ከ እንስሳት አለም / Animals world @animalsworld_ethiopia Channel on Telegram

ከ እንስሳት አለም / Animals world

@animalsworld_ethiopia


ይህ ትክክለኛው የ ቴሌግራም ቻናላችንን ነው ቤተሰብ እንሁን ስለ ተፈጥሮ ያሎትን እውቀት ያስፉ

ከ እንስሳት አለም / Animals world (Amharic)

ከ እንስሳት አለም ቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ነው በዓድዋ ውጤት እና ታሪክ ቅዱስ እና እንስሳት መሆኑን ለማየት በእኛ ጋር የሚያምን ወይም ለማግኘት በመጠቀም አዳም፣ ልዑል፣ ቸርነቱ እና ርእስ ወይም ማንኛውንም ትክክለኛ ትምህርት ክፍል ሲሆን የመልኩን ተᲮንኖ መጠናከ እና ተብሏል ፡፡ ይህ ቴሌግራም የ ቴሌግራም ቻናል ላለው እና ልዩ ነው ፥፥ ይህንን ሰው እንዴት በማስተባበል ተጠቀምሽ ፡፡ በአቶ መገናኛ የነበሩት አንዲት ቴሌግራም ምስክሮችን የመልክቱን ተጠንቅቆ ብቻልኩሽ ፥፥ እነሱ ቴሌግራሞቹ በሽታ ላይ ተጠቃሻ እና እውነተኞች ናቸው ፡፡

ከ እንስሳት አለም / Animals world

21 Dec, 10:16


https://youtu.be/p6yrrzJXSh0

ከ እንስሳት አለም / Animals world

27 Nov, 09:06


ግዙፍ ንስሮች የተራራ ፍየሎችን ተሸክመው እንደሚበሩ ያውቃሉ ?

ንስር የተራራ ፍየሎችን ከተሸከመ በኋላ ከገደል ላይ ቁልቁል ይለቃቸዋል ከዛም ፍየሉ ሲሞት ንስሩ መሬት ወርዶ ረጋ ብሎ ይመገባል።

Youtube ላይ ንስር ፍየል ተሸክሞ ሲበር የሚያሳይ ቪዲዮ ለቀናል እንድታዩ ተጋብዛችኋል ።
ሊንክ:- https://youtu.be/JMQNWEAMMgU

ከ እንስሳት አለም / Animals world

16 Nov, 15:11


#ዝንብ

- በአለማችን ላይ ከ 240,000 በላይ የተለያዩ የዝንብ ዝርያዎች አሉ

- ዝንቦች ለ አለማችን እጅግ በጣም ጠቃሚ ከሆኑ ነብሳቶች ውስጥ ይመደባሉ ። ዝንቦች የሞቱ እንስሳቶችን እና ብስባሾችን አብላልተው ወደ አፈርነት የመቀየር አቅም አላቸው። ይሄም አለማችን የተፈጥሮ ሰንሰለቷን እንድትጠብቅ በጣም ይረዳታል

- የዝንቦች የእድሜ ጣሪያ ቢበዛ 1 ወር ነው። ነገርግን በዚህ ጥቂት ጊዜ ውስጥ በጣም ብዙ እንቁላሎችን ጥለው ነው የሚሞቱት።

- 1 ሴት ዝንብ ብቻ በየ 4 ቀኑ እስከ 500 እንቁላሎች ትጥላለች

- ዝንቦች በሽታን ከሰው ወደ ሰው በማስተላለፍ ተቀዳሚም ናት

ምንጭ :-National Geographic Wild, A-z animals

@hulegebmereja

ከ እንስሳት አለም / Animals world

07 Nov, 14:37


መስክ አጋዘን

- እነዚህ አጋዘኖች የሚገኙት በ ሰሜን ኤዥያ ነው

- ለየት ባለ መልኩ መስክ አጋዘኖች ከሌሎች የአጋዘን ዝርያዎች በተለየ መልኩ 2 ረጃጅም እና ሹል ጥርሶች አሏቸው። ጥርሶቹን የሚጠቀሙት ወንዶቹ ለሴት በሚጣሉበት ወቅት ለመወጋጋት ነው።

