስረጃው።
🔗https://t.me/al_beyann/1235
🔖ክፍል 3 - ኡዝር ቢልጀህል ቁረዓናዊ ማስረጃው።
🔗https://t.me/al_beyann/1237
🔖ክፍል -4 - በኢስላም ኡዝር ቢል ጀህል ለመኖሩ የተዳሰሰበት
🔗https://t.me/al_beyann/1240
🔖ክፍል -5 - በኢስላም ኡዝር ቢል ጀህል ለመኖሩ የተዳሰሰበት
🔗https://t.me/al_beyann/1242
🔖ክፍል -6 - በኢስላም ኡዝር ቢል ጀህል ለመኖሩ የተዳሰሰበት
🔗https://t.me/al_beyann/1246
🔖ክፍል -7 - በኢስላም ኡዝር ቢል ጀህል ለመኖሩ የተዳሰሰበት
🔗https://t.me/al_beyann/1250
📌ክፍል -8- ኡዝር ቢል ጀህል በኡለማዎች እይታ።
🔗https://t.me/al_beyann/1251
📌ክፍል -9- ኡዝር ቢል ጀህል በኡለማዎች እይታ።
🔗https://t.me/al_beyann/1252
📌ክፍል -10- ኡዝር ቢል ጀህል በኡለማዎች እይታ።
🔗https://t.me/al_beyann/1253
📌ክፍል -11- ኡዝር ቢል ጀህል በኡለማዎች እይታ።
🔗https://t.me/al_beyann/1254
📌ክፍል -12 - ኡዝር ቢል ጀህል በኡለማዎች እይታ።
🔗https://t.me/al_beyann/1257
📌ክፍል -13 - ኡዝር ቢል ጀህል በኡለማዎች እይታ።
🔗https://t.me/al_beyann/1258
📌ክፍል -14 - ኡዝር ቢል ጀህል በኡለማዎች እይታ።
🔗https://t.me/al_beyann/1259
🔖ክፍል -15- መሳኢል ዟሂራ እና ኸፍያ።
🔗https://t.me/al_beyann/1269
🔖ክፍል -16-የተክፊርዮች ሹበሀና ማደናገሪያ
🔗https://t.me/al_beyann/1276
🔖ከ3ክፍል -17- ሁጃ/ ወይም ኡዝር ቢል ጀህል የለም ብለው ከኢስላም ለማስወጣት የሚደገፍባቸው ነጥቦች
🔗https://t.me/al_beyann/1282

💠አል-በያን💠

አል-በያን البــيان

05 Nov, 14:53


#ገፅ-➎- ክፍል -❶➐-

-------------------

• ከአላህ ሲፋቶች የአንዷን ትርጉም የቀየረ ወይም ተእዊል ያደረገ፤ በግልፅ ባየነው እንጂ ስለማንበይን ሰውየው ዑዝር አይሰ፞ጠ፞ውም (ካፊር ነው)!!

• አላህ የባሮችን ስራ የፈጠረ መሆኑን የተቃወመ ዑዝር አይሰጠውም (ካፊር ይሆናል)፤ ምክንያቱም እኛ ያለብን ግዴታ በገሃድ ባየነው መፍረድ ነውና!!

• አስካሪ መጠጦችን በተእዊል ሐላል ያደረገ ሰውም በዟሂር በተገኘው መሐከም እንጂ ሌላ ሀላፊነት ስለሌለብን ዑዝር አይሰጠውም፤ (ካፊር ነው።)
፣ ፣ ፣
እንዲህ እያሉ መሐከም ግድ ሊላቸው ነው!!

ይህ ሁሉ ብይን ደግሞ ሸሪዓዊ መረጃዎችና ከአህሉስ ሱና የሆኑ ዑለማእ ሙሐቂ፞ቁን ከሚያራምዱት አቋም ጋር የሚጋጭ ዋልታ ረገጥ ብይን ነው!!

ይህን ቃዒዳ መነሻ አድርገው ዑዝር የማይሰጡ አካላት ግን በገሃድ ሲተ፞ገበሩ በሚታዩ አስከፋሪ በሆኑ በሁሉም ጉዳዮች ላይ ተግባራዊ አላደረጉትም፤ ይልቁንም ሺርካዊ በሆኑ መሳኢሎችና ግልፅ በሆኑ መሳኢሎች ብቻ ነው ቃዒዳውን ገድበው ተግባራዊ የሚያደርጉት።

አንድ ሰው በግልፅ ኩፍር ሲሰራ ከታየ ያ ኩፍር የሆነ ነገር መስአላ ዟሂራ ሳይሆን መስአላ ኸፈያ ከሆነ ወይም ደግሞ ሺርካዊ ጉዳይ ካልሆ ዑዝር ይሰጡታል።

ይህ ደግሞ ሰዎቹ በአካሄዳቸው ተናቁዽ እንዳላቸውና በመሰረቱ የተሳሳቱ መሆናቸውን ያሳያል።

ስለዚህ "በግልፅ በታ፞የ፞ው ይተሓከማል" የሚለውን ቃዒዳ በመያዝ ዑዝር ቢልጀህል የለም በሚሉት ሰዎች አካሄድ ከተጓዝን እፊታችን ሁለት መንገድ እንጂ ሌላ አማራጭ አይኖረንም።

• ወይ፦ በሁሉም አስከፋ፞ሪ በሆኑ ጉዳዮች የዑዝር ቢል ጀህልን በር ዝግ ማድረግ፤ ብሎም አስከፋሪ ነገር ላይ ወድቆ የተገኘ ማንኛውንም ሰው ካፊር ነው ብለን መበየን፤ ምክንያቱም በግልፅ በተገኘው መበየን እንጂ ሌላ ሀላፊነት ስለሌለብን፤ የውስጡ የአላህ ሀላፊነት ነው።

• ወይም ደግሞ፦ ሌሎች በርካታ ሸሪዓዊ መረጃዎች በሚያስፈርዱት መልኩ ቃዒዳው ጋር ተዓሙል ማድረግ ነው። ማለትም፦ የተክፊር ሸርጦች መሟላታቸውንና ከልካዮቹ መወ፞ገዳቸውን እርግጠኛ እስክንሆን ድረስ፤ ግለሰቡን ነጥለን የክህደትን ስያሜ ለመለጠፍ በግልፅ እላዩ ላይ የታየውን ዟሂር ነገር መገኘቱን ብቻ በመመርኮዝ ላና፞ከፍር ነው።

ቃዒዳውን በከፊል ርእሶች ተግባራዊ ለማድረግ ተሞርኩዘውበት፤ በሌሎች ርእሶች ላይ ግን ተግባራዊ ላለማድረግ ቃዒዳውን ባለመሞርከዝ መለያየት፤ በዚህ አካሄዳቸው "ተናቁዽ መንሀጂይ" ውስጥ የወደቁ ከመሆናቸው ጋር መረጃ የሌለውን መከፋፈልን ከፍለዋል።

ባጠቃላይ እስካሁን በተመለከትነው ሰፋ ያለ ዳሰሳ፦ ይህን ቃዒዳ መነሻ አድርገው ዑዝር ቢል ጀህልን የሚከለክሉ አካለቶች ሶስት አይነት ስህተት ውስጥ የወደቁ መሆናቸው ይገለፅለሃል።

①ኛ ዑለማኦች በዚህ ቃዒዳ ምን እንደፈለጉበት አልተገነዘቡም፤ የሚ፞ያ፞ያዝበትን ወይም የሚ፞ንጠለጠልበትን ቦታም በደንብ አልለዩ፞ም።
ምክንያቱም ዟሂር ሲባል መጀመሪያ ላይ እንደተቀደመው፦ ከእሱ ጋር የሚቃረን ሌላ ዟሂር አብሮት ያለ፞ ሳይሆን፤ የሚጋጨው የሌለው ሷፊ ጥርት ያለ ዟሂር ነው የተፈለገበት።

② የኢስላምን ስያሜ ከሚያፀድቀው ዟሂር ይልቅ
የኩፍርን ስያሜ የሚያፀድቀውን ዟሂር አስቀድመዋል። ይህም ከላይ እንዳሳለፍነው ሸሪዓዊ መረጃዎች ከሚጠቁሙት እውነታ ጋር ይጣረሳል።

③ ቃዒዳውን በሺርክ ጉዳዮች ብቻ እንጂ በሁሉም አስከፋሪ ነገሮች ላይ ተግባራዊ አላደረጉትም፤ ይህ ደግሞ መረጃ በሌለበት ነገር ብያኔ ሰጭነት ነው።

ስለዚህ ወንድሜ ሺርክ ላይ የወደቀን ሰው ባየህ ቁጥር "ለና ማ ዞሀረ" በሚል ሑጃ ሙስሊሞችን በማክፈር ዱንያ ኣኺራህን እንዳታጠፋ!!
አትቸኩል፤ በረድ ሰከን በል፤ ተረጋጋ፤ የሰውየውን ሁኔታ አስተውል፤ መስፈርቶች መሟላታቸውንና ከልካዮች መወገዳቸውንም እርግጠኛ ሁን፤ ሰለፊዩን የሆኑ ዑለማኦችን አማክር፤ ከዚያ በኋላ አላህ ፊት የማታፍርበትን ሑክም ከእነሱ በመነሳት ትሐክምበታለህ!!

«فهذا هو الحقُّ ما به خفاءُ

* * * * ***

فَدعْنِي مِن بُنَيَّاتِ الطَّريق».

انتهى المراد.

🫵 هذا المنشور عبارة عن ترجمة مختصرة نقلًا من كتاب مباركٍ بعنوان: «إشكالية الإعذار بالجهل في البحث العَقَدِي»٣١٠ـ ٣١٩  تأليف سلطان بن عبدالرحمن العميري.

💠💠

🖌አቡ ዐብዲላህ ሰዒድ (አስ ሰለፊ)

🗓2/1/1444هـ

-------------------💎----------------------

ثَبَّتَهُ اللهُ عَلَى الإسْلَامِ والسُّنَّة، وأثَابهُ ثَوَابَ الدُّنْيا والْآخِرة، وَجَعَلَ جُهْدَهُ الْمُقِلَّ في مِيزانِ حَسناتهِ.
📋 ------------------⬇️⬇️

⬇️⬇️በሌላ ርዕስ እንገናኝ@

🔗https://t.me/al_beyann/1282
🔗https://t.me/al_beyann/1282

----------------አል-በያን ----------------

📋
#ይቀጥላል...

አል-በያን البــيان

05 Nov, 14:49


#ገፅ-❹- ክፍል-❶➐-
---------

[አንድ ወቅት ሰዕድ ኢብኑ ዑባዳህ እንዲህ አለ፦ "አንድን ሰው ከባለቤቴ ጋር ብመለከተው በሰይፉ ጎን ሳይሆን በስለቱ በኩል እመታው ነበር"፤ ይህም ንግግር መልእክተኛው ﷺ ዘንድ ደረሰና እሳቸውም እንዲህ በማለት ተናገሩ: «በሰዕድ "ጘይራ" ቅናቻ ትገ፞ረ፞ማላችሁን!? በአላህ ይሁንብኝ እኔ ከእሱ የበለጠ "ጘይራ" አለኝ፤ አላህ ደግሞ ከእኔ ይበልጥ "አጝየር" ነው፤ ከዚህም የተነሳ በግልፅም ሆነ በድብቅ የሚሰ፞ሩ፞ መጥፎ ስራዎችን ሐራም አደረገ። ከአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ የበለጠ ቅናቻ ያለው አንድም ሰው የለም። *ከአላህም የበለጠ "ዑዝር" ወይም ሳይቀጣ በስተፊት ማስጠንቀቅ ወደሱ ይበልጥ ተወዳጅ የሚሆንለት ማንም ሰው የለም* ፤ ከዚህም የተነሳ መልእክተኞችን አብሳሪና አስጠንቃቂ አድርጎ ልኳል። ...» ]

ይህ ሐዲሥ ኢዕዛር ማድረግ ኢዕዛር ካለማድረግ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ይጠቁማል፤ እሱም ወደ አላህ ይበልጥ ተወዳጅ ነው።

🔖እነዚህ ሁሉ መረጃዎች ሙስሊም የሆነን አካል ከማክፈር መጠንቀቅ እንደሚኖርብንና ከማክፈር በፊት መረጋጋትና ሊጤ፞ኑ የሚገባቸውን ነገሮች ማጤን ግድ መሆኑን፤ እንዲሁም ለማክፈር መሽቀዳደም ሐራም መሆኑን ይጠቁማሉ።

👉 አህሉስ ሱናዎች ከላይ ያለፉትንና የመሳሰሉትን ማእዘኖች መሰረት በማድረግ ከሌላው ይልቅ የኢስላምን ስያሜ የሚያፀድቀውን መሰረት ያስቀድማሉ፤ ይህም ዑለማኦች አንድን ሙስሊም ያለ በቂ መረጃ ማክፈርን አጠንክረው ያስጠነቀቁበትን ሚስጥር ይገልፅልሃል።

ነገር ግን አህሉስ ሱናዎች ይህን እምነት መከ፞ፈር ለሚገባውም ሰው ሳይቀር የተክፊርን በር ሙሉ ለሙሉ በሚዘጋ መልኩ ሁል ጊዜ  የማይቀየርና የማይለወጥ ነገር አድርገው አያዩትም። ይልቁንም ከዚህ ሁኔታ ወደ ሌላኛው ሁኔታ እንዲሸጋገሩ ግድ የሚያደርግ ግልፅ መረጃ ከተገኘ፤ ማለትም ለሰውየው የኢስላም ስያሜ እንዲፀድቅለት ግድ ከሚያደርግ ዟሂር ይልቅ የክህደት ስያሜ እንዲፀድቅበት ግድ የሚያደርግ ዟሂር ጠንካራና በጣም ግልፅ ከሆነ፤ ያን ትተው ይበልጥ ግልፅ የሆነውን በመያዝ በኩፍር ይሐክሙበታል።

ከዚህም የተነሳ አህሉስ ሱናዎች ከቁርአንና ከሐዲስ መረጃዎች በመነሳት
*የተክፊር ሹሩጦችና ተክፊርን የሚከለክሉ መዋኒዖች* የሚባሉ ማሰሪያዎችን አመጡ።

እነኚህን ነገሮች ያመጡበት ምክንያት፦ በአንዳንድ አስከፋ፞ሪ ተግባራት ላይ የወደቀ ወደ ኢስላም የሚጠጋ ግለሰብ፤ በላዩ ላይ ሁለቱ ሁኔታዎች ሲጋጩባቸው በፍትህ አመዛኙን ብይን ለመበየን እንዲያስችላቸው ነው።
እነሱ ዘንድ ለብይን ግምት ውስጥ የሚገባው፦ ያለ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ እንዲሁ አስከፋሪው ነገር በዟሂር ወይም በግልፅ መገኘቱ ብቻ ቢሆን ኖሮ፤ እነኚህን ሹሩጦችና መዋኒዖች ባላመጡ ነበር።
የአህሉስ ሱናዎች መዝሀብ ሸሪዓዊ መረጃዎች የሚያስፈርዷቸውን ነገሮችና የሰው ልጆችን ተፈጥሯዊ ሁኔታ አጣጥሞ በማስኬድ ላይ የተገነባ ነው። ማለትም ወደ ኢስላም ኢንቲሳብ የሚያደርግ የሆነ ግለሰብ ላይ ሁለት ዟሂሮች ሲጋጩባቸው፦ ግለሰቡ ያለ፞በትን ነባራዊ እውነታና ሁኔታን የሚገልፁ ወደ ሆኑ ሙረጂ፞ሓቶች ወይም አመዛኝ ወደ ሆኑ ነገሮች ይሄዳሉ።

ግለሰቡ ኩፍር ላይ ሲወድቅ እያወቀ በእንቢተኝነትና በአስተባባይነት ከሆነ፤ ወይም ከሐቅ ለማፈንገጥና ሐቁን ለመያዝ ተካሱል በማድረጉና በመሳነፉ ከሆነ፤ አለያም አቅልሎ በማየትም ከሆነ፣ ይህ ሰው ከኢስላም የወጣ ካፊር ተብሎ ይበየንበታል።

ኩፍር የሆነውን ተግባር ሲሰራ ከኢስላም እስከ መውጣት እንደሚያደርሰው የማያውቅ ሆኖ ከሆነ ግን፦

«فإنه يبقى على الأصل، وهو ثبوتُ وصفِ الإسلام له».

ይህ ሰው በመሰረቱ ላይ እንዳለ ተደርጎ ይታሰባል፤ ማለትም የኢስላም ስያሜ እንደፀደቀለት ይቀራል። ይህ አይነቱ ሁኔታ ብዙውን ጊዜ ሙስሊሞች ዘንድ የሚከሰት ነገር ነው።
ምክንያቱም በኢስላምና በነቢዩ አማኝ የሆነ ግለሰብ በርካታ ጉዳዮችን መልእክተኛው የተናገሯቸው ወይም ያዘዙባቸው መሆኑን ሳያውቅ ሊያስተባብልባቸው ወይም ደግሞ ሊቃወማቸው ይችላል፤ መልእክተኛው የተናገሯቸው ወይም ያዘዙባቸው ነገሮች መሆናቸውን ቢያውቅ ኖሮ የሚያስተባብልና የሚቃወም ባልሆነ ነበር፤ ይልቁንም ለንግግራቸው የሚያድር፣ ትእዛዛቸውንም የሚፈፅምና ወደ አላህም ተመላሽ ነበር የሚሆነው።

(انظر مجموع الفتاوى لابن تيمية: 7/237)

በዚህ ዙሪያ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ "መጅሙዑል ፈታዋ" (7/237) ላይ ያወሳውን ተመልከት።

«والحاصلُ ممَّا سبقَ أنَّ تكفيرَ المعيَّن المُنتسِبِ إلى الإسلام لا يصحُّ أن يُعْتَمَدَ في تكفيره على مجرَّدِ ما ظهر منه مِن المكفِّرات، وإنما لا بُدَّ فيه مِن التَّحقُّق مِن حاله ومعرفةِ منشإ أفعاله؛ إذ أنَّ ذلك العبد مُتعارضٌ يحتاج إلى تحقُّقٍ وترجيحٍ وتبيُّنٍ لحقيقة أمره».

🔖ያሳለፍነው ሀሳብ ጠቅለል ሲል፦ ወደ ኢስላም የሚጠጋ የሆነን ሰው በተዕዪይን ነጥሎ ለማክፈር፤ ከሰውየው በዟሂር የሚታዩ አስከፋሪዎች መገኘታቸውን ብቻ በመደ፞ገፍ ማክፈር ትክክል አይደለም። ይልቁንም የሰውየውን ሁኔታ ማረጋገጥና የስራዎቹንም መንስኤ ማወቅ ግድ ነው። ምክንያቱም ሰውየው፦ ማስረገጥ፣ አመዛኙን መለየትና ትክክለኛ የሰውየውን ሁኔታ ማጣራት የሚያስፈልጋቸው ሁለት የሚጋጩ ሁኔታዎች እላዩ ላይ ስለተገኙ ማለት ነው።

🔖"አል ሑክሙ ቢዟ፞ሂር" የሚለውን ቃዒዳ ተደግፈው ሺርክ በሆኑ መሳኢሎች ዑዝር ቢል ጀህል የለም የሚሉ አካላት የተሳሳቱ መሆናቸውን ከሚጠቁሙ ነገሮች መካከል፦ ይህ ንግግራቸው በማንኛውም የሐይማኖቱ መሳኢሎች ወይም ጉዳዮች፦ ሺርካዊ በሆኑትም ይሁን ባልሆኑት፣ መሳኢል ዟሂራም ይሁኑ መሳኢል ኸፊያ፣ በጀህልም ሆነ በተእዊል ዑዝር መስጠት እንዳይኖር የዑዝርን በር ሙሉ በሙሉ መዝጋትን ማስያዙ ወይም (ማስፈረዱ ነው)!!

ምክንያቱም ዑዝር ላለመስጠት ተፅኖ ፈጣሪ ወይም ወሳኝ የሆነው ጉዳይ፦ ከግለሰቡ በዟሂር የታዩት አክፋሪ ተግባራት መገኘታቸው ብቻ ከሆነ፤ ይህን ወሳኝ ነገር በሁሉም ዟሂር በሆኑ ነገሮችም ጭምር ተግባራዊ ሊያደርጉትና ሊያስኬዱት ግድ ይላቸዋል።

«• فمن أنكر صفةً من صفات الله بالجهل، فهو غيرُ معذورٍ؛ بِحُجة أنه ليس لنا إلا الحُكم على الظاهر!

• ومن أوَّل صفةً من الصفات الإلهية فهو غير معذور؛ لأنه ليس لنا إلا الحكم على الظاهر!

• ومن أنكر خَلْقَ الله لأفعال العباد فهو غير معذور؛ لأنه ليس لنا إلا الحكم على الظاهر!

• ومن استحلَّ الخمر بالتأوُّل فهو غير معذور؛ لأنه ليس لنا إلا الحكم على الظاهر!

• ومن سجد لمخلوقٍ جاهِلًا بالحكم فهو غير معذور؛ لأنه ليس لنا إلا الظاهر!

وهذا كله مخالِفٌ لِما دلَّتْ عليه النصوص الشرعية، ولِما عليه العلماءُ المحقِّقون من أهل السنة

ከዚህ በመነሳት፦
👇

• ከአላህ በርካታ ሲፋቶች አንዷን የተቃወመ ግለሰብ ዑዝር አይሰ፞ጠ፞ውም (ካፊር ነው)፤ ለምን? ከተባለ
"በዟሂር በታየው መበየን እንጂ ሌላ ነገር ስለሌለን በሚለው ሑጃ፞"!!

-------
#ወደ ገፅ -➎- ተሸጋገሩ።↩️

አል-በያን البــيان

05 Nov, 14:44


#ገፅ -➌- ክፍል - ❶➐-

---------------------

🔖አህሉስ ـ ሱና ወልጀማዐዎች ከሌሎቹ ሁኔታዎች ይልቅ ኢስላም እንዲፀድቅለት የሚያደርገውን ሁኔታ "ራጂሕነቱን" ወይም አመዛኝነቱን ሲገልፁ ከበርካታ አንግሎች አንፃር ነው።

①ኛ ለአንድ ሰው በተዕዪይን ነጥለን የኢስላምን ስያሜ እንድናፀድቅለት  ከሚጠቁሙ ሸሪዓዊ አካሄዶች ጋር ተስማሚ መሆኑ ነው። ሸሪዓዊ መረጃዎች፦ የኢስላምን ስያሜ ለማፅደቅ በጣም ዝቅተኛ ጠቋሚ የሆነ ነገር መገኘቱ በቂ እንደሆነ ያመላክታሉ።

እንደ ምሳሌ የኡሳመቱ ኢብኑ ዘይድን ሐዲሥ እንመልከት።

• *ኢማሙል ቡኻሪና ኢማም ሙስሊም ኡሳመቱ ኢብኑ ዘይድ የተባለው ሰሓቢይ* እንዲህ ማለቱን ዘግበውልናል፦

[የአላህ መልእክተኛ ﷺ ጁሀይና ወደሚባሉ ጎሳዎች ዘመቻ ላኩን፤ እኛም ሄደን ንጋቱ ላይ በመውረር አሸነፍናቸው። የሸሹትም ሸሹ፤ እኔና የሆነ አንሷሪ አንዱን ሰው ተከትለን ደረስንበት፤ ከበብ አድርገን መፍለክለኪያ ስናሳጣው "ላ ኢላሃ ኢለሏህ" አለ። አንሷሪዩ ተወው፤ እኔ ግን በያዝኩት ጦር ወግቼ ገደልኩት፤ ከዚያ (የሰራሁት ስራ) በጣም ከበደኝና ለነቢዩ ነገርኳቸው። (በሌላ ሪዋያ) {ጉዳዩ ደረሳቸው} እና «ኡሳማ ሆይ! ላ ኢላሃ ኢለሏህ ካለ በኋላ ገደልከውን?» አሉኝ። እኔም: "እንዳንገድለው ፈርቶ በእሷ ለመጠ፞በቅ ፈልጎኮ ነው ቃሏን የተናገራት" አልኳቸው። እሳቸውም: «ይህን የተናገረው ከግድያ ለመጠ፞በቅ ፈልጎ ይሁን አይሁን (ምን አሳወቀህ)፤ ልቡን ሰንጥቀህ አይተኸዋልንዴ!?» አሉኝ። ምነው ከዚህ ቀን በፊት ባልሰለምኩ ብዬ እስከምመኝ ድረስ፤ የአላህ መልእክተኛ ﷺ ይህን መልሳቸውን ከመደጋገም አልተወገዱም።]

• የቁርኣን ሙፈሲሮች ሱረቱ አን ኒሳእ አንቀፅ ቁጥር 94 ስር የጠቀሷቸው የኢብኑ ዐባስና የሚቅዳድ ኢብኑል አስወድ ሐዲሦች፤ እንዲሁም በሰሒሑል ቡኻሪ: (6866) የተዘገበው የሚቅዳድ ኢብኑል አስወድ ሐዲሥ እንደ ተጨማሪ ምሳሌ ይጠቀሳሉ።

እነዚህ ሐዲሦች ላይ የሰውየው *ዟሂር* ኡሳማ እንደተገነዘበው ቃሏን ከግድያ ለመዳን የተናገራት መሆኑን ቢጠቁምም፤ *ከዚህ ዟሂርነት የጎላ ሌላ ተቃራኒ ዟሂር ሰውየው ላይ ስለተገኘ የኢስላም ስያሜ "ኢብቲዳአን" (በጅምሩ) ሊፀድቅለት እንደሚገባ ነቢዩ ﷺ* ገልፀውልናል።

ይህ ክስተት አንድ ግለሰብ ላይ ሁለት ሁኔታዎች የሚጋጩበት ሆነው ከተገኙበት፦ የኢስላምን ስያሜ የሚያፀድቀውን ሁኔታ ማስቀደም እንደሚኖርብን በግልፅ ይጠቁማል!!

