ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም
የክፍለ ከተማው አስተዳደር ሥር ከሚገኙ ርዕሰ መምህራን ፤ የሃይማኖት አባቶች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ምዝገባን አስመልክቶ ምክክር አካሂዷል፡፡
በክፍለ ከተማው የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ፍቃዱ እንዳሉት የብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ምዝገባ ለዲጂታል ኢኮኖሚ እየገነባነው ላለው ሂደት አስፈላጊ እንደሆነ የገለፁ ሲሆን የመረጃ ችግሮችን በመፍታት እና አገልግሎቶችን በማስተሳሰር የተገልጋዮችን ጊዜ ለመቀነስ ሚና እንዳለው አስገንዝበዋል፡፡
አቶ አለማየሁ ጨምረው ብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባ(ፋይዳ) በትምህርት ቤቶች በሚማሩ ተማሪዎች ጭምር ተግባራዊ ስልሚደረግ የትምህርት አመራሩ አስፈላጊውን ትብብር እና ድጋፍ ማድረግ ይገባዋል ብለዋል፡፡
የክፍለ ከተማው ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳኛቸው አበበ በበኩላቸው ብሔራዊ መታወቂያ(ፋይዳ) ማህበረሰቡን የሚጠቅም፤ለሌሎች ስራዎች አጋዥ በመሆኑ ማህበረሰቡ በተዘጋጁ ቦታዎች በመገኘት ያለምንም እንግልት ምዝገባ ማካሄድ እንደሚችል ገልፀዋል፡፡
@ Via:-ኮልፌ ኮሙኒኬሽን