- በሰውነታቸው ውስጥ ያለው እጢ ግሩም መዓዛ ያለው ፈሳሽ ስለሚያመነጭ ሰዎች ለሽቶ መስሪያ ይጠቀሙታል። በዚህም የተነሳ በብዛት ታድነው ቁጥራቸው በ95% ቀንሶ ለመጥፋት ተቃርበዋል

- በህጋዊ መንገድ እጢያቸውን መነገድ ስለማይቻል ህገወጦች በ ጥቁር ገበያ 1 ኪሎ ግራም የ መስክ አጋዘን እጢ በ 45,000 ዶላር ይሸጣሉ

- የሚመገቡት ቅጠላ ቅጠል እና ፍራፍሬዎችን ነው

- ከ 7 እስከ 18 ኪሎ ግራም ይመዝናሉ

- ሴቷ መስክ አጋዘን ከ 150 እስከ 180 ቀናቶች አርግዛ 1 ግልገል ትወልዳለች

የበለጠ እንድንሰራ ሼር በማድረግ አበረታቱን

ከ እንስሳት አለም / Animals world

17 Oct, 11:30


ባቢሩሳ 🐗

ይህ እንስሳ ባቢሩሳ ይባላል የሚገኘው ኢንዶኔዢያ ውስጥ ነው። ወንድ ሆኖ መፈጠር ለዚህ እንስሳ በጣም መጥፎ እድል ነው። ምክንያቱ ደግሞ ወንድ ባቢሩሳዎች አፍንጫቸው ላይ ያሉት ሁለት ረጃጅም ቀንዶች እድገታቸው የማይቋረጥ በመሆኑ አብዛኛው ወንድ ባቢሩሳዎች ቀንዱ ረዝሞ የ እራስ ቅላቸውን ሰብሮ በመግባት ያለ እድሜያቸው ስለሚገድላቸው ነው።

ሴቶቹ እንደዚህ አይነት ቀንድ ስለሌላቸው ረጅም ጊዜ ይኖራሩ አንዳንድ እድለኛ ወንዶችም ቀንዳቸው አበቃቀሉ ወደ ጭንቅላታቸው ካልሆነ የመትረፍ እድል አላቸው። ተፈጥሮ ድንቅ ናት
@hulegebmereja

ከ እንስሳት አለም / Animals world

05 Oct, 14:13


ጆሮ ሰፊ ቀበሮ

- በብዛት የሚገኙት በ ምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ነው

- እነዚህ የቀበሮ ዝርያዎች እንደሌሎች የቀበሮ ዝርያዎች አብዛኛውን ጊዜ እንስሳቶችን ሳይሆን የሚመገቡት ነብሳቶችን ነው።
ዋነኛ ምግባቸው ምስጥ፣ ጢንዚዛ፣ ሸረሪቶች ናቸው

- ወንድ እና ሴት ሰፋፊ ጆሮ ቀበሮዎች የሚመሰርቱት ጥምረት እስከ እድሜ ልክ የሚቀጥል ነው

- ቡችሎች ሁሌ ዋሻ ውስጥ ነው የሚኖሩት። እናት እና አባት የሚለያዩት አንዱ ምግብ ፍለጋ ሲወጣ ሌላኛው ልጆቹን ለመጠበቅ ነው

- ሴት ባለ ሰፋፊ ጆሮ ቀበሮ ልጅ ከወለደቾ በኋላ የምታጠባው ወተት እንዳያልቅባት ወንዱ ረጅም ሰዓት ዋሻ ውስጥ ተቀምጦ ልጆቹን ይጠብቃል እሷ ተዟዙራ በደንብ ተመግባ ትመጣለች