②ኛ አሽ ሸሪይዓ አል ኢስላሚያ ከሙናፊቆች ጋር ሙዓመላ ማድረጉ ነው። የኢስላም ሸሪይዓ ከሙናፊቆች በዟሂር ወይም በግልፅ ከሚታይባቸው ነገሮች በመነሳት ከትክክለኛ ሙስሊሞች ጋር ትስስር ያላቸውን አሕካሞች ለእነሱም ሰጥቷል።
ይህን በተመለከተ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ እንዲህ ይላል፦

«وقد اتَّفق العلماءُ على أنَّ اسْمَ المسلمين في الظاهر يَجري على المنافقين؛ لأنهم استسلموا ظاهرا، وأَتَوْا بما أتوا به مِن الأعمال الظاهرة، بالصلاة الظاهرة والزكاة الظاهرة والحج الظاهر والجهاد الظاهر، كما كان النبيُّ ﷺ يُجْرِي عليهم أحكامَ الإسلام الظاهرِ» (مجموع الفتاوى: 7/351)
 
«የሙስሊሞች ስያሜ በዟሂር ለሙናፊቆች እንደሚ፞ሰ፞ጥ፞ ወይም እንደሚውል ዑለማዎች በእርግጥ ተስማምተዋል፤ ምክንያቱም በዟሂራቸው ኢስላምን ተላብሰዋልና። እንዲሁም ከሚሰሯቸው ግልፅ ስራዎች፣ ግልፅ ሰላት፣ ግልፅ ዘካ፣ ግልፅ ሐጅና ግልፅ ጂሃድን በገሃድ ይተገብሩ ከነበረው ተግባራቸው በመነሳት (የሙስሊሞች ስያሜ ተሰጥቷቸዋል)። ይህ ማለት ልክ የአላህ መልእክተኛ ﷺ በዟሂራቸው ወይም በላያቸው ላይ የሚታየውን የኢስላምን አሕካሞች ይሰጧቸው እንደነበረው ማለት ነው።» (መጅሙዑል ፈታዋ: 7/351)

👌ይህ እንግዲህ የኢስላምን ስያሜ አፅዳቂ የሆነው ዟሂር በሸሪዓችን ጥግ የደረሰ ደረጃና ቦታ እንዳለው ይጠቁማል። ጠንካራ የሆኑ አስረጂ ነገሮች እስካልተገኙም ድረስ እሱን መተላለፍ ትክክል አይሆንም።

③ኛ የኢስላም ስያሜ የፀደቀለትን ግለሰብ ማክፈርንና በዚህ ጉዳይ ላይ መሽቀዳደምን አጥበቀው ከሚያስጠነቅቁ መረጃዎች ጋር ይበልጥ ተስማሚ መሆኑ ነው።

በዚህ ጉዳይ ሙተዋቲር ደረጃ የደረሱ በርካታ የረሱል ﷺ ሐዲሦች መጥተዋል።
ከእነዚህ ሐዲሦች መካከል፦

•¹• ኢማሙል ቡኻሪ አቡ ሁረይራን (ረዺየላሁ ዐንሁ) በመጥቀስ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ማለታቸውን ዘግቧል፦

«إِذَا قَالَ الرَّجُلُ لِأَخِيهِ : يَا كَافِرُ. فَقَدْ بَاءَ بِهِ أَحَدُهُمَا»

 «ሰውየው ወንድሙን "ያ ካፊር!" ካለ፤ በእርግጥ ከሁለቱ ወደ አንድኛቸው ተመለሰ»

•²• ኢማሙ አቡ ዳውድ (4687) ኢብኑ ዑመርን (ረዺየላሁ ዐንሁማ) በመጥቀስ ነቢዩ ﷺ ቀጣዩን ከባድ ዛቻ መናገራቸውን አስተላልፈውልናል፦

«أَيُّمَا رَجُلٍ مُسْلِمٍ أَكْفَرَ رَجُلًا مُسْلِمًا، فَإِنْ كَانَ كَافِرًا وَإِلَّا كَانَ هُوَ الْكَافِرَ»

ማንኛውም ሙስሊም ሰው ሌላን ሙስሊም የሆነን ሰው ካፊር ካደረገው፤ (እንደሱ ብይን ሰውየው በእርግጥ) ካፊር ከሆነ (ጥሩ ወይም ዳነ!!)፤ ያለበለዚያ ግን ተናጋሪው እሱ ራሱ ካፊር ይሆናል»

•³•ኢማሙ ሙስሊም (61) አቡ ዘር፞ን (ረዺየላሁ ዐንሁ) በመጥቀስ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ማለታቸውን ዘግቦልናል፦

«وَمَنْ دَعَا رَجُلًا بِالْكُفْرِ "، أَوْ قَالَ : " عَدُوَّ اللهِ، وَلَيْسَ كَذَلِكَ إِلَّا حَارَ عَلَيْهِ».

«አንድን ግለሰብ በክህደት (ስያሜ) ወይም "አንተ የአላህ ጠላት" በማለት የተጣራ ሰው፤ ሰውየው እንደሚለው ካልሆነ ወደ ተጣሪው ይመለስበታል።»

④ኛ አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ "ኢዕዛርን" ወይም ሰዎችን ሳያስጠነቅቅ በፊት አለመቅጣትን መውደዱና ከቅጣትም ይልቅ ለእሱ ቅድሚያ መስጠቱን የሚያመላክቱ በርካታ መረጃዎች መኖራቸው ነው።

ኢማሙል ቡኻሪ (7416) እና ኢማሙ ሙስሊም (1499) ከሙጚረቱ ኢብኑ ሹዕባ (ረዺየላሁ ዐንሁማ) የተያዘን ቀጣዩን ሐዲሥ አስተላልፈውልናል፦

[قَالَ سَعْدُ بْنُ عُبَادَةَ : لَوْ رَأَيْتُ رَجُلًا مَعَ امْرَأَتِي لَضَرَبْتُهُ بِالسَّيْفِ، غَيْرُ مُصْفِحٍ عَنْهُ، فَبَلَغَ ذَلِكَ رَسُولَ اللهِ ﷺ، فَقَالَ: «أَتَعْجَبُونَ مِنْ غَيْرَةِ سَعْدٍ، فَوَاللهِ، لَأَنَا أَغْيَرُ مِنْهُ، وَاللهُ أَغْيَرُ مِنِّي، مِنْ أَجْلِ غَيْرَةِ اللهِ؛ حَرَّمَ الْفَوَاحِشَ مَا ظَهَرَ مِنْهَا، وَمَا بَطَنَ، وَلَا شَخْصَ أَغْيَرُ مِنَ اللهِ، وَلَا شَخْصَ أَحَبُّ إِلَيْهِ الْعُذْرُ مِنَ اللهِ، مِنْ أَجْلِ ذَلِكَ ؛ بَعَثَ اللهُ الْمُرْسَلِينَ مُبَشِّرِينَ وَمُنْذِرِينَ، وَلَا شَخْصَ أَحَبُّ إِلَيْهِ الْمِدْحَةُ مِنَ الله، مِنْ أَجْلِ ذَلِكَ ؛ وَعَدَ الله الْجَنَّةَ».]
----------------
#ወደ ገፅ -❹- ተሸጋገሩ።↩️

አል-በያን البــيان

05 Nov, 14:40


#ገፅ-➋- ክፉል - ❶➐-
--------------

«وقد أشار ابن القيم إلى هذا المعنى حيث بيَّن أنَّ الشارِع إنما قَبِلَ توبةَ الكافرِ الأصليِّ مِن كُفرهِ بالشهادتين، لأنه ظاهرٌ لا يُعارِضه ما هو أقوى منه؛ فوجب العمل به» . انظر: إعلام الموقعين، لابن القيم: (3/142).

• ኢብኑ ቀዪ፞ሚል ጀውዚያ፞ህ ዐለይሂ ረህመቱላህ "ኢዕላሙል ሙወቂዒን: (3/142) ላይ ይህን ሀሳብ የሚጠቁምን ንግግር በሚከተለው መልኩ ተናግሯል፦
(አንድ አስሊ ካፊር ሸሃደተይንን በማስገኘቱ ምክንያት ከኩፍሩ እንደቶበተ ተደርጎ አላህ ሱብሓሁ ወተዓላ ተውበቱን የተቀበለበት ምክንያት፦ ካስገኘው ሸሃደተይን የበለጠ ሌላ ተቃራኒ ግልፅ ነገር ስለሌለ ብቻ ነው፤ ከዚህም የተነሳ ተውበቱን መቀበልና በዚሁ መስራራት ግድ ሆኗል።)

▪️ፉቀሃዎች ይህን ቃዒዳ በቲዮሪ ደረጃ እንደተነተኑት ሁሉ፤ በእለት ከእለት ተግባራቸውም "ተጥቢይቅ" አድርገውታል።

👉 "በግልፅ በታየው ነገር ላይ አሕካምን መገንባት" የሚለውን አስል በተግባር ደረጃ ኢማሙ አሽ ሻፊዒ ይከተሉት የነበረውን አካሄድ አስተውለን ብንመለከት፦ አሕካሞች የሚገነቡበት ይህ ግልፅ ነገር ጥርት ያለ የሆነውን ግልፅ ብቻ መሆኑን እንረዳለን።
ለምሳሌ ይህል አሽ ሻፊዒ እንዲህ ይላሉ:

«وإن خطب جالِسًا، ولا يَدْرُون أصحيحٌ هو أو مريضٌ؟ فكان صحيحًا أجزأتهم صلاتهم، لأن الظاهر عندهم ألا يخطب إلا مريض، وإنما عليهم الإعادةُ إذا خطب جالسا، وهم يعلمون أنه صحيحٌ» (الأمُّ، للشافعي :1/343)

«ኹጥባ አድራጊው ተቀምጦ ኹጥባ ሲያደርግ ሰወየው ጤነኛ ይሁን ህመምተኛ የማያውቁ ሆነው (ካዳመጡ በኋላ ተከትለውት ቢሰግዱ)
ሰውየው ጤነኛነቱ ከሰገዱ በኋላ ቢረጋገጥም ሶላታቸው ታብቃቃቸዋለች፤ (ደግማችሁ ስገዱ አይባሉም)። ምክንያቱም እነሱ ዘንድ በዟሂር የሚታወቀው፦ ቁጭ ብሎ ኹጥባ የሚያደርገው የታመመ ሰው እንጂ ጤነኛ እንዳልሆነ ነው። ሶላታቸው የማታብቃቃቸውና ደግመው እንዲሰግዱ ግድ የሚሆንባቸው፦ ተቀምጦ ኹጥባ ሲያደርግ ጤነኛ መሆኑን እያወቁ ከሆነ ብቻ ነው።» (አል ኡም፞: 1/343)

• በድጋሚ ከሻፊዒይ ንግግር ሌላ ምሳሌ እንመልከት:


قال الإمام الشافعي رحمه الله: «ولو صلى رجلٌ غريبٌ بقومٍ ثم شكُّوا في صلاتهم فلَمْ يَدْرُوا أكان كافرًا أو مسلمًا لم تكن عليهم إعادة حتى يعلموا أنه كافرٌ؛ لأن الظاهر أن صلاتَه صلاةُ المسلمين لا تكون إلا من مسلمٍ» (الأم: 1/298)


«አንድ የማይታወቅ እንግዳ የሆነ ሰዎች ሰዎችን ኢማም ሆኖ ቢያሰግዳቸው፤ ከዚያም ይህ ያሰገዳቸው ሰውዬ ካፊር ይሁን ወይም ሙስሊም ባለማወቃቸው ምክንያት በሶላታቸው ቢጠራጠሩ፤ የሰውየውን ካፊርነት በገሃድ እስካላወቁ ድረስ ሶላታቸውን የመድገም ግዴታ የለባቸው፤ ምክንያቱም ከሰውየው በዟሂር የታየው ሶላት የሙስሊሞች ሶላት ነውና፤ ከሙስሊም እንጂ አይገኝም።» (አል ኡም፞: 1/298)


وانظر مزيدا من الأمثلة عند الشافعي: الضوابط والقواعد الفقهية في كتاب الأُمِّ للشافعي، عبد الوهاب الحميد (181 -185)

ይህ እንዲህ ከሆነ፤ በሌሎች ጉዳዮችም ያለው ሁኔታ እንዲሁ ነው። ማለትም፦ በአንድ ጉዳይ ላይ በዟሂር በታየው የሚተሓከመው ከእሱ ጋር የሚቃረን ሌላ ዟሂር እስከሌለ ድረስ ነው።

🤏 ከዚህ በመነሳት ወደ ዋናው ጉዳያችን እንመለስና፤ ትልቅ ሺርክ መስራት በገሃድ የታየበት አንድ ሰው፤ ዟሂሩ ከሶስት ሁኔታዎች አይወጣም።

① ሺርኩ ወደ ኢስላም ኢንቲሳብ የሌለውና በኢስላም የማያምን ከሆነ ሰው ሊገኝ ነው። ይህ አይነቱ ሰው ላይ ሌላ ተቀናቃኝ ዟሂር ስለሌለ ከእሱ በዟሂር በታየው በሺርኩ ነው የሚበየንበት።

② ምንነቱ ከማይታወቅ ሰው ሊገኝ ነው፤ ማለትም፦ ወደ ኢስላም ኢንቲሳብ ማድረጉም ሆነ አለማድረጉ በገሃድ የሚታወቅ ነገር የለም፤ ይህም ሰው እላዩ ላይ በገሃድ ከተገኘው ሺርክ ውጪ ሌላ ተቀናቃኝ ዟሂር ስለሌለ ከእሱ በዟሂር በታየው በሺርኩ ይበየንበታል።

③ ያ የሺርክ ተግባር እራሱን ወደ ኢስላም ኢንቲሳብ የሚያደርግ ከሆነ ሰው የተገኘ ሊሆን ነው፤ እንዲሁም በአላህ አንድነት ማመኑ፤ በኢስላም መሰረታዊ ጉዳዮች በጥቅል አማኝነቱና በመልእክተኛው ﷺ ላይም ልቅ የሆነ "ተስዲይቅ" በግልፅ የሚታይበት ከሆነ ሰው ሊገኝ ነው።

«ففي هذه الحال تعارَضَ عندنا ظاهِرانِ: ظاهِرٌ يُوجِبُ ثُبُوتَ الإسلام، وظاهِرٌ يوجبُ ثُبوت الكفر»

እዚህ ላይ ሁለት ግልፅ የሆኑ ነገሮች እርስበርስ ተጋጩብን፤ የኢስላም ስያሜ እንዲፀድቅለት ግድ የሚያደርግ ዟሂር እና የኩፍር ስያሜ እንዲፀድቅለት ግድ የሚያደርግ ዟሂር መሆቸው ናቸው።

«والقِسْمةُ العقليةُ تقتضي ثلاثةَ أحوال: إما أن يُقَدَّم الحالُ الذي يُثْبِتُ له وَصْفَ الإسلام، وإما أن يقدَّم الحالُ الذي يُثْبِتُ له وَصْفَ الكُفر، وإما أن يُتَوَقَّفَ؛ فلا يُحْكَمُ بإسلامه ولا بكفره»

በዚህ ጊዜ ሜንታል ዲቪዥን ወይም አእምሯዊ መከፋፈል የሚባለው ነገር ሶስት አይነት ሁኔታዎች እፊታችን እንዲጋረጡብን ያስፈርዳል።

¹ ወይ የኢስላምን ስያሜ የሚያፀድቀው ሁኔታ ሊቀደም ነው።

² ወይም የኩፍርን ስያሜ የሚያፀድቀው ሁኔታ ሊቀደም ነው።

³ ወይ ደግሞ "ተወቁ፞ፍ" ሊደረግ ነው። ማለትም በኢስላምም ይሁን በኩፍር ስያሜ ላይበየንበት ነው።

👌ከእነዚህ ሶስት ሁኔታዎች ተቀዳሚነት የሚሰጠው ትክክለኛና አመዛኝ የሆነው ነው፤ አመዛኙን ሁኔታ ለመምረጥ የምንመለሰውም ወደ ዐቅል ሳይሆን ወደ ሸሪዓዊ መረጃዎች ነው። መነሻ የምናደርገውም እሱኑ ነው።

ወደፊት እንደምናየው ሸሪዓዊ መረጃዎች ከሌሎቹ ሁኔታዎች ይልቅ የኢስላምን ስያሜ የሚያፀድቀውን ሁኔታ ማስቀደም ግዴታ እንደሚኖርብን በጠነከረና ግልፅ በሆነ መልኩ ይጠቁማሉ።
በመስአላው ሙሐቂቁን የሆኑ የአህሉስ ሱና ዑለማዎች አቋምም ይኸው ነው።

ይህን በተመለከተ አሽ ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ሷሊሕ አል ዑሠይሚን እንዲህ ይላሉ፦

[«فالأصلُ فيمن يَنتسِبُ للإسلام: بقاءُ إسلامِهِ حتى يتحقَّق زوالُ ذلك عنه بمقتضى الدليل الشرعي، ولا يجوز التساهل في تكفيره؛ لأن في ذلك مَحذُورَيْن عظيمين» وهما افتراء الكذب على الله وعلى المؤمنين، وعَوْدُ وصفِ الكفرِ على المتساهِل] .

[«በመሰረቱ አንድ ወደ ኢስላም የሚጠጋ ወይም ሐይማኖቴ ኢስላም ነው የሚል ግለሰብ ሐይማኖቱ ከእሱ መወገዱ ሸሪዓዊ መረጃዎች በሚያስፈርዱት እስኪረጋገጥ ድረስ ሙስሊምነቱ እንዳለ ነው።  ሰውየውን ማክፈርን አቅልሎ መመልከት አይፈቀድም፤ ምክንያቱም ሁለት ከባባድ አደጋዎች ስለሚከተሉ ነው።» እነሱም፦ በአላህ ላይና በአማኞች ላይ መቅጠፍ አለበት። እንዲሁም ሰዎችን ማክፈርን አቅልሎ የሚመለከተው ሰውዬ ላይ የክህደት ስያሜ ወደ ራሱ መመለሱ ነው።]

----------------------
#ወደ ገፅ -➌- ተሸጋገሩ።↩️

አል-በያን البــيان

05 Nov, 14:32


#ገፅ -❶ ክፍል - ❶➐
-----------------
*تمهّلْ يا حديثَ السِّنِّ!*

بسم الله الرحمن الرحيم

الحمد لله والصلاة والسلام على رسول الله وعلى آله ومن اتبع هداه، وبعد:

ወንድሞችና እህቶች!
ዛሬ ـ ኢንሻአላህ ـ ተክፊሪዮችና ድልድዮቻቸው ዑዝር ቢልጀህል የለም ለማለትና ሽርክ ላይ ባለማወቅ የወደቀን ሙስሊም ለማክፈር ወይም ከኢስላም ለማስወጣት ከሚደገፉባቸው መነሻዎች ሁለተኛውን ላስነብባችሁ ብቅ ብያለሁ!!

📚 ፅሁፉ በዐረብኛ ከተዘጋጀ ሰፋ ያለ ጥናታዊ ፅሁፍ የተወሰደ ስለሆነ በሰብር ይነበብ!!

የሰዎቹ መነሻ፦ "ሺርክ የሰራ ሰው (ጃሂልም ቢሆን) በዟሂር ከምናየው በመነሳት ሙሽሪክና ካፊር ነው ተብሎ ይተሐከምበታል" የሚለው ነው!!

يقولون: "لَنا ما ظَهَرَ، فكلُّ مَنْ وقع في الشرك فهو مشركٌ كافر!!"

ይህን ንግግር ተክፊሮችና እውስጣችን የበቀሉት ድልድዮቻቸው ደጋግመውና በሰፊው ሲያጦዙት የአንዳንድ ዑለማኦችን ንግግር አያይዘው ይጠቅሱ ይሆናል።

ሹብሃቸው ሰፋ ብሎ ሲተነተን ይህን ይመስላል፦ [በባሮች መካከል ብይን የሚኖረው ከእነሱ በግልፅ በሚታየው ብቻ ነው፤ አንድ ሰው ላይ ሺርክ ወይም ኩፍር በገሃድ ከታየ፦ በገሃድ ካየነው ስራው ጋር የሚስማማ የሆነን ፍርድ እንፈርድበታለን።]

• ዑዝር ቢል ጀህል የለም ለማለትና ለማክፍር ይህን መነሻ ከተጠቀሙ አካላቶች መካከል፦ ሑሰይን እና ዐብደላህ የተባሉት የሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲል ወሃብ ልጆች ይገኙበታል ። (ረሒመሁሙላሁ ጀሚይዓ)

*N.B* ተክፊሪዮችና ድልድዮቻቸው ሲባል የእውር ድንብር አረማመድ የሚራመዱትን የምታውቋቸውን እንጭጮች እንጂ፤ ለኢጅቲሃድ አህል ሆነው ከኢጅቲሃዳቸው በመነሳት አቋሙን የሚያራምዱትን እነኚህን ዑለማኦችና መሰለቾቻውን የማያካ፞ትት መሆኑን ለሙጘፈ፞ሎች ልገልፅ እወዳለሁ።

ሁለቱ ግለሰቦች (አዱረር አሰኒያ: 5/154) ላይ
እንዲህ የሚል ንግግር ተወስቶላቸዋል:
«ይህ የተውሒድ ደዕዋ ሳይደርሰው የሞተ ሰው የሚበየንበት ብይን (ምንድን ነው ከተባለ)፤ ሺርክ እየሰራና እያመነበት መሞቱ የሚታወቅ ሰው ከሆነ፤ ይህ በዟሂሩ ክህደት ላይ ሆኖ ሞቷል ነው የሚባለው፤ ዱዓም አይደረግለትም፤ አይሰገድበትም፤ ሰደቃም አይሰደቅለትም»

አንዳንድ በዚህ ዘመን ካሉ ግለሰቦችም ይህን አይነት ድምዳሜ በመያዝ: "የሽርክ ተግባር በገሃድ የታየበት ማንኛውም ሰው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ፦ ከኢስላም የወጣ ካፊር ነው!!" እስከ ማለት የደረሰ አለ።

• የተክፊሮችና ድልድዮቻቸው መንጠልጠያ ከሆኑት ኪታቦች መካከል (አልጀዋቡል ሙፊድ ፊ ሑክሚ ጃሂል አት ተውሒድ) የተሰኘው ኪታብ ገፅ 119 ላይ እንዲህ የሚል አለ:

«(አንድ ሰው ሺርክ በመስራቱ ብቻ ያለ ቅድመ ሁኔታ) "ኢብቲዳአን" በተዕዪን ወይም ተነጥሎ የሚከፈረው የዲን መሰረት በሆነው በተውሒድ ጉዳዮች ላይ ከሆነ ነው፤ ምክንያቱም ዱንያዊ ብይኖች የሚበየኑት በገሃድ ከታየው በመነሳት ብቻ ነውና፤ ስለዚህ ከኢስላም የሚያስወጣ የሆነውን ትልቁን ኩፍር የሰራ ሰው፦ በተዕዪን ካፊር ነው ይባላል፤ በግልፅ ካየነው ስራው በመነሳት ማለት ነው!!»

• ወንድሞች! አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ዱንያዊ ብይኖችን በተመለከተ ሰዎች ላይ ግድ ያደረገባቸው፦ በግልፅ በሚያዩት እንዲበይኑና በውስጥ የሚሰ፞ራ፞ውን ደግሞ ለእሱው እንዲተውት መሆኑ የማያጠራጥር ጉዳይ ነው። ይህ በኢስላማዊ ሸሪዓ የተረጋገጠ መሰረት ነው።

ሊደገፉበትና አጥብቀው ሊይዙት የሚገባ ጉዳይ መሆኑ በዑለማዎች መካከል የሚስማሙበት መሆኑን ኢማም አን ነወዊ፣ ኢብኑል ቀዪም፣ ኢብኑ ሐጀርና ሌሎችም በርካታ ዑለማኦች አውስተዋል።

• ኢማም አሽ ሻፊዒይ ከሌሎች ዑለማዎች ይልቅ ይህን ቃዒዳ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት፤ የተለያዩ መረጃዎችን በመጥቀስ ሸሪዓችን ውስጥ ያለውን ደረጃ፣ ከቃዒዳው የተፈለገበትንም እውነታና ወሰኖቹን ልዩ በሆነ ሁኔታ በመግለፅ ከሚታወቁ ቀደምት ኢማም ናቸው።

• (አል ኡም፞ 4/148) የተባለው ኪታባቸው ላይ እንዲህ ብለዋል:
«ብይኖች የሚበየኑት በዟሂር ወይም በግልፅ ከሚታየው በመነሳት ነው፤ በ"ጘይብ" ወይም በውስጥ ስላለውና የማናውቀው የሆነው ነገር ባለቤቱ አላህ ብቻ ነው።... »

(الأُمّ: 4/148) للإمام الشافعي عليه رحمة الله.


