የወሎ ድምፅ/Voice Of Wollo @voiceofwollo Channel on Telegram

የወሎ ድምፅ/Voice Of Wollo

@voiceofwollo


በዚህ የቴሌግራም ቻናል ትክክለኛና ጠቃሚ የሆኑ አጠቃላይ በወሎ ፖለቲካዊ፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁነቶችንን እናቀርባለን።
የቻናላችን አባል ይሁኑ

የወሎ ድምፅ/Voice Of Wollo (Amharic)

በወሎ ድምፅ ቴሌግራም ቻናል አጠቃላይ ተሳታፊ ለቴሌግራም መጽሐፍና ምርጥ የቴሌግራም ፊልምን ለማድረግ በእንስሳ መመልከት ከሚገባ በተደረገ አጠቃላይ በመመልከት የሚገኝ ሐምፒነር ብሪፖራቶችና የቴሌግራም ዝግጅቶችን እናዝናለን። ከዚህም በቴሌግራም እና በተለያዩ ምርጥ ስነ-ምግባር ፓላሲያና ለማግኘት የሚገኝ ውይይትእንዲሁም የቴሌግራም ቻናል በማህበራዊና በማህበረሰብ በኃላ በማህበረሰብ በማህበረሰብ አወዳዳለው እና ምሳለ ኢኮኖሚያዊ መረጃና ቁላቁሉን ለመማጸን በፊት እንችላለን።

የወሎ ድምፅ/Voice Of Wollo

25 Jul, 20:41


የአማራ ክልላዊ መንግስት 2 የፀጥታ ሀላፊዎችን አሰናበተ።
____
የአማራ ክልል መንግስት የክልሉን የፀጥታ ሁኔታ ከገመገመ በኋላ ሀላፊነታቸውን ትተው ከፅንፈኞች ጋር በመሆን ቃለ ማሃላቸውን ክደው ሀገር ሲያፈርሱ ህዝብን ከህዝብ ሲያተራምሱ በመገኘታቸው ሁለቱን ሀላፊወች አግዷል።

1. የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ምክትል ቢሮ ሃላፊ ኮማንደር መንገሻ አውራሪስና

2. የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የፀጥታ አማካሪ ከፋለ እሱባለው ከሃላፊነት ማንሳቱን የተገኘው መረጃ ያሳያል።

የወሎ ድምፅ/Voice Of Wollo

09 Jun, 17:06


#WOLLO|| በጦርነት ለወደሙ አካባቢወች ለመልሶ ግንባታ የተበጀተው 20 ቢሊዮን ብር የት ገባ
______
«በጦርነት የወደሙ አካባቢዎችን ለመልሶ ግንባታ ተብሎ 20 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት መፅደቁ ይታወቃል።በጦርነት ከወደሙት አካባቢዎች መካከል ደግሞ ወሎ በዋነኝነት ተጠቃሽ ነው።ነገር ግን እስካሁን ድረስ መልሶ ግንባታ የሚባል ነገር አልተጀመረም የለም።ስለዚህ ለመልሶ ግንባታው የተበጀተው ብር የት ደረሰ»
የተከበሩ የህዝብ እንደራሴ አቶ ሰይድ መሀመድ

በጀቱ የዋለው ጭራሽ ጦርነቱ ላላያቸውና ለማያውቁት አካባቢወች ነው
የት እና እንደት በእነ ማን አማካኝነት ይህ ገንዘብ ወደ ወሎ እንዳይደረወስ እንደተደረገ ሙሉ መረጃ አለን

@Musab Ibnu Umeyir

የወሎ ድምፅ/Voice Of Wollo

01 Jun, 05:30


ባለፈው ሳምንት ኮንፈረንስ ላይ፦ "እናንተን መሸከም ሰለቸን።ከዚህ በኋላ እኛ ራሳችንን ችለን ለናንተ ሰብስበን የምንሰጠውን ግብር ራሳችንን እናለማበታለን!"
__________________
ባለፈው ሳምንት የደቡብ ወሎ ዞንና የደሴ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በወቅታዊ ሁኔታዎችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ኮንፈረንስ አድርገው ነበር።ኮንፈረንሱ ላይ ብዙ ወቅታዊና ባለፉት 2 አመታት የተፈፀሙ ክስተቶች የተነሱና ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን አመራሩ በባለ 9 ነጥብ የአቋም መግለጫ ሰብሰባውን ጨርሷል።