- የራሳቸውን ዋሻ ከመስራት ይልቅ እንደ አዋልዲጌሳ እና ከርከሮ አይነት እንስሳቶች የቆፈሩትን ዋሻ ይጠቀማሉ

- ምግብ ለማግኘት ከዓይናቸው ይልቅ ጆሮአቸውን እና አፍንጫቸውን ይጠቀማሉ። የሚያድኑትም 85% በለሊት ነው

- በዓመት እስከ 2 ጊዜ ይወልዳሉ። የሚወልዱት እስከ 6 ቡችሎች ሲሆን በመጀመሪያዎቹ 3ሳምንታቶች ብዙ ቡችሎች ይሞታሉ
@hulegebmereja

ከ እንስሳት አለም / Animals world

04 Oct, 11:51


#ሳላ

- ሳላዎች ኢትዮጲያን ጨምሮ የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ይገኛሉ

- ሳላዎች የሚኖሩት ከውሀ የራቀ አጫጭር ሳሮች ያሉበት በርሀማ ቦታ ሲሆን ውሀ ካገኘ ይጠጣል ካላገኘ ደግሞ እርጥብ ሳር ላይ ከሚያገኘው ወሀ መኖር ይችላል

- ብዙ ወሀ ስለማይጠጣ ኩበቱ በጣም ደረቅ ሲሆን ሽንቱም በጣም ትንሽ ነው።

- ሳላዎች አብዛኛውን ጊዜ ሳር የሚግጡት ጠዋት ነው ምክንያቱም በሳሩ ላይ ጤዛ ስለሚኖር ውሀ ለማግኘት ነው።

- የሰውነት ሙቀታቸውን ለመቀነስ ያለከልካሉ

- ሴት ላማዎች 4 ጡቶች ያላቸው ሲሆን በ 8 ወር ተኩል እርግዝና ይወልዳሉ። ከዛም በጥቂት ሳምንታቶች ውስጥ መልሰው ማርገዝ ይችላሉ

- ሴት ሳላዎች ሲወልዱ ለብቻቸው ሆነው ነው። ጥጆቹም እስከ 6 ሳምንታትተደብቀው ይቆያሉ።
ምንጭ:- አጥቢዎች መፅሀፍ
@hulegebmereja

ከ እንስሳት አለም / Animals world

01 Oct, 10:03


#ፐፈር

- ፐፈር አሳዎች ጠላት ሲመጣባቸው ወይም ሲደነግጡ በምስሉ ላይ እንደምታዩት እንደ ኳስ ይነፋሉ ቆዳቸውም እሾሀማ ስለሆነ ለመብላት አስቸጋሪ ስለሚሆኑ ጠላታቸው ትቷቸው ይሄዳል።
በሚነፉበት ጊዜ ከ ዋናው ትልቀታቸው በ 3 እጥፍ ነው የሚጨምሩት።

- ፐፈር አሳዎች አይናቸውን መጨፈን ከሚችሉ ጥቂት የአሳ ዝርያዎች ውስጥ አንዱ ነው

- በ አንድጊዜ 30 ሰዎችን መግደል የሚያስችል አደገኛ መርዝ አላቸው። በዙ ትላልቅ አሳዎች አፋቸው ትላልቅ ስለሆነ ይሄን ፐፈር ፊሽ ይውጡታል ከዛም ተመርዘው ይሞታሉ። የዚህ አሳ መርዝ የማይመርዘው ሻርክን ብቻ ነው።

- በመርዙ አደገኝነት ከአለም በ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል

- የ እድሜ ጣሪያቸው 10 አመታት ነው

- የ Youtube ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ የበለጠ እንድንሰራ ስለምታበረታቱን እናመሠግናለን
https://youtube.com/c/HulegebMereja

