Asham TV | አሻም ቲቪ

@asham_tv


Asham Tv is a privately owned media company, based in Addis Ababa, Ethiopia, that provides news, Analysis, information and other programs.

Asham TV | አሻም ቲቪ

22 Oct, 12:45


🔵 በመርካቶ የገበያ ማዕከል ላይ የተነሳው የእሳት አደጋ ሆነ ተብሎ ነው የሚለው አስተያየት ፍጹም ኃላፊነት የጎደለውና አሉባልታ ነው ሲል የመዲናዋ አስተዳደር በአሻም በኩል ውድቅ አደረገ፡፡

🔵 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በኢትዮጵያ እየሆነ ያለው ለአንድ ሀገር ውድቀት ምክንያት እንጂ የዕድገት ምልክት ሊሆን አይችልም ሲሉ ተናገሩ።

🔵 በኮሪደር ልማት ምክንያት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የንግድ ሱቆቻቸው እንደፈረሰባቸው አሻም ያነጋገረቻቸው የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

🔵 ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዛሬው ዕለት ይፋ ያደረገው የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪ ተገቢነት የሌለው ነው ሲል የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ተቸ፡፡

🔵 ኦብነግ ከትናንት በስቲያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑን አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ ፓርቲውን የሚወክል አይደለም ሲሉ አንድ የግንባሩ አባል ለአሻም ተናገሩ፡፡

👉 ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 12 ቀን 2017 ምሽት 1፡30 ላይ ይጠብቁን።

Asham TV | አሻም ቲቪ

22 Oct, 07:49


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሙሉ ዕወቅና ለመስጠት ሲያስከፍል የነበረው 200 ብር ቢሆንም ከትናንት ጀምሮ ግን 30ሺህ ብር ማድረጉን አስታወቀ፡፡

በመቶኛ ሲሰላ - ከ15000% በላይ ነው፡፡


አሻም ዜና | ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም

ቦርዱ ባወጣው መግለጫ ለሀገር አቀፍና ለክልላዊ ፓርቲ ጊዜያዊ የምስክር ወረቀት ለማግኘት ያስከፍል የነበረው 100 ብር ሲሆን ከትናንት ጀምሮ ግን በአንድ መቶ ሀምሳ ዕጥፍ (15000%) ጨምሮ 15ሺህ ብር አድርሶታል፡፡

የሙሉ ዕወቅና ክፍያ 200 ብር ሆኖ እስከትናንትናው ዕለት ድረስ ቢቆይም እዚህም ላይ የ150 እጥፍ ጭማሪ በማድረግ ቦርዱ 30ሺህ ብር አስግብቶታል፡፡ 30 ብር የነበረው የሰነድ ማሻሻያ ክፍያ ደግሞ በአንድ መቶ ስድሳ ስድስት ነጥብ ስድስት እጥፍ አሻቅቦ 5ሺህ ብር ሆኗል፡፡

ቦርዱ ለዚህ ጭማሪው በየጊዜው መሻሻል እንደሚያስፈልግ በማመኔ ነው ይበል እንጂ ዝርዝር ጉዳዮቹን አልገለጸም፡፡ ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ተግባራዊ የተደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ መሠረታዊ የሚባሉት እንደ አሌክትሪክ ኃይል፣ ቴሌኮም፣ ባንክ፣ ፓስፖርት ያሉት አገልግሎቶች በተጋነነ ዋጋ ጭማሪ ሲያደርጉ ሰንብተዋል፤ አሁን ደግሞ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከአንድ መቶ ሀምሳ እጥፍ በላይ ጭማሪ አድርጓል፡፡

[በዚህ ዘገባ ላይ ማስተካከያ ተደርጎበታል]

አሻም ለኢትዮጵያችን!!

Asham TV | አሻም ቲቪ

21 Oct, 17:16


👉‹‹ ብልጽግና ለጽ/ቤት ማሰሪያ ‹‹ በግዳጅ ›› ገንዘብ እየጠየቀ ነው ›› ነዋሪዎች
👉በእነ ዮሐንስ ቧያለው የችሎት ውሎ ምን ተሰማ?