እዚህ ቃዒዳ ላይ ዟሂር ሲባል የተፈለገበት፦ ከአንድ ሰው በግልፅ የምናየው ወይም የምንሰማው፦ ንግግር፣ ወይም ተግባር፤ ወይም ደግሞ ያመነበት ነገር፣ ወይም አስረጅና ምስክር የቆመበት ነገር ነው።

ይህን በተመለከተ ኢማም አሽ ሻፊዒ እንዲህ ይላሉ፦

«وأحكامُ الله ورسولهِ تدلُّ على أن ليس لأحدٍ أن يحكم على أحدٍ إلا بالظاهر، والظاهرُ:  ما أقر به أو ما قامت به بينةٌ تثبت عليه» (كتاب الأم:1/433)

ويقول أيضا: «والحكم بالظاهر من القول أو البينة أو الاعتراف أو الحجة» (المرجع السابق: 5/187)


«የአላህና የመልእክተኛው አሕካሞች ማንም ሰው በማንኛውም ሰው ላይ በዟሂር በታየው እንጂ የመፍረድ መብት እንደሌለው ይጠቁማሉ። ዟሂር ደግሞ፦ ሰውየው (ስራውን የሰራው መሆኑን) ያመነበት፣ ወይም መስራቱን የሚያረጋግጥ አስረጅ የቀረበበት ነው።» (አል ኡም፞: 1/433)

እንዲህም ብለዋል: «ፍርድ የሚፈረደው በግልፅ ከተገኘው ንግግሩ፣ ወይም በምስክር፣ ወይም በማመኑ፣ ወይም ማስረጃ በመቅረቡ ነው» (አል ኡም፞: 5/187)

▪️ይህ ቃዒዳ ትክክል መሆኑን የሚጠቁሙ በርካታ መረጃዎችም አሉ። ለምሳሌ ያህል፦

• ቁርኣን ውሸታምነታቸውን የገለፀ ከመሆኑ ጋር ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሙናፊቆችን ከእነሱ በግልፅ በሚያዩት ነገር ሙዓመላ ማድረጋቸውና ኢስላማዊ አሕካሞችን ለእነሱ መስጠታቸው ነው።

• እንዲሁም ኡሳመቱ ኢብኑ ዘይድ የተባለው ሰሓቢይ ከሙሽሪኩ ሰውዬ ጋር ጂሃድ ላይ እያሉ የተከሰተውን ክስተት የሚያወራውም ሰሒሕ የሆነ ቂሷ እንደ ምሳሌ ይጠቀሳል።

👌 ይህ ቃዒዳ የተረጋገጠና የፀና ቢሆንም፤ በሺርካዊ ጉዳዮች ዑዝር ቢልጀህል የለም ለሚለው አቋም መደገፊያ ማድረግ ግን ስህተት ነው፤ ትክክል አይደለም!!

*የስህተትነቱ መነሻም ከቃዒዳው የተፈለገውን ሙሉ ሀሳብ ጠለቅ ያለ መገንዘብን ካለመገንዘብ የመነጨ ነው።*

«لأنَّ المقصود بالظاهر الذي في القاعدة إنما هو الظاهرُ المتمحِّضُ الذي لا يُعارِضُهُ ظاهرٌ آخرُ، فإن عارضَه ما هو أقوى منه فإنه يؤخذ بالظاهر الأَقْوى؛ ولهذا قال بعضُ الحنفية: «البِناءُ على الظاهر واجٌبٌ ما لم يَثْبُتْ خِلافُهُ» (انظر "قواعد الفقه" للمجددي، ص:65)، و"ترتيب اللآلي في سلك المالي"، ناظر زادة: 863)

ምክንያቱም እዚህ ቦታ ላይ "ዟሂር" ወይም ግልፅ ሲባል የተፈለገበት፦ ሌላ ዟሂር የማይቃረነው ጥር፞ት ያለ (ሷፊ) ዟሂር ነው። በግልፅነት ከእሱ የበለጠ ሌላ ግልፅ ተቀናቃኝ ከተገኘ፤ በግልፅነት በላጭ የሆነው ነው ተቀዳሚነት የሚኖረው። የሐነፊ መዝሀብ አራማጅ ከሆኑት አንዱ: «ዟሂርን መሰረት አድርጎ ብይንን መበየን ዋጂብ ነው፤ ከእሱ ተቃራኒ እስካልተገኘ ድረስ» ያለውም ለዚሁ ነው።
-----------------
#ወደ ገፅ -➋- ይሸጋገሩ።↩️

አል-በያን البــيان

26 Oct, 18:17


🔶ነገ ኮቻ በሰለፍዮች ትደምቃለች🔷

🔴ልዩ የዳዕዋ እና የዚያራ ፕሮግራም🟣

🟤ደሴና በዙሪያዋ ያላችሁ  ሰለፍዮች  2:00 ሰዐት በውቢቷ ከተማ ኮምቦልቻ እንገናኝ

ከጠዋቱ 3:00 ሰአት ፕሮግራሙ ይጀምራል

እሁድ ጥቅምት 17/02/2017

ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም ይደረጋል።

🌳 ሁሉም ሰው ተገኝቶ እንዲሳተፍ
ከወዲሁ ጥሪያችን እናስተላልፋለን‼️

🌔መገኘት የምትችሉ 💧
⚡️
    ⚡️
        ⚡️
            ⚡️
                ⚡️
                    ⚡️ሩ!!!

🛜ቀጥታ ስርጭት ይኖረናል🛜
 
🔄 Play ▶️ ──◉ 03:00 AM

🟢=∞======🟢=∞=====🟢

📲 አጠቃላይ ፕሮግራሞቻችን በሶሻል
ሚዲያ ለመከታተል:

🗞️ በ Telegram~Channel 👇
🌐
https://t.me/Hudhud_Studio

🟢ይህ የሰለፍዮች ልሳን የሆነው
"ሁድሁድ ስቱድዮ"
            ነው

🔖ሃሳብ አስታየት ካሎት⤵️
🎥t.me/Hud_hud_studio_Bot

👇👇
👍♡ㅤ ❍      👇 ⎙  👉 ⌲ 
ˡᶦᵏᵉ      ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ      ˢᵃᵛᵉ      ˢʰᵃʳᵉ

አል-በያን البــيان

24 Oct, 11:24


#ገፅ -❹- ክፍል -❶❻-
-------------

وإني أقرِّر أن الله قد غفر لهذه الأمة خطأها ، وذلك يعمُّ الخطأ في المسائل الخَبَرية القولية والمسائل العملية .
وما زال السلفُ يتنازعون في كثيرٍ من هذه المسائل ، ولم يشهد أحد منهم على أحدٍ لا بكفرٍ ولا بفسق ولا بمعصية .

• ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ዐለይሂ ረህመቱላህ እንዲህ ብሏል:

[እኔ ሁልጊዜ አንድን ሰው በተዕዪን ለይቶ ወደ ኩፍር፣ ወደ ፊስቅ እና መዕሲያ ማስጠጋትን በጣም አድርገው ከሚቃወሙ ሰዎች የምመደብ ነኝ፤ ይህን እኔን የሚያቀማምጡ ሰዎችም ያውቃሉ!! ነገር ግን የተቃረናት ሰው እንደ ሁኔታው አንዳንዴ ካፊር፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ፋሲቅ ወይም ወንጀለኛ የሚሆንባት ነቢያዊ ሑጃ ሰውዬው ላይ በእርግጥ መቆሙ ከታ፞ወቀ በቀር (ከዚህ ውጭ ሑጃ ሳይቆምበት ካፊር፣ ፋሲቅና ዓሲ እያ፞ሉ መበየንን አጥብቀው ከሚያወግዙ ዑለማዎች ነኝ)።
አሁንም እኔ ለዚህ ህዝበ ሙስሊም አላህ ስህተታቸውን በእርግጥ ምሯቸዋል በማለት ደጋግሜና አስረግጬ እናገራለሁ!! ስህተቱ ደግሞ ዐቂዳዊም ሆነ አሕካማዊ ጉዳዮችን ያጠቃልላል። ሰለፎች በበርካታ መሳኢሎች ከመለያየታቸውም ጋር ከውስጣቸው አንዱ በሌላው ላይ በኩፍር ወይም በፊስቅ ወይም ደግሞ በወንጀል ይሐክሙ አልነበረም]


إلى أن قال : (وكنتُ أبيِّنُ أنَّ ما نُقِلَ عن السلف والأئمة مِن إطلاق القول بتكفير مَن يقول كذا وكذا فهو أيضا حقٌّ؛ لكن يجب التفريقُ بين الإطلاق والتعيين).

• ሸይኸል ኢስላም ቀጥለው እንዲህ አሉ:

[ከሰለፎችና ከአኢማ፞ዎች "ይህን፣ ይህን መሰ፞ል ንግግር የተናገረ ይከፍራል" እያሉ በኢጥላቅ (በልቅ፞) ተናግረውት ወደኛ የደረሰን ንግግራቸው ሐቅ መሆኑን እገልፅ ነበር፤ ነገር ግን በጥቅል የሚሰ፞ጠ፞ውንና በተዕዪን (በተናጠል) የሚተ፞ሓከ፞መውን ብይን መለየት ግድ፞ ነው]
.
.

إلى أن قال : (والتكفيرُ هو من الوعيد ؛ فإنه وإن كان القولُ تكذيبًا لِما قاله الرسولُ صلى الله عليه وسلم لكنَّ الرجل قد يكون حديثَ عهدٍ بإسلام، أو نشأ ببادية بعيدة ، ومِثْلُ هذا لا يُكَفَّر بِجَحْدِ ما يَجْحَدُه حتى تقومَ عليه الحجةُ، وقد يكون الرجلُ لم يسمعْ تلك النصوصَ ، أو سمعها ولم تَثْبُتْ عنده ، أو عَارَضَها عنده معارضٌ آخر أوجبَ تأويلها وإن كان مخطئا) اهـ.

• ሸይኹል ኢስላም አሁንም ቀጠሉ:

[ተክፊይር (ሰውን ከኢስላም ማስወጣት) ከወዒይድ (ዛቻዊ) ነጥቦች ነው፤ አንድ ንግግር መልእክተኛው ﷺ ከተናገሩት ንግግር ጋር የሚቃረን ቢሆንም ተናጋሪው ሰውዬ ግን አዲስ ሰለምቴ ሊሆን ይችላል፤ ወይም ራቅ ያለ ገጠራማ ስፍራ ሊኖር ይችላል፤ ይህን የመሳሰለ ሰው በሚክደው ክህደት ሑጃ እስካልቆመበት ድረስ አይከ፞ፈ፞ርም፤ እንዲሁም ይህ ሰው መረጃዎቹን አልሰማቸው ይሆናል፤ ወይም ሰምቷቸው ነገር ግን እሱ ዘንድ አልሠበቱለት (አልተረጋገጡለት) ይሆናል፤ ወይም መረጃዎቹን የሚቃረንበትና ተእዊል የሚያደርግበት የሆነ (ሹብሃ) እሱ ዘንድ ይኖረው ይሆናል፤ ሰውየው (በትክክለኛ እይታ) ስህተተኛ ቢሆንም።]

(አል ፈታዋ: 3/229 ـ መጅሙዕ ኢብኑ ቃሲም)

مــــــــــــنـــــــــــقــــــــــول.

💠💠

🖌አቡ ዐብዲላህ ሰዒድ (አስ ሰለፊ)

🗓21/12/1443هـ

-------------------💎----------------------

ثَبَّتَهُ اللهُ عَلَى الإسْلَامِ والسُّنَّة، وأثَابهُ ثَوَابَ الدُّنْيا والْآخِرة، وَجَعَلَ جُهْدَهُ الْمُقِلَّ في مِيزانِ حَسناتهِ.
📋 ------------------⬇️⬇️

قلت ( أبو ريان ) جزاك الله خيرا يا أخانا أبا عبد الله قد ألقمتهم حجرا ، لله درك، أسأل الله أن يبارك فيك وفي جهودك الطيبة.

------------
⬇️⬇️በሌላ ርዕስ እንገናኝ@

🔗
https://t.me/al_beyann/1276
🔗
https://t.me/al_beyann/1276
---------
📋
#ይቀጥላል...

አል-በያን البــيان

24 Oct, 11:20


#ገፅ -➌- ክፍል-❶❻-

▪️እንዲሁም ታላቁ የቁርኣን ሙፈሲር ኢማም ኢብኑ ጀሪር አጦ፞በሪ ቀጣዩን አንቀፅ እንዲህ በማለት ይተነትናል፦

{وَاذْكُرُوا نِعْمَتَ اللهِ عَلَيْكُمْ إِذْ كُنتُمْ أَعْدَاءً فَأَلَّفَ بَيْنَ قُلُوبِكُمْ فَأَصْبَحْتُم بِنِعْمَتِهِ إِخْوَانًا وَكُنتُمْ عَلَىٰ شَفَا حُفْرَةٍ مِّنَ النَّارِ فَأَنقَذَكُم مِّنْهَا ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللهُ لَكُمْ آيَاتِهِ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ} (آل عمران: ١٠٣)

{ጠበኞችም በነበራችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ (የዋለውን) የአላህን ጸጋ አስታውሱ፡፡ በልቦቻችሁም መካከል አስማማ፡፡ በጸጋውም ወንድማማቾች ኾናችሁ፡፡ በእሳት ጉድጓድ አፋፍም ላይ ነበራችሁ፡፡ ከእርስዋም አዳናችሁ፡፡ እንደዚሁ ትመሩ ዘንድ አላህ ለእናንተ አንቀጾቹን ያብራራል፡፡} (ኣል ዒምራን: 103)

[...እዚህ ላይ አውስና ኸዝረጅን አላህ ወደ ኢስላም ሳይመራቸው በፊት የነበሩበትን የኩፍር ምሳሌ መግለፁ ነው፤ አላህም ﷻ እንዲህ አላቸው: "በእሱ ምክንያት ወንድማማቾች የሆናችሁበትን የኢስላምን ፀጋ በእናንተ ላይ ሳይውልላችሁ በፊት በነበራችሁበት ኩፍር ምክንያት ጀሀነም አፋፍ ላይ ነበራችሁ፤ በእናንተና ጀሀነም በመግባታችሁ መካከልም ያላችሁበት ኩፍር ላይ ሆናችሁ መሞት እንጂ ምንም ነገር አልነበረም፤ ይህ ቢሆን ኖሮ ደግሞ ዘላለም በውስጧ ትኖሩ ነበር፤ ነገር ግን አላህ ﷻ ወደ ኢማን ስለመራችሁ በእሱ ምክንያት አዳናችሁ"።]


▪️ወኹላሰቱል ከላም፦ በኢስላማዊ ሸሪዓ በጥቅል አማኝ ሆኖ በጀህል ምክንያት ሺርክ ውስጥ የሚወድቅን ሰው፤ ጭራሽ መሰረታቸው ኩፍርና ሺርክ ከሆነባቸው ኩፋሩ ቁረይሽ ጋር አንድ አይነት ብይን መስጠት ይህ ትክክል አይደለም፤ "አልዒብረቱ ቢዑሙሚለ፞ፍዝ ላ ቢኹሱውሲስሰበብ" የሚለውን ቃዒዳ በመያዝ፤ ለኩፋሩ ቁረይሽ የመጡ አናቅፆችን አስላቸው ሙስሊም ለሆኑ አካላት ማውረድና እነሱን ማክፈርም፤ ከእውነታ የራቀ ከመሆኑም በላይ ከባድ ዙልም ነው።

▪️ታዋቂው #የነጅዱ ዓሊም፣ አልዐላ፞መቱ፣ አል ኡሱውሊይ፣ አል ፈቂይህ፣ አል ሙፈሲር፣ አሽ ሸይኽ ዐብደረሕማን አስ ሰዕዲ ረሕመቱላሂ ዐለይህ እንዲህ ይላል፦

«فكلُّ مَن كان مُؤمِنًا بالله ورسوله ، مُصَدِّقًا لهما، مُلتزِمًا طاعتَهما، وأنكر بعضَ ما جاء به الرسول، جهلًا، أو عَدَمَ علمٍ أن الرسول جاء به: فإنه وإن كان ذلك كُفْرًا، ومَن فَعَلَهُ فهو كافرٌ، إلا أنَّ الجهلَ بما جاء به الرسولُ يَمنعُ مِن تكفير ذلك الشخصِ المعيَّنِ، مِن غير فرقٍ بين المسائل الأصولية والفرعية، لأن الكفر جَحْدُ ما جاء به الرسول أو جحدُ بعضِه مع العلم بذلك.
وبهذا عَرفتَ الفرقَ بين المقلِّدين من الكفار بالرسول، وبين المؤمن الجاحد لبعض ما جاء به جهلاً وضلالًا، لا عِلمًا وعِنادًا»
"الفتاوى السعدية" (ص: 443-447).

👆👆👆👇🏻👇🏻👇🏻

«በአላህና በመልእክተኛው አማኝ የሆነና፤ ትእዛዛቸውንም አጥብቆ የያዘ ማንኛውም ሰው፤ በጀህል ወይም ባለማወቅ ምክንያት መልእክተኛው ይዘው የመጡትን ከፊሉን ቢቃወም፤ ይህ ተግባር ኩፍር ነው፤ ሰውየውም ካፊር ነው ተብሎ በኢጥላቅ ቢበየንበትም፤ መልእክተኛው ያመጡትን ነገር አለማወቁ ሰውየውን በተዕዪን ነጥለን ከማክፈር ይከለክለናል። ይህም መሰረታዊ የዲኑን ክፍሎችና መሰረታዊ ያልሆኑትን ባለመለያየት ነው። ምክንያቱም ኩፍር የሚኖረው መልእክተኛው ይዘው የመጡትን ሁሉንም ወይም ከፊሉን እያወቀ ሲክድ ነው፤
ይህ እንግዲህ በመሰረታቸው ጥርት ያሉ በረሱል ከሃዲ በሆኑ ጭፍን ተከታዮች መካከልና ሙእሚን ሆኖ እያወቀና በእምቢተኝነት ሳይሆን፤ ተሳስቶና ሳያውቅ ረሱል የመጡበትን ከፊሉን በሚክድ ሰው መካከል ያለ፞ውን ልዩነት ትገነዘባለህ ማለት ነው።»
"አል ፈታዋ አስ ሰዕዲያ" : (443 _ 447)


• ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ እንዲህ ይላል፦

قال شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله تعالى:
"فهذه المقالات هي كُفْرٌ لكنَّ ثُبُوتَ التكفير في حقِّ الشخص المُعيَّن موقوفٌ على قيام الحجةِ التي يَكْفُرُ تارِكُها"
( بغية المرتاد، ص :353).

• «...እነዚህ ንግግሮች ኩፍር ናቸው፤ አንድን ሰው ነጥሎ እሱን ለማክፈር ግን እንቢ የሚላት ሰው የሚከ፞ፈ፞ርባት የሆነችዋ ሑጃ በመድረሱ ላይ ያጠ፞ረ ወይም የተንጠለጠለ ነው።»
(ቡጝየቱል ሙርታድ: 353)

• وقال: "وليس لأحدٍ أنْ يُكَفِّرَ أحدًا مِن المسلمين وإنْ أخطأ وغَلِطَ حتى تُقَام عليه الحجَّةُ وتُبَيَّنَ له المَحجَّةُ، ومَنْ ثَبَتَ إِسْلامُهُ بيقينٍ لم يَزُلْ ذلك عنه بالشَّكّ، بلْ لا يزول إلَّا بعد إقامةِ الحُجَّة وإزالةِ الشُّبْهة".
مجموع الفتاوى (12/466).

«ከሙስሊሞች የሆነ ማንኛውም ሙስሊም ቢያጠፋም ቢሳሳትም ሑጃ እስከሚደርሰውና ቅኑ መንገድ እስኪገለፅለት ድረስ ለማንም አካል ይህን ሰው ማክፈር አይፈቀድለትም። ሙስሊምነቱ በየቂን የተረጋገጠለት ሰው፤ በጥርጥር ሙስሊምነቱን አይነጠቅም፤ ይልቁንም ሑጃ እስከሚደርሰውና ሹብሃው እስኪወገድለት ድረስ ሙስሊምነቱን አይቀማም!!»
(መጅሙዑል ፈታዋ 12/466)

• وقال ابنُ تيمية رحمه الله : "التَّكْفِيرُ لَهُ شُرُوطٌ وَمَوَانِعُ قَدْ تَنْتَفي فِي حَقِّ الْمُعَيَّنِ، وَأَنَّ تَكْفِيرَ الْمُطْلَقِ لَا يَسْتَلْزِمُ تَكْفِيرَ الْمُعَيَّنِ إلَّا إذَا وُجِدَتْ الشُّرُوطُ وَانْتَفَتْ الْمَوَانِعُ" [مجموع الفتاوى (12/487-488)].

• እንዲህም ብሏል፦ «ሰውን ለማክፈር የራሱ የሆነ መስፈርቶችና ከልካይ ነገሮች አሉት፤ (ይህን፣ይህን የተናገረ ወይም የሰራ ካፈር ነው) እየተባለ በልቅ ሰዎችን ማክፈር፤ አንድን ሰው ነጥሎ ማክፈርን አያስይዝም (አያስፈርድም)፤
ነገር ግን (ኩፍር ላይ የወደቀ አካል ላይ) መስፈርቶች ከተሟሉና ለማክፈር የሚከለክሉ ምክንያቶች ከተወገዱ ካፊር ይደረጋል።»
(መጅሙዑል ፈታዋ: 12/ 487: 488)

• وقال ابن تيمية رحمه الله كما في الفتاوى مجموع ابن قاسم (3/229):

[ ...إني دائمًا ومَنْ جالسني يعلم ذلك مِنِّي، أنِّي مِن أَعْظَمِ الناسِ نَهْياً عن أنْ يُنْسَبَ مُعَيَّنٌ إلى تكفيرٍ وتفسيقٍ ومعصية، إلا إذا عُلِمَ أنه قد قامتْ عليه الحُجَّةُ الرِّساليَّة التي مَن خالَفَها كان كافراً تارة ، وفاسقاً أُخرى ، وعاصياً أخرى ،

-------------
#ወደ ገፅ -❹- ይሸጋገሩ።↩️

አል-በያን البــيان

24 Oct, 11:16


ገፅ -➋- ክፍል ❶❻

«فهذا رجلٌ شكَّ في قُدرةِ الله وفي إعادته إذا ذُرِّيَ، بل اعتقد أنه لا يُعاد، وهذا كُفْرٌ باتِّفاق المسلمين، لكن كان جاهِلاً لا يَعْلَمُ ذلك، وكان مُؤمِناً يَخاف الله أن يُعاقِبه، فَغَفَرَ له بذلك».

• ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ አላህ ይዘንለትና ሐዲሡን ሲተነትን እንዲህ ይላል፦

«ይህ በአላህ ችሎታ የተጠራጠረ ሰው ነው፤ ፈጭተው ከበተኑት አላህ ወደ ነበረበት ሊመልሰው የማይችል መሆኑንም አምኗል፤ ይህም (ተግባር) ኩፍር ለመሆኑ ሙስሊሞች ይስማማሉ፤ ነገር ግን ሰውየው ይህን የማያውቅ ጃሂል ነበር፤ የአላህን ቅጣት የሚፈራ ሙእሚን ወይም አማኝም ነበር፤ አላሁ ﷻ በዚሁ ምክንያት ማረው።» (መጅሙዑል ፈታዋ: 3/231)


▪️وقال أيضا كما في كتابه ( *الاستقامة* 1/164) : «فهذا الرجل اعتقد أن الله لا يَقْدِرُ على جَمْعِه إذا فعل ذلك أو شكَّ، وأنه لا يَبْعَثُه، وكُلٌّ مِن هَٰذَين الاعتقادَين كُفْرٌ يَكْفُرُ مَن قامتْ عليه الحُجَّةُ، لكنَّه كان يَجْهَلُ ذلك، ولم يَبْلُغْه العِلْمُ بما يَرُدُّه عن جَهْلِه، وكان عنده إيمانٌ بالله وبأمره ونهيِهِ وَوَعْدِهِ وَوَعِيدِه، فخافَ مِن عقابه، فغفر الله له بخشيته»

• በድጋሚ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ (አል ኢስቲቃማ: 1/164) የተሰኘው ኪታቡ ላይ እንዲህ ብሏል፦
«ሰውዬው ይህን ካደረገ አላህ እሱን (ከተበተነበት) *መሰብሰብ እንደማይችል* እና *እንደማይቀሰቀስም* እርግጠኛ ሆኖ አምኗል፤ ወይም ሊሰበስበው ቻይ መሆኑን ተጠራጥሯል፤ እነኚህ ሁለት እምነቶች እያንዳንዳቸው ኩፍር (ክህደት) ስለሆኑ ሑጃ የቆመበት ሰው ይከፍርባቸዋል። ነገር ግን እሱ ጃሂል ነበር፤ ከጅህልናው ሊያቅበው የሚችል እውቀትም አልደረሰውም፤ በአላህ፣ በትእዛዛቱ፣ በክልከላዎቹ፣ ቃል በገባባቸውና በዛተባቸውም ነገሮች አማኝ ነበር፤ ከዚህም የተነሳ የአላህን ቅጣት ፈራ፞፤ አላህም ለእሱ ባለው ፍርሃት ምክንያት ምህረትን ለገሰው።»

👈🏻 الشاهد من ذلك ـ بارك الله فينا وفيكم ـ

👇

👌🏻በጀህል ምክንያት ኩፍር ውስጥ ወድቆ የነበረው ይህ "ኢስራኢይሊይ" በስተመጨረሻ አላህ ለእሱ ምህረት ማድረጉ ነው።

*በኣኺራ ምህረትን የሚጎናፀፍ አካል ደግሞ በዱንያ ሙስሊም የነበረ ሰው ነው።* ይህ ሰው በኣኺራ የአላህን ﷻ
ምህረት በማግኘት የጀነት ባለቤት መሆኑና ዱንያ ላይ በኩፍር ስያሜ ካፊር ተብሎ መሰየሙ፤ እነዚህ ሁለት ብይኖች እሱ ላይ ሊሰባሰቡበት አይችሉም።

▪️የኣኺራዊ ብይን መለ፞ያየት፦ የዱንያዊ ብይኖች መለያየታቸውን ከሚጠቁሙ በጣም ግልፅ ከሆኑ ማስረጃዎች የሚመደብ ነው።

ይህ ማለት፦ *በኣኺራ ጀነት አይገባም፦ በዱንያ ሙስሊም የነበረ ሰው ቢሆን እንጂ!!*

በተጨማሪም ይህ ሰውዬ አማኝ ሆኖ አንድ ኩፍር የሆነ ተግባር ላይ ቢወድቅም፤ በኣኺራ እንደ አህሉል ፈትራ ሰዎች ሳይፈ፞ተ፞ን፤ በጅህልናው ምክንያት ምህረት ተደርጎለታል።

▪️انظر كتاب: إشكالية الإعذار بالجهل في البحث العقدي للعميري (ص: ٨٨ ـ ٩٦).

