🔰 ሙርተድ(ከእስልምና የወጣ ይገደላል??ለምን ይገደላል?🔰
አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ ሰዎችንና ጂኖችን የፈጠረበት ዐላማ እሱን ብቻ እንዲያመልኩ ነው።
አላህ እንዲህ ይላል👇
وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ
(📗ሱረቱ አል-ዛሪያት - 56)
ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡
በእስልምና አንድ ሙስሊም ያልሆነ ግለሰብን አስገድዶ ወደ እስልምና ማስገባት የሚባል ነገር የለም።
አላህ እንዲህ ይላል👇
በሃይማኖት ማስገደድ የለም፡፡ ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ፡፡ "(📘ሱራ በቀራ፥ 2:256)
➤ ተገዶ እስልምና መቀበሉ ራሱ ትርጉም የለውም። ጥቅም የለውም። ምክንያቱም እስልምናን የተቀበለው በውጩ እንጂ ልቡ ላይ ሌላ እምነት ካለው ሙናፊቅ ይሆናል። በጣም ትልቅ ቅጣት ይጠብቀዋል።
አላህ እንዲህ ይላል👇.
إِنَّ الْمُنَافِقِينَ فِي الدَّرْكِ الْأَسْفَلِ مِنَ النَّارِ وَلَن تَجِدَ لَهُمْ نَصِيرًا
*መናፍቃን በእርግጥ ከእሳት በታችኛው አዘቅት ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነርሱም ረዳትን አታገኝላቸውም*፡፡
📚 አልኒሳእ 4፥145
➤ አላህ የሚፈልገው ጥርት ያለን አመልኮ እንጂ ሳይፈልጉ በግድ የሚፈፅሙትን አይደለም።
👇ማስረጃ
«وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ حُنَفَاءَ وَيُقِيمُوا الصَّلَاةَ وَيُؤْتُوا الزَّكَاةَ ۚ وَذَٰلِكَ دِينُ الْقَيِّمَةِ»
«አላህን፣ ኃይማኖትን ለርሱ ብቻ አጥሪዎች ቀጥተኞች ኾነው ሊግገዙት፣ ሶላትንም አስተካክለው ሊሰግዱ፣ ዘካንም ሊሰጡ እንጅ ያልታዘዙ ሲኾኑ (ተለያዩ)። ይህም የቀጥተኛዪቱ (ኃይማኖት) ድንጋጌ ነው።»
📚 [አል-በዪይናህ: 5]
ተገደው አላህን የሚያመልኩ ሰዎች አምልኳቸው ጥራት ስለሌለው ጥቅም የለውም። ስለዚህ በእስልምና ሌላን ሰው አስገድዶ ወደ እስልምና ማስገባት የሚባል ነገር የለም ጥቅምም የለውም።
➤ በእስልምና ሌላን ሰው ወደ እስልምና አስገድዶ ማስገባት እንደሌለ ካየን
ሙስሊም ያልሆኑ ግለሰቦች ያስገድዳል ብለው የሚያነሱትን ሀዲስ እንመልከትና መልስ እንስጥበት
ሀዲሱ👇👇👇👇
عنْ اِبْنِ عَبَّاسٍ رَضِيَ اَللَّهُ عَنْهُمَا قَالَ: قَالَ رَسُولُ اَللَّهِ - صلى الله عليه وسلم -{ مَنْ بَدَّلَ دِينَهُ فَاقْتُلُوهُ }
ኢብኑ ዐባስ እንዳስተላለፉት ነቢዩ ሰላሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል" ሀይማኖቱን የቀየረን ግደሉት"
➤➤ በመጀመሪያ ሰዎች በአላህ የማምንና የመካድ ምረጫ ተሰጥቷቸዋል። ነፃ ፈቃድ ተሰጥተዋል።
አላህ እንዲህ ይላል👇
وقلِ الْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ ۖ فَمَن شَاءَ فَلْيُؤْمِن وَمَن شَاءَ فَلْيَكْفُرْ ۚ إِنَّا أَعْتَدْنَا لِلظَّالِمِينَ نَارًا أَحَاطَ بِهِمْ سُرَادِقُهَا ۚ وَإِن يَسْتَغِيثُوا يُغَاثُوا بِمَاءٍ كَالْمُهْلِ يَشْوِي الْوُجُوهَ ۚ بِئْسَ الشَّرَابُ وَسَاءَتْ مُرْتَفَقًا
ሱረቱ አል ከህፍ፥ - 29 ]
«እውነቱም ከጌታችሁ ነው፡፡ የሻም ሰው ይመን፤ የሻም ሰው ይካድ» በላቸው፡፡ እኛ ለበደለኞች አጥሯ በእነሱ የከበበ የኾነችውን እሳት አዘጋጅተናል፡፡ (ከጥም) እርዳታንም ቢፈልጉ እንደ ዘይት ዝቃጭ ባለ ፊቶችን በሚጠብስ ውሃ ይረዳሉ፡፡ መጠጡ ከፋ! መደገፊያይቱም ምንኛ አስከፋች!
