በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك @abu_babelheyr_bin_sadik Channel on Telegram

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

@abu_babelheyr_bin_sadik


ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮ፦
👉 ከቁርኣን፣
👉ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]
👉 ከታማኝ ዑለማዎችና
👉ከትክክለኛ ቂያስ ተጠናቅሮ ይቀርብበታል።

ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ  @Abu_Sibewe ላይ አስፍሩት።

ስህተትም ባያችሁ ጊዜ አርሙኝ።
ጀዛኩሙል`ሏህ ኸይራ!

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك (Amharic)

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!! እስከ ናቡኩበልህር በተመለከት የምትሻገር ምንም ላይ ለማግኘት እንደዚህ መጠን አመታችሁ ማምረት አይጣልሁም። ከዚህበምት አትቁጠሩም። ድንቅና ተግባሩ ከሚባል በኃላፍን ምሳሌ እንዲሰማ አዳምጥ ትቀጣለህ! ከጠቡበልህርስ ዘመን ለዓለም በእግሩ ትውልስ መነስ አቅርብባታለሁ። በለስ ሲያምኑ። ከአምላካቸው በሊገባ ተዋቁ። ከግእዝአችሁ በብቻ መሽሁል ሆኖ አቅርብባታለሁ ብትላቸው እንኑርበረበር። ለምሳሌቸው በተስጠዋርለህ እንከፍሉዋለን። ሁንምራፋይቲ በመንፈሴ ይወጣል።

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

12 Feb, 19:14


◉አንድን ሰው ሙሉ ለሙሉ ስታምን ከሁለት ነገሮች አንዱን ታገኛለህ!!


❶የእድሜ ልክ ጓደኛ ወይም !!
❷የእድሜ ልክ ትምህርት!!


➴ሁለት ሸይኾች ታክሲ መሳፈር ፈለጉና አንዱ ሸይኽ ለባለታክሲው ስንት ትወስደናለህ?ብለው ጠየቁ
ባለታክሲውም ከነሱ ሂሳብ መቀበል አልፈለገምና 'ሊላህ' (ለአላህ ) ብየ ነው የምወስዳችሁ አላቸው
አንደኛው ሸይኽም ፦በነፃ ከሆነ
#በጣም_አስወደድከው ብለው መለሱ
አንድ ሰው ለአላህ ብሎ እርዳታ ሲያደርግልህ አንተ ነህ በነፃ  የተገለገልከው እሱ ግን ወጪ የማይሆን ሂሳብ. ለአኼራው አስቀምጧልና።

ጌታችን ሆይ! መልካም ሰርተው በመልካም ከምትመነዳቸው ባሮችህ አድርገን
  
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

12 Feb, 17:15


◉የረመዳን ወር አቀባበል!!

ክፍል ❶

ታላቁ እንግዳችን! የተከበረውን የረመዳን ወር ለመቀበል ሁሉም በየፊናው ተፍተፍ እያለ ይገኛል። ከፊሉ ቤቱን በማሰናዳት፣ ሌላው የምግብ አይነቶችን በመሸመት፣ እኩሉም የወሩን ትሩፋት ለመጠቀም እቅድ እያወጣ…ወዘተ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

ለመሆኑ ይህ አያሌ የፈጣሪ ትሩፋትን በውስጡ ይዞ የመጣውን ይህን ወር ለመቀበል ትክክለኛው መንገድ የትኛው ነው?

በወሩ ውስጥ ያሉትን እያንዳንዱን የጦዓ (አምልኮ) ወቅቶችን ሁሉ አሟጦ ለመጠቀም ምን ማድረግ ይጠበቅብናል? በነዚህ በተከበሩ ጊዜያት ውስጥ በኸይር ነገሮች መሽቀዳደም ያስፈልጋልና፤ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-

وَفِي ذَٰلِكَ فَلْيَتَنَافَسِ الْمُتَنَافِسُونَ

“በዚህም ተሽቀዳዳሚዎች ይሽቀዳደሙ።”(አል-ሙጦፊፊን 83፤ 26)
በመሆኑም ከዚህ በመቀጠል የረመዳንን ወር በተሻለ መንገድ ለመቀበል የሚረዱ መንገዶች እንጠቁማለን፡-

❶ ዱዐ ማድረግ፡- በፆም፤ በሶላትና በዚክር ላይ እንድትጠነክር አላህ (ሱ.ወ) በሙሉ ጤንነትና አቅም ላይ ሆነህ ረመዳን ወር እንዲያደርስህ ከአሁኑ ዱዓ አድርግ፤ አነስ ቢን ማሊክ (ረ.ዐ) ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) የረጀብ ወር ሲገባ እንዲህ ይሉ ነበር ብለዋል፡-

اللهم بارك لنا في رجب وشعبان وبلغنا رمضان

“አላህ ሆይ! ረጀብንና ሸዕባንን ብሩክ አድርግልን፤ ረመዳንንም አድርሰን” (አህመድና ጦብራኒ ዘግበውታል)።

ሰለፎች (ቀደምት ደጋግ አቦዎች) ረመዳንን እንዲያደርሳቸውና ከዚያም ሥራቸውን እንዲቀበላቸው አላህን (ሱ.ወ) ይለምኑ ነበር፤ ስለዚህ አንተም የረመዳን ጨረቃ ስትወጣ እንዲህ ብለህ ዱዓ አድርግ፡-

الله أكبر اللهم أهله علينا بالأمن والإيمان والسلامة والإسلام , والتوفيق لما تحب وترضى ربي وربك الله

“አላሁ አክበር አላህ ሆይ! ይህን ጨረቃ የአማንና የኢማን፣ የሰላምና የኢስላም፣ እንዲሁም አንተን የሚያስደስት ተግባር መስራት የምንችልበት ጊዜ አድርግልን፤ የኔም የአንተም ጌታ አላህ ነው፤” (ቲርሚዚ ዘግበውታል)።

❷ ምስጋና ማቅረብ፡- ረመዳን ወር ከደረስክ ምስጋና ለአላህ አቅርብ፤ ኢማሙ ነወዊይ አል-አዝካር በተባለው ኪታባቸው ውስጥ እንዲህ ብለዋል

“አንድ አዲስ ፀጋን ያገኘ ወይም አንድ ችግር የተወገደለት ሰው ለአላህን ምስጋና ለማቅረብ ሱጁድ አድረጎ አላህን በሚገባው መልኩ ማወደስ ይገባዋል።

”አላህን ማምለክና የሱን ትእዛዝ መፈጸም መቻል በራሱ አላህ (ሱ.ወ) ለአንድ ሙእሚን ከሚለግሰው ታላላቅ ፀጋዎች ነው።

አንድ ሙእሚን የረመዳን ወር ሲገባ በጥሩ ጤንነት ላይ መገኘቱ ብቻ ፀጋውንና ችሮታውን ለለገሰው አላህ (ሱ.ወ) ምስጋና እንዲያቀርብ የሚያስገድደው በቂ ነገር ነው፤

ስለዚህ የረመዳንን ወር በሰላምና በጤና የደረሰ ሰው ለአላህ (ሱ.ወ) ትልቅ ምስጋና ሊያቀርብና እሱን በብዛት ሊያወድስ ይገባል፤ ለልቅናውና ለግዙፍ ስልጣኑ የሚመጥን ታላቅ ምስጋናና ውዳሴ ለአላህ (ሱ.ወ) ይሁን!!

❸ መደሰት፡- ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) የረመዳን ወር ሲመጣ እንዲህ በማለት ባልደረቦቻቸውን ያበስሩ እንደነበር ተረጋግጧ፡-

جاءكم شهر رمضان شهر مبارك كتب الله عليكم صيامه فيه تفتح أبواب الجنان وتغلق فيه أبواب الجحيم

“የተባረከው የረመዳን ወር መጥቶላችኋል፤ እሱን መፆም አላህ (ሱ.ወ) በናንተ ላይ ደንግጓል፤ በረመዳን ወር የጀነት በሮች ይከፈታሉ፤ የገሀነም በሮች ደግሞ ይዘጋሉ”(አህመድ ዘግበውታል)።

ሰሐባዎችንና ታቢዒዮችን ጨምሮ ያለፉት ደጋግ አቦዎች (ሰለፎች) ለረመዳን ወር ልዩ ትኩረት ይሰጡ ነበር፤ ረመዳን ሲመጣም ይደሰቱ ነበር፤ አዎ ይህ ትልቅ ደስታ ነው!

የኸይርና የአላህ እዝነት መውረጃ የሆነ ወቅት ሲመጣ ጤና ሆኖ በሂይወት ከመኖር የበለጥ የሚያስደስት ነገር አለን?!

❹ ወሩን በአግባቡ ለመጠቀም መወሰንና ቀድሞ እቅድ ማውጣት፡- ብዙ ሙስሊሞች- ዲነኞችን ጨምሮ- ለዱንያ ጉዳያቸው በሚገባ እቅድ ሲያወጡ ይታያሉ፤ ነገር ግን ለአኺራቸው እቅድ በማውጣት የሚሰሩት ጥቂቶች ናቸው።

ይህም የሚሆንበት ምክንያት ሙእሚን በዚች ህይወት ያለውን መልዕክት ካለመረዳትና አንድ ሙእሚን ነፍሱ በአላህ ዲን ላይ ፅናት እንዲኖራት ራሱን ለማለማመድ ከአላህ ዘንድ የሚገኙ መልካም አጋጣሚዎች ችላ ከማለት የሚመነጭ ነው።

ለአኺራ ከምናቅድባቸው ጉዳዮች መካከል የረመዳንን ወር በጧዐና ኢባዳ ለማሳለፍ የምናደርገው ዝግጅትና እቅድ አንዱ ነው፤ ስለሆነም ማንኛውም ሙስሊም የረመዳንን ወር በትክክል አላህን በመታዘዝ ማሳለፍ እንዲችል ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ፕሮግራም ማውጣት ያስልገዋል።

❺ ቁርጠኛ አቋም፡- የረመዳንን ወር በመልካም ሥራዎች ለመሙላት ቁርጠኛ አቋም መያዝ። ከልቡ በእውነት ወደ አላህ የቀረበ ሰው አላህ ይቀበለዋል፤ እሱን ለመገዛትና ኸይር ለመስራትም ያግዘዋል፤ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-

فَلَوْ صَدَقُوا اللَّهَ لَكَانَ خَيْرًا لَّهُمْ

“እውነተኞች በኾኑ ኖሮ ለእነርሱ የተሻለ በኾነ ነበር።” (ሙሐመድ 47፤ 21)

   
#ሼር #ሼር ይደረግ

ክፍል ❷

  ቀ
     ጥ
      ላ
       ል
 
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

11 Feb, 18:55


እጅግ በርካታ ሰዎች በሚዘነጉበት ወር ትልቅ እድል እስቲ ወጣ ብላቹ ጨረቃዋ እንዴት እንዳሸበረቀች ተመልከቷትማ

ነጌ ጀምሮ እስከ ጁሙዐ አያመል ቢድ ነው እንዳያመልጠን

ነጌ ሮብ 13
ሀሙስ 14
ጁሙዐ 15

የአላህ መልእክተኛ ﷺ"በረጀብ እና በረመዷን መካከል የሚገኘው የሸዕባን ወር ብዙ ሰዎች የሚዘናጉበትወር ነው።
በዚህ ወርም መልካም ሥራዎች ወደ ዓለማት ጌታ ይቀርባሉ እኔደግሞ ((ፆመኛ)) ሆኜ ሥራዬ እንዲወጣልኝ እወዳለሁ ብለዋል።"


መፆም ባንችል እንኳ ሌላውን እናስታውስ

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

11 Feb, 16:52


قال بعد أهل العلم
شهر شعبان شهر تخلية
وشهر رمضان شهر تحلية


የሸዕባን ወር ውዳቂ ከሆኑ ተግባሮቻችን እራሳችንን ለማፅዳት የምንታገልበት እና ፅድት የምንልበት ወር ሲሆን

የረመዳን ወር ደሞ በተለያዩ መጌጫዎች የምናጌጥበት ወር ነው

ቆሻሻውን ማስወገድ ከማስጌጥ ይቀደማል❗️


☞ለረመዳን መዘጋጀት ያስፈልጋል

وقال تعالى :( ﻭَﻟَﻮْ ﺃَﺭَﺍﺩُﻭﺍ ﺍﻟْﺨُﺮُﻭﺝَ ﻷَﻋَﺪُّﻭﺍ ﻟَﻪُ ﻋُﺪَّﺓً )
(መውጣትን ቢፈልጉ ኖሮ መዘጋጀትን ይዘጋጁ ነበር )

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

10 Feb, 17:58


➴➴ምንኛ ያማረች ምክር


◉ አያት ለልጅ ልጁ የመከረው ጣፋጭ ምክር!

√➳ የምትወደውን ሰው ማሞገስ አታብዛ፣
√➳ ጌታውን ከማይታዘዝ ሰው ጋር አትጓዝ፣
√➳ ቁጭ ስትል ሰዎችን አትማ፣
√➳ በራሱ ጊዜ ከአንተ የራቀን ጓደኛ ለመቅረብ አትሯሯጥ፣
√ ራስህን አታቅል፥ አትኩራ፣
√➳ እጅግም አትለሳለስ፥ እጅግም አትንጠባረር፣
√➳ እውነቱን የሚያወራ ሰው በብዛት አይምልም፥ ታማኝ ሰው ራሱን መልካም አድርጎ አይስልም፣
√➳ ሥራውን ለአላህ ብሎ የሚሠራ ሰው ኋላ ላይ አይጸጸትም፣
√➳ ቸር ሰው አይመጻደቅም፣
√➳ ራስህን ሁን፥ ሌሎች እንደሚፈልጉት አትሁን፣
√ ➳ሰዎችን ማክበርህ የሆነ የምትፈልግባቸው ጉዳይ አለ ማለት አይደለም። ስለ ዲንህና አስተዳደግህ ልታስተምራቸው ጅማሮ እንጅ፣
√ ➳አክብር → ትከበራለህ!
√➳ በጸባይህ ውብ ሁን!
√➳ ባለህ ተብቃቃ፥ ራስህን ዝቅ በማድረግ ትልቅ ሁን።
√➳ ከኋላህ ሆኖ ስለአንተ ወደሚያወራ ሰው አትመልከት። ምክንያቱም እርሱ በመሠረቱ ከኋላህ እንጅ ከፊት ለፊትህ አይደለም።
√➳ ከቁርኣን ምን ያክል እንደምትሸመድድና እንደምትቀራ ለሰዎች አትንገራቸው። ይልቁንም በአንተ ውሰጥ ቁርኣንን እንዲያዩ አድርጋቸው።
√➳ የተራበን አብላ፣ የተራቆተን አልብስ፣ እርዳታህን የሚሻን አግዝ፣ ለየቲም እዘን፣ የበደለህን እለፈው፣ ለወላጆችህ መልካም ዋል፣ ለሁሉም ፈገግ በል!
√➳ ቁም ነገሩ ከቁርኣን ምን ያክል ደርሰሐል ወይንም ሸምደሃል ሳይሆን፤ ቁርኣን በአንተ ውስጥ የት ደርሷል የሚለው ነው።


https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

09 Feb, 18:25


وَصَـايَـا جَليلَة من الشيخ الفوزان حفظه الله تعالى :

📌قـال الـشّيخ الـعلّامة صالح بن فوزان الـفوزان حفظه الله تعالى :
ሸይህ ፈውዛን እንድህ ይሉናል

الّذِي نـُوصِي بِهِ أَنـفُـسَنَـا وَإِخْـوَانَنَـا :
እኔ ለራሴም ለወንድሞቸም የምመከረው
①- تَـقـْوَى الله والـتّمَسُـكُ بِمَنْـهَجِ الـسّـلـفِ الـصَّالـِحِ
አላህን መፍራት እና የሰለፎችን ፣ የሷሊሆችን መንገድ አጥብቆ መያዝ

②- الـحـَذَرُ مِنَ الـبِـدَعِ وَالـمُبْتَدِعـِينَ،
ከቢደዓ እና የቢደዓ ሰወችን እራቅ

③- الـعِنَـايَة بـِدِرَاسَـةِ الـعَقِـيدَةِ الـصَّحِيْحـَةِ وَمـَا يُضَـادُّهَـا،
አቂዳን በመማር በማስተማር አቂዳን ወይም እምነትን የሚቃረኑ ነገሮች በመማር ሰወችን በማስተማር መታገዝ

④- الأَخـْذَ عَنِ الـعُلَمَـاءِ الـمُوْثُوقِينَ فِي عِلْـمِهِمْ وَفي عَـقِيدَتـِهِمْ،

እውቀትን አቂዳን ትክክለኛ ከሆኑ ኡለሞች በሀቅ ጎዳና ካሉ ኡለሞች ላይ መውሰድ ወይም መማር
⑤- الـحَذَر منْ دُعـاةِ الـسُّـوء الـذّيْن يُلـبِسُـونَ الْـحـَقّ بِالـبَاطِـلِ.
ወደ መጥፎ ከሚጣሩ ዳኢወች መጠንቀቅ ፣መራቅ እነዛ እውነታን በውሸት የሚያለባብሱ የሆኑ መጥፎ የሆኑ ኡለሞ
📖: الأجوبة المفيدة (س١١٢)

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

09 Feb, 16:59


ሱፍያኑ_ሰውሪይ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ :

«በዕድሜው የተጫወተ የመዝሪያው ወቅት ላይ ይጠፋል፣ የመዝሪያው ወቅት ላይ የጠፋ ደግሞ የማጨጃው ወቅት ላይ ይፀፀታል።»

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

09 Feb, 04:24


أذكار الصباح ☕️

اللّهُـمَّ عالِـمَ الغَـيْبِ وَالشّـهادَةِ فاطِـرَ السّماواتِ وَالأرْضِ رَبَّ كـلِّ شَـيءٍ وَمَليـكَه ، أَشْهَـدُ أَنْ لا إِلـهَ إِلاّ أَنْت ، أَعـوذُ بِكَ مِن شَـرِّ نَفْسـي وَمِن شَـرِّ الشَّيْـطانِ وَشِرْكِهِ ، وَأَنْ أَقْتَـرِفَ عَلـى نَفْسـي سوءاً أَوْ أَجُـرَّهُ إِلـى مُسْـلِم.
(مره واحده).

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

09 Feb, 04:24


‏﴿ وَمَا خَلَقْنَا السَّمَاء وَالأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا بَاطِلا ذَلِكَ ظَنُّ الَّذِينَ كَفَرُوا ‏﴾
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

09 Feb, 04:09


አባት ያላችሁ አላህ ረጅም እድሜ ይስጥላችሁ
ሁሉም ነገር ሚታወቀው ከኛ ሲርቅ ነውና ወላጅ ያላቹ ተጠቅሙባቸው አባት ለሌለን አላህ በጀነት ያገናኘን ያረብ

አባቴ አላህ ይዘንልህ ቀብርህ የጀነት ጨፌ ያድርግልህ ያረብ

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

08 Feb, 17:05


زاحموا سَيِّئَاتِكُم بِالِاسْتِغْفَار .

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

08 Feb, 17:04


መሳቅ የተሻለ መድሀኒት ነው ነገር ግን ያለ ምክንያት የምትስቅ ከሆነ ሌላ መድሀኒት ያስፈልገሀል።

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

08 Feb, 05:00


{فَقُلْتُ اسْتَغْفِرُوا رَبَّكُمْ إِنَّهُ كَانَ غَفَّارًا}

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

08 Feb, 04:55


አልከሶ ላይ የሚደረጉ የሽርክ አይነቶች  በጥቂቱ በስልጥኛ ቋንቋ !!



❶ አልከስዬን ካሌ ዩለ አቦተ = ዮክቤ ረክቤን ወዬ በጫረተ

❷ ዮልዬይ ወልዬ አልከስዬ = የረህመተይ በረ ክፈቱዬ

❸ ያልከሶ አባባዬ ትልብል ትልብል = ለማኒ ጣልኩሙኝ ውርውር ልልብል

❹ ያልከሶ አባብዬ ኑዲኒሞ = ኤወዲ እለፈዲ ብለኒሞ

❺ ብንጥረታም ውስጥ ኡፍታሙ ሙለ = አቤት አቤት ይላን የሙሪዲ በላ

❻ አልከስዬን ካሌ ባዬት አለ = የትቆጬ ህንጣብተ ያበቀለ

❼ ያልከሶይ ጎተረ ባባተረ = ለኘ ልዮቡነ ምን ሀተረ

➑ ምንን በባሉሞ ትመጦሞ = አቤት አቤት ህላን በላይ ሰቦ

➒ ያልከሶ አባባዬ ላአሏህ በሎ = ይንጭነናይ ደዊ እትደሎ

❿ ህንጥረት ህንጥሮ ለዙረነ = ተላላፊ ነቶ ለይነቺነ 

=============

ይህነው ሽርክ ማለት !! ቀላል ነገር  አድርገን ማያት የለብንም !! ከቤተሰቦቻችን ጀምረን አከባቢያችነን ጭምር ልናስጠንቅቅ ይገባል ባይነኝ !!
منقول
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

07 Feb, 19:22


‏﴿ قُلِ اللَّهُمَّ مَالِكَ الْمُلْكِ تُؤْتِي الْمُلْكَ مَن تَشَاءُ ‏﴾

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

07 Feb, 18:35


.              ꧁ ﷽ ꧂
.  ╔════❁════❁════╗
.  ሽርክ ማለት ምን ማለት ነው
.  ╚════❁════❁════╝
.     
🍃 هو جعل شريك لله تعلى في ربوبيته وإلهيته.

.       📚 ሽርክ ማለት ፦  በሶስቱ የተውሂድ ክፍሎች አጋር ማድረግ ነው።
በተለይ ደግሞ የተውሂድ አንኳር በሆነው በአላህ ብቸኛ ተመላኪነት ( ተውሂድ አል– ኡሉሂያ) አጋር ማድረግ ነው።

🍃 قول الله تعلى:
[ وعبدوٱ الله ولا تشركوا به،شَيٕاً].

[ አላህን ተገዙ በሱም ላይ አንዳችን እንዳታጋሩ(እንዳታሻርኩ)].

🍃 قول الله تعلى:
{ قل هو الله احد } [الإخلاص:١].

[ በል እርሱ አላህ አንድ ነው]

መልእክተኞች በአጠቃላይ ወደዚሁ ተውሂድ  እንዲጣሩና ከሽርክ እንዳስጠነቅቁ  ነው የተላኩት .
     አላህም ይላል

🍃 قول الله تعلى፡
{ولقد بعثنا فى كل أمة رسولا ان ٱعبدوا الله وجتنبو اطغوت} [النحل:٣٦].

[ በእርግጥም ልከናል በሁሉም ኡመቶች (ህዝቦች) ላይ መልእክተኛን አላህን እንዲገዙ እንዲርቁም ከአላህ ውጭ ማምለክን (ጣጉት)].


. ╔══════ ❁✿❁ ═══════╗
.    የትልቁ ሽርክ አይነቶች
. ╚══════ ❁✿❁ ═══════╝

🍃 الشرك ينقسم الا القسمين.

1⃣ الشرك الأصغر.
2⃣ الشرك الأكبر.


. 📚ሽርክ በዋናነት በሁለት ይከፈላል፦
.        1 ሽርከ አል– አስገር ።
.        2 ሽርከ አል– አክበር።
.       
የታላቁ ሽርክ አይነቶች– በአጭሩ–              ① ከአላህ ውጭ ለሆነ አካል መሳል            ② ከአላህ ውጭ ለሆነ አካል ማረድ          ③ ድግምት                                       ④ ጥንቆላ                                             ⑤ ከአላህ ውጭ ሌላን አካል መለመን                 ⑥ ከአላህ ውጭ ሌላን አካል መፍራት        ⑦ ከአላህ ውጭ ባለ አካል መመካት         ⑧ በውዴታ ማጋራት                               ⑨ በመታዘዝ ማጋራት                              ⑩  በኢስቲጋሳ ማጋራት                          ·                    الدال على الخير كفاعله

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

07 Feb, 12:25


"የትኛው ይበልጥ ይደንቅችዋል ?

የረሱልን ደም ድፋ ተብሎ ደሙን ጭልጥ አርጎ የጠጣውን ሶሀባ ፍቅር?

ወይስ ሀቢቡና ለቀናት ሲለዩት ያማረ ገፅታው እና ሰውነቱ ከስቶ የጠበቃቸው ሶሀባ ፍቅር ?

ነው ወይስ ሀቢቢ ከሞቱ በኋላ በህልማቸው አይቷቸው ከመጣ በኋላ አዛን ማውጣት ያቃተው ናፍቆት?

አሊያም ደሞ እንደሞቱ ሲያረዱት ህልፈታቸውን በጉልበት ላለማመን ሰይፍ እመዛለሁ ያሉት ጥልቅ ፍቅር?

በጦር አውድማ ከቤተሰቧ ህልፈት ባሻገር የነቢ መኖር ያስደሰታትስ ቢሆን ታሪኳ የወርቅ ብእር እንጂ ሌላ አያሻውም እንደው በመለክ እንጂ ሰው አይፅፈውም የተባለላት?

በአዛኙ ነብይ ላይ ሰላዋት እናውርድ

አላሁመሰሊ ወሰሊም ዓላ ሃቢቢና ሙሐመድ
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

06 Feb, 18:28


በውስጥህ የምትይዛቸው እንደ ቂም፣ ቁጣና ጥላቻ ያሉ ስሜቶች አንተ ጠጥተሃቸው ሌላ ሰው እንዲሞት የምትጠብቅባቸው መርዞች ናቸው።

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

06 Feb, 18:00


‏«ألا بذكرِ الله تطمئنُ القُلوب»

ድካም ፣ መረበሽ ፣ ሃሳብ መበታተን እና ጭንቀት ሲያጋጥመን አላህን ከማስታወስ የበለጠ ከነዚህ ስሜቶች ሊያወጣን የሚችል ምንም መፍትሄ የለም
ሁሉንም ነገር ትተን አላህን ማሳታወስ ስናዘወትር በአዲስ ስሜት አዲስ እና የተለየ እስትንፋስ ይኖረናል

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

06 Feb, 04:03


{ إِنَّ ٱلۡمُتَّقِينَ فِي جَنَّٰتٖ وَعُيُونٍ }🌄


📌«እነዚያ (ከኀጢአት) የተጠነቀቁት በአትክልቶችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

06 Feb, 03:57


በአላህ ላይ መመካት
ወደ እሱው መጠጋት
ያለ አንተ ምን ዋጋ አለኝ ማለት
ለስኬት መብቂያ እና ከመከራ መጠበቂያ አዋጩ መንገድ ነው።

( ሺንቂጢይ)

{ وَأُفَوِّضُ أَمْرِي إِلَى اللَّهِ إِنَّ اللَّهَ بَصِيرٌ بِالْعِبَادِ }
{ فَوَقَاهُ اللَّهُ سَيِّئَاتِ مَا مَكَرُوا }. [سُورَةُ غَافِرٍ: ٤٤-٤٥]

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

05 Feb, 18:34


‏﴿اقْرَأْ كِتَابَكَ كَفَىٰ بِنَفْسِكَ الْيَوْمَ عَلَيْكَ حَسِيبًا﴾

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

05 Feb, 18:33


ከአላህ ውጪ ያሉ መጠጊያዎች ሁሉ መጥፊያ ናቸው

መዳንን ከፈለክ ወደ ጌታህ ብቻ ተጠጋ

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

05 Feb, 18:15


ዒልም ኖሮት!
አደቡ አኽላቁ (ስነ–ምግባሩ) የወረደ የዘቀጠ መሆኑን ቢያውቅ ኖሮ!
ዒልምን ከመማሩ በፊት አደብን አኽላቅን (ስነ - ምግባርን) ይማር ነበር!!

አብደሏህ ኢብኑ ሙባረክ -ረሒመሁላህ-
እንዲህ ይላሉ: -
ስነ-ምግባርን ለሰላሳ ዓመታት ያህል ተማርኩኝ! ዒልምን ግን ለሀያ ዓመታት ተማርኩኝ!!!
[غاية النهاية في طبقات القراء(١/١٩٨)]

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

05 Feb, 18:12


قال الإمام أحمد بن حَنْبَل رحمه الله:

"الدنيا دار عمل، والآخرة دار الجزاء، فمن لم يعمل هنا ندم هناك".

📚ذيل طبقات الحنابلة ١/ ٢٩٨.

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

05 Feb, 05:55


📮 ረድ 030 አር-ረሕማን ከዐርሹ በላይ ከፍ አለ

🔖 አላህ ከዐርሹ በላይ ስለመሆኑ እና ዐርሽ ደግሞ ከሰባቱ ሰማያት በላይ ለመሆኑ ከቁርኣን ከሐዲስ በቀደምቶች አረዳድ የተብራራበት ትምህርት...

🔖 በተጨማሪም የነ ኢማሙ አቡ ሐኒፋ ኢማሙ ሻፊዒ ኢማሙ ማሊክ በዚህ ጉዳይ ላይ ያላቸው አቋም ተዳሰውበታል።

🔖 አህባሾች ለሚያመጡት ሹቡሃ መልስ አለበት።

📌 በሚል ርዕስ በጥያቄ እና መልስ የቀረበ እጥር ምጥን ያለ መደመጥ ያለበት 030 ኛ ረድ።

🎙 በኡስታዝ:- አቡ አሲያ አብደላህ አላህ ይጠብቀው።

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

04 Feb, 21:16


አንደኛው እንዲህ አለ:-

‏- القلب مفتوحٌ لكل نزيلةٍ …
‏                      تبغى الإقامة والمكان رحيبُ”


ለመጣችው ሁሉ ልቤን ከፈትኩላት
መኖር ለፈለገች ምቹ ማረፊያ ናት

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

04 Feb, 21:13


.
                     ⭕️ጠቃሚ ምክሮች‼️



قـالـ الإمام الحافظ ابن القيم - رحمه الله -

۞ أربعة تهدم البدن
❶ - الهم ..
❷ - والحزن !!
❸ - والجوع
❹ - والسهر
ኢብኑል ቀይም እንዲህ ይላል:-

☆ አራት ነገራቶች ሰውነትን ያደክማሉ
__ ሀሳብ ማብዛት
__ ትካዜ
__ ረሀብ
__ እንቅልፍ ማጣት



۞ وأربعة تزيد في ماء الوجه وبهجته
❶ - المروءة !!
❷ - والوفاء
❸ - والكرم
❹ - والتقوى

☆ አራት ነገራቶች የፊት ውበት ይጨምራሉ

__ አደብ(መልካም ስነ ምግባር)
__  ቃል መጠበቅ
__ የአላህ ፍራቻ
__ መልካምነት (ደግ)

۞ وأربعة تجلب البغضاء والمقت
❶ - الكبر ..
❷ - والحسد !!
❸ - والكذب .
❹ - والنميمة !!

☆ አራት ነገር ጥላቻን ያስወርሳሉ
__  ኩራት
__ ምቀኝነት
__ ውሸታምነት
__ ነገር ማዋሰድ


۞ وأربعة تجلب الرزق
❶ -  قيام الليل ..
❷ - وكثرة الإستغفار بالأسحار .. !!
❸ -  وتعاهد الصدقة !!
❹ - والذكر أول النهار وآخره


☆ አራት ነገር ሪዝቅን ያሰፋሉ

__ ለይል መስገድ
__ ለሊት የሚደረግ እስቲግፋር
__ ሰደቃ ማብዛት
__ ከቀኑ መጀመሪያና መጨረሻ የሚደረግ ዚክር


۞  وأربعة تمنع الرزق
❶ - نوم الصبحة ..
❷ - وقلة الصلاة  !!
❸ - والكسل ..
❹ - والخيانة !!

☆ አራት ነገር ሪዝቅን ያጣብባሉ:-

__ የጧት እንቅልፍ
__ ሶላት ማሳነስ
__ ስልቹነት
__ አታላይነት


📚ዛድ አል መዓድ

❒ انظر [ زاد المعاد (٣٧٨/٤) ]
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

03 Feb, 18:32


«ከጩኸት ዝምታ እጂጉን ይሰማል፡»
«አስተውሎ ማዝገም ከሩጫ ይቀድማል፡»
      .....ኑር.....

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

03 Feb, 04:12


ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል።
በዱንያ ላይ ካሉ ትልልቅ ቅጣት ውስጥ አንዱ፦ ምላስህ አላህን እንዳያወሳ መያዙ ነው።
ምክንያቱም አላህ በተከበረው ቁርአኑ እንዲህ ብሏልና፦
【اسْتَحْوَذَ عَلَيْهِمُ الشَّيْطَانُ فَأَنسَاهُمْ ذِكْرَ اللَّهِ ۚ أُولَـٰئِكَ حِزْبُ الشَّيْطَانِ ۚ أَلَا إِنَّ حِزْبَ الشَّيْطَانِ هُمُ الْخَاسِرُون
◉በእነርሱ ላይ ሰይጣን ተሾመባቸው፡፡ አላህንም ማስታወስን አስረሳቸው፡፡ እነዚያ የሰይጣን ጭፍሮች ናቸው፡፡ ንቁ! የሰይጣን ጭፍሮች ከሳሪዎቹ እነርሱ ናቸው
(ሱረቱ አል-ሙጀድላህ )

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik
    

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

02 Feb, 05:45


◉ማንነት መለኪያ !!!

