በዓውደ-ርዕዩ ላይ በብቸኝነት ሙሉ የባንክ አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን ዓውደ-ርዕዩ ስኬታማ ይሆን ዘንድ ከአጋራ ድርጅቶች ጋር እየሰራ ነው።
ባንኩ በቅርቡ ያሰተዋወቃቸውን አገልግሎቶች ጨምሮ ለክቡራን ደንበኞቹ ያቀረባቸውን አገልግሎቶች ለተሳታፊዎች በስፋት እያስተዋወቀ ይገኛል።
ከጣሊያን ኤምባሲ ጋር በመተባበር በተዘጋጀው በዚህ የፓስታ ዓውደ-ርዕይ ከ10 በላይ የጣልያን ሬስቶራንቶች፣ምግብና መጠጥ አምራችና አቅራቢ ድርጅቶች እየተሳተፉበት ይገኛል።
የዓውደ - ርዕዩ ተሳታፊዎች ምርትና አገልግሎታቸውን ለማስተዋወቅ ሁነቱ እንደሚያግዛቸው አመላክተዋል።
ዳሸን ባንክ ማሕበራዊ ሐላፊነቱን ለመወጣት "ዳሸን ካልቸር ክለብ" በማቋቋም ባህልና ኪነጥበብን እያበረታታ ይገኛል። በዚህም ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመተባበር የባህል ትውውቅ እንዲዳብርና የጥበብ ባለሙያዎች ስራቸውን እንዲያስተዋውቁ በመስራት ላይ ነው።
በቅርቡም ከፕሮሎግ ማርኬቲንግ ጋር በመተባበር የስነ-ጥበብ፣ የቡና እንዲሁም ሌሎች ዓውደ-ርዕዮችን ማዘጋጀቱ ይታወሳል።