አሻም  ዜናዎች እነዚህን እና ሌሎችም  ዜናዎችን በዝርዝርና በጥልቀት  ለማዳመጥ ከታች የተቀመጠውን ማሰፈንጠሪያ ይጫኑ።
https://youtu.be/m_sAkZqmjTE

Asham TV | አሻም ቲቪ

21 Oct, 12:49


🔵 በወላይታ ዞን ለብልጽግና ጽ/ቤት ማሰሪያ 350 ሚሊዮን ብር አዋጡ በሚል የፓርቲው አባል ባልሆኑት ላይ ጭምር ከፍተኛ እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑን ለአሻም አስተያየታቸውን የሰጡ ነዋሪዎች አቤቱታቸውን አሰሙ፡፡

🔵 በእነዮሐንስ ቧያለው መዝገብ የቀረበውን የክስ ማሻሻል ጥያቄ አቃቤ ህግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበው ይግባኝ ብይን እስኪሰጥበት በከፍተኛው ፍርድ ቤት ክሱ ታግዶ እንዲቆይ ተወሰነ፡፡

🔵 እናት ፓርቲ የሰነድ ማጭበርበርና ማታለል፣ የፋይናንስ ምንጭ’ና አስተዳደር ችግሮች ያለበት መሆኑን የቀድሞው የስራ ኃላፊዎች ሲከሱ ፓርቲው በበኩሉ ውንጀላውን ውድቅ አደረገ፡፡

🔵 በአማራ ክልል ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ዳኞች መገደላቸውንና አስራ አንዱ መታሰራቸውን የክልሉ ዳኞች ማህበር ለአሻም ተናገረ፡፡

🔵 በግጭት ዐውድ ውስጥ ያሉ አካላቶችን ያላካተተ ምክክር ውጤታማነቱ አስተማማኝ አይደለም ሲሉ አሻም ያነጋገረቻቸው ባለድርሻ አካላት ገለጹ፡፡

🔵 የገንዘብ ሚኒስቴር የጥቅምት ወር ደመወዝ ክፍያ አዲስ በተሻሻለው ስኬል መሠረት ክፍያ እንደሚፈጸም አስታወቀ፡፡

👉 ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ምሽት 1፡30 ላይ ይጠብቁን።

አሻም ለኢትዮጵያችን!

Asham TV | አሻም ቲቪ

21 Oct, 12:05


#ወረት

ዛሬ ምሽት 2:30 ይጠብቁን !

አሻም ለኢትዮጵያችን!!!

Asham TV | አሻም ቲቪ

20 Oct, 16:07


<< የሰውን ሞት በኮሪደር ልማት አታሳቡ >> - ብልጽግና ፓርቲ

ኮሪደር ልማትና ራስን ማጥፋት

አሻም ዜና | ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም

ለአንድ ሰዓት ከሠላሳ ደቂቃዎች ገደማ በዘለቀው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ሃላፊዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ውይይት ሌላው የተነሳው ነጥብ ከኮሪደር ልማት ጋር የተያያዙ የሰዎች ሞትን/ ራስን ማጥፋት የተመለከተው ነው።

ይህንኑ በተመለከተ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ [አብን] በመወከል በውይይቱ የተሳተፉት ኤርሚያስ ተገኔ የተባሉ ፖለቲከኛ ጥያቄ ሰንዝረዋል። ጥያቄያቸውን ለህብረተሰቡ የሥነ ልቦና ድጋፍ ቢመቻቹ ጥሩ መሆኑን በመጥቀስ ነው የጀመሩት።

ለዚህ ምክንያታቸው << አንዳንድ የምንሰማቸው ድንገተኛ ሞቶች ስላሉ >> መሆኑን ያስረዱት ኤርሚያስ << ገና ለገና በስጋት የምከራየው ቤት አጣለሁ ብሎ ራሱን የሚያጠፋ ፣ እንዲሁም ደግሞ በግፊት [ደም]  የሰው ሕይወት እያለፈ ስለሆነ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች ከውይይት በዘለለ ከሥነ ልቦና ባለሙያዎች ከሃይማኖት አባቶች ጋር በመሆን ቢመቻች >> ብለዋል።

ይህን ጥያቄያቸውን በምሳሌ ያስደገፉት ፖለቲከኛው <<  አንድ ግለሰብ ግንፍሌ አካባቢ ያለ ሆቴል ባለቤት የንግድ ቦታውን ከግለሰብ ቁልፍ እንደገዛ..ከዛ በኋላ እንደቆየ እና አድስ ተብሎ ካደሰ በኋላ በዚህም ምክንያት ቤቱ ሲፈርስ በግፊት [ደም] ምክንያት ሕይወቱ እንዳለፈ መረጃዎች ሰምቼያለሁ >> ሲሉ ተናግረዋል።