አይደል ጀለብያህ ኮፍያ ጥምጣሙ
አንደበተ ጣፋጭ በንግግር ጣሙ

አይሆንም ጅልባቡ ቢለበስ ኒቃቡ
የሠለፎች መንገድ ሣይሞላ አደቡ

ምላስ ቢያወራ ከሌለ ተግባሩ
ቂርአት ደርድሮ በእሡ ካልሠሩ

ቢድዓን ትተው በሡና ካልኖሩ
ሽርክን አባረው ተውሂድ ካልተማሩ

ምን ጠቅሞ እውቀት መባሉስ ቀሩ
አሊም ሼኽ ናቸው ሽርጥ አሣጠሩ

ጅልባብ ኒቀቡም መልበሷ ነው ጥሩ
ምንም ጥቅም የለው ከላይ ማማሩ

ውስጥ በተቅዋ አላህን ካልፈሩ
ለሠው መስሎ መኖር ምን ይሆን ቀመሩ

ስለዚህ እንትጋ ውስጥ  ማሣመሩ
እላይን የማያይ ነው የፈጠረን ጀባሩ

ውስጥ ካጡሩ ከላይ ለማሣመር
በቂ ነው ጌታችን ማንም ሣይጨመር

  👑መልክ ኣለኝ በለህ አትመፃደቅ‼️

መች ጠቅሞ  ቁንጅና ሣይኖርበት ፀባይ
ስንት ዘመን መጥቷል ሣይገደብ አባይ

እላያችን አምሮ ቢቀመጥ በሙዳይ
ህይወት ጠዕም የለው በመጥፎ ፀባይ ላይ

ሠው አይኖር ከመልክ ከብር ጌጣጌጥ
ፉንጋነት ማን አይቶት በፀባይ ሲያጌጥ

በጥሩ ስብእና በመልካም ምግባር
የመልክ ቁንጅናን ሣይበልጠው አይቀር።
     
     
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

02 Feb, 05:40


◉ሶስት ነገሮች እውቀትን ይጨምራሉ

❶➳ከሊቃውንት ጋር መቀመጥ
❷➳እውነተኞች ጋር መዋል
❸ ➳የማይመለከተን ነገር አለመናገር።

          [ኢማሙ-ሻፍዒይ ረሂመሁላህ]


https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

31 Jan, 04:47


🎙 ሱረቱ አል ካህፍ

إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا

ሱረቱል  ካፍ   
ከጁመዓ ቀን ሱናዎች
↩️‏ سنن_يوم_الجمعة
➊ الغسل
➋ الطيب
➌ السواك
➍ لبس الجميل
➎ قراءة سورة الكهف
➏ التبكير لصلاة الجمعة
➐ الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي ﷺ
🔹ገላን መታጠብ
🔹ሽቶ መቀባት
🔹ሲዋክ መጠቀም
🔹ጥሩ ልብስ መልበስ
🔹ሱረቱ ከህፍን መቅራት
🔹በጧት ለጁመዓ ሶላት መጣድ
🔹በነብዩ ﷺ ላይ ዱዓና ሰለዋት  ማብዛት

اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد
      
الَّلهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّد ٍﷺ 
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

30 Jan, 18:00


"ثم خلقنا النطفة علقة ...
فتبارك الله أحسن الخالقين

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

29 Jan, 18:34


በዛሬው ረቡዕ ምሽት፣ የሸዕባን ወር አዲስ ጨረቃ መታየት ባለመቻሏ የሸዕባን ወር የሚጀምረው
ከነገ ወዲያ ጁሙዐ ጥር 23 ቀን 2017 ይሆናል፡፡

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

29 Jan, 04:19


◉ስንቅ

➴ጀነትን የሚከጅል ሰው ለመልካም ስራ ይጣደፍ።
➴ጀሀነምን የሚፈራ ደግሞ ከፈተናዎች ይጠበቅ።
➴ሞት አይቀሬ መሆኑን ጠንቅቆ ያወቀ ደስታን ይታቀባል።
➴የዚህችን አለም ምንነት የተረዳም መከራ ሲገጥመው በጽናት ይሸከማል»
ዐሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ)


https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

29 Jan, 04:15


አናስጠላም?ትላንት ተሰብረን የጠገነንን፣ አጥተን ያስገኘንን ጌታ መሻታችን ከሞላ ቡሃላ እሱን ማስታወስና ወደሱ መሮጥን እንዘነጋለን::

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

28 Jan, 18:01


📚አጠር ያለ ፁሁፍ ለአህባሾች እና መሰሎቻቸው ከፊል ጥያቄውች ተካተዋል ....


👇👇 ተቀላቀሉ👇👇
https://t.me/httpgoto
https://t.me/httpgoto

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

28 Jan, 17:50


ወደ ወንጀል በተጠጋህ ቁጥር ' ተው መዋረድ ይቅርብህ፣ ወደነበርክበት ቦታህ ተመለስ !' የሚልህ ብርቱ ቀልብ አላህ ይስጠን

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

28 Jan, 17:48


አደገኛ መተግበሪያ በማኅበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ መሆኑን ንግድ ባንክ አስታወቀ‼️

#Ethiopia  | ከጫናችሁ ያለፈቃድ ገንዘብ ይቆረጥባችኃል!

ደምበኞች በዋትስ አፕ እና በቴልግራም የሚሠራጭ Pharma+/CBE Vacancy መተግበሪያን እንዳይጭኑ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሳስቧል።

ባንኩ ባስተላለፈው የማስጠንቀቂያ መልዕክት፤ ባደረገው ምርመራ መሠረት አደገኛ መተግበሪያ ማግኘቱን ገልጿል።

ይህ Pharma+/CBE Vacancy የተሰኘ አሳሳች መተግበሪያ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በሰፊው እየተሰራጨ እንደሆነ በመጥቀስ፤ ይህ መተግበሪያ በቴሌግራም እና ዋትስአፕ ወደ ደንበኞቹ እየደረሰ መሆኑን ጠቁሟል።

መተግበሪያው በስልክ ላይ ከተጫነ ያለ ፈቃድ ገንዘብ ማስተላለፍ እንደሚችልም አሳውቋል።

ባንኩ ከዚህ አይነት አደጋ ለመጠበቅ ከቴሌግራም ወይም ዋትስአፕ መተግበሪያዎችን አታውርዱ ብሏል።

ደንበኞች መሰል ተግባራት ሲገጥሟቸው በ951 ነጻ የስልክ መስመር ደውለው እንዲያሳውቁ አሳስቧል።

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

27 Jan, 17:55


🛤በውስጥ መስመር የተላከልኝ ማስታወሻ
- ስሞት አላስብም፣ አልጨነቅም፣

- ገላዬ ፈራሽ ነውና ምን አሳሰበኝ

ሙስሊም ወንድሞቼ መደረግ ያለበትን ሁሉ ያደርጉልኛል፡፡

1- ልብሴን ያወልቃሉ፣

2- ያጥቡኛል፣

3- ይከፍኑኛል፣

4- ከቤቴ ይዘውኝ ይወጣሉ፣

5- ወደ አዲሱ ቤቴ (መቃብር) ይወስዱኛል፣

6- ብዙዎች ጀናዛዬን ለመሸኘት ይመጣሉ፣

7- እኔን ለመቅበር ሥራቸውንና ቀጠሯቸውን ሁሉ ትተው የሚመጡ አሉ፡፡

ቀጠሯቸ መካከል ምናልባት ላንዳፍታ እንኳን ስለኔ አስበው የማያውቁ ብዙ ናቸው፡፡

8- ቤተሰቦቼ እኔን ላለማስታወስ ያለኝን ነገር ሁሉ አውጥተው ይጥሉ ይሆናል፤ አሊያም በኔ ሥም ይመፀውቱ ይሆናል

- ቁልፎቼ 🔑🗝

- መጽሐፎቼ 📚

- ጫማዎቼ 👟

- ልብሦቼ 👖👔…..

በአንድ ነገር ግን እርግጠኛ ሁኑ፡፡

- በመሞቴ ይህች ዱንያ ሐዘኗ አልበዛም፣ አለች አልፈረሠችም፣

- የዓለም 🌍 እንቅስቃሴም ላፍታ አልቆመም፣

- የኢኮኖሚው 💰 ቀውስም አልተፈጠረም፣

- በሥራ ቦታዬ ላይ ሰው ለመቅጠር ማስታወቂያ🧾 ይወጣል፣

- ንብረቴ 💸🏠🚘 የወራሾቼ ይሆናል፣ በትንሽ በትልቁም ኦዲት የምደረገው ግን እኔ ነኝ፣

- ስሞት መጀመሪያ ከኔ የሚገፈፈው ስሜ ነው፡፡ በሥሜ መጠራቴ ይቀራል፤

- ጀናዛው የታለ እባላለሁ፡፡ ጀናዛውን ዉሰዱ፣ አምጡ እንስገድበት፣ ጀናዛውን እንቅበር … ይባላል

- ሥልጣኔ፣ ከተከበረ ቤተሰብ መሆኔ፣ ጎሳዬ … ሁሉ ዋጋ ያጣል፤



ዱንያ ይህን ያህል ቀላልና ተራ ነገር ነች፤ የምንሄድበት ዓለም ግን አቤት ክብደቱ! ማስፈራቱ! …

በሕይወት ያለህ ወዳጄ ሆይ! በመሞትህ ሦስት ዓይነት ሐዘን አለ

1- የሚያውቁህ ዋ ያ ሚስኪን እኮ ሞተ! ይላሉ

2- ባልደረቦችህ ለሰዓታት አለያም ለቀናት ያዝኑና ወደ ሳቅና ጨዋታቸው ይመለሳሉ፣

3- ትልቁ ሐዘን ያለው ቤትህ ነው፣ ቤተሰብህ ጋ … ሁሌም ያስታውሱህ ይሆናል፣

የዱንያ ታሪክህ በዚህ መልኩ አበቃ ፤ የመጨረሻው ዓለም ታሪክህ ተጀመረ

ሁሉ ነገርህ ተወሰደ፣ ፈረሠ፣ አለፈ፣ ጠፋ!!!

1- መልክህ፣

2- ሀብትህ፣

4- ጤናህ፣

5- ልጅህ፣

6- ቪላህ፣

7- ዝናህ፣

8- ሚስትህ/ባልሽ

ካንተ ጋር ሥራህ ብቻ ቀረ

እውነተኛው ሕይወት ተጀመረ፡፡

እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ/ሽ

ለአኺራህ ምን አዘጋጀህ!! እስቲ በጥልቀት አስብ፡፡

እናም በርታ፣ በርቺ እህቴ

1- በግዴታዎች፣

2- በሱንና ነገሮች፣

3- በድብቅ መፅውት፣

4- መልካም ሥራ አብዛ፣

5- ሌሊት ተነስተህ ስገድ፣

ትድን ዘንድ ጠንክር፣ ይሳካልህ ዘንድ በርታ፡፡
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

27 Jan, 17:03


🐌ከቀንድ አውጣው እንሰሳ የተሰራው ቅባት ነጃሳ ነው ወይስ ጠኃራ⁉️

Snail Hair Oil

(ነፍሳቶች Insects)

👌በሶብርና በትዕግስ ይነበብ።ለሌ ሎችም ሼር ይደረግ። ባረከሏሁ ፊኩም።

መንደርደሪያ ቀንድ አውጣው ሁለት አይነት ነው።በሪይ( በየብስ የሚኖር) በሕሪይ (በበሕር ውስጥ የሚኖር) በበሕር ውስጥ የተገኘ እንሰሳ ምንም ይሁን ምን ሀራምነታቸው ከተጠቀሱት (እንቁራሪ…) በስተቀር ሀላል ነው። የላቀው ጌታ እንዲህ ይላል ፦

أُحِلَّ لَكُمْ صَيْدُ الْبَحْرِ وَطَعَامُهُ مَتَاعًا لَّكُمْ وَلِلسَّيَّارَةِ ۖ وَحُرِّمَ عَلَيْكُمْ صَيْدُ الْبَرِّ مَا دُمْتُمْ حُرُمًا ۗ وَاتَّقُوا اللَّهَ الَّذِي إِلَيْهِ تُحْشَرُونَ

የባሕር ታዳኝና ምግቡ ለእናንተም ለመንገደኞችም መጠቀሚያ ይኾን ዘንድ ለናንተ ተፈቀደ፡፡ በሐጅም ላይ እስካላችሁ ድረስ የየብስ አውሬ በናንተ ላይ እርም ተደረገ፡፡ ያንንም ወደርሱ የምትሰበሰቡበትን አላህን ፍሩ፡፡

[አልማኢደህ 96]

በመሆኑም በሕር ውስጥ የሚገኝ የትኛውም እንሰሳ ኖሮም ሞቶም ሐላል ነው።መብላቱ ከተፈቀ መቀመሙ፣ከሱ የተለያዩ መዐዲኖችን በማዘጋጀት ቅባት ማዘጋጀት ፣ሌሎችንም ነገራቶች መጠቀም ሀላል ይሆናል።በበሕር ውስጥ የሚኖረውን ቀንድ አውጣ መጠቀም ይፈቀዳል።ይህኛው በህር ውስጥ ያለው ቀንድ አውጣ ስሆን ሁለተኛው ደሞ የብስ ውስጥ  ስለሚኖረው ይሆናል።

ولا يحل أكل (الحلزون البري )ولا شيئ من الحشرات كلها كالوزغ والخنافس والنمل والنحل والذباب والدبر والدود كله –طيارة وغير طيارة  –والقمل والبراغيث والبق والبعوض وكل ما كان من أنواعها لقوله تعالى (حرمت عليكم الميتة)
የብስ ላይ የሚኖረውን  ቀንድ አውጣ (حلزون) መብላት አይፈቀድም።አንዳችም ነገር ከምድር ነፍሳቶች መብላት አይፈቀድም።እንሽላሊት፣  ጥንዚዛ…ጉንዳን፣ንብ፣ዝንብ፣ተርብ፣ ትል ሁሉንም በራሪ ብሆን ባይሆንም…፣ቅማል፣በረሮ፣ትኳን፣ትንኝ ሁሉ ከሷ አይነት የሆኑትን መብላት አይፈቀድም።ላቅ ያለው ጌታ እንዲህ ይላል፦ (በናንተ ላይ የሞቱ ነገራቶች ክልክል ሆኑ)

አልማኢደህ

"ለማረድ ምቹ የሚሆነው ነገር ጎሮሮው ላይ ብለዋ ማረፍ የምቻልበት እንሰሳ መሆን ኣለበት።ማረድ በጉሮሮ እንጂ በሌላ መሆን አይችልም።ማረዱ ያልተቻለ ነገር ወደ መብላቱ ምንም አይነት መንገድ የለውም። "

የላቀው ጌታችን"የሞተ ነገር ሐራም/ ክልክ ሆነባችሁ" ሲል" ያረዳችሁት" ሲቀር ብሏል።አሁን የተጠቀሱት ቀንድ አውጣውን ጨምሮ ለመታረድ ባለመቻሉ እሱን መጥበሱም ሆነ ፈጭቶ መጠቀሙ፣መብላቱ የተከለከለ ተግባር ይሆናል። ወይም ነጃሳ እንደ መብላት ነው።

«ዝንብ በአንዳችሁ እቃ ላይ ከወደቀ ወደ ውስጥ ነክሮት  ይጣለው» ብለዋል።ነጃሳ ባይሆን ወደ ውጭ ጣሉት ባላሉ ነበር።

ከዐብዱረሕማን ብን ዑስማን ተይዞ "አንድ ዶክተር ወደ ነብዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ መጣና እንቁራሪትን ለመድኃኒትነት ልያደርጋት ጠይቃቸው ከለከሉት "ይላል።

የብስ ላይ ያሉ ነፍሳት( Insects)  ሐላል ብሆኑ ኖሮ ባልከለከሉት ነበር።ቀንድ አውጣው ከነፍሳቶች መካከል መሆኑ አጠራጣሪ አይደለም።

ኢማሙ ነወዊይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ፦
ﻣﺬﺍﻫﺐ ﺍﻟﻌﻠﻤﺎﺀ ﻓﻲ ﺣﺸﺮﺍﺕ ﺍﻷﺭﺽ .... ﻣﺬﻫﺒﻨﺎ ﺃﻧﻬﺎ ﺣﺮﺍﻡ ، ﻭﺑﻪ ﻗﺎﻝ ﺃﺑﻮ
ﺣﻨﻴﻔﺔ ﻭﺃﺣﻤﺪ ﻭﺩﺍﻭﺩ .
ﺍﻟﻤﺠﻤﻮﻉ " ‏( 9/16‏)

የዑሞች አካሄድ በምድ ነፍሳት ላይ እሷ ሐራም ናት( የምል ነው) በሱ( በዚህ አቃም) አቡ ሐኒፋ ፣አህመድ፣ዳውድ ሄደውበታል።

ኢማሙ ኢብኑ ሐዝም እንዲህ ይላሉ፦
ﻭﻗﺎﻝ ﺍﺑﻦ ﺣﺰﻡ ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ :
"ﻭﻻ ﻳﺤﻞ ﺃﻛﻞ ﺍﻟﺤﻠﺰﻭﻥ ﺍﻟﺒﺮﻱ , ﻭﻻ ﺷﻲﺀ ﻣﻦ ﺍﻟﺤﺸﺮﺍﺕ ﻛﻠﻬﺎ

"የብስ ላይ የሚኖር ቀንድ አውጣ (snail) መብላት አይፈቀድም።አንዳችም ከነፍሳት ከሁሉዋም።"

ጁምሁሮች የሄዱበት አቃም የሚፈስ ደም የሌለው የሆነ ነገር ለማረድ አይመችም የምለው ነው።ይህን አቃም የሚቃወም ከዑለሞች መካከል ኣለን

ኣዎ !ኢማሙ ማሊክ እንዲህ ይላሉ፦

ﺳﺌﻞ ﻣﺎﻟﻚ ﻋﻦ ﺷﻲﺀ ﻳﻜﻮﻥ ﻓﻲ ﺍﻟﻤﻐﺮﺏ ﻳﻘﺎﻝ ﻟﻪ ﺍﻟﺤﻠﺰﻭﻥ ﻳﻜﻮﻥ ﻓﻲ
ﺍﻟﺼﺤﺎﺭﻯ ﻳﺘﻌﻠﻖ ﺑﺎﻟﺸﺠﺮ ﺃﻳﺆﻛﻞ ؟ ﻗﺎﻝ : ﺃﺭﺍﻩ ﻣﺜﻞ ﺍﻟﺠﺮﺍﺩ ، ﻣﺎ ﺃﺧﺬ ﻣﻨﻪ
ﺣﻴّﺎً ﻓﺴﻠﻖ ﺃﻭ ﺷﻮﻱ : ﻓﻼ ﺃﺭﻯ ﺑﺄﻛﻠﻪ ﺑﺄﺳﺎً , ﻭﻣﺎ ﻭﺟﺪ ﻣﻨﻪ ﻣﻴﺘﺎً : ﻓﻼ
ﻳﺆﻛﻞ " ﺍﻧﺘﻬﻰ .
ﻭﻓﻲ " ﺍﻟﻤﻨﺘﻘﻰ ﺷﺮﺡ ﺍﻟﻤﻮﻃﺄ " ‏( 3 / 110 ‏) ﻷﺑﻲ ﺍﻟﻮﻟﻴﺪ ﺍﻟﺒﺎﺟﻲ ﺭﺣﻤﻪ
ﺍﻟﻠﻪ
ኢማሙ ማሊክ ሞሮኮ ላይ ስለሚገኝ ሐየዋን  ቀንድ አውጣ ስለሚባል ፣በረሃ ላይ የሚገኝና በዛፎች የሚለጠፍ እንሰሳ ይበላልን ተብለው  ተጠየቁ  እሳቸውም "እንደ አንበጣ (ይመስለኛል) ብለው ኣሉ። ከሱ በህይወት የተያዘው ነገር ይፈጫል ወይም ይጠበሳል። በመመገቡ ችግር አላይበትም ። ሞቶ የተገኘው አይበላም" ይላሉ።( ሙንተቃ)

ይሁን እንጂ ማስረጃው ግን ፍንጭም አይሰጣቸውም። 

አንኳር‼️

የቀንድ አውጣውን ቅባትም ሆነ ሌላ ነሩንም የምትጠቀሙ እህት ወንድሞች ከዚህ ቀደም ለሰራችሁት አላህ ይቅር ይበላችሁና ከዚህ ቦኃላ ነጃሳ መሆኑን አውቃችሁ ማቆም ኣለባችሁ።"እንትና ፈትዋ ሰቶበታል እንትና ሼኽ የሚባል ነገር አይሰራም።ማስረጃው ይህ ነው።ይህንን ርእስ ለመፃፍ የተገደድኩት ብዙ እህት ወንድሞች ስወዛገቡና ኮሜንትም ላይ ስጠይቁ ስለነበረ ነው።ስለ ቀንድ አውጣው ቅባት እውነታው ይህ ነው።
https://t.me/Fetwawoch_bicha/873?single

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

27 Jan, 05:46


👇قال العلامة صالح الفوزان -حفظه الله- :

✍️« ولزوم السنة ماهو بالأمر السهل، فيه ابتلاء وامتحان، هناك أناس يعيرونك، ويؤذونك، ويتنقصونك،

ويقولون: هذا متشدد متنطع إلى آخره، أو ربما أنهم لا يكتفون بالكلام، ربما أنهم يقتلونك، أو يضربونك، أو يسجنونك .

ولكن اصبر، إذا كنت تريد النجاة، وأن تشرب من هذا الحوض، اصبر على التمسك بسنة رسول الله صلى الله عليه وسلم إلى أن تلقاه على الحوض » .

📙[شرح الدرة المضية (١٩٠)].
  ሸይኽ ፈውዛን (ሀፊዞሁሏህ) እንድህ ብሏል፦
"ሱናን መያዝ ቀላል ነገር አይደለም ብዙ ፈተናዎችና ሙከራዎች አሉበት።ሱናን አጥብቀህ በምቲዝበት ግዜ እሚያነውሩህ፣እሚያስቸግሩህ ና  እሚያጓድሉህ  ሰዎች አሉ  ይህ አጥባቂ፣ፅንፈኛ ፣ወዘተ ነው ይሉሀል።እንደውም  በንግግር ብቻም ላይብቃቁ ይችላሉ  ሊገድሉህ ሁላ ይችላሉ ወይም ይደበድቡሀል ወይም ያስሩሀል ነገር ግን አንተ መዳንን እና ከነብዩ (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም)ሀውድ(ማኒጋ)መጠጣትን እምትፈልግ ከሆነ በዚህ ሁሉ ነገር ላይ ታገስ ከነብዩ  (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) ጋር ከሀውዳቸው እስከምትገናኝ ድረስ ሱናቸውን አጥብቀህ በመያዝ ላይ ታገስ(ፅና)"!!

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

26 Jan, 16:25


ስልክ በገመድ በታሰረበት ዘመን፣ የሰው ልጅ ነፃነት ላይ ነበር።
ዛሬ አብዛኛው የሰው ዘር የስማርት ስልኩ እስረኛ ሆኗል።
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

26 Jan, 16:22


إنا لله وإنا إليه راجعون
ሞተች

- አዎ እድሜዋ ረጅም መስሏት ታስብ ነበር
ግን ሞተች
- ሂጃብ እለብሳለሁኝ
- እሰግዳለሁኝ
- ያ ከወንዶች ጋር ያለኝ የሀራም ግንኙነትንም
እተዋለሁኝ
- ሰዎችን ማስቀየም ማማትም ሆነ
ማስቸገርንም እተዋለሁኝ
- ሀራም ከማየትም አይኔን አስብራለሁኝ
ትል ነበር
- ቁርአንንንም እቀራለሁኝ እሀፍዘዋለሁኝም
- ዘፈንና ዘመዶቹንም ከመስማት እቆጠባለሁኝ
ብላም ታስብ ነበር።

ነገር ግን አሁን ሞታለች

እህቴ ተውበትን አታዘግይ ሩሀችን መቼና በምን ቅፅበት እንደምትያዝ አናውቅምኮ።

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

24 Jan, 05:55


📌ጊዜ
ኢብነል ቀይም አላህ ይዘንላቸዉና እደዚህ አሉ


ግዜን ማባከን ከሞት  ይበልጥ አደጋ ነው‼️

ምክናየቱም ጊዜን ማባከን ከአላህና ከመጨረሻው አለም ያቋርጣል ሞት ግን ከዱኒያና ከባለቤቶቿ ያቋርጣል።

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

23 Jan, 13:14


🌿 ሱናን አጥብቆ መያዝ

ማከክ እንኳን ብትፈልግ እንዴት እንደሚታከክ የሚሳይ ማስረጃ ካለ በዛ ማስረጃ መሰረት እንጂ እንዳታክ!!!

(ሱፊያን አስ ሰውሪ)

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

21 Jan, 16:15


…………

ለታላቁ የ ኢባዳ ወር ፣ የሙእሚኖች ነፍስ ለምትጓጓለት እና ለምትናፍቀው የረመዳን ወር ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውታል

ታዲያ ይሄን ታላቅ የኢባዳ ወር :-

● ወንጀል እና መዳረሻዎቹን በመራቅ።
● አላህ ለዚህ የተከበረ ወር በሰላም እንዲያደርሰን እና በሱም ተጠቅመውበት ወንጀላቸው ተምሮ ከሚያሳልፉት ባሮቹ እንዲያደርገን አብዝቶ በመለመን።
● ሱና ሰላቶችን ቁርአን አዝካሮችን ሰደቃ ሌሎችንም ወደ አላህ የሚያቃርቡ ኢባዳዎችን በማዘውተር ነፍሲያችንን በማለማመድ።
● ልባችንን ከቂም፣ ከጥላቻ እና ምቀኝነት በማፅዳት
● ስለ ረመዳን ደረጃ እና ክብር እያሰብን ቀደምቶች ከዚህ ወር ጋር የነበራቸውን ሁኔታ እያስተነተንን በናፍቆት እና በጉጉት ልንጠብቀው ይገባል።

አላህ ለዚህ የተከበረ ወር ረመዳን በሰላም አድርሶ የምንጠቀምበት ያድርገን


منقول

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

20 Jan, 16:20


ፈገግ ያላችሁ !!

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

20 Jan, 03:44


ይህንን ያውቃሉ⁉️

ቲክቶክ ንብረትነቱ የቻይና ቢሆንም ቻይና ውስጥ እንዳይሰራ አድርገውታል።ምክንያቱን ሲያስቀምጡ ደግሞ "ቲክቶክ የኛ ንብረት ቢሆንም ከህዝባችን ስነ ልቦና ጋር አይሄድም" ብለው ነው።

በሌላው አለም ግን ይሰራል።ብልጧ ቻይና አለም እያደነዘዘች ህዝቧ ከእብደት ጠብቃለች።

ከአንተና ከእኔ ስነ ልቦናስ ይሄድ ይሁን??

منقول

አጂብ ነው

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

19 Jan, 15:24


⭕️ጓደኛ መምረጥ ይከብዳል
       አይደል ?⁉️

◉ሶስት ጓደኞች ነበሩኝ ስማቸው
በምህጻረ ቃል ‹‹
#ገ›› ‹‹#ቤ›› ‹‹#ስ›› ናቸው፡፡
❶አንደኛወን ጎደኛዬን ‹‹
#ገ››ን ጠራሁትና እኔ ስሞት ምን ይሰማሃል አልኩት ‹‹#ገ››

◉አንተ ከሞትክ አልቀብርህም  በጓሮ በር ሹልክ ብዬ እወጣለሁ አለኝ፡፡

❷ ሀለተኛዉን ጓደኛዬን ‹‹
#ቤ››ን ጠራሁትና እኔ ስሞት እንዴት ትሆናለህ አልኩት፡

◉ እሱም አንተማ ስትሞት አጥቤ ከፍኝ እቀብርሃለሁና እመለሳለሁ አለኝ፡፡

❸ ሶስተኛ ጓደኛዬን ‹‹
#ስ››ን ጠራሁትና እኔ ስሞት አንተ እንዴት ትሆናለህ አልኩት፡?

◉አንተማ ከሞትክ አብሬህ ነው የምቃበረው ከንተ አልለይም አለኝ፡፡

➴የቱ ጓደኛዬ ነው ለኔ አሪፍ ትላላቹህ
ከ ‹ገ› ከ ‹ቤ› ከ‹ስ›??

➴ ቆይ ግን እነዚህን ጓደኞቼን ለምን አልዘረዝርላችሁም

◉የመጀመሪያው ጎደኛዬ  ‹‹
#ገ›› ያልኳችሁ #ገንዘቤ ነው እኔ ስሞት የሰበሰብኩት ገንዘብ ምንም አይጠቅመኝም ጥሎኝ በጓሮ በር ነው የሚጠፋው፡፡

◉ሁለተኛው ጎደኛዬ ‹‹
#ቤ››ያልኳችሁ #ቤተሰቤ ነው አጥቦ ከፍኖ የሚቀብረኝ ነው፡፡

◉ ሶስተኛው ጓደኛዬ ‹‹
#ስ›› ያልኳችሁ #ስራዬ ነው አብሮኝ ጉድጓድ የሚገባው አብሮኝ የሚቀበረው፡፡

⭕️ዋና ጓደኛችን ስራችን ነው !!

ስንሞት አብሮን የሚቀበረውን ስራችንን አላህ ያሳምርልን!!🤲🤲

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

19 Jan, 07:09



   "1አምላክ" vs "44ታቦት"

   ቀጥታ ከቃሉ እንደ ምንረዳው "አምላክ" ማለት የሚመለክ ማለት ነው። የሚመለክ ማለት………
   የሚሰገድለት፣ ድረስልኝ፣ ጠብቀኝ፣ አድነኝ፣ እርዳኝ የሚባል፣ ስለት የሚደረግለት፣ በእሱ የሚማል፣ እና አጠቃላይ የአምልኮ ተግባር የሚሰጠው ማለት ነው።

🔥  ክርስቲያኖችን ካየን ግን  ለአርባ አራት አካላቶች በአጠቃላይ የተጠቀሱትን አምልኮ ይፈፅማሉ።
  
🔥 ታቦቱስ ምንድን ነው
 
ታቦቱ የሚዘጋጀው ከተለያዩ እንጨትብረታ ብረት፣ ወርቅብር ወይም ከሌላ ማቴሪያል
  ተጠርቦተሰንጥቆበልኩ ተቆርጦ የሚገጠም፤
  ከዝያም የተመረጠለትን ቅርፅ የሚወጣለት፣ የተመረጠ ስያሜ የሚሰየምለት፣ የተመረጠ ቀለም የሚቀባ እና
  በተመረጠለት ቦታ የሚቀመጥ ቁስ አካል ነው። የአሰራሩ ቅደም ተከተል ብሳሳት አያሳስብም።

ይህ ማለት……
   አንድ ሰው የሚፈልገውን ሳጥን በሚፈልገው ቁስ፣ በሚፈልገው ቅርፅና ቀለም እንደ ሚያሰራው ማለት ነው።

  በዚህ መልኩ ተጠርቦና ተቀልሞ የተዘጋጀው 🔥 "ታቦት" 🔥 የሚባለውን ቁስ አካል  "ሊጠቅምና ሊጎዳ ይችላል" ተብሎ ለእሱ መስገድ፣ ከእሱ እገዛና ከለላ መፈለግ፣ በእሱ መጠበቅና እሱን መለመን
  ምሽትና ንጋትን ለይቶ ከሚያውቅ ጤነኛ ሰው የሚፈፀም ተግባር አይደለም።

🔥   የሀገራችን ክርስቲያኖች ግን ይህንን ነው የሚፈፅሙት¡¡

  ስለ "ታቦቶች" ከተነሳ ጥያቄው መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ የለውም። ስለኾነም አያይዤ መጠየቅ የምፈልገው ጥያቄ አለኝ……
  እንዳሳለፍነው የታቦቶቹ ብዛት አርባ አራት ናቸው ክርስቲያኖች ደግሞ ብዙ ጊዜ ስናያቸው አንዱ "ገብርኤል ጠብቀኝ" ይላል፣ ሌላኛው "ሚካኤል ጠብቀኝ" ይላል፣ ሌላኛው "ኡራዔል ጠብቀኝ" ይላል፣ ሌላውም  ሌላ ይላል።
ልብ በሉ አርባ አራቱንም በአንድ ጊዜ እየጠራ ሳይሆን በንጥል ነው የሚጠራው።

ጥያቄዬ………
   "ገብርኤል ጠብቀኝ" ያለው እንደው ገብርኤል "እሺ" ቢለውና ሚካኤል ግን ለገብርኤል በመጠየቁ ቅር ብሎት ሊያጠፋው ቢፈልግ የማን ፍላጎት ነው ተፈፃሚ የሚሆነው?? የገብርኤል ፍላጎት ወይንስ የሚካኤል ፍላጎት??
    ዋነኛው ፈጣሪና መመለክ የሚገባው አምላክስ ተትቷል ነው??