በዚህ ኮንፈረንስ ላይ ለተገኙት የክልል አመራሮች ከተሰብሳቢወቹ የወሎን ልማትና ከልማት መገለል ብዙ ጥያቄ የተነሳ ሲሆን ከተነሱት መካከልም
"እናንተን መሸከም ሰለቸን።ከዚህ በኋላ እኛ ራሳችንን ችለን ለናንተ ሰብስበን የምንሰጠውን ግብር ራሳችንን እናለማበታለን!" የሚለውና ብዙ ያነጋገረው ይገኝበታል!!
@Musab Ibn Umer

የወሎ ድምፅ/Voice Of Wollo

25 May, 08:00


ከደሴ ከተማ ባልታወቁ ሰዎች ተሰርቃ ለ11 ወራት ተሰውራ የነበረችው ታዳጊ በማህበራዊ ሚዲያ አማካኝነት ተገኘች
======
ባልታወቁ ሰዎች ተሰርቃ ለ11 ወራት ተሰውራ የነበረችው የሦስት ዓመቷ ታዳጊ ሕፃን በማህበራዊ ሚዲያ አማካኝነት ተገኝታለች፡፡

የሦስት ዓመቷ ታዳጊ ሕፃን ረድኤት ዘሩ ሰኔ 12 ቀን 2014 ዓ.ም በደሴ ከተማ ሆጤ ክፍለ ከተማ 07 ቀበሌ ከጓደኞቿ ጋር እየተጫወተች እያለች ነበር ባልታወቁ ሰዎች ተሰርቃ የተወሰደችው።

በደሴ ከተማ አስተዳደር 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ የሴቶችና ሕፃናት ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር የሆኑት የህጻኗ ወላጅ እናት ወ/ሮ ማንጠግቦሽ ደሴ ከሥራ ሲመለሱ ነበር የልጃቸውን መጥፋት የሰሙት።

በሁኔታው የተደናገጡት የረድኤት ቤተሰቦች በፍለጋ ቢደክሙም ሕጻኗን ሊያገኟት አልቻሉም ነበር። በቀጣይ ቀናቶችም በራዲዮና በተለያዩ ማስታወቂያዎች ማፈላለጉን ቢቀጥሉም ሕፃን ረድኤትን አየሁ የሚል ጠፋ።

የፀጥታ ኃይሉ እና የአካባቢው ነዋሪዎች ፍለጋውን ቢያጠናክሩም ሕጻን ረድኤት ሳትገኝ ወራት በወራት እየተተኩ ለአስራ አንድ ወር ያክል የውሃ ሽታ ሆና ቀረች።

ጉዳዩ በከንቲባው ጽሕፈት ቤት ከተያዘ በኋላ እንደ አማራጭ በማኅበራዊ ሚዲያ ልጅቱን የማፈላለግ አማራጭ ተይዞ፣ በደሴ ከተማ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንና በደሴ ብልጽግና ፓርቲ ይፋዊ የፌስቡክ ገጾች የአፋልጉኝ ማስታወቂያ ከሕፃኗ ፎቶ ጋር ተያይዞ ተለጠፈ።

ማስታወቂያውን የተመለከቱ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችም ለበርካታ ሰዎች ማጋራታቸውን ተከትሎ ግንቦት 12 ቀን 2015 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ልጅቱን አየሁ የሚል ጥቆማ ተሰማ።

ለእናት ማንጠግቦሽ ደሴ የተደወለ ስልክ ልጅቱ አዲስ አበባ እንዳለችና በቦሌ ክፍለ ከተማ አካባቢ አንዲት ሴት ለወራት ያክል ለልመና እየተጠቀመችባት እንደኾነ ተነገራቸው።

ቤተሰቦቿም አዲሰ አበባ ለሚያውቋቸው ሰዎች ስለጉዳዩ በማስረዳት ሕፃን ረድኤት ዘሩንና እየለመነችባት ነው ስለተባለችው ግለሰብ ጉዳይ ለፖሊስ እንዲያሳውቁ በማድረግ ግለሰቧ በቁጥጥር ስር ዋለች።

አዲስ አበባ የሚገኙ ዘመዶቻቸውም የጠፋችው ትክክለኝ ልጃቸው መኾኗን ለማረጋገጥ የሕፃን ረድኤት ፎቶ ለወላጆቿ ላኩ። ስለ ሁኔታው ለደሴ ኮሚዩኒኬሽን የተናገሩት እናት ማንጠግቦሽ በእንግልትና ስቃይ ውስጥ የተነሳችውን "የልጄን ፎቶ ስመለከት ጥርጣሬ ገብቶኝ ነበር" ብለዋል።