ለዚህ ጥያቄ ምላሾችን የሰጡት ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ ሞገስ ባልቻ ናቸው።

የብልጽግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ ሞገስ ባልቻ << ሁኔታዎች ጋር ድርጊቶች ጋር ከሆነ፣ ከሚያጋጥም ድርጊት ጋር associate ማድረግ [ማያያዝ ] አግባብነት የለውም >> በማለት ውድቅ በማድረግ ምላሻቸውን ይጀምራሉ።

<< የሰው ልጅ በህይወት ቢኖር ጥሩ ነው፤ ነገር ግን ረዥም ሥራ ሰርተን፣ ምርጥ ነገሮችን ሰርተን ስናበቃ በመሃል ሰው የሚያልፍ [ የሚሞት ] ከሆነ ከኮሪደር ጋር መሳበብ የለበትም >> ሲሉ ጥያቄውን በመንቀፍ ተከላክለዋል።

ለዚህ ምክንያታቸው << ብዙ ሰው ነው ያወያየነው፤ ይሄን ሥራ እንደምንሰራ ይሄንን እንደምናደርግ፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ ደግሞ ሊኖራቸው የሚገባቸው መብቶችና ጥቅሞች ምን እንደሆነ መነሻ አድርገን በደንብ አውርተናል >> የሚል ነው።

የብልጽግናው አመራር ሲቀጥሉ << ከዛ ውስጥ አንድ ሰው የአርባ ቀን ዕጣ ፈንታው ሆኖ እንትን ካደረገ [ ከሞተ/ካረፈ ] ከኮሪደር ጋር ማገናኘት፣ ከተነሺዎች ጋር ማገናኘት አይጠቅምም >> ሲሉ ዳግም ውድቅ አድርገውታል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው ምላሽ መስጠት የጀመሩት << ከሞት ጋር ያያዛችሁትን ተውት ፤ እውነት፤ ጥሩ አይደለም >> በማለት ነው።

ከንቲባው መከራከሪያቸውን ሲያቀርቡ << የካ ላይ አንድ ጋዜጠኛ ጻፈች ተብሎ እንዲጣራ አደረግን፤ በእርግጥ በግፊት  [ደም] ቢሆንም ኮሪደር ልማት [ ግን ] ምክንያት አይደለም >> ብለዋል።

አዳነች ለተነሳው ጥያቄ ምሳሌዎችን በመጥቀስ ይቀጥሉና ሌላ ድርጊትን ያነሳሉ።

<< በተመሳሳይ አንደኛው ክፍለ ከተማ የቤተሰብ ግጭት ተፈጠረና በሆነ ምክንያት ዝርዝሩን አናውቅም፤ ግን የቤተሰብ ጉዳይ ነው፤ ራስን የማጥፋት ተከሰተ ተባለ >> ሲሉ ነገሩን ማስረዳት ይቀጥላሉ።

<< ከኮሪደር ጋር .. ሲጀመር ቤትም የላቸውም፤ ቤቱ የሚፈርስበት እኮ ቤት ያለው ሰው ነው እኮ አይደለ? >> ሲሉ የጠየቁት ከንቲባዋ << አብረን ኮሚቴ አቋቁመን እናጣራ ብንል ማፈር ይመጣል፤ ያሳፍራል>> ሲሉ በተመሳሳይ ውድቅ አድርገዋል።

አክለውም << ትክክል አይደለም፤ ህዝባችን በዚህ ጫና ቢፈጠርበትና ቢጨነቅ ምን እናገኛለን?፤ ምን ጥቅም እናገኛለን?፤ የምንመራው ህዝብ እኮ ያስፈልገናል፤ ነገ ተመርጠን ስልጣን ካገኘን >> ሲሉ ተናግረዋል።

አሻም ለኢትዮጵያችን!!

