የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ @sumuslim_jemaa Channel on Telegram

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ

@sumuslim_jemaa


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ውድ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ይህ ቻናል የተከፈተው በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀምዓ የሚሰጡ ትምህርቶች፣መልዕክቶች የሚሰራጭበት ቻናል ነው

በዚህ ቻናል ማንኛውንም ሙስሊም ተማሪዎች ወደ ቻናሉ በመጋበዝ ተጠቃሚ ያድርጉ


የመጋበዣ ሊንክ
👇👇👇👇👇👇👇👇


https://t.me/sumuslim_jemaa

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ (Amharic)

በላቀ ትግርኛ በቻንክሽን ላይ ይጠቀሙ 'ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ' ማህበረሰብ እና መልእክቶች አሉት። ይህ ቻናል እንዲህ ነው፦ አሁንም ሳህጣን ሁንዴሳን ገጽ ግዙፍ አዝናኝነት እና እንቅስቃሴ በሙስሊም ተማሪዎች ይገኛል። ይህቻናል ገጽ በዚህ አማራጭ በመጋበዝ የሚቀየሩትን ሙስሊም ተማሪዎች እና መንሰርዎችን ይወዳሉ። በማግኘታው በዚህ ቻናሉ በመጋበዝ ማንኛውንም ሙስሊም ተማሪዎች ወደ ቻናሉ መጋበዝ እና ለቻናሉ መጉረጥ የሚችሉ ተጠቃሚዎች እንደሚቀርቡ ቀረቡ።

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ

21 Nov, 06:35


~እንግዳ የሚበዛበት ቤት አላህ የሚወደው ቤት ነው ይላሉ።ለትንሽ ትልቁ ልድሃ ሀብታም ሚከፈትን ቤት የሰዉም ሆነ  የመላኢካ ዱዓ አይለየዉም። የአላህ ችሮታም አይጎድልበትም።እንግዳ እቤት ሲገባ በረከትና የአላህ እዝነት አብሮት ይገባል።እንግዳው ብዙ ችሮታዎችን ይዞ ይመጣል፣ ወንጀልም አጥቦ ይሄዳል።«በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ያመነ እንግዳዉን  ያክብር።» ብለዋል የአላህ መልዕክተኛ ﷺ―
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ

18 Nov, 17:38


🌹🌹Beeksisa🌹🌹

Barattoota Afaan Arabaa digriidhaan  barachuuf barbaaddan hundaaf
Afaan Arabaa Yuunivarsiitii Wallootti akka kennamu ni beekama.  yuunivarsiitiin Walloo bara barnoota 2017tti barattoota Afaan Arabaa barachuuf fedhii qaban yuunivarsiitii mootummaa hundaa irraa galmeesse barsiisuu barbaada .
kanaafuu bara barnoota 2016 freshman course kan fudhattan fi bara barnoota 2017tti qabxii darbiinsa yuunivarsiitii fiddan sadaasa 05_20 /2017tti rijistiraala yuunivarsiitii walloo damee daseetti akka galmooftan isinii beeksiisna .
Odeeffannoo dabalataaf
0920114937
Muhammad  / Dura taa,a  Afaan Arabaa yuunivarsiitii walloo /.

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ

18 Nov, 13:14


~ከረፈደ እና ምናልባት ካጣነው በኋላ ከምናውቀው ፍቅር ውስጥ ግንባር ቀደሙ የአባት ፍቅር ነው።እጅግ ጠንካራ፣ በመስወዓትነትና በድርጊት የታጀበ ፍቅር ሆኖ ሳለ ለመረዳት የሚቸግረን ፍቅር ውስጥ የአባት ፍቅር ነው። አባቶቻችን ድንቅ አፍቃሪና ፍቅርን አዋቂ ናቸው። ግና በይበልጥ ለቃላት የተገሩ ስላልሆኑ እንደሚወዱን እንኳ ላለማመን አቅም እናገኛለን። እመኑኝ አባቶቻችሁ ፍቅርን ያውቃሉ። ያፈቅሯችኋል። አባት ለልጆቹ ፍቅሩን ለመግለፅ እየታተረ ነው የሚያልፈው። ፍቅሩ ግን ጥልቅ ነው።  የሕይወት መስወዓትነት ለሚከፍልላችሁ አፍቃሪያችሁ ለሆነው አባታችሁ ውዴታችሁን ነግራችሁት ታውቁ ይሆን?
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ

17 Nov, 14:13


💡ሚስጥር መጠበቅ!

ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إِذَا حَدَّثَ الرَّجُلُ الْحَدِيثَ، ثُمَّ الْتَفَتَ فَهِيَ أَمَانَةٌ﴾

“አንድ ሰው ግራ ቀኙን ተመልክቶ የሆነ ወሬ
ከነገረህ አማና (ሚስጥር) ነው ማለት ነው።”

📚 ቲርሚዚ ሶሂህ ብለውታል: 1959

🙁☹️😭🙁😭🙁☹️

በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

✈️፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

📞፦ https://bit.ly/486xnrS

👤፦ https://bit.ly/41zEZkk

📸፦ https://bit.ly/4arMbTx

💬፦ https://bit.ly/41tIUPv

🎥፦ https://bit.ly/3UTTSwh

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ

16 Nov, 12:53


ክብር ለህክምና ባለሙያዎች
ኢማሙ አሻፊዒ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ ፦
''ከሀላል እና ሀራም እውቀት በኃላ እንደ ህክምና እውቀት የተከበረ እውቀት አላውቅም።''
📚ሲየሩ አዕላሚ ኑበላእ (57/10)

«ይላሉ ጠንከር በሉ ጤናዎች እኛ ነን እንጅ ህእ!

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ

14 Nov, 18:20


#ጥቆማ

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ካመጡ ተማሪዎች መካከል በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በዐረብኛ ቋንቋና ሥነ - ጽሑፍ የትምህርት መስክ በመጀመሪያ ዲግሪ ለመማር ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች ከሁሉም የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ተቀብሎ በመደበኛ ፕሮግራም ማስተማር ይፈልጋል፡፡

በመኾኑም መስፈርቱን የምታሟሉና ፍላጎቱ ያላችሁ አመልካቾች ከ8ኛ-12ኛ ክፍል ሙሉ የትምህርት ማስረጃችሁን ይዛችሁ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ደሴ ካምፓስ ዋናው ሬጅስትራር በአካል በመቅረብ ከኅዳር 05 - 20/2017 ዓ.ም ድረስ ማመልከት የምትችሉ መኾኑ ተገልጿል።

በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሪሚዲያል ፕሮግራም ተምራችሁ ወደ ፍሬሽማን ፕሮግራም ያለፋችሁ ተማሪዎች የዕድሉ ተጠቃሚ መኾን ትችላላችሁ ተብሏል።

ለበለጠ መረጃ:-
📱0920114937
(ሙሐመድ፣ የዐረብኛ ትምህርት ክፍል ኃላፊ)
(Muhammad, head Department of Arabic Language & Literature)

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ

11 Nov, 17:59


➧ታላቁ ዓሊም ዐብዱል ዐዚዝ ኢብኑ ባዝ አላህ ይማራቸውና እዲህ ይላሉ‼️

➺ አንተ እኮ ልትበላና ልትጠጣ አይደለም የተፈጠርከው። ህንፃ ዎችን ልትገነባ ፣ ዛፎችን ልትተክል ፣ ወንዞችን ልትሰነጥቅ ፣ ለወሲባዊ ግንኙነት ወይም ለሌላ አልተፈጠርክም። በፍፁም! አንተ የተፈጠርከው ጌታህን እንድታመልክ ነው ። አንተ የተፈጠርከው በትዛዙ ላይ እንድትፀና እና መልክተኛውን ﷺ እንድትከተል ነው ። የተፈጠርከው ለዚህ ነው ። በምድር ላይ ያለ ነገር ሁሉ አላህን ለመታዘዝ ፣ እሱን ከማመፅም ለመራቅ እንድትታገዝበት ነው የተፈጠረው ። እንጂ ለስሜትህ እንድትታገዝበት አይደለም የተፈጠረው ።[ አል ፈተዋ ፡ 7/98]

