አዲስ ለውጥ @amaregna_filmoch Channel on Telegram

አዲስ ለውጥ

@amaregna_filmoch


አርዓያ ስብዕና ስኬት ከፍታ ቤተሰብ ከእኛ ጋር

አዲስ ለውጥ (Amharic)

አዲስ ለውጥ ከማን ነው? አና ነኝ! አዲስ ለውጥ በእኛ ጋር አዲስ አርዓያ ስብዕና ስኬት ከፍታችንንን ለማስታወቅ የምናመልከውን ስብስብ ቦታ ነዋሪዎችንና አስፈላጊ የፊልሞች ቪዲዮዎችን ይማሩ። እናንት በተለያዩ ስብዓዊ ምርጥ የሚሰራባቸው ፊልሞችን በጣም በተጨማሪ መንገዶች እና አጋር በካሬያው በወቅታዊ ዘመን በፍፃሜ ያግኙ። ለማነሳም በምትከተለው ለውጥ ላይ የስብስቦች ተከታታይ ፊልሞችንና ይዘቱን እንመለከታለን። ትክክለኛ ታሪክ፣ ሌሎች ሰዎችን ለመምረጥ እና ምንም በረስና መልኩ እና ስለ ውጥ የሚሰማ ቪዲዮውን ሊኖሯቸው ይገልጻል።

አዲስ ለውጥ

10 Jan, 09:06


በራስ መደነቅ ብዙ መጥፎ ሥነ ምግባራትን እና ባሕርያትን ያመነጫል፤ በዋናነት ሌሎችን መናቅ!

አዲስ ለውጥ

08 Jan, 09:13


ግፈኞች እና ጨቋኞች መቼም ቢሆን ለስኬት አይታደሉም።

አዲስ ለውጥ

03 Jan, 18:42


መሳለቅ በግለሰብና በህብረተሰብ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ አለው፤ ጥላቻንና ምቀኝነትን ይወልዳል።

አዲስ ለውጥ

02 Jan, 07:02


በሰዎች ላይ መሳለቅ የጥላቻን ዘር ይዘራል፤ ቂምና ጥልን ያወርሳል።

አዲስ ለውጥ

01 Jan, 14:23


ማፌዝ በወንድማማችነት፣ በመዋደድና በመተሳሰብ ላይ የተመሰረተ ማህበራዊ ትስስርን ያቀጭጫል!

አዲስ ለውጥ

30 Dec, 08:46


ቂም እሳቤን የሚመርዝና አእምሮውን የሚወጥር ከባድ ሸክም ነው።

አዲስ ለውጥ

28 Dec, 06:04


ምቀኝነት ወደ መኮራረፍ፣ ዝምድናን መቁረጥ፣ ጥላቻና ቂም ይመራል።

አዲስ ለውጥ

27 Dec, 08:26


ደረቅ ሙግት ተከራካሪውን እውነትን እንዲክድና እንዳይቀበል ያደርገዋል።

አዲስ ለውጥ

26 Dec, 07:37


ሰዎችን በጭፍን መከተል እውነታዎችን እንዳንገነዘብ እንቅፋት ነውና ማንንም በጭፍን አይከተሉ።

አዲስ ለውጥ

25 Dec, 09:33


ሰዎችን መሰለል ማህበረሰቡ ውስጥ ጥላቻና በቀል ያነግሳል።

አዲስ ለውጥ

24 Dec, 11:10


ሰላይነት ህይወት በጥርጣሬና ስጋት የተሞላች እንድትሆን ያዳርጋልና ይራቁት።

አዲስ ለውጥ

23 Dec, 06:35


ጥርጣሬን ራቁ፤ ምክንያቱም  ጥርጣሬ ከቅጥፈቶች ሁሉ የላቀው ነውና።

አዲስ ለውጥ

21 Dec, 06:45


ሀሜት ደካማ ሰው ያደርግሀል። የሰዎችን ነውር እየተከታተልክ ከመኖር ራስህን አቅብ።

አዲስ ለውጥ

20 Dec, 08:46


ሀሜት በሰዎች መካከል ጥርጣሬ እንዲያድርና ጸብ እንዲፈጠር ከሚያደርጉ ምክንያቶቹ አንዱ ነው።

አዲስ ለውጥ

19 Dec, 08:48


ሰው ላይ ክፉ መሆኑን የሚቀበል በራሱ ላይ የስነምግባር ዝቅጠትን መስክሯል።

አዲስ ለውጥ

18 Dec, 14:40


ቃል ኪዳንን መፈፀም ዓለም ላይ ደህንነትን ያረጋግጣል፤ ደም መፋሰስን ያስቀራል።

አዲስ ለውጥ

16 Dec, 08:43


ከሰዎች ጋር መወዳጀት የሚፈልግ ይቅር ይበል፤ ጥፋታችውንም ይለፍ።

አዲስ ለውጥ

14 Dec, 13:58


በፍቅር ትገናኙ ዘንድ ከባልንጀራህ ጋር በመኖሪያ ቤት ተራራቁ!

