Top Students

@top_students1


👌ለፈጣን_እና_ታማኝ_መረጃ

"
#በትምህርት_ዓለም_ትናንትም_ነገም_ዛሬ_ነው_ስለዚህ_ዛሬውኑ_አቅደህ_ተነስ"


ለአስተያየት / ለማስታወቂያ
@mulea27

Top Students (Amharic)

በተከታታይ የስልጠና ቅኝት ውስጥ የትምህርት ትናንትን እንዲያሳድር የTop Students ቻናል ተማሪዎች እና ተነስታኞች በትምህርት ዓለም ያሉበላይ የትምህርት መረጃዎችን ማሳጃር ይችላሉ። የትምህርት ዓለም ትናንትም ነገም ዛሬ ለማንኛውም ዓለም ተካሄደ ከመሆኑ ዛሬውን እና በንሱ ተዘጋጁ። የትምህርት ዓለም ለጠየቅ ለማስታወቂያና ለተማሪዎች የሚሰራ ቻናል ነው። በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ የትምህርት መረጃዎችን ለመለያየት ይጻፍበታል። እናመሠረቱ፣ @mulea27 ተመልክተዋል።

Top Students

21 Oct, 13:29


#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምደባ በቅርቡ እንደሚገለጽ አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ፤ " በ2016 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ምደባ በቅርቡ ይገለጸል " ብሏል።

ተማሪዎች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጥሪ አቅርቧል።

#share
#share

https://t.me/top_students1
https://t.me/top_students1

Top Students

21 Oct, 12:30


🔺#ተከፈተ💻

🔸2017 Freshman Discussion  groups.

🔺ባለፈው ዓመት ሬሜዲያል ተምራችሁ ወደ ፍሬሽማን የተቀላቀላችሁ እንዲሁም በዚህ ዓመት 12ኛ ክፍል ተፈትናችሁ Universty የደረሳችሁ ተማሪዎች(ያላያችሁ Officially MOE ሲገልፅ ገብታችሁ ትወያያላችሁ) ያያችሁ በየግሩፖቻችሁ ገብታችሁ መተዋወቅ ይኖርባቹሃል። ትውውቃችሁን ግቢ ሳትገቡ በቴሌግራም ከጨረሳችሁ  ትምህርቱን በአንድነት ትወጣላችሁ❗️

🔸ስለጉዞ መረጃ :ግቢም ከገባችሁ በኋላ ፋይል ለመለዋወጥ እንዲሁም የፍረሽማን የሚድና ፋይናል ሁሉንም በአንድ  ለመለዋወጥ እጅግ በጣም አስፈላጊ 🔸

አስታዉሱ :መረጃ  የዩኒቨርስቲ ቆይታችሁ ስኬታማነት ከሚወስንባቸው ነገሮች አንዱና ዋነኛዉ ነው ❗️

🔹ለሁሉም ጓደኞቻችሁ ሼር
አድርጉላቸው
🔻


💠 Addis ababa university
https://t.me/AAUfreshmen_2017

💠 Arba Minch University
https://t.me/Amufreshman2017

💠Bahirdar University.
https://t.me/BDUFreshman2017

💠  University of Gondar
https://t.me/UOGFreshman2017

💠Hawassa University
https://t.me/HawasaFreshman2017

💠Haramaya University
https://t.me/HAU_Freshman_2017
 💠Jimma University
https://t.me/Jufreshman2017

💠Dire dawa University
https://t.me/DDUFreshman2017

💠Debra Markos University
https://t.me/DmuFreshman2017

💠Debreberhan University
https://t.me/DBUFreshman2017

💠Wollo University
https://t.me/WOU_Freshman2017

💠Ambo University
https://t.me/AmboFreshman2017

💠Wolkite University
https://t.me/WkuFreshman_2017

💠Wolayita sodo University
https://t.me/WSUFreshman2017
 
💠Wachamo University
https://t.me/Wachufreshman2017

 💠Arsi University6
https://t.me/Aufreshman2017

💠Bulehora  University
https://t.me/BHU_Freshman2017

💠Jigjiga University
https://t.me/JJU_Freshman2017

💠MEKELE UNIVERSITY
https://t.me/Mufreshman2017

💠AASTU
https://t.me/AASTU_Freshman2017

💠ASTU
https://t.me/ASTU_Freshmen2017

💠ASOSA UNIVERSITY
https://t.me/Assosa_freshman2017

💠Worabe University
https://t.me/Wru_Freshman2017

💠SELALE UNIVERSITY
https://t.me/Slu_Freshman2017

💠Madda welabo University
https://t.me/MedaWulabuFreshman_2017

💠Dilla University
https://t.me/DuFreshman2017

💠Adigrat University
https://t.me/AdigratFreshman2017

💠Axum University https://t.me/AxumFreshman2017

💠Mizan Tepi University
https://t.me/MizanTepi_Freshman2017

💠Semera University
https://t.me/Semera_Uni_Freshman2017

💠All other Universities
https://t.me/Universty_Freshman2017

Top Students

21 Oct, 10:26


የ2017 የቴክኒክና ሙያ የመደበኛ ስልጠና ዘመን መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆኗል።

የተፈጥሮ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት !

🟢 የስልጠና ደረጃ 1 እና 2

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 141 እና ከዚያ በታች፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 137 እና ከዚያ በታች፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 138 እና ከዚያ በታች፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 134 እና ከዚያ በታች፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 124 እና ከዚያ በታች፤

🟡 የስልጠና ደረጀ 3 እና 4 ፦

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 142 እና ከዚያ በላይ፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 138 እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 139 እና እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 135 እና ከዚያ በላይ፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 125 እና ከዚያ በላይ፤

🔴 የስልጠና ደረጀ 5 ፦

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 179 እና ከዚያ በላይ፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 167 እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 170 እና እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 162 እና ከዚያ በላይ፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 154 እና ከዚያ በላይ፤

⬇️

የማህበራዊ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት !

🟢 የስልጠና ደረጃ 1 እና 2

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 139 ከዚያ በታች፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 135 እና ከዚያ በታች፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 134 እና ከዚያ በታች፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 124 እና ከዚያ በታች፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 124 እና ከዚያ በታች፤

🟡 የስልጠና ደረጀ 3 እና 4 ፦

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 140 ከዚያ በላይ፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 136 እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 135 እና እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 125 እና ከዚያ በላይ፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 125 እና ከዚያ በላይ፤

🔴 የስልጠና ደረጀ 5 ፦

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 172 ከዚያ በላይ፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 164 እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 165 እና እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 160 እና ከዚያ በላይ፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 154 እና ከዚያ በላይ፤

https://t.me/top_students1
https://t.me/top_students1

Top Students

21 Oct, 05:44


Physics

📝Mid exam

for freshman student's

➡️different universities


 
https://t.me/+XB6r-VdV0lpiMGZk ❤️

Top Students

20 Oct, 16:08


🎓MGW 2017 Freshman Tutorial and Exam Practice  🙌

ለመሆኑ ክላሱ ለማን ያገለግላል ?

✍️በ2017 Freshman ለሚጀምሩ ተማሪዎች በሙሉ ፤ ለተፈጥሮ ሳይንስና ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በሙሉ☺️

ምን ምን ኮርሶች ይሰጣሉ ?

Natural Science Freshman Courses List for Our Tutorial.

Logic and critical thinking
Psychology
Geography
C.English
Freshman Mathematics
Physics
Emerging Technology

Freshman Social Science Courses given at our classes:

Logic and Critical thinking
Psychology
Civics and Moral education
Global Trends
Entrepreneurship
Economics
Geography
Communicative English

ተማሪዎች ለቲቶሪያል ቢመዘገቡ ምን ጥቅም ያገኛሉ ?

💻 Freshman አሪፍ Grade ሰርተው የሚፈልጉት Department እንዲገቡ በማስቻል ረገድ የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል ፤  ሴሜስተሩን ሙሉ እኛጋር ናችሁ 🤗

የቲቶሪያል ክፍያ ስንትብር ነው  ?

200ብር ብቻ😊፤ ዛሬ በ200ብር ምንም አይገኝም ነገር ግን ከተማሪዎቻችን በላይ ሌላ ትልቅ ክብር የለንም ።

ክፍያ በየወሩ ነው ወይስ እንድጊዜ ብቻ ?

ለፍረሽማን Course ክፍያ አንድጊዜ 200ብር ብቻ ሲሆን ፤ ሌላ ተጨማሪ ድጋሚ ክፍያ የለም 🟩

ኑ...ተቀላቀሉን ❗️

🟥ለFreshman ምዝገባ 👇
@MGW_Freshman_Reg_Bot

🫧ስለቱቶሪያል ለመጠየቅ
📞0704282565
📞0906014772

🟥ባለፈው ዓመት ከነበረን በውጤት የታጀበ ቆይታ በጥቂቱ👇
https://t.me/medicalgateway1

ይቀላቀሉን 👇
https://t.me/+kEB9-ojwbeQ3YmNk
https://t.me/+kEB9-ojwbeQ3YmNk

Top Students

20 Oct, 05:34


የማስታወስ ችሎታዎን ለማሻሻል 11 ዘዴዎች

የሚከተሉት 11 በጥናት የተረጋገጡ ስልቶች የማስታወስ ችሎታን በብቃት ሊያሻሽሉ፣ ማስታወስን ሊያሳድጉ እና መረጃን ማቆየት ሊጨምሩ ይችላሉ።

1. ትኩረትዎን ይስጡ

➤ ትኩረት ከማስታወስ ዋና ዋና ክፍሎች አንዱ ነው. መረጃ ከአጭር ጊዜ ማህደረ ትውስታ ወደ የረጅም ጊዜ ማህደረ ትውስታዎ እንዲሸጋገር ፣ ይህንን መረጃ በንቃት መከታተል ያስፈልግዎታል። እንደ ቴሌቪዥን፣ ሙዚቃ እና ሌሎች ትኩረትን የሚከፋፍሉ ነገሮች በሌሉበት ቦታ ያጥኑ::

2. መጨናነቅን ያስወግዱ

➤ ቁሳቁሶችን በበርካታ ክፍለ ጊዜዎች ማጥናት መረጃን በበቂ ሁኔታ ለማስኬድ የሚያስፈልግዎትን ጊዜ ይሰጥዎታል። ጥናቶች በተከታታይ እንደሚያሳዩት በመደበኛነት የሚያጠኑ ተማሪዎች በአንድ የማራቶን ክፍለ ጊዜ ትምህርታቸውን ከሚከታተሉት በተሻለ ሁኔታ ትምህርቱን ያስታውሳሉ።

3. መዋቅር እና ማደራጀት

➤ ተመራማሪዎች መረጃ በማህደረ ትውስታ ውስጥ በተዛማጅ ስብስቦች ውስጥ የተደራጁ መሆናቸውን ደርሰውበታል::ተመሳሳይ ጽንሰ-ሀሳቦችን እና ቃላትን አንድ ላይ ለመቧደን ይሞክሩ::

4. ምኒሞኒክ መሳሪያዎችን ይጠቀሙ

➤ የማስታወሻ መሳሪያዎች ብዙውን ጊዜ ተማሪዎች ለማስታወስ የሚረዱ ዘዴዎች ናቸው። ምኒሞኒክ በቀላሉ መረጃን ለማስታወስ መንገድ ነው። ለምሳሌ፣ ማስታወስ ያለብዎትን ቃል እርስዎ ከሚያውቁት የተለመደ ነገር ጋር ሊያያይዙት ይችላሉ።

5. ይግለጹ እና ይለማመዱ

በጣም ውጤታማ ከሆኑ የኢኮዲንግ ቴክኒኮች አንዱ ገላጭ ልምምድ በመባል ይታወቃል።የዚህ ዘዴ ምሳሌ የአንድ ቁልፍ ቃል ፍቺን ማንበብ, የቃሉን ፍቺ ማጥናት እና ከዚያም ይህ ቃል ምን ማለት እንደሆነ የበለጠ ዝርዝር መግለጫ ማንበብ ነው.

