የወረታ ከተማ ሰለፊያ የቂራዓት መድረክ @weretaselefiyaqiraat Channel on Telegram

የወረታ ከተማ ሰለፊያ የቂራዓት መድረክ

@weretaselefiyaqiraat


በወረታ ከተማ በሸይኽ አሕመድ አቡ ኑሀ የሚሰጡ ኹጥባወች፣ የዓቂዳ፣የመንሀጅ፣የፊቅህ፣የሀዲስ፣የአህካም፣የሶርፍ፣የነህው እና ሌሎችም የፈን ቂራአቶች የሚሰጡበት ቻናል ነው።ሁላችንም እንጠቀምበት

የወረታ ከተማ ሰለፊያ የቂራዓት መድረክ (Amharic)

ሰላም ሰላም! እንኳን ወንድሞቻችን፣ ወንድሙን፣ እና ሴትየብ፣ ሴትየብ፣ በወረታ ከተማ ሰለፊያ የቂራዓት መድረክ በአጭር መዝገበ አገልግሎት ውስጥ ነን። የምስክር። ካርቬት። የሚጋለጡ እና ሌሎች መድረኮችን ይምረጡ ፡፡ እንዴት ትንሽ ነሽ፣ በወረታ ከተማ በሸይኽ አሕመድ አቡ ኑሀ የሚሰጡ ኹጥባወች፣ የዓቂዳ፣ የመንሀጅ፣ የፊቅህ፣ የሀዲስ፣ የአህካም፣ የሶርፍ፣ የነህው እና ሌሎችም የፈን ቂራአቶች የሚሰጡበት ቻናል ነው። ሁላችንም እንጠቀምበት ።

የወረታ ከተማ ሰለፊያ የቂራዓት መድረክ

24 Nov, 16:26


ይደመጥ ስለ መስጂዳችን

የወረታ ከተማ ሰለፊያ የቂራዓት መድረክ

14 Nov, 09:54


መስጂዱ ያለበት ሁኔታ☝️☝️☝️

የወረታ ከተማ ሰለፊያ የቂራዓት መድረክ

06 Nov, 10:30


قال الامام البربهاري
-رحمه الله-:

" ومن خالف الكتاب والسنة فهو صاحب بدعة وإن كان كثير العلم والكتب ".

📚شرح السنة ١٠٤

የወረታ ከተማ ሰለፊያ የቂራዓት መድረክ

05 Nov, 16:05


🎤ይሄንን ርዕስ(ዑዝር ቢል ጀህል ጋር ተያያዥነት ባለው መልኩ) በሰፊው እንመለስበታለን ኢንሻአሏህ።

የወረታ ከተማ ሰለፊያ የቂራዓት መድረክ

05 Nov, 16:01


🔉ተክፊረል ሙጥለቅ እና ተክፊረል ሙዐየን

🟥 እውነት ተክፊሮች እንደሚሉት ተክፊረል ሙጥለቅ እና ተክፊረል ሙዐየን የሚባል የለም?

🟥 ግለሰብ ላይ በኩፍር ለመፈረጅ ማንም ግለሰብ እየተነሳ ብይን መስጠት ይቺላል? ወይስ የእውቀት ባለቤቶች ናቸው?

🔊መልሱን ከሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን

የወረታ ከተማ ሰለፊያ የቂራዓት መድረክ

03 Nov, 17:54


https://t.me/+Fvah5bEZ0zNlYmM8

የወረታ ከተማ ሰለፊያ የቂራዓት መድረክ

03 Nov, 17:23


መስጂደል አቅሷ ግንባታው ያለበት ደረጃ....
በአሏህ እገዛ ከዛም በወንድምና እህቶች እገዛ እዚህ ላይ ይገኛል
አሁንም የአሏህን ቤት መገንባታችንን አንዘንጋ
ስንትና ስንት ሰወች አሉ ይሄ ከቀብር በኋላም የሚሻገር ኸይር ስራ ያለፋቸው????