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ

10 Nov, 08:38


أسأل الله أن يبارك لكما
وأن يرزقكما الذرية الصالحة
وأن يرزقكما الحب والمودة،
وأن يلهمكما الاستقرار والاجتماع دومًا في طاعته وعلى حبه، يا أحلي زوجين الليلة، وسبب فرحي الكبير

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ

10 Nov, 08:35


በዛሬው ቀን የጊቢያችን የ ኢንቫይሮመንት አሚር የሆነው ወንድማችን ሚፍታህ ሹመት እና ሰአዳ ሰኢድ ኒካህ አስረዋል::          

እኛም ኒካሀችሁ የተባረካ; ለሙእሚኖች ተምሳሌት የምትሆኑበት; ፍቅራችሁም እስከ ወዲያኛው የሚዘልቅ ያደርግላችሁ ዘንድ በጥንዶች መካከል ውዴታና እዝነት ያደረገው ጌታችን አላህን እንማፀነዋለን
ውድ የsemera university ሙስሊም ተማሪዎች እና የቻናላችን ተከታዩች መልካም ምኞታችሁን እየገለፆችሁላቸዉ በዱአም እንዳትረሷቸዉ መልእክታችን ነው::

بارك الله لكما وبارك عليكما وجمع بينكما في الخير

ወንድማቹህ ከማል ሰኢድ

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ

10 Nov, 08:19


«ሰርጉን ብቻችሁን የበላችሁ ተማሪዎች ታዝበናል»

ለማንኛውም ወንድማችን ሚፍታህ እና እህታችን ሰዓዳ

«ባረከሏሁ ለኩማ ወበረካ አለይኩማ ወጀመአ በይነኩማ ፊ ኸይር!!

አላህ ያማረ ዘላቂ የሆነ ትዳር ያድርግላችሁ ወልዳችሁ ክበዱ!!

ወንድማችሁ አቡ ኡበይዳ ነኝ

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ

07 Nov, 10:17


እንዲህ አይነት ዜና ናፍቆናል!
በርቱ

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ

07 Nov, 09:52


አሰላሙዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱህ 👋👋👋👋
ውድ እና የተከበራቹህ
ወንድሞች እና እህቶች

በ ሰመራ ዩኒቨርስቲ የሙስሊም ተማሪዎች ጀመዐ ውስጥ ከሚደረጉ ኸይር ስራዎች አንዱ የሆነው የሐላል ፍቅርን የማሳካት ሰበብ ማድረስ  ሂደት ቀጥሏል

በአላህ ፍቃድ ሆኖ እሁድ 2:30
ወንደማችን:-
እህታችን:- 

በአላህ ቃልኪዳን (ኒካሕ) ሊተሳሰሩ ነው
ኒካሕን በአደባባይ ማድረጉ ሱና እንደመሆኑ
የነሱንም ደስታቸው እንደ ጀማዐ እና እንደ ወንድም እና እህትነት እንድንካፈል ተጋብዘናል ።
በብዛ እናድምቀው
በአለንላቹህ እናሸብርቀው
ማንም እንዳይቀር
የቻለ አውጥቶ ስጦታ ከዱዐ በመቀጠል ይገፍትር !!!!
ያልቻለ ራሱን በማስገኘት ዱዐውን ያድርስ ።

በተስፋ እንጠብቃለን
የሙስሊም ሐቅ" ሲጠራህ እሺ ልትለው ነው "
ረሱል አለይሰላቱ ወሰላም

ይህን በማስመልከት  ኡስታዞች ይጋበዛሉ
ያላገባ እንዲያገባ ያነሳሳሉ
ያገባ ያለበትን ኒዕማ እንዳይዘነጋ ያስታውሱታል ኢንሻአላህ የተለያዩ ፕሮግራሞች ይኖራሉ እንዳያመልጦ እንካን መቅረት ማርፈድ ያስቆጫል!