6. ጽንሰ-ሐሳቦችን በዓይነ ሕሊናህ ተመልከት

➤ ብዙ ሰዎች የሚያጠኑትን መረጃ በዓይነ ሕሊናቸው በማየት በእጅጉ ይጠቀማሉ። በመማሪያ መጽሐፍትዎ ውስጥ ላሉ ፎቶግራፎች፣እና ሌሎች ግራፊክሶች ትኩረት ይስጡ። በማስታወሻዎችዎ ጠርዝ ላይ ገበታዎችን ወይም ምስሎችን ይሳሉ ወይም ተዛማጅ ሀሳቦችን በጽሑፍ የጥናት ማቴሪያሎችዎ ውስጥ ለመቧደን በተለያየ ቀለም ያጌጡ ወይም እስክሪብቶችን ይጠቀሙ።

7. አዲስ መረጃን አስቀድመው ከሚያውቋቸው ነገሮች ጋር ያገናኙ

➤ የማታውቀውን ነገር በምታጠናበት ጊዜ ይህ መረጃ ከምታውቀው ነገር ጋር እንዴት እንደሚዛመድ ለማሰብ ጊዜ ወስደህ አስብ።

8. ጮክ ብለህ አንብብ

➤ ጮክ ብለው ማንበብ የማስታወስ ችሎታዎን በእጅጉ ያሻሽላል። አስተማሪዎች እና የሥነ ልቦና ባለሙያዎች ተማሪዎች በእውነቱ አዲስ ጽንሰ-ሀሳቦችን ለሌሎች እንዲያስተምሩ ማድረጉ ግንዛቤን እና ትውስታን እንደሚያሳድግ ደርሰውበታል።

9. ለአስቸጋሪ መረጃ ተጨማሪ ትኩረት ይስጡ

➤ ከመካከለኛ መረጃን ማስታወስ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ ይህንን መረጃ በመለማመድ ተጨማሪ ጊዜ በማጥፋት ይህንን ችግር ማሸነፍ ይችላሉ። በተለይ አስቸጋሪ የሆነ ፅንሰ-ሀሳብ ሲያጋጥሙ፣ መረጃውን ለማስታወስ የተወሰነ ተጨማሪ ጊዜ ይውሰዱ።

10. የጥናት መደበኛ ስራዎን ይቀይሩ

የማስታወስ ችሎታዎን ለመጨመር ሌላው ጥሩ መንገድ የጥናትዎን መደበኛነት መለወጥ ነው። በአንድ የተወሰነ ቦታ ማጥናት ከለመዱ በሚቀጥለው የጥናት ክፍለ ጊዜ ወደ ሌላ ቦታ ለመሄድ ይሞክሩ።

11. እንቅልፍ ያግኙ

አዲስ ነገር ከተማሩ በኋላ ትንሽ መተኛት በፍጥነት እንዲማሩ እና በደንብ እንዲያስታውሱ እንደሚያግዝ ጥናቶች አረጋግጠዋል። ስለዚህ ካጠኑ በኋላ ጥሩ እንቅልፍ ለመተኛት ያስቡበት።


#share
#share

https://t.me/top_students1
https://t.me/top_students1

Top Students

19 Oct, 16:28


🎓MGW 2017 Freshman Tutorial and Exam Practice  🙌

ለመሆኑ ክላሱ ለማን ያገለግላል ?

✍️በ2017 Freshman ለሚጀምሩ ተማሪዎች በሙሉ ፤ ለተፈጥሮ ሳይንስና ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በሙሉ☺️

ምን ምን ኮርሶች ይሰጣሉ ?

Natural Science Freshman Courses List for Our Tutorial.

Logic and critical thinking
Psychology
Geography
C.English
Freshman Mathematics
Physics
Emerging Technology

Freshman Social Science Courses given at our classes:

Logic and Critical thinking
Psychology
Civics and Moral education
Global Trends
Entrepreneurship
Economics
Geography
Communicative English

ተማሪዎች ለቲቶሪያል ቢመዘገቡ ምን ጥቅም ያገኛሉ ?

💻 Freshman አሪፍ Grade ሰርተው የሚፈልጉት Department እንዲገቡ በማስቻል ረገድ የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል ፤  ሴሜስተሩን ሙሉ እኛጋር ናችሁ 🤗

የቲቶሪያል ክፍያ ስንትብር ነው  ?

200ብር ብቻ😊፤ ዛሬ በ200ብር ምንም አይገኝም ነገር ግን ከተማሪዎቻችን በላይ ሌላ ትልቅ ክብር የለንም ።

ክፍያ በየወሩ ነው ወይስ እንድጊዜ ብቻ ?