②ኛ ተክፊሪዮችና ድልድዮቻቸው የሚሞግቱት አጉል ሙግት ማለትም "በሺርክ የተሰየሙ የጃሂሊያ ዘመን ሰዎች ሁሉ ሑጃ ያልደረሳቸውና የአህሉል ፈትራ ብይን የሚሰጣቸው ናቸው" የሚለው አባባላቸው፦ ትክክል አይደለም፤ ይልቁንም ኢማም አን ـ ነወዊና ሌሎችም እንደሚሉት፦ እነኚህ ሰዎች: በዘመነል ፈትራ ውስጥ በመኖራቸው ምክንያት ምንም አይነት ሑጃ ያልደረሳቸው ሆነው በኣኺራ እንደሚፈተኑት ሰዎች አይነት እንዳልሆኑና ሑጃ የደረሳቸው መሆናቸውን ገልፀዋል።

▪️انظر شرح صحيح مسلم للإمام النووي تحت حديث (203): «إن أبي وأباك في النار».

وسيأتي كلامُه قريبًا مترجَمًا إن شاء الله.

🤏 ለዚህም ብዙ አመላካች ነገሮች አሉ። ከእነዚህም መካከል፦

•¹• ሑጃ ማቆም ወይም ማድረስ የሚባለው ጉዳይ የአላህ መልእክተኛ ብቻ እንጂ ሌላ አካል ሊወ፞ጣ፞ው የማይችል ሀላፊነት አይደለም፤ ይልቁንም የመልእክተኛውን ተልእኮ ይፋ ማድረግ የሚችል ማንኛውም ግለሰብ ከተገኘ ሑጃውን ለማድረስ በቂ ነው።

በዚህ ዙሪያ ኢማም አሽ ـ ሸውካኒ ሱረቱል ቀሰስ አንቀፅ ቁጥር (47) ላይ ያስቀመጠውን ትንታኔ ተመልከት። (ፈትሑል ቀዲይር)

•²• በዚያ ጃሂሊይ በሆነ ዘመን *ዘይድ ኢብኑ ዐምር ኢብኑ ኑፈይል* እና የመሳሰሉ አላህን ﷻ በብቸኝነት የሚያመልኩና በእሱም የማያሻርኩ መልካም የአላህ ባሮች ነበሩ።

• (ኢማሙል ቡኻሪ: 3826) እና (ኢማም አሕመድ: 5369) ኢብኑ ዑመርን በመጥቀስ ያስተላለፉት ሐዲሥ ላይ እንዲህ የሚል አለ፦
«ነቢዩ ﷺ ወሕይ ሳይወርድላቸው በስተፊት ዘይድ ኢብኑ ዐምር ኢብኑ ኑፈይልን ታችኛው "በልደሕ" የሚባል አካባቢ አገኙት፤ ያን ጊዜ ለነቢዩ ﷺ ስጋ ያለበት የምግብ ማእድ ተቀረበላቸው፤ እሳቸውም መብላትን እንቢ አሉ፤ እሳቸውም ለዘይድ አቀረቡለት፤ ዘይድም እንቢ አልበላም በማለት ቀጥሎ እንዲህ አለ: "እኔኮ እናንተ ለጣኦቶቻችሁ ከምታርዱላቸው ምግብ አልመገብም፤ እኔ የምመገበው የአላህ ስም ብቻ ተወስቶ የታረደን ምግብ ነው።»

• እንዲሁም ኢማሙል ቡኻሪ (3827) በዘገቡት ሐዲሥ ላይ አስማእ ቢንት አቢ በክር ረዲየላሁ ዐንሁማ እንዲህ ብላለች፦
«ዘይድ ኢብኑ ዐምርን ጀርባውን ከዕባ ላይ በማስደገፍ የቆመ ሆኖ ቁረይሾችን: (እናንተ ሰዎች ሆይ! በአላህ ﷻ ይሁንብኝ
ከእኔ ሌላ እናንተ መካከል በኢብራሂም ዐለይሂሰላም ሐይማኖት ላይ ያለ፞ ማንም ሰው የለም)።» ይል እንደነበር አስተላልፋለች።

•³• ኢማም ሙስሊም (203) ላይ እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ ﷺ ለሰሓቢዩ: «የእኔም የአንተም አባቶች የእሳት ናቸው» ማለታቸው።

•⁴• በድጋሚ ኢማም ሙስሊም (976) ላይ እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ ﷺ: «ለእናቴ ኢስተጝፋር እንድጠይቅላት አላህን ፈቃድ ብጠይቀውም አልፈቀደልኝም፤ ቀብሯን እንድዘይርም አስፈቀድኩት፤ እሱም ፈቀደልኝ።» ማለታቸው።

ይህ ማለት የረሱል ﷺ ወላጆች የእሳት ናቸው ማለት ነው። አህሉል ጃሂሊያዎችም በኣኺራ ይፈተናሉ የሚባልላቸው አይደሉም ማለት ነው። ምክንያቱም አላህ ﷻ ሑጃን ሳያቆም አይቀጣምና።
አህሉል ፈትራዎችም በኣኺራ እንደሚፈተኑ መረጃዎች መጥተዋል፤ ስለዚህ በዚያ ዘመን ይኖሩ የነበሩት የነቢዩ ﷺ ቤተሰቦችና መሰሎቻቸው የእሳት መሆናቸው በረሱል አንደበት መነገሩ፦ እነዚህ ሰዎች በዱንያ ሑጃ የደረሳቸው መሆናቸውንና በኣኺራ የማይፈተኑ መሆናቸውን ይጠቁማል!!

• ኢማም አን ـ ነወዊ "አባቴም አባትህም የእሳት ናቸው" የሚለውን የረሱልን ﷺ ንግግር ሲያብራሩ እንዲህ ብለዋል፦ «በዘመነል ፈትራ ወይም ነቢይ በሌለበት ዘመን ዐረቦች በነበሩበት የጣኦት አምልኮ ላይ ሆኖ የሞተ ሰው በኣኺራ የእሳት ነው፤ ይህ ሲባል የነቢያት ደዕዋ ወይም ሑጃ ሳይደርሳቸው እነሱን ተጠያቂ ማድረግና ተቀጭ ናቸው ማለት አይደለም፤ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች (የተቀጡትና ተጠያቂ የተደረጉት) የነቢዩላህ ኢብራሂምና የሌሎች ነቢያት ደዕዋ በእርግጥ ስለደረሳቸው ነው።)

#ወደ ገፅ -➌- ተሸጋገሩ።↩️

አል-በያን البــيان

24 Oct, 10:59


#ገፅ -❶-

📢 *مهلًا يا حُدثاء الأسنان* !!

بـســــم الله الرحمن الرحيـم
الحمد لله والصلاة والسلام على رسول الله وعلى آله وصحبه ومن والاه، وبعد:

🔖የተክፊሪዮች ሹበሀ እና ማደናገሪያ
📚📚

#ክፍል❶❻


📋ሙስሊም ወንድሜ ሆይ! ዛሬ አንድን የተክፊሮችንና ሰለፊዮች ውስጥ የበቀሉት ድልድዮቻቸውን ሹብሃ በአላህ ፈቃድ ለመግለፅ እሞክራለሁ። ስለዚህ ቢረዝምም ትእግስት ኖሮህ አንብብ፤ ተጠቀም፤ ለሌሎችም አጋራው።

🔖እሱም፦ እነዚህ አካላት በተለያየ ምክንያት አንዳንድ የሽርክ ተግባራት ላይ የወደቁ የዘመናችን ሙስሊም የሆኑ ማህበረሰቦችንና በጃሂሊያ ዘመን ይኖሩ የነበሩ ሙሽሪኮችን አንድ አድርገው ማየታቸውና አለመለያየታቸው ነው።

"ሑደሣኡል አስናን" የሆኑ ተክፊይሪዮችና ድልድዮቻቸው:
«ከቁርኣን መውረድና ከረሱል መልላክ በፊት ይኖሩ የነበሩ ዐረቦች ሑጃ ሳይደርሳቸው አላሁ ﷻ ሙሽሪክ ብሎ ሰይሟቸዋል፤ ስለዚህ ዛሬ ጊዜ ሺርክ ላይ ከመውደቃቸው ጋር ሙስሊም ብላችሁ የምትሰይሟቸው አካላትም እንደነዚያው ሙሽሪኮች ናቸው» ይላሉ።

"العبرة بعموم اللفظ لا بخصوص السبب"

የሚለውን ቃዒዳ እንደወረደ በመያዝ ማለት ነው።

ለዚህ አቋማቸውም የሚከተሉትን የቁርኣን አናቅፆችን ያጣቅሳሉ፦

١ـ {وَإِنْ أَحَدٌ مِّنَ الْمُشْرِكِينَ اسْتَجَارَكَ فَأَجِرْهُ حَتَّىٰ يَسْمَعَ كَلَامَ اللهِ ثُمَّ أَبْلِغْهُ مَأْمَنَهُ ۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ قَوْمٌ لَّا يَعْلَمُونَ} (التوبة: ٦)

{ከአጋሪዎችም አንዱ ጥገኝነትን ቢጠይቅ የአላህን ቃል ይሰማ ዘንድ አስጠጋው፡፡ ከዚያም ወደ መጠበቂያው ስፍራ አድርሰው፡፡ ይህ እነሱ የማያውቁ ሕዝቦች በመኾናቸው ነው፡፡} (አት ـ ተውባ: 6)

• አንቀፁ ላይ እነሱ እንደሚሉት: "ሑጃ ሊሆንበት የሚችለውን የአላህን ንግግር ከመስማቱ በፊት ሙሽሪክ ብሎ ገልፆታል"።

٢ـ {لَمْ يَكُنِ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ وَالْمُشْرِكِينَ مُنفَكِّينَ حَتَّىٰ تَأْتِيَهُمُ الْبَيِّنَةُ} (البينة: ١)

{እነዚያ ከመጽሐፉ ባለቤቶች ከአጋሪዎቹም የካዱት ግልጹ አስረጅ እስከ መጣላቸው ድረስ (ከነበሩበት ላይ) ተወጋጆች አልነበሩም፡፡} (አል በዪናህ:1)

• እዚህ ላይም እንዲሁ "ማስረጃ ሳይመጣቸው በፊት ሙሽሪክ ብሎ ሰይሟቸዋል" ይላሉ።

በተጨማሪ መልእክተኛው ሙሐመድ ﷺ ለሰው ልጆች ሑጃ አድራሽ የሆኑ መልእክተኞች መልላካቸው ከተቋረጠ በኋላ የተላኩ መሆናቸው እነኚሁ አካላቶች ያሉበትን አቋም የሚያጠናክርላቸው አድርገው ያስባሉ።

በዚህ ዙሪያ አላሁ ﷻ እንዲህ ብሏል:

{يَا أَهْلَ الْكِتَابِ قَدْ جَاءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ عَلَىٰ فَتْرَةٍ مِّنَ الرُّسُلِ أَن تَقُولُوا مَا جَاءَنَا مِن بَشِيرٍ وَلَا نَذِيرٍ ۖ فَقَدْ جَاءَكُم بَشِيرٌ وَنَذِيرٌ ۗ وَاللهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ} ( المائدة: ١٩)

{እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! «አብሳሪና አስፈራሪ አልመጣልንም» እንዳትሉ ከመልክተኞች በመቋረጥ ጊዜ ላይ ሲኾን (ሕጋችንን) የሚያብራራ ኾኖ መልክተኛችን በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ አብሳሪና አስፈራሪም በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡} (አል ማኢዳህ: 19)

እነዚህንና የመሳሰሉ አናቅፆችን መነሻ በማድረግ የቀድሞ ዘመናት የዐረብ ሙሽሪክ ማህበረሰቦች ሁጃ ሳይደርሳቸው ሙሽሪክ መባላቸውን ከድምዳሜ በመድረስ፤ በዘመናችን ያሉ ሽርክ ላይ የወደቁ ሙስሊሞችም ያላቸው ብይን ከእነዚያ ጋር አንድ አይነት ነው ይላሉ፤ በተጨማሪም ዱንያ ላይ ሙሽሪክ ስለሆኑ እነሱን መጋደል እንደሚቻልና በኣኺራ ግን ሁጃ ሳይቆምባቸው እንደማይቀጡ ድምዳሜ የደረሱ የተክፊር ቫይረስ የተጠናወታቸው ከፊል አካላት ቢኖሩም፤ ሌሎች ደግሞ በዱንያ ውስጥ እነሱን መጋደል አይቻልም፤ በኣኺራም ቅጣት አይከተላቸውም፤ ነገር ግን በሽርካቸው ምክንያት ኩፋ፞ር (ከሃዲዎችና ሙሽሪኮች) ናቸው የሚሉ አሉ።

▪️ለዚህ አቋማቸው ኢንሻአላህ በተለያየ መንገድ መልስ ለመስጠት እሞክራለሁ።

①ኛ በአላህ ﷻ አንድነትና ትክክለኛ አምላክነት፣ እንዲሁም በሙሐመድ ﷺ መልእክተኛነት ፈፅሞ የማያምኑና በመሰረቱ ጥርት ያሉ ሙሽሪኮች ወይም ኩፋሮች ላይ የተሰጡ የኩፍርና የሺርክ ስያሜዎችን፤ አስላቸው (መሰረታቸው) ከእነዚህ ተቃራኒ በሆኑት ላይ ማለትም፦ በአላህ አንድነትና ትክክለኛ አምላክነት እንዲሁም በሙሐመድ ﷺ መልእክተኛነት በኢጅማል ወይም በጥቅል የሚያምኑ በሆኑ ሙስሊሞች ላይ እነዚህን ስያሜዎች መለጠፍና ሁለቱን አካሎች አንድ አድርጎ መመልከት፦ *ከባድ ዙልም* ከመሆኑም በላይ በርካታ ሸሪዓዊ መረጃዎች ጋር ይቃረናል።

▪️የቀድሞዎቹ ሙሽሪኮች ሁጃ ሳይቆምባቸው በስተፊት ይህ ስያሜ የተሰጠባቸው ምክንያት፦ የአላህን አንድነትና ብቸኛ የአምልኮ ተገቢነቱን ባለማመናቸውና በርካታ የሽርካሽርክ ተግባራት ውስጥ የተዘፈቁ በመሆናቸው ነው። አስላቸውና ፈስላቸው ሙሽሪክ የሚያሰኛቸው ተግባራት እንጂ ሌላ ምንም የእምነት ወይም የተውሒድ ተግባራት ስለሌላቸው ማለት ነው። እነዚህ ሰዎች ሁጃ ያልደረሳቸው በመሆኑ "የእሳት ናቸው" ተብሎም አይበየንባቸውም። ምክንያቱም ሁጃ አድራሽ መልእክተኞች በሌሉበት ዘመን የነበሩ ሽርክ ውስጥ የተዘፈቁና በአላህ ያላመኑ ሰዎች በኣኺራ እንደሚፈተኑ የሚጠቁሙ መረጃዎች ስለመጡ ማለት ነው።

▪️ነገር ግን በኢስላም ድንጋጌዎች በጥቅል አማኝ የሆኑ ሙስሊሞች በጀህል ወይም ባለማወቅ ምክንያት አንዳንድ የሽርክ ተግባራት ላይ ቢወድቁ ዑዝር ይሰ፞ጣ፞ቸ፞ዋል (አይከ፞ፈ፞ሩም)፤ በጀህል ሰበብ ያጠፉትም ስህተት ይቅር ይባልላቸዋል።  በኣኺራም ብዙዎቹ ዑለማዎች እንደሚሉት ጉዳያቸው ወደ አላህ ይመለሳል።
ምክንያቱም ይህን እውነታ የሚደግፉ በርካታ መረጃዎች በመኖራቸው ነው።
ለምሳሌ ያህል:

🤏 ከብዙ ሰሓቢዮች ተወርቶ ቡኻሪ፣ ሙስሊምና ሌሎችም በዘገቡት የነቢዩ ﷺ ሐዲሥ ላይ እንዲህ የሚል አለ፦

[መልካም ስራ የሌለው አንድ (ኢስራኢይሊይ) የሆነ ሰው ሊሞት ሲል ልጆቹን እንዲህ ሲል ተናዘዘ፦
"እኔ ለእናንተ ምን አይነት ወላጅ ነኝ?"
እነሱም "ምን ያምር ወላጅ ነህ!" አሉት።
"እንግዲያውስ ስሞት አቃጥሉኝና ፍጩኝ። ከዚያም በነፋሻማ ወቅት ባህር ውስጥ አመዱን በትኑት። በአላህ ይሁንብኝ! አላህ እኔን ከሞት ለማንሳት ችሎ ቢቀሰቅሰኝ (እና ቢያገኘኝ) አለማት ላይ ካሉ ፍጡራኖች ማንኛውንም የማይቀጣውን ቅጣት ይቀጣኛል።" አላቸው።
በሞተ ጊዜ ልጆቹ የታዘዙትን ፈፀሙ። ከዚያም አላህ ﷻ ባህሩንም የብሱንም የተበተነውን አመድ እንዲሰበስቡ አዘዘ፤ ሰውየውንም ቀሰቀሰውና:  "ይህን ለማድረግ ያነሳሳህ ምንድን ነው? " አለው። እሱም: "ጌታዬ! ፈርቼህ ነው" ሲል መለሰ።
አላህም ﷻ "በእርግጥ ምሬ፞ሃለሁ" አለው።)


▪️قال شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله تعالى كما في (مجموع الفتاوى: 3/231) : 
---------------
#ወደ_ገፅ-➋- ይሸጋገሩ↩️

አል-በያን البــيان

21 Oct, 12:53


📚ይቀጥላል..

➨➨

አል-በያን البــيان

21 Oct, 11:40


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
.
-----------------------📚📚------------------------

📋ከታች የምትመለከቶቸው በክፍል የቀረቡ ርዕሶች የተከፊርዮችን የሹበሀ ወጥመዶችንና ጥመት ከብዙ በትቂቱ የተዳሰሰበት ወቅታዊ የሆነ ትምህርቶችን ይዟል።

⬇️⬇️ሊንኮቹን በመጫን ትምህርቱን ይከታተሉ።


📚📚

🔖ክፍል 1 - ኡዝር ቢል ጀህል ማለት ምን ማለትነው?
🔗https://t.me/al_beyann/1234
🔖ክፍል 2 - ኡዝር ቢልጀህል ቁረዓናዊ ማስረጃው።
🔗https://t.me/al_beyann/1235
🔖ክፍል 3 - ኡዝር ቢልጀህል ቁረዓናዊ ማስረጃው።
🔗https://t.me/al_beyann/1237
🔖ክፍል -4 - በኢስላም ኡዝር ቢል ጀህል ለመኖሩ የተዳሰሰበት
🔗https://t.me/al_beyann/1240
🔖ክፍል -5 - በኢስላም ኡዝር ቢል ጀህል ለመኖሩ የተዳሰሰበት
🔗https://t.me/al_beyann/1242
🔖ክፍል -6 - በኢስላም ኡዝር ቢል ጀህል ለመኖሩ የተዳሰሰበት
🔗https://t.me/al_beyann/1246
🔖ክፍል -7 - በኢስላም ኡዝር ቢል ጀህል ለመኖሩ የተዳሰሰበት
🔗https://t.me/al_beyann/1250
📌ክፍል -8- ኡዝር ቢል ጀህል በኡለማዎች እይታ።
🔗https://t.me/al_beyann/1251
📌ክፍል -9- ኡዝር ቢል ጀህል በኡለማዎች እይታ።
🔗https://t.me/al_beyann/1252
📌ክፍል -10- ኡዝር ቢል ጀህል በኡለማዎች እይታ።
🔗https://t.me/al_beyann/1253
📌ክፍል -11- ኡዝር ቢል ጀህል በኡለማዎች እይታ።
🔗https://t.me/al_beyann/1254
📌ክፍል -12 - ኡዝር ቢል ጀህል በኡለማዎች እይታ።
🔗https://t.me/al_beyann/1257
📌ክፍል -13 - ኡዝር ቢል ጀህል በኡለማዎች እይታ።
🔗https://t.me/al_beyann/1258
📌ክፍል -14 - ኡዝር ቢል ጀህል በኡለማዎች እይታ።
🔗https://t.me/al_beyann/1259
🔖ክፍል -15- መሳኢል ዟሂራ እና ኸፍያ።
🔗https://t.me/al_beyann/1269

አል-በያን البــيان

11 Oct, 20:59


#ገፅ -❽- ክፍል➊➐ ቁጥር❾
--------------------__-------------------

*ኢብኑል ሙለቂን ያዘጋጁትን "አል በድሩል ሙኒር"* (8/637)  እና *ሷሊሕ ኣሉሽ ሸይኽ* ያዘጋጀውን *"አት ተክሚል ሊማ ፋተሁ ተኽሪይጁሁ ሚን ኢርዋኢል ጘሊል"* : (170) ላይ ተመልከት።

👌ይህ አሠር በገሃድ እንደሚያሳየን *ሰውየው በሸሪዓ ሐራምነቱ ዟሂር የሆነን ጉዳይ ሐላል አድርጎ እንኳ ዑመር ረዺየላሁ ዐንሁ አላከፈረውም፤* "ሐድ" ቅጣትም እንዲቀጣ አላደረገውም!!

٢ـ ومن ذلك ما رواه يحيى بن عبد الرحمن عنأبيه قال: «توفِّي حاطبٌ، فأعتق من صلى من رقيقه وصام، وكانت له أمة نوبية قد صلت وصامت، وهي أعجمية لم تفقه، فلم ترعه إلا بحبلها، وكانت ثيبًا، فذهب إلى عمر رضي الله عنه فحدثه .
فقال: لأنت الرجل لا تأتي بخير.
فأفزعه ذلك .
فأرسل إليها عمر رضي الله عنه فقال : أحبلت ؟
فقالت: نعم، من مرعوش بدرهمين.
فإذا هي تستهل بذلك لا تكتمه.
قال: و صادف عليًّا، وعثمان، وعبد الرحمن بن عوف رضي الله عنهم، فقال: أشيروا عليًّ.
وكان عثمان رضي الله عنه جالسًا فاضطجع.
فقال علي، وعبد الرحمن : قد وقع عليها الحد.
فقال : أشر عليَّ يا عثمان.
فقال : قد أشار عليك أخواك.
قال : أشر عليَّ أنت.
قال : أراها تستهل به كأنها لا تعلمه، وليس الحد إلا على من علمه.
فقال : صدقت، والذي نفسي بيده ما الحد إلا على من علمه.
فجلدها عمر ـ رضي الله عنه ـ مائة، وغربها عامًا»

أخرجه عبد الرزاق في المصنف: (١٣٦٤٤)، والبيهقي في السنن: (١٦٨٤٢)، وهو صحيح الإسناد، انظر: "التكميل لما فاته تخريجه من إرواء الغليل" (١٧٠) للشيخ صالح آل الشيخ.

•²• የሕያ ኢብኑ ዐብዲረሕማን ከአባቱ ይዞ ባወራው አሠር እንዲህ ይላል፦ «አያቴ ሓጢብ ሲሞት አባቴ ዐብዱረሕማን ከሓጢብ ባሮች መካከል የሚሰግዱትንና የሚፆሙትን ነፃ አወጣቸው፤ ነፃ ከወጡት መካከልም ዐረብ ያልሆነች አንዲት እውቀት የሌላት ጥቁር ሴት ነበረች፤ እሷንም ድንገት እርጉዝ ሆና አይቷት ደነገጠ፤ እሷ ደግሞ አግብታ የምታውቅ ናት፤ እናም ወዲያው ወደ ዑመር ረዺየላሁ ዐንሁ በመሄድ ጉዳዩን ነገረው። ዑመርም: "አንተ እንደው በመልካም ነገር የማትመጣ ሰው ነህ" አለው። ይህ አባባል ታድያ ዐብዱረሕማንን አስደነገጠው፤ ዑመርም ወዲያው ሰው ልኮባት ቀረበችና: "አርግዘሻል ወይ?" ሲል ጠየቃት፤ እሷም ከምንም ሳትቆጥረው፤ ምንም ሳትደብቅና ጉዳዩን ቅልል፞ አድርጋ: "አዎ አርግዣለሁ፤ ያውም ከመርዑሽ በሁለት ዲርሃም" ብላ መለሰችለት።

الفوائد السلفية, [8/23/22, 2:56 PM]
[Posted by بن أحمد]
በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለ ድንገት ዐሊይን፣ ዑሥማንንና ዐብዱረሕማን ኢብኑ ዐውፍን በማግኘቱ "እስኪ ስለዚህ ጉዳይ ምን ትሉኛላችሁ?" በሚል ሀሳባቸውን እንዲያጋሩት ጠየቃቸው። ዑሥማን ቁጭ ብሎ ነበርና ገደም አለ፤ ዐሊይና ዐብዱረሕማንም: "ይህቺ ሴት ሀድ፞ (ተቀጥቅጦ መገደል) ተረጋግጦባታል" አሉት። ዑመር "አንተሳ ዑሥማን ምን አይነት ምክረ ሀሳብ ትሰጠኛለህ?" አለው። ዑሥማንም "በእርግጥ ሁለት ወንድሞችህ ሀሳባቸውን ለግሰውሃል" አለው። በዚህጊዜ:  "(ያ እንዳለ ሆኖ) አንተም ሀሳብ ስጠኝ" አለው ዑመር። ይህኔ ዑሥማን እንዲህ አለ: "እኔ መቼም ሴትየዋ ጉዳዩን ቅልል አድርጋ ስታወራ ነው የማያት፤ (ሐራምነቱን) የማታውቀው ትመስላለች፤ ሀድ፞ ደግሞ በሚያውቅ ሰው ላይ እንጂ (በማያውቅ ላይ) አይፈፀምም።" ዑመርም "እውነትህን ነው፤ ነፍሴ በእጁ በሆነው ጌታ ይሁንብኝ ሀድ፞ በሚያውቅ ሰው ላይ እንጂ (በማያውቅ ላይ) የለም።" በማለት የዑስማንን ሀሳብ መደገፉን አረጋገጠ። ከዚያም ዑመር ረዺየላሁ ዐንሁ አንድ መቶ ግርፋት እንድትገረፍና ለአንድ አመት ያህል ከሀገሯ ርቃ እንድትኖር ወሰነባት።»

[ዐብዱረዛቅ አስ ሰንዓኒ "ሙሶነፉ" (13644) ላይ እና በይሀቂይ "ሱነኑ" (16842) ላይ ትክክለኛ በሆነ የዘገባ ሰንሰለት ዘግበውታል። ሷሊሕ ኣሉሽ ሸይኽ* ያዘጋጀውን *"አት ተክሚል ሊማ ፋተሁ ተኽሪይጁሁ ሚን ኢርዋኢል ጘሊል"* : (170) ላይ ተመልከት።]

➨ይህ አሠር በግልፅ እንደሚጠቁመን ሴትየዋ ከባርነት ነፃ የወጣች አግብታ ምታውቅ ዝሙተኛ በመሆኗ የእሷ ሀድ፞ ወይም የቅጣት ወሰን ተቀጥቅጦ መገ፞ደል ነበር፤ ነገር ግን ዑመር ረዺየላሁ ዐንሁ በጅህልናዋ ምክንያት ይህን ቅጣት አነሳ፞ላት፤ ለ"ተዕዚይር" ወይም ለመቀጣጫና አደብ ማስያዣ የሚሆናትን መቶ ግርፋትና አመት ያህል ከሀገሯ መርራቅንም ወሰነባት። ይህ የዑመር ውሳኔ መቀጣጫ የሆነ "ተዕዚይር" እንጂ "ሀድ፞" አለመሆኑንና "ሀድዱን" በጅህልናዋ ሰበብ ያነሳላት መሆኑን ኢማሙል በይሀቂ "ሱነኑ" (8/238) ላይ ተንቢህ አድርጓል።

➨ባጠቃላይ እነዚህ ሁሉ ኣሣሮች ሶሓቦች ዘንድ በጀህል ዑዝር ለመስጠት ግምት ውስጥ የሚገባው የሑጃው መድረስ ወይም አለመድረስ እንጂ የመስአላዋ አይነት ብቻ እንዳልሆነ ያረጋግጥልናል።

*በዚህ ዙሪያ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ እንዲህ ይላል፦*

«وقد زنتْ على عهد عمر امرأةٌ، فلما أقرَّتْ به، قال عثمان: (إنها لتستهل به استهلالَ مَن لم يعلم أنه حرامٌ). فلما تبين للصحابة أنها لا تعرف التحريم لم يحدُّوها، واستحلال الزنى خطأٌ قطعًا» "مجموع الفتاوى" : (19/210)، وانظر "منهاج السنة": (5/51)

«በዑመር ዘመን የሆነች ሴት ዝሙት ሰርታ፤ መስራቷንም ባመነች ጊዜ ዑሥማን እንዲህ አለ: "ኧረ ይቺ ሴትዮ ሐራምነቱን የማያውቅ ሰው አቅልሎ እንደሚያየው እሷም ጉዳዩን ቅልል አድርጋ የምታይ ናት!!" አለ። ሴትየዋ የዝሙትን ሐራምነት የማታውቅ መሆኗ ለሰሓቦች በተገለፀላቸውም ጊዜ (አግብቶ የሚያውቅ ዝሙተኛ የሚገ፞ባ፞ውን) ሀድ፞ ሳያቆሙባት ቀርተዋል። ዝሙትን ሐላል ማድረግ ደግሞ በእርግጠኝነት ከባድ የሆነ ስህተት ነው» "መጅሙዑል ፈታዋ" : (19/210)፣ "ሚንሃጅ አስ ሱንና" ሊብኒ ተይሚያ: (5/51) ላይ ተመልከት።

انتهى المراد بحول الله وقوته في ضحى يوم الثلاثاء:  ٢٥/١/١٤٤٤

💠💠

🖌አቡ ዐብዲላህ ሰዒድ (አስ ሰለፊ)

🗓25/1/1444هـ

-------------------💎----------------------
🔗https://t.me/al_beyann/1269

አል-በያን البــيان

11 Oct, 20:48


#ገፅ-➐- ክፍል➊➐ ቁጥር❾
------------------___---------------------

[ሑዘይፈቱ ኢብኑል የማን የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ፦
«ልብስ ላይ ያለ፞ ዲዛይን አሮጌ ሆኖ እንደሚጠፋው ሁሉ፦ ፆም፣ ሶላት፣ እርድ (አምልኮ) እና ሰደቃ መታወቅ የማይችሉበትና የሚረሱበት ደረጃ እስሚደርሱ ድረስ ኢስላምም ይጠፋል (ፋናው ይታበሳል)፤ የአላህ መፅሀፍ (ቁርኣንም) ምድር ላይ አንዲት አንቀፅ እንኳ እስከማትቀር ድረስ በአንድ ምሽት ይነ፞ሳ፞ል። "እኛኮ አባቶቻችንን ላ ኢላሀ ኢለሏህ በምትለዋ ቃል ላይ  ስላገኘናቸው እኛም (በምላሳችን) እንላታለን" የሚሉ ሽማግሌዎችንና ባልቴቶችን ጨምሮ ከሰዎች የተወሰኑ ጀማዓዎች ይቀራሉ።» ብለዋል አለ። በዚህ ጊዜ ሲለህ የተባለው የሐዲሡ ዘጋቢ ሰው ለሑዘይፋ: "እነኚህ ሰዎች ፆም፣ ሶላት፣ እርድ (አምልኮ ወይም ሐጅ) እና ሰደቃ የሚባሉት ዒባዳዎች ምን እንደሆኑ የማያውቁ ሆነው ሳለ፤ ላ ኢላሃ ኢለሏህ ምን ትጠቅማቸዋለች!?" አለው። ሑዘይፋም መልስ ሳይሰጠው ትቶት ዞረ። አሁንም ደግሞ ሲጠይቀው ትቶት ይዞራል፤ ለሶስተኛ ጊዜ ሲጠይቀው ግን ወደ ሲለህ በመዞር ቀጣዩን ንግግር ሶስት ጊዜ ደጋግሞ የሚናገር ሲሆን "ሲለህ ሆይ! ከእሳት ታድናቸዋለች" ብሎ መለሰለት።]
[ሐዲሡን፦ ኢብኑ ማጀህ "ሱነኑ" ውስጥ ኪታቡል ፊተን (4049) ላይ ዘግቦታል፣ ሓኪም "ሙሰተድረክ"  ውስጥ ኪታቡልፊተን ወልመላሒም (4/473) ላይ ዘግቦት:  "ቡኻሪና ሙስሊም ባይዘግቡትም በኢማም ሙስሊም ሸርጥ ሰሒሕ የሆነ ሐዲሥ ነው" ብሎታል፤ ቡሰይሪ ዘዋኢድ ላይ (3/254) ኢስናዱ ሰሒህ ነው ብሎታል፤ ኢማሙል አልባኒም "አስ ሰሒሓ": (87/1/171) እና "ሰሒሕ ኢብን ማጀህ" ላይ ሐዲሡን ሰሒሕ አድርገውታል።]

👌እንደሚታወቀው ሶላት፣ ዘካና ፆም አሳሳቢ ከሆኑት የኢስላም መገለጫዎችና ከሌሎች ዒባዳዎች ይልቅ በሙስሊሞች መካከል በሰፊው ተሰራጭተውና በገሃድ የሚታወቁ ሆነው የሚገኙ ዒባዳዎች ናቸው። ከመሆኑም ጋር ግን ይህ ሀዲሥ እንደሚጠቁመን ግልፅነታቸውና መንሰራፋታቸው ጠፍቶ፤ ያኔ ሙስሊሞች የማያውቋቸውና የማይተገብሯቸው ከሆኑት  ከመሳኢል ኸፊያ (ከድብቅ ሀይማኖታዊ ጉዳዮች) የሚሆኑበት ዘመን ይመጣል።

👌ይህ ሐዲሥ ደግሞ ስለ ሰለምቴዎች ወይም ከኩፍር ወደ ኢስላም የተመለሱበት ጊዜያቸው ቅርብ ስለሆኑ ሰዎች የሚተርክ ሳይሆን፤ ዒልም ጥቂት በሆነበትና ጅህልና በተንሰራፋበት ዘመን ስለሚገኙ ሰዎች ብቻ ነው የሚያትተው።

Nb: ሙኻሊፎች: "ይህ ሐዲሥ ሰዎቹ ሺርክ ላይ ስላልወደቁ ከመስአላችን ጋር አይሄድም" ሊሉ ይችላሉ። ይህ ኢዕቲራዽ ትክክል አይደለም፤ ምክንያቱም ሀዲሡ እነኚህ ሰዎች ከኢስላም መገለጫ በጣም ግልፅና ከፍ ያለ ደረጃ ያላቸው የሆኑ ጉዳዮችን እስከመቃረን ያበቃቸው ሀይለኛ የሆነ ጅህልና ላይ መሆናቸውን ያረጋግጥልናልና። ይህ እንዲህ ከሆነ በግልፅነት የእነዚህ መገለጫዎች አምሳያ የሆኑ ነገሮች ላይ መውደቃቸው አይቀሬ ነው። በተጨማሪም ሰዎቹ እነዚህን ግልፅ የዲኑ መገለጫዎችን ትተው ባለማወቃቸው ምክንያት
ዑዝር ከተሰጣቸው፤ እነኚህን ጉዳዮች በግልፅነት በሚጋ፞ሩ፞ ሌሎች የኢስላም መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይም ጀህል ዑዝር የሚያሰ፞ጥ፞ ከልካይ ምክንያት መሆኑን ይጠቁማል ማለት ነው።

الفوائد السلفية, [8/23/22, 2:56 PM]
[Posted by بن أحمد]
💫 "ዙሁውር" እና "ኸፋእ" ወይም ግልፅነትና መደበቅ አንፃራዊ መሆኑንና "ኒስቢይነት" ሰዎች ላይ ሑክም ከመስጠት ጋር የጠበቀ ትስስር እንዳለው ከሚጠቁሙ መረጃዎች መካከል ሁለተኛ:

በዑመር ኢብኑል ኸጧብ የኺላፋ ዘመን "ሚነስ ሳቢቂነል አወ፞ሊን" (ከመጀመሪያዎችና ቀዳሚ ከነበሩት ሙስሊሞች) አንዱ የነበረው፤ እንዲሁም በድር ዘመቻ የተሳተፈው *ቁዳመቱ ኢብኑ መዝዑንና ጓደኞቹ* ሙተአውዊሎች ሆነው አስካሪ መጠጥን (ኸምርን) መጠጣት ሐላል ባደረጉ ጊዜ ሶሓቦች ከእነሱ ጋር ያደረጉት ሙዓመላ ነው።

እንደሚታወቀው ኸምርን መጠጣት ሐራም መሆኑ በኢስላም ግልፅ ከሆኑ መሳኢሎች ነው። ሐራምን ሐላል፤ ሐላልን ሐራም ማድረግ ደግሞ ከኢስላም የሚያስወጣ ትልቅ የሆነ ኩፍር ነው። ከመሆኑም ጋር ግን ሶሓቦች አላከፈሯቸውም፤ ይልቁንም በተእዊላቸው ምክንያት ዑዝር ሰጥተዋቸዋል። *ቁዳመቱ ኢብኑ መዝዑን አዲስ ሰለምቴ አልነበረም፤ እውቀት ካለበት ስፍራም የራቀ አልነበረም* ። ይልቁንም በነቢዩ ﷺ ዘመን በድር ዘመቻ ከተሳተፉትና በኢስላማቸው ቀዳሚ ከነበሩ ሶሓቦች ነበር።

👌ይህ እንግዲህ ሶሐቦች ዘንድ በሰው ላይ ሑክም ለመስጠት ግምት ውስጥ የሚገባው፦ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሑጃ ደርሶታል፤ ወይስ አልደረሰውም የሚለው ነጥብ እንጂ፤ ሙኻለፋ የተከሰተባት የመስአላዋ አይነት እንዳልሆነ በገሃድ ያረጋግጥልናል ማለት ነው!!

💫 ልክ እንደዚሁ *ወደ ኢስላም ቀደም ብለው ከገቡት ሶሓቦች አንዱ የነበረው አቡ ጀንደል ኢብን ሱሀይል የተባለው ሰሓቢይና ጓደኞቹ* በዑመር ዘመን ሻም ሀገር ላይ የማኢዳን አንቀፅ (93) ተእዊል አድርገው እንደመረጃ በመጠቀም ኸምርን ሐላል ባደረጉና በጠጡ ጊዜ ሶሐቦች አላከፈሯቸውም፤ ይልቁንም ስህተተኞች መሆናቸውን አሳውቀዋቸው ለጠጡበት ጥፋት ሀድ፞ ገርፈዋቸዋል፤ እነሱም ቶብተዋል።

ቂሷውን ዐብደረዛቅ አስ ሰንዓኒ "ሙሶነፍ": (9/244) ላይ፣ ኢብኑ ዐብዲል በር፞ "አል ኢስቲይዓብ": (4/1622) አውስተውታል።

ይህ የቁዳማና የአቡ ጀንደል ቂሷ እንዲሁም ሶሓቦች ከእነሱ ጋር ያደረጉት ሙዓመላ፤ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ በመሳኢል ዟሂራም ይሁን በሌሎች መሳኢሎች ላይ በጀህልና በተእዊል ዑዝር ሲሰጥ መዝሀቡ ከቆመባቸው አሳሳቢና ወሳኝ ከሆኑት መደገፊያዎቹ የሚመደብ ነው።
ይህም ሸይኹ ቂሷውን ብዙ ጊዜ ደጋግሞ የሚያወሳበትንና እንደመረጃ የሚጠቀምበትን ሚስጥር ይገልፅልናል።

💫 ሶስተኛ: *ባለማወቅ ዝሙትን ሐላል ያደረገ ሰው ጋር ኸሊፋው ዑመር ረዺየላሁ ዐንሁ ያደረገው ሙዓመላ ነው።*

በዚህ ጉዳይ በርካታና ትክክለኛ የሆኑ አኽባሮች ተዘግበዋል።

ከነዚህም መካከል፦

١ـ عن ابن المسيب قال: (ذكروا الزنا بالشام، فقال رجلٌ: زنيتُ، قيل: ما تقول؟ قال: أَوَ حرَّمَهُ اللهُ، ماعلمتُ أن الله حرَّمه، فَكُتِبَ إلى عمرَ بنِ الخطاب، فَكَتَبَ: إِنْ عَلِمَ أن الله حرَّمه فحدُّوه، وإن كان لم يعلم فعلِّموه، وإن عاد فحدُّوه)
صحيح:
أخرجه عبد الرزاق (7/ 403) عن ابن عيينة عن عمرو بن دينار عن ابن المسيب به.


•¹• ዐብደረዛቅ አስ ሰንዓኒ "ሙሰነ፞ፍ": (7/403) ላይ ከሰዒድ ኢብኑል ሙሰየብ የተያዘን አሠር ትክክለኛ በሆነ ሰነድ እንዲህ ሲል ዘግቧል:

«ሻም ሀገር አንድ ወቅት ስለ ዚና ሲወ፞ራ የሰማ የሆነ ሰው (ሳይሸማቀቅ ዘና ብሎ): "እኔ ሰርቻለሁ!" አላቸው። አብረውት ያሉት ሰዎችም: "ምን እያልክ ነው?" አሉት። እሱም "አላህ ሐራም አድርጎታልንዴ!? እኔኮ አላህ ሐራም ማድረጉን አላውቅም!" አላቸው።
ከዚያ ጉዳዩ ወደ ዑመር ተፅፎ ተላከ፤ ዑመርም:  «አላህ ሐራም ማድረጉን የሚያውቅ ከሆነ የዝሙተኛን *ሀድ፞ (ቅጣት) ቅጡት* ፤ የማያውቅ ከሆነም አስተምሩት፤ ዳግመኛ ከሰራ ግን ሀድ፞ (ቅጣትን) ቅጡት።» የሚልን መልስ በፅሁፍ ላከላቸው።

➦------➦-------➦------➦

#ወደ ገፅ -❽- ተሸጋገሩ።↩️

አል-በያን البــيان

11 Oct, 20:38


#ገፅ -❻- ክፍል➊➐ ቁጥር❾
---------------------__----------------------

እስካሁን ከተጠቀሰው በመነሳት ሀሳቡ ጠቅለል ሲል👇

አንዲት መስአላ ከፊል ሰዎች ዘንድ ዟሂራ መሆኗ ከእነሱ ሌላ ያለ እያንዳንዱ ሰው ሁሉ ዘንድ ዟሂራ መሆኗን አያስይዝም፤ ይህ ሲባል "የሆነች መስአላ ፦ ዟሂራ ናት፤ ወይም ሙተዋቲራ ናት ብሎ መሐከም አይቻልም" ማለት አይደለም፤ ነገር ግን መስአላዋን ዟሂራ ናት ብለን  ከሐከምን በኋላ፤ ይህ ሑክም ሁሉም ሰው ዘንድ የፀና፞ እና ሁሉም ሰው ዘንድ የሚገኝ አድርገን ማመናችን ትክክል አይደለም። ይልቁንም ከእውቀት ማግኛ ስፍራ በመራቃቸው አሊያም ደግሞ ትክክለኛ ባልሆነ ተእዊልና በመሳሰሉት ምክንያቶች ይህ ባህሪ ከነሱ እንዲወገድ ግድ የሚያደርጉ የተለያዩ የሰዎች ሁኔታዎች ግምት ውስጥ መግባታቸው ግድ ይላል።

👌መስአላ ዟሂራና ኸፊያን በመለያየት ዑዝር ቢል ጀህል የለም ለማለት እንደ መደገፊያ መጠቀምን ስህተት መሆኑን ከገለፁ ዑለማኦች መካከል ሸይኽ ሙሐመድ ኢብን ሷሊሕ አል ዑሠይሚን አንዱ ናቸው።
እሳቸውም (ሊቃኣቱል ባቢል መፍቱሕ: (48) (3/45) የተሰኘው ኪታባቸው ላይ እንዲህ ይላሉ:

«تجب إقامة الحجة قبل التكفير، وذلك في كل المسائل التي يمكن أن يجهلها الناس، فلا نقسِّم المسائل إلى مسائل ظاهرة ومسائل خفية؛ لأن الظهور والخفاء أمرٌ نِسبيٌّ، قد تكون المسألة ظاهرة عندي وخفية عند غيري، فلا بد إذًا من إقامة الحجة وعدم التسرع في التكفير؛ لأن إخراج رجل من ملة الإسلام ليس بالأمر الهين».
(لقاءات الباب المفتوح :(48)، (3/45)، وانظر (الشرح الممتع: 2/25)

الفوائد السلفية, [8/23/22, 2:56 PM]
[Posted by بن أحمد]
«ሰውን ከማክፈር በፊት ሑጃን ማቆም ግድ ነው። ይህም ሰዎች ላያውቁት በሚችሉት ነገር ሁሉ ነው። መሳኢል ዟሂራ ( እነሱ እንደሚሉት: ለማክፈር ሑጃ ማቆም መስፈርት የማይሆንበት) እና መሳኢል ኸፊያ (ለማክፈር ሑጃ ማቆም መስፈርት የሚሆንበት) በማለት አንከፋፍልም።
ምክንያቱም ግልፅነትና ድብቅነት "ኒስቢይ" ወይም አንፃራዊ ነገር ነውና፤ መስአላዋ እኔ ዘንድ ግልፅ ሆና ከእኔ ሌላ ያለ ሰው ዘንድ ግን ድብቅ ልትሆን ትችላለች። ስለዚህ ሑጃን ማቆምና ለማክፈርም አለመቸኮል አይቀሬ የሆነ ጉዳይ ነው። ምክንያቱም አንድን ሰው ከኢስላም ማስወጣት ቀላል ነገር አይደለምና።»

💠💠

ወደኋላ መለ፞ስ፞ ብሎ ኢስላማዊ ዘመናትን የሚቃኝ ሰው የዚህን መሰረት እውነታ ማለትም ግልፅ መሆንና ድብቅ መሆን አንፃራዊ መሆናቸውን ይገነዘባል።

👌የኢብኑ ተይሚያ ዘመን ደርሶ አላህ ይህን በሕር የሆነ ዓሊምና መሰ፞ል ዑለማኦችን ለዚች ኡማ፞ እስኪያመጣላት ድረስ
የአህሉስ ሱናዎች መዝሀብ ጥቂት ሰዎች እንጂ የማያውቁት ድብቅ ነገር ሆኖና ለሐቅ ተቃራኒ የሆኑ መዛሂቦች ደግሞ ግልፅና ታዋቂ ሆነው የቆዩባቸው በርካታ ዘመናት በዚህች ኡምማ ላይ አልፈውባታል።

እነኚህ ዑለማኦች ሲመጡ ግን አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ የአህሉሱናዎችን መዝሀብ በዑለሞቹ ሰበብ ዳግም እንዲያብብና እንዲሰራጭ አደረገው።
እንዲሁም የሺርክ ጉዳዮችና ኢስቲጛሣ ቢጘይሪላህ በገሃድ ተንሰራፍቶ፤ የተውሒድና ዒባዳን ለአላህ ብቻ ጥርት አድርጎ የማዋል ጉዳይ በጣም የተደበቀበት ዘመናትም በኡማዋ ላይ አልፈዋል።
ሸይኽ ሙሐመድ ኢብን ዐብዲል ወሃብና የተባረከች ደዕዋውን አራማጅ የሆኑት ተከታዮቹ መጥተው፤ ለሰዎች የሺርክና የተውሒድ ጉዳዮችን አብራርተው መግለፅን የተያያዙት ጊዜ ግን የተውሒድ መንሰራፋትና ይፋ መሆን ዳግም ሊያብብና ግልፅ ሊሆን ቻለ።
ሸይኹ ራሱ በሱ ዘመንና ከእሱ ቀደም ብሎ በነበረው ዘመን የተውሒድ እንግድነትና ድብቅነት እንዲሁም የሺርክ መንሰራፋት ምን ያህል አሳስቦት ስሞታ ያቀርብ እንደነበር የታሪክ መዛግብቶች ይዘውት ያለ እውነታ ነው።
ይህ ሁሉ የታሪክ ክስተት:

• አንዲት የሆነች መስአላ በሆነ ዘመን ዟሂራ ሆና መቆየቷ፤ በሁሉም ዘመናትም ዟሂራ መሆኗን እንደማያስፈርድ ያረጋግጥልናል።

• አንዲት ጀማዓ ዘንድ ግልፅ መሆኗም ሁሉም ጀማዓዎች ዘንድ ግልፅ የሆነች መስአላ መሆኗን አያስይዝም።

• እንዲሁም የሆነ አካባቢ ላይ ቀጥዒያ መሆኗ በሁሉም ቦታዎችና አካባቢዎች ቀጥዒያ መሆኗን አያስፈርድም ማለት ነው።

---------------🔭🔭

💎ግልፅነትና ድብቅነት አንፃራዊ መሆኑን ከሚጠቁሙ መረጃዎች መካከል አንዱ ቀጣዩ የሰሓቢዩ ሑዘይፋ ሐዲሥ ነው።

عَنْ حُذَيْفَةَ بْنِ الْيَمَانِ قَالَ : قَالَ رَسُولُ الله صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : «يَدْرُسُ الْإِسْلَامُ كَمَا يَدْرُسُ وَشْيُ الثَّوْبِ، حَتَّى لَا يُدْرَى مَا صِيَامٌ، وَلَا صَلَاةٌ، وَلَا نُسُكٌ، وَلَا صَدَقَةٌ، وَلَيُسْرَى عَلَى كِتَابِ اللهِ عَزَّ وَجَلَّ فِي لَيْلَةٍ، فَلَا يَبْقَى فِي الْأَرْضِ مِنْهُ آيَةٌ، وَتَبْقَى طَوَائِفُ مِنَ النَّاسِ ؛ الشَّيْخُ الْكَبِيرُ وَالْعَجُوزُ يَقُولُونَ : أَدْرَكْنَا آبَاءَنَا عَلَى هَذِهِ الْكَلِمَةِ : لَا إِلَهَ إِلَّا الله، فَنَحْنُ نَقُولُهَا». فَقَالَ لَهُ صِلَةُ : مَا تُغْنِي عَنْهُمْ : لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ، وَهُمْ لَا يَدْرُونَ مَا صَلَاةٌ، وَلَا صِيَامٌ، وَلَا نُسُكٌ، وَلَا صَدَقَةٌ ؟ فَأَعْرَضَ عَنْهُ حُذَيْفَةُ، ثُمَّ رَدَّهَا عَلَيْهِ ثَلَاثًا، كُلُّ ذَلِكَ يُعْرِضُ عَنْهُ حُذَيْفَةُ، ثُمَّ أَقْبَلَ عَلَيْهِ فِي الثَّالِثَةِ، فَقَالَ : يَا صِلَةُ، تُنْجِيهِمْ مِنَ النَّارِ. ثَلَاثًا)