እናት "ልጄ ለወራት ያክል በደረሰባት እንግልትና ስቃይ መልኳና ሰውነቷ መቀየሯ ታውቆኛል" ሲሉ አስታውሰው፣ ነገር ግን በአካል ሄደው ማየትና ማረጋገጥ ስለፈለጉ ወደ አዲስ አበባ እንደመጡ ይናገራሉ።

"ገና ከርቀት እንዳየኋት ራሴን መቆጣጠር አቃተኝ፤ ቹቹ ብየ ስሟን ጠርቼ እንዳቀፍኳት እንባዬም መፍሰስ ጀመረ፤ ሰውነቴ ተንቀጠቀጠ“ የሚሉት ወላጅ አባት ዘሩ ሰይድ “ፈጣሪ ዳግም እንደ ፈጠረኝ ነው የማምነው” ሲሉ ነበር ስሜታቸውን የገለጹት።

የሕጻን ረድኤት ቤተሰቦች ግንቦት 16 ቀን 2015 ዓ.ም ደሴ ከተማ ሲገቡ በደሴ ከተማ አሥተዳደር የሥራ ኀላፊዎች፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በጎረቤቶቻቸውና ስለ ጉዳዩ በሰሙ በከተማይቱ ነዋሪዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በቤታቸው ተገኝተው እንኳን ደስ ያላችሁ ያሉት የደሴ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ ማኅበራዊ ሚድያን በአግባቡ ከተጠቀምን እንዲህ ልጅን ከቤተሰብ ማገናኘት ይቻላል ብለዋል።

ወንጀለኞችን ለመከላከል ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል ኃላፊነቱን መወጣት አለበት ያሉት ከንቲባው ለወራት በልጃቸው መጥፋት ቅስማቸው ለተሰበረው ቤተሰብ ከተማ አሥተዳደሩ የቤት ስጦታ እንዳዘጋጀላቸውና በፈለጉት ጊዜ መረከብ እንደሚችሉ አስታውቀዋል።

ከሕፃን ረድኤት ዘሩ ያለችበትን የጠቆመችው ምንታምር በለጠ የምትባል በአዲስ አበባ በሊስትሮ ሥራ የሚትተዳደር ሴት መሆኗን የሕጻኗ በተሰቦቿ ተናግረው፤ ለወሮታዋም የደሴ ከተማ አሥተዳደር የ50 ሺህ ብር ሽልማት እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

ሕፃን ረድኤት ዘሩን በመስረቅና ለልመና ስትጠቀምባት የነበረችው ወይንሽት መኮንን የተባለችው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውላ ምርመራ እየተደረገባት ይገኛል።

የወሎ ድምፅ/Voice Of Wollo

09 May, 09:06


#ወሎ|| #ደሴ| #ቦሩ_ሜዳ_ሆስፒታል🙏
__
በደሴ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል ከአንድ ሺህ ለሚበልጡ ሰዎች ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና በዘመቻ መስጠት መጀመሩን አስታወቀ።

የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሲሳይ ተበጀ እንደገለጹት በዓይን ሞራ ግርዶሽ የሚሰቃዩ ሰዎችን ችግር ለመፍታት ነጻ የቀዶ ሕክምና አገልግሎቱ ከትላንት ጀምሮ እየተሰጠ ነው።

ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር መስጠት በተጀመረው የሕክምና አገልግሎት 6 የዘርፉ ስፔሻላይዝድ ዶክተሮችን ጨምሮ ሌሎች የዓይን ሐኪሞች እየተሳተፉ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

ከደሴ፣ ከደቡብ ወሎ፣ ከሰሜን ወሎ እና ከኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች ሕክምናውን እንዲወስዱ በባለሙያዎች ለተለዩ ሰዎች ሕክምናው እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዘመቻው ከሚያዚያ 30 እስከ ግንቦት 4/2015 ዓ/ም ለተከታታይ 5 ቀናት የሚቆይ ሲሆን እስካሁን ከ200 ለሚበልጡ ሰዎች ህክምናው መሰጠቱን አስታውቀዋል፡፡

ዘመቻው በሕክምና መዳን እየቻሉ በተለያየ ምክንያት መታከም ያልቻሉና በዓይን ሞራ ግርዶች እየተሰቃዩ ያሉ ወገኖችን ችግር ለመፍታት የሚያስችል ነው ብለዋል።

