ከንቲባ አዳነች አቤቤ "የ97 የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች የሚባል አናውቅም " አሉ‼️
ይህ የተባለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ነው።
በብሔራዊው ቴሌቪዥን ጣቢያ በተሰራጨውና ትኩረቱን የኮሪደር ልማት ላይ ባደረገው በዚህ ውይይት የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ( ኢሕአፓ ) የአዲስ አበበ ኮሚቴ ሰብሳቢ አበበ አካሉ የ97 ተመዝጋቢዎችን የተመለከተ ጥያቄ ይሰነዝራሉ።
ፖለቲከኛው ጥያቄያቸውን ሲጀምሩ የኮሪደር ልማቱን ተከትሎ ቤታቸው ለፈረሰባቸው ሰዎች የሚሰጠው የኮንዶሚኒየም ቤቶች እና ከተማ አስተዳደሩ ላይ የ97 ተመዝጋቢዎች ያነሱታል ያሉትን ሀሜት በማስቀደም ነው።
<< እኛ በቆጠብነው ገንዘብ ነው ተፈናቃዮች ወይም የልማት ተነሺዎች እያሰፈሩ ነው የሚል እሮሮ አለ >> ያሉት አበበ << ለዚህ ምን ምላሽ ነው ያላችሁ፤ ከ97 ጀምሮ የቆጠቡ ሰዎች ...መቼ ነው የሚኖሩበት? ሳይኖሩበት ሊሞቱ ነው እኮ >> ሲሉ በስሜት ተሞልተው ጠይቀዋል።
ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ << የ97 የሚባል የለም >> በማለት ማብራሪያቸውን ይጀምራሉ።
ከንቲባዋ ሲቀጥሉ << [ እኛ እስከምናውቀው ድረስ ] የ97 የሚባል ዘግተናል >> ሲሉ ተናግረዋል።
<< ባለፈው ያስጨረስናቸውን ኮንዶሚኒየም ቤቶች ቅድማያ ለ97 active [ ንቁ ] ቆጣቢዎች ሁሉ ዕጣ እንዲወጣላቸው ተደርጓል >> ሲሉ አስታውሰዋል።
አክለውም << እነርሱ እንዲወጣላቸው ከተደረገ በኋላ deactivate ያደረገውን [ የዘጋውን] አካውንት activate [መቆጠብ የጀመረ ] ያደረገ ካለ
እሱ ለሚቀጥለው ጊዜ ..ያው ቆጥቧል፤ ቤት ስለሚፈልግ ነው activate የሚያደርገው ሊታይ ይገባል እንጂ በዚህ መንገድ መቅረብ ያለበት አይመስለኝም >> ሲሉ ደምድመዋል።
Via:አሻም
@min_ddis