ህዳር9 /2017 ዓ.ም
«መፀዳጃ ቤት ለሰላም ቦታ»
የአለም የመፀዳጃ ቤት ቀን በየአመቱ እ.ኤ.አ ህዳር 19 ይከበራል።
በዓለም ለ11ኛ ጊዜ የሚከበረው የዓለም የመፀዳጃ ቤት ቀን «መፀዳጃ ቤት ለሰላም ቦታ» በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡ መሪ ቃሉ ዘላቂ ንጽህና ለጤናማ እና የተረጋጋ ማህበረሰብ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ያሳያል፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ3.5 ቢሊዮን በላይ ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ መፀዳጃ ቤት ሳያገኙ እንደሚኖሩ መረጃዎች ያሳያል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዘላቂ የልማት ግቦች ተብለው ከተቀመጡት ውስጥ እ.ኤ.አ በ2030 ውሃና ንፅህና ለሁሉም ማዳረስ አንዱ ግብ ሆኖ ተቀምጧል፡፡
በመሆኑም እኤአ ከ2013 ጀምሮ የዓለም የመፀዳጃ ቤት ቀን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አመታዊ በዓል ሆኖ በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እየተከበረ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣንም በዘመናዊ ፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት እና የፍሻስ መሰረተ ልማት ጠቀሜታና ለፍሳሽ መሰረተ ልማት ሊደረግ በሚገቡ ጥንቃቄዎች ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመስራት ያከብራል፡፡
ባለስልጣኑ ከተማዋ ዘመናዊ የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት ይገባታል በሚል ጠንካራ አቋም ዘመናዊ የፍሳሽ ጣቢያዎች ግንባታ፤ ዘመናዊ ፍሳሽ መስመር ዝርጋታ እና ደንበኞችን ዘመናዊ የፍሻሽ መስመር ተጠቃሚ የማድረግ ስራዎችን በማከናወን ከተማዋ በሚመጥን ልክ ዘመናዊ፣ ጤናማ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ የማድረግ ሂደት እያፋጠነ ይገኛል ፡፡
ባለስልጣኑ ባለፉት ዓመታት በሰራቸው በርካታ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ፤ የከፍተኛ እና መለስተኛ ፍሳሽ መስመር ዝርጋታ እና የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓቱን ሊያዘምኑ የሚችሉ ኘሮጀክቶችን ሲሰራ ቆይቷል፡፡
ለአብነትም፡-
-43 ዘመናዊ የፍሰሽ ማጣሪያ ጣቢያዎችን ተገንብቷል
-139 ከፍተኛ እና 1,631 መለስተኛ የፍሳሽ መስመር በጠቅላላው 1,770 የከፍተኛ እና የመለስተኛ የፍሻሽ መስመር ዝርጋ ስራዎች ተከናውናኗል፡፡
-የከተማዋን ነዋሪ ዘመናዊ የፍሻስ አወጋገድ ስርዓት ተጠቃሚ በማድረግ ሂደት 272,339 ደንበኞችን የዘመናዊ የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት ተጠቃሚ ተደርጓል፡፡
ይሁንና አዲስ አበባ በማያቋርጥ ፈጣን እድገት ውስጥ የምትገኝ ከተማ መሆኗን ተከትሎ ባለስልጣኑ በቀጣይ የኮሪደር ልማት በሚሰሩባቸው አካባቢዎች፣ በጋራ መኖሪያ ቤቶች እና በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ዘመናዊ የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት ተጠቃሚ ለማድረግ የፍሳሽ ፍኖተ ካርታውን በሶስት ተፋሰሶች ማለትም በምስራቅ ተፋሰስ፤ በቦሌ አራብሳ እና በኮዬ ፍቼ ተፋሰሶች በመክፈል እየሰራ ይገኛል፡፡
በተጨማሪም በደቡብ አቃቂ ተፋሰስ ፍኖተ ካርታው እና አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ተግባር ለመግባት በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል፡፡
ዘመናዊ የፍሳሽ አወጋድ ስርዓት ተጠቃሚ በመሆን የከተማችን ፅዳትና ውበት ይጠብቃል፤ በመንገዶች ላይ ፍሳሽ እንዳይወጣ ይከላከላል፤ ከሽንት ቤት መሙላትና መገንፈል ያድናል፤ ከተለያዩ በሽታዎች እንጠበቃል፤ ከተማችንን ጽዱ እና ለነዋራቿ ምቹ የማድረግ ሂደት እናፋጥናለን፡፡
በመሆኑም ዘመናዊ የፍሳሽ መሰረተ ልማት በተዘረጋባቸው አካባቢዎች ቅጥያ በማሰራት ሁሉም ማህበረሰብ የዘመናዊ ፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት ተጠቃሚ እንዲሆን ባለስልጣኑ ጥሪውን ያስተላልፋል ። ከዚህም ባሻገር የፍሳሽ መሰረተ ልማት የጋራ ሀብታችን በመሆኑ ባዕድ ነገሮችን ባለመጨመር እንዲሁም ከስርቆትና ህገ-ወጥ ተግባራት ሊጠብቅ ይገባል ፡፡