ኢትዮ መረጃ - NEWS

@ethio_mereja_news


ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት

ማክበር ባትችል አታዋርዳት
ማራመድ ባትችል አታዘግያት
መጠበቅ ባትችል አትበትናት።
ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም።

ለአስታየት @ethio_merjabot
@biruke_promotion

ኢትዮ መረጃ - NEWS (Amharic)

ኢትዮ መረጃ - NEWS ከአዲስ አበባ እና ታሪካዊ አለም አቀፍ ኢትዮጵያን ለመውደድ የሚረታቸውን መረጃዎችን የሚያግዝ ፍቅር አልበምም። በተጨማሪም የዓለም አቀፍ መረጃዎችን ለማቅረብ በተከታታይ ነገር ተካተተ። ታሪክን መከታት። ታሪክን ወደተቃወሞ አስተያየት እና መንገድ እና ሰጥቶአል። ይህን በማድረግ ለመከታት እና ለሰጥቶአል።

ኢትዮ መረጃ - NEWS

22 Oct, 16:09


በወልዲያ አንዲት እናት በአንድ ጊዜ 4 ልጆችን በሰላም መገላገሏን የወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ገለጸ።

የወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚድዋይፍሪ ባለሞያ የሆኑት ወጋየው ገብሬ እንደገለጹት፤ሰላማዊት ደርቤ የተባለች የ31 ዓመት እናት በትናትናው እለት ንጋት ላይ 4 ሴት ልጆችን በሆስፒታሉ በሰላም ተገላግላለች፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news

ኢትዮ መረጃ - NEWS

22 Oct, 14:17


#ኦርቶዶክስተዋሕዶ

" ...አለመግባባት በዝቷል፤ ማኵረፍና መቀያየም ሰፍቷል ፤ ነገሩ ሁሉ ግራ የሚያጋባና የተመሰቃቀለ ሆኖ ይታያል፡፡ ችግሩ ከሕዝብ አልፎ የአምልኮ ስፍራዎችንና የአምልኮው ፈጻሚዎችን ዒላማ ያደረገ እግዚአብሔርን መዳፈር እየተለመደ መጥቷል " - ቅዱስነታቸው

የጥቅምት 2017 ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ተጀመረ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወሕዶ ቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ አገልግሎትና የስራ አፈጻጸም ላይ ለመምከርና ለመወሰን ኃላፊነት ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ መደበኛና ዓመታዊ ጉባኤውን ጀምሯል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የጉባኤውን መጀመረ አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከመልዕክታቸው ፦

" የሰው ልጆች በዚህ ዓለም ሲኖሩ የተሟላ ሰላምና ጣዕመ ሕይወት ሊኖራቸው የሚችለው በመንፈሳዊ ኑሮአቸው የተሻለ ነገር ስላገኙ ብቻ አይደለም፡፡

ሰዎች ከሥጋዊ ክዋኔም ጭምር የተፈጠሩ እንጂ እንደመላእክት ሥጋ የሌላቸው መንፈስ ስላይደሉ ለኑሮአቸውና ለሥጋዊ ክዋኔአቸው የሚሆን ነገር ያስፈልጋቸዋል፡፡

በዚህም ዓለማዊው አስተዳደር የተመቻቸ መደላድል ሊፈጥርላቸው ግድ ነው፤ ዓለማዊው አስተዳደርም የመለኮትን ተልእኮ ለመፈጸም የተሾመ ሹመኛ እንደመሆኑ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በትክክል መምራት ይጠበቅበታል፡፡

ምንም ቢሆን የተቀበለው ኃላፊነት የእግዚአብሔር ነውና በሚሰራው ሁሉ በሿሚው አምላክ ከመጠየቅ አያመልጥም፡፡

እኛም በዚህ ዓለም የእግዚአብሔር ወኪሎች ስለሆንን ቢሰሙንም ባይሰሙንም ዓለማውያን ሹማምንትን የማስተማርና የመምከር ኃላፊነት አለብን፡፡

ይህ የሁለታችን ኃላፊነት እንደ እግዚብሔር ፈቃድ ስንፈጽም የሕዝብ ሰላምና በረከት፣ ፍቅርና አንድነት፣ ዕድገትና ልማት በአስተማማኝ ሁኔታ ይረጋገጣል፡፡

ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በሀገራችንም ሆነ በአካባቢያችን እየሆነ ያለው ይህ አይደለም፤ አለመግባባት በዝቶአል፣ ማኵረፍና መቀያየም ሰፍቶአል፤ ነገሩ ሁሉ ግራ የሚያጋባና የተመሰቃቀለ ሆኖ ይታያል፡፡

ችግሩ ከሕዝብ አልፎ የአምልኮ ስፍራዎችንና የአምልኮው ፈጻሚዎችን ዒላማ ያደረገ እግዚአብሔርን መዳፈር እየተለመደ መጥቶአል፤ ይህ ለአንድ ሀገር ወይም ሕዝብ የውድቀት ምክንያት ከሚሆን በቀር ከቶውኑም የዕድገት ምልክት ሊሆን አይችልም፡፡

ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ደግሞ ይህ ክፉ ድርጊት እየተፈጸመ ያለው በእኛው ልጆች በኢትዮጵያውያን መሆኑ ነው፤ ስለሆነም በከተማም፣ በጫካም፣ በገጠርም በየትኛውም ስፍራ የምትገኙ ልጆቻችን ምንም ይሁን ምን ሀገርንና ሕዝብን ከመጉዳት ተቆጠቡ፡፡

በተለይም ከቤተ ክርስቲያንና ከሀገር እንደዚሁም ሕዝቡን ከሚያገለግሉ ካህናትና ሲቪል ሰራተኞች እባካችሁ እጃችሁን አንሡ፤ ቤተ ክርስቲያን እኮ የእናንተና የሕዝቡ ሁሉ እናት ናት፤ በእናታችሁ ላይ መጨከንን እንዴት ተለማመዳችሁት ? አሁንም ንስሐ ግቡ ያለፈው ይበቃል፡፡

ልብ በሉ ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት አይበጅም፤ ሰውን መጉዳትና እግዚአብሔርን መዳፈር አቁሙ፤ የእግዚአብሔር ገንዘብ የሆነውን ሥርዓተ አምልኮም ያለቦታው አታውሉ፤ ጥያቄአችሁን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ዕድል ስጡ፡፡

በእግዚአብሔር ስም ለመላው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንና ልጆቻችን የምናስተላፈው ወቅታዊ መልእክታችን ይህ ነው፡፡ "

(የቅዱስነታቸው ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል)

#tikvahethiopia

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news

ኢትዮ መረጃ - NEWS

22 Oct, 14:12


#የሚያስረዳኝ ሰው ሳይኖር እንዴት አድርጌ አስተውላለሁ…


ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ባኮስ የታላቋ ንግስት ሕንደኬ የግዛቷ ሁሉ አዛዥና በገንዘቧም የሰለጠነ ነበር፡፡ ጃንደረባው እንደዘመናችን ሕትመት ባልተስፋፋበት በዚያ ዘመን በ34 ዓ.ም ወደ ኢየሩሳሌም ሊሰግድ ሔዶ ሲመለስ ትንቢተ ኢሳይያስን ያነብ ነበር፡፡

በሐዋርያት ስራ 8÷26 ጀምሮ እንደተጻፈው የእግዚአብሔር መልአክ ወደ ሀዋርያው ቅዱስ ፊሊጳስ በመምጣት ጃንደረባውን እንዲያገኘው አዘዘው፡፡ ሐዋርያውም መጥቶ ባኮስን “በውኑ የምታነበውን ታስተውለዋለህን?” አለው፡፡ እርሱም “የሚያስረዳኝ ሰው ሳይኖር እንዴት አድርጌ አስተውላለሁ?” ሲል መለሰለት፡፡

ባያስተውለውም፣ ባይገባውም፣ እንደ ዘመናችን ሕትመት ባይስፋፋም ጃንደረባው ግን በሞላው በተረፈው የንግስቲቱ ሃብት ላይ አዛዥ ሆኖ ሳለ ኢየሩሳሌም ሔዶ መስገድና ትንቢተ ኢሳያስን ማንበብ ነበር ምርጫው፡፡ በዚህ ዘመን እግዚአብሔር በሃብት የባረከን ሰዎች በገንዘባችን፣ የት መሔድ፣ ምን ማንበብ፣ ምን ማድረግ፣ ምንስ መስራት ይሆን የምንፈልገው?

የቁስጥንጥንያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “በጉዞ ላይ ሆኖ ያውም በሠረገላ ላይ ተቀምጦ ማንበብ አለማቋረጥ ምን ያህል ትጋት የሚጠይቅ እንደሆነ እንድታስተውሉ እጠይቃችኋለሁ በቤታቸው እንኳን ቁጭ ብለው ማንበብን ለማይፈልጉ ሰዎች ይህ ታሪክ ሊስተዋል ይገባዋል፤ ይልቁንም መጻሕፍትን ማንበብን ጊዜን እንደማጥፋት የሚቆጥሩ ወይም የተለያየ ምክንያት የሚሰነዝሩ ሰዎች ቅዱሳት መጻሕፍትን የማንበብ ጠቀሜታ አይታያቸውም” የሐዋርያት በማለት ሥራን በተረጎመበት መጽሐፉ አድንቆ ተናግሯል፡፡


ሐዋርያው ቅዱስ ፊሊጶስም ሲያነበው የነበረውን “እንደ በግ ወደ መታረድ ተነዳ፣ የበግ ጠቦትም በሸላቹ ፊት ዝም እንደሚል እንዲሁ አፉን አልከፈተም። በውርደቱ ፍርዱ ተወገደ። ሕይወቱ ከምድር ተወግዳለችና። ትውሉዱንስ ማን ይናገራል።” የሚለውን በትንቢተ ኢሳይያስ 53÷7 የሚለውን ቃል መነሻ አድርጎ ስለ ጌታችን የሰው ልጅን ማዳንና ፍቅር አስተማረው፡፡ በፈቃዱም አምኖ ተጠመቀ፡፡

ስጋዊ ሃብታችንን የነፍሳችንን ድህነት የምንሰራበት መሳሪያ አድርጎ ሰጥቶናል፡፡ እንደ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ የቅዱሳን መካናትን በረከት ለማግኘት እንትጋ፡፡

በዘመናችንም ቅዱሳን ገዳማውያንና አባቶች ያሉባቸውን ገዳማት እናግዝ፣ በፍጹም ልግስና ከሚያልፈው ገንዘባችን ሰጥተን ከማያልፈው የጸሎታቸውን በረከት እንካፈል፡፡ የቅዱስ ፊሊጶስና የጃንደረባው በረከት ይደርብን!!!

ድጋፍ ለማድረግ:-ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

ኢትዮ መረጃ - NEWS

22 Oct, 14:07


በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ በደረሰው የእሳት አደጋ የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ 33 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ/ም ምሽት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሸማ ተራ ነባር የገበያ ማዕከልና በአካባቢው በአጋጠመ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት የአዲስ አበባ ፖሊስ ከፌዴራል ፖሊስ የፎረንሲክ ምርመራ ቡድን ጋር በመቀናጀት ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።

አደጋውን ለመከላከል እና በአደጋው ምክንያት ሌላ ወንጀል እንዳይፈፀም እንዲሁም የአደጋ ተከላከይ ሰራተኞች ተግባራቸውን በአግባቡ መወጣት እንዲችሉ እና ተጨማሪ ጉዳት እንዳያጋጥም የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የመከላከያ ሠራዊት፣ ሪፐብሊካን ጋርድ፣ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ የሠላምና ፀጥታ መዋቅር፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ሌሎች ተቋማትም ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ አደጋው እንዳይባባስ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል።

አደጋውን እንደ ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ 33 ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን እና ከአደጋው ጋር በተያያዘ በ7 ሰዎች ቀላል በሁለት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

አደጋውን ለመከለከል የፀጥታና ሌሎች ተቋማት እንዲሁም የአካባቢው ህብረተሰብ ላደረገው ድጋፍና ተባባሪነት ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ በደረሰው የእሳት አደጋ የተሰማውን ሃዘን ገልፆ ወደፊት በምርመራ የደረሰበትን ውጤት ለህዝብ እንሚያሳውቅም አስታውቋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news

ኢትዮ መረጃ - NEWS

22 Oct, 10:11


ፎቶ ፦ ' መርካቶ ሸማ ተራ ' ከትላንት ምሽቱ አስከፊና ከባድ የእሳት አደጋ በኃላ ዛሬ ላይ ከላይ በፎቶው የምትመለከቱትን ይመስላል።

ከቆርቆሮ እና ከኮነቴነር ቤቶች አቅራቢያ ወዳለው ' ነባር የገበያ ማዕከል (ህንጻ) ' የተዛመተው እሳት የህንጻውን አንደኛውን ክፍል ክፉኛ አውድሞታል።

እስካሁን ሰው ላይ ስለደረሰ ጉዳት ሪፖርት አልተደረገም።

በትላንት ምሽቱ የእሳት አደጋ ምንም እንኳን ይፋዊ የጉዳት መጠን ባይገለጽም የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ነው።

በርካቶች ብዙ የደከሙበት ንብረታቸው በአንድ ምሽት ወደ አመድነት ተቀይሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፥ " በአደጋው የደረሰውን የጉዳት መጠኑን የተመለከተ ዝርዝር ጥናት ተደርጎ ከባለሃብቶች እና ከህብረተሰቡም ጋር በመሆን በፍጥነት መልሶ የማቋቋም ስራ ይሰራል ፤ ቦታውንም ወደ ቀደመው የንግድ ተግባር እንዲመለስ የማድረግ ስራ እንሰራለን "  ብሏል።

via #tikvahethiopia

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news

ኢትዮ መረጃ - NEWS

22 Oct, 06:59


የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የናይጀሪያ ባለሥልጣናት የሚያካሂዱበትን ስም ማጥፋት የአገሪቱ ፕሬዝዳንት እንዲያስቆሙለት በደብዳቤ መጠየቁን የአገሩቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የናይጀሪያ አየር መንገድ ቢቋቋም ኢትዮጵያዊያን የአዲሱን አየር መንገድ የሃላፊነት ቦታዎች እንዲይዙ ታስቦ እንደነበር፣ የአየር መንገዱ ትርፍ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚሄድና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ታክስ እንደማይከፍል አድርገው የአገሪቱ ሲቪል አቬሽን ሚንስትር የሚያሠራጩት መረጃ እውነታነት እንደሌለው አየር መንገዱ መግለጡን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል።

ሲቢል አቬሽን ሚንስትሩ ለምን ስሙን እንደሚያጠፉ ግልጽ እንዳልኾነለት የጠቀሰው አየር መንገዱ፣ የናይጀሪያ መንግሥት የአገሪቱን አየር መንገድ በጋራ ለማቋቋም በተደረሰበት ስምምነት ላይ ሃሳቡን በመቀየሩ ችግር እንደሌለበት ገልጧል ተብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ49 በመቶ ድርሻ የናይጀሪያ አየር መንገድን ለማቋቋም የደረሰበት ስምምነት መክሸፉ ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news

ኢትዮ መረጃ - NEWS

22 Oct, 04:22


በመርካቶ ሸማ ተራ በተባለ አካባቢ ትናንት ምሽት የተነሳው ከፍተኛ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።

በርካታ የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎችና ሠራተኞች የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር ከአራት ሰዓታት በላይ ከፍተኛ ጥረት እንዳደረጉ የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አባቤ አስታውቀዋል።

ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ገደማ የተነሳውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር የተቻለው፣ ከምሽቱ 5:00 ሰዓት በኋላ እንደነበር ታውቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news

ኢትዮ መረጃ - NEWS

21 Oct, 18:54


የእሳት አደጋው በቪድዮ‼️

ፈጣሪ ይርዳቹ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news

ኢትዮ መረጃ - NEWS

21 Oct, 18:26


በሸማ ተራ የተነሳውን የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ጥረት እየተደረገ ነው

ዛሬ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ማምሻዉን በመርካቶ ሸማተራ አየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በንግድ ሱቆች ላይ የተነሳዉን የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ለማዋል የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቃል የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችና ባለድርሻ አካላት ርብርብ እያደረጉ ነዉ።

አካባቢው የተጨናነቀ እና ለተሽከርካሪ አስቸጋሪ በመሆኑ እሳቱን በፍጥነት ለመቆጣጠር አስቸጋረ አድርጎታል ሲሉ የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ተናግረዋል።

የአደጋ ገዜ ባለሙያዎች እና ተሽከርካሪዎች በስፍራው ከሚገኘው ቅርንጫፍ በተጨማሪ ከሌሎች ቅርንጫፎች መላካቸውን ለማወቅ ችለናል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news

ኢትዮ መረጃ - NEWS

21 Oct, 17:54


የእሳት አደጋ‼️

መርካቶ ሸማ ተራ የእሳት አደጋ ተከክቷል።

በአዲስአበባ መርካቶ ሸማ ተራ ከፍተኛ የሆነ እሳት አደጋ ያጋጠመ ሲሆን እሳቱን ለመቆጣጠር የእሳት አደጋ ሰራተኞች ጨምሮ የአካባቢዉ ህዝብ እየተረባረበ ይገኛል ፡፡

እሳቱ ጠንከር ያለ መሆኑ በስፍራው የሚገኙ ነዋሪዎች ገልፀዋል።

እሳቱ ከተነሳ በርከታ ደቂቃዎች ቢቆጠሩም እስካሁን መቆጣጠር እንዳልተቻለ በስፍራው የሚገኙ የአይን እማኞች ገልጸዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news

ኢትዮ መረጃ - NEWS

21 Oct, 16:35


የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ ላለፉት ሦስት ወራት ከሐምሌ ወር ጀምሮ በተለይ በአማራ ክልል 548 ሺሕ 318 ዜጎች በወባ ወረርሽኝ መያዛቸውን ማስታወቁን ጠቅሶ ሪፖርተር አስነብቧል።

በክልሉ በ2016 በጀት ዓመት ብቻ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች የወባ በሽታ ሕክምና አግኝተዋል ተብሏል፡፡

በክልሉ በ2016 በጀት ዓመት እስከ ሰኔ ወር ድረስ የወባ ሥርጭት በ34 ወረዳዎች መታየቱንና ባለፈው ሳምንት ብቻ 51 ሺሕ 650 ሕሙማን ሕክምና እንዳገኙም ኢንስቲትዩቱ መናገሩን ዘገባው ጠቅሷል።

በክልሉ የጤና ግብዓትን በማሠራጨት ረገድ የከፋ ችግር እንዳላጋጠመው የጠቀሰው ኢንስቲትዩቱ፣ ባለሙያዎችና መድሃኒት የጫኑ ተሽከርካሪዎች በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ ተፋላሚ ወገኖች ትብብር ማድረግ እንዲቀጥሉ መጠየቁንም ዘገባው አመልክቷል።

ወረርሽኙ፣ በደቡብ ኢትዮጵያና ኦሮሚያ ክልሎችም በከፍተኛ ደረጃ በዜጎች ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው ተብሏል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news

ኢትዮ መረጃ - NEWS

21 Oct, 15:25


ኮንትራት በመጥራት ሹፌሮችን በመግደል ተሽከርካሪ ሲሰርቁ የነበሩ አራት ግለሰቦች በሞት እንዲቀጡ ውሳኔ ተላለፈባቸው

በተለያዩ ጊዜያት አሽከርካሪዎችን  ራቅ ወዳለ ስፍራ እየወሰዱ በመግደል ተሽከርካሪዎችን ሲሰርቁ የነበሩ አራት ግለሰቦች በቁጥጥር  ስር ውለው በሞት እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።

በአዲስ አበባ ገላን ክፍለ ከተማ፣ በሳሪስ እንዲሁም በቢሾፍቱ መኖሪያቸውን ያደረጉት ቴዎድሮስ ብርሃኔ እና  እዩኤል ቴዎድሮስ እንዲሁም በሌላ በኩል ተፈሪ ተስፋዬ እና ዩሃንስ አረፋ  የተባሉት ግለሰቦች  ከአዲስ አበባ ቢሾፍቱ በመመላለስ ድርጊቱን ሲፈጽሙ እንደነበር  የሸገር ከተማ አስተዳደር  ዓቃቢ ህግ ጽ/ቤት የተለያዩ ወንጀሎች ምርመራ ዓቃቢ ህግ አቶ ሚዴቅሳ አጋሩ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። አራት ግለሰቦች ከግል ተበዳዮች በኮንትራት በመውሰድ ከዋናው መንገድ ውጪ በማስውጣት የአሽከርካሪዎቹን ህይወት በማጣፋት ተሽከርካሪዎቹን ይዞ በመሰወር  ለተለያዩ ጋራዦች እና  ግለሰቦች በመሸጥ ድርጊቱን ሲፈጽሙ እንደነበር ተገልጿል። ቴዎድሮስ እና እዮኤል የተባሉት ተከሳሾች   ሰለሞን አሊ የተባለ  የጭነት ተሽከርካሪ   አይሱዚ አሽከርካሪን ከዱከም ከተማ እንጨት ትጭንልናለህ  በማለት በኮንትራት ዋጋ  ተስማምተው ወደ ቢሾፍቱ ከተማ ያቀናሉ።