ምን ይሄ ብቻ………
  እንደ ሚታወቀው በየ አመቱ "ጥምቀት" ብለው የሚያከብሩት በዓል አላቸው።

በዚህ ቀን ሁሉም ታቦቶች ተሰብስበው ወደ ወንዝ (ሜዳ) ይወሰዱና ይጠመቃሉ። ከተጠመቁ በኋላ ወደየመጡበት ይመለሳሉ። ታድያ በዚህ ጊዜ ከብልጥ በፊት ሞኝ የሚስቅበት የኾነ አባባል አላቸው። ታቦቶቹን ተሸክመው በሚወስዱበት ጊዜ……
"ታቦቱ አልሄድ አለ" ይላሉ።

የሰው ልጅ ከጨለመበት መጨረሻ የለውም።
ተመልከቱ………
   ታቦቱ ጠርቦ፣ ቀርፆ፣ ቀልሞ የሰራው የሰው ልጅ ነው፤ ራሳቸው ተሸክመው ወስደው አጥበውት፤ ራሳቸው ተሸክመው እየመለሱት "ታቦቱ አልሄድ አለ" እያሉ ይጃጃላሉ። ተከታዮቻቸውም «እውነት» ብለው ይቀበላሉ።

  እኔ ግን እንዲህ ዐይነት የቂል ጨዋታ «ሀይማኖታዊ ስርዓት» ተብሎ አይደለም የሰፈር ህፃናት ተሰብስበው በዚህ መልኩ ዕቃቃ ሲጫወቱ ባገኛቸው "አዕምሯችሁ ይጀዝባል" ብዬ ነበር ጨዋታ የማስቀይራቸው።

   እ ያ ሰ ብ ን  እንጂ ወገን!!

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

18 Jan, 05:29


👆 .....ባለቤቷ ከሞተ ቡኋላ ልብሱን ቁም ሳጥን ውስጥ አንጠልጥላው ገንዘብ ታስቀምጥበታለች ።
➴ ለተለያየ ጉዳይ ወጪ ሲጠይቋት .....

➳ከአባታችሁ ኪስ ውሰዱ ትላቸዋለች "

ብቸኛው ምክንያቷ ልጆቿ የአባታቸውን ቸርነት እንዳይዘነጉ ና የቲም ነን ብለው እንዳያስቡ ለማስታወስ ነው !

እናት ትምህርት ቤት ናት!!!


https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

17 Jan, 04:04


◉ غربة أهل السنة

◉ የአህለል ሱንናህ ባይተዋርነት

➴ ኢማሙ አልባኒ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይሉሃል:-

🔹إن تكلمت عن التوحيد نبذك أهل الشرك

➴ስለ ተውሒድ ስትናገር የሽርክ ሰዎች ይቃወሙሃል።

🔸وإن تكلمت عن السنة نبذك أهل البدعة

➴ስለ ሱና ስታወራ የቢድዓ ሰዎች ይቃወሙሃል።

🔹وإن تكلمت عن الدليل والحجة نبذك أهل التعصب المذهبي والمتصوفة والجهلة

➴ስለ ማስረጃና ማረጋገጫ ስትናገር የመዝሃብ ጭፍን ተከታዮች ሱፍዮች እና መሃይማን ይቃወሙሃል።

🔸وإن تكلمت عن طاعة ولاة الأمر بالمعروف والدعاء والنصح لهم وعقيدة أهل السنة نبذك المتحزبة

🔸ስለ በመልካም ነገር (ሙስሊም) መሪዎችን ስለመታዘዝ፣ ለነርሱ ዱዓ ስለማድረግ፣ እነርሱን ስለመምከር፣ እና ስለ አህለል ሱንናህ ዓቂዳ ስትናገር ኸዋሪጆች እና ሌሎች አፈንጋጭ ቡድንተኞች ይቃወሙሃል።

🔹وإن تكلمت عن الإسلام وربطته بالحياة نبذك العلمانيون والليبراليون وأشباههم ممن يريدون فصل الدين عن الحياة

◉ስለኢስላም እና በእለት ተእለት ኑራችን(ኢስላምን) ስለመተግበር ስትናገር ሴኩላሪስቶች፣ ሊበራሊስቶች (ፀረ–እምነት ቡድኖች) እና እነሱን የመሳሰሉ ዲናችንን ከእለት ተእለት ኑራችን መለየት የሚፈልጉት ይቃወሙሃል።

👌 غربة شديدة على أهل السنة!!

⭕️አህለል ሱንናህ እጅጉን ባይተዋሮች (እንግዶች) ናቸው!!

🔹حاربونا بجميع الوسائل

➴እነዚያ (የጥመት) ቡድኖች በእኛ ላይ በሚቻላቸው ሁሉ ጦርነት አውጀዋል።

🔸حاربونا بالإعلام المسموع والمرئي والمكتوب

➴በድምፅ በሚታይ፣ በፅህፈት ጦርነት አውጀውብናል።

‼️حتى أصبح الأهل والأصحاب يحاربون هذا الغريب المتمسك بكتاب الله وسنة رسول الله،

‼️ ቤተሰብና ጓደኛ ሁሉ ሳይቀር በዚህ እንግዳ ላይ ጦርነትን አውጀዋል።

🔹ورغم هذا ،نحن سعداء بهذه الغربة ونفتخر بها

◉ሆኖም ይህ በእንዲህ እንዳለ እኛ ግን በዚህ ባይተዋርነታችን ደስተኞች ነን። እንኮራበታለንም።

☑️ ﻷن رسول الله ﷺ أثنى على هؤلاء الغرباء

☑️ ምክንያቱም የአላህ መልእክተኛ ﷺ ባይተዋሮችን አወድሰዋቸዋልና።

فقال ﷺ : "إن الإسلام بدأ غريبًا ، وسيعودُ غريبًا كما بدأَ ، فطُوبَى للغُرباءِ قيل : من هم يا رسولَ اللهِ ؟ قال : الذينَ يصلحونَ إذا فسدَ الناسُ".

የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:

◉ኢስላም እንግዳ ሆኖ ጀምሯል። እንደ ጅማሮውም እንግዳ ሆኖ ይመለሳል። ለእንግዶቹ ‘ጡባ’ (ጀነት ውስጥ የምትገኝ ዛፍ ወይንም መልካም ነገር) አለቻቸው።”

◉እነርሱ (እንግዶቹ) እነማን ናቸው?” ተብለው በተጠየቁም ጊዜ የአላህ መልእክተኛ ﷺ :
“ሰዎች በተበላሹ ጊዜ (እራሳቸውን እና ሌሎችንም) አስተካካዮች ናቸው።” ብለው መለሱ።»

📚 السلسلة الصحيحة رقم : 1273
    

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

16 Jan, 04:36


አዲስ ግጥም❗️(ወይ አሜሪካ ደካማ ነሽ ለካ።)

ዛሬ ልዩ ቀን ነው እንኳን ደስ አላችሁ።

ሸይጣኗ በሀጃዋ ስትገባ የጋዛ ሰላም ተስፋ አሳይቷል።

ጥር 7/2017

በጁሀር ኡመር

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

15 Jan, 03:38


ፍልስጤማውያን ዓመት ሙሉ በቦንብ ሲነዱ አይቶ እንዳላየ ዝም ያለ ሁላ አሁን ለካሊፎርኒያው እሣት የውሃ ባልዲ ካላቀበልኩ ይላል።

አላህ ሆይ ምን ማድረግ እንዳለብህ እኛ አንነግርህም። የኛ ድርሻ ዱዓ ብቻ ነው።

አላህ ሆይ
ለተበዳዮች ተበቀልልን!
ያቃጠሉንን አቃጥልልን!
ምንም የማያውቁ ሕፃናትን የፈጁትን ሁሉ አንድድልን!

አሁንም ዓለምን ሰላም የነሱትን፣ ጉልበተኞች ነን ማንም አይችለንም ያሉትን ሁሉ ልካቸውን አሳይልን!

እነርሱን በመቅጣት ምንም ጉልበት እንደሌላቸው ንገርልን!

ክፉ ክፉውን ሁሉ ቀና እንዳይል አድርገህ ምታልን!

አሚን

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

13 Jan, 17:09


قال الله عزوجل: "واتقوا يوما ترجعون فيه إلى الله ثم توفى كل نفس ما كسبت وهم لا يظلمون"

"ወደ አላህ የምትመለሱበትንና ከዚያም የማይበደሉ ሲሆኑ ነፍስ ሁሉ የሠራችውን ሥራ የምትመነዳበትን ቀን ተጠንቀቁ፡፡"
[ አል-በቀራህ - 281 ]

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

13 Jan, 17:06


◉ የኔ የቂያማ እለት🔥

ህይወትን አገኘን ከአለማት ፈጣሪ
ሞትም ተዘጋጀ እንዳንሆን ዘውታሪ
እኛ ተመላሽ ነን ወደ ጀሊላችን
ተጠያቂ ልንሆን በዱንያ ስራችን
እዚህ በሰራነው በያንዳንዱ ስራ
ተጠያቂዎች ነን ያኔ በየተራ
ረቂብ እና አቲድ ስራን መዝግበዋል
ከመጥፎም ከጥሩም ሁሉንም ፅፈዋል
ጨለማን ሸፍነን ከሰራነው ወንጀል
ማንም አይኖርም የሚያድነን ሀይል
ከጀሊሉ ውጪ ስልጣን ያለው የለም
ለቅሶ ላይ ነው ያኔ ሁሉም በኒ አደም
ዋይታውን ያሰማል እርዳታን ፍለጋ
ልቡ ፍርሃት ላይ ናት ሲመሽም ሲነጋ
ማንም አይረዳውም ከአላህ በስተቀር
ምንዳውን ያገኛል ለፈፀመው ተግባር
አላህ የወደደው አላህ ያዘነለት
መኖሪያው ይሆናል ከትልቋ ጀነት
አላህ ያደርገዋል ከአርሽ ጥላ ስር
ላባችን ሲሞላን ፀሀይ ቀርባ ስንዝር
አላህን ያስቆጣ አላህ ያዘነበት
ዘውታሪ ይሆናል ከጀሀነም እሳት
ያኔ አይባልም ህያው አሊያም ሙት
ሲሰቃይ ይኖራል በእሳት እንፋሎት
አላህ ይዘንልን አብዝቶ ይውደደን
በጀነተል ፊርዶስ ዘውታሪ ያድርገን!!🤲

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

11 Jan, 19:38


ስለ አብሬት ሸይኸ ምን ያውቃሉ?

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

11 Jan, 19:25


👉   ሰዎች ወደ አብሬት ለምን ይጓዛሉ ?

  የኢስላም ጠላቶች የእስልምና ጮራ ከፈነጠቀበት ጊዜ አንስተው ብርሀኑን ለመግታት ከቻሉም ለማጥፋት ብዙ ሞክረዋል ። በተለይ የመጀመሪያው ትውልድ የኢስላምን አድማስ እያሰፋ በነበረበት ጊዜ በዐለም ላይ የነበሩ ሀያላን የሚባሉ ሀገራት ከኢስላሙ ብርሀን ፊት ለመቆም ብዙ ዋጋ ከፍለዋል ። ግን ልፋታቸው ያ ትውልድ ከአላህ ጋር በነበረው ጥብቅ ትስስር ምክንያት መክኖ እንዲቀር አድርጎታል ።
      ተስፋ የማይቆርጠው የሸይጣን ሰራዊት አንዱ ሜዳ ላይ ሲሸነፍ ሌላ ሜዳ ፊቱን እያዞረ ከአራሕማን ሰራዊት ጋር ሲፋጠጥ ምኞቱ ከስሞ ቅስሙ ተሰብሮ መመለስ እንጂ ወደ ፊት መቀጠል አልቻለም ። የዚህ አይነቱ ሽንፈት ሚስጢር ሳይገባቸው በማያውቁት ነገር የኪሳራ ካባ ሲደራርቡ ሚስጢሩን ማወቅ አለብን አሉ ።
   በዚህም ቆም ብለው ያሳለፉትን በህሊናቸው መስኮት እያማተሩ ሲያዩ ብዙ ሰራዊት በቁጥርም በትጥቅም የማይገናኝ ከጥቂቶች ፊት መቆም እንዲያቅተው ያደረገው በአራሕማን ሰራዊት ልብ ውስጥ የነበረው የኢማን ሀይል መሆኑን አወቁ ።
     እየተሸነፉ ያሉት በመሳሪያና በሰራዊት ብዛት እንዳልሆነ ይልቁንም ትንሹ ሰራዊት ከአላህ ጋር ባለው የጠበቀ ትስስር በአላህ እርዳታ መሆኑን ገባቸው ። እያሸነፋቸው ያለው የተውሒድ አቅም እንጂ የሰራዊት አቅም አለመሆኑን አመኑ ።
     የዚህን ጊዜ እስትራቴጂ መቀየር አስፈላጊ ሆነ ። ጦርነቱ ከኢማን ጋር  ከተውሒድ ጋር ሆነ ለዚህም ሰራዊት መመልመል ጀመሩ ። የአሁኑ መሳሪያ በጀርባ አዝለውት በትከሻ ተሸክመውት የሚሄዱት አይደለም ። ቀላል ሆኖ በጣም አጥፊ መሳሪያ ነው ። በሙስሊሞች ልቦና ውስጥ ያለውን ተውሒድ የሚያጨልም ኢማናቸውን የሚያቀልጥ የሹብሃ መሳሪያ የስሜት መከተል መሳሪያ መታኮስ መሳየፍ የማያስፈልገው በጥቂት ቃላቶች የሚገለፅ ቶሎ ልብ ላይ የሚሰርፅ መሳሪያ መጠቀም ጀመሩ ።
     የጦርነቱ ሜዳ ከበረሀ ወደ ሽርክና ቢዳዓ ፋብሪካ ተዛወረ ። ከሙስሊሙ ውስጥ ለዚህ ፋብሪካ ሰራዊት መለመሉ ከበላይ የሚመራው የዐብዱላሂ ኢብኑ ሰበእ አልየሁድይ ሀላፊነቱ የተወሰነ የኩፍር ማህበር ሆነ ። የሺዓ ፋብሪካ ተከፈተ በወልይ ስም ሙታኖች ይጠቅማሉ ፣ ይሰማሉ ፣ ይረዳሉ ፣ አላህ ስልጣን ሰጥቷቸዋል በሚል አላህን ትቶ እነርሱን መጥራት ተንሰራፋ ። ጎን ለጎን የተለያዩ የቢዳዓ ፋብሪካዎች እየተከፈቱ የሙታን መንፈስ ማምለኩ አድማሱ እያሰፋ ቅርንጫፉ እየበዛ ለዓለም ተዳረሰ ። የሱፍያው እህት ኩባንያ ይህን ሽርክ የማስፋፋቱ ስራ በሰፊው ተያያዘው ።
      በዚህም በቀላሉ ከሙስሊሙ ማህበረሰብ አላህ ያዘነለት ሲቀር ከውስጡ በአላህ ማመን የሚባለውን ማውጣት ቻሉ ። በዚህም አብዛኛውን ሙስሊም ኮፍያ ጥምጣምና ጀለብያ የለበሰ ቆሞ የሚሄድ ውስጡ ባዶ የሆነ እስከሌተን አደረጉት ።
    የኢስላም ጠላቶች ሀገራችን ላይ ሙስሊሙን ከኢማኑ ለማራቆት ከከፈትዋቸው የሽርክ ፋብሪካዎች አንዱ አብሬት ያለው ሀድራ ነው ። ቅርንጫፉ ጠቅላይ ቢሮ የሚባለው አ/አ ነው ።
     ሰዎች በየአመቱ ወደ አብሬት የሚገርፉት በአላህ ላይ ለማጋራት ውስጣቸውን አላህ ይጠቅማል ከሚለው ኢማን ባዶ አድርገው ያብሬት ሸይኾች ይጠቅማሉ በሚል ቀይረው ለሳቸው ችግራቸውን ለመንገር ነው ።
    አው አብሬት የሚሄድ ሙሪድ ኮፍያ ያደረገ ፣ ጀለብያ የለበሰ ፣ ጥምጣም የጠመጠመ ወይም ስሙ ሙሐመድ ፣ አሕመድ ፣ ከማል ፣ ሰፋ ፣ ጀማል የሆነ የሙታን መንፈስ አምላኪ ነው ። ሀድራውን የሚመሩት ጫት ናላቸውን ያዞራቸው ጠንቋዮች ናቸው ። ህዝቡን ቁርኣንና ሐዲስ ሳይሆን ያብሬትዬ የሚሉት ሸይጣን ወሕይ የሚያደርግላቸው ገድል ነው ።
    አብዛኛው አብሬትዬ ይመጣሉ በሚል ከሀገሩ የወጣ ነው ። ዱዓእ ሲያደርጉ በሀድራቸው አላህ ያስገባቸው የሚል ነው ። ይህ ተራውን ህዝብ የሚያስተኙበት እንጂ ገስግስ እንደገደላቸው ያውቃሉ ። የራሳቸው ልጆች አንዱ ሌላውን አባታችንን አስገድለዋል በሚል ክስ ላይ ናቸው ። ይህ ከመሆኑ ጋር ወደ አብሬት የሚጎርፈው ህዝብ ችግሩን ለአብሬትዬ ይናገራል ። ዘር ስጡኝ ፣ ከጭንቅ አውጡኝ ፣ ድረሱልኝ ፣ ለማን ተውኝ ይላል ። መከራውን ፣ ችግሩን ፣ ሐዘኑን ፣ ማጣቱን ፣ መጎዳቱን ፣ ፍርሀቱን ለሳቸው ይናገራል ። እርዱኝ ፣ አክብሩኝ ፣ እጄን ያዙኝ ይላል ።
     ኧናገራ ያለውን የአባታቸው ቀብር ( ኧቁባይ ) ሄዶ አፈር ይበላል ። በእንብርክኩ ወደ ቀብሩ ይደርሳል ። ስልኩን አጥፍቶ ጫማውን ከሐረሙ ( ከጊቢ ) ውጪ አስቀምጦ በእንብርክክ ሄዶ ቀብሩ ጋር ስጁድ አድርጎ በጠዋፍ ዞሮ ለአላህ እንጂ የማይገባ አምልኮ ያደርጋል ። ጉዱ በዚህ አይቆምም በየአመቱ የሚሄዱ አንድ ላምስት ተደራጅተው ወደዚህ ቀብር አምልኮ ለመጣራት ተስማምተው ይመጣሉ ።
       አሕባሽና ሱፍዮች የዚህ አይነቱን የሽርክና የኩፍር ተግባር በገንዘብ በመርዳት አድማሱ እንዲሰፋና ሙስሊሞች ቀብር አምላኪ እንዲሆኑ ቀንና ለሊት ይሰራሉ ። ይህ ከእስልምና የሚያወጣ ሽርክ ነው ተብሎ ስፍር ቁጥር የሌላቸው የቁርኣን አንቀፆች ሲነገራቸው ለከሀዲያን የወረዱ የቁርኣን አንቀፆች ለሙስሊሞች ያደርጋሉ ይላሉ ።
     እነዚያ አላህ ሙሽሪክ ያላቸው ከሀዲ ያላቸው ሰዎች ጥቁር ፣ቀይ ፣ ዐረብ ፣ ዐጀም ፣ አጭር ፣ ረዥም ፣ ስለነበሩ ነው  ወይስ የሚሰሩት የነበረው ተግባር የኩፍርና የሽርክ ተግባር ስለነበረ ነው ? በእነዚ አባባል ስለ ሶላት ፆምና ዘካ የሚናገሩ አንቀፆች ለእነዛ በዛ ዘመን ለነበሩት ብቻ ነበር አሁን አይሰራባቸውም ማለት ነው ።
     ሁሉም በየትኛውም ጉዳይ የመጡ የቁርኣንና የሐዲስ መረጃዎች በየትኛውም ዘመን የትም ቦታ ይሰራሉ ። ሙሽሪኮቹ ሲሰሩት የነበረውን ሺርክ የሚሰራ ሙሽሪክ ይባላል ። ከሀዲያን የሚሰሩትን የኩፍር ተግባር የሚሰራ ካፊር ይባላል ። በግለሰብ ላይ ብይኑን ለመስጠት የሚያስችሉ መስፈርቶች ተሟልተው ከልካዮች ሲወገዱ መረጃው ሲደርስ ያግለሰብ ካፍር ነው ይባላል ። የቁርኣን ህጎች በወረዱበት ምክንያት የተገደቡ አይደሉም ። ቃሉ በያዘው ብይን እስከቂያማ ይሰራሉ ።
      በመሆኑም እናትና አባቶቻችንን ከአሕባሽና ሱፍዮች እጅ ለማውጣትና ወደ ተውሒድና ትክክለኛ እስልምና ለማምጣት የምንችለውን ማድረግ ይጠበቅብናል ።

       አላህ ይወፍቀን ።

   منقول
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

10 Jan, 05:11


በአላህ አሻረከ የሞተ ሰብ ዘላለም ይረቭረታ ጀኸነሙ

( إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ وَالْمُشْرِكِينَ فِي نَارِ جَهَنَّمَ خَالِدِينَ فِيهَا ۚ أُولَٰئِكَ هُمْ شَرُّ الْبَرِيَّةِ )
البيِّنة (6)
"ዛ ኪታብ አውዮምታ ኧከፈረው ሰብ፣ በአላህ ያትጋረው ሰብ በጀኸነም ደን ዘዉታሪ ሒተውታ ይረቭረውተይ። ህኖ ተኸልቅ እን ሙጥጥ ሸረኛ ሰቭኖ። ” [አል-በይናህ፡ 6]


ጎፓያሁ ኑር የ44ት

https://telegram.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

10 Jan, 05:11


ምክር


“ሉቅማን ኧትከታ ቲመሁን 👉""ትከኞ_በአላህ_አትቃር_እናትጋራኸ/እናትሻረክኸ

👉በአላህ_አትጋሮት_ተወንጀል_እን_ንቅየ_ወንጀሉ። ኧዋረንኸ ዝግድ”(ባረኖም ኧነብየንራ ሰለላሁ አለይሒ ወሰለም)

[አል ሉቅማን፡ 13]

( وَإِذْ قَالَ لُقْمَانُ لِابْنِهِ وَهُوَ يَعِظُهُ يَا بُنَيَّ لَا تُشْرِكْ بِاللَّهِ ۖ إِنَّ الشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ )
لقمان (13)

Nur ከ44ት

https://telegram.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

10 Jan, 05:04


የራሱን አላዋቂነት ማን ያውቃል⁉️
======================
👉"ከማንም በላይ እኔ አውቃለሁ" ከማለት የበለጠ አላዋቂነት የለም።
ዓይንህ ውስጥ ያለውን ግንድ ዘንግተህ የሰዎች ዓይን ውስጥ ያለን ስንጥር ከማየት የበለጠ እውርነትም የለም።
كَدَعواكِ كُلٌّ يَدَّعي صِحَّةَ العَقلِ-
وَمَن ذا الَّذي يَدري بِما فيهِ مِن جَهل.
የገጣሚዎች አሚር የነበረው አልሙተነቢ አላህ ይዘንለት እንዲህ ይል ነበር 👇

👌ልክ እንዳንቺ ሙጉት ሁሉም ሰው የዓቅሉንና የአስተሳሰቡን ትክክለኛነት ይሞግታል፣ እራሱ ዘንድ ያለን አላዋቂነትና ሞኝነት ማን ያውቃል⁉️


@Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

10 Jan, 03:56


የሆሊውድ ተራራ እሳት ለብሷል

አሏሁም'መ ዚድ

በጋዛ ሙስሌሞች ላይ ሲደርስ በነበረው የእሳት ዶፍ እግራቸውን ሰቅለው ይስቁ የነበሩ ሁሉ አሁን አንገታቸውን ደፍተው ያለቅሳሉ።የእኛ ጌታ እንዲህ ነው።ይታገሳል እንጂ፡አይረሳ፤አይሳነው።አሏሁም'መ ዚድሁም!!

منقول

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

09 Jan, 17:28


👉ይድረሥ ለአብሬትዬ ሙሪዶች⁉️

⭕️ ዛ አብሬት ጀግጀግ ተበረው ሰብ ውር ጥጥ ጣይ ሻም ኩታራ ኧቁባይ ግፍር ባዶ ኧጅማኸ ሆር ትርፈታ ኪሳራው አሄራኸ ታብላሽ ታው የኸ ተዣቨር ትቢት አይጥጥኸ ነገ ባኸይ ጎጀ አትቨታ አይገቫታ

⭕️ታአሏህ ቅጣት :-
ትከማኸ አያተርፍኸታ
ንብረትማኸ አያተርፍኸታ
አብሬትዬም አያተርፍኸታ
ዘርማኸ አያተርፍኸታ
አበሩስማኸ አያተርፍኸታ
👉ኧቾትሆን/አፐሆን ወሄይ ማይና ቢኸር ባንኸረይ


https://telegram.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

09 Jan, 17:19


🔺አብሬት ላይ ከሚባሉ  የሽርክ ጥቅሶች መካከል #ክፍል~2
~~~~

#በጉራጉኛ
ሸሊላህ አቡራሙዜ #አሁ_ትንጠራ #ባሸና ይፈዜ
#ትርጉሙ « የአብሬት ሼይህ አበራሙዝ እርሶ ስጠራ ከበሽታዬ እፈወሳለሁ»።
إنا لله وإنا إليه راجعون
ወንድም እህቶች ሆይ?!
ያን በችግር ግዜ የሚለመነው  ማንንነው?!
ካአላህ ውጭ የሚያሽር አለን?!
ካአላህ ውጭ የሚጠቅም የሚጎዳ አለን?!
የለም!!
ጌታችን አላህﷻ እንዲህ ይላል:-
أَمَّن يُجِيبُ الْمُضْطَرَّ إِذَا دَعَاهُ وَيَكْشِفُ السُّوءَ وَيَجْعَلُكُمْ خُلَفَاءَ الْأَرْضِ ۗ أَإِلَٰهٌ مَّعَ اللَّهِ ۚ قَلِيلًا مَّا تَذَكَّرُونَ 
 ያ ችግረኛ በለመነው ጊዜ የሚቀበል፣ መከራንም የሚያስወግድ፣ በምድርም ላይ ምትኮች የሚያደረጋችሁ፤ ይበልጣልን ወይስ የሚያጋሩት ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን ጥቂትንም አትገሠጹም፡፡ አል ነምል 62📚
መከራና እና ችግር ከላያችን ላይ የሚያነሳው አላህ ነው እንጂ የአብሬት ሼይህ ከበሽታ አያድኑም የአብሬት ሼይህ ሌላውን ቀርቶ እራሳቸውን ከጉዳት መከላከል አይችሉም።
ጌታችን አላህﷻ በሌላም የቁርኣን አያህ እንዲህ ይላል:-
وَلاَ تَدْعُ مِن دُونِ اللّهِ مَا لاَيَنفَعُكَ وَلاَ يَضُرُّكَ فَإِن فَعَلْتَ فَإِنَّكَ إِذًا مِّنَ الظَّالِمِينَ  وَإِن يَمْسَسْكَ اللّهُ بِضُرٍّ فَلاَ كَاشِفَ لَهُ إِلاَّ هُوَ
 ከአላህ ውጭ ያሉት ነገሮች ለእናንተ ምንም ሊጠቅሙዋችሁም ሊጎዱዋችሁም አይችሉም አትጥሩዋቸው እነሱ የምትጠሩ ከሆነ በእርግጥ ከበደለኞች ናችሁ።አላህ በጉዳት ቢነካህ ከእሱ ውጭ ማን ጉዳቱ ሚያነሳልህ አለ ?

#ከሽርክ ስንኞች መካከል ሌላኛው:-
#በጉራጉኛ
ሼሌላ የቁባይ ጠቐ ታወጦ ተጭንቅ ታነቐ ::
« ይግባኝ የቁባይ ብርቱ የሆኑት ሆይ ታወጣላቹሂ( ታላቅቅ) አላቹሁ  ከጭንቀት ከጥበት »

ለዚህ መልስ ከላይ የጠቀስካቸው የቁራን አንቀፅ በቂ ምላሽ የሚሰጥ ከመሆኑጋ
አላህ የላካቸው ነቢዩላህ አዩብ በበሽታ ሲሰቃዩ #ብቸኛው የችግር ደራሽ የሆነው ወደ አላህ እንዲ ብለው ነበር የተማጸኑት፦
 وَأَيُّوبَ إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُ أَنِّي مَسَّنِيَ الضُّرُّ وَأَنتَ أَرْحَمُ الرَّاحِمِينَ
አዩብንም ለአላህ «እኔ መከራ አገኘኝ አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ» ሲል በተጣራ ጊዜ አስታውስ፡፡  

እዲሁም ነብዩላህ ዩሱፍም ልጃቸው ጠፍቶባቸው እንዲ ብለዋል፦
قَالَ إِنَّمَا أَشْكُو بَثِّي وَحُزْنِي إِلَى اللَّهِ
«ጭንቀቴንና ሐዘኔን የማሰማው ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡

ይህ ነው አላህ ያላቃቸው ነቢያት እምነት።

ካአላህ ውጭ ከጭንቅ ከመከራ ከችግር ሚያላቅቅ የለም!!  የአብሬት ሼይህም አባታቸውም ይሁን ማንም ከችግር  ከመከራ ማላቀቅ አይችልም።

አላህን ፍሩ!! ከዚህ የጥፋት ማበል ያላቹሁ ውጡ!! ከሽርክ ራቁ!! አዎን የአብሬት ሼይኽ  የ አላህ መብት ሊሰጣቸው አይገባም!! የአብሬት ሼይኽ ሊመለኩ አይገባም ። የአብሬት ሼይኽ ሊለመኑ አይገባም #ኧግዟን ( አግዙኝ) ሊባሉ አይገባም!! #በጥራራሁ (በጥበቃቹሁ)  ሊባሉ አይገባም!!…
♻️አብሬት ላይ ከሚባሉ  የሽርክ ጥቅሶች መካከል እጅግ በጣም ዘግናኝና የአላህን ሀቅ አሳልፈው የአብሬት ሼኸህ የሰጡባቸው እነዚህና መሰል ስንኖች ይገኙበታል :-
#በጉራጉኛ
የሉህ አባ (የሩህ አባትሆይ) ×

#በስልጥኛ
ዋቡና ዋብና መቶ መቶ ኤለ ባሎት ኤላ ባቱም ኤት
#ትርጉሙም
ስጡን መቶ መቶ ስጡን መቶ መቶ ኤለም ማለት የለም ባነቱ ቦታ። ×

#ተመርሮታሙ ወስፍ  ኤለይ ተመርሮታሙ ቂጫ ኤለይ አላህ ለገክካ ገረመኢ
ትርጉሙም
እዝነቶ ወስፍ የለውም
እዝነቶ ልክና /ገደብ የለውም
ለአላህ እራሱ ገርመው።
……
አላህ እኛንም ሆነ ቤተሰቦቻችን ከሽርክ ይጠብቀን አውቀውም ሆነ   ባለማወቅ  በሽርክ በኩፍር በቢዳአ የተዘፈቁት ወደ ሀቁ ይመልሳቸው!
ይቀጥላል………✍🏾

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

09 Jan, 17:17


🔺አብሬት ላይ ከሚባሉ  የሽርክ ጥቅሶች መካከል ክፍል~1
~~~~

ምስጋና ለአላህ ይገባው ፡፡ በእርሱ እመካለሁ ፣ ወደርሱ ተጸጽቸ እመለሳለሁ ፡፡ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የሌለ መሆኑን ፣ ሙሐመድﷺ የአላህ
አገልጋይና መልክተኛ መሆናቸውን ፣ እስከ እለተ ሞታቸው ድረስ ህዝብን በትክክል የመከሩና የተሰጣቸውን አደራ በአግባቡ የተወጡ መሆናቸውን ፤ መልካም ነገር ኖሮ ያላመላከቱት ፣ መጥፎ ነገር ኖሮ ያላስጠነቀቁት አንድም ነገር የለም ብየ በእርግጠኝነት እመሰክራለሁ፡፡ በእርሳቸው ፣ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ የአላህ ሶላትና ሰላምታ ይስፈን፡፡

እርሴ ላይ እደተመለከታቹሁት አብሬት ላይ ከሚባሉ የ ሽርክ ጥቅሶች መካከል የሚል ና እዛ ቦታ ላይ የሚሰራው የሽርክ ተግባራቶች አውቀን ተረድተን  እራሳችንና ቤተሰቦቻችን…ከዚህ የጥፋት ጎዳና እንድን ዘንድ አቅሜን በሚፈቅድልኝ ትንሽ ልላቹሁ ወደድኩ።

አብሬት የሚገኘው  በጉራጌ ዞን ቸሃ ወረዳ ሲሆን በዚህ ስፍራ በእየ አመቱ ረጀብ 15 ከተለያዩ የሀገራችን ከተሞች #ጓዛቸው_ጠቅልለው ሱቃቸው ዘግተው መኪና ተኮናትረው ልጆቻቸው ይዘው አብሬት መንደር ውስጥ የነበሩት የአንድ ግለሰብ  የአብሬት ሼይኽ (ሰይድ ቡደላ) ልደት(መውሊድ)ለማክበር ነው። በሚል ይሰባሰባሉ።

ገና ይህን እስልም ና ሀይማኖት የማያውቀው መሰረተቢስ ና መጤ ተግባር  ተከትሎ እጅግ ከባባድ ወንጀሎች ይፈፀማሉ ይህን በእንዲህ እዳለ  የጥንት የጠዋቱ ለማሰመሰል የሚጥር ና የህን ጊዜ ያፈራው የሱፊያ ና ያህባሽ የዘቀጥ አካየድና እምነት ልክ ና ትክክለኛ መስሎዋቸው መንገድን የሳቱት ጥቂት  አይደሉም።
ወንድምና እህቶች ሆይ⁉️
ከዚህ ጥመታዊ አካየድ እራሳችንና ቤተሰቦቻችንና መላውን ማህበረ ሰባችን ልታደገው ይገባል።
ከነሳራዎች ና ከየይሁዳ የተወረሰው
ልደት ማክበር (መውሊድ) ስለተባለው ቢድአ ምንነት ከማብራራት ጋር
እዛን ቦታ ስለ ሚባሉ ና ሚሰሩ ሽርኪያቶች በማብራራት እውነታውን መግለፃ አቅማችን በሚችለው መጣር ይጠበቅብናል!