-----➦-----➦-----➦-----➦-----➦-----➦-----

#ወደ ገፅ -➐- ይሸጋገሩ ↩️

አል-በያን البــيان

11 Oct, 20:23


#ገፅ -❺- ክፍል➊➐ ቁጥር❾
----------------------_ _ ----------------------

فإذا رأيت إماما قد غَلَّظَ على قائلٍ مقالته أو كفَّرهُ فيها: فلا يعتبر هذا حُكْمًا عاما في كل من قالها، إلا إذا حصل فيه الشرطُ الذي يستحق به التغليظ عليه، والتكفير له ؛ فإن من جحد شيئا من الشرائع الظاهرة، وكان حديثَ العهدِ بالإسلام، أو ناشئا ببلد جهلٍ: لا يكفر حتى تبلغه الحجة النبوية .
وكذلك العكس؛ إذا رأيت المقالة المخطئة قد صدرت من إمام قديم: فاغتُفِرَت ؛ لعدم بُلوغ الحجة له ؛ فلا يغتفر لمن بَلَغَتْهُ الحجة ما اغْتُفِر للأول» (مجموع الفتاوى: 6/61)

«ከተናጋሪዎች አንድ የሆነ ተናጋሪ ሌላን ሰው በንግግሩ ምክንያት ካፊር እስከማድረግ በሚያበቃው መልኩ ንግግሩን ይቃወመው ይሆናል። ወይም ደግሞ ለሀጅር ተገቢ የሆነ ሰው ባይሆንም፤ ሀጅር ሊደረግ የሚገባ ሙብተዲዕ ፋሲቅ ያደርገዋል። ይህም ኢጅቲሃድ ነው፤ ተቃራኒዋ የሚከፈርባት የሆነችዋ ሱንና ግልፅ በመሆኗ (ወይም መረጃዋ ለሰዎቹ በመገለፇ) ምክንያትና ተናጋሪው ንግግር ውስጥ ሙብተዲዕ እንዲሆን የሚያስችለው ጥፋት በመኖሩ፦ ይህ ከባድ የሆነ ብይን ለአንዳንድ ሰዎችና በአንዳንድ ሁኔታዎች (ቢበ፞የ፞ን) ትክክል ሊሆን ይችላል። እነዚህን  ነገሮች አስተዋይ የሆነ ሰው ሊያውቃቸው የሚገቡ ነገሮች ናቸው።

الفوائد السلفية, [8/23/22, 2:56 PM]
[Posted by بن أحمد]
ምክንያቱም አንድ ንግግር እውነተኛ የሚባለው፦ የማትነጠለውና ሁሌ እሱጋ የምትገኘዋ ባህሪው ስለሱ  ከሚነገርለት ነገር ወይም ዋቂዑ ጋር ተስማሚ የሆነው ነውና።
አድማጩ ዘንድ የሚታወቅ ወይም የሚጠራጠርበት ወይም የማይታወቅ መሆኑ፤ ወይም ደግሞ ቀጥዒይ ወይም ዞንኒይ መሆኑ፤ ሊቀ፞በ፞ሉት ግድ የሆነ ወይም መቀበሉ ሐራም የሆነ መሆኑ፤ ተቃዋሚው የሚከፈርበት ወይም የማይከፈርበት መሆኑ፦ እነዚህ ነገሮች ሁሉ እንደ ሰዎቹና ሁኔታዎች መለያየት የሚለያዩ ተግባራዊ የሆኑ አሕካሞች ወይም ብይኖች ናቸው።
ስለዚህ አንድን ኢማም በአንድ ተናጋሪ ላይ (በተዕዪን ነጥሎ) ከበድ ያለ ሑክም ሲሰጥ ወይም ሲያከፍረው ብትመለከት፤
ይህ የኢማሙ ሑክም: ከበድ ያለ ሑክም ሊሰ፞ጠ፞ውና ሊከ፞ፈ፞ር ተገቢ የሚያደርገው መስፈርት ካልተገኘበት በስተቀር ፦
ያን አይነት ንግግር የተናገረን ሰው ሁሉ የሚያካትትና የሚጠቀልል  ተደርጎ አይቆጠርም። ምክንያቱም የእስልምና ጊዜው ቅርብ የሆነ ወይም ጅህልና የተንሰራፋበት ሀገር ያደገ ሆኖ *ግልፅ የሆኑ ሸሪዓዊ ጉዳዮችን የሚቃወም ሰው ነቢያዊ ማስረጃዎች እስካልደረሱት ድረስ አይከ፞ፈ፞ርምና።*
በዚህ ተቃራኒም እንዲሁ ነው፦ ጥፋተኛ የምታስደርገው ንግግር ከአንድ ቀደም ካለ ኢማም ተገኝታ ብትመለከት፤ መረጃ ስላልደረሰው ምህረት ይደረግለታል፤  መረጃ የደረሰው አካል ግን የመጀመሪያው ያገኘውን ምህረት እሱ ሊያገኝ አይችልም።»

👌ይህ የኢብኑ ተይሚያ ንግግር "ኒስቢይያ" ወይም አንፃራዊነት እውቀትንና መሰ፞ል መገለጫዎቹን ግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑን ከመግለፁ አኳያና ሑክም ለመስጠት ወሳኝ የሆነውን የሑክምን ትክክለኛ መወጠ፞ኛ ወይም ማሰሪያ ቦታውን ከመግለፁ አንፃር ሙሂም፞ የሆነ የሸይኹ ንግግር ነው።

«فكلُّ من بلغتْهُ الحجةُ البلوغَ المُعْتَبَر، فإن حكم الفعل ينطبق عليه ولو كان حديثَ عهدٍ بكفرٍ، وكل من لم تبلغه الحجة ـ التي يرتفع بها وصفُ الجهالة ـ فإن حكم الفعل لا ينطبق عليه ولو كان يعيش في بلاد المسلمين»

«ስለዚህ ማንኛውም ሰው ማስረጃ ተገቢ የሆነ መድረስን ከደረሰው ከኩፍር ወደ ኢስላም የተመለሰበት ጊዜው ቅርብ ቢሆንም የስራው ብይን እላዩ ላይ መበ፞የኑ ተስማሚነት ይኖረዋል፤ ከላዩ ላይ መሀይምነቱን የምታነሳለት ሑጃ ያልደረሰችው ሰው ሙስሊሞች ሀገር ቢኖርም እሱ ላይ የስራው ብይን ቢበ፞የ፞ን ተስማሚነት አይኖረውም።» (አል ዑመይሪ)

• ይህ መርህ ኢብኑ ተይሚያ ሙኻሊፎች ጋር ተዓሙል ለማድረግ እንዲሁም የፈላሲፋዎችንና የዒልመል ከላም ሰዎችን ንግግሮች ለማፈራረስ የሚደገፍበት ጠንካራ የሆነ መሰረት ነው። ከዚህም የተነሳ ብዙ ቦታዎች ላይ በተደጋጋሚ ሲያወሳው ይታያል።

ከዲናዊ ጉዳይ መሆናቸው በግልፅ የሚታወቁ ነገሮች እንደየሰዎቹ ሁኔታ ግልፅነታቸው ሊለያዩ የሚችሉ አንፃራዊ ጉዳዮች መሆናቸውንም ብዙ ጊዜ ደጋግሞ ይናገራል።
ለምሳሌ ያህል እንዲህ ይላል፦

«فكونُ الشيء معلومًا من الدين ضرورةً أمرٌ إضافيٌّ ، فحديث العهد بالإسلام ، ومن نشأ ببادية بعيدة : قد لا يعلم هذا بالكلية ، فضلا عن كونه يعلمه بالضرورة . وكثير من العلماء يعلم بالضرورة أن النبي صلى الله عليه وسلم سجد للسهو ، وقضى بالدية على العاقلة ، وقضى أن الولد للفراش ، وغير ذلك مما يعلمه الخاصة بالضرورة ، وأكثر الناس لا يعلمه ألبتة» (مجموع الفتاوى: 13/118)

«አንድ ነገር በግልፅ የሚታወቅ ዲናዊ ጉዳይ መሆኑ፤ ይህ አንፃራዊ ነገር ነው። ምክንያቱም አዲስ ሰለምቴ ወይም (ከዒልምና ከዑለማእ) ራቅ ያለ መንደር ያደገ ሰው ጉዳዩን በግልፅ ሊያውቀው ይቅርና ጭራሽ ሙሉ በሙሉ ላያውቀው ሁሉ ይችላልና። ነቢዩ ﷺ የእርሳና ሱጁድ መስገዳቸውን፣ የገዳይ አባት ወገኖች የሟችን ካሳ እንዲከፍሉ መወሰ፞ናቸውን፣ የዝሙት ልጅ ልጅነቱ በዝሙት ለወለደው ወላጁ ሳይሆን ዝሙተኛዋ ሴት ባለትዳር ከሆነች ለባሏ፤ ባሪያ ከሆነች ደግሞ የአሳዳሪዋ መሆኑን መወሰናቸውንና አዋቂዎች በግልፅ የሚያውቋቸው የመሳሰሉትን ነገሮች *ብዙዎቹ* ዑለማኦች ቢያውቋቸውም *አብዛኛዎቹ* ሰዎች ግን ፈፅሞ አያውቋቸውም።» (መጅሙዑል ፈታዋ: 13/118)

ኢብኑ ተይሚያ ረሕመቱላሂ ዐለይህ እዚህ መሰረት ላይ መደገፊያውን በግልፅ አብራርቷል፤ እሱም የግንዛቤ መገለጫዎች፦ እንደ እውቀት፣ መሀይምነት፣ እርግጠኝነት፣ ወደ እርግጠኝነት አመዛኝ የሆነ ግምት፣ ግልፅ መሆንና ድብቅ መሆን የሚባሉ መገላጫዎች፦ አጠቃላይ ነገሮች ላይ የቆሙና እላያቸው ላይ የሚገኙ ባህሪያት አለመሆናቸውን፤ እንዲሁም ከነገሮቹ የማይነ፞ጠሉና የማይለ፞ዩ እንዳልሆኑም ገልፇል፤ ይልቁንም ስለ ነገሮች ምንነት ተገንዛቢ በሆኑ ነፍሶች ውስጥ የቆሙና የሚገኙ ባህሪያት ናቸው፤ አንድ ነገር ዐምር የተባለ ግለሰብ ዘንድ የተረጋገጠና በግልፅ የሚታወቅ ጉዳይ ሊሆን ይችላል፤ እንዲህ አድርጎ እንዲገነዘብ የሚያስችሉት አስባቦች በመገኘታቸው ምክንያት ማለት ነው። ነገር ግን ዘይድ የተባለ ሰው ዘንድ ጉዳዩ "መዝኑን" አጠራጣሪ ወይም ለእርግጠኝነት ቀረብ ያለ ግምታዊ ጉዳይ ሊሆን ይችላል፤ እሱም እንዲህ አድርጎ እንዲገነዘብ የሚያስችሉት አስባቦች በመገኘታቸው ምክንያት ነው። (የኢብኑ ተይሚያን መጅሙዑል ፈታዋ: 19/211) ላይ ተመልከት።

-----➦-----➦------➦------➦------➦-----

#ወደ ገፅ -❻-ይሸጋገሩ።

አል-በያን البــيان

11 Oct, 20:10


#ገፅ -❹- ክፍል➊➐ ቁጥር❾
----------------------__-----------------------

فان من رأى الأمور الموجودة في مكانه وزمانه كانت عنده من الحِسِّيَّات المُشاهَدات، وهي عند مَن عَلِمَها بالتواتر من المتواترات، وقد يكون بعضُ الناس إنما عَلِمَها بخبرٍ ظنٍّيٍّ فتكون عنده من باب الظنِّيات؛ فان لم يسمعها فهي عنده من المجهولات، وكذلك العقليات، فان الناس يتفاوتون في الإدراك تفاوُتًا لا يكادُ يَنضبِطُ طَرَفَاه، ولِبَعضِهم مِن العلم البَديهي عنده والضروري ما يَنفِيه غيرُه أو

يشكُّ فيه، وهذا بَيِّنٌ في التصورات والتصديقات». (الرد على المنطقيِّين: 13_ 14)


«አንድ የሆነ ነገር እንዲሁ "በዲይሂየ፞ን" በቀላሉ መታወቁ ወይም "ነዞሪየ፞ን" ማለትም በቲዮሪቲካል ስለ ጉዳዩ ግራ ቀኙን ተመልክተን ወይም ሌሎች ነገሮችን ካገላበጥን በኋላ የሚታወቅ መሆኑ፤ ይህ "ኒስቢይ" ወይም አንፃራዊ ከሆኑ ጉዳዮች ነው። ለምሳሌ ጉዳዩ የተረጋገጠ ወይም ወደ እርግጠኝነት ያደፋ፞ ግምታዊ የሆነ ሊሆን ይችላል፤ ምክንያቱም ዘይድ (የተባለ ሰው) እርግጠኛ የሆነበትን ጉዳይ፤ ዐምር እርግጠኛ ላይሆንበት ይችላል፤ ሌሎች ሰዎች ነገሮችን አገላብጠውና ተመልክተው እንጂ የማያውቁትን ሀሳብ ዘይድ እንዲሁ በቀላሉ ሊያውቀው ይችላል።

الفوائد السلفية, [8/23/22, 2:56 PM]
[Posted by بن أحمد]
ዘይድ ዘንድ በተጨባጭ የሚታወቀው ነገር ዐምር ዘንድ ላይታወቅ ይችላል።
በግልፅ የሚታወቀውም ይሁን፤ ተፈልጎ የሚገኘው፤ በቀላሉ የሚገነዘቡትም ይሁን፤ ነገሮችን ተመልክተው የሚገነዘቡት አንድ የሆነ የተወሰነ እውቀት፦ ሁሉም ሰው በተመሳሳይ የግንዛቤ ደረጃ የሚጋ፞ራ፞ባ፞ቸውና ከሰዎቹም የማይነጠሉ እንደውም ሰዎቹ ጋር ተጣብቀው የሚገኙ አድርገው ብዙዎቹ ሰዎች ይህን መገመታቸው፦ ይህ ከባድ  ሆነ ስህተት ከመሆኑም በላይ ከነባራዊው እውነታ ጋር የሚቃረን ነገር ነው።
ባለበት ቦታና ጊዜ የሚገኙ ነገሮችን በአይኑ የተመለከተ ሰው፤ እነኚህ ነገሮች እሱ ዘንድ በተጨባጭ ያገኛቸውና የሚያውቃቸው ይሆናሉ፤ እነኚህን ነገሮች ከተመለከቱ ከሙተዋቲሮች ወይም ከበርካታ የመረጃ ምንጮች በመነሳት ያወቃቸው ሰው ዘንድ ደግሞ ከሙተዋቲራት ይሆናሉ፤ ማለትም ከማይጠራጠርባቸው በርካታ ምንጮች የተገኙ እውቀቶች ተደርገው ይታሰባሉ፤
አንዳንዱ ሰው ደግሞ ነገሮቹን እርግጠኛ ባልሆነበት መንገድ ብቻ አውቋቸው፤ እሱ ዘንድ ከዘንኒያት ወይም እርግጠኛ ካልሆነባቸው እውቀቶቹ ተደርገው ይቆጠራሉ፤ ስለ ነገሮቹ ያልሰማ (እና መረጃው ያልደረሰው) ሰው ደግሞ ፦ እሱ ዘንድ ከመጅሁላት ወይም ከማያውቃቸው ጉዳዮች ይሆናሉ ማለት ነው።
በአእምሯዊ እውቀቶችም ያለው ሂደት እንደዚሁ ነው። ምክንያቱም ሁለቱ ወገኖች ለመጣጣም በማይቀርቡበት መልኩ በአገነዛዘባቸውና በአመለካከታቸው ከፍተኛ የሆነ መለያየትን ይለያያሉ።  ከፊሉ ሰው ዘንድ በቀላሉ የሚታወቅና በጣም ግልፅ የሆነ ጉዳይ ተደርጎ የሚታየው ነገር፤ ሌላው ሰው ዘንድ የሚያወግዘው ወይም የሚጠራጠርበት ጉዳይ ሆኖ ሊገኝ ይችላል። ይህ በተሶውራቶችና በተስዲይቃት ጉዳዮች ላይ በግልፅ የሚታይ ነገር ነው»

የዚህ መሰረታዊ ጉዳይ ጥቅል ሀሳብ እንደሚከተለው ይገለፃል፦

•የተወሰኑ ማህበረሰቦች ዘንድ፣ ወይም የሆኑ አካባቢዎች ወይም ዘመናቶች ላይ አንድ የሆነ ነገር ዟሂር የሆነ ጉዳይ መሆኑ፦ ሁሉም ሰዎች ዘንድ እንዲሁም ሁሉም ቦታዎችና ዘመናቶች ላይ ግልፅ መሆኑን አያስይዝም።

•የሶላት ዋጅብነት በሆነ ቦታ፣ በተወሰነ ዘመንና የተወሰኑ ጀማዓዎች ዘንድ በግልፅ የሚታወቅ ጉዳይ መሆኑ፦ ሁሉም ቦታዎችና ዘመናት ውስጥ እንዲሁም እያንዳንዱ በኢስላም ጥላ ስር የሚገኝ አካል ዘንድ ግልፅ የሆነ ነገር መሆኑን አያስፈርድም።

•በሞቱ ሰዎችና በመቃብሮች እስቲጛሣ ማድረግ ሐራምነቱና ሺርክነቱ የተወሰኑ ጀማዓዎች በማይጠራጠሩበት መልኩ እነሱ ዘንድ ግልፅ መሆኑ፦ የዚህ ፀያፍ ተግባር ሑክም ሁሉም ሰዎች ዘንድ፣ በሁሉም ቦታዎችና ዘመናት ግልፅ መሆኑን አያስይዝም።

ይህን በተመለከተ ኢብኑ ተይሚያ ዐለይሂ ረሕመቱላህ (መጅሙዑል ፈታዋ: 23/347፣ 19/211) ላይ እንዲህ ይላል፦

«وكونُ المسألةِ قطعيَّة أو ظنيَّة هو مِن الأمور الإضافية، وقد تكون المسألة عند رجلٍ قطعيةً لِظُهور الدليل القاطع له، كمن سمع النصَّ من الرسول، وتيقَّن مُرادَه منه، وعند رجلٍ لا تكون ظنية، فضلاً عن أن تكون قطعية؛ لِعَدَمِ بُلوغِ النصِّ إيَّاه، أو لِعدَمِ ثُبُوتِه عنده، أو لِعَدَمِ تَمَكُّنهِ من العلم بدلالته» (مجموع الفتاوى: (23/347) (19/211)

«አንዲት የሆነች መስአላህ "ቀጥዒያ" (እርግጠኛና ቆራጭ የሆነች መሆኗ) ወይም "ዞንኒያ" (ወደ እርግጠኝነት አመዛኝ የሆነ ግምት) መሆኗ ይህ አንፃራዊ ከሆኑ ጉዳዮች ነው። አንድ ሰው ቆራጭ የሆነ መረጃ ስለተገለፀለት መስአላዋ እሱ ዘንድ "ቀጥዒይያ" ልትሆንለት ትችላለች፤ ለምሳሌ ሰውየው ከመልእክተኛው ﷺ መረጃን ሰምቶና በመረጃው የተፈለገበትን ሀሳብ በደንብ በመገንዘቡ ምክንያት (መስአላዋ እሱ ዘንድ የተረጋገጠች ልትሆን ትችላለች)፤ ሌላው ሰው ደግሞ መረጃው ስላልደረሰው፤ ወይም የሠበ፞ተ (የፀደቀ) አድርጎ ስለማያየው፤ አሊያም ደግሞ የጉዳዩን ሀሳብ በመረጃ ለመገንዘብ የማይችል በመሆኑ ምክንያት ይህ ሰውየ ዘንድ መስአላዋ "ቀጥዒያ" መሆኗ ይቅርና "ዞንኒያም" ላትሆን ትችላለች።»

✍️ ይህን መሰረሰታዊ ጉዳይ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ በተክፊርም ሆነ በሌሎች መስአላዎች ላይ በርካታ ንግግሮቹን ለመገንባት ተጠቅሞበታል።

በዚህ ዙሪያ ከተናገራቸው በርካታ ንግግሮች አሳሳቢ የሆነው ንግግሩ ላይ እንዲህ ይላል፦

«وقد يُنْكِر أحدُ القائلين على القائلِ الآخر قولَه إنكارًا يجعلهُ كافرًا أو مبتدعًا فاسقًا يستحق الهجرَ وإن لم يستحق ذلك.
وهو ـ أيضا ـ اجتهاد .
وقد يكون ذلك التغليظ صحيحا في بعض الأشخاص أو بعض الأحوال لظهور السنة التي يكفر من خالفها؛ ولِما في القول الآخر من المفسدة الذي يبدع قائله؛ فهذه أمور ينبغي أن يعرفها العاقل؛ فإن القول الصدق إذا قيل : فإن صفته الثبوتية اللازمة أن يكون مطابقا للمخبر .
أما كونه عند المستمع معلوما، أو مظنونا، أو مجهولا، أو قطعيا، أو ظنيا، أو يَجِب قبوله، أو يحرم، أو يكفر جاحده، أو لا يكفر : فهذه أحكام عملية تختلف باختلاف الأشخاص والأحوال .

----------------------🔜-----------------------

#ወደ ገፅ-❺- ተሸጋገሩ።↩️

አል-በያን البــيان

11 Oct, 20:01


#ገፅ-❸- ክፍል ➊➐ ቁጥር ❾
--------------------__---------------------

فأجاب ابن تيمية: «الحمد لله رب العالمين من استغاث بميت أو غائب من البشر بحيث يدعوه في الشدائد والكربات ويطلب منه قضاء الحوائج فيقول: يا سيدي الشيخ فلان أنا في حسبك وجوارك أو يقول عند هجوم العدو: يا سيدي فلان يستوحيه ويستغيث به أو يقول ذلك عند مرضه وفقره وغير ذلك من حاجاته: فإن هذا ضال جاهل مشرك عاص لله تعالى باتفاق المسلمين فإنهم متفقون على أن الميت لا يدعى ولا يطلب منه شيء

الفوائد السلفية, [8/23/22, 2:56 PM]
[Posted by بن أحمد]
سواء كان نبيا أو شيخا أو غير ذلك ..وهذا الشرك إذا قامت على الإنسان الحجة فيه ولم ينته وجب قتله كقتل أمثاله من المشركين ولم يدفن في مقابر المسلمين ولم يصلَّ عليه وأما إذا كان جاهلا لم يبلغه العلم ولم يعرف حقيقة الشرك الذي قاتل عليه النبي صلى الله عليه وسلم المشركين فإنه لا يُحكم بكفره ولا سيما وقد كثر هذا الشرك في المنتسبين إلى الإسلام ومن اعتقد مثل هذا قربة وطاعة فإنه ضال باتفاق المسلمين وهو بعد قيام الحجة كافر ». ]
جامع المسائل (3/145 – 151)


«መሻዪኾችን ስለሚያልቁ፣ በመከራዎች ጊዜ በእነሱ ኢስቲጛሣ ስለሚያደርጉ፣ ለእነሱም የሚዋደቁ፣ መቃብሮቻቸውንም የሚዘይሩና የሚስሙ፤ ከአፈሩም በረካ የሚፈልጉ ስለሆኑ ሰዎች የዲኑ መሪዎች ዑለማኦቻችንና አለቆቻችን ምን አይነት ብይን ይሰጣሉ» በሚል *ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ* ተጠየቀ

*ኢብኑ ተይሚያም* እንዲህ በማለት መልስ ሰጠ:

«ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው፤ በሞተ ወይም ህያው ሆኖ ነገር ግን ሩቅ ስፍራ ባለ ሰው ኢስቲጛሣ የሚያደርግ፤ ማለትም በመከራዎችና አስጨናቂ በሆኑ ክስተቶች ሐጃዎቹን እንዲፈፅምለት:
" ያ ሰይዪዲ ሸህ እገሌ ሆይ! እኔ በአንተ ጥበ፞ቃና መብቃት ውስጥ ነኝ" በማለት የሚለምን ሰው፤ ወይም ጠላት ሊያጠቃው ሲከብበው፣ ወይም ህመም ሲደርስበት፣ ወይም ደግሞ ድህነት ሲያገኘው "ያ ሰይዪዲ ፉላን ··· " እያለ ኢስቲጛሣ የሚያደርግ ይህ አይነቱ ሰው በሙስሊሞች ስምምነት፦ ዿል፣ጃሂል፣ሙሽሪክና አላህን ያመፀ ነው።
ምክንያቱም የሞተ ሰው ነቢይም ሆነ ሸይኽ ወይም ሌላ የሆነ ይሁን እንደማይለመንና ከእሱም ምንም አይነት ሓጃ እንደማይፈለግ ሙስሊሞች ስምምነት አላቸው። *ይህ አይነቱን ሺርክ የፈፀመ ሰው ሑጃ ከቆመበትና መረጃ ደርሶት ካለበት ተግባር ካልታቀበ* የእሱ አምሳያ ሙሽሪኮች እንደሚገደሉት እሱንም መግደል ግድ ነው፤ ሙስሊሞች መቃብር አይቀበርም፤ አይሰገድበትምም።
ነገር ግን *እውቀት ያልደረሰው ጃሂል የሆነ ሰው ከሆነና ነቢዩ ﷺ ሙሽሪኮችን የተጋደሉበትን ሺርክ ሐቂቃውን የማያውቅ ከሆነ፤ ይህ አይነቱ ሰው ካፊር ተብሎ አይተሓከምበትም*
በተለይ ይህ አይነቱ ሺርክ ራሳቸውን ወደ ኢስላም የሚያስጠጉ የሆኑ ሰዎች ውስጥ በብዛት እየተከሰተ ባለበት ወቅት (ካፊር ሙሽሪክ እያሉ ከኢስላም የሚወጣበት በሆነ ብይን አይበየንበትም)።
ይህ አይነቱን የሺርክ ተግባር ኸይር ስራና ወደ አላህ መቃረቢያ አድርጎ ኢዕቲቃድ የሚያደርግ ወይም የሚያምን ሰው በሙስሊሞች ስምምነት፦ ዿል ነው፤ *ሑጃ ከደረሰውም በኋላ ካፊር ይደረጋል* » (ጃሚዑል መሳኢል:3/145 _ 151)