ከ እንስሳት አለም / Animals world

20 Sep, 08:55


#አነር

- አነር በ አፍሪካ ብቻ ነው የሚገኘው

- የ ወንዱ ክብደት 13 ኪሎ ገደማ ሲሆን የሴቷ ደግሞ 11 ኪሎ ድረስ ትሆናለች

- አነር አይጥ ፣ አይጠ መጎጥ እና በረጃጅም ሳሮች ውስጥ የሚገኙ ወፎችን አድኖ የመብላት ድንቅ ችሎታ የተላበሱ ናቸው

- እንደ አንቴና የሚያገለግሉት ቀጥ ያሉ ጆሮዎቹ የሚታደኑትን እንስሳቶች ድምፅ ከሩቁ መስማት ይችላሉ

- እንስሳቶችን ሲያድኑ 59% ይሳካላቸዋል ። ማለትም አድነው ላይዙ የሚችሉት 41% ብቻ ነው

- ሴት አነር ከ 65 እስከ 75 ቀኖች አርግዛ ትወልዳለች

- የተወለዱትን ግልገሎች አጥብታ ካሳደገች በኋላ ልክ ወንዶቹ ግልገሎች ራሳቸውን ችለው ማደን ሲጀምሩ እናትየዋ ታባራቸዋለች። እነሱም ተበታትነው የራሳቸውን ኑሮ ይመሠርታሉ። ሴቶቹ ግልገሎች ግን ረዘም ላለ ጊዜ ከ እናታቸው ጋር ይቆያሉ።
ምንጭ :- አጥቢዎች መፅሀፍ (ዶ/ር ሰለሞን ይርጋ)
@hulegebmereja

ከ እንስሳት አለም / Animals world

12 Sep, 07:46


ጠቃሚ መረጃ🐆
ታይገር ፣ ሊዮፓርድ፣ ቺታ(አቦሸማኔ) ፣ ግስላ ፣ ጃጓር እና ፑማን አንዱን ከአንዱ በቀላል መንገድ ለመለየት የሚያስችል መረጃ ከምስል ጋር ከታች አቅርበንላችኋል

1 ቁጥር :- ታይገር ይባላል ከድመት ዝርያዎች በሙሉ ትልቁ ነው። በጣም ጠንካራ እና ቁጡ ነው። የሚገኘውም በ ኤዥያ ብቻ ነው

2 ቁጥር ሊዮፓርድ ይባላል በጣም ቀልጣፋ አዳኝ ነው። ከራሱ ሰውነት የሚከብዱ እንስሳዎችን ገድሎ ዛፍ ላይ መስቀል የሚያስችል ጥንካሬ አለው

3 ቁጥር:- ቺታ (አቦሸማኔ) ይባላል። ዋና መለያቸው ከ አይናቸው እስከ አፋቸው ድረስ እንደ እንባ የሚወርድ ጥቁር ቀለም አላቸው። የአለማችን ፈጣን ሯጮች ናቸው። የሚጮሁትም እንደ ነብር ሳይሆን እንደ ድመት " ሚያው" እያሉ ነው።

4 ቁጥር :- ግስላ ይባላል። ግስላ ቀለሙ ጥቁር የሆነ ሊዮፓርድ ነው።

5ቁጥር :- ጃጓር ይባላል። ጃጓሮች በጣም ጥሩ ዋናተኞች ናቸው ውስጥ ለውስጥ ጭምር መዋኘት የሚችሉ ሲሆን አስፈሪውን አዞ ገድለው ሁላ ይመገባሉ

6 ቁጥር :- ፑማ ይባላል በጣም ጥሩ ዘላይ እንዲሁም ጠንካራ መንጋጋ ያለው ሲሆን መልኩም ሆነ የሰውነት ቅርፁ ለየት ይላል

መረጃውን ከወደዳችሁት ላይክ እና ሼር በማድረግ አበረታቱን ።
@hulegebmereja

ከ እንስሳት አለም / Animals world

10 Sep, 12:52


#ማንትስ ( mantis)

- ኢትዮጲያን ጨምሮ በአብዛኛው የአለማችን ክፍል የሚገኙ ነብሳቶች ናቸው

- ማንትሶች ሊበሉት ያሰቡትን ነገር ለመግደል በጣም ፈጣኖች እና የራሳቸውን ለየት ያለ የእንቅስቃሴ ጥበብ ይጠቀማሉ።

- " ኩንጉፉ " በመባል የሚታወቀው የቻይና ካራቴ ትምህርት ላይ የ ማንትስ ጥበብ የተሞላበት የአደን እንቅስቃሴዎችን በትምህርት መልክ ይወስዳሉ። የሰው ልጅ ከዚች ነብሳት ራስን መከላከል እና የ ማጥቃትን ጥበብን ተምሯል