ንግድ ባንክ---1000450118013
ዳሽን ባንክ----2918929445411
አቢሲኒያ-------86404648

የአካውንት ስም👇
ሰዒድ ዩሱፍ
ዒሳ ይብሬ እና
ሙስጠፋ ሱለይማን

የወረታ ከተማ ሰለፊያ የቂራዓት መድረክ

03 Nov, 03:01


♦️የልብ ንፅህና

↪️ ወንድሜ ሆይ! የላይ ገፅታህን ከማጥራት ይልቅ ልብህን በማጥራት ላይ ጥረት አድርግ!!


↪️ ስንትና ስንት ሰው ይሰግዳል …
▪️ይፆማል …
▪️ሰደቐ ያደርጋል …
▪️ሀጅ ያደርጋል …

ነገር ግን ልቡ የተበላሸ ነው
እነሱም ኸዋሪጆች ናቸው ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ ስለነሱ የተናገሩላቸው:-
▶️ እነሱ ይሰግዳሉ
▶️ ይፆማሉ
▶️ ፀደቐ ይሰጣሉ
▶️ ቁርዓንን ያነባሉ
▶️ የለይል ሶላት ይቆማሉ
▶️ ያለቅሳሉ
▶️ አንድ ሶሃባ ሶላቱን ከነሱ ሶላት ብያነፃፅር ሶሃባው ሶላቱን ያሳንሳል/ከነሱ አንፃር የሱን ሶላት ይንቀዋል

ነገር ግን ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) “ኢማናቸው ከጎሮሯዋቸው አልፎ አይወርድም።” ብለዋሉ።
ኢማኑ ልባቸው ውስጥ አይገባም። የላይ ገፅታቸው መልካም ከመሆኑም ጋር ግን አልጠቀማቸውም!

⛔️ በላይ ገፅታህ አትታለል! ከሁሉም ነገር በፊት ወደ ልብህ ተመልከት!!
አላህ ልቤንና ልባችሁን እንዲያሳምረው እጠይቀዋለሁ!!
👉🏾 አንገብጋቢው ነገር እሱም ልብ ነው!!

[ሸርህ ሪያድ አስ-ሷሊሂን 2/327 ሊብኒ ዑሰይሚን]
✍🏻ኢብን ሽፋ
#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

የወረታ ከተማ ሰለፊያ የቂራዓት መድረክ

08 Oct, 05:37


በአይነቱ ልዩ የሆነ ታላቅ ኢስላማዊ ኮንፈረንስ

የኮንፈረንሱ መሪ ቃል “ዲናችንን ማወቅ መተግበርና ማስተማር”

🏝 የኢትዮጵያ አህለ ሱና ኢስላማዊ ማህበር ታላቅ ሀገር ቀፍ ኢስላማዊ ኮንፈረንስ ጥቅምት ላይ   በአዲስ አበባ ከተማ ለማካሄድ አስቧል።
ለዚህ ፕሮግራም የአዳራሽ ኪራይ፣ ለተሳታፊዎች ሻይ ቡና ፣ ለዑለማዎች ትራንስፖርትና ማረፊያ ወዘተ የሚያስፈልገውን ወጪ ለመሸፈን እንዲቻል የአንድ ሰው መግቢያ ትኬት 1000 ብር ነው።

🔹 ስለሆነም ትኬት በአካል መግዛት ለምትፈልጉ፦
➡️  አል ኢስላሕ መድረሳ
➡️  ዳሩ ሱና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል

🔹በባንክ አካውንት ለምትጠቀሙ
የባንክ አካውንት ቁጥር፦ 1000650550718
          ሙሒዲን ሳሊሕ እና ዩሱፍ ኸድር

   የኢትዮዽያ አህሉ ሱና ኢስላማዊ ማህበር

https://t.me/alateriqilhaq

የወረታ ከተማ ሰለፊያ የቂራዓት መድረክ

20 Sep, 14:29


https://t.me/weretaselefiya

የወረታ ከተማ ሰለፊያ የቂራዓት መድረክ

20 Sep, 14:28


አሁን ላይ መስጁዱ ያለበት ሁኔታ ይሄን ይመስላል☝️

የወረታ ከተማ ሰለፊያ የቂራዓት መድረክ

10 Sep, 15:00


የ መስጂዱ ሁኔታ በአጭሩ በዚህ የድምፅ ፋይል ተቀምጧል።

ቀጣይ ያለበትን ሁኔታ የሚያሳይ ሌላ Video ይዘን እንመለሳለን ኢንሻአሏህ።

https://t.me/weretaselefiya

የወረታ ከተማ ሰለፊያ የቂራዓት መድረክ

10 Sep, 14:37


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
የአሏህ ፈቃድ ሆኖ መስጂዳችን መሰረቱ በዚህ በምታዩት መልኩ በ 4 ሜትር ወጥቷል(ኢንተርኔት ስላላገኘን ነው እንጂ ታችኛው አርማታው ተሞልቶ አልቋል)

እስከዛሬ ድረስ ስራው ሳይቋረጥ በአሏህ ፍቃድ እና እገዛ ከዛም በወንድሞች እገዛ የቀጠለ ሲሆን ታችኛው በምናየው መልኩ ተጠናቋል(አርማታ ተሞልቶ ቀጣይ እንለቃለን ኢንሻአሏህ) ለአሏህ ላቅ ያለ ምስጋናው የተገባው ነው።

አሁን ላይ በእጃችን ያለው ብር አልቆ ግን ስራው እንዳይቋረጥ ሲባል በተወሰኑ ከዚሁ ባሉ በሱና ወንድሞች እስከ 500ሺ ብር በዚህ ቅርብ ቀን ሰጥተውና ስራው ቀጥሏል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ያለን ገንዘብ እያለቀ ስለሆነ የሰለፊያ ደዕዋ የሚያሳስባችሁ ወንድምና እህቶች ስራው እንዳይቆምና በቅርቡ ቶሎ ወደ መስጂዳችን ገብተን ዒባዳችንን እና ቂራአታችን እንድንቀጥል የቻልነውን ሁሉ እናድርግ።ይሄ እድል ላይገኝ ይቺላል(አንድ አሏህ የወፈቀው ሰው መጥቶ ሊሰራው ይቺላል) እና ከዛ በፊት አሏህ የኸይር ስራን በር ከፍቶልናል ከሞትን በኋላ የማይቋረጥ አጂር ያለው ስራ አመቻችቶልናል እና እንጠቀምበት።እኛ ባንቺል እንኳን አቅም ላላቸው ለሰለፍይ ወንድሞች share እናድርገው።

ሰሞኑንም አንድ እዚሁ ያለ ወንድም 100ኩንታል ሲሚንቶ ነይቶልናል።ሌላ ወንድሞችም እስከ 100ሺ ነይተውልናል።

አሁን ላይ የምንፈልገው ላይኛውን ስላቭ ሞልተን ፎቋን ጨርሰን ታችኛውንና ላይኛውን ቦሎኬት መሙላት ነው።


በዚህም ሂደት ለበር፣ለመስኮት፣ለቦሎኬት እና ለሌሎች ወጭወች ሆኖ የታችኛውን እስከ ስላቭ ጨርሰን ለመግባት 800ሺ ሲያስፈልገን።

በእጃችን የተወሰነ ፌሮ ብረት፣ሲሚንቶ፣አሸዋ፣ጠጠር ይገኛል።

ያለን ንብረት የተወሰነ የሚያስቀጥለን ቢሆንም ነገር ግን ስለማያስጨርሰን እና ስራው እንዳይቆም ስንል ወደናንተ ጉዳዩን አምጥተነዋል።