በሆስፒታሉ የዓይን ሕክምና ክፍል ሃላፊና የዘመቻው አስተባባሪ አቶ እንዳልክ ያረጋሌ በበኩላቸው፤ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ብዙ ጊዜ ከዕድሜ ጋር ተያይዞ የሚከሰት ነው።

የዓይን ሞራ ግርዶች በወቅቱ ከታከመ እንደሚድን ጠቁመው፣ ይህ ካልሆነ ሙሉ በሙሉ የዓይን ብርሃንን እስከማሳጣት የሚያደርስ መሆኑን ገልፀዋል።

የቀዶ ሕክምና ዘመቻው ዓላማም በሆስፒታል ለመታከም እድሉን ያላገኙ ወገኖችን ለማገዝ መሆኑን አብራርተዋል።

የቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል ባለፉት አራት ዓመታት ከ8 ሺህ ለሚበልጡ ሰዎች የዓይን ሕክምና መስጠት እንደቻለ ከሆስፒታሉ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
(#ደሴ_ኮሙኒኬሺን)

የወሎ ድምፅ/Voice Of Wollo

09 May, 05:51


ከሰውነት ውጭ ምንም አይነት ነገር የማያውቀው የወሎ ማሕበረሰብ እንኳ የዚህ ቫይረስ ተጠቂ ሆኗል!!
__
«በዚህ 5 አመት የገጠመን ፅንፍ የረገጠ የዘውግ ፖለቲካ ደግሞ ይለያል።እናትና ልጅን፣ባልና ሚስቲን፣እህትና ወንዲምን እስከማለያየትና ማገዳደል የሚደርስ ነው።

የሚገርመው ነገር እስከ አሁን ድረስ ከሰውነት ውጭ ምንም አይነት የዘርና እምነት ልዩነቶችን የማያውቀው የወሎ ማህበረሰብን እንኳ ከዛ ከዚህ እያዋከቡ የዚህ መጥፎ ቫይረስ ተጠቂ አዲሆን አድርገውት እያየን ነው።ይህን ለማንም አይበጅም በተለይ የእምነት አባቶችና የሀገር ሽማግሌወች መታገል አለባቸው።ልጆቻቸውን በመቆጣትና በመምከር ከዚህ በሽታ ማከም አለባቸው!»
(ዲ/ን ዳንኤል ክብረት)

የወሎ ድምፅ/Voice Of Wollo

08 May, 12:01


ስልጣንንና ፍላጎትን በኀይልና በጉልበት ለመጫንና ለመንጠቅ የሚደረግን እንቅስቃሴ መታገል እንደሚገባ የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ገለጸ።

ከሚሴ፡ ሚያዝያ 30/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ከሚሴ ከተማ ግድያን የሚቃወም ሕዝባዊ ሰልፍ ተካሂዷል።

ሰላማዊ ሰልፉ ላይ የከሚሴ ከተማና ደዋጨፋ ወረዳ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

በሕዝባዊ ሰልፉ ላይ የህግ የበላይነት ይከበር፣ መሪን በመግደል የሚቆም ትግል የለም፣ እርስ በእርስ በመጋጨት የሚፈሰው ደም እንጂ የሚለወጥ ሀገር የለም፣ ፅንፈኝነት የወቅቱ ፈተና ነው እና ሌሎች መልዕክቶች ተላልፈዋል።

የከሚሴ ከተማና ደዋጨፋ ወረዳ ነዋሪዎች ፅንፈኛ ኀይሎች በክልላችን እንቁ አመራሮች ላይ የሚያደርጉትን ግድያ እንቃወማለን በማለት መንግስት እነዚህ አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ ሊወስድ ይገባል ብለዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ አህመድ አሊ በሰልፉ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ስልጣንንና ፍላጎትን በኀይልና በጉልበት ለመጫንና ለመንጠቅ የሚደረግን እንቅስቃሴ መታገል እንደሚገባ ገልጸዋል።

በየአካባቢያችን አንድነታችንንና ሰላማችንን ለመንጠቅ የሚጥሩ ፅንፈኛ ኀይሎችን አጀንዳ በመረዳት ልናወግዝ ይገባል ብለዋል።

#አሚኮ (ዘጋቢ፦ ይማም ኢብራሂም )
https://www.facebook.com/Voiceofwollo2019/