☝️ አላህ እዚህ አንቀፅ ላይ ሰዎች የማመንና የመካድ ነፃ ፈቃድ እንዳላቸው ከጠቀሰ በኃላ እነዚያ የካዱ ሰዎች ቅጣት እንደሚያገኙ ይጠቅስልናል።
ይህ ማለት ሰዎች የማመንና የመካድ ምርጫ እንዳላቸው፣ የመካድ መብት ግን እንደሌላቸው እንረዳለን። የመካድ መብት ቢኖራቸው በክህደታቸው ባልተቀጡ ነበር።
ይህንን ካየን ከእስልምና የወጣ ሰው ለምን ይገደላል። የመካድ ምርጫ ካለው ለምን ይገደላል ለሚለው መልሱ👇👇
➤➤1. በእስልምና حد ሐድ ( የወንጀል መቅጫ ህግ፣ውሳኔ) የሚባል ነገር አለ። ይህም አንድ ሙስሊም ለሚተገብራቸው ወንጀሎች የተቀመጠ ቅጣት ነው።
ለምሳሌ "حد الزاني " አግብቶ ዝሙት የሰራ ቅጣት(መግደል)፣حد السرقة የስርቆት ህግ(እጁን መቁረጥ), حد القتل የግድያ ቅጣት(መገደል) ወዘተ የሚባሉ ህግጋቶች አሉ። እነዚህን ወንጀሎች የተዳፈረ ከላይ የተጠቀሰውን ቅጣት ያገኛል ምክንያቱም ከላይ እንደተጠቀሰው ሰዎች የመካድ፣ወንጀል የመስራት ምርጫ እንጂ መብት ስለሌላቸው ይቀጣሉ ይጠየቃሉ። ለምሳሌ አግብቶ ዝሙት የሰራ ሰው ዝሙት የሚባል ወንጀል ስለሰራ ይገደላል። ዝሙት መስራት መብቱ ነው አይባልም ልክንደዚሁ አንድ ሙስሊም ከከፈረ ከዝሙት የባሰ የተለቀ ኩፍር(አምላክን መካድ) የሚባል ትልቅ ወንጀል ስለሰራ ይገደላል። አምላኩን መካድ መብቱ ነው አይባልም።
ሰዎች በፈጠሯቸው በተለያዩ ሀገሮች ህግ ላይ ራሱ " ሀገሩን የካደ ሰው ይገደላል" የሚል ህግ አላቸው። ሀገርን መካድ መብቱ ነው እንደማይባለው ሁሉ አምላክን መካድም መብቱ አይደለም።
ሀገርን የካደ ሰው ከተገደለ ሀገርን የፈጠረ አምላክን ሲክድ ይገደል ቢባል ምኑ ነው ሚገርመው።
በአጭሩ ከእስልምና የወጣ ሰው የሚገደለው አምላኩን ስለካደ ክህደት ስለፈፀመ ይገደላል እንጂ አስገድደን እንዲሰልም አይደለም።
➤➤2. ሙርተድ የሚገደልበት ሁለተኛው ምክንያት ለሙስሊሞች ፊትና ስለሚሆን ነው። ከድሮ ጀምሮ "ከእስልምና ወጥቻለሁ፣መስሊም ነበርኩ ወዘተ እያሉ እስልምና ላይ እየቀጠፉ የእስልምና ስም እንደሚያጠፉት ለሙስሊሞች ፊትና ስለሚሆኑ ሙስሊሞችን ከንደዚህ አይነት ፈታኝ ከሆኑ ሰዎች ነፃ ለማድረግ(ሰዎች በነሱ ቅጥፈት እንዳይፈተኑ) ተብሎ ይገደላሉ።
አላህ እንዲህ ይላል
ۚ وَالْفِتْنَةُ أَكْبَرُ مِنَ الْقَتْلِ ۗ وَلَا يَزَالُونَ يُقَاتِلُونَكُمْ حَتَّىٰ يَرُدُّوكُمْ عَن دِينِكُمْ إِنِ اسْتَطَاعُوا ۚ وَمَن يَرْتَدِدْ مِنكُمْ عَن دِينِهِ فَيَمُتْ وَهُوَ كَافِرٌ فَأُولَٰئِكَ حَبِطَتْ أَعْمَالُهُمْ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ ۖ وَأُولَٰئِك أَصْحابُ النَّارِ ۖ هُمْ فِيهَا خَالِدون
ፈተናም (ማጋራት) ከመግደል ይበልጥ ከባድ ነው፡፡ (ከሐዲዎች) ቢችሉ ከሃይማኖታችሁ እስከሚመልሳችሁ ድረስ የሚዋጉዋችሁ ከመሆን አይቦዝኑም፡፡ ከእናንተ ውስጥም ከሃይማኖቱ የሚመለስና እርሱም ከሐዲ ሆኖ የሚሞት ሰው እነዚያ (በጎ) ሥራቸው በቅርቢቱም በመጨረሻይቱም አገር ተበላሸች፡፡ እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡ እነርሱ በርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡»(📚አልበቀራህ 2:217)
ይቀጥላል......👇 ሙሉውን አንብቡት👇👇👇👇👇👇
https://t.me/iwnetlehullu1/376 የኢስላም እውነት ለሁሉ Truth for all, [Dec 17, 2024 at 16:53]
➤➤3. በሌላ ሀዲስ ላይ እንደተጠቀሰውም ሙርተዱ የሙስሊሞች ጀማዓን(ስብስብን) ስለሚለይ ነው።