ለፍረሽማን Course ክፍያ አንድጊዜ 200ብር ብቻ ሲሆን ፤ ሌላ ተጨማሪ ድጋሚ ክፍያ የለም 🟩

ኑ...ተቀላቀሉን ❗️

🟥ለFreshman ምዝገባ 👇
@MGW_Freshman_Reg_Bot

🫧ስለቱቶሪያል ለመጠየቅ
📞0704282565
📞0906014772

🟥ባለፈው ዓመት ከነበረን በውጤት የታጀበ ቆይታ በጥቂቱ👇
https://t.me/medicalgateway1

ይቀላቀሉን 👇
https://t.me/+kEB9-ojwbeQ3YmNk
https://t.me/+kEB9-ojwbeQ3YmNk

Top Students

19 Oct, 13:24


📢 ስለ Grade እና Grade አሰራር ትንሽ ነገር እንበላችሁ።

A+ 👉🏾100-90👉🏾4
A   👉🏾89-85 👉🏾4
A-  👉🏾84-80 👉🏾3.75
B+ 👉🏾79-75 👉🏾3.5
B   👉🏾74-70 👉🏾3
B-  👉🏾69-65 👉🏾2.75
C+ 👉🏾64-60 👉🏾2.5
C   👉🏾59-50 👉🏾2
C-  👉🏾49-45 👉🏾1.75
D   👉🏾44-40 👉🏾1
Fx 👉🏾39-35 👉🏾Final Exam ድጋሜ መፈተን ይቻላል። ግን ተመልሶ Fx ከሆነ Fxሱ ወደ F ይለወጣል።

👉🏾 35-0  👉🏾 በሚመጣው ዓመት (Nex Year) Courseን ድጋሜ እንደ አዲስ ይወሰዳል።

📌 የ Grade አሰራር

ሁሉም Grade በ Credit Hour ተባዝቶ ከዛ አንድ ላይ ተደምሮ በሴሚስተሩ ተማሪዉ በወሰደዉ Credit Hour ይካፈላል።
Example

"A" ቢሆን Gradeዱ እና የCourseሱ Credit Hour 5 ቢሆን
4×5=20
If The other course Grade is "A-" and the Credit Hour is 5
3.75×5=18.75
If The third course Grade is "B" and the Credit Hour is 3
3×3=9

So the Grade of this student will be
20+18.75+9=47.75
5+5+3=13 (Credit Hour)
47.75÷13=3.67 or (B+)
ስለዚህ ይሄ ተማሪ በሴሚስተር 3.67 አመጣ ይባላል።

#share
#share

https://t.me/top_students1
https://t.me/top_students1

Top Students

19 Oct, 12:37


#MekelleUniversity

መቐለ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም በግል የሪሚድያል ትምህርት ተከታትላችሁ በ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ዲግሪ ለመማር የሚያስችል ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች ማመልክት እንደምትችሉ ገልጿል፡፡

በመሆኑም በመቐለ ዩኒቨርሲቲ እና በሌሎች የግል እና የመንግስት የትምህርት ተቋማት ተምራችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ የሪሚዲያል ተማሪዎች ከዛሬ ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም በኦንላይን በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ዌብሳይት (e-student.mu.edu.et) ገብታችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል፡፡

የመግቢያ መስፈርት፦
በትምህርት ሚኒስተር የሚሰላ (70%) እና በተማራችሁበት ትምህርት ተቋም የሚሰላ (30%) በድምሩ 50% እና በላይ ውጤት ያስመዘገባችሁ ልትሆኑ ይገባል::


https://t.me/top_students1
https://t.me/top_students1

Top Students

19 Oct, 11:16


#ምርጥ_ምርጥ_አጋዥ_መፅሐፍት

#Top book, Royal book, Modern book, Galaxy book እና extreme book በpdf ለምትፈልጉ ብቻ join አድርጉ::

እዚህ ጋር ይንኩት
Click here

Share it for your friends 🙏

Top Students

19 Oct, 05:43


📢 እንደምን አደራችሁ፣ ዛሬ ወሳኝ በሆነ ርዕስ ላይ የተጻፈ ጹሑፉ ላጋራችሁ ነው፤ ለመሆኑ ፕረዘንቴሽን ላይ የሚፈጠረውን ፍርሀትን እንዴት ማስወገድ እንችላለን

Here it is ...🙌🏾

ፕረዘንቴሽን በትምህርት ሂወታችን ውስጥ ከሚያጋጥሙን ሂደቶችና የመፈተኛ መንገዶች ውስጥ አንዱ ነው።በተለይ በከፍተኛ ትምህርት ላይ መምህራን አሳሳይንመንቶችን፣
ፕሮጀክቶችን፣ የምርምር ስራዎችን እና የመሳሰሉትን ተማሪዎች በክላስ ውስጥ ፕረዘንት እንዲያደርጉ ይጠይቃሉ፡፡
ከትምህርት አለም ውጪም በተለያዮ የስራ ጉዳዮች ላይ ፕረዘንት እንድናደርግ ሊጠበቅብን ይችላል፡፡

ታዲያ በፕረዘንቴሽን ጊዜ የብዙዎች ችግር ፍርሀት ነው፡፡ሰው ፊት ቆሞ የመናገር ፍርሀት፡፡

የፕረዘንቴሽን ፍርሀት የብዙ ሰዎች ችግር ነው፡፡ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት እስከ 80% የሚሆኑት ሰዎች ጋር ያለ ችግር ነው፡፡ በእርግጥ ችግር ነው ተብሎም ሊነሳም አይችል ይሆናል፡፡ ምክንያቱም መምህራንን ጨምሮ የ public speaking ልምድ ያላቸው አርቲስቶች፣ ፓለቲከኞች፣ የሀይማኖት መሪዎች ሁሉ የሚጋሩት common ስሜት ስለሆነ ነው፡፡

ይህ የፕረዘንቴሽን (public speaking) ፍርሀት ጤናማ ስሜት ነው፡፡ የሁሉም ሰው የጋራ ሰሜትና እንዲያውም የራሱ ጥቅሞችም ያሉት ስሜት ነው፡፡ ችግር የሚሆነው ፍርሀቱ በጣም ከበዛና ቅጥ ካጣ ነው፡፡