አዲስ ለውጥ

13 Dec, 08:19


መልካም ስነምግባር ሰዎች ዘንድ ፍቅርን ለማግኘት ሰበብ ነው።

አዲስ ለውጥ

12 Dec, 05:42


ከሰዎች ጋር በጥሩ ምግባር መኗኗር ዝግ የሆኑ ልቦችን ይከፍታል።

አዲስ ለውጥ

11 Dec, 05:21


ለሰዎች መልካም የሆነ በልባቸው ታላቅ ሰው ይሆናል።

አዲስ ለውጥ

09 Dec, 07:00


ፅድቅ ሥራ ለአእምሮ ሰላምና ራስን ለማረጋጋት ፍቱን መድኃኒት ነው።

አዲስ ለውጥ

07 Dec, 06:32


ትብብር ማህበራዊ አንድነትን ሲያመጣ የመከፋፈል መንስኤዎችን እንዲመነምኑ ያደርጋል።

አዲስ ለውጥ

05 Dec, 11:50


ትብብር የስራ እና የሀላፊነት ጫና ይቀንሳል።

አዲስ ለውጥ

03 Dec, 09:13


ለሌሎች ጥቅም በቅድሚያ ማሰብ መንፈሳዊ እርካታ እና ቁሳዊ በረከት እንዲያገኙ ይረዳል።

አዲስ ለውጥ

02 Dec, 13:54


ለሌሎች ጥቅም በቅድሚያ ማሰብ የትብብርና መተሳሰብ ስሜት መኖር ማስረጃ ነው።

አዲስ ለውጥ

30 Nov, 06:13


ታማኝነት የተስፋፋበት ማህበረሰብ የመልካምና የበረከት ማህበረሰብ ነው።

አዲስ ለውጥ

29 Nov, 11:32


ያመንከው እንዲከዳህ እንደማትፈልገው አንተም ላመነህ ታመን።

አዲስ ለውጥ

28 Nov, 06:09


ምስጢርህ እንዲጠበቅ ትውዳለህ? እንግዲያውስ የሌሎችን ምስጢር ጠብቅ።

አዲስ ለውጥ

26 Nov, 14:07


ክብር በትህትና ነው፤ በትዕቢት ክብር የሚፈልግ ከእሳት ውኃ እንደመጠየቅ ነው።

አዲስ ለውጥ

25 Nov, 09:17


የእውነተኝነት ማረጋገጫው፤ ውሸት ብቻ የሚያድንህ ቦታ ላይ እውነቱን መናገርህ ነው።

አዲስ ለውጥ

23 Nov, 09:06


የእውነተኝነት ክብሩ ባለቤቱ ጠላቱ ላይ ቢሆን እንኳ አለመዋሸቱ ነው።

አዲስ ለውጥ

22 Nov, 11:36


ትሁት ሰው ነውርን ይደብቃል፤ ይመክራል፤ አያጋልጥም።

አዲስ ለውጥ

21 Nov, 06:23


ለሰዎች በጎ መዋል ከመጥፎ ውድቀት ይጠብቃል።

አዲስ ለውጥ

20 Nov, 06:12


የተረጋጋ ሰው ሁሌም ትክክል እንደሆነ ሁሉ፤ ችኩል ሰው በጭራሽ ከስህተት አይድንም።

አዲስ ለውጥ

19 Nov, 18:08


ሰዎች ከሞትክ በኋላ አብዝተው እንዲያመሰግኑህ ከፈለግህ በብሩህ ፈገግታ ተገናኛቸው።

አዲስ ለውጥ

18 Nov, 06:48


ያለ ቦታው የሚደረግ መተናነስ የእውነትን ካባ የለበሰ ውርደት ነው።

አዲስ ለውጥ

15 Nov, 09:25


የሚችሉትን ያህል በጎ ለመሆን ጥረት ያድርጉ፤ ምላሹን አይጠብቁ።

አዲስ ለውጥ

14 Nov, 14:19


ሌሎችን ማዳመጥ ስሜታቸውን የመረዳትና የመተርጎም ችሎታዎን ይጨምራል።

አዲስ ለውጥ

13 Nov, 14:07


መተማመን በሰዎች ግንኙነት ስኬታማነት ውስጥ ወሳኝ ቁልፍ ስለሆነ ሌሎችን ይመኑ።

አዲስ ለውጥ

11 Nov, 06:41


በሰዎች ስኬት ቅናት ወይም ምቀኝነት እንዲቆጣጠርህ በፍጹም አትፍቀድ።

አዲስ ለውጥ

10 Nov, 10:14


ከሌሎች ጋር ሲኗኗሩ ከራስ ወዳድነት ይራቁ፤ የመስጠትን መርህ ከነሱ ጋር በቋሚነት ይቅረፁ።

አዲስ ለውጥ

08 Nov, 15:38


ሰዎች ላንተ ፍቅር፣ ክብር፣ እምነትና ደህንነት እንዲሰማቸው አታስመስል!

አዲስ ለውጥ

07 Nov, 08:42


ትንሽ ቢሆንም ስጦታዎችን ከሌሎች ጋር መለዋወጥ በሰዎች መካከል ፍቅርን ይጨምራል!