ስለ ሸይኸል ኢስላም ለመቆያ ያህል ይህን ካየን ወደዚያኞቹ እንመለስ።
ከላይ እንዳሳለፍነው እነዚያ አካላት በሺርክ ጉዳዮች ዑዝር ቢል ጀህል የለም ለማለት መስአላ ዟሂራንና ኸፊያን በመለያየት ላይ መደገፋቸው ትክክል አይደለም፤ ስህተት ነው። የስህተቱ መንስኤም፦ ወደ መስአላዋ በሚመለሰው ነገር መካከልና አቅማዳም የደረሰ ሰው በመስአላዋ ላይ ሊኖረው ወደሚችለው የእውቀት መጠን መካከል አለመለየ፞ታቸው ነው።

👌እርግጥ ነው ሸሪዓዊ ጉዳዮች በቀድር፣ በደረጃ፣ ይበልጥ በመታወቅና ባለመታወቅ አንድ አይነት መጠን የላቸውም። ይልቁንም ከፊሉ ከከፊሉ ከፍ ያለ አለ፤ ከፊሉ ደግሞ ከከፊሉ ይበልጥ የሚታወቅና በሙስሊሞች መሀል ተሰራጭቶ የሚገኝ ከመሆኑ የተነሳ ከኢስላማዊ ጉዳዮች መሆኑ አብዛኞች ዘንድ በግልፅ የሚታወቅ የሆነ አለ።

ነገር ግን ሁሉም ሙስሊሞች ስለነዚህ ጉዳዮች ትክክለኛ ምንነትና ስለ ብይናቸው እኩል የእውቀት ደረጃና ተመሳሳይ የማስታወስ ብቃት ያላቸው መሆኑን አያስይዝም።
በአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ዲን ውስጥ ያለች አንዲት ዟሂራ የሆነች መስአላ በአንዳንድ ሙስሊሞች ላይ ሑክሟ ሊደበቅባቸው ይችላል።
ምክንያቱ ደግሞ የሰዎች ግንዛቤ ከነገሮች ጋር ወዳለው ትስስራዊ ባህሪ ይመለሳል።

የግንዛቤ መገለጫዎች፦ እንደ እውቀት፣ መሀይምነት፣ እርግጠኝነት፣ ግምት፣ አእምሮ በቀላሉ የሚ፞ረ፞ዳ፞ው፣ የማይረ፞ዳ፞ው፣ ግልፅ መሆን፣ ድብቅ መሆንና የመሳሰሉት መገላጫዎች፦ አጠቃላይ ነገሮች ወይም መሳኢሎች ላይ የቆሙና እላያቸው ላይ ተጣብቀው የሚገኙ ባህሪያት አይደሉም፤ እንዲሁም ከነገሮቹ የማይነ፞ጠሉና የማይለ፞ዩ የሆኑም አይደሉም፤ ይልቁንም ስለ ነገሮች ምንነት ተገንዛቢ በሆኑ ነፍሶች ውስጥ የቆሙና የሚገኙ ባህሪያት ናቸው። ማለትም በሰው ልጆች ላይ የሚገኙ እንጂ መስአላዋ ላይ ተለጥፈው ያሉ ወይም ወደሷ የሚመለሱ አይደሉም። ሰዎች ደግሞ በእውቀቶቻቸውና በግንዛቤዎቻቸው የሚ፞ለያዩና የሚበ፞ላለጡ መሆናቸው የማያጠራጥር እውነታ ነው። ለዚህም ነው እነኚህ ባህሪያት ሰዎች በብዛት ከሚለያዩባቸው አንፃራዊ ከሆኑ ነገሮች የሆኑት።

ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ "አር ረዱ፞ ዐለል መንጢቂዪይን: 13_14) ላይ ይህን ሀሳብ ሲያብራራ እንዲህ ይላል፦

«كَونُ العلمِ بَديهيًّا أو نظريًّا هو مِن الأُمُور النِّسْبِيِّة الإضافية مثل كون القضيَّة يَقِينيَّة أو ظَنِّيَّة؛ إذ قد يَتيقَّنُ زيدٌ ما يظنُّه عمرٌو، وقد يبده زيدا من المعاني ما لا يعرفه غيره إلا بالنظر، وقد يكون حِسِّيًّا لزيدٍ من العلوم ما هو خبريٌّ عند عمرو.
وإن كان كثير من الناس يحسب أنَّ كونَ العلم المعيَّن ضروريًّا أو كسبيًّا أو بديهيًّا أو نظريًّا هو من الأمور اللَّازمة له بحيث يشترك في ذلك جميعُ الناس وهذا غلطٌ عظيمٌ وهو مخالف للواقع.

-----------------------🔜-------------------------

#ወደ ገፅ -❹-ተሸጋገሩ።↩️

አል-በያን البــيان

03 Oct, 11:11


#ገፅ -➋- ክፍል ➊❻ ቁጥር ❾

📌 ሸይኽ ሙላ ዐሊይ ቃሪእንና አል ኢማም ሺሃቡዲን አልቀራፊን የመሳሰሉ የአራቱ መዝሀብ ተከታይ የሆኑ ዑለማኦች፦ "ከኢስላማዊ ጉዳዮች መሆናቸው በግልፅ የሚታወቁ ነገሮችን የሚቃረን ሰው ዑዝር ቢል ጀህል እንደማይሰ፞ጠ፞ው የገለፁ መሆናቸውን፤ እንዲሁም እነኚሁ መሻዪኾች መስአላ ዟሂራንና መስአላ ኸፊያን ለያይተው እንደሚያዩ የ(ዓሪዹል ጀህል) ባለቤት አቡል ዑላ አራሺድ እዚሁ ኪታቡ ላይ ገልፇል።

الفوائد السلفية, [8/23/22, 2:56 PM]

«የአምስት አውቃት ሰላቶችን ግዴታነት ያላመነ፣ ፈርድ የሆነውንም ዘካ ዋጅብነት፣ የረመዿን ወር ፆምን ግዴታነትና ጥንታዊውን ቤት መጎብኘት ዋጅብ መሆኑን ያላመነ ሰው፤ እንዲሁም፦ ዙልም፣ ሺርክ፣ ቅጥፈትና የመሳሰሉት አላህና መልእክተኛው ሐራም ያደረጓቸው ነገሮችን ሐራም አድርጎ የማያምን ከሆነ፤ ይህ ሰው ካፊርና ሙርተድ ነው፤ ተውበት ይጠየቃል፤ ከቶበተ ጥሩ፤ ካልሆነ ግን በአኢመቱል ሙስሊሚን ስምምነት ይገደላል። ላ ኢላሀ ኢለ፞ሏ፞ህ፤ ሙሐመዱን ረሱሉላህ ማለቱ አይጠቅመውም»

📋እነሱ እንደሚሉት ኢብኑ ተይሚያ በዚህና በመሳሰሉት ንግግሮቹ "የሺርክ ተግባራትን የሰራ ሰው ካፊር ነው" በማለት በጥቅል በይኗል፤ በእነዚህ ነገሮች ላይ ለጃሂል ዑዝር መስጠት እምነቱ ቢሆን ኖሮ "ጃሂል ሲቀር" በሚል ከጥቅል ብይኑ ያወጣው ነበር። በዚህ ዙሪያ አቡ ቡጠይን መላኢካዎችን የተገዛ ሰው ካፊርነቱን የበየነበትን የሸይኸል ኢስላምን ንግግር ሲያብራራ እንዲህ ይላል ፦

📑(فانظر قوله: «فهو كافرٌ بإجماع المسلمين»، فحكم بكفر من هذه حاله، وأنه إجماع المسلمين، ولم يقل في هذا الموضع لم يمكن تكفيره بذلك حتى يبين له ما جاء به الرسول، وقوله: «فمن جعل الوسائط على هذا الوجه فهو كافر مشرك يجب قتله» فجزم بكفره قبل الاستتابة) (فتاوى الأئمة النجدية: 3/307)

[«እሱ በሙስሊሞች ስምምነት ካፊር ነው» ማለቱን ተመልከት፤ እንደምታየው ባህሪው ይህ የሆነን ሰው በኩፍር ሀክሞበታል፤ በዚህም ላይ ሙስሊሞች ኢጅማዕ እንዳላቸው ገልፇል።  እዚህ ቦታ ላይ «መልእክተኛው ይዘው የመጡት እስኪገለፅለት ወይም ሑጃ እስኪቆምበት ድረስ ይህን በማድረጉ ብቻ ሰውየውን ማክፈር አይቻልም» አላለም። «በዚህ መልኩ አቃራቢዎችን የያዘ ሰው ካፊር ነው ሙሽሪክም ነው፤…» በማለት የተናገረውንም ተመልከት፤ ተውበት ሳይጠየቅ በፊት ካፊርነቱን ቁር፞ጥ፞ አድርጎ ነው የበየነበት።] (ፈታዋ አል አኢማህ አን ነጅዲያ: 3/307)

📋በተጨማሪም የሰሪው ሁክምና የስራው ሁክም ኢብኑ ተይሚያ ዘንድ ተለያይቶ የሚታየው በመሳኢል ዟሂራ ሳይሆን በመሳኢል ኸፊያ ብቻ መሆኑን በርካታ የነጅድ ዑለማና አኢማዎች ገልፀዋል። በዚህ ዙሪያ *ዐብደላህና ኢብራሂም የተባሉ የሸይኽ ዐብደለ፞ጢፍ ልጆችና ሱለይማን ኢብኑ ሰሕማን*  በአንዳንድ ሙኻሊፎች ላይ ረድ ሲያደርጉ (አድ ዱረር አስ ሰኒያ:10/432) ላይ እንዲህ ብለዋል፦

«وأما قوله: "نقول بأن القول كفرٌ، ولا نحكم بكفر القائل"؛ فإطلاق هذا جهل صِرفٌ، لأن هذه العبارة لا تنطبق إلا على معين، ومسألة تكفير المعين مسألة معروفة إذا قال قولاً يكون به كفراً، فيقال: من قال بهذا القول فهوا كافر، لكن الشخص المعين إذا قال ذلك لا يحكم بكفره حتى تقام عليه الحجة التي يكفر تاركها، وهذا في المسائل الخفية التي قد يخفى دليلها على بعض الناس، كما في مسائل القدر والإرجاء ونحو ذلك مما قاله أهل الأهواء، فإن بعض أقوالهم تتضمن أموراً كفرية، من رد أدلة الكتاب والسنة المتواترة، فيكون القول المتضمن لرد بعض النصوص كفراً، ولا يحكم على قائله بالكفر، لاحتمال وجود مانع كالجهل» (الدرر السنية: 10/432)

[«ንግግሩ ኩፍር ነው እንላለን፤ ተናጋሪው ላይ ግን በኩፍር አንሐክምበትም» የሚለው አባባሉን በልቅ መናገሩ፦ ጥር፞ት፞ ያለ ጅህልና ነው፤ ምክንያቱም ይቺ አባባል ከሙዐየ፞ን ወይም ተነጥሎ ከሚተሓከምበት ሰው ጋር እንጂ ተዛማጅነት የሌላት ናትና። አንድን ሰው ነጥሎ በተዕዪይን ስለ ማክፈር የምታጠነጥነው መስአላ ደግሞ ታዋቂ የሆነች መስአላ ናት፤ ሲናገሩት ኩፍር የሚሆንን ንግግር አንድ ሰው ከተናገረው፤ ይህን ንግግር የተናገረ ሰው (በኢጥላቅ) ካፊር ነው ይባላል። አንድን ሰው ነጥለን ለማክፈር ግን የሚተዋት ሰው ካፊር የሚደረግባት ሑጃ እስካልቆመችበት ድረስ በካፊርነት አይበየንበትም።
ይህም የሚሆነው መረጃዎቿ በአንዳንድ ሰዎች ላይ ልትደበቅባቸው ወይም ግልፅ ላትሆንላቸው በምትችል በመስአላ ኸፊያ ነው። አህሉል አህዋእ በቀደር፣ በኢርጃእና በመሳሰሉት መሳኢሎች እንደተናገሯቸው ያሉ ንግግሮች ማለት ነው። ምክንያቱም እነዚህ አካላት ከፊል ንግግሮች ውስጥ የቁርኣንና ሙተዋቲር የሆኑ የሐዲሥ ማስረጃዎችን የሚመልሱበት ወይም የሚያስተባብሉበት ኩፍር የሆኑ አባባሎች ስለሚገኙ ነው። ስለዚህ አንዳንድ መረጃዎችን መመለስን አካትቶ የያዘው ንግግራቸው ኩፍር ቢሆንም በተናጋሪው ላይ ግን የኩፍር ብይን አይበየንበትም፤ ምክንያቱም፦ ሰውየው በተዕዪይን ተለይቶ እንዳይከፈር የሚከለክሉ ጅህልና እና የመሳሰሉት ከልካይ ነገሮች ሊኖሩ ስለሚችሉ ነው።»

🩸🩸🩸

መስአላውን ወደ ኢብኑ ተይሚያ ማስጠጋታቸው ትክክል አለመሆኑን ወደፊት ኢንሻአላህ  ራሱን በቻለ ርዕስ እንመለስበታለን፤ ለጊዜው እንደ ጥቅል በሺርክ ጉዳዮች ዑዝር ቢል ጀህል የለም ለማለት መስአላ ዟሂራንና ኸፊያን በመለያየት ላይ መደገፋቸው ትክክል አለመሆኑን ከማየታችን በፊት፤ *ሸይኸል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ* ዘንድ ሰውን ለማክፈር ወሳኙ ነገር ሰውየው የወደቀበት ሺርክ መስአላ ዟሂራ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ሳይሆን፤ ሰውየው ሑጃው ደርሶታል ወይም አልደረሰውም የሚለው ጉዳይ እንደሆነና፤ እሱ ዘንድ የማክፈሪያ መወጠኛውና ማሰሪያው ይህ መሆኑን እንመለከታለን። ለዚህ ደግሞ የሸይኹን አቋም የሚገልፁ በርካታ ንግግሮች ቢኖሩም ወደ ፊት ሰፋ ባለ ሁኔታ እስከምናያቸው ድረስ ለዛሬ አንዱን ፍንትው ያለ ፈትዋውን ብቻ ላስነብባችሁ።

📌 እንደሚታወቀው ከአላህ ውጪ እሱ እንጂ ማንም በማይችለው ጉዳይ በሙታኖችም ሆነ ህያው በሆኑ አካሎች ኢስቲጛሣ ማድረግ ከኢስላም የሚያስወጣ መስአላ ዟሂራ የሆነና ትልቅ የሆነ ሺርክ ነው፤ ከመሆኑም ጋር ሰዎች ሑጃ ሳይደርሳቸው ባለማወቅ ይህ አይነት ሺርክ ውስጥ የሚወድቁ ከሆነ እንደማይከፈሩና ሑጃ ከደረሳቸው በኋላ ግን እንደሚከፈሩ የተናገረበት ሁኔታ አለ።

📋ሸይኸል ኢስላም ተጠየቀ:-
[سئل شيخ الإسلام بن تيمية رحمه الله  : ما تقول السادة العلماء أئمة الدين ـ رضي الله عنهم أجمعين ـ في قومٍ يعظِّمون المشايخ بكون أنهم يستغيثون بهم في الشدائد ويتضرعون إليهم ويزورون قبورهم ويقبلونها وتبركون بترابها …

------------
#ወደ ገፅ -➂- ይሸጋገሩ።↩️

አል-በያን البــيان

03 Oct, 09:06


ገፅ -➊- ክፍል ➊➎ ቁጥር ❾

بســـم الله الرحمن الرحيم
الحمد لله وحده، والصلاة والسلام على من لا نبي بعده، وبعد:


📋ኡዝር ቢል ጀህል ክፍል 1⃣5⃣
-----------
📌 #የተንጠልጣዮች ሁነኛ ምሽግ ወደሆነው መሳኢል ዟሂራ እና መሳኢል ኸፊያ  ማብራሪያና ሹበሀ

#ቁጥር ❾
🩸🩸

ኢኽዋኒ ወአኸዋቲ! ለዛሬ ይዤላችሁ የቀረብኩት፦

➡️ባለማወቅ ሺርክ ላይ የወደቀ ሙስሊምን ዑዝር ቢል ጀህል ለመንፈግና ከኢስላም ለማስወጣት ተክፊሮችና መሰ፞ሎቻቸው ከሚንጠለጠሉባቸው ነገሮች ከባድ መንጠልጠያና ሁነኛ ምሽግ አድርገው በሚያስቡት መደበቂያቸው ዙሪያ ነው።

እሱም ፦ በመሳኢል ዟሂራ እና መሳኢል ኸፊያ መካከል መለያየታቸው ነው።

📌የፅሁፉ መሰረት ሱዑዲያዊው ሸይኽ የሆነው ሱልጧን ቢን ዐብዲረሕማን አል ዑመይሪ ያዘጋጀው *«ኢሽካሊየቱ አል ኢዕዛር ቢል ጀህል ፊል በሕሥ አልዐቀዲይ»* (319_330) የተሰኘው ጥናታዊ ኪታብ ነው።

በዚሁ አጋጣሚ፤ ኪታቡ እጅግ በጣም የተዋጣለት በመሆኑ ዐረብኛ መረዳት የሚችል እያንዳንዱ ሙስሊም ሰለፊዩም ሆነ ተክፊይሪዩ፣፣፣ እንዲያነቡት እመክራለሁ።

👌የዛሬው ፅሁፍ በቅድሚያ መስአላ ዟሂራና ኸፊያ የሚሏቸው ነገሮች ምንና እነማን እንደሆኑ ያትታል፤ ከዚያም በመስአላ ኸፊያ እንጂ በመስአላ ዟሂራ ዑዝር እንደማይሰ፞ጥ፞ የተናገሩ ዑለማኦች ንግግር ተወስቶበታል፤ እንዲሁም ሁለቱን መስአላዎች በመለያየት ዑዝርን ውድቅ ማድረግ ትክክል እንዳልሆነ ሰፋ ባለ መልኩ የተዳሰሰበት ረዘም ያለ ፅሁፍ ነው።

ስለዚህ ወንድሜ አንብብ፤ ተገንዘብ፤ ተጠቀም፤ እራስህንም አድንና ለሌሎችም መዳን ሰበብ ሁን!!

📌በእርግጥ ዛሬ ላይ ያለ፞ ትውልድ ብዙው ማለት ይቻላል የሂማ፞ ጉዳይ ሆኖ አጫጭር ፖስቶችንና ተጝሪዳቶችን እንጂ ረጃጅም ለሆኑ ዲናዊ ፅሁፎች ትኩረቱን ሰጥቶ ጀምሮ የሚጨርስ መኖሩ አጠያያቂ ሆኗል፤ ማንበብ እንደሚታወቀው ነቢያችን ﷺ ለመጀመሪያ ጊዜ ነቢይ ተደርገው ሊታጩ ሲሉ የታዘዙበት ቁጥር አንድ መለኮታዊ ትእዛዝ ነው። ከሰለፎች አንስቶም እስከ ቅርብ ዘመናት ድረስ ታላላቅ የዲኑ ሰዎች እዚህ ደረጃ የደረሱበትና ዲኑም እኛ ዘንድ የደረሰበት ምክንያት ንባብ ላይ ባላቸው የልፋትና ጥረት ምክንያት ነው።

ተርጓሚው በዚህ የትርጉም ስራው ላይ አንባቢያን በሚፈልጉት መጠንና ደረጃ ያህል ለማቅረብ የማይችል ቢሆንም፤ የአቅሙንና የተቻለውን ለማድረግ ይሞክራል። በዚህም ሆነ በሌላ ምክንያት አብዛኞች ችላ ቢሉትም ዛሬ ላይ አላህ የሻላቸው ይጠቀሙበትና ወደፊት ደግሞ ይበልጥ አንብበው የሚጠቀሙ የሆኑ የተሻሉ ትውልዶች ይፈጠሩ ይሆናል፤ ያንኔ ታድያ ዛሬ የተተከለ ተክል ነው ለእነሱ ከሹቡሃት ሐራራ መጠለያ ወይም ፍሬያማ ሆኖ ሊያገኙት የሚችሉት።

--------------------------------

📌 #ወደ_ዋና_ጉዳዩ_ስገባ


🔖#መሳኢል_ዟሂራ_ማለት፦ ለሁሉም ግልፅ የሆኑ የዲኑ ክፍሎች ሲሆኑ፤ ኸፊያዎቹ ደግሞ ለአንዳንድ ሰዎች ግልፅ ያልሆኑ ኢስላማዊ ጉዳዮች ናቸው።

እንደነሱ አባባል፦ መሳኢል ዟሂራዎቹ ሙስሊሞች መካከል በሰፊው ተሰራጭተው የሚገኙና ከኢስላማዊ ጉዳዮች መሆናቸው በግልፅ የሚታወቅ ስለሆነ፤ ማንኛውም ሰው በየትኛውም ዘመንም ሆነ ቦታ ይኑር፤ በጀህልም ሆነ በተእዊል ዑዝር አይሰ፞ጥ፞ባ፞ቸውም።

📌#መሳኢል_ዟሂራ ከሚባሉት ውስጥ ለምሳሌ ያህል፦ ከተውሒድ አል ኡሉሂያና አር ሩቡቢያ ጋር ትስስር ያላቸው መሳኢሎች፣ ከትልቀኛው ሺርክ ጋር የሚያያዙ መሳኢሎች፣ ከኢስላማዊ ጉዳዮች የሚካተቱ መሆናቸው በገሃድ የሚታወቁ፦ አምስት አውቃት የሚሰገዱ ሰላቶች፣ ዘካ፣ ፆም፣ ሐጅና የመሳሰሉት፤ እንዲሁም የዝሙት፣ የአስካሪ መጠጦችና የመሳሰሉት አፅፀያፊ ተግባራት ሐራምነት፣፣፣ እነኚህ እንግዲህ በግልፅ የሚታወቁ ነገሮች ስለሆኑ አዲስ የሰለመ ሰውና ከዒልም መንደር ራቅ፞ ያለ ስፍራ የሚኖር ሰው ካልሆነ በስተቀር በእነዚህ ግልፅ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በጅህልናም ሆነ በተእዊል ዑዝር አይሰ፞ጥም!!

➨ የተክፊሮችና መሰ፞ሎቻቸው ወሳኝ ከሆኑ መመለሻዎች አንዱ የሆነው;
"አቡል ዑላ አራ፞ሺድ" ያዘጋጀውን " *ዓሪዹል ጀህል* :39" ላይ ተመልከት።

• #መሳኢል_ኸፊያ የሚሏቸው ደግሞ፦ ከአላህ ስሞችና ባህሪያት ጋር ተያያዥነት ያላቸው መሳኢሎች፣ የአህሉስ ሱናዎችን ፈለግ የሚቃረኑ የሆኑ አካላት የሚያምኑባቸው ዐቂዳዊ ጉዳዮችና መሰረታዊ ያልሆኑ የኢስላም ክፍሎች እንደምሳሌ ይጠቀሳሉ። (ዓሪዹል ጀህል: 43)

እነኚህ አካላት ለዚህ አቋማቸው የተደገፉበት ነገር፦ መሳኢል ዟሂራና ኸፊያን መለያየትን በግልፅ የሚያስገነዝቡ ሀሳቦችን ያዘሉ *የነጅድ ደዕዋ መሪዎችና* የሌሎች ዑለማዎች ተቅሪራቶች ወይም ንግግሮች ናቸው።

➨ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ዐብዲል ወሃብ በአንዳንድ ንግግሩ፣ ሸይኽ ዐብደላህ አቡ ቡጠይን፣ ሱለይማን ቢን ሰሕማን፣ ሐመድ ኢብን ዐቲይቅና ሌሎችም፦ በንግግሮቻቸው ከተደገፉባቸው ዑለማዎች እንደምሳሌ የሚጠቀሱ ናቸው።
*(አቡል ዑላ ያዘጋጀውን "ዸዋቢጡ ተክፊይሪል ሙዐየ፞ን":* 71 — 74) ላይ ተመልከት።

• ሸይኽ ሐመድ ኢብን ዐቲይቅ (አድ ዱረር አስ ሰኒያ: 10/433) ላይ እንዲህ ይላል፦

«ومسألة تكفير المعين مسألة معروفة، إذا قال قولا يكون القول به كفرا، فيقال: من قال بهذا القول فهو كافر، لكن الشخص المعين، إذا قال ذلك لا يحكم بكفره، حتى تقوم عليه الحجة التي يكفر تاركها.
وهذا في المسائل الخفية، التي قد يخفى دليلها على بعض الناس، كما في مسائل القدر والإرجاء ونحو ذلك مما قاله أهل الأهواء، فإن بعض أقوالهم تتضمن أمورا كفرية، مِن رَدِّ أدلة الكتاب والسنة المتواترة، فيكون القول المتضمن لرد بعض النصوص كفرا، ولا يحكم على قائله بالكفر، لاحتمال وجود مانع كالجهل، وعدم العلم بنقض النص، أو بدلالته» 

📋«አንድን ሰው ነጥሎ በተዕዪይን ስለ ማክፈር የምታጠነጥነው መስአላ ታዋቂ የሆነች መስአላ ናት፤ ሲናገሩት ኩፍር የሚሆንን ንግግር አንድ ሰው ከተናገረው፤ ይህን ንግግር የተናገረ ሰው (በኢጥላቅ) ካፊር ነው ይባላል። አንድን ሰው ነጥለን ለማክፈር ግን የሚተዋት ሰው ካፊር የሚደረግባት ሑጃ እስካልቆመችበት ድረስ በካፊርነት አይበየንበትም።
ይህ የሚሆነው ደግሞ መረጃዎቿ በአንዳንድ ሰዎች ላይ ልትደበቅባቸው ወይም ግልፅ ላትሆንላቸው በምትችለው በመስአላ ኸፊያ ነው። አህሉል አህዋእ በቀደር፣ በኢርጃእና በመሳሰሉት መሳኢሎች እንደተናገሯቸው ያሉ ንግግሮች ማለት ነው። ምክንያቱም እነዚህ አካላት ከፊል ንግግሮች ውስጥ የቁርኣንና ሙተዋቲር የሆኑ የሐዲሥ ማስረጃዎችን የሚመልሱበት ወይም የሚያስተባብሉበት ኩፍር የሆኑ አባባሎች ስለሚገኙ ነው። ስለዚህ አንዳንድ መረጃዎችን መመለስን አካትቶ የያዘው ንግግራቸው ኩፍር ቢሆንም በተናጋሪው ላይ ግን የኩፍር ብይን አይበየንበትም፤ ምክንያቱም፦ ሰውየው በተዕዪይን ተለይቶ እንዳይከፈር የሚከለክሉ ጅህልና እና የመሳሰሉ ከልካይ ነገሮች ሊኖሩ ስለሚችሉ ነው።»
--------------------
↩️#ወደ ገፅ-➋-ይሸጋገሩ።

አል-በያን البــيان

26 Sep, 10:53


📢📢ይቀጥላል...