የሚከተሉት መንገዶች የፕረዘንቴሽንን ፍርሀት ለመቀነስና ውጤታማ ፕረዘንቴሽን ለማድረግ ያግዛሉ፡፡

1. የፕረዘንቴሽን ፍርሀት ጤናማና common ስሜት እንደሆነ መረዳት። Literally ሁሉም ሰው ይፈራል፡፡ ልዮነቱ አንዳንዶች ማኔጅ ያደርጉታል አንዳንዶች አያደርጉትም፡፡ይህ የፍርሀት ስሜት ሊያስደነግጠን ሳይሆን በደንብ እንድንዘጋጅ ሊያመላክተን ይገባል፡፡ፍርሀት ጥቅም አለው፡፡ ይሄውም ባዮሎጂካሊ በሰውነታችን ውስጥ የሆርሞንን መጠን ከፍ በማድረግ የበለጠ ኢነርጂ እንዲኖረን ያደርጋል፡፡

2. ፕረዘንቴሽን ልምምድ (rehearsal )
ፕረዘንቴሽን ልምምድ ይፈልጋል፡፡ ፕረዘንት የምናደርገውን ነገር በደንብ ማወቃችንን፣ ቋንቋችንን፣ ድምፃችንን እንዲሁም ሰአት አጠቃቀማችንን የምናስተካክለው በልምምድ ነው። ፕረዘንት የሚያደርግ ሰው ልክ እንደ መድረክ ተዋናይ ነው፡፡ ፕረዘንቴሽንም በራሱ በተወሰነ መንገድ ትወና ነው፡፡
.
በመሆኑም ማንም ተዋናይ በደንብ ሳይለማመድ መድረክ ላይ እንደማይወጣ ሁሉ ፕረዘንት የሚያደርግ ሰውም በበቂ ሁኔታ ልምምድ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
በምንለማመድበት ጊዜ ጓደኞቻችን ፊት ሊሆን ይችላል ወይም ብቻችንን ቆመን ሰው ፊት እንዳለን በማሰብ መለማመድ ይቻላል፡፡" Practice makes perfect"

3. መረጋጋት፣ እራስን ማረጋጋት

4. በቂ አየር መውሰድ ፣ መተንፈስ

5. ፕረዘንት የምናደርግበትን ቦታና መምህራኑን ቀድሞ ማወቅ፡፡ ይህም ሲባል ፕረዘንት የምናደርግበት ቦታ ቀደም ብለን በመሄድ ማየትና የምንቆምበትን ቦታ ስሜቱን መረዳት ነው፡፡

6. አለባበስን ማስተካከል፡፡ ጥሩ አለባበስ በራስ መተማመንን ይጨምራል፡፡

7. ፕረዘንት የማድረግ ፍላጎትን ማዳበር፣ ይህም ሲባል ፕረዘንቴሽንን እንደ ግዴታ ሳይሆን የሰራነውን ነገር ለሰዎች እንደምናሳይበት እንደ ጥሩ አጋጣሚ መውሰድ፡፡

8. በቂ አረፍት ወስዶ መገኘት

9. ቀደም ብሎ መገኘት (አለማርፈድ)

10. ከመጀመሪያው ውጤታማ ስራ መስራት፡፡ ምክንያቱም የአንዳንዶች የፍርሀት ምንጭ በቂ ስራ ካለመስራትና ካለመዘጋጀት ነው፡፡


©Psychology zone

#share
#share

https://t.me/top_students1
https://t.me/top_students1

Top Students

18 Oct, 16:28


💻Logic and Critical Thinking

እናስታዋውቃችሁ 🥰

Logic ምንድነው ?

🔹የ2017 ዓ.ም Freshman ተማሪ ከሆናችሁ ይሄ ለእናንተ ነው

💠ዘንድሮ አንላቀቅም ከ90+/100 ነው የምታመጡት

📚 ሴሜስተሩን ሙሉ ደስ ብሎን እየተዝናናንም እየተማማርንም ከእኔጋር አብራችሁ ናችሁ 🤗


💻ለFreshman ምዝገባ 👇
@MGW_Freshman_Reg_Bot

🟥ስለቱቶሪያል ለመጠየቅ
📞0704282565
📞0906014772

🔻ባለፈው ዓመት ከነበረን በውጤት የታጀበ ቆይታ በጥቂቱ👇
https://t.me/medicalgateway1

🟥ይቀላቀሉን 👇
https://t.me/+kEB9-ojwbeQ3YmNk
https://t.me/+kEB9-ojwbeQ3YmNk

Top Students

18 Oct, 05:59


👨‍🎓🧑‍🎓የተማሪዎች አይነት (types of learners)

📮ይህ ፅሁፍ ሁሉም የትምህርት ብቃት እንዳለው ነገር ግን የትምህርቱ ዘዴ እና አቀባበላችን እንደሚለያይ
ያሳያል። ለዚህም ይረዳ ዘንድ የተለያዩ አይነት ተማሪዎችን እና የሚቀላቸውን የመማር ዘዴ ማጣጣም ያስፈልጋል።
የራሳችሁ የመማር ምርጫ ከየት እንደሆነ መመርመርም አትርሱ።

🧑‍🎓1— የእይታ ተማሪዎች (Visual learners)

እነዚህ የተማሪ አይነቶች የሚገባቸው መማር በእይታ ሲሆን ነው። ያዩት ነገር እንዲሁ በቃል ከሚነገራቸው
ይልቅ አይረሳቸውም። እነዚህ ተማሪዎች በተግባር ማየት ካልቻሉ በሃሳባቸው እየሳሉ ቢያነቡ በቀላሉ ማስታወስ ይችላሉ።

🧑‍🎓2— የተግባር ተማሪዎች (Kineshetic learners)

እነዚህ በበኩላቸው ራሳቸው በተግባር የሞከሩት ነገር ቶሎ ይገባቸዋል፣ አይረሱትም። ሰው ሲያደርግ ከማየት
በላይ ራሳቸው በማድረግ ይማራሉ። ለነዚህ ወደ ተግባር እየቀየሩ መሞከር ይመከራል።

🧑‍🎓3– የመስማት ተማሪዎች (auditory learners)

እነዚህ አንድን ነገር ከሰሙት በቂያቸው ነው። ብዙ ከማጥናት በላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲያዳምጡ ይመከራሉ። የሰሙትን ነገር ይረዳሉ።

