Ethio telecom

@ethio_telecom


The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Ethio telecom Telegram Channel (English)

Welcome to the official Ethio telecom Telegram Channel! As the first Telecom operator in Africa, Ethio telecom has been a pioneer in providing reliable and affordable communication services to the people of Ethiopia. With a commitment to connecting communities and empowering individuals, Ethio telecom plays a crucial role in driving the country's socio-economic development. By joining our Telegram Channel, you will have access to the latest updates on our services, promotions, and initiatives. You can also engage with other members of the Ethio telecom community, share your feedback, and ask any questions you may have. Stay connected with us and be part of our journey towards a more connected Ethiopia. Join us today at https://t.me/EthiotelecomChatBot and experience the power of communication with Ethio telecom!

Ethio telecom

22 Oct, 14:02


በዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ፍሬህይወት ታምሩ የተመራ የኩባንያችን የሥራ አመራር ከባህር ዳር ከተማ መስተዳድር ከንቲባ እና ኃላፊዎች ጋር በጋራ በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት እንቅስቃሴዎች ተዘዋውረው ጎበኙ፡፡

በዚህም ወቅት ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን በባህር ዳር ከተማ እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት የጎበኙ ሲሆን ፕሮጀክቱ ከእቅድ እና ዲዛይን ጀምሮ ከኩባንያችን ጋር በቅንጅት እየተተገበረ መሆኑን አድንቀዋል፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን አክለውም ኩባንያችን ከመስተዳድሩ ጋር በቅርበት በመስራት የቴሌኮም መሰረተ ልማቶችን በጥንቃቄ እያዘዋወረ መሆኑን በመግለጽ የሚነሱ የቴሌኮም መስመሮች ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ በፋይበር የማዘመን ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

በከተማዋ የሚከናወኑ የ5ጂ ሞባይል ኔትወርክ፣ ስማርት ሲቲ እና ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶች የባህር ዳር ከተማን ለኢንቨስትመንት፣ ቱሪዝም እና ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ተመራጭ በማድረግ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ለመጨመር እንደሚያስችል አጽንኦት ተሰጥቷል፡፡

ኩባንያችን የከተማዋን ዲጂታላይዜሽን የሚያፋጥኑ የ5ኛው ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ ጅማሮን ማብሰሩ እንዲሁም የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ከመስተዳድሩ ጋር መፈራረሙ ይታወቃል፡፡

#ዲጂታልኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ

#GSMA #ITU #WorldBank #OECD #AMECO #BahirDarcityadministration

Ethio telecom

22 Oct, 09:03


ምዝገባ ካልፈጸሙ በአካል ቀርበው በነጻ ይመዝገቡ!

የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ምዝገባ በሁሉም የአገልግሎት ማዕከሎቻችን እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/uecbbr ውስጥ በተካተተው አቅጣጫ ጠቋሚ መተግበሪያ በመታገዝ አቅራቢያዎ የሚገኘውን የምዝገባ ማዕከል ይወቁ፤ በአካል ቀርበው በነጻ ይመዝገቡ!

ለተጨማሪ መረጃ https://bit.ly/45NUZRy ይጎብኙ!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalID #Fayda #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia

Ethio telecom

22 Oct, 06:02


https://youtu.be/ZPixD9LLLGI

Ethio telecom

21 Oct, 15:00


ኩባንያችን በዛሬው እለት የስማርት ሲቲ (ስማርት ባህር ዳር) ፕሮጀክት ለመተግበር የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ከባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ጋር ተፈራረመ፡፡

ስምምነቱ በምዕራፍ ተከፋፍሎ የሚከናወን ሲሆን የክላውድ፣ ጥሪ ማዕከል፣ ዳታ ሴንተር፣ ባለ ከፍተኛ አቅም ኢንተርኔት እና ተያያዥ የዲጂታል መሰረተ ልማት በመገንባት እንደ ትምህርት፣ ጤና፣ ግብርና፣ ትራንስፖርት፣ ቱሪዝም ያሉ ዘርፎችን 'ስማርት' ከማድረግ ባሻገር ደህንነቷ አስተማማኝ የሆነ ከተማ እውን ለማድረግ ያለመ ነው፡፡

የስማርት ባህር ዳር ፕሮጀክቱ የከተማ አስተዳደሩን በዲጂታል ሶሉሽኖች በማስታጠቅ እንዲሁም ክፍያዎችን በቴሌብር በማስተሳሰር የማስፈጸም አቅማቸውን እና ውጤታማነታቸውን ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ ያስችላል፡፡

ይህም ተገልጋዮች ቀልጣፋ አገልግሎት ለማግኘት እንዲችሉ በማገዝ፣ እንግልትን በመቀነስ ህይወታቸውን ለማቅለል እና የአኗኗር ዘይቤያቸውን ለመቀየር ያስችላል፡፡

የፕሮጀክቱ ትግበራ ከተማዋን ለቱሪዝም እና ኢንቨስትመንት መዳረሻነት ምቹና ተመራጭ በማድረግ ተወዳዳሪነትን የሚጨምር ሲሆን የቢዝነስ እንቅስቃሴ በማሳለጥ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ያሻሽላል፡፡

ለስማርት ሲቲ አስቻይ መደላድል የሚፈጥረውን ፈጣኑን የ5ኛ ትውልድ ኔትወርክ አገልግሎት በባህር ዳር መጀመሩን በትናንትናው ዕለት ማብሰራችን ይታወሳል።

#ዲጂታል_ኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ

#DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia #GSMA #ITU

Ethio telecom

21 Oct, 13:00


🏆 የቴሌብር ቤተሰብዎን ያብዙ፤ እስከ 10,000 ብር ስጦታ ያግኙ!

ቴሌብር ሱፐርአፕ ላይ “ይጋብዙ ይሸለሙ” የሚለውን አማራጭ በመጠቀም

💬 በአጭር መልእክት ወይም
🌐 በማኅበራዊ ሚዲያ

መተግበሪያውን ያጋሩ፤ ወዳጆችዎ ግብይት ሲጀምሩ እርስዎ የ30 ብር ስጦታ ያገኛሉ፡፡

💁‍♂️ በተጨማሪም 20 አዲስ ደንበኞችን ሲያገኙ ታብሌቶችና ስማርት ስልኮች እንዲሁም ሌሎች ሽልማቶችን ባካተተው የዕድል ጨዋታ ብቁ ይሆናሉ!

🔗 ቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/uecbbr ይጫኑ!


ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!

#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSupperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia