@Banchi Abera ከሰበታ💚💛

@crayfista


እግርኳስና ስፖርታዊ ጉዳዮች ይዳሰስበታል⚽️🇪🇹

@Banchi Abera ከሰበታ💚💛

11 Oct, 10:58


ኤንዞ ማሬስካ እና ኮል ፓልመር የወሩ ምርጥ ተጫዋችና አሰልጣኝ ተብለው ተመርጠዋል። ባሳዩት ነገር ሁለቱም ይገባቸዋል።👏👏👏💙

@Banchi Abera ከሰበታ💚💛

04 Oct, 15:48


ለማንኛው ሁሉም ነገር ተቋጭቷል! በኦሮሞ ባህል በአባገዳዎች በኢሬቻ ዋዜማ ሰላም ወርዷል እርቅ ተፈፅሟል። ኃይሌ ገብረስላሴ ትልቁን ድርሻ ይወስዳል። የሁለቱም ምርጥ ወንድምና ጓደኛ👏👏👏

📷 #Haile

@Banchi Abera ከሰበታ💚💛

22 Sep, 18:34


ከዚህ በላይ መለወጥ ከየትም ልታሳይ አትችልም። አርሰናል በትክክል ተለውጧል በቃ ይሄ ቡድን የሚቀረው ዋንጫ ብቻ ነው አለቀ። ላትወደው ትችላለህ ላደግፍ ትችላለህ ያለማድነቅ ግን ንፉግነት ነው። ማሸነፍ አይደለም ነጥብ መጋራት ብርቅ በሆነበት ኢትሀድ አምና ተጋርቶ አሳየ ዛሬ ደግሞ በሽርፍራፊ ሰከንዶች ተአምር ከሦስት ነጥብ ወደ አንድ ነጥብ ተሸጋገረ የሲቲ እስከመጨረሻ ደቂቃ ተጋድሎ ቢሆንም አርሰናልን ያለማድነቅ ከባድ ነው።

አራቱንም ጨዋታዎች ያሸነፈ አራት ተከታታይ አመት ሻምፒዮን የሆነ ያውም ደግሞ ኢትሀድ ላይ በተጨማሪ ሁለተኛ አጋማሽ በ10 ተጫዋች ገጥሞ አንድ ነጥብ የምር ያስጨበጭባል። አለም ተገልብጣ የእግርኳስ ጠላት የተባለውን the special one ማስደነቅ ስለጀመረች ደስ ብሎኛል። ስለዚህ ዛሬ አርሰናል አንድ ነጥብ አገኘ ሳይሆን እንደኔ ሁለት ነጥብ ጣለ ብያለው።

ያው የዲብርያን ያለመኖርና የሮድሪ በጊዜ ተጎድቶ ከሜዳ መውጣት ሲቲን ቢያጎድለውም በጎዶሎ ተጫዋች ተጫውቶ ነጥብ ይዞ መውጣት የአርቴታ ቡድን ተገንብቶ ማለቁንና በቅርቡ የንግስና ዙፋኑን ከመምህሩ እንደሚቀበል በግልፅ ያሳየ ምሽት ነበር። በኳስ ቁጥጥር በምናምን ምናምን ሲቲ ድብን አድርጎ በልጧል ውጤቱ ግን 2ለ2 አንድ አንድ ነጥብ ተጋርተዋል።

አርቴታ ግን ስለ ዋንጫ ፍክክር ካሰበ ተጫዋቾቹ መብሰልና በአይምሮ ማደግ እንዳለባቸው ማስተማር አለበት። አንዱ ከአንዱ ስህተት የማይማር ከሆነ ስለ መጠረሻው ሳቅ ማሰብ ከንቱ ድካም ነው የሚሆነው።

@Banchi Abera ከሰበታ💚💛

21 Sep, 13:53


ዘንድሮ ይታያል የተባለው ኮል ፓልመር በአምስት ጨዋታ ሁለት ጎል አራት አሲስት በመብሰል ሂደት ላይ የሚገኘው ኒኮላስ ጃክሰን አራት ጎል ሁለት አሲስት ተገፍቶ የመጣው ሳንቾ በሁለት ጨዋታ ሁለት አሲስት 💪🔥

ቼልሲ በደርቢ ጨዋታ ዌስተሀም ዩናይትድን ከጨዋታ ብልጫ ጋር 3-0 መርታት ችሏል። ከድሉ በላይ የዛሬው ቼልሲ በጣም የተረጋጋ የሚናበብ በኳስ ቁጥጥሩም የተሻለ ነበር። ቀጣይ በሚኖሩትም ጨዋታ በተመሳሳይ ማስቀጠል ከቻለ ትልቅ ለውጥ ይኖራል። በፎፋና over ኮምፊደንስ ደስ አይለኝም ያስበላል። የዛሬው ቼልሲ ምንም እንከን የማይወጣለት ምርጥ ነበር!!!🔥 Congra💙 London is always blue💙💙💙🚶‍♀️🚶‍♀️🚶‍♀️