ሙሀደራውን የሚሰጡን ኡስታዞች
1 አቡ ሂዛም አብዱረህማን ሰኢድ
2 አቡ ፈውዛን ኸድር
3 ሙሐመድ ሰዒድ

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ

04 Nov, 19:45


ኒካሕና ቃዲ
~
እንደሚታወቀው በኢስላም የትኛዋም ሴት ያለ ወሊይ ፈፅሞ ልታገባ አይፈቅድላትም። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:–

أَيُّمَا امْرَأَةٍ نُكِحَتْ بِغَيْرِ إِذْنِ وَلِيِّهَا فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ، فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ، فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ
"ያለ ወሊዩዋ ይሁንታ የተገባች የትኛዋም ሴት ጋብቻዋ ውድቅ ነው! ጋብቻዋ ውድቅ ነው! ጋብቻዋ ውድቅ ነው!" [አቡ ዳውድና ቲርሚዚ ዘግበውታል።]

ወሊይ ከሌለስ? በዚህን ጊዜ ኒካሑ በቃዲ ይታሰራል። ስለዚህ ኒካሕ ለማሰር ቃዲ የሚያስፈልገው ወሊይ ለሌላት ሴት ነው ማለት ነው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
َ (فالسلطان ولي من لا ولي له)
"አስተዳዳሪ ወሊይ ለሌለው ወሊይ ነው።" [አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል]

በተጨማሪም ወሊዮች ያለ ተጨባጭ ምክንያት ለመዳር ፈቃደኛ ሳይሆኑ ከቀሩ ኒካሑ በቃዲ ይታሰራል። ከዚህ ውጭ አባት ወይም ሌላ ወሊይ ወይም ወኪል ካለ ኒካሑን የሚያስሩት እነሱ እንጂ ቃዲዎች አይደሉም። ወሊይ ወይም ወኪሉ "ሰጥቻለሁ" ካለ፣ አግቢው ወይም ተወካዩ "ተቀብያለሁ" ካለ ኒካሕ ታስሯል። ኹጥባውን (ሸርጥ ካለመሆኑም ጋር) ወሊይ ወይም ሌላ ቦታው ላይ የተገኘ ሰው ሊያደርገው ይችላል።

ኒካሕ ለማሰር የተለየ ውስብስብ መስፈርት የለም። የዐረብኛ ቃላት መጠቀምም አይጠበቅም። መስፈርቶች እስከተሟሉ ድረስ በየትኛውም ቋንቋ ቢሆን መስጠትና መቀበል ከተገኘ ኒካሕ ታስሯል። ስለዚህ በሃገራችን በሰፊው እንደሚደረገው ወሊይ እያለ ቃዲ መጥራት አይጠበቅም። ቃዲዎች ወሊይ ባለበት ሁኔታ ኒካሕ ለማሰር አትቀደሙ። ያለ ስልጣናችሁ ጣልቃ አትግቡ።

ወሊይ የሆናችሁ ሰዎች ደግሞ ቃዲዎችን ለሰርግ ከጠራችሁ እንደማንኛውም እድምተኛ ተስተናግደው ይመለሱ እንጂ እዚያው ተቀምጣችሁ ለነሱ ውክልና አትስጡ። "ልጄን እከሊትን ድሬሃለሁ" ማለት ያቅታችኋል? ምንም የተለየ የተቀመጠ ቃል የለምኮ። እሱም "ተቀብያለሁ" ካለ፣ ቦታው ላይ ሁለት ታማኝ ምስክሮች ከኖሩ ኒካሑ ታስሯል አለቀ። ባገር እያለህ፣ ዐቅልህ ጤነኛ ሆኖ ሳለ እንዴት ከፊትህ ለሚፈፀም ጉዳይ ውክልና ትሰጣለህ? ምንም የሚያስፈራ ነገር የለምና እራስህ ፈፅመው። ሁሉም ነገር በቃዲ በኩል እንዲያልፍ መደረጉ አንዳንድ መረን የለቀቁ ባለስልጣናት በማያገባቸው የእምነታችን ጉዳይ ጣልቃ እንዲገቡ በር እየከፈተ ነው። አንዳንድ ቃዲዎችም ጉዳዩን ያላግባብ የሚጠቀሙበት ሁኔታ አለ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

1,070

subscribers

126

photos

37

videos