Asham TV | አሻም ቲቪ

20 Oct, 14:58


መንግስት፣ የ97 የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች የሚባል << አላውቅም >> አለ።

አሻም ዜና | ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም


ይህ የተባለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ነው።

በብሔራዊው ቴሌቪዥን ጣቢያ በተሰራጨውና ትኩረቱን የኮሪደር ልማት ላይ ባደረገው በዚህ ውይይት የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ( ኢሕአፓ ) የአዲስ አበበ ኮሚቴ ሰብሳቢ አበበ አካሉ
የ97 ተመዝጋቢዎችን የተመለከተ ጥያቄ ይሰነዝራሉ።

ፖለቲከኛው ጥያቄያቸውን ሲጀምሩ የኮሪደር ልማቱን ተከትሎ ቤታቸው ለፈረሰባቸው ሰዎች የሚሰጠው የኮንዶሚኒየም ቤቶች እና ከተማ አስተዳደሩ ላይ የ97 ተመዝጋቢዎች ያነሱታል ያሉትን ሀሜት በማስቀደም ነው።

<< እኛ በቆጠብነው ገንዘብ ነው ተፈናቃዮች ወይም የልማት ተነሺዎች እያሰፈሩ ነው የሚል እሮሮ አለ >> ያሉት አበበ << ለዚህ ምን ምላሽ ነው ያላችሁ፤ ከ97 ጀምሮ የቆጠቡ ሰዎች ...መቼ ነው የሚኖሩበት? ሳይኖሩበት ሊሞቱ ነው እኮ >> ሲሉ በስሜት ተሞልተው ጠይቀዋል።

ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ << የ97 የሚባል የለም >> በማለት ማብራሪያቸውን ይጀምራሉ።

ከንቲባዋ ሲቀጥሉ << [ እኛ እስከምናውቀው ድረስ ] የ97 የሚባል ዘግተናል >> ሲሉ ተናግረናል።

<< ባለፈው ያስጨረስናቸውን ኮንዶሚኒየም ቤቶች ቅድማያ ለ97 active [ ንቁ ] ቆጣቢዎች ሁሉ ዕጣ እንዲወጣላቸው ተደርጓል >> ሲሉ አስታውሰዋል።

አክለውም << እነርሱ እንዲወጣላቸው ከተደረገ በኋላ deactivate ያደረገውን [ የዘጋውን] አካውንት activate [መቆጠብ የጀመረ ] ያደረገ ካለ
እሱ ለሚቀጥለው ጊዜ ..ያው ቆጥቧል፤ ቤት ስለሚፈልግ ነው activate  የሚያደርገው ሊታይ ይገባል እንጂ በዚህ መንገድ መቅረብ ያለበት አይመስለኝም >> ሲሉ ደምድመዋል።

አሻም ለኢትዮጵያችን!!

Asham TV | አሻም ቲቪ

20 Oct, 06:45


‹‹ ኮሪደር ልማቱ [ ፒያሳ ] በጎ ጎኑ ያመዝናል ›› - ኢዜማ |ከኢዜማ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሙሉዓለም ተገነኘወርቅ (ዶ/ር) ጋር የተደረገ ቆይታ

https://youtu.be/T17lZVp8Oec?si=ZFFzK6LBMM7aFb5R

Asham TV | አሻም ቲቪ

19 Oct, 12:03


‹‹ ከመንግስት ጋር በመሥራቴ ኢትዮጵያን ከመፍረስ አትርፊያለሁ ›› - ኢዜማ

አሻም ወቅታዊ | ጥቆማ | ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም


የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ ፓርቲ ( ኢዜማ ) የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሙሉዓለም ተገኘወርቅ (ዶ/ር)
የዚህ ሳምንት የአሻም ወቅታዊ እንግዳ ናቸው።

ኢዜማ ከመንግስት ጋር ስላለው ግንኙነት፣ የኮሪደር ልማት፣ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የቃለምልልሱ አስኳሎች ናቸው።

የኮሪደር ልማቱ በተለይ የፒያሳው አወንታዊ ጎኖቹ እንደሚያመዝን ሙሉዓለም ለአሻም ነግረዋታል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን አጥብቆ እንደሚቃወም የገለጸው  ኢዜማ በዚህ ውሳኔ << የመንግስትነቱንም ሆነ የኢትዮጵያን ልዕልናን ለአበዳሪዎቹ ፍላጎት አሳልፎ ሰጥቷል >> ሲል  የዐብይ አህመድ(ዶ/ር) መንግስትን ወንጅሏል።

በሌላ በኩል ኢዜማ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ግን አንዳች ዓይነት << ለውጥ ያመጣል >> የሚል ዕምነት አለው።

ከኢዜማ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሙሉዓለም ተገኘወርቅ (ዶ/ር) ጋር የተደረገውን ቆይታ ዛሬ ቅዳሜ ምሽት 2:30 እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

በቴሌቪዥን ቃለምልልሱን መከታተል ያልቻላችሁ #በአሻም_ዜና / #Asham_News ይፋዊ የዩቱብ አድራሻ ልታገኙት ትችላላችሁ።

አሻም ለኢትዮጵያችን!!

