Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

@addismaleda


ዜና ከምንጩ

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

22 Oct, 11:33


ቦርዱ በተለያዩ ምክንያቶች በ11 የፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ የዕግድ ውሳኔ አሳለፈ

ማክሰኞ ጥቅምት 12 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በጠቅላላ ጉባዔ፣ በኦዲት እና በሴት አባላት አማካኝነት ከሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ጋር በተያያዘ የዕግድ ደብዳቤ ይፋ አድርጓል፡፡

የወላይታ ብሄራዊ ንቅናቄና፣የአገው ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲን ጨምሮ 11 ፓርቲዎች ናቸው በቦርዱ እግድ የተጣለባቸው፡፡

ቦርዱ ፓርቲዎቹን ለምን እንዳገደ እስኪያሳውቅ ድረስም ፓርቲዎች ምንም አይነት ህጋዊ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደማይችሉም ነው ያስታወቀው፡፡

ቦርዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት  እግድ የተጣለባቸው ፓርቲዎች ምንም አይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ክትትል እንዲያደርግም አሳስቧል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

22 Oct, 10:37


ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው የጡት ካንሰር ህመም

ይህ መረጃ ከየጤና ወግ በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር የቀረበ ነው

✍️✍️ በየአመቱ የጥቅምት ወር ለጡት ካንሰር ግንዛቤ በማስጨበጥ ታስቦ ይውላል።

💥 የጡት ካንሰር በአመት ከ 1.2 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ያጠቃል።

👉 የዘንድሮ የዓለም አቀፍ የጡት ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር "ማንም ሰው የጡት ካንሰርን ብቻውን መጋፈጥ የለበትም''። በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል።

✍️ግንዛቤ ማስጨበጫው በራስ ላይ የሚደረግ የጡት ምርመራን አስፈላጊነትና በሽታው ከመሰራጨቱ በፊት ለመድረስና ለመዳን ያለውን ፍይዳ ይገልፃል።

✍️የጡት ካንሰር ምርመራ እንዴትና መቼ ይደረግ?

👉 የጡት ካንሰር ምልክቶች ምንድናቸው?

የጡት ካንሰር በሴቶች ላይ ሊከሰቱ ከሚችሉ ካንሰሮች አንዱ ነው። በአለም አቀፍ ሁኔታ በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር አይነቶች የጡት ካንሰር በ 1 ኛ ደረጃ ይቀመጣል። የጡት ሴሎች (ህዋሶች ) ከተለመደው ወጣ ባለ እና ጤናማ ባልሆነ መልኩ ሲያድጉ እና ሲባዙ ይፈጠራል ። የጡት ካንሰር በአብዛኛው የሚከሰተው በሴቶች ቢሆንም በወንዶች ላይም ሊከሰት ይችላል።

ለሙሉ ዘገባ፡ https://addismaleda.com/archives/39371

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

22 Oct, 08:27


ምርጫ ቦርድ የፓርቲዎች የክፍያ ተመን ላይ ከፍተኛ ጭማሪ አደረገ

ማክሰኞ ጥቅምት 12 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአገልግሎት ክፍያ ላይ ጭማሪ አድርጓል።

በዚህም መሰረት ለሀገር አቀፍና ለክልላዊ ፖለቲካ ፓርቲ ጊዜያዊ ሰርተፊኬት ለማግኘት 100 ብር፤ ለሙሉ ዕውቅና ለሀገር አቀፍና ክልላዊ ፓርቲ 200 ብር እንዲሁም የተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሰረታዊ ሰነዶቻቸውን በጉባኤ አሻሽለው ሲያቀርቡ 30 ብር ይከፍሉ እንደነበር ቦርዱ አስታውሷል።

እነዚህን የክፍያ ተመኖች ላይ ማስተካከያ እንዲደረግባቸው መወሰኑን ያስታወቀው ቦርዱ አሁን ባደረገው ጭማሪም ጊዜያዊ ዕውቅና ክፍያ 15000 (አስራ አምስት ሺህ) ብር ፤ የሙሉ ዕውቅና ክፍያ 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ብር እና የሰነድ ማሻሻያ ክፍያ 5000 (አምስት ሺህ) ብር እንዲሆን መወሰኑን ቦርዱ አስታውቋል ።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

21 Oct, 19:08


በመርካቶ ሸማ ተራ አከባቢ የተከሰተውን የእሳት አደጋ እስከ አሁን መቆጣጠር ባለመቻሉ በሄሊኮፕተር እየተሞከረ መሆኑ ተገለጸ

👉 "በመርካቶ ሸማ ተራ አከባቢ በተከሰተው የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ለደረሰው ጉዳት እጅግ አዝነናል" ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የተከሰተውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር ከእሳት አደጋ  እና ስጋት መከላከል እንዲሁም  ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን ርብርብ እየተደረገ  ስለመሆኑ የገለጹት ከንቲባዋ አደጋውን ቶሎ ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለዉን ጥረት  አዳጋች ያደረገዉ የአካባቢው መንገድ የእሳት አደጋ መኪና በተሟላ ሁኔታ ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ በመሆኑ ምክንያት ነው ብለዋል።

በመሆኑም የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር በሄሊኮፕተር ለመጠቀም እየጣርን  ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል። 

ከንቲባዋ አክለውም ይህንን አደጋ ለመቀነስ ርብርብ እያደረጉ የሚገኙትን አካላት ሁሉ ጥረታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

21 Oct, 17:05


በአዲስ አበባ መርካቶ ሸማ ተራ የእሳት አደጋ በዚህ ሰአት ተከስቷል

👉 እሳቱ ጠንከር ያለ ነው ፤ እስካሁን አልጠፋም ፤ ሰው ንብረት እያሸሸ ነው " - በስፍራው የሚገኙ ሰዎች

ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ መርካቶ ሸማ ተራ የእሳት አደጋ ተከስቷል።

እሳቱ ከተነሳ በርከታ ደቂቃዎች ቢቆጠሩም እስካሁን መቆጣጠር እንዳልተቻለ በስፍራው የሚገኙ የአይን እማኞች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

የአይን እማኞቹ " እሳቱ ጠንከር ያለ ነው ፤ በስፍራው እሳት አደጋዎች ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ ቢሆንም ምንም ሊጠፋ አልቻለም።" ተብለዋል።

በስፍራው ላሉ የአደጋ ሰራተኞች ተጨማሪ ቦቴና እገዛ ያስፈልጋል ፤ በውሃ ብቻም የሚሆን አይደለም " ብለዋል።

" በአካባቢው ያሉ እሳቱ ያልደረሰባቸው ሰዎች ንብረታቸውን እያሸሹ ይገኛሉ " ተብሏል።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

21 Oct, 17:02


“የአዲስ አበባ የባለቤትነት ጉዳይ ቀዳሚው የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ነው፡፡

እኛ እንደ ኦነግ አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ስር መሆን አለባት ነው የምንለው! የፌደራሉ መንግስት መሬት የለውም፤ ከፈለገ ባህርዳርን ዋና ከተማው ማድረግ ይችላል፡፡”

አዲስ ማለዳ ከአንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ ቀጄላ መርዳሳ ጋር ያደረገችውን ቃለምልልስ ከስር ባለው መስፈንጠሪያ ተጠቅመው ይከታተላሉ።

https://youtu.be/Y9o4949cJsQ?si=I-2AlP1dqLug6AYp

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

21 Oct, 15:24


“እናት ፓርቲ ለሁለት ሊከፈል ነው” በሚል ሲናፈስ የቆየው መረጃ ሀሰት ነው ሲል ፓርቲው አስተባበለ

ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) እናት ፓርቲ ከሰሞኑ የላዕላይ ምክር ቤትና የስራ አስፈፃሚ አባላት ተፈርሞ ለምርጫ ቦርድ በገባ ደብዳቤ ላይ የፓርቲው የተወሰኑ የስራ አስፈፃሚ አባላት በስልጣን ፍላጎት እና በተለያዩ የአሰራር ጥሰቶች መክሰሳቸው ተቋሙን ለመከፋፈል የሚያደርስ አይደለም ሲል አስተባብሏል፡፡

ፓርቲው ለአዲስ ማለዳ በላከው መግለጫ እንደገለጸው በፓርቲው ላይ ክስ እና ውንጀላ ያቀረቡ አካላት ከሀገር ውጪ የሚገኙ እንዲሁም ከፓርቲው አባልነት የለቀቁ ከዚህ ቀደምም ከፓርቲው አካሄድ እና አስተሳሰብ ጋር የማይገናኝ ጥፋት ላይ ተገኝተው በማስጠንቀቂያ የታለፉ ናቸው ብሏል፡፡

በተጨማሪም ፓርቲው የውስጥ ችግሮች ሲፈጠሩ የቅሬታ አፈታት ሂደት በመተዳደሪያ ደንብ ላይ የተገለጸ ቢሆንም ቅሬታ አቅራቢዎቹ የፓርቲውን ደንብ ያልጠበቀ ክስ አቅርበዋል ሲል ኮንኗል፡፡

በመሆኑም ፓርቲው በጥቂት ሰዎች በተነሳ ቅሬታ አንድን ተቋም “ለሁለት ሊከፈል ነው” ከሚል አንጻር ሰው እንዲመለከተው ማድረግ አግባብነት የለውም ሲል አስታውቋል፡፡

የፓርቲውን መደበኛና ህጋዊ መዋቅር ወደ ጎን በመተው አዲስ አወቃቀር በመዘርጋት በፓርቲ ውስጥ “ጥያቄ የሚያነሱ” አባላትንና በማባረርና በማገድ አሁን ያለው አመራር የራሱን አዲስ አወቃቀር እየዘረጋ መሆኑንም የላዕላይ ምክር ቤት አባላት ያሉበት ቅሬታ አቅራቢ ቡድን አስታውቆ እንደነበር ይታወሳል፡፡

እንዲሁም በፋይናንስ አሰራርና በሰራተኛ ቅጥር ዙሪያ ብልሹ አሰራር ሰፍኗል የሚለው ቅሬታ አቅራቢ ቡድን ምርጫ ቦርድ ጣልቃ ገብቶ የኦዲት ምርመራ እንዲያደርግ ጠይቆ ነበር፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

21 Oct, 14:02


“የአዲስ አበባ የባለቤትነት ጉዳይ ቀዳሚው የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ነው፡፡

እኛ እንደ ኦነግ አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ስር መሆን አለባት ነው የምንለው! የፌደራሉ መንግስት መሬት የለውም፤ ከፈለገ ባህርዳርን ዋና ከተማው ማድረግ ይችላል፡፡”

አዲስ ማለዳ ከአንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ ቀጄላ መርዳሳ ጋር ያደረገችውን ቃለምልልስ ከስር ባለው መስፈንጠሪያ ተጠቅመው ይከታተላሉ።

https://youtu.be/Y9o4949cJsQ?si=I-2AlP1dqLug6AYp

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

21 Oct, 13:21


በጫሞ ሀይቅ ላይ በተከሰተው አደጋ የ13 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ

ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከአቡሎ አርፋጮ ወደ አርባምንጭ ከተማ 16 ሰዎችን እና ሙዝ ጭና ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ባሳለፍነው ሐሙስ 10 ሠዓት ከ20 ገደማ ጫሞ ሐይቅ ላይ ሰጥማ ነበር፡፡

የተለያዩ ስጋቶች በመኖራቸው እንዲሁም በጸጥታ ችግር ሳቢያ የትኛውም አይነት ጀልባ እንዳይጓዝ በተከለከለበት በጫሞ ሐይቅ ላይ 16 ሰዎችን እንዲሁም ሙዝ ጭና ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ሰጥማ፤ ከተሳፈሩ 16 ሰዎች ውስጥ ሁለቱ በህይወት ተገኝተው የተቀሩትን 14 ሰዎች የመፈለጉ ሥራ ቀጥሎ መቆየቱን የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

አሁን ላይ የሦስት ሰዎችን ሕይወት በፍለጋ ማዳን መቻሉን እና 13 ደግሞ ሕይወታቸው ማጣታቸውን እንዲሁም የሟቾች አስክሬን ከእልህ አስጨራሽ ፍለጋ በኋላ ሙሉ በሙሉ መገኘቱን እና ወደ ቤተሰቦቻቸው መላኩን የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት ገጽታ ግንባታ ዲቪዥን ኋላፊ ኮማንደር ረታ ተክሉ  መናገራቸው ተጠቁሟል፡፡

የአደጋው መንስኤ በተከለከለበት ቦታ መጓዛቸው ብቻ ሳይሆን ጀልባዋ ከመጫን አቅሟ በላይ በመጫኗ እና የጀልባዋ የመጫን አቅም 35 ኩንታል ቢሆንም በዕለቱ 70 ኩንታል ሙዝ እና 16 ሰዎችን መጫኗ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

21 Oct, 12:14


የመምህራን የመኖሪያ ቤት እና የመሥሪያ ቦታ በሚፈለገው ፍጥነት እየተከናወነ አለመሆኑን ማህበሩ አስታወቀ

ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር 37ኛ መደበኛ የምክር ቤት ስብሰባውን ማጠናቀቁን ገልጿል።

የማህበሩ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሐንስ በንቲ በስብሰባ ላይ የ2016 ዓ.ም የስራ አፈፃፀምና የኦዲት ሪፖርት ካቀረቡ በኋላ ሰፊ ውይይት መደረጉን ማህበሩ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በውይይቱም መምህራንን እየተፈታተነ ያለው ከፍተኛ የኑሮ ውድነት፣ረጅም ጊዜ አገልግሎት ያላቸው መምህራን የደረጃ እድገት ወይም የእርከን ጭማሪ አለመኖር፣በአንዳንድ ክልሎች የመምህራን ደሞዝ በጊዜ አለመከፈል ብሎም እየተቆራረጠ መከፈል፣ያለመምህራን ዕውቅናና ፈቃድ በተለያዩ ምክንያቶች የደሞዝ መቆረጥ ችግሮት መነሳታቸው ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም ቀደም ብሎ የተጀመረው የመምህራን የመኖሪያ ቤት እና የመሥሪያ ቦታ በሚፈለገው ፍጥነት እየተከናወነ ያለመሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ደግሞ ጭራሽ አለመጀመሩ፣በትርፍ ሰዓት ክፍያ ላይ ተደራራቢ ግብር መቆረጡ፣የመጽሐፍትና ሌሎች ግብአቶች እጥረት እና የክረምት መምህራን ስልጠናና ያጋጠሙ ችግሮች በተሳታፊዎች በአስተያየት እና በጥያቄ መልክ ተነስተዋል።

የትምህርት ሚንስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ  ጡሹነ ከመምህራን ጥቅማ ጥቅም ጋር በተያያዘ እየታየ ያለው ጥያቄ የተጀመረው የትምህርት ሴክተር ሪፎርም ተጠናቆ ተግባራዊ ሲሆን ብዙ ጉዳዮች እንደሚፈቱ ገልፀዋል ።

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

21 Oct, 10:44


የ2017 የቴክኒክና ሙያ የመደበኛ ስልጠና ዘመን መቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ

ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ዘመን መቁረጫ ነጥብ በዛሬው እለት ይፋ ሆኗል፡፡

የተፈጥሮ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት በስልጠና ደረጃ 1 እና 2 ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 141 እና ከዚያ በታች ፤ ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች 137 እና ከዚያ በታች እንደሆነ ተገልጻል፡፡