አዎን ካአላህ ውጭ ያለን አካል ልጅ ስጡኝ? ሀብት ስጡኝ ፡እርዱኝ  ካአላህ ውጭ ያለን  አካል መሳላቱ የቀብር አፉር መብላት ለቀብር መደፋት   ወንድና ሴት መቀላቀልና አፀያፍ ተግባር ላይ መውደቅ ወላሂ ወቢላሂ  የጥፋት መንገድነው
በቅርቢቱ አለምም ሆነ በመጪው አለም ለታቅ ክስረት የሚዳርግ ተግባር ለመሆኑ ምንም አጠራጣሪ ጉዳይ አይደለም።
ከበደሎች ሁሉ ትልቁ በደል ሽርክ ነው። በደል ማለት አንድ  ነገር ያለ ትክክለኛው ቦታው ማስቀመጥ ነው። ከአላህ ሌላ ያመለከ ሰው ኢባዳው ያለ ቦታው አስቀመጠ ለማይገባው ለሌላ ሰጠ። ይሄ ከበደሎች ሁሉ ትልቁ በደል ነው።
ጌታችን አላህ  እዲህ ይላል:-
وَإِذْ قَالَ لُقْمَانُ لِابْنِهِ وَهُوَ يَعِظُهُ يَا بُنَيَّ لَا تُشْرِكْ بِاللَّهِ ۖ إِنَّ الشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ
ሉቅማንም ለልጁ እርሱ የሚገሥጸው ሲኾን «ልጄ ሆይ! በአላህ ጣዖትን አታጋራ፡፡ ማጋራት ታላቅ በደል ነውና»፡፡

የአብሬት ሼይኽ (ሰይድ ቡደላ)ላይ ድበር ከታለፉ ባቸው ጥቅሶች መካከል በጥቂቱ እንይ:- …… ክ/2
ይ ቀ  ጥ ላ ል✍🏾

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

09 Jan, 16:13


ዋይት ሐውዝን ጨምሮ አላህ በተሻለ በላእ ያንበሻብሻችሁ!


At least fire has the right to defend itself.

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

07 Jan, 05:21


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ፦
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.

ለራሴ የምወደውንና ከልቤ አምኜ የተከተልኩትን ብቸኛውን ትክክለኛ እምነት #እስልምናን- አላህ ይወፍቃችሁ ዘንድ ምኞቴ ነው።

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

06 Jan, 03:57


የእሁድ ሙሀደራ ከቋንጤ ....  ቁ -1

👌!!ከፊል በአብፌት የሚሰሩ ሙኻለፍዎች!!

በሚል ርዕስ   በጉራግኛ  የተዘጋጀ ወቅታዊ ሁሉም ሰው ሊያዳምጠው የሚገባ መካሪ የሆነ ሙሐደራ....

🎙በወንድማችን አቡ ሀምዛ አብዱል ወዱድ  አላህ ይጠብቀው።

በደምብ ወደ ህብረተሰቡ እንዲዳረስ ሼር ሼር ይደረግ

🕌 መስጂድ አሱናህ  (ቋንጤ )

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik
 

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

06 Jan, 03:46


-ወንዶች የሚያስታውሷቸውና
የሚረሷቸው አምስት ነገሮች

የሚያስታውሷቸው ነገሮች:

① والتِي تكاد أعينهم تنطِق بذَلك: مثنى وثلاث ورباع.

②: إنّ كيدهنّ عظِيم.

③: النّساء ناقصات عقلٍ ودِين.

④: الرّجال قوّامون على النّساء.

⑤: للذكَر مثل حظّ الأنثَيين.

-
የሚረሷቸው ነገሮች:

①: وَعاشِروهنّ بالمعروف.

②: استوْصوا بالنّساء خيرًا.

③: رفقًا بالقَوارير.

④: خيرُكم خيرُكم لأهلِه وأنا خيركم لأهلِي.

⑤: ما أكرَمهنّ إلّا كرِيم ومَا أهانهنّ إلّا لئِيم.

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

06 Jan, 03:44


📖 {…وَمَا نُرْسِلُ بِالْآيَاتِ إِلَّا تَخْوِيفًا}
{…ተዓምራቶችንም ለማስፈራራት እንጂ አንልክም።}

    [አል_ኢስራእ: ⁵⁹]

ግን ደግሞ…………👇

📖 {…وَنُخَوِّفُهُمْ فَمَا يَزِيدُهُمْ إِلَّا طُغْيَانًا كَبِيرًا}
{…እናስፈራራቸዋለን: ትልቅ የሆነ ጥመት እንጂ አይጨምርላቸውም።}

      [አል_ኢስራእ: ⁶⁰]

   የሰሞኑ አስፈሪ እና አስደንጋጭ የሆነው የዐዛብ ሚስኮል ከደረሰን በኋላ: እንዲው ሰው አጠገብ ከንፈር ከመምጠጥ በዘለለ ፈርተን ተደናግጠን ተውበት አድርገን ወደ አላህ ተመልሰናል ወይ??

منقول

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

06 Jan, 03:42


"አስቀያሚ ህይወት ማለት አካል ህያው
ሆኖ ዲን ሲሞት ነው ".

أحمدُ بنُ حنبل رحمه الله.👉ምንጭ

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

06 Jan, 03:39


ቪድዮ በሌሊቱ መንቀጥቀጥ በአዲስ አበባ ቤቶች ላይ ያሳየው የንዝረቱ ልክ በእንቅስቃሴ ሲታይ!!

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

04 Jan, 16:56


የመሬት መንቀጥቀጥ የትንሳዔ መቅረብ ምልክት ነው። ቢሆንም ነገሩ ሲከሰት ወደ አላህ በተውበት (በንስሃ) መመለስ እንዳለብን ዑለማዎች ይመክራሉ። በተረፈ ለጥንቃቄ ይረዳን ዘንድ ከባለሙያዎች የሚተላለፉ መልዕክቶችን ከማድመጥ ባለፈ፤ ያገኙትን ሁሉ ከሚያወሩ የሶሻል ሚዲያ ገፆች በሚተላለፉ መልዕክቶች ልንረበሽ አይገባም!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿لا تَقُومُ السّاعَةُ حتّى يُقْبَضَ العِلْمُ، وتَكْثُرَ الزَّلازِلُ﴾

“ሰዓቲቱ ‘ትንሳዔ’ አትቆምም እውቀት እስከሚነሳና የመሬት መንቀጥቀጥ እስከሚበዛ ድረስ።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 1036



©: ቡኻሪና ሙስሊም
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

03 Jan, 04:00


መዝሪያችን አሁን ነው!

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

02 Jan, 19:26


☞ከአስገራሚው የኢማሙ ሻፊዒይ ዲዋን መካከል

🍂إذا المرء لا يرعاك إلا تكلفا
      ❀❀فدعه ولا تكثر عليه التأسفا

ከአንገት በላይ በግድ የሚቀርብህ ከሆን
እርግፍ አድርገህ ተወው አታብዛ ፀፀትን

ففي الناس أبدال وفي الترك راحة
      ❀❀وفي القلب صبر للحبيب وإن جفا

ከሰውም ልዋጭ አለው በመተውም እረፍት
በልብ ውስጥም አለ ለወዳጅ የሚሆን ፅናት

🍂فما كل من تهواه يهواك قلبه
      ❀❀ولا كل من صافيته لك قد صفا

የምትወደው ሁሉ ልቡ አይወድህም
ንፁህ የሆንክለት ኩሉ ንፁህ አይሆንልህም

إذا لم يكن صفو الوداد طبيعة
      ❀❀فلا خير في ود يجيء تكلفا

ከልብ መውደድና ንፁህነት ባህሪ ካልሆነ
በግድ የሚመጣ ውዴታ መልካምም አልሆነ

🍂ولا خير في خل يخون خليله
      ❀❀ويلقاه من بعد المودة بالجفا

ወዳጅን የሚክድ ወዳጅ መቼም ኸይር የለውም
ከውዴታ ቡኋላ የሚገፋው ከሆን ፍፁም አይበጀውም

وينكر عيشا قد تقادم عهده
      ❀❀ويظهر سرا كان بالأمس قد خفا

አብረው የኖሩትን ዘመንን ከድቶ ክፋቱን ያወጣል
ትላንት ያፈነውን የእምነት ሚስጥርን  ይዘረግፋል

🍂سلام على الدنيا إذا لم يكن بها
      ❀❀صديق صدوق صادق الوعد منصفا

በዱንያ ላይ ሰላም! እንሰናበታት በሷ ላይ ከጠፋ
እውነተኛ ወዳጅ  ቃሉን የሚያከብር ፍትሓዊ ሙንሲፋ

    •┈┈┈••✿👑✿••┈┈┈•

አል-ኢማሙ ሻፊዒይ

【روائع من ديوان الامام الشافعي رحمه
الله】

        https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

02 Jan, 03:56


~በረጀብ ወር ዑምራ ማድረግ ይበረታታል። ኢብኑ አቢ ሸይባ በትክክለኛ ሰነድ እንደዘገበው ዑመር፣ ዑስማን፣ ዐኢሻ፣ ኢብኑ ዑመርና ሌሎችም ሶሃባዎች በረጀብ ዑምራ አድርገዋል። ኢብኑ ረጀብ እንደገለፁት ዑመር ቢን ኸጧብ በረጀብ ዑምራ ማድረግን ይወድ ነበር። ኢብኑ ሲሪንም ሰለፎች በረጀብ ወር ዑምራ ያደርጉ ነበር ብሎ አስተላልፏል።
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

02 Jan, 03:52


☁️🌟🌟🌟☁️

ፈገግ ይበሉ


👉ያው እንደሚታወቀው በሻፊኢይ መዝሀብ ሁሉም ኢባዳዎች ላይ ንያን በንግግር ማስገኘት ሱና ነው

💥ከአዝናኝ(አስቂኝ) የፉቀሀዎች ንግግር


አቡል ፈድል አል መህዛኒይ የሚባሉ የሻፊኢይ መዝሀብ ተከታይ ናቸው እና አባቱ በጣም ፈቂህ ነበሩ ልጅ አቡል ፈድል እንዲህ ይላል

አባቴ እኔን መምታት ሲፈልግ በምቱ ላይ ድንበር እንዳያል በፍራት እንዲህ ይል ነበር

"ልክ አላህ እንዳዘዘው አደብ እንዲይዝ ብዬ ልጄን ለመምታት ነየትኩኝ "
يقول: نويتُ أن أضربَ ولدي تأديباً كما أمر الله


እና አባቴ ንያውን ጨርሶ እስኪያሟላ ድረስ ሸሽቼ አመልጥ ነበር ይላል።

🌱البداية والنهاية (١٢/ ١٨٨)🌱👉ምንጭ

☁️🌟🌟🌟☁️

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

01 Jan, 16:10


☞ አንዱ ለሷሊሕ ብን ዐብዱልቁዱስ እንዲህ ብሎ ፃፈላቸው፦


المَوْتُ بَابٌ وكلُّ الناس داخلُهُ
فليتَ شعري بعدَ البابِ ما الدارُ ؟

ሞት እኮ መግቢያ ነው - ሁሉም ሚዘልቅበቱ
እስኪ አሳውቁኝ - ምን ይሆን ቤቱ የተገባበቱ

እሳቸውም እንዲህ ብለው መለሱለት፦

فأجابه:

الدَّارُ جَنَّاتُ عَدْنٍ إنْ عمِلْتَ بما
يُرضي الإلهَ ، وإن خالفتَ فالنارُ

هُمَا مَحَلَّانِ ما لِلناسِ غيرُهما
فانظُرْ لِنفسِك ماذا أنت تختار


ቤቱማ ይሆናል - ዘውታሪ መኖሪያ በዛ በጀነት
መልካምን ከሰራህ - ጌታን ሚያስደስት
ደግሞ ከተቃረንክ - መርጊያህ ነው እሳት
ከሁለቱ በቀር - ለሰዎች ማረፊያ ሌላም የላቸው
ለነፍስህ ተመልከት - ምርጫው ያንተ ነው

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

01 Jan, 04:06


የምንችለውን እናስተምር

ኢብኑል ሙባረክ - ረሒመሁላህ - "ከእድሜህ አንድ ቀን ብቻ ነው የቀረህ ብትባል ምን ትሰራ ነበር?" ተብለው ተጠየቁ።
"ሰዎችን አስተምር ነበር" አሉ።

[አልመድኸል ኢለሱነን፣ አልበይሀቂይ፡ 309]

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

01 Jan, 04:04


ለረመዷን 60 ቀን ቀረው❗️ያረብ🤲

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

31 Dec, 11:03


~የ‌ተ‌ከ‌በ‌ሩ‌ ወ‌ራ‌ት‌ (አ‌ሽ‌ሁ‌ሩ‌ል‌‐ሑ‌ሩ‌ም‌)

አላህ እንዲህ ብሏል፦
"إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِندَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ ۚ ذَٰلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ ۚ فَلَا تَظْلِمُوا فِيهِنَّ أَنفُسَكُمْ"
«የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን ዐሥራ ሁለት ወር ነው፡፡ ከእነሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው፡፡ ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው፡፡ በእነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ፡፡»

የተከበሩ ወራት አራት ናቸው:
• ዙል‐ቀዕዳ (ቂዕዳ አትበሉ)
• ዙል‐ሒጃ
• ሙሐር‐ረም
• ረጀብ
ሦስቱ ተከታታይ ወራት ናቸው። አንዱ ብቸኛ ነው። እርሱም ረጀብ ነው። በሂጅራ አቆጣጠር ሰባተኛው ወር ነው።

ኢማም አል‐ቁርጡቢይ እንዲህ ብለዋል: ‐
«በእነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ፡፡»
(ከላይ የጠቀስነው አያ ውስጥ)ኃጢኣት በመፈፀም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ ማለት ነው። ምክንያቱም የመልካም ሥራዎች ምንዳ እንደሚነባበረው ሁሉ በዚህ ጊዜ የሚፈፀም ኃጢኣትም ቅጣቱ ይነባበራል። 
ቀታዳ እንዲህ ብለዋል: ‐ «በተከበሩት ወራት የሚፈፀም በደል በሌላ ጊዜ ከሚፈፀመው እጅግ የከፋ ወንጀል ነው።»

ለነፍሳችን መዳን የምንመርጠው ጊዜ ላይ አለንና እናስብበት!

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

31 Dec, 03:58


"ምድር ላይ ዝቅ ያልክ ሁነህ እንጂ እንዳትራመድ
ካንተ በላይ ክብር ያላቸው ስንቶች ከምድር በታች ናቸው"

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

30 Dec, 03:57


እነዚህን 4 ዱዐዎች ሁሌም ልንረሳቸው አይገባም:
‏- اللهُم إني أسألك حُسنٌ الخَاتمة
‏- اللهُم ارزقنيِ توبة نصوحة قبل الموت
‏- اللهُم يا مُقلب القلوب ثبت قلبي على دينك
‏- اللَّهم إنَّك عفوٌ كريمٌ تحبُّ العفوَ فاعفُ عنّا

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

30 Dec, 03:49


ማንኛዉም ጉዳይ ሲከብድህ
ዱንያ ከመስፋቷ ጋር ስትጠብህ
ልብህን ጥደህ አላህን በ الفتاح ስሙ ችክ ብለህ ተማጸነው

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

29 Dec, 05:27


◉ውዷ ―እህቴ ―ጊዜው― የኒቃብነው!


¤" ብዙዎቹ ኒቃብ ለምን? ይላሉ።
ግን ዙሪያችንን ብናስተነትን
.
①" ምድር ሽፋን ያላት መሆኑ
.
②ለሰይፍ ሽፋን አፎት መኖሩ
.
③"እስክሪብቶ ያለ ሽፋን
ቀለሙ ቶሎ መድረቁ
.
④አፕል ሽፋኑ ባይኖር ኖሮ ወዲያውኑ መበላሸቱ
.
⑤"ሙዝ ሽፋኑ ቢነሳ ወዲያውኑ መጥቆሩ
.
⑥"ተማሪዎቻችን ደብተሮቻቸውን የሚሸፍኑት እንዳይበላሽባቸው መሆኑን በአስተውሎት
ብንመለከት ሽፋን ያለውን ጥቅም እንረዳ ነበር።
.
🎖ሴቶች ደግሞ ከሁሉም በላይ ውብ ናቸውና የሚሸፈኑበት ሂጃብ ( ኒቃብ ) ያስፈልጋቸዋል!!!
.

🎖ሌላው ቀርቶ ለስልኮቻችን እራሱ ሽፋን ከየትም አፈላልገን ገዝተን እናደርጋለን ፡፡
.
🎖ታድያ ውዷ እህቴ አንቺ ከሙዝ በምን ታንሺያለሽ ፣ ከሞባይል በምን ታንሽያለሽ ?
        አንቺ ፦
.
🎖እኮ አላህ እሱ በፈለገውና ባማረ ቅርፅ ፈጥሮሽ ሲያበቃ የወንዶች ቀልብ ማረፊያ አደረገሽ ፡፡

·
🎖የሚገርመው አንድ ሠው ምኑንም ያክል ሀብታም ቢሆን ምኑንም ያክል የተከበረ
ባለስልጣን ቢሆን የደስታው ጥግ ያለው ሴት ጋር ነው ፡፡
.
🎖ለዚህም ነው የአላህ መልዐክተኛ(ﷺ) እንዲህ ብለዋል
ዱንያ ውስጥ ካሉት ከሚያስደስቷቸው ነገሮች መካከል【 ሴቶችን】
የጠቀሱት ፡፡
.
🎖 ከምንም በላይ ደግሞ አህቴ "አላህን ልትፈሪ ይገባል " አንድ ጥያቄ እራስሽን
ጠይቂ?
.

🎖 አሁን ያለሽበትን ይህን ያማረ ገፅታ ማን ነው የፈጠረው " ..?
.
መልስሽ አላህ ከሆነ ፦
.
አላህ በሰጠሽ ፀጋ እሱ ታምጭዋለሽ ?
.

🎖አላህ ለእናንተ ሂጃብ የምትለብሱበትን ለኛ ( (ለወንዶች )) ዐይናችንን የምንሰብርበትን
ኢማን ይስጠን !!!
      
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

29 Dec, 05:23


https://www.facebook.com/100088806304266/posts/112337231736487/

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

27 Dec, 04:28


ቁርአን የልብ መርጊያ ለደረቀ ልብ ማረስረሻ ነው።
{የጁመዓ ቀን ሱናዎች}

↩️💎 ‏سنن يوم الجمعة
💎الغسل
💎 الطيب
💎السواك
💎 لبس الجميل
💎 قراءة سورة الكهف
💎 التبكير لصلاة الجمعة
💎الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي

➊ ➛መታጠብ
➋ ➛ሽቶ መቀባት
➌➛ ሲዋክ መጠቀም
➍ ➛ጥሩ ልብስ መልበስ
➎ ➛ሱረቱል ካህፍን መቅራት ከቻልን
➏ ➛ለጁመዓ ሶላት መጣድ
➐ ➛በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማብዛት


እንዲሁም ብለዋል ﷺ የጁመዕ ሌቀኑ ለይ በኔ ሰለዋትን  አብዙ። ሶለዋታችሁ እኮ ለኔ ይቀርብ ነው።
«اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ،
كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ،
اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ،
كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ
 

➛በሰለዋት በዚክርያውለን

ﷺ  ﷺ ﷺ
ﷺ ﷺ  ﷺ ﷺ ﷺ
ﷺ ﷺﷺ ﷺ ﷺ ﷺ

إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

26 Dec, 18:38


🔷  ለጥንቃቄ

በቴሌግራም መረጃዎች እየተመዘበሩ እንደሆነ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር / ኢንሳ አሳውቋል።

ኢንሳ በዛሬው ዕለት በቴሌግራም መረጃዎች እየተመዘበሩ በመሆኑ ተጠቃሚዎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲል አሳስቧል።

ኢንሳ ብዙ የቴሌግራም አካውንቶች በተለያዩ ማስገሪያ (ፊሺንግ ሊንክ) አማካኝነት መረጃዎች እየተመዘበሩ እንደሆነ ገልጷል።

በመሆኑንም ከማንኛውም የቴሌግራም ተጠቃሚ (ከሚያውቁትም ሆነ ከማያውቁት) ግለሰብ ሊንክ ቢላክ መክፈት ተገቢ እንዳልሆነ እና ወዲያውኑ ማጥፋት እንደሚገባ አሳስቧል።

       Via- የቲክቫህ ኢትዮዽያ ነው ።

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

26 Dec, 18:20


﴿إِنَّ المُتَّقينَ في جَنّاتٍ وَعُيونٍ﴾.

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

26 Dec, 18:18


«ጌታዬ! ወንጀል ባይኖርብኝ ኖሮ ቅጣትህን አልፈራም ነበር።  ቸርነትህን ባላውቅ ኖሮ ምንዳህን አልከጅልም ነበር።»

ጥሩ ገለፃ!
@Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

26 Dec, 18:15


➢30 ሸሪዓዊ ክልክላት ለሴቶች‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
❶) ፀጉር መቀጠል (ማስቀጠል)
ﻧﻬﻲ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻋﻦ ﻭﺻﻞ ﺷﻌﺮﻫﺎ.

❷) ጥርስ መሞረድ እና ንቅሳት።
ﻧﻬﻲ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻋﻦ ﺍﻟﻮﺷﻢ ﻭﺍﻟﻔﻠﺞ ﻭﺍﻟﻨﻤﺺ .

❸) ሽቶ ተቀብታ ከቤት መውጣት።
ﻧﻬﻲ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻋﻦ ﺍﻟﺨﺮﻭﺝ ﻣﺘﻄﻴﺒﺔ.

❹) አጅነቢይ ወንድ ፊት ጌጧን እና መልካን ማሳየት።
ﻧﻬﻲ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻋﻦ ﺇﺑﺪﺍﺀ ﺍﻟﺰﻳﻨﺔ والجمال ﺃﻣﺎﻡ ﺍﻟﺮﺟﺎﻝ.

❺) ባሏ ወደ ፍራሹ ሲጠራት እምቢ ማለት።
ﻧﻬﻲ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻋﻦ ﺍﻹﻣﺘﻨﺎﻉ ﻋﻦ ﻓﺮﺍﺵ ﺯﻭﺟﻬﺎ.

❻) ባሏ ጋር የምታደርገውን የፍራሽ ሚስጥር ለሌላ ሰው ማውራት።
ﻧﻬﻲ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻋﻦ ﺇﺫﺍﻋﺔ ﺃﺳﺮﺍﺭ ﺍﻹﺳﺘﻤﺘﺎﻉ ﺑﻴﻦ ﺍﻟﺰﻭﺟﻴﻦ .

❼) ከባሏ እየኖረች ያለፍቃዱ ሱና ፆም መፆም።
ﻧﻬﻲ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻋﻦ ﺻﻮﻡ ﺍﻟﺘﻄﻮﻉ ﻭﺯﻭﺟﻬﺎ ﺣﺎﺿﺮ ﺇﻻ ﺑﺈﺫﻧﻪ.

❽) ያለፍቃዱ ከበሏ ገንዘብ መሰደቅ።
ﻧﻬﻲ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻋﻦ ﺍﻹﻧﻔﺎﻕ ﻣﻦ ﺑﻴﺖ ﺯﻭﺟﻬﺎ ﺇﻻ ﺑﺈﺫﻧﻪ .

❾) አሏህ የከለከለው ነገር ባልሆነ ጉዳይ ባሏን ማመፅ።
ﻧﻬﻲ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻋﻦ ﻣﻌﺼﻴﺔ ﺯﻭﺟﻬﺎ .

❿) አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት ከባሏ ፍቺ መጠየቅ።
ﻧﻬﻲ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻋﻦ ﻃﻠﺐ ﺍﻟﻄﻼﻕ ﻣﻦ ﺯﻭﺟﻬﺎ ﻓﻲ ﻏﻴﺮ ﻣﺎ ﺑﺄﺱ .

❶❶) የባሏን ውለታ መካድ።
ﻧﻬﻲ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻋﻦ ﻛﻔﺮﺍﻥ ﺍﻟﻌﺸﻴﺮ .

❶❷) ባእድ ከሆነ ወንድ ጋር ብቻዋን መሆን።
ﻧﻬﻲ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻋﻦ ﺍﻟﺨﻠﻮﺓ ﺑﺄﺟﻨﺒﻲ .

❶❸) ወደ አጅነቢይ ወንድ መመልከት።
ﻧﻬﻲ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻋﻦ ﺍﻟﻨﻈﺮ ﺇﻟﻰ ﺍﻷﺟﺎﻧﺐ.

❶❹) አጅነቢይ ወንድ ጋር መጨባበጥ።
ﻧﻬﻲ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻋﻦ ﻣﺼﺎﻓﺤﺔ ﺍﻷﺟﺎﻧﺐ .

❶❺) ወንዶች ጋር መመሳሰል።
ﻧﻬﻲ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻋﻦ ﺍﻟﺘﺸﺒﻪ ﺑﺎﻟﺮﺟﺎﻝ .

❶❻) የሌላ ሴት ቁንጅና እና ባህሪ ለባሏን ማውራት።
ﻧﻬﻲ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻋﻦ ﺃﻥ ﺗﺼﻒ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻟﺰﻭﺟﻬﺎ.

❶❼) የሌላን ሴት ብልት ማየት እና አንድ ልብስ መልበስ።
ﻧﻬﻲ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻋﻦ ﺍﻟﻨﻈﺮ ﺇﻟﻰ ﻋﻮﺭﺓ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﺃﻭ ﻣﺒﺎﺷﺮﺗﻬﺎ ﻓﻲ ﺍﻟﺜﻮﺏ ﺍﻟﻮﺍﺣﺪ .

❶❽) መሕረም ከሚሆንላት ወንድ (ባል) ውጭ ብቻዋን ጉዞ መውጣት።
ﻧﻬﻲ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻋﻦ ﺍﻟﺴﻔﺮ ﺑﻐﻴﺮ ﻣﺤﺮﻡ .

❶❾) ያለምክንያት ከቤት መውጣት።
ﻧﻬﻲ ﺍﻟﻤﺮﺍﺓ ﻋﻦ ﺍﻟﺨﺮﻭﺝ ﻣﻦ ﻣﻨﺰﻟﻬﺎ ﻟﻐﻴﺮ ﺣﺎﺟﺔ .

❷0) በአደጋው ግዜ ጩሆ ማልቀስ፤ ፊትን መምታት እና ልብስን መቅደድ።
ﻧﻬﻲ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻋﻦ ﺍﻟﻨﻮﺡ ﻭ ﺍﻟﻠﻄﻢ ﻭﺷﻖ ﺍﻟﺜﻴﺎﺏ ﻋﻨﺪ ﺍﻟﻤﺼﻴﺒﺔ .

❷❶) ሐሜት፣ ወሬ በማዋሰድ ሰውን ማጣላት፣ ጆሮ ጠቢነት እና መበደል።
ﻧﻬﻲ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻋﻦ ﺍﻟﻐﻴﺒﺔ ﻭﺍﻟﻨﻤﻴﻤﺔ ﻭﺍﻟﺘﺠﺴﺲ ﻭﺍﻟﻈﻠﻢ .

❷❷) ከ3 ቀናት በላይ ሙስሊምን ማነኩሮፍ።
ﻧﻬﻲ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻋﻦ ﺍﻟﻬﺠﺮﺍﻥ ﺑﻴﻦ ﺍﻟﻤﺴﻠﻤﻴﻦ ﻓﻮﻕ ﺛﻼﺛﺔ ﺃﻳﺎﻡ .
❷❸) ሬሳ መከተል።
ﻧﻬﻲ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻋﻦ ﺍﺗﺒﺎﻉ ﺍﻟﺠﻨﺎﺋﺰ . 

❷❹) መቃብር ጉብኝት ማብዛት  እና ዝምድናን መቁረጥ።
ﻧﻬﻲ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻋﻦ ﻛﺜﺮﺓ ﺯﻳﺎﺭﺓ ﺍﻟﻘﺒﻮﺭ ﻭﻗﻄﻴﻌﺔ ﺍﻟﺮﺣﻢ .

❷❺) መተተኞች እና ኮከብ ቆጣሪዎች ጋር መሄድ።
ﻧﻬﻲ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻋﻦ ﺇﺗﻴﺎﻥ ﺍﻟﻜﻬﺎﻥ ﻭﺍﻟﻤﻨﺠﻤﻴﻦ .

❷❻) ልጆችን መራገም።
ﻧﻬﻲ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻋﻦ ﺍﻟﺪﻋﺎﺀ ﻋﻠﻰ ﺍﻷﻭﻻﺩ .

❷❼) አገልጋዮችን ማሰቃየት።
ﻧﻬﻲ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻋﻦ ﺗﻌﺬﻳﺐ ﺍﻟﺨﺪﻡ .

❷❽) ጎረቤትን ማስቸገር።
ﻧﻬﻲ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻋﻦ ﺇﻳﺬﺍﺀ ﺍﻟﺠﺎﺭ .

❷❾) በሞተ ሰው ላይ ከ3ቀን በላይ መነጣጣት የተከለከለ ነው ከባሏ ስቀር ለባሏ ግን 4 ወር ከ10 ቀን ታዝናለች(ትነጣጣለች)።
ﻧﻬﻲ ﺍﻟﻤﺮﺃﺓ ﻋﻦ ﺍﻟﺤﺪﺍﺩ ﻋﻠﻰ ﻣﻴﺖ ﻓﻮﻕ ﺛﻼﺙ ﺃﻳﺎﻡ ﺇﻻ ﻋﻠﻰ ﺯﻭﺟﻬﺎ ﺃﺭﺑﻌﺔ ﺃﺷﻬﺮ ﻭﻋﺸﺮﺓ ﺃﻳﺎﻡ .

❸0) ፀጉሯን እንደ ግመል ሻኛ ማድረግ።
°
እህቶቻችሁን አስታውሱበት
!
Copy

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

26 Dec, 05:18


"*واتَّقُوا يَوْمًا تُرْجَعُونَ فِيهِ إِلَى اللهِ ثُمَّ تُوَفَّى كُلُّ نَفْسٍ مَّا كَسَبَتْ وَهُمْ لاَ يُظْلَمُونَ*"

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

25 Dec, 16:33


አሪፍም አይደለህ❗️

ጎበዝም አይደለህ❗️

ሒሳብ ትችል የለ❗️

እስኪ ዋጋ አውጣለት ፈጣሪ ለሰጠህ❗️

ዋጋ አውጣለት ለአይንህ❗️

ዋጋ አውጣለት ለእጅህ❗️

ዋጋ አውጣለት ለጤናህ❗️

ዋጋ አውጣለት ለልጅህ

ስንት ነው ሚሆነው ያንተ ቆሞ መሄድ⁉️

ስንት ነው ሚሆነው በጤና መራመድ⁉️

ስንት ያወጣ ነበር የምትተነፍሰው አየሩ ቢነገድ⁉️

ዋጋ ክፈል ቢልህ ስንት ትከፍላለህ⁉️

ሂሳቡን አውጥተህ ቀምረህ ስትጨርስ

ይህን ላሰብክበት አዕምሮ ለሰጠህ ምስጋናህን አድርስ

ምስጋና ነውና ከጀነት የሚያደርስ

ዝም አትበል አድርስ❗️❗️❗️

{فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ} [الرحمن : 13]

አላህ ግን ከኛ ሚፈልገው ትልቁ ነገር ይህ ነው
                        👇👇👇👇
﴿ فَمَنْ يَكْفُرْ بِالطَّاغُوتِ وَيُؤْمِنْ بِاللَّهِ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَى لا انفِصَامَ لَهَا ﴾

Via-thvcsbvc3610gdxl

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

24 Dec, 17:27


🍃🌸

መሀመድ ኢብኑ ከዕብ አል ቁረዚይ :

"ቁርአን የሀፈዘ ሰው እድሜው
መቶዎቹ ቢደርስ እንኳ አላህ
በአእምሮው ያስጠቅመዋል
ይላሉ።!".


