ATC NEWS

@atc_news


#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA
ለመልዕክት 👇🏻
@mujaabot

For Advertisement👇🏿
@atcads

ATC NEWS (Amharic)

አሁን ከተሻለ በኋላ ከመልዕክት ማንኛውን መረጃዎች አንዳንድ ሰዎች መረጃ ይዘምሩት? ላይክ ብቻዎትን ATC NEWS ተመልከቱ! ይህ ቡድን የሚሆነው መሰረታዊ ውይይት መረጃና ተጨማሪ መግለጫዎችን በአስፋላ እንዴት መመለስ እንደሆነ ማቅረብ ይችላል። ATC NEWS ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያውያንን እና በአፍሪካ እንዴት ያልተሳካከው መረጃ እንደሆነ እንዲልቅም ምንም አናውቅም እናንተም አስከፊልአለሁ! ጥሩ ቅርብ መረጃዎችን ማቀርበያ በሚችል ታስቦ ሊሆንኩት ነው። በተጨማሪ፣ በዚህ በኋላ በአፍሪካ እንዴት ያልተሳካከው መረጃዎችን መረጃ ማስከበስ ለድምጹ ፕሮሌክስ ለማሳየቱ በፊት እንጠቀማለን። ከታች ያሉትን መሰረታዊ ውይይቶች ለመታየት ለማሳየት የቡድንህን በርካታ ቦታ በኢትዮጵያ ለማየት ብቻ ከመንገድ እና ስራ ማህበራዊ ሰውነቱን እንዴት በማስገባት እንደሆነ ለምን ማዋል እንደሚረዳት ብዬ መረጃዎችን ለመስጠት ሊደርስ ነው።

ATC NEWS

22 Oct, 07:57


#ጥቆማ

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ለ2017 ትምህርት ዘመን በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ሰልጣኞችን መመዝገብ ጀምሯል፡፡

መስፈርቶች
▪️የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ የሆነ/የሆነች፣
▪️በ2015/16 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የማለፊያ ውጤት (50%) ያለው/ያላት፣
▪️በ2014/15 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተከታትለው ያጠናቀቁ

ስልጠናው በአዲስ አበባ ላምበረት መናኸሪያ አካባቢ በሚገኘው የኢንስቲትዩቱ ግቢ የሚሰጥ ሲሆን፤ በተጨማሪም የቻይንኛ እና ኮሪያኛ ስልጠናዎች ይሰጣሉ፡፡ ኢንስቲትዩቱ የምግብ እና የዶርም አገልግሎቶች ያቀርባል፡፡

የምዝገባ ጊዜ፦
ጥቅምት 11-15/2017 ዓ.ም
የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ፦
ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም
ትምህርት የሚጀምረው፦
ኅዳር 2/2017 ዓ.ም

አስፈላጊ ሰነዶች
▪️ የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት
▪️ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሰርተፊኬት
▪️ የሪሚዲያል ፕሮግራም ሰርተፊኬት


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC NEWS

22 Oct, 04:42


የመርካቶው የእሳት አደጋ አሁናዊ ሁኔታ ከቦታው

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC NEWS

21 Oct, 20:58


በዛሬው የእሳት አደጋ ይህ ህንፃ ነው ለረጅም ሰዓታት ሲነድ የቆየው

የእሳት አደጋው በርካታ የንግድ ሱቆችን ሙሉ ለሙሉ ያወደመ ሲሆን በሰው እና በንብረት ላይ ስላደረሰው ዝርዝር አደጋ በመንግስት ተጣርቶ ሲገለፅ የምናደርሳቹህ ይሆናል።


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC NEWS

21 Oct, 20:41


የእሳት አደጋው አሁናዊ ሁኔታ(ከቦታው )

አሁን ላይ እሳቱ በቁጥጥር ስር ውሏል‼️

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC NEWS

21 Oct, 20:37


መርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል።

መርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል፡፡

ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው፣ የእሳት አደጋዉን በቁጥጥር ስር በማዋል ርብርብ ላደረጉ፤ በርካታ ሎጀስትክ በማቅረብ የደገፉ እና ከዚህ በላይ ሊደርስ የነበረዉን ጉዳት የቀነሱ አካላትን አመስግነዋል፡፡

በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳትና መንስኤዉን በማጣራት ቀጣይ ለህብረተሰቡ የምናሳዉቅ ይሆናልም ብለዋል፡፡

ህብረተሰቡ መሰል አደጋዎች እንዳይከሰቱ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግም አሳስበዋል፡፡


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC NEWS

21 Oct, 20:28


#Update

ምሽት 1 ሰዓት አካባቢ በመርካቶ ሸማ ተራ የተነሳውን እሳት እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ስር ማዋል አልተቻለም።

ርብርቡ ግን እንደቀጠለ መሆኑ ተሰምቷል።

የአዲስ አበባ እሣትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍሬ ግዛው ምን አሉ ?