በመቀጠል ወደ ሰንዳፋ  መስመር እንዲሄድ በጦር መሳሪያ በማስገደድ ጨፌዶሳ የተባለ ቦታ  ሲደርስ በሽጉጥ በመምታት ጥለውት ተሽከርካሪውን  ይዘው ተሰውረው ቆይተው እንደሸጡት ተገልጿል ። በሌላ በኩል ተፈሪ ተስፋዬ እና ዩሃንስ አረፋ  የተባሉት የሁለተኛው የወንጀል ቡድን አባላት ደግሞ አቶ  ከበደ በለው የተባሉ ነዋሪነታቸው  አዲስ አበባ  አቃቂ አካባቢ  የሆኑ እና ሃይሩፍ የህዝብ ማመላለሻ  ሚኒባስ  ከአዲስ አበባ አሰላ በማሽከርከር የሚተዳደሩ ሲሆን  ከቦሌ አውሮፕላን  ማረፊያ  ሰው እናመጣለን በማለት  ከወሰዷቸው በኋላ በመሳሪያ በማስገደድ  ወደ ገላን ከተማ በመውሰድ በገመድ አንቀው በመግደል ተሽከርካሪውን  በጎሮ በኩል  ገላን ከተማ በመውሰድ አንዶዴ የተባለው ቦታ  አስከሬኑን ጥለው መሰወራቸውን ዓቃቢ ህጉ ገልፀዋል።በተመሳሳይ  የሜትር ታክሲ አሽከርካሪው ሚኪያስ ተስፋዬ የተባለ የ28 ዓመት ወጣት   እየኤል ቴዎድሮስ የተባለው ማታ ላይ  ደውሎለት ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ  የምንቀበለው  እንግዳ አለ  በማለት ምሽት ላይ ቢሾፍቱ ከተማ በተከራዩበት ቤት በመውሰድ በሽጉጥ መግደላቸውን  የፖሊስ ማስረጃ አረጋግጧል።

ፖሊስ ባደረገው ክትትል ቴዎድሮስ ብርሃኔ  እና  እዮኤል ቴዎድሮስ በቁጥጥር  ስር  በማዋል  የምርመራ ሂደቱ ሲያጣራ የቆየ ሲሆን በዚህም ሰለሞን የተባለው አሽከርሪውን ገለው ጫካ ውስጥ መጣላቸውን  የጭነት  ተሽከርካሪውን በ700ሺህ ብር  መሸጣቸውን  ለፖሊስ መርተው  አሳይተዋል። በመቀጠል  ሚኪያስ  ተስፋየ የተባለውን አሽከርካሪ ገድለው እንደጣሉት እና  ኮሮላ ተሽከርካሪውን   የደበቁበትን ቦታ ለፖሊስ ይጠቁማሉ። ፖሊስ ምርመራውን በመቀጠል  የአቶ ከበደ ገዳዮችን ለመያዝ  ባደረገው  ክትትል አዲስ አበባ ሳሪስ  ዶሮ ተራ ከሚባል ስፍራ በመያዝ  በሁለቱም ግለሰቦች ላይ ጥልቅ ምርመራ በማድረግ ሃይሩፍ ተሽከርካሪውን እንዲፈታታ በማድረግ  ለመሸጥ ሲሞከር  በቁጥጥር  ስር ለማዋለወ ተችሏል ።  በመሆኑም  ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን በማጠናቀቅ  ለዓቃቢ ህግ ይልካል።

ዓቃቢ ህግ ከፖሊስ የደረሰውን የምርመራ መዝገብ  በመመልከት  ተከሳሾች በመደራጀት የጦር መሳሪያ  በመታጠቅ በአሰቃቂ ሁኔታ  የሰው መግደል ወንጀል  መፈጸማቸውን በመጥቀስ  በወንጀል ህግ 530 መሰረት ክስ መስርቷል። በዓቃቢ ህግ የተመሰረተውን  ክስ የተመለከተው የሸገር  ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራቱም ተከሳሾች  የፈጸሙት የወንጀል  ድርጊት  በመመልከት  ከባድ እና አደገኛ  በመሆኑ  የቅጣት ማክበጃ በመጥቀስ  በአራቱም ተከሳሾች ላይ በሞት እንዲቀጡ  ውሳኔ አስተላልፏል። በተጨማሪም ተሽከርካሪዎች  የደበቁ  አራት ግለሰቦች  በእስራት እና  በገንዘብ እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ማስተላለፉን የሸገር ከተማ አስተዳደር  ዓቃቢ ህግ ጽ/ቤት የተለያዩ ወንጀሎች ምርመራ ዓቃቢ ህግ  አቶ ሚዴቅሳ አጋሩ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።(Bisrat)

@sheger_press
@sheger_press