- ቀለማቸው ከዛፎ ቅጠሎች ጋር ስለሚመሳሰሉ ቅጠል ላይ ሲቆሙ በአይን ለማየት ያስቸግራሉ

- በጣም የሚያስገርመው ወንዱ እና ሴቷ ማንትሶች ፆታዊ ግንኙነት ካደረጉ በኋላ ሴቷ ማንትስ ወንዱን ሙሉ ለሙሉ ቀረጣጥፋ ትበላዋለች።ከሴቷ ግድያ ለማምለጥ የሚችሉት ከ 10 % አይበልጡም😢

- ማንትሶች በትክክለኛው የአይን አቀማመጥ የተቀመጡ 2 ትላልቅ አይን ያላቸው ሲሆን ጭንቅላታቸው ላይ ደግሞ በጣም ትናንሽ 3 አይኖች አሏቸው። በአጠቃላይ 5 አይኖች አላቸው

- እጃቸው ላይ ያለው መጋዝ መሰል ነገር በቀላሉ ያደኑትን ነገር ለመቆራረጥ እና ጭምቅ አርጎ ለመያዝ ይጠቅማቸዋል

- ማንትሶች በአደን ወቅት ፈጣን አጥቂ ቢሆኑም ሲራመዱ ግን እጅግ በጣም ቀርፋፋዎች ናቸው።

- እነዚህ ማንትሶች ነብሳቶችን ፣ ወፎችን፣ እባቦችን እንዲሁም እስስቶችን ይበላሉ። ሲበሉ ደግሞ ገድለው ሳይሆን በህይወት እያለ ነው መዘልዘል የሚጀምሩት

- ማንትስ በድንቅ የአደን ስልት ትልቅ እስስት በመጋዟ ቀርጥፋ ስትበላው የሚያሳይ ቪዲዮ የ Youtube ገፃችን ላይ ስለለቀቅን ከታች ባለው ሊንክ ገብታችሁ እንድትመለከቱ እንጋብዛለን
ሊንክ :- https://youtu.be/tf8JKX9jWI4

ከ እንስሳት አለም / Animals world

03 Sep, 12:50


#የአፍሪካ_ዝሆን

- የ አፍሪካ ዝሆን መሬት ላይ ከሚኖሩ እንስሳቶች በሙሉ ቁጥር 1 ትልቁ ነው

- የ አፍሪካ ዝሆን ትላልቅ ጆሮዎች የሰውነት ሙቀቱን ለመቀነስ ይረዱታል ( በሙቀት ሰዓት ጆሮዎቹን በማራገብ ራሱን ያቀዘቅዛል)

- የ አፍሪካ የዝሆን ኩንቢ እስከ 40,000 የሚደርስ ጡንቻዎች አሉት።

- ኩንቢያቸው እንደ እጅ ለመሸከም ፣ ለመቀንጠስ እና ለመጉረስ ይገለገሉበታል ፣ እንደ አፍንጫ ያሸቱበታል ፣ ውሀ ለመጠጣት ፣ ድምፅ ለማውጣት ፣ ራሳቸውን ለመከላከል እና ለማጥቃትም ያገለግላቸዋል

- ሴት ዝሆን አርግዛ ለመውለድ 2አመት ይፈጅባታል

- ዝሆኖች ቁመታቸው እስከ 3 ሜትር ይደርሳል

- በ ቀን 190 ሊትር ውሀ ይጠጣሉ ( ይገርማል )

- እስከ 5400 ኪሎ ይመዝናሉ

- የ እድሜ ጣርያቸው 70 አመት ነው

- በዝሆኖች ዘንድ ወንድ መሪ መሆን አይችልም። በእድሜ ትልቅ የሆነችው ሴት ዝሆን መንጋውን ትመራለች
ምንጭ :- National Geographic Wild