📖: البداية والنهاية (٢٧٠/٩ 👉ምንጭ

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

24 Dec, 17:21


☀️ያ ኡኽቲ الـــكــريـــمـــة

ነገ ወደፊት እሰልማለሁ ይቅርና
ነገ ወደፊት እሰግዳለሁ የሚልሽንን
ከማግባት ተጠንቀቂ‼️

ምክንያቱም ለአሏህ ያልሆነ
ላንቺም አይሆንም። መኖር መስገድ ያለበት ለጌታው ነው እንጂ ላንቺ አይደለም ።
በእንደዚ አይነት ቃላቶች እንዳይሸውዱሽ
አንቺን በእጁ ለማስገባት ሚጠቀማቸው ቃላቶች ናቸው #ተጠንቀቂው
منقول
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

24 Dec, 03:56


⁾⁾⁾⁾⁾አቡ - ሐኒፋ⁽⁽⁽⁽⁽


በእለተ አንድ ቀን አቡ - ሐኒፋ (አላህ ይዘንላቸው) እና ከባልደረቦቻቸው ጋር በአንድ መስጂድ በኩል ሲያልፉ አንድ ሕፃን ልጅ መስጂድ ውስጥ ➴ስቅስቅ ብሎ እያለቀሰ አላህን ሲለምን (ዱዓ) ሲያደርግ ተመልክተው ልጁን ለምን እንደሚያለቅስ ይጠይቁታል፡፡
ልጁም:- ‹‹ኢማም ሆይ! እባክዎ ይተዉኝ፡፡›› አላቸው፡፡ እሳቸውም እያግባቡ እንዲነግራቸው የሙጥኝ አሉ፡፡ ልጁም:-
‹‹ያቺ መቀጣጠያዋ ሰዎችና ድንጋዮች የሆነችውን እሳት፤ ለካሐዲዎች ተደግሳለች፡፡›› (አል-በቀራህ፡ 24) የሚለውን የቁርኣን አንቀፅ አንበብዋልን?›› አላቸው፡፡ እሳቸውም:-

‹‹በትከክል አንብቢያለሁ፡፡ ነገር ግን ልጄ ሆይ! አንተ ግን ገና ጨቅላ ነህና ይህ አንቀፅ ባንተ ላይ ተግባራዊ አይሆንም፡፡››  አሉት፡፡ ልጁም:-

‹‹ኢማም ሆይ! እሳት ለማቀጣጠል ስንፈልግ ➴ከትልቅ እንጨት ይልቅ ትንሽ እንጨት አይደለምን የምንመርጠው?›› አላቸው፡
እሳቸውም:- ‹‹እንዴታ!››   አሉት፡፡ ልጁም:- ‹‹ታዲያ ይህ አንቀፅ እንዴት እኔን አይመልከትም!?›› አላቸው፡፡ ይህን ጊዜ ኢማም አቡ-ሐኒፋ ወደባልደረቦቻቸው ዞረው :-
‹‹በአላህ እምላለሁ! ይህ ጨቅላ ከእኛ ይበልጥ አላህን ይፈራል፡፡›› አሉ፡፡
       
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

24 Dec, 03:50


👆 ለፈገግታ 👆

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

23 Dec, 14:34


https://t.me/httpgoto

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

21 Dec, 03:48


🚫ልቅ የሆኑ የወሲብ ፊልሞችና ምስሎችን በመመልከት ለተለከፉ ሁሉ!

♻️እነዚህ ፊልሞችና ምስሎች የጀሀነም በሮች ናቸው!

📵እነዚህን የበከቱና የተግማሙ ዝሙተኞችን በማየት እስረኛ የሆንክ/ሽ ሁሉ በዚህ ሰበብ ምን እንደሚከተልህ/ሽ ተከታዩን እስተውለህ/ሽ አንብብ/ቢ!

☞ለላጤዎችና ለባለትዳሮች መጨረሻ  ላይ የተቀመጠውን መፍትሄ በጥሞና አንብቡት!

☞የተራቆቱ ዝሞተኞችን ማየት እጅግ ከባባድ ወንጀሎች ውስጥ እንደሚካተቱ ታውቃለህ?

☞እነዚህን ዝሙተኞች መመልከት ውርደትና ደካማነት እንደሚያወርስ ታውቃለህ?

☞እነዚህን ዝሙተኞች መመልከት በሰዎች አይን ያነስክና ወራዳ እንደሚያደርግህ ታውቃለህ?

☞እነዚህን አፀያፊ ምስሎችና ቪድዮዎች በማየት የተለከፈ ወጣት በቀላሉ ካገኘው ተቃራኒ ፆታ ጋር ሁሉ ዝሙት ላይ  የሚወድቅ ይሆናል። እንዲሁም ራስን ወደ ማርካት (masturbation) ሱስና የስንፈተ ወሲብ አደጋ ተጋላጭ የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው።

☞እነዚህን የዝሙት ዌብሳይቶችና የቪድዮ ምስሎች መመልከት በአእምሮህና በአይንህ ላይ ድክመትን እንደሚከስት ታውቃለህ?  ይህን በመመልከት ሱሰኛ የሆነ ሰው ቀለል ያሉ ጉዳዮችን በቀላሉ ይረሳል። ይህ አደጋ እያደገ ሲሄድ የአእምሮ ድክመት አስከትሎበት እንዴት መናገር እንዳለበት ሁሉ ላያውቅ ይችላል! ሌሎችም ብዙ የጤና እክሎች ያጋጥሙታል!

☞ይህ ወንጀል አላህ ዘንድ ወራዳ ሰው እንደሚያደርግህ ታውቃለህ?

☞የእነዚህ ዝሙተኞች ምስል አእምሮህ ላይ ተቀርፇል?  (ይህ የአላህ ቁጣ ምልክት ነው!)

☞እነዚህን ነገሮች መመልከት ትንንሽ ነገሮችን ሁሉ የምትሰጋ ፈሪና ልፍስፍስ እንደሚያደርግህ ታውቃለህ?

☞ይህን እርቃን ብልግና የምትመለከት ሆይ!  የሸሪዓ እውቀትን ብርሃን በፍፁም ማግኘት እንደማትችል ታውቃለህ?

☞በዚህ ወንጀልህ ከምትወዳትና ከምትወድህ የህይወት አጋርህ ባለቤትህ ጋር የተረጋጋ ህይወት መኖር እንደምትነፈግ ታውቃለህ?

☞ይህን አስቀያሚ ተግባር የምትመለከት ከሆነ ደጋግ የአላህ ባሪያዎች ይህን ቀፋፊ ተግባርህን ባትነግራቸውም እንኳን ሊጠሉህ እንደሚችሉ ታውቃለህ?

☞እነዚህን ዝሙተኞችን ማየት ግዴታ የሚሆንብህ በዝሙት ወንጀላቸው በድንጋይ ተወግረው ሲገደሉ ብቻ እንደሆነ ታውቃለህ?

☞ ከዚህ ከምትመለከተው ቀፋፊ ምልከታ እውነተኛ ተውበት አድርገህ ወደ አላህ ካልተመለስክ እጅግ ከባድ ዋጋ ለወደፊት እንደሚያስከፍልህ ታውቃለህ?

☞እጅግ የምትወደውና የምትቀርበው ሰው ሞት ዜና ይህን ነገር እየተመለከትክ ብትሰማ ትወዳለህ?

☞ ከዚህ ወንጀል አፀያፊነት የተነሳ አላህ መሬትን ደርምሶ ሊያስውጥህ እንደሚችል ታውቃለህ?

☞በዚህ ቀፋፊ ምልከታ ላይ ሆነህ ሞት ሊመጣህ እንደሚችል ታውቃለህ? አስከፊ ኻቲማ ሊያስደነግጥህ እንደማይችል እርግጠኛ ነህ?

☞ጌታህ ቻይ ነው!  ለግዜው ይተውኃል፤ ነገር ግን በምትሰራው ወንጀል ደስተኛ ሆኖ እንዳይመስልህ!  ከዚህ ወንጀልህ ተውበት ካላደረክ ለወደፊትም ቢሆን ከባድ መከራ ትጋረጣለህ!

☞ የዒባዳህን ጥፍጥና እንደሚያሳጣህ አምልኮ ላይ ደካማ እንደሚያደርግህ ታውቃለህ? 

ለዒባዳ በቆምክ ቁጥር የምታያቸው ምስሎች አዕምሮህን ተቆጣጥረው እንደሚፈታተኑህ ታውቃለህ? በዚህም ከአምልኮ መሸሽና ተስፋ ቢስነት ሊሰማህ ይችላል። ይህ ደግሞ ወደ አደገኛው አዘቅት ክህደት የሚጎትት ጠንቅ ነው።

☞ ራስህን የምትጠላ የወንጀል ምርኮኛ እንደሚያደርግህ ታውቃለህ?

☞ለአላህ ብሎ አንዳች ነገርን
የተወ ሰው አላህ የተሻለ መልካም ነገር እንደሚተካለት ታውቃለህ?

☞አላህ በባሪያው መመለስ የሚደሰት የተብቃቃና ምስጉን ጌታ መሆኑን ታውቃለህ?

☞ከወንጀል ጥብቅ ከሆንክ አላህ ከችሮታው እንደሚያብቃቃህ ታውቃለህ?

☞ለደቂቃዎች (ሻህዋ) ስሜት ተብለው የሚሰሩ ወንጀሎች የአመታት ቅጣት እንደሚያመጡ ታውቃለህ? 

☞ዛሬ በዱንያ ላይ የምትሰራቸው ወንጀሎች፦ የተከለከለን ማየት፣ መስራትና ሌሎችንም በዱንያ ላይ ቅጣቱን በድህነት፣ በአደጋ፣ ሪዝቅህን በመከልከል በቤተሰብህ፣ በልጆችህና በቅርብ ሰዎች ላይ አደጋ ሊከስት እንደሚችል ታውቃለህ?

☞ይህ ወንጀል አእምሮህን ተቆጣጥሮ ከምትመለከታት ሴት ሁሉ ቀፋፊው ዝሙት ላይ ለመወደቅ እንደሚገፋፋህ ታውቃለህ?





☞ለላጤዎች ምክር!

♻️ያላገባህ እንደሆነ በተቻለህ መጠን ለማግባት ሞክር!

♻️ስለ ትዳር በቂ እውቀት ይዘህ ወደ ትዳር ግባ!

♻️ ማግባት ካልቻልክ ትርፍ የምትለውን ግዜህን በመልካም ነገር አሳልፍ፦ በፆም፣ በንባብ፣ ስፖርት በመስራት፣  መልካም ኢስላማዊ ትምህርቶችን በመማር፣ በመስማትና በማየት.......

♻️በብዛት ብቻህን ከመሆን ተቆጠብ

♻️አላህን ከዚህ ቀፋፊ ወንጀል ነፃ እንዲያደርግህ ተማፀን!

♻️መልካም ሰዎች ጋር ለመቀማመጥ ሞክር!

♻️ሸይጣን ይህን ወንጀል ባስታወሰህ ቁጥር ቆራጥ ሆነህ ላለመመለስ ሞክር!  መጀመሪያው ቢከብድብም በሂደት አላህ ይረዳሃል!

☞ለባለ ትዳሮች ምክር

♻️አግብተህ ከሆነ ከትዳር  አጋርህ ጋር ስለ  ህይወታቹህ ያለ እፍረት በግልፅ በመነጋገር የምትፈልጉትን እርካታ ሁሉ ማግኘት እንደምትችል እውቅ!

♻️ በኢስላም ጥላ ስር ያሉ ታማኝ ከትዳር ህይወት ጋር የተያያዙ አስፈላጊ ትምህርቶችንና ጥናታዊ ፅሁፎችን አንብብ!

♻️ በዚህ ላይ የተሻለ እውቀት ያላቸውን አላህን የሚፈሩ ብለህ የምታስባቸውን ወንድሞችህን አማክር!

♻️ ሚስትም የዘመኑን ክፋት ልትረዳና ነቃ ብላ ከትዳር አጓሯ ጎን ልትቆም ይገባል። በግልፅ ማውራትና ፍላጎቱን ማሟላት ብልግና ሳይሆን ብልጠት መሆኑን አውቃ በተቻለ መጠን ውበቷን በመጠበቅ የባሏ ልብ እንዳይሸፍትና እንዳይሰላች የበኩሏን ጥረት ሁሉ በማድረግ ባለቤቷን ማስደሰት አለባት!

✖️እነዚህ የተግማሙና የበከቱ ዝሙተኞች ይህችን አጭር ህይወትን እንዲያበላሹ አትፍቀድ!  ጀግና ሁን/ሁኚ!

♻️በመጨረሻም የመልካም ሰዎችን ታሪክ አንብብ! እንዴት አላህን እንደሚጠነቀቁ አስተውል። አስተንትን! በዚህ ወንጀልህ የሰማያትና የምድር ጌታን እያመፅክ መሆኑ ይሰማህ! 
ኮምፒዩተሮችህና ስማርት ስልኮችን የመዋረጃህ ሰበብ አታድርጋቸው!

ኢብኑ'ል ወርዲይ በግጥማቸው እንዲህ ብለዋል ፦
إنَّ أحلى عيشةٍ قضيتُها
ذهبتْ لذاتُها والإثمُ حلْ

ስሜቴን ያራገፍኩባቸው ጣፋጭ ግዜያቶች
ጥፍጥናቸው ሄዷል ወንጀሉ ግን ቀርቷል/ተመዝግቧል
©️opy

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

20 Dec, 18:00


ለሞቱ ጊዜ የሰራ ባርያ አላህ ይዘንለት

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

20 Dec, 04:45


🎙 ሱረቱ አል ካህፍ

إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا

ሱረቱል  ካፍ   
ከጁመዓ ቀን ሱናዎች
↩️‏ سنن_يوم_الجمعة
➊ الغسل
➋ الطيب
➌ السواك
➍ لبس الجميل
➎ قراءة سورة الكهف
➏ التبكير لصلاة الجمعة
➐ الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي ﷺ
🔹ገላን መታጠብ
🔹ሽቶ መቀባት
🔹ሲዋክ መጠቀም
🔹ጥሩ ልብስ መልበስ
🔹ሱረቱ ከህፍን መቅራት
🔹በጧት ለጁመዓ ሶላት መጣድ
🔹በነብዩ ﷺ ላይ ዱዓና ሰለዋት  ማብዛት

اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد
      
الَّلهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّد ٍﷺ 
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

19 Dec, 17:28


👉 አታህያቱ ላይ ጣትን ማንቀሳቀስ


👉 ሶላት ውስጥ ተቀምጠን ተሸሁድን ስንቀራ ጣታችንን የምናመለክተው አታህያቱ ብለን ስንጀምር ነው ወይስ አሸሀዱ አላኢላሀኢለሏህ ሰንል ነው

    መልስ
----
👉 የመጀመሪያውም ላይ ይሁን የሁለተኛው ተሸሁድ (መቀመጥ) ላይ የሌባ ጣትን ከፍ ማድረግ የሚወደድ ተግባር ነው።
ይህም ጣቱን ቀጥ የሚያረገው ከተቀመጠ ግዜ ጀምሮ ለመቆም እስኪነሳ ወይም እስኪያሰላምት ድረስ እንጂ አሽሀዱ አላኢላሀኢለሏህ ሲል ብቻ አይደለም ቀጥ የሚያረገው ።

👉 ጣትን ማንቀሳቀሱ ደግሞ በላጩ ዱዓ ላይ ሲደርስ ትንሽ ቢያነቀሳቅሰው የሚወደድ ተግባር ነው።
እሱም ለምሳሌ አሏሁመ ሷሊ አላ ሙሀመድ... አዑዙ ቢላሂ ሚን አዛቢ ጀሀነም...  ረበና አቲና ፊዱንያ ሀሰናህ ... እና ሌላም ዱዓዎችን ሲያደርግ ግዜ  ማንቀሳቀሱ ይወዳል።

📚ምንጭ  ሸይኹል አልባኒ ረሒመሁሏህ
ተማሙል ሚናህ/223
ኢብኑ ባዝ ረሒመሁሏህ መጅሙዑል ፈታዋ

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

19 Dec, 05:14


ሀራም ፊልምን ከማየት ጋር የተከሰተ

አስደማሚ የአንድ ወጣት ታሪክ :
@Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

18 Dec, 16:42


ቁጥርን ማብዛትን ብቻ መፈለግ የሂዝቢዬች ባህሪ ነው!

አሼይኸ ሙቅቢል رحمه الله እንዲህ ይላሉ:

وأنصح الإخوة السلفيين أن يبتعدوا عن هؤلاء الحزبيين، لأنّهم لا يريدون إلا تكثير سواد حزبهم.

ሰለፍይ ወንድሞቼን ከነዚያ ሂዘቢዬች እንዲሩቁ እመክራለሁ እነሱ የሂዝቢያቸውን (የቡድናቸውን ቁጥር) ማብዛትን ቢሆን እንጂ ሌላን አይፈልጉም እና

تحفة المجيب على أسئلة الحاضر والغريب، صفحة ١٤٦

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

18 Dec, 16:34


ሁሉም አዋቂ ነው መባል መፈለጉ ለዕውቀት ከዝና ይበቃዋል❗️

#እውቀት

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

18 Dec, 04:43


ዱኒያ ዋጋዋ!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿لَوْ كَانَتِ الدُّنْيَا تَعْدِلُ عِنْدَ اللَّهِ جَنَاحَ بَعُوضَةٍ مَا سَقَى كَافِرًا مِنْهَا شَرْبَةَ مَاءٍ﴾

“ዱኒያ አላህ ዘንድ የትንኝ ክንፍ ምታክል ቦታ ቢኖረት ኖሮ በአላህ የካዱ ሰዎች አንድ ጉንጭ ውሀ አይጎነጩም ነበር።”

📚 ቲርሚዚ ዘግበውታል: 2320
@Abu_babelheyr_bin_Sadik

🌺 ሰባህል ኸይር 🌺

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

17 Dec, 17:23


"ጤንነት ብልጠት ቁንጅና ሀይልና መሰል
ነገሮች አላህ ለበርካታ ፍጡሮቹ ይሰጣል
የልብ እርጋታ ግን በውሳኔው ከምርጥ ባሮቹ ብቻ ነው ሚሰጠው።"

@Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

17 Dec, 17:07


ለሚያውቀኝ ሁሉ የምለው ዑመር ኢብኑ ዐብዲልዓዚዝ ለጓደኛው እንዳለው ነው።

«መንገድ ስቼ ካገኘኸኝ። ልብሴን ሰብስበህ አንገቴ ስር ቀፍድደህ ያዘኝና በደንብ አድርገህ አንቀህ ነቅንቀኝ። ከዛም ዑመር ሆይ! አላህን ፍራ! ነገ ሟች ነህ! በለኝ።»

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

17 Dec, 11:51


የውብና አስደማሚ ቂርአት መሰረቶች

1⃣የሂፍዝ ጥንካሬ ከነ ሙተሻቢህ
መጣራቱና አለመምታታት
2⃣ፊደሎች በአወጣጥም ሆነ በባህሪ
ሰላም መሆናቸው ማረጋገጥ
3⃣የተጅዊድ ህጎችን ሁሉ ተግባር ላይ
ማዋል መቻል
4⃣የማቆሚያና የመነሻ ቦታዎችን አመራረጥ
ማማር
5⃣የቁርአን ቀላቶችና ፊደሎች ዘመን
ሚዛንን መጠበቅ መቻል

🌹اللهم نسألك
         من فضلك ورحمتك🌹

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

16 Dec, 04:12


                 እናት
        

እናት እንዲ ትላለች 3 ወንድ ልጆቼን ዳርኳቸዉ አንድ ቀን ትልቁ ልጅ ጋር ሄጄ
እዛ እድቀመጥ ጠየኩት እሱም እሺ አለኝ
ጠዋት በማግስቱ ለሚስቱ የዉዱ ዉሃ እድታመጣልኝ ጠየኳት አመጣችልኝ

ካመጣችልኝ ቡሀላ ኡዱ አድርጌ ሰግጄ
ስጨርስ በጆክ የተረፈዉን ዉሃ የተኛሁ
በት አልጋ ላይ ደፋሁት ሚስቱ ሻይ ይዛልኝ ስትመጣ ልጄ የእድሜ ነገር ነዉ
መሰለኝ አልጋዉ ላይ ሽንቴን ሸናዉ አልኳት እሳም በጣም ተናዳ ተቆጥታ

አዉጥተሽ እጠቢዉ አለችኝ  ልጄም ምንም ነገር አላላትም እኔም ከዛ ቤት
በጣም አዝኜ ወደ ሁለተኛዉ ልጄ ጋር
ሄድኩ ልክ እዳንደኛዉ ልጄ ጋር እዳደ
ረኩት እነሱም ቤት አደረኩ እዚ ግን
ሚስቱ ቢቻ ሳትሆን እሱም ጭምር

ነዉ የተቆጣኝ ከዛም ቤት በጣም አዝኜ
ወደ ሶስተኛዉ ልጄ ጋር ሄድኩ ልክ ሁለቱም ቤት እዳደረኩት እዚም ቤት
አደረኩ እሳ ግን ምላሻ ይሄ ነበር አብሽር
እናቴ እኛ ልጅ እያለን በናተ ላይ አይደል
እየሸናን ያደግነዉ አለች የዛኔ እናት

በጣም ደስ አላት በልጅቱ ንግግር ለሳም
ስጦታ ለመስጠት በጠዋት ተነስታ እናት
ወደ ወርቅ መሸጫ ቦታ ወርቁን ገዝታ
ከመጣች ቡሀላ ልጆችዋን እንዳለ

ሰበሰበቻቸዉ ከሚስቶቻቸዉ ጋር ከዜ እናት እንዲ አለች እኔ ልፈትናቹ ያደረኩት
ነገር ነዉ እንጂ ሸንቼ አይደለም አልጋ ላይ
የነበረዉ ዉሃ ነዉ አለቻቸዉ ከዛም የገዛቹው ወርቅ ለ 3ኛዉ የልጅዋ ሚስት
ተሰጣት ………የዛኔ እነሱም ባደረጉት ነገር
አፈሩ