G+1 ለመጨረሰ ደግሞ እስከ 1.6 ሚሊዮን ያስፈልገናል።ስለሆነም ሁላችንም ለአኺራችን ስንል አሻራችንን እናሳርፍ።


እኛ ሰበቡን እናድርስ አሏህ ግን ያሳካዋል ኢንሻአሏህ።

https://t.me/weretaselefiya

የወረታ ከተማ ሰለፊያ የቂራዓት መድረክ

03 Sep, 05:48


📚ይህ የሸይኻችን አሸይኽ አህመድ አወል አቡ ኑሀ ፈዋኢዶችና ትምህርቶች የሚተላለፍበት የቴሌግራም ቻናላቸው ነው።ስለሆነም ሁላችንም ጆይን በማድረግና ሼር በማድረግ የአጅሩ ተቋዳሽ እንዲሆኑ እንመክራለን።
👇👇#join and share👇👇
https://t.me/shekabunuhaahmed
https://t.me/shekabunuhaahmed
https://t.me/shekabunuhaahmed

የወረታ ከተማ ሰለፊያ የቂራዓት መድረክ

03 Sep, 05:47


ልዩ የመውሊድ ስጦታ ለአስተዋዮች!!
—————ክፍል 2
ክፍል 1 በሚከተለው ሊንክ ታገኙታላችሁ
https://t.me/IbnShifa/3362

እህቴ ሆይ! እስቲ ልጠይቅሽ? በአላህ ይሁንብሽ! ለኔ ባትመልሺልኝም ቆም ብለሽ አስተውለሽ ጥያቄውን ለራስሽ መልሺው። ከላይም ከታችም ያለው ጥያቄ አንቺንም ይመለከታል!! ግን ተጨማሪ በሴትነትሽ የተወሰኑ ጥያቄዎችን ልጨምርልሽ ወደድኩ…

» መውሊድ ማከብረው ለነቢዩ ﷺ ውዴታ መግለጫ ነው ካልሽ ነቢዩ ﷺ በሚጠሉት በቢድዓ መንገድ ነው ምትገልጪላቸው እንዴ?
ከልብሽ አስተውይ! አንቺን ባልሽ እወድሻለሁ እያለሽ አንቺ በእጅጉ የምትጠይውን ነገር እያወቀ ሚሰራ ከሆነ እውነትም ይወደኛል ብለሽ ታምኚዋለሽ?!

» ወይስ የነቢዩን ﷺ ውዴታ ምትገልጪበት ሱናቸውን ሁሉ ጨርሰሽ ተግብረሽ ጭማሪ አስፈልጎሽ በመውሊድ ውዴታቸውን ለመግለፅ ነው የተነሳሽው?!

» ቆይ ግን አንቺ ነቢዩን ﷺ ከተወዳጁ የጓደኛቸው የአቢበክር ልጅና ሚስታቸው ከሆነችው ዓኢሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) የበለጠ ትወጂያቸዋለሽ?!

» ታዲያ ይህች ውድ እናትሽ የታላቁ ነቢይ ድንቅና ውድ የሆነችው ምስታቸው ዓኢሻ፣ ለዚህ ህዝብ ዲኑን ያስተማረችው ምርጧ የዚህ ህዝብ እናት መውሊድን አክብራለች?! የትና መቼ?

» ለመሆኑ በአለባበስሽ፣ በአመጋገብሽ፣ በአነጋገርሽ፣ ነቢዩ ﷺ ያዘዙሽን ፈፅመሻል?

» ብረት እንደሚገፋ ወንድ ሰውነትሽን ወጣጥረሽ፣ እንደ አርሶ አደር (ገበሬ) ቁምጣ የሆነ ቁርድ ለብሰሽ፣ ሰርግ ሳይኖር ሰርግ አስመስለሽ ድቤ እየደበደብሽ የሞቱበትን ቀን እያከበርሽ ነው እወዳቸዋለሁ ምትይኝ?! ቤትሽ ውስጥ አህያ ቢኖርና መሳቅ ቢችል ይህን ሰምቶሽ ሁሌ እያስታወሰ በተግባርሽ ይስቅብሽ ነበር።