ሼር በማድረግ ገፃችን እንዲያድግ እንዲሁም የበለጠ እንድንሰራ ያበረታቱን መልካም ቀን
@hulegebmereja

ከ እንስሳት አለም / Animals world

02 Sep, 11:28


#ኦራንጉታን

- ኦራንጉታኖች የሚገኙት በ ማሌዢያ እና በኢንዶኔዥያ ፤ ሱማትራ እና ቦርኔኦ በሚባሉ ደሴቶች ብቻ ነው። ፊታቸው ጠፍጣፋ ነው

- ወንዱ ኦራንጉታን ከ ሴቷ ኦራንጉታን በእጥፍ ክብደቱ ይበልጣል። ማለትም ሴቷ 50 ኪሎ ገደማ ስትሆን ወንዱ ደግሞ 100 ኪሎ ይመዝናል

- የሰው ልጅ ኦራንጉታኖችን አሰልጥኗቸው በምልክት ቋንቋ ከሰው ጋር እንዲግባቡ ማድረግ ችሏል።

- ከ አንዱ ዛፍ ወደ ሌላኛው ዛፍ ለመሄድ እንደ ጦጣ አይዘሉም። አንዱን ቅርንጫፍ ከያዙ በኋላ ሌላውን በመልቀቅ ( በመንጠላጠል) ነው የሚጓዙት። ያረጁ ወንዶች ግን ከ ክብደታቸው እና ከእድሜያቸው አንፃር መሬት ወርደው ከተጓዙ በኋላ የሚፈልጉት ዛፍ ጋር ሲደርሱ ይወጣሉ።

- እግሮቻቸውም ሆነ እጆቻቸው እኩል እንደ እጅ ነው የሚያገለግሉት በሁሉም መጨበጥ ይችላሉ ። በቀላሉ ባለ አራት እጅ ማለት ይቀላል

- አዲስ የተወለዱ ኦራንጉታኖችን የምትንከባከበው እናትየዋ ብቻ ናት። አባት ኦራንጉታን ልጅ አያሳድግም

- ቁመታቸው እንደ ሰው ከ 1.4ሜትር እስከ 1.8 ሜትር ይሆናል

- አማካኝ የ እድሜ ጣርያቸው 45 ነው
ምንጭ :- National Geographic Wild

ሼር በማድረግ ገፃችን እንዲያድግ እንዲሁም የበለጠ እንድንሰራ ያበረታቱን መልካም ቀን
@hulegebmereja

ከ እንስሳት አለም / Animals world

01 Sep, 09:23


#ሽልምልም_ጅብ

- ሽልምልም ጅብ ብዙ ጊዜ ጥንብ ይበላል እንጂ ማደን አይፈልግም። ካደነ ግን እስከ መካከለኛ ክብደት እንስሳቶች መግደል ይችላል

- የጫካ ፍራፍሬዎችንም ይመገባል

- ሽልምልም ጅቦች እንደ ተራ ጅብ በቀን እንደልብ አይታዩም። በጭለማ መንቀሳቀስ ነው የሚወዱት

- ምንም የሞተ ነገር አያመልጣቸውም ። ከፍተኛ በሆነው የማሽተት ችሎታቸው እያንዳንዷን ክፍተት እና ጉድጓድ እያነፈነፉ ፈልገው የሞተ ነገሮችን ይመገባሉ

- ሽልምልም ጅቦች ከ ተራ ጅብ የሚለያቸው ምግብ የሚፈልጉት ለብቻቸው እንጂ በጋራ አይደለም።

- ሽልምልም ጅቦች ልጆች ሲወለዱ አይናቸው ተጨፍኖ ጆሮአቸውም ተዘግቶ ነው። ከ 5- 9 ቀናቶች ውስጥ ዓይናቸው ይከፈታል

- የ ሽልምልም ጅብ ቡችላዎች ከተወለዱ ከ 6 ወር በኋላ ነው ከ እናታቸው ጋር በመሆን የመጀመሪያ የምግብ ፍለጋ ማድረግ የሚጀምሩት
ምንጭ :- አጥቢዎች መፅሀፍ (ዶ/ር ሰለሞን ይርጋ)

