ይህ የተገለጸው በዞኑ አዲዮ ወረዳ ቦቃ ቀበሌ የመስክ ጉብኝት በተደረገበት ወቅት ነው፡፡
የመምሪያው ሀላፊ አቶ ጋዎ አባመጫ በመኸር አዝመራ ከ1 መቶ 17 ሺህ 800 ሄክታር በላይ ማሳ ላይ የደረሰ ምርት እየተሰበሰበ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከዚህም 2 ነጥብ 7 ሚለዮን ኩንታል እንደሚጠበቅ ገልጸው እስካሁን ባለው 615 ሺ 523 ኩንታል ምርት ተሰብስቧል ብለዋል፡፡
የምርት ብክነት እንዳይከሰት አደረጃጀቶችን በመጠቀም የመሰብሰቡ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
በካፋ ዞን ከ405 ሺ 1 መቶ ሄክታር በላይ መሬት አሲዳማ መሆኑን የተናገሩት አቶ ጋዎ 600 ሄክታሩን ማሳ በኖራ የማከም ስራ ተሰርቷል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
መሬትን በኖራ በማከም ምርታማነት እንዲያድግ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።
የአዲዮ ወረዳ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገረመው ገብሬ በወረዳው የተለያዩ ሰብሎች በስፋት እንደሚመረቱ ገልጸዋል።
በ2016/17 የምርት ዘመን በዋና ዋና ሰብሎች በሙሉ ፖኬጅና በኖራ ህክምና 22 ሺ 129 ሄክታር ማሳ በኩታ ገጠምና በክላስተር መልማቱን ተናግረዋል፡፡
5 መቶ 2 ሺህ ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ተናግረው እሰከአሁን ባለው 119 ሺህ ኩንታል ምርት መሰብሰቡን ገልጸዋል፡፡
የዞኑ ዋና አሰተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ በዚህ ጊዜ ባሰተላለፉት መልዕክት አርሶ-አደሮች የተሟላ ግብአት ተጠቅመው ምርትና ምርታማነታቸውን እንዲያረጋግጡ ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት እንደሚጠይቅ ገልጸው በየደረጃው የሚገኙ አካላት ለተግባራዊነቱ እየሰሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
በአሲዳማነት የተጠቃን ማሳ በኖራ በማከም ክልል አቀፍ የማስጀመሪያ መርሃ-ግብር የክልሉ ርዕስ-መስተዳድር ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ፣ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ፣ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላችው እንግዶች ተካሂዷል፡፡
የዘገበው ቦንጋ ኤፍ ኤም 97.4 ሬዲዮ ጣቢያ ነው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የካፋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ዠ።
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ፦
ፌስቡክ ገፃችንን
https://www.facebook.com/kfzgca
የቴሌግራም ቻናላችንን
https://t.me/ahkafaZGCAffairs
ዩቲዩብ ቻናላችንን
@KaffaZoneCommunicationAffairs
የቲክቶኮ ቻናላችንን
https://vm.tiktok.com/ZMrxuoNNL/
Like, comment ,share በማድረግ ድረገፃችንን ይወዳጁ