አዲስ ለውጥ

06 Nov, 15:49


ይቅርታ መጠየቅ ደረጃዎን ከፍ ያደርገዋል እንጂ አይቀንስም።

አዲስ ለውጥ

04 Nov, 10:25


አንድ ሰው ቢያስከፋዎ በመልካም አንደበት ሀሳቦን ለመግለፅ ይሞክሩ።

አዲስ ለውጥ

02 Nov, 08:06


ምንም ያህል ደረጃዎ ከፍ ቢልም ትሑት ይሁኑ፤ ሌሎችን አያዋረዱ።

አዲስ ለውጥ

31 Oct, 17:55


አንድ ግለሰብ ቃላቱና ተግባሩ ያልተጋነነ በሆነ ቁጥር ወደ ሰዎች ልብ ይቀርባል።

አዲስ ለውጥ

29 Oct, 11:07


በቀጠሮ አለመገኘት ግዴለሽ ሰው መሆንዎን ያሳያል።

አዲስ ለውጥ

28 Oct, 10:52


ብሩህ ፈገግታ ማህበራዊ ግንኙነት ለማሻሻልና ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

አዲስ ለውጥ

26 Oct, 08:22


አያስመስሉ! ውሸት የማህበራዊ ግንኙነት  ውድቀት ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታልና።

አዲስ ለውጥ

11 Oct, 08:28


የቁም ሕልም አታልም፡፡ በሕልም ብቻ ግብን ማሳካት አይቻልም።

አዲስ ለውጥ

09 Oct, 14:14


ስኬትን ከፈለጉ አሉታዊ፣ ሟርተኛና ምቀኛ ከሆኑ ሰዎች ይራቁ።

አዲስ ለውጥ

08 Oct, 11:03


ድክመቶችህን ለማስወገድና እንዳይባባሱ ለማድረግ ቅድሚያ ድክመቶችህን ለማወቅ ሞክር።

አዲስ ለውጥ

04 Oct, 08:41


የምታባክነውን ጊዜ ብትጠቀመው ስኬታማ ሰው እንድትሆን ያደርግህ ነበር።

አዲስ ለውጥ

02 Oct, 13:48


ራስን መለወጥ በሂደትና ዘውታሪ በሆኑ እርምጃዎች እንጂ በአንድ ጀምበር አይከሰትም።

አዲስ ለውጥ

30 Sep, 07:36


የሆነ ቀን እውን ይሆናልና፤ አንድ ነገር ከመወሰንዎ በፊት እውነተኛ ፍላጎትዎን ይወቁ።

አዲስ ለውጥ

24 Sep, 05:52


ዛሬን በመሸሽ የነገን ኃላፊነት ማምለጥ አይችሉም።

አዲስ ለውጥ

21 Sep, 08:45


የነገ ስኬትዎ የሚወሰነው ዛሬ በምትሠራው ሥራ ላይ ነው።ራስዎን ለመለወጥ አሁኑኑ እንቀስቃሴ ይጀምሩ፤ ዛሬ ላይ የተሻለ ነገን መገንባት ይችላሉ።

አዲስ ለውጥ

18 Sep, 10:59


በመንገድህ የሚመጡትን ማንኛውንም ችግሮች ተፋለማቸው፤ አብዛኞቹ ፍርሃቶች እውነት አይደሉምና።

አዲስ ለውጥ

12 Sep, 14:20


ጥሩ ሰዎችን ተጎዳኝ፤ እኩይ ሰዎችን ራቅ፤ ከክፉ ሰዎች ጋር መዋል ለጥፋት ይዳርጋል።

አዲስ ለውጥ

11 Sep, 11:47


ስለ ውድቀትህ በማሰብ ጊዜህን አታባክን፤ ይልቅ ያንን ጉልበት ለሌላ ጠቃሚ አላማ አውለው።

አዲስ ለውጥ

21 Jan, 18:59


ከሰዎች ጋር መወዳጀት የሚፈልግ ይቅር ይበል፤ ጥፋታችውንም ይለፍ።

አዲስ ለውጥ

17 Jan, 14:25


የተረጋጋ ሰው ሁሌም ትክክል እንደሆነ ሁሉ፤ ችኩል ሰው በጭራሽ ከስህተት አይድንም።

አዲስ ለውጥ

16 Jan, 09:09


ጊዜውን የሚያጠፋ ምሳሌው ሀብቱን ሁሉ ይዞ መጥቶ ባህር ውስጥ እንደጣለ ሰው ነው።

አዲስ ለውጥ

04 Jan, 07:52


Channel name was changed to «አዲስ አማርኛ adis amaregna»

አዲስ ለውጥ

04 Jan, 07:52


Channel photo updated

አዲስ ለውጥ

04 Jan, 05:41


ወርቅ ቢጠፋብህ አንድ ቀን መልሰህ ታገኘዋለህ፤ ሰከንድ ካለፈህ ግን መልሶ ማግኘት አይቻልም።

አዲስ ለውጥ

12 Apr, 07:49


አዲስ ለውጥ pinned Deleted message

አዲስ ለውጥ

17 Sep, 08:38


Channel created