ሼር በማድረግ ገፃችን እንዲያድግ እንዲሁም የበለጠ እንድንሰራ ያበረታቱን መልካም ቀን
@hulegebmereja

ከ እንስሳት አለም / Animals world

30 Aug, 10:12


#አዋልዲጌሳ

- የ አዋልዲጌሳ ጥርሶች ለየት ያሉ ናቸው። የፊት ጥርስ እና የውሻ ክራንቻ የላቸውም ነገር ግን 20 መንጋጋ ጥርሶች አሏቸው

- ጠርሶቻቸው ውስጥ ብዙ ትቦዎች አሏቸው

- በየ ጣቶቻቸው ጫፍ ላይ አካፋ የመሳሰሉ ረጃጅም ጠንካራ ኮኮኔዎች አሏቸው። ይሄም ጉድጓድ በፍጥነት ለመቆፈር ይረዳቸዋል

- አዋልዲጌሳ ከአጥቢዎች ሁሉ የበለጠ የመቆፈር ችሎታ አላቸው

- ክብደታቸው እስከ 65 ኪ.ግ ይደርሳል

- አዋልዲጌሳዎች በአብዛኛው ጊዜ የሚንቀሳቀሱት በ ለሊት ነው።

- በ በጋ የሚመገቡት ጉንዳን ሲሆን በ ክረምት ደግሞ ምስጥ ይመገባሉ

- አዋልዲጌሳዎች ጉድጓዳቸውን ለቀው ሲወጡ ሌሎች እንደ ከርከሮ እና እንደ እባብ አይነት እንስሳቶች ገብተው ይኖሩበታል

- ልክ እንደ ድመት አዋልዲጌሳዎች ዓይነ ምድራቸውን ጉድጓድ ቆፍረው ከተፀዳዱ በኋላ በጥንቃቄ ይቀብራሉ

- ከ 7 እስከ 8 ወራቶች አርግዘው አንድ ግልገል ይወልዳሉ
ምንጭ :- አጥቢዎች መፅሀፍ

ሼር በማድረግ ገፃችን እንዲያድግ እንዲሁም የበለጠ እንድንሰራ ያበረታቱን መልካም ቀን
@hulegebmereja

ከ እንስሳት አለም / Animals world

24 Aug, 11:34


- አንበሳ ከጠገበ መልሶ እስኪርበው ድረስ ለ አደን አይነሳም ፣ ሊዮፓርዶች ግን በፎቶ ላይ እንደምታዩት ቢጠግቡም እንኳን አድነው ለነጋቸው ዛፍ ላይ ሰቅለው ሰቅለው ያስቀምጣሉ። ይህ የሚያሳየው አንበሳ "የ ነገን ፈጣሪ ያውቃል ዛሬ ብቻ ልኑር" የሚል ሲሆን ሊዮፓርዶች ግን " ለነገ ዛሬ መቆጠብ " የሚሉ ናቸው።

- ሊዮፓርዶች የመራቢያ ወቅት የላቸውም በማንኛውም ጊዜ መራባት ይችላሉ

- የሊዮፓርድ ልጆች ሲወለዱ ለጥቂት ጊዜ አይናቸውን አይገልጡም

- ህፃናቶቹ ሊዮፓርዶች ከተወለዱ እስከ 8ኛው ሳምንት ድረስ ከእናታቸው ከተለዩ ጫካ ውስጥ በጠላት የመሞት እድላቸው ከፍተኛ ነው።

- ሊዮፓርዶች ከ 10 እስከ 15 አመት የመኖር እድል አላቸው

ምንጭ :- National Geographic Wild
@hulegebmereja

ከ እንስሳት አለም / Animals world

23 Aug, 10:15


#ከርከሮ

- ከርከሮዎች ሲሞቃቸው ጭቃ ውስጥ ይተኛሉ። ጭቃው ሰውነታቸውን ቀዝቀዝ ያደርግላቸዋል

- ከርከሮ ወደ ጉድጓዱ የሚገባው ወደ ኋላ ነው። ምክንያቱ ደግሞ ጠላት ወደ ጉድጓዱ ቢገባ ጀርባውን ሳይሆን ፊቱን ስለሚያገኘው ራሱን ለመከላከል ይጠቅመዋል