ለሴት ተማሪዎች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 138 እና ከዚያ በታች ፤ ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች 134 እና ከዚያ በታች እንዲሁም ለሁሉም የአካል ጉዳተኞች የመቁረጫ ነጥቡ 124 እና ከዚያ በታች መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም የማህበራዊ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት በስልጠና ደረጃ 1 እና 2 ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 139 ከዚያ በታች፤ ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች 135 እና ከዚያ በታች ያለ ነጥብ ነው፡፡

ለሴቶች በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 134 እና ከዚያ በታች፤ ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች 124 እና ከዚያ በታች በተመሳሳይ ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 124 እና ከዚያ በታች መሆኑ ተመላክቷል፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

21 Oct, 07:35


የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ከሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተሳትፎ እራሱን ማግለሉን አስታወቀ

ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ድርጅት አሳታፊነትና ግልጸኝነት ስላላየሁበት ከአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተሳታፊነት እራሴን አግልያለሁ ሲል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በሱማሌ ክልል የገዢው ፓርቲ መዋቅር ተሳታፊዎችን የሚለይበትና የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ድምጽ የሚያፍንበት ህገ-ወጥ አሰራር መዘርጋቱን የሚገልጸው ፓርቲው በዚህ ሂደት ውስጥ በምክክር መሳተፍ ረብ የለሽ ነው ሲልም ገልጾታል፡፡

ይህ አግላይ አሰራር አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተቋቋመበትን አላማ የሚጥስ ነው ሲልም በምክክር ኮሚሽኑ ሂደት ላይ ጥያቄ አንስቷል፡፡

ፓርቲው ከሱማሌ ክልል ውጪ በአማራና ኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳሱ የታጠቁ ሃይሎች ባልተሳተፉበት ሁኔታ እንዴት የምክክር ሂደቱ ሊሳካ ይችላል ሲልም በጥያቄ መልስ አንስቷል፡፡

በቀጣይም ሁሉን አቀፍ የድርድር መድረክ እስካልተዘጋጀ ድረስ በዚህ ሂደት ውስጥ መሳተፍ እንደማይችልም ጠቁሟል፡፡

ኦብነግ በ2010 ዓ.ም ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴን ለማድረግ ከፌዴራሉ መንግስት ጋር ስምምነት አድርጎ መግባቱ አይዘነጋም፡፡

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

20 Oct, 16:23


ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በአምስተርዳም ማራቶን ድል  አድርገዋል

እሁድ ጥቅምት 10 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በሴቶች በተካሄደው ውድድር የአለምዘርፍ የኃላው የውድድሩን ክብረወሰን በማሻሻል በ2:16:52 አሸንፋለች::

ከሁለት አመት በፊት ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊ አልማዝ አያና የክብረወሰኑ ባለቤት እንደነበረች ይታወሳል::

የአለምዘርፍ ክብረወሰኑን በ28 ሰከንድ ነው ያሻሻለችው::ኢትዮጵያዊቷ ሄቨን ሀይሉ በ2:19:29 ሁለተኛ ጨርሳለች::

በወንዶች ውድድር ፀጋዬ ጌታቸው በ2:05:38 አንደኛ ጨርሷል:: ይህንንም በማሳካት ከሁለት አመት በፊት ያስመዘገውን ድል መድገም ችሏል:: 

የሀገሩ ልጅ ቦኪ አሰፋ በ2:05:40 ሁለተኛ በመሆን አጠናቋል::

በብሩክ ገነነ

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

19 Oct, 16:24


ከኦሮሞ ጥያቄ እና ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ አዲስ ማለዳ ከአንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ ቀጄላ መርዳሳ ጋር ቆይታ አድርጋለች። ሙሉ ቃለምልልሱን በአዲስ ማለዳ ዩቲዩብ በቅርብ ቀን ይጠብቁን።

https://youtu.be/lDZ8nEA4Z1A?si=7rm1PUnoebYw9OQY