Asham TV | አሻም ቲቪ

18 Oct, 16:40


👉‹‹ ኢትዮጵያ በስህተት ጎዳና ላይ ናት ›› - ኢትዮጵያውያን
👉በአማራ ክልል ከ5ሺህ በላይ ፆታዊ ጥቃቶች ተፈጽመዋል

አሻም  ዜናዎች እነዚህን እና ሌሎችም  ዜናዎችን በዝርዝርና በጥልቀት  ለማዳመጥ ከታች የተቀመጠውን ማሰፈንጠሪያ ይጫኑ።
https://youtu.be/ZnvCwbuUjvs

Asham TV | አሻም ቲቪ

18 Oct, 13:42


🔵 በመንግስት የፀጥታ አካላትና በፋኖ ኃይሎች መካከል በሚካሄደው በትጥቅ የታገዘ ግጭት ምክንያት ከ5ሺህ በላይ ፆታዊ ጥቃቶች ሴቶች ላይ እንደተፈጸሙ አንድ ጥናት አጋለጠ፡፡

🔵 በሰላሌ ሀገረ ስብከት ደራ ወረዳ ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት መካከል 70 በመቶ የሚያህሉት አገልግሎት መስጠት ማቆማቸውን የወረዳው ቤተ ክህነት ለአሻም ተናገረ፡፡

🔵 56 በመቶ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸው በስህተት ጎዳና እየተጓዘች ነው ብለው እንደሚያምኑ መናገራቸውን የአፍሮ ባሮ ሜትር ጥናት አመለከተ፡፡

🔵 የትግራይ ነጻነት ፓርቲ (ውናት) ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እንዳላደርግ ግድያን ጨምሮ ከፍተኛ ጫና እያሳደረብኝ ነው ሲል ለአሻም ተናገረ፡፡

🔵 መንግስት አድርጌዋለሁ ያለውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ መደበኛ ሕይወትን ለመግፋት እንደተቸገሩ አሻም ያነጋገረቻቸው የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

🔵 በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሹ በሚገኘው የፖሊስ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ካፌ ውስጥ አንድ የአልሻባብ አጥፍቶ ጠፊ በፈጸመው ጥቃት ሰባት ሰዎች ተገደሉ፡፡

👉 ዛሬ አርብ ጥቅምት 8 ቀን 2017 ምሽት 1፡30 ላይ ይጠብቁን።

Asham TV | አሻም ቲቪ

18 Oct, 11:10


🔵 አሻም በሳምንቱ

ዛሬ ዓርብ ከምሽት 1:30 ዜና እወጃ በኋላ ይጠብቁን!

አሻም ለኢትዮጵያችን!!

Asham TV | አሻም ቲቪ

17 Oct, 16:58


👉አሻም ቲቪ ስሟ ፀንቶ ይቀጥላል
👉በአማራ ክልል ያልተቋረጠው የድሮን ጥቃት

አሻም  ዜናዎች እነዚህን እና ሌሎችም  ዜናዎችን በዝርዝርና በጥልቀት  ለማዳመጥ ከታች የተቀመጠውን ማሰፈንጠሪያ ይጫኑ።
https://youtu.be/xy0lKd181xk

Asham TV | አሻም ቲቪ

17 Oct, 13:03


Asham TV | አሻም ቲቪ pinned «አሻም ቲቪ ስያሜዋን በመጠቀም ትቀጥላለች፡፡ አሻም ዜና | ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍተሐብሔር ምድብ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 228079 በቀን 20/08/2014 ዓ.ም እና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 229220 በቀን 21/10/2016 ዓ.ም አሻም የሚለውን ስያሜ ፍርድ ቤት የሰጠውን ትዕዛዝ ለማስፈጸም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለአሻም የማሳሰቢያ…»