ለናትክ ክብር ስጣት
~~~
ሚስትክ ብትሞት
ሌላ ታገባለክ
~~~
ልጅክ ቢሞት ሌላ
   ትወልዳለክ
~~~
እናትክን ብታጣት ግን...
መንቁል
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

16 Dec, 03:49


"اللهم اجعل كل همي الآخرة"
☀️ጌታዬ ሆይ! ጭንቄ ሁሉ ስለ
መጨረሻይቱ ዓለም አድርግልኝ

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

15 Dec, 05:20


☀️ያንን የሱና ሰው  ጀግናውን ምረጪው
በኒቃብ ተውበሽ ያንቺ ይሁን አምጪው

የነቢያት ወራሽ የኢስላም #ናሙና
ሰለፍዩን ወጣት ምረጪው ያን ጀግና

ምረጪው ጀግናውን ያን ሰለፊይ ወጣት
ጎስቋላ ቢሆንም ቢጎዳውም ማጣት

منقول

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

15 Dec, 05:12


↬እውን ነው በርግጥ  ሳሊህሆች ለሳሊሆች ናቸው።

↬አንዳንዴ …ግን ሂወት ወጥ መርህ የለውምና  ምርጥ የተባለችዋ ኡ እሱ ከተባለለት አረመኔ ዘንድ እጣ ፋናታዋ  ይሆናል::  ወንዱም በተመሳሳይ::

↬የ ነቢዩላሂ ኑህ ና  ሉጥ ሚስቶች ሁኔታ  ስትማር እንዲሁም ከ ፊራአውን  ቤት የኖረችዋን የ አሲያ ሁኔታ ስታስተውል ይህኑ እውነታ በግልፅ ይታይሃል..

ስለዚህ አንዱ ን/አንድዋን  የማይሆናት (የማቶነው )ሰው ዘንድ ወስዶ ጥሎት (ሏት) ብታዩ

የአንዱ መጥፎነት ለሌላኛው ወስዳቹሁ አታከናንቡ
↬አዎን እስዋ እኮ መልካም  ነበረች እሱ እንጂ
↬እሱ መልካም ነበረ እስዋ እንጂ የሚባሉ ቡዙ ባለ ትዳሮች አስተውለናል ሰምተናል አይተናል>
     እናም
   ↬ አትፍረድ  ጌታህ ጥበበኛነውና:: የጥበቡ ሚስጥር በአንተ አቅል ሚለካ አይደለም::

  አላህ መልካም አድርጎ ከመልካሞች ያገጣጥመን!

       ብቻ <<ቶኸይ አዎር>> በሮቱ!
𝖆𝖇𝖚 𝐋Ǫ𝖒𝖆𝖓
              ••ৡ✵

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

03 Dec, 17:53


በጣም ነው እንዴ የቃመው⁉️

The first law of ጫት የተበላሸን መኪና ከላይ ሆኖ መግፋት።የሚያመጣው ለውጥን ያጠናል።

The second law and the third law of ጫት ለናንተው ትቼዋለሁ። እውነትም physics ከተማራችሁ።

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

03 Dec, 17:30


ደገምከዋ ? ላትመለስ ምለህ ተገዝተህ በሰራኸው ተሸማቀህ ራስህን ጠልተህ ነበር ..ግን ተመለስካ ?
እምባሽን በፀፀት ግፊት አዝንበሽው ነበር ! በድርጊትሽ አፍረሽ ላትመለሽ ምለሽ ነበር ..በሸይጣን ላትሸነፊ ከሱ ብዙ በብዙ ልትርቂ ወስነሽ ነበራ ?  ግን ተመለሽ ..ለአንድ ደቂቃ..ሰዓት..ወይ ቀናት ደስታ ረጅም ዘመን ተሳቀቅና ? ደካማ ሰነፍ ወንጀለኛ የሚሉት ቃላቶች ቤታቸው በኛ ተቀለሰ አይደል ? ከሰራነው ወንጀል ይልቅ የሰይጣን ስላቅ አሳቀቀና ..በሱ ደስታ ተሸበርና ? ለሰዎች ደስታ መሆን ቢያስደስተንም ለሸይጣን ደስታ ሰበብ እንደመሆን ምንም አያምማ ? ያንቺ ያንተ እንዲሁም የጌታህ ጠላት ባንተ ስህተት ስኬቱን ሲቆጥር በስኬቱ ልክ ውድቀትህ ሲፋጠን ህመምህ በረታ አይደል ?

ግንኮ አሁንም ቢሆን ጌታህ መመለስህን እየጠበቀ ነው! ያቺ አስከፍተሀት ከቤት ወጥተህ ስታመሽ አይኗን ከበሩ ተክላ መመለስህን  እንደምትጠብቅው እናት ..መመለስሽን እንደምትጠብቀው እናት ጌታሽም በተውበቱ በር ዳግም ስትመላለሺ ለማየት እየጠበቀ ነው ሺ ጊዜ ወድቀን ሺ አንድ ጊዜ ሊያነሳን እየጠበቀን ነው ! ጌታዮ ስንለው ባርያዬ ሊለን እየጠበቀን ነው ! ወንጀል ውስጥ ነሀ ? ውጣ ጌታህ ግድ የለውም ብቻ ተመለስ ! ተመልሰህ ኖሮ ዳግም ወደወንጀል ሰጠምካ ? አሁንም ጌታህ ግድ የለውም መመለስህን ይጠብቃል በመመላለስህ ጌታህ አይሰለችልም ጠቅልለህ እስክትመለስ ግን ተመላለስ ሄደህ አትቅር ጌታህ እየጠበቀህ ነውና! አንቺንም::

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

    

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

01 Dec, 16:53


ለፈገግታ

ባል እና ሚስት በጣም ተጨቃጨቁና
በቃ ንግግር አልፈልግም 

የኔ ነው ያልከውን ነገር ይዘህ
ከቤት ውጣ አለችው።

እሷን ተሸክሟት ወጣ¡

የኔ የሚለው አንቺ ነሽ ማለቱ ነው .ክክክ
ኮፒ

https://t.me/+Se4xqUVr3TtG4W9L

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

30 Nov, 15:53


በቃ ዱኒያ  ይች ነች  !!

መላች ስትል የምትጎድል  ወጣሁ ስትል  የምትወርድባት    የተሞላ ደስታ የሌለባት በቃ ተሳካልኝ ብለህ አረፍ  ስትል ሌላ ፈተና ይዛ ምትጠብቅህ

አንድ ቀን የተሞላ   ደስታ  የሌለባት   ታዲያ ዱኒያ  ምንድነት  ያስኳት ስትል  እምታመልጥህ  ኖርኩባት ስትል  የምትለያት  እንደለፊህ  እንደወጣህ እንደወረድክ  እንደተቸገርክ  ዛሬ አለቀ ተሳካ ስትል አንድ ቀን የተሞላ ስኬት ሳይኖርህ  እንደለፋህ  ከሷ የምትላቀቅባት  ሀገር  ነች  ::

በቃ ለኔ  ዲኒያ  ይች  ነች!!

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

30 Nov, 15:52


ሰው   ሆይ ስለወንጀሎችህ በሁለት ምክንያቶች ለሰወች አትናገር

👉የመጀመሪያው የሚያኮራ ጥሩ ነገር አይደለም!!

👉ሁለተኛው ተውበት ብታደርግም ሰወች አይረሱም።

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

29 Nov, 04:55


ሰዎች ወንጀልን በአደባባይ እየፈፀሙ
"እድሜ አንዴ ነው" ማለትም ጀምረዋል።

ጥሩ እድሜ አንዴ ከሆነ ጀሀነም ደግሞ
እድሜ ሙሉ ነው።

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

28 Nov, 17:30


አንድ ሰባኪ ናቸው፣ በሰበካቸው መሀል ምዕመኑን ይጠይቃሉ፦

"ማርያም የማን ልጅ ናት?" ምዕመኑ ይመልሳል

"የእግዚአብሔር"፣

ቀጠለ "እግዚአብሔርስ የማን ልጅ ነው?"

አሁን የምዕመኑ ድምጽ ትንሽ ቀነሰ፣ አባ እራሳቸው መለሱት

"የማርያም"

ይህንን ካሉ በኃላ ግን ትንሽ ግራ ተጋቡ መሠል፣ ሲደመድሙት ምን አሉ፦ " ይሄ ሚስጥር በእርግጥ በጣም ከባድ ነው"
.
.
አባ! ታዲያ እርስዎ ከከበዶት ማን ይቅለለው?

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

28 Nov, 07:23


ግን የሰው ልጅ ሲከፋው ብቻ ነው እንዴ "ሁሉም ያልፋል"የሚለውን ጥቅስ የሚያስታውሰውና እራሱን የሚያፅናናው?

"ሁሉም" የሚለው ቃል እኮ ሁሉንም ነገር ያካትታል።

ሀዘንና ችግርም እንደሚያልፉ ሁሉ ደስታና ድሎትም ያልፋሉ!

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

27 Nov, 18:06


ዒልም ኖሮት!
አደቡ አኽላቁ (ስነ–ምግባሩ) የወረደ የዘቀጠ መሆኑን ቢያውቅ ኖሮ!
ዒልምን ከመማሩ በፊት አደብን አኽላቅን (ስነ - ምግባርን) ይማር ነበር!!

አብደሏህ ኢብኑ ሙባረክ -ረሒመሁላህ-
እንዲህ ይላሉ: -
ስነ-ምግባርን ለሰላሳ ዓመታት ያህል ተማርኩኝ! ዒልምን ግን ለሀያ ዓመታት ተማርኩኝ!!!
[غاية النهاية في طبقات القراء(١/١٩٨)]
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

27 Nov, 17:20


ሁለቴ በሽንት ማለፊያ የሚያልፍ ፍጡር ኩራተኛ ሲኾን ይደንቃል!!!

   አሕነፍ ቢን ቀይስ (ረ.ዐ)              
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

27 Nov, 17:16


ትናንት ጉድጓድ ዉስጥ ዩሱፍን የጣለች እጅ
ከበርካታ አመታት ብሃላ እጆን ዘርግታ
በኛ ላይ መልካም ዋልልን ሰደቃ ስጠን ብላ ዛሬ እጆን ዘርግታ መጣች!
አላህ ሁኔታወችን በማስኬድ ያሳምራልና አትዘኑ!              
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

26 Nov, 16:31


የአስራ ሁለት አመቱ  ወጣት የሆነው የውዱ ሱሃብይ አስገራሚ ታሪክ ‼️


➴ነገሩ እንዲህ ነበር ፣
ቦታው  መካ ውስጥ ነው ገና ለጋ ልጅ ነበር ምናልባትም 12ተኛ አመቱን
በቅጡ እንኳ  አልደፈነም ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ➴እንደተገደሉ ሲሰማ
ይህ ህፃን➴ ልቡ በንዴት ተቃጠለ ! ➴አይኑ በእንባ ተሞላ ! አላስችልህ ሲለው
ወሬውን አጣርቶ እውነት ከሆነ የነቢዩን ገዳይ ለመግደል # ሰይፉን ከአፎቱ
እንዳወጣ ወደ ሶፋ ተንቀሳቀሰ !

🌷 ነብዩ ወደ ሚያስተምሩበት ቦታ እየሄደ ሰዎች
አካሄዱንና ሰይፍ ማንጠልጠሉን ሲያዩ "ምን ሆነሃል?" እያሉ ይጠይቁታል ! እርሱ
ግን  ደንታ አልሰጣቸውም ! ነገሩን በራሱ ማጣራት የፈለገ ይመስላል ! የፈለገ
ቢሆን ኩፋሮችን ተፋልሞ ወይ ገድሎ አልያም ተገድሎ ካልሆነ ላለመመስ
ወስኗል!

🌷ሶፋ ደረሰ ረሱልን ፊት ለፊቱ አያቸው ! የተነዛው ወሬ  ሀሰት መሆኑን አረጋገጠ !

ልቡ በሃሴት ተሞላች!!

➴ነብዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሰይፍ መያዙን ሲያስተውሉ" ምን ሆነሀል...?"
አሉት። ➴"የአላህ መልዕክተኛ ተገድለዋል ሲባል ሰምቼ ነው !"ሲል መለሰ።"ምን
ታደርግ ነበር ?" ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሲሉ ጠየቁት !
"በአላህ ይሁንብኝ የመካ ሰዎችን እፋለማቸው ነበር !" አለ በወኔ ነብዩም ሰለላሁ
ዐለይሂ ወሰለም # የወጣቱን መልስ ሲሰሙ አላህ እርሱንም ሰይፉን
# እንዲባርካቸው ዱዓ አደረጉለት !

🌷በዚህ ነበር በኢስላም የመጀመሪያው
#ሰይፍ የተባለው !
ያ አላህ""! የአስራ ሁለት አመት ልጅ"!
አወ"! እርሱ የነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አክስት፣ የአላህ አንበሳ ሀምዛ እህት
የሆነችው የጀግናዋ ሶፊያ ቢንት ዐብዱል ሙጦሊብ ልጅ የአቡበክር አሲዲቅ
አማች የአብዱሏህ ብኑ ዙበይር አባት
#ዙበይር_ኢብኑል_ዐዋም ነበር።


🌷ከነብዩ በነበረው ቅርበትና ተወዳጅነት ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ለሁሉም
ነብይ ሀዋሪያ አለው ። የኔ ሀዋሪያ  ዙበይር ነው !" ብለው መስክረውለታል።
ዙበይር በጀግንነቱ እና በጦር ሜዳ  ጀብዱ ከኻሊድ ኢብኑል ወሊድ ውጭ
የሚስተካከለው አልነበረም ። በሁለት ሰይፍ ጠላትን የሚያጠቁ ብቸኛ ጀግኖች
ነበሩ። የዙበይር ገድል በዚህ አያልቅም ፣በበድር፣በኡሁድ፣በአህዛብ፣በኸይበርና
በሌሎች ፍልሚያወች #! የአንበሳ ድርሻ ነበረው.....
ረዲየሏሁ ዐንሁ!!!
     


https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

26 Nov, 03:41


ቀደርህን ዉደድ

«በሱ ስራ ዉስጥ ጥበብን እንጂ አታገኝም!

  √ ነብዩሏህ ዩሱፍን ( عليه السلام)  አባቱ ከልጆቹ ለይቶ ወደደው - መወደዱ - በራሱ መልካም ሆኖ ሳለ ~ ውጤቱ ግን በጉድጓድ መጣል ሆነ!

√ ጉድጓድ ውስጥ መጣል ክፉ ነገር ሆኖ ሳለ ~ በንጉሱ ቤተመግስት ለመግባት ግን ምክንያት ሆነ !

√ በንጉሱ መኖርያ ማደግ መልካም ሆኖ ሳለ ~የንጉሱን ሚስት ለፈተና አጋልጦ ዩሱፍን ( ዐ ሰ)  ለእስር ዳረገው!

√ እስር የስቃይ ቦታ ስለሆነ መጥፎ ነገር ይመስላል  ~ ውጤቱ ግን የሀገሪቷ ዋና ወሳኝ ሰው ሆኖ እንዲወጣ ምክንያት ሆነ !

መልዕክቱ ፡- አሁን ያለህበት ፈተና እና ውጥረት ቀጥሎ ለሚመጣው ስኬትህ እና ለግብህ መሳካት ቅድመ ክፍያ መሆኑን አውቀህ ፅናበት!»

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

25 Nov, 03:44


👉 ለምን ታስባለህ
👉 ለምን ትጨነቂያለሽ


የሞትና የቀብር ጉዳይ ካስተነተንን
የዱንያው ሂወት ጨዋታ መሆኑን በደንብ ይገባናል ።


👉 ጀሀንም የገቡ ሰዎች ከስራቸውም ከላያቸውም እሳት ነው

﴿ لَهُمْ مِنْ فَوْقِهِمْ ظُلَلٌ مِنَ النَّارِ وَمِنْ تَحْتِهِمْ ظُلَلٌ

👉 ልብሳቸው እሳት ነው

﴿فَالَّذِينَ كَفَرُوا قُطِّعَتْ لَهُمْ ثِيَابٌ مِنْ نَارٍ﴾

👉 መጠጣቸው እሳት የሆነ አንጀትን ቁርጥርጥ የሚያደርግ የጋለ ውሀ ነው

﴿وَسُقُوا مَاءً حَمِيمًا فَقَطَّعَ أَمْعَاءَهُمْ﴾

👉 ዙሪያቸው እሳት ነው

👉 ማምለጫ የለም
👉 እረፍትም የለም
👉 መውጣትም አይቻልም
👉 መሞትም አይቻልም

👉 ቅጣቱም አይቀንስም

በአላህ ቁጣ ስር በእሳት ተከበው ቆዳቸው ሲያልቅ ሌላ ቆዳ ተቀይሮላቸው ይኖሯታል

﴿وَإِنَّ جَهَنَّمَ لَمُحِيطَةٌ بِالْكَافِرِينَ﴾

👌 ነጌ እሳት ገቢ የሆነን ሰው ዛሬ ላይ ማግኘቱና መጥገቡ መደሰቱና መኩራቱ ምን ይጠቅመዋል

የሽርክና የኩፍር የአመፅና የኩራት ውጤት ይሄው ነው

🤲 ያአላህ ያረበና ከእሳትህ ጠብቀን

https://t.me/abduselamabumeryem/5319

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

25 Nov, 03:38


----🔺------🔺-----

🔺--የሸይኹል ኢስላም የልጅ ልጅ ኢማም ዓብዱ ለጢፍ አሉ ሸይኽ
....❗️
========

👌 ሽርክ የሚሰራው ጃሒልን ከሆነ አስተምረው ጃሒል ካልሆነ እንቢተኛ ነው ። ነገር ግን ሁለቱም ሙስሊሞች አይባልም ።

Copy

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

24 Nov, 15:06


እንደ ነቢዩ ሱለይማን ሥልጣን ቢሠጠኝ ኖሮ የተወሰኑ ጅኖችን ልኬ ነበር የምወስድሽ አላት።

ጉረኛ! እስቲ የጅኑን ነገር እርሳና የተወሰኑ ሸማግሌዎችን ብቻ ልከህ ውሰደኝ።
አለችው።
منقول

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

23 Nov, 16:52


🌱አንድ ሰው በአይን በልቶኝ ውሀ ለመጠየቅ ከፈራሁት ኡዱ ያደረገበት ቦታ አፈሩን ወስጄ ብታጠብ አይቻልም ወይ

🎙በታላቁና በተወዳጁ ወንድማችን አቡ የህያ ኤልያስ አወል حفظه الله تعالى
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/Abu_Yehya_ilyas_Awel

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

23 Nov, 14:49


ወንድ ልጅ በሴት ደካማ ነው‼️
የፈለገ  በድኑ ጀግና፣ አንበሳ ፣አይበገሬ ፣ካራቲስት፣ ስፖርተኛ ፣ቦክሰኛ፣ ጡንቻው የጠነከረ  አለ የተባለ ወንድ ቢሆንም 50ኪሎ  የማትሞላ ሴት ታሸንፈዋለች  ልቡን ጥርግ አድርጋ ትወስዳለች ለሌሎች አልበገር ያለው ወንድ በሴት ድክም ያለ ነው ።ለዚህ ከሀድስ ማስረጃ👇
ረሡል ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንድህ አሉ ሴቶችን በተመለከተ ፦

ከአቅል እና ከድን ጎደሎ አላየሁም ጀግና የተባለ ከእናንተ  የአንድኛችሁን (የወንድን ልጅ)«ልብ»👈 ከሚወስዱ ሴቶች አሉ!!
📚ሐድሱን ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል

እና እንደፈለኩ ብሆን ሴት አትፈትነኝም ብለህ ራስህን አታታል በሴት ደካማ መሆንህን አምነህ ተቀብለህ ጥንቃቄ ማድረግ  ይሻለሀል...

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

22 Nov, 16:19


የሚያሳፍር⁉️

ብዙ ጀነት መግቢያ መንገዶች ተመቻችተውልን ይህን ማድረግ እንኳ ከበደን......አጂብ‼️

💫የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «ከየግዴታ (ፈርድ) ሶላት በሗላ አየተል ኩርሲይን (ከሱረቱል በቀራ አንቀፅ 255-256) የቀራ የሆነ ሰው ጀነት ከመግባት ምንም አይከለክለውም ሞት እንጂ።» ነሳዒይ

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

22 Nov, 16:04


አላህን የሚያስረሳ ምን አገኘንና ነው ከርሱ የራቅነው? ከሱ የተሻለ የሚሰጠንን ፣ ከርሱ በላይ የሚወደንን አገኘን? ከርሱ በላይ የሚጠግነንስ? ወይስ ከርሱ ቅጣት የሚከላከልልንን አገኘን?

"فَمَا لَهُمْ لَا يُؤْمِنُونَ"
{ የማያምኑት ለእነርሱ ምን አላቸው? }

ምንም የለንም ጌታችን... ደስታም ሰላሙም መረጋጋቱም አንተው ጋር ብቻ ነው... ሰጪውም ጠጋኙም አንተው ነህ... መመለሻው ጠፍቶን ነው አንተው ወዳንተው መልሰን::

@Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

22 Nov, 04:43


ሱረቱል  ካፍ   
ከጁመዓ ቀን ሱናዎች
↩️‏ #سنن_يوم_الجمعة
➊ الغسل
➋ الطيب
➌ السواك
➍ لبس الجميل
➎ قراءة سورة الكهف
➏ التبكير لصلاة الجمعة
➐ الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي ﷺ
🔹ገላን መታጠብ
🔹ሽቶ መቀባት
🔹ሲዋክ መጠቀም
🔹ጥሩ ልብስ መልበስ
🔹ሱረቱ ከህፍን መቅራት
🔹በጧት ለጁመዓ ሶላት መጣድ
🔹በነብዩ ﷺ ላይ ዱዓና ሰለዋት  ማብዛት
اللَّهُمَّ اجْعَلْ صَلَوَاتِكَ وَبَرَكَاتِكَ وَرَحْمَتَكَ عَلَى سَيِّدِ المُرْسَلِينَ وَإمَامِ المُتَّقِينَ وَخَاتَمِ النَّبِيِّينَ مُحَمَّدٍ عَبْدِكَ وَرَسُولِكَ إمَامِ الخَيْرِ وَقَائِدِ الخَيْرِ وَرَسُولِ الرَّحْمَةِ ، اللَّهُمَّ ابْعَثْهُ مَقَامًا مَحْمُودًا يَغْبِطُهُ بِهِ الأوَّلُونَ وَالآخِرُونَ ، اللَّهُمَّ تَقَبَّلْ شَفَاعَتَهُ الكُبْرَى وَارْفَعْ دَرَجَتَهُ العُلْيَا وَآتِهِ سُؤْلَهُ فِي الآخِرَةِ وَالأُولَى كَمَا آتَيْتَ إبْرَاهِيمَ وَمُوسَى .. اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إبْرَاهِيمَ إنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إبْرَاهِيمَ إنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ»

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

21 Nov, 17:16


➩◎ድርብርብ  ጥፋቶች ‼️

🍃نسأالله السلامة والعافية 🍃

➲በሃላል ተጋቡ አላህን አታስቆጡ ሸሪዓ ድንጋጌን አትጣሱ‼️

➲አሏህን ፍሩ ወደ ጌታችሁ ተመለሡ‼️

➲አላህ በተከበር ቃሉ ዝሙትን አትቅርቡት ነው ያለው‼️

➲ዝሙት  መፈጸም እርግዝ በመፈጠሩ ተደናግጦ  ጽንሱን  ማስወረድ በተለይ  ሩህ ከተነፋበት በኋላ ‼️

➲ዝሙት  መፈጸም
ከዚያ ልጅቷ ማርገዟን ሲያረጋግጡ  ተሯሩጦ  ኒካህ ማድረግ‼️

➲በእርግዝና  ላይ ያለች  ሴት እስካልወለደች ድረስ ኒካህ ማድረግ አለመቻሉን የኢማሙ  ማሊክ፣ የሻፍኢይ፣ እንድሁም ከሀነፊያ  መዝሀብ የአቡ ዩሱፍ  አቋም  ሲሆን ዑለማዎችም  ኢብኑ ባዝ፣ ኢብኑ  ቀዑድ፣ኢብኑ ዑሰይሚን  የሚደግፉት  አቋም  ነው‼️

➲ዝሙት መፈፀም  ማርገዟ ሲረጋገጥ ኒካህ ማሰር ሸሪዓዊ ባልሆነ መልኩ የሚወለደውን ልጅ ልጄ ነው ብሎ መሞገትና ለልጅ የሚሰጡ ሀቆችን በሙሉ መስጠት‼️

➲ሚስት ማግባት ወንዱ መሃን መሆኑን ሲያረጋግጥ ሂጂና ከየትም አርግዥልኝ‼️

➲ እኛ እናሳድገዋለን ብሎ ሚስቱን እንድትባልግ ወደሌሎች መላክ ከሌላ እንዳረገዘችው እያወቁ የራሳቸው ልጅ ማስመሰል‼️

➲እነዚህ ሁሉ በሀገራችን በስፋት የሚታዩ ድርብርብ ወንጀሎች ናቸው‼️

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

21 Nov, 15:45


በኩላሊት እጥበት ጊዜ ደም ከሰውነታች በቀዩ ቱቦ ይወጣና በ Dialysis Machine አልፎ በሰማያዊ ቱቦ ተመልሶ ወደ ሰውነታች ይገባል።

እንዲህ እያለ ለ 4 ሰዓታት ይቆያል  ይህ Dialysis በሳምንት 3 ጊዜ በወር 12 ጊዜ ይደረጋል። በአጠቃላይ በወር ለ 48 ሰዓታት ታማሚው ሳይንቀሳቀስ Dialysis ያደርጋል።
እኔ እና እናንተ ግን በቀን 36 ጊዜ ኩላሊታችን ራሱን ያጥባል ያውም ያለ ምንም ህመም እና ስቃይ።
አላህ የዋለልንን ፀጋ እናስታውስ
አልሀምዱሊላህ እንበል
በዚህ ህመም ለሚሰቃዩ አላህ ጤናቸውን ይመልስላቸው
..........
{ وَإِن تَعُدُّواْ نِعۡمَةَ ٱللَّهِ لَا تُحۡصُوهَآۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَغَفُورٞ رَّحِيمٞ }

የአላህንም ጸጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም፡፡ አላህ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

20 Nov, 17:18


⭕️አይ የኛ የወንዶች ነገር  الرجال قوامون على النساء አር-ሪጃል ቀዋሙን ዐለ'ኒሳእ!! ተብለናል ብለን በቃ  እምቡር እምቡር እንላለን ኣ⁉️

ሀቢቢ ቀዋምነት
#የማዕረግ ሳይሆን #የኃላፊነት ጉዳይ ነው!!

እሷ አጋልጋይህ ሳትሆን ንግሥትህ ናት!!

እሷ ሠራተኛህ ሳትሆን  እመቤትህ ናት!!

እሷ የበታችህ ሳትሆን  ባልደረባህ ናት!!

ልታከብራት ላትንቃት!!

ልትንከባከባት፣ ላታጣጥላት ኃላፊነት አለብህ‼️

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

19 Nov, 16:02


👉ዉድድርህ ከሰዎች ጋር አይደለም!!!

ዉድድርህ:-👇

ከገደልከዉ ሰአት!!

ከፈጠርከዉ በሽታ!!!

መማር እያለብህ ችላ ካልከዉ እዉቀት!!!

መስዋእት ካረከዉ ጤናህ!!

አዲስ ሃሳብን አልቀበልም ካልከዉ ማንነት!!!

ያንተን መጣር ከማይወዱ ሰዎች!!!

እድለ ቢስ እንደሆንክ ከሚነግርህ ሰይጣን ጋር ነዉ...!!!


https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

18 Nov, 07:29


ዐብዱላህ ኢብኑ ሙባረክ: ‐ «እድሜህ አንድ ቀን ብቻ ነው የቀረው ብትባል ምን ትሰራበት ነበር?» በማለት ተጠየቁ።
እርሳቸውም: ‐ «ሰዎችን አስተምር ነበር።» በማለት መለሱ።

https://t.me/+Se4xqUVr3TtG4W9L

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

15 Nov, 18:02


መልካምና ሙተደይና ወደሆነችው እህቴ

በዲኑ ከአንቺ የበታችና የወረደ የሆነውን ሰው ለትዳርሽ አትምረጪ

መምረጥ ካለብሽም 👌

ሸይኽሽ አስተማሪሽ በዲንሽና በአኺራ ጉዳይሽ ላይ ስኬታማ እንድትሆኝ
ጠንካራ ወኔ ያለውና ለአንቺ ሚራራ የሆነውን ምረጪ

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

15 Nov, 18:00


ኢብኑ ዑሰይሚን رحمه الله :

የሰዎች ሪዝቅ በተለያዩ ሰበቦች ላይ የተወሰኑና የተፃፉ እንደሆነው ሁሉ ትዳርም የተፃፈና ተወስኖ ያለቀ ነገር ነው

በእርግጥም እያንዳንዱ ጥንዳሞች አንዱ ለሌላኛው ጥንድ እንዲሆን ተለየቶ ተፅፏል ይላሉ።

[ نور علـى الدرب ( صـ 36 )]👉ምንጭ
ــــــــــــ ❁ ❁ ❁ ❁ ــــــــــــ

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

15 Nov, 17:01


⭕️ ለማግባት ስትፈልግ አላህ   ሶስት ነገር እንዲሰጣቹ ለምኑት

አላህ ሆይ አንተን ለማስታወስ የምትረዳኝ የትዳር አጋርን ስጠኝ

ያ አላህ ባንተፍቃድ ያንተን ፍላጎት አሟልታ በጀነት አብረን
እንድንኖር የምትረዳኝን ስጠኝ

ያ አላህ የኢማን ደረጃዬን የምታሳድግልኝ አጋር ስጠኝ

ብላችሁ ለምኑት
🤲

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

14 Nov, 18:13


💥ወደድንም ጠላንም ከተማ ዉስጥ ተቀምጠን ኡዝር ቢል ጀህል አለ? ወይስ የለም?

እያልን ከመነታረክ ወደ ገጠሩ ክፍል ጠልቀን በመግባት ይከፍራል ወይስ አይከፍርም?
እያልን የምንጨቃጨቅበትን የዋህ ማህበረሰብ ንፁሁን ኢስላም ማስተማር በእጅጉ የበለጠ ነዉ‼️

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

14 Nov, 14:12


ፈጅር ወቅት ላይ ከተማና መንደሮች ፀት ማለታቸው ንጋት ላይ በስራ ሰአት በሰዎች
ብዛት መጨናነቃቸው ትውልዱ አኺራን መርሳቱና በዱንያ ፍቅር መወጠሩ ያሳያል።

اللهم لا تجعل الدنيا أكبر همّنا...🌸

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

14 Nov, 02:22


#ፈጅር ... ሰላት     
⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡     
   ፈጅር ....         
ለፊትህ ብርሀን ፣  ለልብህ እረፍት  ፣  ለነፍስህ መርጊያ ናት ! 
 
حي على الصلاة
حي على اافلاح   
الصلاة خير من النون  ❗️ 

 🇰🇼ፈጅር አዛን 5.28

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

13 Nov, 17:27


◉ ፅኚ በሂጃብሽ !!

በሱረቱል አህዛብ በደማቅ ተከትቧል
ከአንገትሽ ቀናበይ  ታሪክሽ ተውቧል

ድንቅ ነው ኢስላምሽ ከአምላክ የተሰጠሽ
ቅይጥ የሌለበት ጥርት ያለ ሀብትሽ

እስኪ መለስ በይ እልፍ አመታትን
ትእዝዛ ሲመጣ ወህይ ከአምላካችን
እንዴት ነበረ እስኪ ድንቁ ታሪካችን?

የሂጃቡ ኣያ ሲወርድ ለአለማት
ያኔ ሲታዘዙ እኒያ ሶሀቢያት

ሀገሩን አስዋቡት በጥቁር ቀለማት
በኒቃብ በጅልባብ አበሩ በውበት።

አንቺስ ምንሽ ሞኙ ማማር የምትጠይው
በሂጃብ ተውበሽ አምላክሽን ታዘዢው

አዎ ታዘዢው ሀያሉን ህልምሽ እንዲሳካ፤
በዱንያም በአኼራም እንድትይ ፈካ

አትስጊ በፍፁም ባል ይጠፋል ብለሽ
እዝነቱን ፈልገሽ ኒቃብ በመልበስሽ

አንቺ ጀግና ሆነሽ ለትእዛዙ ካደርሽ
ቤትሽን ያንኳኳል ይቆማል ከበርሽ።

ዒልምሽን ተማሪ ጠዋት ማታ ድከሚ
ጅህልናን ለመግፈፍ በደሊል ታከሚ

በሰላሙ ጊዜ ስንቅሽን ካልሰነቅሽ
ጎታችሽ ይበዛል አንችም ትሄጃለሽ

ስለዚህ እህቴ ዒልም ላይ ጠንክሪ
አሰሱን ገሰሱን ቆሼ ፍርፋሪ

እንደ እስፓንጅ አትምጠጭ ፈጣሪሽን ፍሪ
አህባሹ ሲመጣ ከአህባሽ አትስፈሪ

ከኢኽዋን ዘናጩ ከሱናው ርቆ
ላይሽ አልመኝም ያ ውበትሽ ደርቆ

ከጀምዒይ ለስላሴ ልወደድ ባይ ከንቱ
ላይሽ አልመኝም ስትቀሪ ከንቱ።

ያንቺ መታለልሽ መሸወድ ሳይበቃ
ትውልድ ይበላሻል የኢስላም ውድ እቃ

የነገውም ተስፋ ያ እንቁ ፀሀይ
አንድነት ይሰብካል ከኢኽዋን ስትውይ
ከተውሂድን ይርቃል ከሱና ሰማይ

ከአህባሽም ከዋልሽ ትውልድ ይበላሻል፤
ከተውሂድ ርቆ በሽርክ ይደበቃል

በዱአው አሳቦ ከሱስም ይወድቃል
ከድቤ ዳንኪራ አጥር ይወሸቃል

ከተብሊጉም ከዋልሽ ትውልድ ይበላሻል
ኡሉህያን ርቆ እድሜውን ይፈጃል

በ 3  በ40 ቀን በተብሊግ ፍከራ
ወገኑን ሊታደግ ተውሂድ ሳይጣራ
እድሜውን ይፈጃል አንድ ውል ሳይሰራ

ለዚህ ሁሉ ስህተት ምክንያቷ አንቺ ነሽ
በኢስላም ስር ውለሽ መንሀጅ ስላልገባሽ

መሰረት የጣልሽው ካለቦታው ሆኖ
ግንቡን አፈረሽው የትም ቀረ ተኖ

ሰንደቅሽ ከፍ ብሎ ሁሌም እንዲያምርብሽ
እዛም እዛም አትበይ ይለይ መንሀጅሽ

እውነቱን ልንገርሽ የሂጃብሽን ዋጋ
ሊያናግርሽ ያፍራል ካንቺ የተጠጋ

መናቅኮ አይደለም ክብር ስላለው ነው
ሊቀርብሽ ያልቻለው በሩቁ የሸሸው

አንቱታን አተረፍሽ በ15 አመትሽ
ድል አጎናፀፈሽ ኒቃብ በመልበስሽ

ወለም ዘለም አትበይ ፅኚ በሂጃብሽ
ፊትናም አትፍጠሪ ተደበቂ ቤትሽ

ምድር ሁኝ ለባልሽ ሰማይ እንዲሆንልሽ፤
ክብርን አጎናፅፊው እሱም እንዲያከብርሽ

ደሞ ሴቶች አሉ ፀጉር የሚቆልሉ
ሂጃብ ለበስን ብለው የሚንቀዋለሉ

ረሱል ተራግመዋል ብለሽ ስትነግሪያቸው
አቦ አታጠባብቂ እነሱን ተያቸው

ገና አልሰለጠኑም ኃላ ቀር ናቸው
ብለው ያሾፋሉ ሞኛ ሞኝ ናቸው

ፀጉር መቆለሉ ደሞም መወጣጠር
ቅርፅን ማሳየቱ ሂጃብን መወርወር
ይሄ አይደል መስፈርቱ ለትዳርሽ መስመር

ይልቅማ አዳምጪኝ ለትዳርሽ ማማር
ዘላቂው መፍትሄ በሰላም ለመኖር
ሁሌ ለመወደድ ሁሌም ለመፈቀር

ሂጃብ ነው ሚስጥሩ ልቀቂው ከላይሽ
ሀያእም ተላበሽ አርጊው ጎረቤትሽ

ፈላስፋም አትሁኝ ማስረጃን ሰንቂ
ለምትሰሪው ስራም ደሊሉን እወቂ

ይህንን ካደረግሽ እህቴ እወቂ
ፍፁም አትወድቂም የለሽም ነቅናቂ።
 
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

12 Nov, 05:08


◉ሂጃብሽን አደራ!!!


ከቤት ስትወጪ ስትዉይ ከገበያ
ወይንም ሌላም ቦታ ከህዝብ መዋያ
ሂጃብሽን አትርሽ ሀራም መከልከያ

የትም የትም ቢሆን የዲንሽ ዉበቱ
ልፋትሽ ጥረትሽ የሚያምረዉ ዉጤቱ

የምትኮሪበት በሙስሊምነትሽ
ለሀራም ለዚና ሁሉ እንዳይመኝሽ

የሰፈር ቦዘኔ እንዳይቀልድብሽ
እንቶኔ ሰካራም እንዳይዳፈርሽ
ሂጃብሽን አደራ እሱ ነዉ መከታሽ።

ሲያዩት ያላማረ ሲበሉት ያቅራል
ያልተሸፋፈነ በዝንብ ይወረራል!!!

ስለዚህ ለመኖር በሸሪአ ጎራ
አይን ሳይበዛብሽ ሆነሽ ከሴት ተራ
ሂጃብሽን አትርሽ ሀራም መከልከያ።

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

12 Nov, 04:49


💫እድሜ ወደዘላዓለመዊ ሐገር ( ወደ ጀነት) መጓጓዣ የሆነች እቃ መሆኗን ያወቀ  አያባክናትም  ። በል እንዳውም ይሥገበገብለታል ፣ከገንዘቡም በላይ ይሳሳለታል ።

   ابن الجوزي رحمه الله
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

10 Nov, 18:51


አሏህ ሆይ ግፈኞችን የዕጃቻውን እዚሁ በዱንያ አሳየን!!🤲አሏሁ ማአሚን

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

10 Nov, 18:31


ያለነው ዱንያ ላይ ነው። ብዙ ሰው ተበድሎ ፍትህ የሚያጣበት ሃገር። ጉልበተኛ በጉልበቱ፣ ሹመኛ በስልጣኑ፣ ሃብታም በገንዘቡ፣ ዘረኛ በወገኑ፣ ቡድንተኛ በመንጋው፣ ተንኮለኛ በሴራው ፣ ... ሐቅህን ቢነጥቅ፣ ገንዘብህን ቢወስድ፣ ስምህን ቢያጎድፍ፣ ጩኸትህን ቢቀማህ ሐቄ ከንቱ ይቀራል ብለህ አትጨነቅ። ክስህን ለአላህ አሳልፍ። ፋይልህን ወደ አኺራ አሻግር። ስለ ምስክር አታስብ። ነገ ሌላ ቀን ነው። ኣኺራ ዱንያ አይደለም። በደለኛ ላይ የገዛ አካሉ የሚመሰክርበት ጊዜ። ዳኛው ኃያሉ ጌታ ነው። አይረሳ፤ አይዘነጋ፤ ጉቦ አይቀበል፤ በጥቅም አይደለል፤ በማስፈራሪያ አይታፈን። የሰው ልጅ ስራ ትንሽ ትልቁ ተመዝግቦ ለሚዛን የሚቀርብበት ጊዜ።

ይልቅ ያንን ቀን ፍራ! ይልቅ ለዚያ ቀን ተዘጋጅ።
ይልቅ ከበደል ራቅ።
መንቁል

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

09 Nov, 16:02


ሙአዚኑ ለፈጅር ሶላት ሲጣራ አንተ በሁለት አማራጮች ውስጥ ነህ።

አንድም ህልምህን ለመጨረስ መተኛት
አልያም ህልምህን እውን ለማድረግ መነሳት።


ምርጫው ያንተ ነው !


@Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

09 Nov, 02:19


የሱብሒ አዛን❗️

• ከሌሎች የሶላት አዛኖች በተለየ መልኩ በሱብሒ አዛን ላይ የምትጨመር ቃል አለች፡፡ «አሶላቱ ኸይሩን ሚነነውም» ሶላት ከእንቅልፍ በላጭ ናት፡፡― የምትል፡፡ አዎን ሶላት ከእንቅልፍ በላጭ ናት፡፡

እንቅልፍ የሥጋ ጥሪ ነው፤ ደከመኝ አሳርፉኝ ይላል። ሶላት የአላህ ጥሪ ነው፡፡ አላህ ወደኔ ኑ እረፉ ይለናል፡፡
እንቅልፍ ሞት ነው፤ ሶላት ደግሞ ሕይወት፡፡ በሶላትህ ነፍስ ዝራ፣ ከነፍስህ ጌታ ጋር ተገናኝ፡፡
እንቅልፍን አካልን ያሳርፋል፤ ሶላት ግን ቀልብን ያረጋጋል፣ መንፈስን ያሰክናል፡፡
ሶላት የአማኞች መለያ ናት፤ ጌታ እንደሌለው ባሪያ ያለ ሀሳብ ዥው ብለህ አትተኛ፡፡ ተለይተህ ተነሳ፡፡
እንቅልፍ ሲበዛ ያሰንፋል፣ ለድካምም ለዱካክም ያጋልጣል፡፡ተነስቶ መስገድ ንቃትን ይሠጣል፣ አካልን ያፍታታል፣ ፊትን ያበራል፣ ወዝን ይመልሳል፡፡
የማለዳ አየር የተለየና ፀጥ ያለ ነው፡፡ ለዒባዳም፣ ሀሳብን አሰባስቦ አላህን ለመማፀንም ምቹ ነው፡፡
በሶላት የተከፈተ ቀን ድል አለው፣ በረከትና ስኬት አለው፡፡
ሱብሒ ላይ የሚተኛ የሸይጣን ምርኮኛ ነው፤ ለሸይጧን ጆሮ የሠጠ ነው፡፡ አልነጋም ተኛ ይለዋል፡፡

የሱብሒ ጊዜ እንዴት ያማረ ጊዜና ዉብ ሰዓት መሠላችሁ!

☞ የሱብሒ ሶላት ሱንናው በዱንያ እና በዉስጡ ካሉ ነገሮች ሁሉ በላጭ ነው፡፡
☞ የሱብሒ ሶላት ግዴታው የአላህን ጥበቃና ዋስትና ያስገኛል፡፡
በርግጥም «አሶላቱ ኸይሩን ሚነ ነውም'ን» እየሰሙ «ሐይየ ዐላ ሶላህ፣ ሐይየ ዐለል ፈላሕ'ን» እያዳመጡ መተኛት ይከብዳል።

ወዳጆቼ ለይል ቢያቅተን አሁን ላይ ሆነን ሱብሒን ብናስብ ምን ይለናል!?

منقول
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

09 Nov, 02:15


🔬እንዴት መለየት ይቻላል

📚 ሱና ሚከተል የሆነ ሰውና
🛤 ስሜቱ ሚከተል የሆነ ሰው እንዴት ለይቶ ማወቅ ይቻላል

ሸይህ ፈውዛን ሀያሉ ይጠብቃቸው እንዲህ ይላሉ👇
إذا قلت لصاحب الحق إذا أخطأ: أنت أخطأت الدليل، أخطأت السنة، فإنه يقبل، لأن قصده الحق، وليس قصده الانتصار لرأيه، أما إذا قلت لصاحب الهوى: أنت أخطأت، فإنه يغضب ويشتد، وهذه علامة أهل الأهواء، أن كل واحد يريد أن ينتصر لهواه.
  /شرح السنة للبربهاري/56/
👌ሀቅ ሱና ሚከተል ለሆነ ሰው በተሳሳተ ጊዜ
=>መረጃው ስተሃል; ሱናው ስተሃል (ተሳስተሃል)  ስትለው👉ይቀበልሃል ምክንያቱም
👇
👉 ፍላጎቱ ሀቅ መግጠም እንጂ ስሜቱን ማራመድ አይደለምና።


👌🏿የስሜቱ ተከታይ የሆነ ሰው ግን በሚሳሳት ጊዜ
=> ተሳስተሃል ስትለው 👉ይቆጣሃል ይበረታብሃል።

👉 ይህ ነው የስሜት ተከታዮች ምልክታቸው።
ሁላቸውም ስሜታቸውን ማራመድና መርዳት ይፈልጋሉ።


ht🔬እንዴት መለየት ይቻላል

📚 ሱና ሚከተል የሆነ ሰውና
🛤 ስሜቱ ሚከተል የሆነ ሰው እንዴት ለይቶ ማወቅ ይቻላል

ሸይህ ፈውዛን ሀያሉ ይጠብቃቸው እንዲህ ይላሉ👇
إذا قلت لصاحب الحق إذا أخطأ: أنت أخطأت الدليل، أخطأت السنة، فإنه يقبل، لأن قصده الحق، وليس قصده الانتصار لرأيه، أما إذا قلت لصاحب الهوى: أنت أخطأت، فإنه يغضب ويشتد، وهذه علامة أهل الأهواء، أن كل واحد يريد أن ينتصر لهواه.
  /شرح السنة للبربهاري/56/
👌ሀቅ ሱና ሚከተል ለሆነ ሰው በተሳሳተ ጊዜ
=>መረጃው ስተሃል; ሱናው ስተሃል (ተሳስተሃል)  ስትለው👉ይቀበልሃል ምክንያቱም
👇
👉 ፍላጎቱ ሀቅ መግጠም እንጂ ስሜቱን ማራመድ አይደለምና።


👌🏿የስሜቱ ተከታይ የሆነ ሰው ግን በሚሳሳት ጊዜ
=> ተሳስተሃል ስትለው 👉ይቆጣሃል ይበረታብሃል።

👉 ይህ ነው የስሜት ተከታዮች ምልክታቸው።
ሁላቸውም ስሜታቸውን ማራመድና መርዳት ይፈልጋሉ።

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

09 Nov, 02:15


👌 ከፊሎች ለተስሚያ ኡዝር ቢልጀህል የለም ማለት ለሙስጠፋ ዲፋዕ ማድረግና የሙስጠፋን አጋር መሆን አድርገው ያዩታል


👉 ይህ ነጥብ ሙስጠፋ ወደዚች ዱንያ ገና ብቅ ከማለቱ በፊት አኢማዎች ብዙ ያወሩበትና የፃፉበት የሆነ መስአላ ነው ።


ሌላው ለአዚሮች
ማስረጃ መልስ መስጠትም የኡለሞችን ክብር መንካት አይደለም

አልባኒ ሴት ልጅ ፊቷን መሸፈን ዋጂብ አይደለም ሲል እኮ ሌሎች ዋጂብ ነው ያሉት እሱ ማስረጃ ያለው ማስረጃ አይሆንም ብለው መልስ ሰጥተዋሉ


ለዲን ያገለገለ ሁሉ ክብር ይገባዋል

ነብያችን ﷺ እውራ ዶሮ ለሰላት ይቀስቅሳልና አትስደቡት አሉ

ተመልከቱ ዶሮ እንኳ ጩሀቱ ለሰላት ለመነሳት ሰበብ ስለሚሆን ተከብሯል

ማይሳሳት የለም ማንም ሊሳሳት ይችላል


عن زيد بن خالد الجهني قال نهى رسولُ اللهِ - صلَّى اللهُ عليهِ وسلَّمَ - عن سبِّ الدِّيكِ، وقال : إنهُ يؤذِّنُ للصلاةِ رواه أبو داود وصححه الألباني

قال الحليمي: كما في فيض القدير:
فيه دليل على أن كل من استفيد منه خير لا ينبغي أن يسب ولا يستهان به بل حقه الإكرام والشكر ويتلقى بالإحسان

https://t.me/abduselamabumeryem/5307

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

08 Nov, 17:54


"አላህ ፀሀይ በመግቢያዋ እስክትወጣ ድረስ ቀናቸውን በወንጀል ያሳለፉ ሰዎች ወደእርሱ እንዲመለሱ ምሽት ላይ እጁን ይዘረጋል እንዲሁም ምሽታቸውን በወንጀል ያሳለፉ ሰዎች ወደእርሱ እንዲመለሱ ቀን ላይ እጁን ይዘረጋል"

#ረሱል

"ጌታችን ሆይ! ነፍሶቻችንን በወንጀል በድለናል ይቅር ካላልከን እና ካላዘንክልን ከከሳሪዎች እንሆናለን!"

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

06 Nov, 16:26


◉ውዷ ―እህቴ ―ጊዜው― የኒቃብነው!


¤" ብዙዎቹ ኒቃብ ለምን? ይላሉ።
ግን ዙሪያችንን ብናስተነትን
.
①" ምድር ሽፋን ያላት መሆኑ
.
②ለሰይፍ ሽፋን አፎት መኖሩ
.
③"እስክሪብቶ ያለ ሽፋን
ቀለሙ ቶሎ መድረቁ
.
④አፕል ሽፋኑ ባይኖር ኖሮ ወዲያውኑ መበላሸቱ
.
⑤"ሙዝ ሽፋኑ ቢነሳ ወዲያውኑ መጥቆሩ
.
⑥"ተማሪዎቻችን ደብተሮቻቸውን የሚሸፍኑት እንዳይበላሽባቸው መሆኑን በአስተውሎት
ብንመለከት ሽፋን ያለውን ጥቅም እንረዳ ነበር።
.
🎖ሴቶች ደግሞ ከሁሉም በላይ ውብ ናቸውና የሚሸፈኑበት ሂጃብ ( ኒቃብ ) ያስፈልጋቸዋል!!!
.

🎖ሌላው ቀርቶ ለስልኮቻችን እራሱ ሽፋን ከየትም አፈላልገን ገዝተን እናደርጋለን ፡፡
.
🎖ታድያ ውዷ እህቴ አንቺ ከሙዝ በምን ታንሺያለሽ ፣ ከሞባይል በምን ታንሽያለሽ ?
        አንቺ ፦
.
🎖እኮ አላህ እሱ በፈለገውና ባማረ ቅርፅ ፈጥሮሽ ሲያበቃ የወንዶች ቀልብ ማረፊያ አደረገሽ ፡፡

·
🎖የሚገርመው አንድ ሠው ምኑንም ያክል ሀብታም ቢሆን ምኑንም ያክል የተከበረ
ባለስልጣን ቢሆን የደስታው ጥግ ያለው ሴት ጋር ነው ፡፡
.
🎖ለዚህም ነው የአላህ መልዐክተኛ(ﷺ) እንዲህ ብለዋል
ዱንያ ውስጥ ካሉት ከሚያስደስቷቸው ነገሮች መካከል【 ሴቶችን】
የጠቀሱት ፡፡
.
🎖 ከምንም በላይ ደግሞ አህቴ "አላህን ልትፈሪ ይገባል " አንድ ጥያቄ እራስሽን
ጠይቂ?
.

🎖 አሁን ያለሽበትን ይህን ያማረ ገፅታ ማን ነው የፈጠረው " ..?
.
መልስሽ አላህ ከሆነ ፦
.
አላህ በሰጠሽ ፀጋ እሱ ታምጭዋለሽ ?
.

🎖አላህ ለእናንተ ሂጃብ የምትለብሱበትን ለኛ ( (ለወንዶች )) ዐይናችንን የምንሰብርበትን
ኢማን ይስጠን !!!
      
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

06 Nov, 06:12


ማሳሰቢያ ⚠️

ሰሞኑን በቴሌግራም መልዕክት የተለያዩ ሊንኮች እየተላኩ የብዙ ሰዎች የቴሌግራም አካውንት እየተጠለፈ ሲሆን ራሳችሁን እነዚህን ማስፈንጠሪያ ሊንኮች ባለመንካት ጠብቁ፤ እነዚህ ማስፈንጠሪያ ሊንኮች የቴሌግራም Login Page በማስመሰልና ስልክ ቁጥራችሁን እና ሌሎች መረጃችሁን በመቀበል አካውንታችሁን እስከመጨረሻው ይወስዱታል፡፡

Warning ⚠️

Recently, many people's Telegram accounts are being hacked by sending various links via Telegram message chats. These hacking links will impersonate the Telegram Login Page and take your phone number also other information to take over your account.

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

05 Nov, 04:39


ህመምና መከራ ሲመጣበት
ጌታዬ ሆይ ብሎ ተጣራ
ልጅ ሲያጣና ብቸኝነት ሲሰማው
ጌታዬ ሆይ ብሌ ተጣራ
ችግርና ጭንቀት ሲደርስበት
ጌታዬ ሆይ ብሎ ተጣራ
አላህም አላዋረዳቸውም
ዱዓቸውን ተቀበለ ፍላጎታቸውንም
አሟላላቸው, ካሉበት ችግርም አወጣቸው ።

‎(وَأَيُّوبَ إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُ أَنِّي مَسَّنِيَ الضُّرُّ وَأَنْتَ أَرْحَمُ الرَّاحِمِينَ)
አዩብንም ጌታውን «እኔ መከራ አገኘኝ
አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ
ሲል በተጣራ ጊዜ (አስታውስ) ፡፡"
[አንቢያእ 83]

‎(وَزَكَرِيَّا إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُ رَبِّ لَا تَذَرْنِي فَرْدًا وَأَنْتَ خَيْرُ الْوَارِثِينَ)
ዘከሪያንም «ጌታዬ ሆይ! ብቻዬን አትተወኝ
አንተም ከወራሾች ሁሉ በላጭ ነህ ሲል»
ጌታውን በተጣራ ጊዜ (አስታውስ) ፡፡"
[አንቢያእ 89]


وَنُوحًا إِذْ نَادَىٰ مِنْ قَبْلُ فَاسْتَجَبْنَا لَه فَنَجَّيْنَاهُ وَأَهْلَهُ مِنَ الْكَرْبِ الْعَظِيمِ)
ኑሕንም ከዚያ በፊት
(ጌታውን) በጠራ ጊዜ (አስታውስ)
ለእርሱም (ጥሪውን) ተቀበልነው
እርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳን ፡፡
[አንቢያእ 76]

አንተም ሙሲባዎች ሲደርሱብህ
ሰውን ወደ ጎን ትተህ እጆችህን አንሳና
ጌታዬ ሆይ ብለህ ተጣራ አዛኙ, ሩህሩሁና ቸሩ አላህ አያዋርድህም‼️

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

04 Nov, 14:58


◉የሙእሚን ህይወት
በመፈተን እንጂ አትሆንም!!

⇨ ፈተና ጣእም የሚኖረው
ሰብር ሲኖር ነው
⇨ ሰብር ደግሞ ሙሉ የሚሆነው
የአላህን ቀዳ እና ቀደር አምኖ እና
ወዶ መቀበል ሲኖር ነው !!!

☞ በህይወት ጉዞ ስኬት ማለት
ይህ ነው ።
     
@Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

04 Nov, 14:56


ከሶላትህ ከተዳከምክ ቁርኣንን ችላ ካልክና ከዚክር ከተዘናጋህ በኋላ የሐዘንና ጭንቀት  ወታደሮች ቢወሩህና ቢያሹህ ነፍስህን እንጂ  ማንንም እንዳትወቅስ!!


https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

03 Nov, 11:34


ለአዚሮች ማስረጃ መልስ ቁ.2


ስሞት አቃጥላቹህ በትኑኝ ያለው ሰውዬ ሀዲስ

ለቀብር አምላኪዎች ባለማወቃቸው ኡዝር ለመጠት ማስረጃ አይሆንም

https://t.me/abduselamabumeryem/5299

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

03 Nov, 11:32


…"በአሉባልታ ተመርተህ ጭፍን ጥላቻ አታመርቅዝ የአንዱን ጥፋት በሌሎች ላይ አትለጥፍ የበደል ገፈት መራራ ነውና ከምትጠላውም ሰው ጋር ቢሆን ሁል ጊዜ ፍታሃዊ ሁን"።
https://t.me/WATESiMU/5002

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

02 Nov, 04:10


ህይወት ከባድ  ናት ‼️
~~
      ◎ በኑሮህ  ውጣ  ውረድ  አትዘን _ ከመሰናክል  ማምለጥ  አትችልም
◉   ህይወት  ብዙውን  ጊዜ  ስራና  ኃላፊነት  ነው  ። 
◉ ደስታ አልፎ አልፎ የሚመጣና  የሚሄድ ክስተት  ነው  ።  ይህን ህይወት ትናፍቃለህ ። ነገር  ግን  አሏህ  ይህ  ህይወት  ለቀን  ባሪያዎቹ ቋሚ መኖሪያ እንዲሆን አልፈለገም ‼️
            ◎  ይህ  ዓለም  የፈተና  ቦታ  ባይሆን  ኖሮ  ከበሽታና ከችግር  የፀዳ በሆነ ነበር  ።  ለምርጥ  ሰዎች   _ ለመልዕክተኞችና ለነብያት ምቹ  መኖሪያ በሆነ ነበር  ።
         ነብዩሏህ  አደም  ዓለይሂ ሰላም ይህችን  ዓለም  እስከተሰናበቱባት  ቀን  ድረስ  ብዙ መከራና  ችግር  ደርሶባቸዋል
            ነብዩሏህ  ኑህ  ዓለይሂ ሰላም  የራሳቸው  ሰዎች  አንጓጠዋቸዋል  ፤   አንቋሸዋቸዋል ‼️
 ነብዩሏህ  ኢብራሂም ዓለይሂ   ሰላም    በእሳትና  ልጅህን  እረድ  በሚል  ትዕዛዝ   ተፈትነዋል  ‼️
          ነብዩሏህ  ያዕቁብ  ዓለይሂ ሰላም ከልጃቸው   ጋር  ተለያይተው  አይናቸው  እስኪጠፋ
ድረስ  አልቅሰዋል  ‼️
       ነብዩሏህ  ሙሳ  ዓለይሂ ሰላም  የፊርዓውንን  ጭቆና በኋላም የህዝቦቻቸውን  አልታዘዝ  ባይነት  ተቋቁመዋል ‼️
       ነብዩሏህ  ዒሳ  ዓለይሂ  ሰላም  ድሃ  ነበሩ  ‼️
       ነብዩ  ሙሐመድ  ሶለሏሁ ዓለይሂ  ወሰላም  ድህነትንና  የህዝቦቻቸውን  አመፅ   በትዕግስት  ተቋቁመዋል  ።    የሚወዷቸውን  አጎታቸውን  ሐምዛን  ረድየሏሁ ዐንሁ ወአርዷህ   በማጣታቸው  እጅግ  አዝነዋል  ። 
              ነብዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰላም   « ይህች  ዓለም  ለሙዕሚኖች  እስር ቤት   ለከሃዲዎች  ጀነት ናት»   ይሉ  ነበር  ።  
    ◉   በእምነታቸው  የታሰሩ  ሙዕሚኖች  ፣ ምሁራኖችና  ሀቀኞች  ስፍር  ቁጥር  የላቸውም  ።
ቆም  ብለህ  አስተንትን!!
      ◎    ዘይድ  ኢብኑ ሳቢት  ረድየሏሁ ዐንሁ የአሏህ  መልዕክተኛ  ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰላም  እንዲህ  ሲሉ ሰምቻለሁ  ብሏል ።   « ዋነኛ  ጭንቀቱ  ይህ ዓለም  የሆነ  ሰው   አሏህ  ጉዳዮቹን  ይበታትንበታል ። ድህነትንም  በአይኖቹ መካከል   ያደርግበታል  ።  ሆኖም  ከተፃፈለት  በስተቀር  ከዚህ  ዓለም  ወደሱ የሚመጣ  ነገር  የለም  ።   መጪውን  ዓለም  ለሚናፍቁ   ሰዎች  አሏህ  ጉዳያቸውን  ይሰበስብላቸዋል (ገር  ያደርግላቸዋል)  ።   በልባቸው  ውስጥ ሀብትን  ይሞላላቸዋል  ። ዱኒያ  ወደነሱ  ትመጣለች  ።   ባይፈልጓትም  እንኳ»  ።
              ◎ ዐብዱሏህ  ኢብን መስዑድ  ረድየሏሁ ዐንሁ  ነብዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰላም   ቀጣዩን    ሲሉ ሰምቻለሁ  ብለዋል  ።
            « ጭንቀቶቹን  ሁሉ  ወደ አንድና  ወደ  መጪው ዓለም  ጭንቀት ያሸጋገረ  ሰው  አሏህ  በዚህ  ዓለም ላይ  ያለውን  ፍላጎቱን  ያሟላለታል  ። ጭንቀቱን   ለዓለማዊ ጉዳዮች ያደረገ  ሰው  ግን  የሱ  ሁኔታ  አሏህን   አያሳስበውም»
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

02 Nov, 03:29


ኢማም ከነ 12 ቤተሰቦቻቸው ጋር ተገደሉ‼️

በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ አካባቢ ታግተው የነበሩት የመስጅድ ኢማም ከነ 12 ቤተሰቦቻቸው መገደላቸው ተሰማ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ገንዳ አረቦ ተብሎ በሚጣራው አካባቢ ከሀጂ አህመድ መስጅድ በታጣቂዎች ታግተው የነበሩት የሀጂ አህመድ መስጅድ ኢማም ሼይኽ ሙሀመድ መኪን ሸይኽ ሙሀመድ አሪፍ አብረዋቸው ታግተው ከነበሩት 12 ቤተሰቦቻቸው ጋር በዛሬው ዕለት መገደላቸው ተሰምቷል።
ሼይኽ ሙሀመድ ከሳምንታት በፊት የሱብኺ ሶላት አሰግደው በሚመለሱበት ወቅት ነበር ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ ከ30 በላይ የሚሆኑ የአካባቢው ሰዎች ታግተው መወሰዳቸው የተገለፀው። ከቀናት በኋላ በተደረገ የገንዘብ ድርድር የኢማሙን እናት እና ባለቤት ጨምሮ ጥቂት ሰዎች መለቀቃቸው ተጠቁሟል።
ኢማሙን ጨምሮ 12 ቤተሰቦቻቸው ግን በዛሬው እለት መገደላቸው ተሰምቷል።

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

01 Nov, 04:18


ከጁመዓ ቀን ሱናዎች
↩️‏ #سنن_يوم_الجمعة
➊ الغسل
➋ الطيب
➌ السواك
➍ لبس الجميل
➎ قراءة سورة الكهف
➏ التبكير لصلاة الجمعة
➐ الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي ﷺ
🔹ገላን መታጠብ
🔹ሽቶ መቀባት
🔹ሲዋክ መጠቀም
🔹ጥሩ ልብስ መልበስ
🔹ሱረቱ ከህፍን መቅራት
🔹በጧት ለጁመዓ ሶላት መጣድ
🔹በነብዩ ﷺ ላይ ዱዓና ሰለዋት  ማብዛት
اللَّهُمَّ اجْعَلْ صَلَوَاتِكَ وَبَرَكَاتِكَ وَرَحْمَتَكَ عَلَى سَيِّدِ المُرْسَلِينَ وَإمَامِ المُتَّقِينَ وَخَاتَمِ النَّبِيِّينَ مُحَمَّدٍ عَبْدِكَ وَرَسُولِكَ إمَامِ الخَيْرِ وَقَائِدِ الخَيْرِ وَرَسُولِ الرَّحْمَةِ ، اللَّهُمَّ ابْعَثْهُ مَقَامًا مَحْمُودًا يَغْبِطُهُ بِهِ الأوَّلُونَ وَالآخِرُونَ ، اللَّهُمَّ تَقَبَّلْ شَفَاعَتَهُ الكُبْرَى وَارْفَعْ دَرَجَتَهُ العُلْيَا وَآتِهِ سُؤْلَهُ فِي الآخِرَةِ وَالأُولَى كَمَا آتَيْتَ إبْرَاهِيمَ وَمُوسَى .. اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إبْرَاهِيمَ إنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إبْرَاهِيمَ إنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ»

https://t.me/+Se4xqUVr3TtG4W9L

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

31 Oct, 18:59


የቁጥር መብዛት አይሸንግልህ
የቁጥር ማነስም አያሳስብህ
ሁሌም ግን በሀቅ ላይ መሆንህ
ይገባል ሊያሳስብህ ሊያስጨንቅህ

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

31 Oct, 16:17


በመረጃ እንጂ በጠመንጃ ማሳመን የለም!
👇
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚየህ ረሂመሁሏህ እንዲህ ይላል: በሰዎች ላይ የሚቃወም አካል በመረጃ እና በደሊል ላይ መሆን ሊታወቅ ግድ ይላል

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

31 Oct, 13:22


ጀግና ስትሆን የሰዎች አሉባልታ ስድብ ጫጫታ ማንቋሸሽ ማብጠልጠል ቦታ አትሰጥም ለአፀያፊ ስድባቸው መልስ አትመልስም በል እንደውም በክብርህ ለተረማመዱት ሁሉ አውፍ ትላለህ ጉዞህን ግን አታቆምም የብዙ ውሾች ድምፅ አይበግርህም ትንኝ ያለፈብህ እንኳ አይመስልህም ትገሰግሳለህ በሁጃና ማስረጃ እንጂ ማንም ምንም የሚገድብህ ሀይል አይኖርም ::

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

31 Oct, 13:17


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ብቻ እንድታውቁልኝ ብዬ ነው

👌በምንም አይነት መልኩ አላህን በብቸኝነት ያላመለከና
የሙታኖች አምልኮ ላይ ያለን ሰው ምላሴ ታዞልኝ ህሌናዬ ፈቅዶልኝ ሙስሊም ልለው አልችልም

👉 ሀቅን ስለምፈልግ የአዚሮችን ማስረጃ በደንብ አይቻለሁ አንድም ማስረጃ ላገኝ አልቻልኩም

👌 የአላህ ኡሉሂያና ሩቡቢያ ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ ወይም ጃሂል ስለሆነ ምናምን የሚያስብል ነገር አይደለም

👆
👉ሰዎች የተፈጠሩለት ትልቁ አላማ የእስልምና ዋናው መሰረት የጀነት መግቢያ ቁልፍ አላህን በብቸኝነት ማምለክ እሱን በአምልኮ መነጠል ነው
ያለዚህ መሰረት አንድ ሰው ሙስሊም ሊሆን አይችልም

👉ይሄ እምነቴ ነው ኢልም ደግሞ አማና ነው የያዝኩትን አማና መደበቅ አይቻልልኝም

👉ስድቦች👇
👉የተክፊር ጅራት
👉መፍቱን ለማትረፍ
👉ሊታወቅ የሚፈልግ ጎረምሳ
👉በተክፊር የተመታ
👉የፊትና ሰው ወ ዘ ተ
ስላላቹኝ ፈርቼ ማቆም መስሏቹህ ከሆነ ተሳስታቹሀል

እንደውም ይሄ ለኔ ብርታት ነው ሰዎች ብዙ ማወቅ ያለባቸው ነገር እንዳለ ማስረጃ ነው

👇👇
👉በነገራችን ላይ በባለፈ ስለ ዘረኝነት ከተናገርኩኝ ጊዜ አንስቶ ቂም የያዙብኝ አሉ ምክንያቱም ዘረኞቹ የነ ማን ጓደኞች ከነማን ጋር እንደሚቀማመጡ ተልእኮ ከነማን እንደሚወስዱ ስለታወቀ ህመማቸው የቱ ጋ እንደሆነ ተረድቻለሁ

አሁንም እየተሳደቡ ያሉት እነሱ ናቸው

ይሄን መስአላ ሽፋን አርገው ሂሳብ ለማወራረድ ነው

🫵 ሁላቹም ምስክሮቼ ናቹህ አንድም ሰው ስሙን ጠርቼ እከሌ ብዬ የፃፍኩበትም ይሁን የተናገርኩበት ሰው የለም

👉 በኔ ተበሳጭተው የሚሳደቡበት ሌላው ምክንያት ትልቁን ሽርክ የሰራ ሰው ሙስሊም አለማለቴ ነው
ይሄ ደሞ በማስረጃ የታጠረ የአኢማዎች የሰለፊዮች እምነት ነው

ግፍ ጥሩ አይደለም
ፍትህ ይኑረን

በማስረጃ ስላመንኩበት ነጥብ ማውራት መብቴ ነው

በመጨረሻም👇
የምጠላውና ቂም የያዝኩበት
አንድም ዳዒ ይቅርና ተራ ሰለፊ እንኳን የለም ለሰደባቹኝ ሁሉ አፍው ብያለሁ

🤲 በሀቅ አኖሮን በጀነት ይሰብስበን


https://t.me/abduselamabumeryem/5297