- 1 ከርከሮ በቀን በአማካኝ 7 ኪሎሜትር ይጓዛል

- ከርከሮዎች ከጠላታቸው ሲያመልጡ ጭራቸውን ሽቅብ አቁመው ነው

- አፋቸው አካባቢ ረዘም ብለው የሚታዩት ሹል ነገሮች የውሻ ክራንቻ ጥርሳቸው እንጂ ቀንድ አይደለም

- ሴት ከርከሮ ከ 160 እስከ 170 ቀናት አርግና ነው የምትወልደው። በአንድ ጊዜ ከ 2 እስከ 3 ልጆችን ትወልዳለች
ምንጭ :- አጥቢዎች መፅሀፍ ( ዶክተርነት ሰለሞን ይርጋ )

ሼር በማድረግ ገፃችን እንዲያድግ እንዲሁም የበለጠ እንድንሰራ ያበረታቱን መልካም ቀን
@hulegebmereja

ከ እንስሳት አለም / Animals world

20 Aug, 12:45


#ሸለመጥማጥ

- ሸለመጥማጦች በጫካም ሆነ ሰው በሚበዛባቸው ቦታዎች የሚኖሩ ስጋ በል እንስሳቶች ናቸው።

- በኢትዮጲያ ብቻ የሚገኘው የሸለመጥማጥ ዝርያ የታወቀ የዶሮ ሌባ ነው። ዶሮ የሚረባበት ቤቶችን ከሩቁ በማሽተት ያውቃል።
በአፍሪካ ውስጥ ብዙ የሸለመጥማጥ ዝርያዎች አሉ

- እንደ ሰው ልጅ ሸለመጥማጦችም 5 ጣቶች ነው ያላቸው

- ሸለመጥማጦች ግለኛ ናቸው ለብቻቸው መኖር ነው የሚወዱት። ህፃናቶችም ከ እናታቸው የሚለዩት ጡት መጥባት እንዳቆሙ ነው

- ሸለመጥማጦች ከፍተኛ የሆነ የማሽተት ብቃት አላቸው።

- አደን የሚያድኑት በለሊት ስለሆነ ቀን ቀን የመታየት እድላቸው ጠባብ ነው።

- ሸለመጥማጦች ቅባታማ የሆነ ሽታ ያለው ፈሳሽ የሚያመነጭ እጢ አላቸው። ያን ፈሳሽ በዛፎች ላይ በመታከክ ይለቀልቁታል። ፈሳሹ ይህ የኔ ድንበር ነው የሚል ማስጠንቀቂያ ነው።

- የሚመገቡት ዶሮ ፣ አይጥ ፣ የለሊት ወፍ እና የመሳሰሉትን ነው

- ሸለመጥማጦች በ 1 አመት 2 ጊዜ የሚወልዱ ሲሆን በ 1 ጊዜ ከ 2 እስከ 3 ልጆች ይወልዳሉ።

ምንጭ:- አጥቢዎች መፅሀፍ ( ዶ/ር ሰለሞን ይርጋ)
@hulegebmereja

ከ እንስሳት አለም / Animals world

19 Aug, 12:49


አደገኛው የ እባቦች ደሴት !!!

በ አለማችን ላይ መሬቱም ሆነ ዛፉ በአጠቃላይ ሁሉም ቦታ መርዛማ እባቦች ብቻ የሚገኙበት ምንም አይነት አጥቢ እንስሳ የማይገኝበት አደገኛ ደሴት እንዳለ ያውቃሉ ? ደሴቱ በሙሉ የ እባብ ክምር ብቻ ነው ።
ስለዚህ አስገራሚ እና አስፈሪ ደሴት ሙሉ መረጃ ከ አስደናቂ ምስሎች ጋር አዘጋጅተን የ Youtube ገፃችን ላይ ለቀናል። እንድታዩ ተጋብዛችኋል

ሊንክ 👇
https://youtu.be/NXVOVhBev0k