🧑‍🎓4– የጭንቀት ተማሪዎች (Stress learners)

ያስጨነቃቸው ነገር አይረሳቸውም። ተጨናንቀው ግዴታ አውቄ መግባት አለብኝ ካሉ ማን እንደነሱ። ትኩረት
መስጠት እና መጣር ይመከራሉ።

🧑‍🎓5— የመዝናናት ተማሪዎች (Ease learners)

ዘና ፈታ ብለው ያነበቡት እና የተማሩት አይረሳቸውም። እነዚህ ሳይጨናነቁ፣ አእምሯቸውን ዘና አድርገው እና ጥሩ ስሜት ውስጥ ሆነው ቢያነቡ በጣም ውጤታማ ይሆናሉ።

🧑‍🎓6– የፅሁፍ ተማሪዎች (Scrubble learners)

ለየት ባለ መልኩ ትምህርት ወደ አእምሯቸው የሚገባው ሲፅፉት ነው። እንዳልረሳው ብለው ቢፅፋም
ስለማይረሱት ደግመው ላያዩት ይችላሉ። እነዚህ ሲያጠኑ ደጋግመው እንዲፅፉ እና ከጥናት በሗላም ራሳቸውን የሚፈትኑት ያጠኑትን በወረቀት ላይ ደግመው
ለመፃፍ በመሞከር እንዲሆን ይመከራል።

🧑‍🎓7— የእምነት ተማሪዎች (trust learners)

አነዚህ ከሚያምኑት ወይም ከሚያከብሩት አለያም ከባለስልጣን የተሰጠን ትምህርት በጭራሽ አይረሱም። ትምህርቱ ሳይሆን መምህሩ ነው ለነሱ ወሳኙ። ይሄን
ከሆን የተማርነውን ከምናምነው ሰው እንደተነገረ አድርገን እያሰብን ድጋግሞ ከማጥናት የተሻለ ምክር አይኖርም።

🧑‍🎓8— በማስተማር የሚማሩ (teach learners)

እነዚህ አንድን ነገር ካስተማሩት አለቀ—ተመጠጠ ማለት ይቀላል። እና ሁሌም ተማሪ ስለማይገኝ የተወሰነ አንብበው ቀሪውን– ቆም ብሎ፣ ተማሪዎች
እንዳሉ ራስን አሳምኖ፣ ጮክ ብሎ በማስተማር ማጥናት ይመከራል።

🧑‍🎓9— ተመሳሳዩን በመስራት የሚማሩ (copy learners)

ለየት ባለ ሁኔታ ያዩትን ወይንም የተማሩትን ነገር አስመስለው ሲሰሩት አይረሱትም። ያየነውን ነገር ደግመን ሁሉንም ቅደም ተከተል ሳንረሳ አስመስሎ
ለመስራት በመሞከር እንዲያጠኑ ይመከራል።

#ማጠቃለያ፦ አንድ አይነት ዘዴ በመጠቀም የሁሉንም ተማሪዎች የመማር ምርጫ እና ብቃት ማሟላት አይቻልም ::

#share
#share

https://t.me/top_students1
https://t.me/top_students1

Top Students

13 Oct, 12:58


📢 SQ3R የጥናት  ዘዴ

የSQ3R ዘዴ ተማሪዎች ጠቃሚ እውነታዎችን እንዲለዩ እና በመማሪያ መጽሐፋቸው ውስጥ መረጃ እንዲይዙ የሚያግዝ የማንበብ ግንዛቤ ቴክኒክ ነው። SQ3R (ወይም SQRRR) የንባብ ግንዛቤ ሂደት አምስት ደረጃዎችን የሚያመለክት ምህጻረ ቃል ነው። ለበለጠ ቀልጣፋ እና ውጤታማ የጥናት ክፍለ ጊዜ እነዚህን ደረጃዎች ይሞክሩ

✳️ S- Survey የዳሰሳ ጥናት

ሙሉውን መጽሐፍ ከማንበብ ይልቅ የመጀመሪያውን ምዕራፍ በመዝለል እና በማንኛውም አርእስት፣ ንዑስ ርዕሶች፣ ምስሎች ወይም ሌሎች እንደ ገበታዎች ያሉ ጎላ ያሉ ባህሪያት ላይ ማስታወሻ በመያዝ ይጀምሩ።

✳️ Q- Question: ጥያቄ

በምዕራፉ ይዘት ዙሪያ ጥያቄዎችን ይቅረጹ፣ ለምሳሌ፣ ይህ ምዕራፍ ስለ ምንድን ነው? ስለዚህ ጉዳይ አስቀድሜ የማውቀው ነገር ምንድን ነው?

✳️ R-Read; አንብብ

ሙሉውን ምዕራፍ ማንበብ ጀምር እና ለቀረጻካቸው ጥያቄዎች መልስ ፈልግ።

✳️ R-Recite

አንድን ክፍል ካነበቡ በኋላ ያነበቡትን በራስዎ ቃላት ያጠቃልሉት። ዋና ዋና ነጥቦችን ለማስታወስ እና ለመለየት ይሞክሩ እና ከሁለተኛው ደረጃ ማንኛውንም ጥያቄዎች ይመልሱ።

✳️ R-Review ግምገማ

ምዕራፉን ከጨረሱ በኋላ ሙሉ በሙሉ ለመረዳት ጽሑፉን መከለስ አስፈላጊ ነው. በፈጠሯቸው ጥያቄዎች እራስዎን ይጠይቁ እና የሚፈልጉትን ማንኛውንም ክፍል እንደገና ያንብቡ።

ከወደዳችሁት Reaction 👍🏾


#share
#share

https://t.me/top_students1
https://t.me/top_students1

Top Students

12 Oct, 11:14


#BuleHoraUniversity

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለነባር መደበኛ እና ለ2016 ሪሚዲያል ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