- የእሳት አደጋው የተከሰተው 1 ሰዓት ገደማ ነው።

- እሳት መነሳቱን በሰማን ጊዜ አብዛኛዎቹ የእሳት ማጥፊያ መኪናዎች ርብርብ እንዲያደርጉ አሰማርተናል።

- መኪናዎች በወቅቱ ነበር የደረሱት፤ ከደረሱ በኃላ የእሳቱ ባህሪና ሁኔታ ሲታይ ለሌሎች አጋዥ አካላት ፦
° አየር መንገድ
° ፌዴራል ፖሊስ
° ሌሎች ከተማ ውስጥ ያሉ ውሃ አቅራቢ ተቋማት በሙሉ እንዲረባረቡ ተደርጎ እሳቱን ለማጥፋት ጥረት እያደረግን ነው።

- ቦታው በጣም አስቸጋሪ ነው።

- በሁሉም አቅጣጫ በኩል መኪና ገብቶ እሳቱን ለማጥፋት በጣም ፈትኖናል። በተለይ በዙሪያ የሚቀመጡ እቃዎች ቶሎ ተገብቶ የእሳቱን መሰረት እንዳይመታ አድርጓል።

- አካባቢው በቆርቆሮ የተያያዘ ነው። መንገዱ በጣም ጠባብ ነው። ገብተን ለማጥፋት ተቸግረናል።

- በአጋጣሚ ባለሱቆች፣ ነጋዴዎች ዘግተው ወጥተው ነበር። የቆሙ መኪኖችንም ለማስነሳት ችግር ሆኖብን ነበር።

- አሁን ላይ ከቅድሙ እየተሻሻለ ነው። የመቀነስ እና የመጥፋት አዝማሚያ አለው። በተለይ ከዚህ እንዳይሰፋ ወደታች ከወረደ በጣም ሰፊ ቦታ ነው ያለው ቆርቆሮ በቆርቆሮ እሱ ጋር እንዳይደርስ ከበን ለመያዝ ሞክረናል።

- አጋዦች ከመጡ በኃላ እሳቱ ባህሪው እንዳይሰፋ ተሞክሯል። አሁንም ህብረተሰቡ አግዞን ለማጥፋት እየሞከርን ነው። እናጠፋዋለን ብለን እናምናለን።

#AMN #TIKVAH
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC NEWS

21 Oct, 19:27


#Update

1 ሰዓት ላይ የጀመረዉን የእሳት አደጋ እስካሁን
መቆጣጠር አልተቻለም‼️


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC NEWS

21 Oct, 18:28


የእሳት አደጋው አሁንም በቁጥጥር ስር አልዋለም 😢


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC NEWS

21 Oct, 17:31


#Update

በመርካቶ ' ሸማ ተራ ' የተነሳው እሳት እስካሁን ሊጠፋ አልቻለም።

እሳቱን ለመቆጣጠር ርብርብ እየተደረገ ቢሆንም ከእሳቱ መፋፋምና ከቦታው አለመመቸት የተነሳ ሁኔታውን እንዳከበደው በስፍራው የሚገኙ የቤተሰባችን አባላት ጠቁመዋል።

እሳቱ ያልደረሰባቸው ሱቆች እቃቸውን ከስፍራው እያሸሹ ናቸው።

እስካሁን የጉዳቱ መጠን ምን ያህል እንደሆነ ባይታወቀም በርከት ያሉ ሱቆች ግን እየተቃጠሉ ናቸው።


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC NEWS

21 Oct, 17:09


" እሳቱ ጠንከር ያለ ነው ፤ እስካሁን አልጠፋም ፤ ሰው ንብረት እያሸሸ ነው " - በስፍራው የሚገኙ ሰዎች

በአዲስ አበባ መርካቶ ሸማ ተራ የእሳት አደጋ ተከስቷል።

እሳቱ ከተነሳ በርከታ ደቂቃዎች ቢቆጠሩም እስካሁን መቆጣጠር እንዳልተቻለ በስፍራው የሚገኙ የቤተሰባችን አባላት ገልጸዋል።

" እሳቱ ጠንከር ያለ ነው ፤ በስፍራው እሳት አደጋዎች ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ ቢሆንም ምንም ሊጠፋ አልቻለም። በስፍራው ላሉ የአደጋ ሰራተኞች ተጨማሪ ቦቴና እገዛ ያስፈልጋል ፤ በውሃ ብቻም የሚሆን አይደለም " ብለዋል።

" በአካባቢው ያሉ እሳቱ ያልደረሰባቸው ሰዎች ንብረታቸውን እያሸሹ ይገኛሉ " ሲሉም አክለዋል።


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC NEWS

21 Oct, 16:48


#FireAlert 🔥

መርካቶ ሸማ ተራ የእሳት አደጋ ተከስቷል። የእሳት አደጋ ሰራተኞች በቦታው መድረሳቸውንና እሳቱን ለማጥፋት በጥረት ላይ ይገኛሉ ተብሏል።


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news