ኡዝር ቢል ጀህል ክፍል -- 16
____
💥 #የተንጠልጣዮች ሁነኛ ምሽግ ወደሆነው
መሳኢል ዟሂራ እና መሳኢል ኸፊያ ማብራሪያና ሹበሀ

#በቁጥር 9

📢📢ይጠብቁን..

አል-በያን البــيان

26 Sep, 10:41


🔺ኡዝር ቢል ጀህል  ክፍል ➊❹
~~ ~ ~ ~
#ዑዝር  ቢል  ጀህል 
በዑለማዎች  እይታ (ቁጥር)

⬇️⬇️
#የአኢመቱ  አድ ደዕዋ አን #ነጅዲያ ተማሪዎች ከሸይኾቻቸው ቀስመውና ሰብስበው ያዘጋጁት ታዋቂ የሆነው #ኪታብ ላይም እንዲህ የሚል አለ:-
📌جاء فى : كتاب مجموعة الرسائل والمسائل النجدية
المبحث الثالث: فيمن مات على التوحيد، وإقامة قواعد الإسلام الخمس، وأصول الإيمان الستة، ولكنه كان يدعو وينادي ويتوسل في الدعاء إذا دعا ربه  ويتوجه بنبيه في دعائه معتمدا على الحديثين اللذين ذكرناهما، أو جهلا منه وغباوة، كيف حكمهم؟

(فالجواب) أن يقال: قد قدمنا الكلام على سؤال الميت، والاستغاثة به، وبينا الفرق بينه، وبين التوسل به في الدعاء، وأن سؤال الميت، والاستغاثة به في قضاء الحاجات وتفريج الكربات، من الشرك الأكبر الذي حرمه الله تعالى ورسوله، واتفقت الكتب الإلهية، والدعوات النبوية على تحريمه وتكفير فاعله والبراءة منه ومعاداته؛ ولكن في أزمنة الفترات، وغلبة الجهل لا يكفر الشخص المعين بذلك حتى تقوم عليه الحجة بالرسالة، ويبين له ويعرف أن هذا هو الشرك الأكبر الذي حرمه الله ورسوله. فإذا بلغته الحجة، وتليت عليه الآيات القرآنية، والأحاديث النبوية، ثم أصر على شركه فهو كافر؛ بخلاف من فعل ذلك جهالة منه ولم ينبه على ذلك.فالجاهل فعله كفر، ولكن لا يحكم بكفره إلا بعد بلوغ الحجة إليه؛ فإذا قامت عليه الحجة ثم أصر على شركه فقد كفر، ولو كان يشهد أن لا إله إلا الله، وأن محمدا رسول الله، ويصلي، ويزكي، ويؤمن بالأصول الستة. (الدرر السنية في الكتب النجدية – 13 / 273)

«ሶስተኛው ጭብጥ መልእክት:
አምስቱን የኢስላም ማእዘኖችና ስድስቱን የኢማን መሰረቶች በማስገኘት በተውሒድ ላይ የሞተ ሰው፤ ነገር ግን አላህን ሲለምን ከላይ ባወሳናቸው ሁለት ሐዲሦች በመደገፍ ወይም ከጅህልናውና ከሞኝነቱ የተነሳ (ከአላህ ውጭ ያለ፞ን አካል) በመጣራት ተወሱል ያደርጋል፤ በዱዓውም ውስጥ በነብይህ ይሁንብህ ይላል። የዚህ አይነቱ ሰው ሑክም እንዴት ነው⁉️

📌መልስ: የሞተን ሰው መለመንና በእሱም ኢስቲጛሣ ማድረግን በተመለከተ ንግግርን በርግጥ አሳልፈናል። በዚህ አይነቱ (የሺርክ) ተግባር እና በሞተው ሰውዬ ይሁንብህ እየተባለ በሚደረገው ተወሱል መካከል ያለውን ልዩነትም አብራርተናል። ሐጃዎችን እንዲፈፅምና ጭንቆችን እንዲያስወግድ የሞተን ሰው መለመንና በእሱም ኢስቲጛሣ ማድረግ አላህና መልእክተኛው ሐራም ካደረጉት #ከትልልቁ_ሺርክ_የሚመደብ_መሆኑንም_ገልፀናል። መለኮታዊ መፅሀፎችና የነቢያት ደዕዋዎችም ስራው ሐራም መሆኑን፣ ሰሪውም ካፊር መደረግ እንዳለበት፣ ከእሱ መፅዳት እንዳለብንና ጠላት ተደርጎ መይያዝ እንዳለበትም ተስማምተዋል።

👉ነገር ግን ነቢያዊ ደዕዋ በሚቋረጥባቸውና በሚጠፉባቸው ዘመናት እንዲሁም ጅህልና በሚሃይልበት ወቅት ነቢያዊ ሑጃ፞ እስከሚደርሰውና ተግባሩ አላህና መልእክተኛው ሐራም ያደረጉት ትልቁ ሺርክ መሆኑ ተገልፆለት እስከሚያውቅ ድረስ ያን ስራ በመስራቱ (ብቻ) ግለሰቡ ተነጥሎ በተዕዬይን #አይከ፞ፈ፞ርም።

ቁርኣናዊ አንቀፆችና ነቢያዊ ሐዲሦች ተነብበውለት ሑጃ ከደረሰው ከዚያም በሺርኩ ላይ ከዘወተረ ግለሰቡ ካፊር ይሆናል። የዚህ አይነቱ ሰው ሑክም፦ ጃሂል ሆኖና የሚያስታውሰው ባለመኖሩ ምክንያት ሺርኩን ከሚሰራው ሰውዬ ሑክም ይለ፞ያ፞ል። ጃሂል ሆኖ (ይህን ተግባር) የሚሰራ ሰው #ስራው_ኩፍር_ነው። #ነገር_ግን ሑጃ_ከደረሰው_በኋላ እንጂ #ካፊር_ተብሎ_አይተሐከምበትም።

👉ሑጃ ቆሞበት ከዚያ በሺርኩ ላይ ከዘወተረ ግን ላ ኢላሃ ኢለላህ ሙሐመዱን ረሱሉላህ ቢልም፣ ቢሰግድም፣ ዘካ ቢሰጥና በስድስቶቹ የኢማን መሰረቶች ቢያምንም በርግጥ ካፊር ይሆናል።»
📚(አድ ዱረር አስ ሰኒያ ፊል ኩቱብ አን ነጅዲያ: 13/227)

🖌አቡ  ዓብዲላህ ሰዒድ (አስ ـ ሰለፊ)
🩸🩸
🔗https://t.me/al_beyann/1259

አል-በያን البــيان

26 Sep, 10:37


🔺ኡዝር  ቢል  ጀህል  ክፍል➊➌
~~
#ዑዝር  ቢል  ጀህል 
በዑለማዎች  እይታ(ቁጥር) ➏


قال العلامة السلفي الأصولي القاضي أحمد بن حجر آل بوطامي (1335 ـ 1423) رحمه الله في كتابه"العقائد السلفية بأدلتها النقلية والعقلية" (1/39) :

«هل يُحْكَم على الشخص المعيَّنِ أو الطائفة المخصوصة ـ المتلوِّثة بتلك الخصال المُنافِيةِ للتوحيد ـ بالشِّرك والكفر مع أنها مؤمنةٌ بالله والرسول وآتيةٌ بِسائر الشرائع؟

الجواب : يقالُ هذا العملُ شركٌ أو كفر مثلًا كالسجود لولي أو الطواف بقبره والنذر له، ولكن الشخص المعين أو الطائفة المخصوصة لا نُبادِرُها بالتكفير، بل الواجب تَبليغُها بآيات القرآن وأحاديث الرسول ﷺ المبيِّنة للشرك والمحذِّرة عنه وأنْ ليس لصاحبه نصيبٌ من الجنة، وأنَّ هذه الأعمالَ هي شركٌ ، فإذا أصرَّ الشخصُ المعيَّنُ أو الطائفةُ المخصوصةُ وعاندتْ ولم تقبلْ، فعند ذلك يحلُّ عليها إطلاقُ الشرك أو عليه إن كان فردًا معيَّنًا»


የሱዑዲያ ጠቅላይ ሙፍቲ የሆኑት የሸይኽ ዐብደል ዐዚዝ ኣሉሸ፞ይኽ አስተማሪ የነበሩትና ከ1335 እሰከ 1423 ሂጅሪ ይኖሩ የነበሩት አል ዐላመቱ አስ ሰለፊ አሕመድ ኢብኑ ሐጀር ኣል ቡጧሚ አላህ ይዘንላቸውና "አል ዐቃኢዱ አስ ሰለፊያ ቢአዲለቲሃ አነቅሊያ ወል ዐቅሊያ" (1/39) የተሰኘው ኪታባቸው ላይ እንዲህ ብለዋል፦

«አንድን ሰው ወይም በአላህና በመልእክተኛው ﷺ አማኝ ሆና እና ሌሎችንም ሸሪዓዊ ድንጋጌዎችን ከመተግበሯ ጋር ተውሒድን የሚቃረኑ በሆኑ ባህሪያት የተለወሰችን አንዲትን ጀማዓ በተዕዪይን ነጥሎ በሺርክ ወይም በኩፍር ይበየናልን?

መልስ: ይህ ተግባር ሺርክ ነው ወይም ኩፍር ነው ይባላል፤ ለምሳሌ ለወልይ ሱጁድ ማድረግ ወይም በቀብሩ ዙሪያ ጠዋፍ ማድረግ፣ ወይም ለሱ ስለትን መሳል (ይህ አይነቱ ተግባር ሽርክ ነው ወይም ኩፍር ነው ሊባል ይችላል)፤ ነገር ግን (ይህን ተግባር የሚሰራን) አንድን ግለሰብ ወይም የሆነችን ጀማዓ በተዕዪይን ነጥለን በኩፍር ለመሐከም አንሽቀዳደምም።
ይልቁንም (ከማክፈር በፊት) ሺርክን የሚገልፁና ከሱም የሚያስጠነቅቁ፣ ስራዎቹ ሺርክ መሆናቸውንና ይህን ተግባር የፈፀመ ሰው በጀነት እጣ ፈንታ የሌለው መሆኑን የሚያብራሩ ቁርኣናዊ አንቀፆችንና ነቢያዊ ሐዲሦችን ልናደርሳቸው ግድ ነው።
ያ ግለሰብ ወይም ያቺ ጀማኣ ከተመከረች በኋላ ባሉበት ስራ ላይ ከዘወተሩና ሐቅን ባለመቀበል እንቢተኛ ከሆኑ በተዕዪይን ነጥሎ የሺርክ ሑክም ይተሓከምባቸዋል።»

تنبيه: الشيخ ابن حجر آل بوطامي هو مِن مشايخ سماحة الشيخ عبد العزيز بن عبدالله آل الشيخ مفتي عام المملكة.

🖌አቡ  ዓብዲላህ ሰዒድ (አስ ـ ሰለፊ)

🩸🩸
🔗https://t.me/al_beyann/1258

አል-በያን البــيان

26 Sep, 10:33


#ገፅ ❸
⬇️⬇️

📨ባጠቃላይ አንድ ሰው የሚናገረው ንግግር ወይም የሚሰራው ስራ ኩፍር ወይም ፊስቅ መሆኑን ሳያውቅ ቢናገር ወይም ቢሰራ ዑዝር ይሰ፞ጠ፞ዋል። ይህም በቁርኣንና በሐዲስ መረጃዎች እንዲሁም በዑለማዎች ንግግር መሰረት ነው።» ኢ ን ተ ሃ ።

📜ምንጭ: (መጅሙውዑ ፈታዋ አሸ፞ይኽ አል ዑሠይሚይን 2/224 የዚህ ቁጥር ጥያቄ መልስ ላይ)።

🖌አቡ  ዓብዲላህ ሰዒድ (አስ ـ ሰለፊ)

🩸🩸

🔗https://t.me/al_beyann/1257

አል-በያን البــيان

26 Sep, 10:25


#ገፅ -➋
⬇️⬇️
«መስማት የሚለው ቃል የተፈለገበት ሀሳብ፦ ከእሱ ጋር (ቁርአንን) የሚገነዘብበት የሆነ መስማት መሆኑ በእርግጥ የታወቀ ጉዳይ ነው፤ ምክንያቱም መገንዘብ በማይቻለው መልኩ ቃሉን በመስማቱ ብቻ የሚፈለገው አላማ አይገኝምና! ዐረብ ያልሆነ ሰው ከሆነ ሑጃው እንዲቆምበት በቋንቋው ሊተረጎምለት ግድ ነው፤ ዐረብ እንኳ ሆኖ ነገር ግን ቁርኣን ውስጥ እንግዳ የሆኑ ቃላቶች በመኖራቸው ሰውየው "ፉስሓ" የሆነው የቁርኣንን ቋንቋ ከማይናገሩትና ከማይነገዘቡት ዐረብ ከሆነ ሊብራራለት ግድ ነው።»]

ከዑለማዎች ንግግር ለምሳሌ ያህል:
• (ኢብኑ ቁዳማ) "ሙጝኒ" 8/131) የተባለው ኪታቡ ላይ እንዲህ ብሏል:
«ግዴታነቱን የማያውቅ ከሆነ፤ ለምሳሌ አዲስ ሰለምቴ የሆነ፣ ከኢስላም ሀገራት ውጪ ያደገ፣ ወይም ከከተሞችና ከዑለማዎች ራቅ ያለ ገጠራማ ቦታ የሚኖር ሰው ከሆነ፤ ካፊር ተብሎ አይተሓከ፞ምበትም።»
• ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ "አል ፈታዋ: 3/229 ـ መጅሙዕ ኢብኑ ቃሲም" ላይ እንዲህ ብሏል:
«እኔ ሁልጊዜ አንድን ሰው በተዕዪን ለይቶ ወደ ኩፍር፣ ወደ ፊስቅና መዕሲያ ማስጠጋትን በጣም አድርገው ከሚቃወሙ ሰዎች የምመደብ ነኝ፤ ይህንንም እኔን የሚያቀማምጡ ሰዎችም ያውቃሉ!! ነገር ግን የታቀረናት ሰው እንደ ሁኔታው አንዳንዴ ካፊር፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ፋሲቅ ወይም ወንጀለኛ የሚሆንባት ነቢያዊ ሑጃ ሰውዬው ላይ በእርግጥ መቆሙ ከታ፞ወቀ በቀር (ከዚህ ውጭ ሑጃ ሳይቆምበት ካፊር ፋሲቅ ዓሲ    እያ፞ሉ መበየንን አጥብቀው ከሚያወግዙ ዑለማዎች ነኝ)።
አሁንም እኔ ለዚህ ህዝበ ሙስሊም አላህ ስህተታቸውን በእርግጥ ምሯቸዋል በማለት ደጋግሜና አስረግጬ እናገራለሁ!! ስህተቱ ደግሞ ዐቂዳዊም ሆነ አሕካማዊ ጉዳዮችን ያጠቃልላል። ሰለፎች በበርካታ መሳኡሎች ከመለያየታቸውም ጋር ከውስጣቸው አንዱ በሌላው ላይ በኩፍር ወይም በፊስቅ ወይም ደግሞ በወንጀል ይሐክሙ አልነበረም!!»
ሸይኸል ኢስላም ቀጥለው እንዲህ አሉ:
«ከሰለፎችና ከአኢማ፞ዎች "ይህን፣ ይህን መሰ፞ል ንግግር የተናገረ ይከፍራል" እያሉ  በኢጥላቅ (በልቅ፞) ተናግረውት ወደኛ የደረሰን ንግግራቸው ሐቅ መሆኑን እገልፅ ነበር፤ ነገር ግን በጥቅል የሚሰ፞ጠ፞ውንና በተዕዪን (በተናጠል) የሚተ፞ሓከ፞መውን ብይን መለየት ግድ፞ ነው»
ሸይኹል ኢስላም አሁንም ቀጠሉ:
«ተክፊይር (ሰውን ከኢስላም ማስወጣት) ከወዒይድ (ዛቻዊ) ነጥቦች ነው፤ አንድ ንግግር መልእክተኛው ﷺ ከተናገሩት ንግግር ጋር የሚቃረን ቢሆንም ተናጋሪው ሰውዬ ግን አዲስ ሰለምቴ ሊሆን ይችላል፤ ወይም ራቅ ያለ ገጠራማ ስፍራ ሊኖር ይችላል፤ ይህ አይነቱ ሰው በሚክደው ክህደት ሑጃ እስካልቆመበት ድረስ አይከ፞ፈ፞ርም፤ እንዲሁም ይህ ሰው መረጃዎቹን አልሰማቸው ይሆናል፤ ወይም ሰምቷቸው ነገር ግን እሱ ዘንድ አልሠበቱለት (አልተረጋገጡለት) ይሆናል፤ ወይም መረጃዎቹን የሚቃረንበትና ተእዊል የሚያደርግበት የሆነ (ሹብሃ) እሱ ዘንድ ይኖረው ይሆናል፤ ሰውየው (በትክክለኛ እይታ) ስህተተኛ ቢሆንም።»
• ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብደል ወሃብ "አድ ـ ዱረር አስ ـ ሰኒያ: 1/56"
ላይ እንዲህ ብሏል:
«ስለተክፊር (እናውራ ከተባለ) የመልእክተኛውን ﷺ ሐይማኖት አውቆ፤ ከተረዳው በኋላ የሚሰድበው ከሆነ፤ ሰዎችንም (እንዳያምኑበት) የሚከለክል ከሆነ፤ በኢስላም የሚሰሩ ሰዎችንም ጠላት አድርጎ ከያዘ፤ እኔ የማከፍረው ይህ አይነቱን ሰው ነው!!»
(ያለፈው ምንጭ) ገፅ : 66 ላይም እንዲህ ይላል:
«በእኛ ላይ የሚዋሹብንና የሚቀጥፉብንማ፤ እኛ በጥቅል እንደምናከፍርና ሀገራቸው ላይ ሐይማኖታቸውን በነፃነት ይፋ ማድረግ የሚችሉ ሰዎችን ወደኛ መሰደድ ግዴታ አለባችሁ እንደምንል አድርገው የሚያስወሩት ሁሉ፤ ይህ ሰዎችን ከአላህና ከመልእክተኛው ዲን ለማገድ ከሚዋሹብንና ከሚቀጥፉብን ነገሮች ነው።
በዐብደልቃዲር አልጀይላኒ፣ በአሕመድ አልበደዊና በሌሎች መሰ፞ል አካላት መቃብር ላይ የተገነቡ ታቦቶችን (ዶሪሖችን) የሚያመልኩ ሰዎች ባለማወቃቸውና የሚገስፃቸው ሰው ባለመኖሩ ምክንያት ካላከፈ፞ርናቸው፤ በአላህ የማያጋራን ሰው ወደእኛ ባለመሰ፞ደዱ፣ ባለማክፈሩና ከእኛ ጋር ሆኖ ጠላትን ባለመፋ፞ለሙ ምክንያት እንዴት እናከፍረዋለን!?
አላህ ሆይ ጥራት ይገባህ፤ ይህ ከባድ የሆነ ቅጥፈት ነው።»
ይህ አቋም የቁርአንና የሐዲስ መረጃዎች እንዲሁም የዑለማዎች ንግግሮች የሚያስፈርዱት ነገር ነው፤ የአላህ ﷻ ጥበብ እዝነትና ርህራሄም ይህንኑ ነው የሚያስፈርዱት፤ ከዚህም የተነሳ ሑጃ ሳያቆም በፊት ማንንም አይቀጣም።
ምክንያቱም የሰው ልጅ አእምሮ ከአላህ ዘንድ ሑጃ የሚሆን መልእክት ሳይደርሰው እንዲሁ ራሱን ችሎ ለአላህ ምን፣ ምን እንደሚገ፞ባ፞ው ሊያውቅ አይችልም፤ ይህ ቢሆን ኖሮ በሰው ልጆች ላይ ሑጃን ማቆም በመልእክተኞች መልላክ አያጥርም ነበር።
በሸሪዓዊ መረጃ የሰውየው እስልምና መወገዱ እስካልተረጋገጠ ድረስ፤ በመሰረቱ ወደ ኢስላም የሚጠጋ ሰው በኢስላም ላይ እንዳለ፞ ነው።
አንድን ሰው ከኢስላም ከማስወጣታችን በፊት ሁለት ነገሮችን ማጤን ግድ ይላል።
① በአላህ ላይ መዋሸት እንዳይሆን ያ አክፋሪ ተደርጎ የታየው ነገር የቁርአንና የሐዲሥ መረጃዎች አክፋሪነቱን ሊጠቁሙ ይገ፞ባ፞ል።
② ካፊር የሚለው ብይን ሰውዬው ላይ ተስማሚ መሆኑ ልብ ሊባል ነው። ማለትም እንድናከፍረው የሚያስችሉን መስፍርቶች ተገኝተው፤ እንዳናከፍረው የሚከለክሉ ነገሮችም ከተወገዱ ማለት ነው።
አሳሳቢ ከሆኑት መስፈርቶች መካከል አንዱ: እንዲከፍር ግድ ያደረገችበት ነገር ከኢስላም ጋር ተፃፃሪ መሆኗን ማወቁ ነው።
ምክንያቱም አላህ ﷻ እንዲህ ብሏልና:
{وَمَن يُشَاقِقِ الرَّسُولَ مِن بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ الْهُدَىٰ وَيَتَّبِعْ غَيْرَ سَبِيلِ الْمُؤْمِنِينَ نُوَلِّهِ مَا تَوَلَّىٰ وَنُصْلِهِ جَهَنَّمَ ۖ وَسَاءَتْ مَصِيرًا} (النساء: 115)
{ቅኑም መንገድ ለእሱ ከተገለጸ በኋላ መልክተኛውን የሚጨቃጨቅና ከምእምኖቹ መንገድ ሌላ የኾነን የሚከተል ሰው (በዚህ ዓለም) በተሾመበት (ጥመት) ላይ እንሾመዋለን፤ ገሀነምንም እናስገባዋለን፡፡ መመለሻይቱም ከፋች!}
(እዚህ ላይ እንደምታዩት) ሰውየው በእሳት ይቀ፞ጣ፞ ዘንድ ቅኑ መንገድ ከተገለፀለት በኋላ መልእከተኛውን የሚቃረን መሆኑ መስፈርት ተደርጓል።
"የሰራት ሙኻለፋ ኩፍርም ሆነ ሌላ ውጤት እንደምታስከትል ማወቁ እንደመስፈርት ይታያል? ወይስ ሙኻለፋዋ የምታስከትለውን ውጤት ባያውቅም እንዲሁ ከቅኑ መንገድ ጋር የሚቃረን መሆኑን ማወቁ ብቻ በቂ ነው ? " ከተባለ፤
መልሱ፦ መረጃዎች በግልፅ እንደሚጠቁሙት ሰውየው ላይ በሚገ፞ባው ልክ ለመበየን ከቅኑ መንገድ ጋር የሚቃረን መሆኑን ማወቁ ብቻ በቂ ነው። ምክንያቱም ባለቤቱን በረመዷን በቀን የተገናኘው ሰውየ "ከፋ፞ራ" እንዳለበት ካለማወቁ ጋር ነገር ግን ከሐቅ ጋር እንደተቃረነ ስላወቀ ብቻ ነቢዩ ﷺ ከፋ፞ራህን ግድ አድርገውበታል።
እንዲሁም የዝሙትን ሐራምነት የሚያውቅ ሆኖ ያገባ፞ ዝሙት ሰሪ፤ ጥፋቱ ተቀጥቅጦ መገ፞ደልን የሚያስከትል መሆኑን ባያውቅም ይገደላል። ምናልባት የሚያስከትለውን ቢያውቅ ላይሰራ ይችል ይሆናል።

ወደ↩️ ገፅ ❸ ይሸጋገሩ።

2,225

subscribers

1

photos

44

videos