በዚህም በ2016 ዓ.ም በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሱ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች እንዲሁም ነባር የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የ2017 ትምህርት ዘመን ምዝገባ ጥቅምት 11 እና 12/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

https://t.me/top_students1
https://t.me/top_students1

Top Students

10 Oct, 17:10


📢 ፕረዘንቴሽን የማቅረብ ጥበብ ለተማሪዎች በ ቀሰም(ቻLu) የተዘጋጀ


*⃣ ፕረዘንት ለማድረግ ምን ብለን እንጀምር
ዳስተር /Eraser ከተቀመጠበት ለማንሳት ረጋ ብላችሁ እየተረዳመዳችሁ Hello my classmates ፡
Hello dear our ......(Subject) teacher;
ዳስተሩን አንስታችሁ ቦርድ እያጠፋችሁ ንግግራችሁን ሳታቋርጡ ቀጥሉ
Here we are going to see about ..........(your lesson topic)
e.g Here we are going to see about philosophy .....ቦርድ ላይ ቀን ካልተፃፈ ፃፉ ...about philosopy ስትሉ ቦርድ ላይ ከድምፃችሁ እኩል ፅፋችሁ ጨርሱ

ወደ ተማሪዎቹ ዞር ብላችሁ

So if you are ready ,let's began.Philosophy means ....

So here we go.Philosophy means.... የሚል skeleton ተጠቅማችሁ ወደ ፕረዘንቴሽናችሁ መግባት

🔰ፕረዘንቴሽ ስናቀርብ ማድረግ ያለብን ነገሮች!

1⃣ ሰዓት አጠቃቀም

የተሰጣችሁን ሰዓት በዓግባብ ካልተጠቀማችሁበት ማለት የምትፈልጉትን ሃሳብ ሳትናገሩ ወደመቀመጫችሁ ትሸኛላችሁ!ስለዚህ ጊዜ ለመቆጠብ ፦


1)አንድ ነገር እየደጋገማችሁ ለማስረዳት አትሞክሩ።

2) ለተማሪዎች ኖት ለመፃፍ አትሂዱ!ኖት ከመፃፍ ይልቅ ትናንት ባሳየኋችሁ ምሳሌ መሰረት draft ያደረጋችሁትን Outline በBullet & numbering ቦርዱን አሸብርቁት!

3) ጊዜ ለመቆጠብ ከፈለጋችሁ በምታወሯቸው ቃል ማህል እንደ ባለስልጣን ' እእእ...' እያላችሁ ንግግር አታቆርፍዱ! ሳዓት ያልቃል ፤ ንግግራችሁ ይደብራል ፤ ነጥባችሁንም ያስጎምዳል!

2⃣ ቦታ አጠቃቀም

ሙሉ ቦታ ለመጠቀም ብላችሁ እንደ Dance chirography መድረኩን አትፈንጩበት!

ከመድረኩ ቀኝ ረድፍ ላይ መቆም ካለባችሁ ቆሙ ፤ በግራ መልኩ መሆን ካለባችሁ እንደዛው አክት አርጉ!ዘና በሉና

❗️Warning : calculation ከሆነ ቦርድ ላይ የምትሰሩት ተማሪዎችን ሳትከልሉ ፤ ራሳችሁን ከቦርዱ ወደ ዳር ገለል አርጋችሁ ማቀጣጠል ይኖርባችኋል!

❗️THINK 'BOUT DIS : ቦታ አጠቃቀም ላይ ጎበዝ ካልሆናችሁ የመድረኩ ማህከል ላይ ሁኑ!በግራም በቀኝም ፤ በማህልም ረድፍ ያሉ ተማሪዎች ትኩረታችሁን አይነፍጓችሁም!

3⃣የሰውነት እንቅስቃሴ አጠቃቀም!

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ''በቃል ለቃል ምልልስ'' ጊዜ የሰውነት እንቅስቃሴዎች ሃሳባችንን በ 30% ጭማሪ ቀላል እና ግልፅ ያረጉታል።ስለዚህ የሰውነት እንቅስቃሴያችሁ እንደሚከተለው ይሁን!

  የእጅ እንቅስቃሴ አጠቃቀም

1)እጃችሁን ከጭንቃላታችሁ በላይ አታወራጩ!...የሚመለከታችሁ ሰው ይደክመዋል)

2) ነገሮችን በተለመዱ የእጅ መልክቶችን ለመግለፅ ሞክሩ!...ለምሳሌ

መሮጥ ከሆኑ ቃሉ እነ ሃይሌ ገ/ስላሴ ሲረጡ እጃቸውን እይደሚያረጉት ማሳየት ...

3) እጃችሁን ኪሳችሁ አታርጉ!...የጋጣወጥ ባህሪ አላችሁ ተብሎ ይታሰባልና

4) እያወራችሁ ሳለ እጃችሁን አትፈትጉ። የእጃችሁን ጣቶች ለማንቋቋት አትሞክሩ!እንደዛ ስታረጉ ሰው አይኑቹን እጃችሁ ላይ ያረጋል!ያኔ ድንብርብራችሁ ይወጣል!

5) አደራ እየፃፋችሁ የምትሳሳቱት ነገር ካያችሁ በእጃችሁ አታጥፉ!ምምህሩ እና ተማሪዎቹ ለናንተ ያላቸው ቦታ ይቀንሳል!ለምን አንድ ፊደል አትሆንም ከተሳሳተች በዳስተር አጥፉ!

  የእግር እንቅስቃሴ አጠቃቀም!

1).በተለይ ሴቶች 😡ጭነታችሁን  በአንድ እግራችሁ ላይ አታርጉ!ቆፈጠን በሉ! የተመጣጠነ አረማመድ ይኑራችሁ!ላንዴ እንኳን ዘንበል የሚል አቋቋም እንዳይኖራችሁ!