» ለመሆኑ ነቢዩ ﷺ "ሽቶ ተቀብታ ከቤቷ የወጣች ሴት ዝሙተኛ ናትና ወደ ቤቷ ተመልሳ የጀናባ ትጥበትን ትታጠብ።" እያሉ፣ ተቀባብቶ መውጣቱ ሀራም መሆኑን እያወቅሽ፣ ተቀብተሽ እየወጣሽ ተመልሰሽም እንደ ጀናባ ትጥበት መታጠብ ሳትችይ ነው እንዴ ስለምወዳቸው ነው መውሊዳቸውን የማከብረው ምትይው? ትንሽ እንኳን ሀፍረት አይሰማሽም በአላህ?! አትሸማቀቂም?!
ይልቅ ወደራስሽ ተመለሺ፣ ሱናቸውን ካላወቅሽ ተማሪ!! ቁርኣንና ሀዲስን በትክክለኛ ሰዎች ተማሪ። ተግብሪው። ዓኢሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) ለባሏና ለተወዳጁ ነቢይ ፍቅሯን እና ውዴታዋን የገለፀችበት መንገድ (እሱም ችለሽ ከተገበርሺው) በቂሽ ነው!!! እሷ የገለፀችበትን መንገድ ለማወቅ ከፈለግሽ፣ ቁርኣንና ሀዲስን ሳያጭበረብሩ በትክክል በሚያስተምሩ ሰዎች ላይ መማር ነው።

⑦ » አላህ ዲኑን ሙሉ አድርጌዋለሁ እያለ ነው፣ አንተ ከዲኑ ውጪ የሆነውን መውሊድን አከብራለሁ ስትል፣ ከአላህ በላይ በዲኑ ላይ ህግ አወጣለሁ ስለ ዲኑም አውቃለሁ እያልከ ነውን??

"ዑለማዎች እንዲከበር አዘዋል" አትበለኝ!!
⑧ » የትኛዎች ዑለማዎች ናቸው?
እነዚያ መንገዱን ተሳስተው አሳሳቾች ናቸው? ነቢዩ ﷺ ጠመው አጥማሚ መጥፎ የጥመት ዓሊሞች ያሉዋቸው ናቸው?
⑨ »  ወይስ ከነቢዩ ﷺ ዲኑን አቀበት ቁል ቁለቱን፣ ጋራ ሸንተረሩን፣ ወጥተው ወርደው ቸነፈር እያሰቃያቸው፣ ወርሰው በትክክል ያስወረሱንን እንደ እነ ኢማሙ ሻፊዒይና ኢማሙ አህመድ ያሉ ብርቅዬ የጨለማ ማብራት የነበሩ ከዋክብቶችን ነው ምትለኝ?
» እነሱ መውሊድን አክብረዋልን? የታለ ማሰረጃህ? ኢማሙ አቡ ሀኒፋ፣ ኢማሙ ሻፊዒይ፣ ኢማሙ አህመድ፣ ኢማሙ ማሊክ አክብረዋል????

ይልቅ በትክክል የአላህ እና የመልእክተኛው ﷺ ወዳጅ ነኝ ካልን፣ በምን እንደሚገለፅ እንዲህ በማለት አላህ በተቀደሰው ቃሉ መልሱን በአጭሩ አስቀምጦታል:-

﴿قُل إِن كُنتُم تُحِبّونَ اللَّهَ فَاتَّبِعوني يُحبِبكُمُ اللَّهُ وَيَغفِر لَكُم ذُنوبَكُم وَاللَّهُ غَفورٌ رَحيمٌ﴾ آل عمران ٣١

አላህን የምትወዱ እንደሆናችሁ #ተከተሉኝ (በላቸው)፣ አላህ ይወዳችኋልና። ኃጢያቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና። አላህ መሃሪ አዛኝ ነው።” ኣል ዒምራን 31

እውነት ከልባችን አላህን እና መልእክተኛውን ﷺ የምንወድ ከሆነ ውዴታችን መግለፅ የምንችለው በትክክል መልእክተኛውን በመከተል ብቻና ብቻ ነው!!።
ብዙ ማለት ብፈልግም፣ ብዙ ሰው ረጅም ፅሁፍ ማንበብ ስለማይወድ እዚህጋ ለማቆም እገደዳለሁ።
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)

#Join ⤵️
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa

1,610

subscribers

30

photos

12

videos