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

30 Oct, 17:37


ከየትኛው ቀዳዳ ገብቶ ነው ሙስሊም የሆነው

https://t.me/abduselamabumeryem/5286
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

30 Oct, 17:37


👉 ጥያቄ ለአዚሮች

ሽርክ ላይ የወደቁ ሰዎች
የ لا إله إلا الله ትርጉም አውቀውት ነው ወይስ ሳያውቁት ቀርተው ነው

ትርጉሙን ካወቁ በኋላ ከሆነ ሽርክ የሚሰሩት በራሳቸው ላይ ሁጃ አቁመዋል ማለት ነው

ትርጉሙን ሳያውቁት ቀርተው ከሆነ ሽርክ የሰሩት ይህ ሲጀመር ሙስሊም ላለመሆናቸው ማስረጃ ነው ምክንያቱም ሙስሊም ለመሆን
የ لا إله إلاالله ትርጉም አውቆ አላህን በብቸኝነት ማምለክ መስፈርት ነው

በቁርአንና በሱና በሙስሊሞችም ኢጅማዕ ሙስሊም ለመሆን
የ لا إله إلا الله ትርጉም ማወቅን መስፈርት ተርጎ እያለ

አዚሮች ግን የ لا إله إلا الله ትርጉም አለማወቅን ሙስሊም ለመሆን መስፈርት እያደረጉት ነው

እንዴት ከተባለ
ባለማወቁ ሽርክ የሰራ ሙሽሪክ ሙስሊም ነው ሲሉ ሙስሊም ነው ያሉበት ምክንያት አለማወቁ እኮ ነው

{ فَمَن یَكۡفُرۡ بِٱلطَّـٰغُوتِ وَیُؤۡمِنۢ بِٱللَّهِ } [سُورَةُ البَقَرَةِ: ٢٥٦]


https://t.me/abduselamabumeryem/5289
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

28 Oct, 22:30


◉እነዚህን ጥያቄዎች አስተውለክ ታውቃለህ? 👇

    ◉ ﻟﻤﺎﺫﺍ ﺍﻟﻤُﺴﻠﻤﻴﻦ ﻣُﺴﺘﻀﻌﻔﻴﻦ ؟

◉ ሙስሊሞች ለምን ደካማ ሆኑ?

◉ ﻓﻲ ﻛﻞ ﺍﻟﺪُﻭﻝ ﻭﻣﺨﺬﻭﻟﻴﻦ ؟

◉በሁሉም ሀገር ላይ የተዋረዱት?

◉ ﻭﻣُﺸـﺮﺩﻳـﻦ ﻭﻣُﺸﺘﺘﻴـﻦ ؟

◉ የሚባረሩት የሚሰደዱት?

◉ ﻭﻳﻘﺘـﻠـﻮﻥ ﻭﻳﻐﺘﺼﺒـﻮﻥ ؟

◉ የሚገደሉት የሚዘረፉት?

⭕️ﺇﻗــﺮﺃ ﺍﻟـﺠﻮﺍﺏ

⭕️ ለመልሱ ⇩ አንብብ

◉ﻗﺎﻝ ﺷﻴﺦ ﺍﻹﺳﻼم ﺍﺑﻦ ﺗﻴﻤﻴﺔ  ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ ﻭﻏﻔـﺮ ﻟﻪ ورفع درجته في المهديين -:

⚠️ ﻭﺇﺫﺍ ﻛﺎﻥ ﻓﻲ ﺍﻟﻤﺴﻠﻤﻴﻦ ﺿﻌﻒ
⚠️ ﻭﻛﺎﻥ ﻋﺪﻭﻫﻢ ﻣﺴﺘﻈﻬﺮًﺍ ﻋﻠﻴﻬﻢ
⚠️ ﻭﻳﺬﺑﺤـﻮﻥ ﻭﻳﺸﻨﻘــﻮﻥ؟

⬅️ ﻛﺎﻥ ﺫﻟﻚ ﺑﺴﺒﺐ ﺫﻧﻮﺑﻬﻢ ﻭﺧﻄﺎﻳﺎﻫﻢ

▪️ﺇﻣﺎ ﻟﺘﻔﺮﻳﻄﻬﻢ ﻓﻲ ﺃﺩﺍﺀ ﺍﻟﻮﺍﺟﺒﺎﺕ ﺑﺎﻃﻨًﺎ ﻭﻇﺎﻫﺮًﺍ
▪️ﻭﺇﻣﺎ ﻟﻌﺪﻭﺍﻧﻬﻢ ﺑﺘﻌﺪﻱ ﺍﻟﺤﺪﻭﺩ ﺑﺎﻃﻨًﺎ ﻭﻇﺎﻫﺮًﺍ

⭕️ ሙስሊሞች ደካማ ከሆኑ

⭕️ ጠላታቸው ከበላያቸው ከሆነ

⭕️ የሚያንቃቸውና የሚገድላቸው ከሆነ ይህ የሆነው

➡️ በወንጀሎቻቸውና በስህተታቸው ምክኒያት ነው‼️

⭕️ወይ አሏህ ዋጂብ ያደረጋቸውን ነገራቶች በውስጥም በውጭም በማጓደላቸው ነው።

◉ ወይም የአሏህን ድንበሮች [ወሰኖች] በውስጥም በውጭም በመሻገራቸው ነው።
(ﻣﺠﻤﻮﻉ ﺍﻟﻔﺘﺎﻭﻯ)

👇👇


https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

28 Oct, 04:37


◉النّفْسُ ميّالةٌ للكسَلِ إلّا مَن غَلَبَها

◉ ነፍስ ለስንፍና የተጋለጠች ናት። ያሸነፋት ሲቀር!!


https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

28 Oct, 04:36


‏لا يجب أن تقول كل ما تعرف ..ولكن يجب أن تعرف كل ما تقول .

የምታውቀውን ሁሉ መናገር አይጠበቅብህም፣ ነገር ግን የምትናገረውን ሁሉ ማወቅ ይጠበቅብሃል።

  
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

27 Oct, 18:11


​​ || ▂▂▂▂▂ (✏️)


👉 ከልብ የሆነ ምክር ለእኔም ለእናንተም.tt


የግሩፕህ ሰው ብዛት ማነስ ወይም የምትፖስታቸው አስተማሪ ፅሁፎችም
ሆነ ሌላም የሚያሰራጭልህ ሰው
ማነሱ ወይም በፖሰቶችህ የሚገረምብህና በሀሳብ ሚደግፍህ ሰው ማነሱ

👉አላህ ይህን መልካም ስራህን
አልተቀበለህም ማለት አይደለም
👉 ሰዎችም ከፖስትከው አልተጠቀሙም
ማለትም አይደም


እንግዲያውስ ይህ መልካም
ስራህን ላይክና ሼር ኮሜንት
በሚሰጡህ ሰዎች
ላይ አታንጠልጥለው

ሁሌም ቢሆን በምትፅፋት እያንዳንዷ
ቃላት ላይ ከአላህ አጅርህን ተሳሰብ
ንያህንም ዘወትር አክማት

ከአንተ ጋር አብሮህ ያለ ሰው ማነሱ ብቻህ እንኳን ብትሆን በጭራሽ እንዳይጎዳህ አላህ እውነትን ሁሌም ይረዳዋል።‼️

وباالله التوفيق

|| ▂▂▂▂▂ (✏️)

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

27 Oct, 17:05


ሀገራችንና ፈረንሳይ ለኢስላማዊ አለባበስ ያላቸውን ጥላቻ ያመሳስላቸዋል።እህቶቻችን ኒቃብ በመልበሳቸው የሚደነግጡበት የሚፈሩበት ሀገር እየሆነ ነው።

የኒቃብ ጥላቻ ነው እንጂ የኒቃቡ መብት ለማክበር እና ለማስከበር መፍትሔ ጠፍቶ አይደለም።

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

23 Oct, 04:50


فليست هذه الدنيا بشيء ... تسوئك حقبة وتسر وقتا
وغايتها إذا فكرت فيها ... كفيئك أو كحلمك إذ حلمتا
سجنت بها وأنت لها محب... فكيف تحب ما فيه سجنتا
      ምንም አየደለችም የዱንያዋ ህይወት
        ዘመን አስደስታህ ታዝናለህ ሌላ ወቅት

       ድካዋ'ኮ የሧ ስታስተነትናት
      ወይ እንዳንተ  ጥላ ወይ እንደ ህልምህ ናት

      ታሥረሃል በውስጧ የሷ ወዳጅ ሆነህ
      !?የታሰርክበትን እንዴት ትወዳለህ

ከታኢየቱል ኢልቢሪ የተወሰደ
ግርድፍ

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

23 Oct, 03:55


ስማ…

አንተም ፈተና ደረሰብኝ ትላለህ?

ከቀልቡ ውጭ አንድም ጤነኛ ሰውነት አልቀረውም። መላ ሰውነቱ ታመመ። ከሚስቱ ውጭ የቅርብም የሩቅም ሰው ራቀው። ጭራሽ ከአካባቢው ይወገድ እስከማለት ድረስ አገለሉት። ለ18 አመታት ያክል በህመም ተሰቃየ።

ይህ ብቻ ትላለህ… በህዝቦቹ ዘንድ በጣም ሃብታም ነበር። በርካታ ማሳና አዝዕርት ነበረው። ግን በቅፅበት እንዳልነበር ሆነና ወደመበት።

በርካታ ልጆች ነበሩት። ሁሉንም በድንገተኛ አደጋ አጣቸው።


ግን…

ታገሰ። ወደ አላህም ስሞታውን አሰማ። አላህም የታጋሾችን ምንዳ መላሽ ነውና ከበፊቱ የበለጠ ሃብትና ልጆች ሰጠው። ሐታ 26 ወንድ ልጆችን ወለደ ይባላል። ጤናውም ተመለሰለት።

أيوب عليه السلام

አላህ ምን እንዳለ ተመልከት፦


(وَاذْكُرْ عَبْدَنَا أَيُّوبَ إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُ أَنِّي مَسَّنِيَ الشَّيْطَانُ بِنُصْبٍ وَعَذَابٍ

ባሪያችንን አዩብንም አውሳላቸው፡፡ «እኔ ሰይጣን በጉዳትና በስቃይ ነካኝ» ሲል ጌታውን በተጣራ ጊዜ፡፡


ارْكُضْ بِرِجْلِكَ ۖ هَٰذَا مُغْتَسَلٌ بَارِدٌ وَشَرَابٌ

«በእግርህ (ምድርን) ምታ፡፡ ይህ ቀዝቃዛ መታጠቢያ መጠጥም ነው» (ተባለ)፡፡


وَوَهَبْنَا لَهُ أَهْلَهُ وَمِثْلَهُم مَّعَهُمْ رَحْمَةً مِّنَّا وَذِكْرَىٰ لِأُولِي الْأَلْبَابِ

ለእርሱም ከእኛ ዘንድ ለችሮታ ባለአእምሮዎችንም ለመገሠጽ ቤተሰቦቹን ከእነርሱም ጋር መሰላቸውን ሰጠነው፡፡


وَخُذْ بِيَدِكَ ضِغْثًا فَاضْرِب بِّهِ وَلَا تَحْنَثْ ۗ إِنَّا وَجَدْنَاهُ صَابِرًا ۚ نِّعْمَ الْعَبْدُ ۖ إِنَّهُ أَوَّابٌ

«በእጅህም ጭብጥ አርጩሜን ያዝ፡፡ በእርሱም (ሚስትህን) ምታ፡፡ ማላህንም አታፍርስ» (አልነው)፡፡ እኛ ታጋሸ ኾኖ አገኘነው፡፡ ምን ያምር ባሪያ እርሱ በጣም መላሳ ነው፡፡)

[ሷድ: 41–44]


ሰማህ ሰማህ…?

«ታጋሸ ኾኖ አገኘነው፡፡ ምን ያምር ባሪያ»

አላሁ አክበር

በል ታገስ ሐቢቢ! በአላህ ተመካ። ከምታገኘው ጸጋ አንፃር «እንኳንም ያ ፈተና ደረሰብኝ!» እስክትል ድረስ የበለጠ ይክስሃል።

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

23 Oct, 03:46


ዱንያ ላይ ዘውታሪ ነገር የለም   ሁሉም ነገር ጠፊ ነው
كُلُّ مَنْ عَلَيْهَا فَانٍ

በእርሷ (በምድር) ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው፡፡
አላህ በራሳቹ በቤተሰቦቻቹ በጤናቹ ላይ የመጣ ሙስባ መመለሻ ያርግላቹ በተሻለው ይተካላቹ ያረብ🤲

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

22 Oct, 18:25


ይነበብ !
※※※※※※※※※
ከደረሰብን ጉዳት በላይ የሚያሳምመን ለጉዳቱ የሰጠነው ትርጉም ነው ። አብራራዋለሁ !
መንገድ እየሄድክ አንዱ ከኋላህ አናትህን መታ ቢያደርግህ በንዴት ገንፍለህ ለመጣላት ትዞራለህ ። ስትዞር ግን ጎደኛህን አገኘኸው… ተጨማዶ የነበረው ፊትህ ይፈታል ። ለቦክስ የጨበጥከው መዳፍህም ለሰላምታ ይዘረጋል ። ይህ የሆነው ምንም የተለየ ነገር ስለተፈጠረ ሳይሆን አንተ ለድርጊቱ የሰጠኸው ትርጉም ስለተለየ ብቻ ነው ።

ትላንት እና ዛሬ የተወሰኑ ጉዳዮች ቢዚ አድርገውኝ ቀኑን ሙሉ ስራብ ቆይቼ ከመሸ ነው ምግብ የቀመስኩት ። እንዲህ መሆኑን ተከትሎም ከረሀብ ስሜት በዘለለ feel ያደረግኩት ተጨማሪ አንድም ስሜት አልነበረም ። ነገር ግን ሁለቱንም ዕለት ቀኑን ሙሉ የተራብኩት መመገብ የሚከለክል በሽታ ይዞኝ ቢሆን አልያም የሚቀመስ የምሸምትበት ገንዘብ ሳይኖረኝ ቀርቶ ቢሆን እድሜ ልኬን ውስጤን የሚያሳዝነኝ እና የሚሰብረኝ ክስተት ሆኖ ነበር የሚያልፈው ። ነገር ግን ጉዳዮቼን ለማሳካት በፈቃዴ ስሯሯጥ በመሆኑ አንዳችም ረባሽ ስሜት ሳይፈጠርብኝ አልፏል ።

ከዐመታት በፊት ከስራ ጋር በተገናኘ የሆኑ ገጠመኞች ኪሴን አመናመኑት ድንገት እንዳልጠበቅኩት ሆኖ ሁሉ ነገር ተሟጠጠ ። ለቅርብ ቅርብ መንገዶች ሳይቀር ታክሲ መጠቀምን እርም ብዬ የራይድ ቋሚ ደንበኛ የነበርኩ ሰውዬ ነገር ተገልብጦ የታክሲ መቸገር ጀመርኩ ። የሆነ ዕለትም ከገባሁበት አጣብቂኝ ለመውጣት አማራጭ ፍለጋ ሰዎችን በስራ ጉዳይ ላወራ ቀጠሮ ይዤ ያሉበት ድረስ ስጓዝ በመሃል ከኪሴ ያለችው ብር ተሟጠጠች ። ምንም እንኳ የለበስኩት ጫማ ለጉዞ ባይመችም ምርጫ ስላልነበረኝ ቀሪውን መንገድ በእግሬ ተያያዝኩት ። የተቀጣጠርኳቸው ሰዎችም ስላረፈድኩባቸው አንድ ቦታ ተቀምጠው መጠበቅ ተሰላችተው ከቦታ ቦታ እየቀያየሩ ስለነበር ያሉበትን ትክክለኛ ቦታ ለማወቅ ደጋግመን መደዋወል ነበረብን ። ስልኬ ላይ የነበረችውም ሳንቲም ከሰዎቹ ጋር ደጋግሜ በመደዋወሌ ልታልቅ ትንሽ ቀራት…. ይህንን ስሜት በህይወት እስካለሁ መቼም የምረሳው አይደለም ።

የሚደንቀው ከዚህ ክስተት በፊት ነገር ሁሉ በአማን ሳለ በገዛ ፈቃዴ ሲሜን በሶፍት ጠቅልዬ አስቀምጬ ስልክ ለ8 ወራት በቃኝ ብዬ ነበር ። የዚያኔም መደወል የፈለግኩ ጊዜ በቅርብ ያገኘኋቸውን ሰዎች አስቸግር ነበር ። እንደዚያ በማድረጌም ምንም አይሰማኝም ነበር። በተመሳሳይ በፈቃዴ ለመዝናናትረጃጅም መንገዶችንም በእግር እጓዝ ነበር ። ታዲያ ነገሮች ጠበው ገንዘብ ያልነበረኝ ጊዜ በእግር መሄዴም ሆነ ስልኬ ባላንስ በማጣቱ እንዲያ አዝኜ በፈቃዴ ስልኬን የተውኩም ሆነ የእግር ጉዞ ያደረግኩ ጊዜ ለምን አላዘንኩም ? መልሱ ቀላል ነው ። ለክስተቶቹ የሰጠሁት ትርጉም እንጂ በሁለቱም ወቅት የተፈጠረው ተመሳሳይ ነበር ። ሁለቱም ጊዜ በእግር ተጉዣለሁ ስልክም መደወል አልችልም ነበር ።

አንድ ሰው ከሁለት ዐመት በኋላ በብዙ የሚቆጠሩ ሚሊየኖች ይኖርሃል እስከዚያ ግን እጅግ በጣም ትቸገራለህ ቢባል ምንም ሳይመስለው ድህነቱን እና ማጣቱንም ሳያፍርበት ሁለቱን አመት ቀለል አድርጎ ያልፋቸዋል ። ነገ ሁሉም ይቀየራል የሚለው ጠንካራ ተስፋ የዛሬን መራራ ያስረሳዋል ። ለዚህም ነው “ ከችግሩ በላይ የሚያሳምመን ለችግሩ የምንሰጠው ትርጉም ነው “ የሚባለው ።

አላህን የሚያምን ከዛሬም ነገ የተሻለ እንደሚሆን እርግጠኛ የሚሆን በዛሬ ክስተት ልቡ ድቅቅ እስኪል አይሰበርም ። ሀዘኑም ቅጥ አያጣም ። ብዙም አይደነግጥም !

( የነገራቶች ) መጨረሻይቱም ከመጀመሪያይቱ ይልቅ ላንተ በላጭ ናት ፡፡
[ ሱረቱ አድ ዱሓ 4 ]

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

21 Oct, 18:54


ምስክርነት ከራሳቸው አፍ⁉️ይህ ክርስቲያን የነበረ ሰው መሰረታዊ በክርስትና ውስጥ ያሉ አወዛጋቢ የሆኑ ርእሶችን አንስቶ ያወጋናል።

አዳምጡትና ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር በአኽላቅ ተወያዩባቸው።

ማንኛውም ሰው 100% ማሰብ ከቻለ ሙስሊም ይሆናል።

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

21 Oct, 18:50


√ የታላቁ ሶሐባ የአቡበክር ልጅ ዐብደ-ል'ሏህ አገባት፤ ሸሂድ ሆነ።

√ ከዚያም ዘይድ ኢብኑ-ል-ኸ-ጥ'ጧብ አገባት፤ ሸሂድ ሆነ።

√ ከዚያም ሁለተኛው ኸሊፋህ ዑመር ኢብኑ-ል-ኸ-ጥ'ጧብ አገቧት፤ ሸሂድ ሆኑ።

√ ከዚያም ዙበይር ኢብኑ-ል-ዐዋም አገባት፤ ሸሂድ ሆነ።

√ ከዚያም የ4ኛው ኸሊፋ የዐልይ ልጅ የሆነው ሑሴን አገባት፤ ሸሂድ ሆነ።

የመዲና ሰዎች «ሸሂድ መሆን የፈለገ እርሷን ያግባት!» እስከማለት ደረሱ።

ይህቺ ብርቅዬ፣ ሐያእ ያላትና እጅግ በጣም ቆንጆ ሴት ማን ናት?

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

21 Oct, 04:40


አስደሳች ዜና 👇👇

♻️ እንደ ሚታወቀው ጉራጌ ዞን ጌቶ ወረዳ የሰለፊዮች መስጂድ መስጂድ አል-ሱና (ጉቶ )በአንድ አንድ ግጭት ምክንኛት ተዘግቶ እንደ ነበረ ይታወቃል.....
.
.
.
👉 እነሆ በዛሬው እለት እለተ እሁድ !10-2-2017 )መከፈቱን ሰምታናል አልሃምዱ ሊላህ በጣም ደስ ብሎናል አላህ መጨረሻው ያማረ ያድርገው ....

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

20 Oct, 05:01


ዶክተር  አቡ  በክር  የሚባለው  ሙሽሪክ  አቡጀህል   ወሐብዮች  ካፊሮች  ናቸው  ተከትሎ  መስገድ  አይቻልም  አለ...። 

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

16 Oct, 16:33


⭕️በመንሀጀ ሰለፍ ላይ መፅናት እና ለፅናት የሚያግዙን ነገሮች‼️

በአላህ ስም እጅግ ሩህሩህ እና ፍፁም አዛኝ በሆነው።

#ፅናት" ማለት በሀቅ ላይ ቀጥ መለት ነው‼️

#መንሀጅ" ማለት ሙስሊም የሆነ ሰው የሚጓዝበት መንገድ ነው‼️

እሱም ቀጥተኛው መንገድ ነው።
ﻗﺎﻝ ﺗﺒﺎﺭﻙ ﻭﺗﻌﺎﻟﻰ :  ﻗُﻞْ ﻫَﺬِﻩِ ﺳَﺒِﻴﻠِﻲ ﺃَﺩْﻋُﻮ ﺇِﻟَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻋَﻠَﻰ ﺑَﺼِﻴﺮَﺓٍ ﺃَﻧَﺎ ﻭَﻣَﻦِ ﺍﺗَّﺒَﻌَﻨِﻲ ﻭَﺳُﺒْﺤَﺎﻥَ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻭَﻣَﺎ ﺃَﻧَﺎ ﻣِﻦَ ﺍﻟْﻤُﺸْﺮِﻛِﻴﻦَ  ( ﻳﻮﺳﻒ  )
አላህ እንዲህ ይላል
◉ይህቺ መንገዴ ናት። ወደአላህ እጣራለሁ እኔም የተከተለኝም ሰው በግልፅ ማስረጃ ላይ ነን። ጥራት ለአላህ ይገባው። እኔም ከአጋሪዎች አይደለሁም" በል። ዩሱፍ 108)

⭕️ በሀቅ ላይ እስከለተ ሞታችን ድረስ መፅናት በጣም አሳሳቢ ነው የመጨረሻችን ነገር ሊያሳስበን ሊያስጨንቀን ይገባል ለዚህም ሶላት በሰገድን ቁጥር "ቀጥተኛውን መንገድ ምራን" በማለት በቀጥተኛው መንገድላይ ፅናት እንዲሰጠን መማፀን ተደንግጓልናል
◉ﻗﺎﻝ ﺍﺑﻦ ﺗﻴﻤﻴﺔ ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ :  ﻭﻟﻬﺬﺍ ﻛﺎﻥ ﺃﻧﻔﻊ ﺍﻟﺪﻋﺎﺀ، ﻭﺃﻋﻈﻤﻪ ﻭﺃﺣﻜﻤﻪ ﺩﻋﺎﺀ ﺍﻟﻔﺎﺗﺤﺔ :  ﺍﻫﺪِﻧَﺎ ﺍﻟﺼِّﺮَﺍﻁَ ﺍﻟﻤُﺴﺘَﻘِﻴﻢَ ﺻِﺮَﺍﻁَ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺃَﻧﻌَﻤﺖَ ﻋَﻠَﻴﻬِﻢْ ﻏَﻴﺮِ ﺍﻟﻤَﻐﻀُﻮﺏِ ﻋَﻠَﻴﻬِﻢْ ﻭَﻻَ ﺍﻟﻀَّﺎﻟِّﻴﻦَ
} [ ﺍﻟﻔﺎﺗﺤﺔ 6:  7 ]  ﻓﺈﻧﻪ ﺇﺫﺍ ﻫﺪﺍﻩ ﻫﺬﺍ ﺍﻟﺼﺮﺍﻁ ﺃﻋﺎﻧﻪ ﻋﻠﻰ ﻃﺎﻋﺘﻪ ﻭﺗﺮﻙ ﻣﻌﺼﻴﺘﻪ، ﻓﻠﻢ ﻳﺼﺒﻪ ﺷﺮ  ﻻ ﻓﻲ ﺍﻟﺪﻧﻴﺎ ﻭﻻ ﻓﻲ ﺍﻵﺧﺮﺓ
◉ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይምያ አላህ ይዘንለዎት እና እንዲህ ይላሉ
➴ለዚህም ሲባል ጠቃሚ እና ጥቅል እንዲሁም ትልቅ ዱአ የፋቲሀ ዱአ ነው 'ቀጥተኛውን መንገድ ምራን የእነዚያን በነሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውን እና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ' (ምራን በሉ)። (ፋቲሀ )

◉እሱ (አላህ ባሪያን) እሄን መንገድ ከመራው እሱን በመታዘዝ እና እሱን ማመፅን በመተው ላይ አገዘው በዱኒያም ይሁን በአኼራ ሸር(ተንኮል) አያገኘውም" መጅሙኡል ፈታዋ 14/320—321

⭕️በዲን ላይ መፅናት የነብዮች ኑዛዜ ነው‼️
ﻗﺎﻝ ﺗﻌﺎﻟﻰ :  ﻭَﻭَﺻَّﻰ ﺑِﻬَﺎ ﺇِﺑْﺮَﺍﻫِﻴﻢُ ﺑَﻨِﻴﻪِ ﻭَﻳَﻌْﻘُﻮﺏُ ﻳَﺎ ﺑَﻨِﻲَّ ﺇِﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﺍﺻْﻄَﻔَﻰ ﻟَﻜُﻢُ ﺍﻟﺪِّﻳﻦَ ﻓَﻼ ﺗَﻤُﻮﺗُﻦَّ ﺇِﻟَّﺎ ﻭَﺃَﻧْﺘُﻢْ ﻣُﺴْﻠِﻤُﻮﻥَ              ( ﺍﻟﺒﻘﺮﺓ 132: )
◉በርሷ (በህግጋቲቱ) እብራሂም ልጆቹን አዘዘ የእቁብም (እንደዚሁ ልጆቹን አዘዘ) ልጆቸ ሆይ! አላህ ለናንተ ሀይማኖትመረጠ ስለዚህ እናንተ ሙስሊሞች ሁናችሁ እንጅ አትሙቱ" አላቸው

⭕️በሀቅ ላይ ለመፅናት የሚረዱን ነገሮች‼️

❶  ኢማንን ማረጋገጥ
❷ መልካም ስራ
❸ በእውነት ላይ አደራ መባባል
❹ በትእግስት ላይ አደራ መባባል

◎ለነዚህ ሁሉ መረጃው የአላህ ቃል ነው።
{ ﻭَﺍﻟْﻌَﺼْﺮِ . ﺇِﻥَّ ﺍﻟْﺄِﻧْﺴَﺎﻥَ ﻟَﻔِﻲ ﺧُﺴْﺮٍ . ﺇِﻟَّﺎ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍ ﻭَﻋَﻤِﻠُﻮﺍ ﺍﻟﺼَّﺎﻟِﺤَﺎﺕِ ﻭَﺗَﻮَﺍﺻَﻮْﺍ ﺑِﺎﻟْﺤَﻖِّ ﻭَﺗَﻮَﺍﺻَﻮْﺍ ﺑِﺎﻟﺼَّﺒْﺮِ
◎በግዚያት እምላለሁ። ሰው ሁሉ በእርግጥ በከሳራ ውስጥ ነው። እነዚያ ያመኑት እና መልካሞችን የሰሩት፣በመታገስም አደራ የተባባሉት ሲቀሩ።

አሁንም በዚህ ላይ የአላህ ቃል መረጃ ነው።

◎አላህ እነዚያን ያመኑትን በቅርቢቱም ሕይወት በመጨረሻይቱም (በመቃብር) በተረጋገጠው ቃል ላይ ያረጋቸዋል ከሀዴዎችንም አላህ ያሳስታቸዋል አላህም የሚሻውን ይሰራል።
[ኢብራሂም]

አሁንም በዚህላይ የአላህ ቃል መረጃ ይሆናል
: { ﻭَﺍﺳْﺘَﻌِﻴﻨُﻮﺍ ﺑِﺎﻟﺼَّﺒْﺮِ ﻭَﺍﻟﺼَّﻼﺓِ ﻭَﺇِﻧَّﻬَﺎ ﻟَﻜَﺒِﻴﺮَﺓٌ ﺇِﻟَّﺎ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟْﺨَﺎﺷِﻌِﻴﻦَ } ( ﺍﻟﺒﻘﺮﺓ 45
◎በመታገስ እና በሶላት ተረዱ እሩሷም (ሶላት) በፈሪይዎች ላይ እንጅ በሌላው ላይ በእርግጥ ከባድ ናት።"

◉እውነተኛ በሆነ መንሀጅ ላይ መፅናት የአህሉሱናዎች ባህሪ ነው‼️

◉ በዲን ላይ መገለባበጥ እና ሀቅ በሆነ መንሀጅ ላይ አለመፅናት የአህሉል ቢደእ ባህሪ ነው ‼️

ﻗﺎﻝ ﺍﺑﻦ ﺗﻴﻤﻴﺔ ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ :  ﺇﻧﻚ ﺗﺠﺪ ﺃﻫﻞ ﺍﻟﻜﻼﻡ ﺃﻛﺜﺮ ﺍﻟﻨﺎﺱ ﺍﻧﺘﻘﺎﻻً ﻣﻦ ﻗﻮﻝ ﺇﻟﻰ ﻗﻮﻝ، ﻭﺟﺰﻣًﺎ ﺑﺎﻟﻘﻮﻝ ﻓﻲ ﻣﻮﺿﻊ، ﻭﺟﺰﻣًﺎ ﺑﻨﻘﻴﻀﻪ ﻭﺗﻜﻔﻴﺮ ﻗﺎﺋﻠﻪ ﻓﻲ ﻣﻮﺿﻊ ﺁﺧﺮ، ﻭﻫﺬﺍ ﺩﻟﻴﻞ ﻋﺪﻡ ﺍﻟﻴﻘﻴﻦ

◉ለዚህም ሲባል ሸይኹል ኢስላም እንዲህ ይላሉ:-
"አንተ የፍልስፍና ባልተቤቶችን ከአንድ ንግግር ወደ አንድ ንግግር ባንድ ቦታ በንግግር መቁረጥን በሌላቦታ ደግሞ ያን ንግግራቸውን በማፍረስ እንዲሁም (ይባስ ብለው) የዚያን የንግግር ባልተቤት በሌላ ቦታ በማክፈር ታገኛቸዋለህ ይህ ደግሞ (በያዙት አቋም ላይ) እርግጠኝነት እንደሌላቸው መረጃ ነው" መጅሙኡል ፈታዋ 4/ 50

ከቢዳአ ሰዎች አንዱ በአንድ መንገድ ላይ ያነጋል በሌላ መንገድ ላይ ያመሻል ከልቦና እና ከአስተያየት ጋር ከመገለበበጥ አይወገድም በአንድ ነገር ላይ አይፀናም ምክኒያቱም እሱ ዘንድ (የሚፀናበት) እርግጠኛ የሆነ ነገር የለም
አህሉሱናዎች ጋር (የሚፀኑበት) ቁራአን እና ሀዲስ አለ እነሱም መልእክተኛው ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም የመጡባቸው እውነታዎች ናቸዉ
◎ሁዘይፋ ረዲየላሁ አንሁ እንዲህ ይላል:-
◉ እውነተኛ ጥመት ብሎ ማለት መጥፎ የምትለውን ነገር ጥሩ አድርገህ ልትመለከት ነው ወይንም ጥሩ የምትለውን መጥፎ አድርገህ ልትመለከት ነው በዲን ላይ መገለባበጥን አደራህን የአላህ ዲን አንድ ነው" [አብረዛቅ ፊል ሙሰነፍ (11/249) አላለካእይ (120)]

(ሰለፎች) በዲን ላይ መገለባበጥን ይጠሉ ነበር" [አል-ኢባነቱል ኩብራ(574)]
ኢማሙ ማሊክ እንዲህ ይላአሉ!

◉መድሀኒት የለለው በሽታ በዲን ላይ መከረባበት ነው [አልኢባነቱል ኩብራ (576)]
አሁንም በሀቅላይ ለመፅናት ከሚያግዙን ነገሮች ክርክርን እና በዲን ላይ ጭቅጭቅን መተው
ﻭﻟﻬﺬﺍ يقول  ﻋﻤﺮ ﺑﻦ ﻋﺒﺪ ﺍﻟﻌﺰﻳﺰ:- ﻣﻦ ﺟﻌﻞ ﺩﻳﻨﻪ ﻏﺮﺿًﺎ ﻟﻠﺨﺼﻮﻣﺎﺕ ﺃﻛﺜﺮ ﺍﻟﺘﻨﻘﻞ
ለዚህም ሲል ኡመር ኢብኑ አብዱልአዚዝ እንዲህ ይላል
◉ዲኑን ክርክር ያደረገ መገለባበጥ ያበዛል!! መጅሙኡል ፈታዋ

ሌላው ለሰባት ከሚረዳ ነገር ቂራአት መቅራት ቂራአት የቀራ ሰው እና ጃሂል መቸም ቢሆን ሊነፃፀር አይችልም በተለይ በዚህ ሹበሀ በበዛበት ዘመን ከምን በላይ ቂራአት አስፈላጊ ነው እውቀት ከሌለን ጯሂን ሁሉ እነከተላለን ሰዎች ሂዱ ሲሉን እነሄዳለን ተቀመጡ ሲሉንም እንቀመጣለን እንደው ባጭሩ ኢልም ከሌለን የጯሂ ሁሉ ተከታይ ነው የምንሆነው በቃ ድምፁን ከፍ አድርጎ የጮህ ሁሉ ሀቅ ላይ ያለ ነው የሚመስለን

በመቀጠል አላህ በሀቅ ላይ እንዲያፀናን ዘውትር ዱአ ማድረግ አለብን

ኡሙ ሰለማ እንዳስተላለፈችው የነብዩ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ብዙዱአ "አንተ ልቦችን የምታገለባብጥ (ጌታ ሆይ) ልቤን በአንተ ሀይ ማኖት ላይ አፅናልኝ" ነበር ትላለች (ትርሚዝይ ዘግበውታል)

እኛም እነዚህን እና መሰል ዱአዎች ሰባት እንዲሰጠን ማብዛት አለብን

አላህ በመንሀጀ ሰለፍ ላይ ፀንተው መጨረሻቸው አምሮላቸው ከሚሞቱት ያድርገን🤲

  
@Abu_babelheyr_bin_Sadik

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

15 Oct, 01:51


እጅግ አስደናቂ ታሪክ!
"ይህ ክስተት ከችሎት ቤት ወጥቶ የግብረ ገብ ኪታብ ውስጥ መፃፍ አለበት!"
አቡ ዐብደላህ ሙሐመድ ኢብኑ አሕመድ ኢብኑ ሙሳ አል– ቃዲ "- በአር-ረይ - ከተማ በሁለት መቶ ሰማንያ ስድስት አ/ሂ ምክር ቤት ተገኘሁ።" ይላሉ። የሰሙት እና ያዩት አሰደናቂ ክስተት እንዲህ ሲሉ ያጫውቱናል።

"አንዲት ሴት ፍርድ ቤት ለክስ ቀረበች፣ ቅርብ ሀላፊዋ (ወሊዯ) ባሏ ላይ አምስት መቶ ዲናር መህር እዳ እንዳለበት ክስ መሰረተ፣ ባልየው ግን የተባለው ብር እዳ የለብኝም በማለት ክሱን አልተቀበለም።

ዳኛውም፦ “ምስክሮችህ የት አሉ?” ሲል ጥያቄ አቀረበ።
ባልም፦ “ሁሉም እዚህ ተገኝተዋል” በማለት መለሰ።
ዳኛውም፦ ከምስክሮች መካከል አንዱን ጠርቶ፤ " "ሴትየዋ እሷ መሆኗን እንዲመለከትና ምስክርነቱ እንዲሰጥ አዘዘ።
ምስክሩም ተነስቶ፣ ሴቲቱን፦ “ተነሺ” አላት።

ባልየውም(በቅናት መንፈስ)፦ "ምን እየሰራህ ነው?" ምን ልታደርጋት ነው?! ሲል ጥያቄ አቀረበ።

የሴቲቱ ወኪል፡- "ሚስትህን በትክክል ለይቶ ያውቃት ዘንድ ኒቃቧን ከፍታ ሊመለከታት ነዋ።"

ባልየውም ለዳኛዋ ፦ " ፊቷን በፍፁም እንዳትገልጥለት! የምትለውን ጥሎሽ የማግኘት መብት እንዳላት ለዳኛው እመሰክራለሁ!" አለ።

ሴቲቷም ክሷን ወዲያውኑ ሰርዛ፡- "ጥሎሽን አውፍ ብየዋለሁ! በዱንያም ሆነ በአኼራ ነፃ እንዳደረግኩት ለዳኛው እመሰክራለሁ!" አለች።

ዳኛውም፡- "ይህ ክስተት ከችሎት ቤት ወጥቶ በመልካም ሥነ ምግባር ኪታብ ውስጥ ይስፈር!" ብሎ ትእዛዝ አስተላለፈ።

📚ኸጢብ አልበግዳዲይ "ታሪኽ አልበግዳድ" በተሰኘው ኪታባቸው (13/55) ላይ ኢብኑል ጀውዚይ ደግሞ " አልሙንተዘም ፊ ታሪኽ አል ኡመም ወል ሙሉክ (12/403) ላይ አስፍረውታል።

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

11 Oct, 06:34


ጁሙዐ ጧት ፂሙን ሙልጭ አድርጎ ላጭቶ ወይም ከርክሞ ከዚያም ሚንበር ላይ ይወጣና:–

عليكم بسنتي وسنة الخلفاء الراشدين

ይላል። ግራ ነው!! ሚንበር ማለት ከባድ ቦታ ነው። ትልቅ አማና ነው። ቃሉና ምግባሩ የማይገናኝ፣ ለህዝብ አርአያ መሆን የማይችል ሰው ፊጥ ሲልበት ዋጋው ይረክሳል።
(یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ لِمَ تَقُولُونَ مَا لَا تَفۡعَلُونَ ۝  كَبُرَ مَقۡتًا عِندَ ٱللَّهِ أَن تَقُولُوا۟ مَا لَا تَفۡعَلُونَ)

"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የማትሰሩትን ነገር ለምን ትናገራላችሁ? የማትሰሩን ነገር መናገራችሁ አላህ ዘንድ መጠላቱ ተለቀ፡፡" [አሶ፞ፍ: 2 - 3]

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

09 Oct, 04:55


ሁሌም ሳስበዉ የሚገርመኝ ጂብሪል عليه سلام ወሕይ ይዞ ወደ ረሱል صلى الله عليه وسلم መምጣት  ሲጀምር አከባቢ ነቢዩ (صل الله عليه وسلم)  ወደ #ኸዲጃ መገስገስ ነዉ አንድ ሰዉ ብቻ ባንተ ልብ ዉስጥ እምነትን ሰላምንና እርጋታን መዝራት እንደሚችል ተረድቻለሁ።ነበር።

▸ ለሁላችሁም የልብ ሰዉ አሏህ ይስጣቹ


https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك

09 Oct, 03:58


በአፋር ክልል ዱለሳ ወረዳ በተከሰተ " የመሬት መንቀጥቀጥ " ምክንያት ከተፈጠረ የመሬት ስንጥቅ ውስጥ ፍል ውሃ ፈልቋል سبحان الله

1,240

subscribers

796

photos

224

videos