    የጭንቅላት እንቅስቃሴ አጠቃቀም

1) ይሄ እንኳን ብዙ አይጠፋችሁም ፤ ራስ በመነቅነቅ የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው!

4⃣የአቀራረብ ዘዴ

1). ተማሪዉን የሚያሳትፍ ከባቢ ፍጠሩ!

ለተማሪዎች ስታስረዱ ጥያቄ ጠይቋቸው ፣ መልሳቸውንም እየሰማችሁ የተነቃቃ audience ያዙ!መምህሩ አሪፌ እንቅስቃሴ ሲያይ ደስ ይለዋል!

2).ፕረዘንቴሽን ማቅረብ ከጀመራችሁበት second አንስቶ ለ አንዴ እንኳን ወደ መምህሩ እንዳታዩ!

አንዳንድ ደግ  መምህር አለ ልክ ዞር ብላችሁ ስታዩት ራሱን እየነቀነቀ ልክ መሆናችሁን እየነገረ የሚያበረታታችሁ!

ሌሎች ግን መስመር ሊያስቷችሁ ነው ሚፈልጉት!በዛላይ አስረዱ የተባላችሁት ተማሪዎችን እንጂ መምህሩን አይደለም!

3.) ፕረዘንት ስታረጉ ልክ እንደመምህሩ ማድረግ ያለባችሁ ነገሮች አርጉ!
የሚረብሽ ካለ ከክፍል አሶጡ ፤ የሚንጫጫ ካለ ተቆጡ!

4.)የተለየ ፈፈግታ ወይም መሽኮርመም አታሳዩ!ሙዳችሁ ይጠፋባችኋልና

5.) ሁሉንም ተማሪ በዓይ ለመጎብኘት ሞክሩ!ይህ ካልተመቻችሁ !ደስ በሚል ሁኔታ ትምህርቱን በመከታተል ላይ ያሉ ቀና ተማሪዎችን መርጣችሁ ከነሱ ጋር የአይን ንግግር አርጉ!

...........Done !

ለመሆኑ Presentation ላይ ልዩ ቄንጦች ምንድናቸው?
የሚከተሉትን ቄንጦቾ ስትጠቀሙ በእርግጥ ክላሱ ሁሉ እናንተን ለማየት ይናፍቃል!
❗️Warning ፡ አንዳንድ ቄንጥ የማይወድ ወግ አጥባቂ መምህር አለ!ቦታ ለይታችሁ ተጠቀሙ ቄንጦቹ ፦

🔰 እያስተማራችሁ እያለ በእጃችሁ የያዛችሁትን ረጅም chalk ከዳሯ ላይ በጣታችሁ ሽርፍ በማድረግ ሽራፊዋን ወደ ምድር በንቀት መወርወር ....😎

🔰 ኮት ነገር አጥልቃችሁ ከነበር አሁን በንግግር ላይ ሳላቹ ኮታችሁን አውልቃችሁ ....chair lay ጣል ማረግ😎😎

🔰የሆነ diagram አንስታችሁ እያወራችሁ ከቦርዱ ራቅ በሉና ...ድንገት ከፍ ባለ ድምፅ ....ተመልአቱ እዛ መሃል ያለውን ነገር ብላችሁ እጃችሁን መሰንዘር.... ህዝቤ ከዛን ሰፍ 😎

🔰የኮት ቁልፍ መፍታት (በተለይ ሳንቃ ደረት ላላችሁ ወንዶች)

ገልፃ እያረጋችሁ ጀነን ባለ መልኩ የኮት ቁልፍ ቀስ ብላችሁ ፈታ ማረግ

አንዳንድ ተማሪ ቄንጥ ናቸው ብሎ የሚያስባቸው ነገር ግን ስግጥና የሆኑ ቄንጦች በ presentstion

🚫 አንገት ማሸሻት.......


🚫 ፀጉር በአንድ ጣት ማከክ....


❤️ልብ በሉ : አንዳንድ ተማሪ አለ present እያረጋችሁ ጥያቄ ጠይቆ ግራ ሊያጋባችሁ ሚፈልግ !ስለዚህ ማንም ተማሪ ቢሆን ጥያቄ ለመጠየቅ እጁን ካወጣ ስጨርስ መልስልሃለው በሉት!በኋላ ላይ ወላ ሊረሳው ይችላል!

❤️ልብ በሉ: Present አርጋችሁ ከጨረሳችሁ በኋላ ከተማሪዎች እንዲሁም ከመምህሩ ጥያቄ ይነሳባችኋል!ይህን ጊዜ ተማሪዎች እንዲሳተፉ እድል መስጠት ብልጥነት ነው!

#share
#share

https://t.me/top_students1
https://t.me/top_students1

Top Students

09 Oct, 12:52


#JimmaUniversity

ለጅማ ዩኒቨርሲቲ ነባር የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

ተራዝሞ የነበረው የ2017ዓ.ም. ትምህርት ዘመን ምዝገባችሁ በመጪው ጥቅምት 14 -15/2017 ትምህርታችሁን የሚካሄድ ስለሆነ በምትከታተሉባቸው ካምፓሶች በአካል በመገኘት እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በSRS አካውንታችሁ በመግባት የOnline ምዝገባችሁን እንድትፈጽሙ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፤

ከዚህ በፊት እንደተገለጸው የነባር Remedial ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው በ2017ዓ.ም ለዩኒቨርስቲው ከሚመደቡ የፍሬሽማን ፕሮግራም ተማሪዎች ጋር ስለሆነ ይህ የምዝገባ ሰሌዳ አይመለከታቸውም፡፡

https://t.me/top_students1
https://t.me/top_students1

Top Students

09 Oct, 12:36


#ዋቸሞ ዩንቨርስቲ

ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች የመግቢያ ቀኑን አራዝሟል :: ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ምስሉን ይመልከቱ ::

#share
#share

https://t.me/top_students1
https://t.me/top_students1