✝️✝️የጥበብ ዕይታ✝️✝️ @siletibebb Channel on Telegram

✝️✝️የጥበብ ዕይታ✝️✝️

@siletibebb


ስለ ጥበብ

✝️✝️የጥበብ ዕይታ✝️✝️ (Amharic)

የጥበብ ዕይታ የተወሰነ እና የተካሄደ ስለ ጥበብ የሚናገር ትምህርት እና የፈጥሮ መረጃዎችን ለመዝጋት እንደሚከተለው ከተማ Telegram ቻናሎች ይገኛል። የሚበላበት ጥበብ እና የተወሰነ እና የተካሄደ ጥበብ ትምህርትን ሴቶችዎን ለመቀበል እና ለሌሎች ተጨማሪ አስተያየቶች እንዲሁም መዝጋት በጥበብ ስርዓት ውስጥ ለመቅረብ ያግዙ። እባኮት ለምሳሌ ማስፈራሪያዎች እና መረጃዎች ላይ ሊገኝ ያግዛል። እናንተ ስለናወጡ ጥበብ እና መረጃዎች እንደምንቀምጥ ከአስተያየቶች እና መዝጋት እንዲሁም ተጨማሪ መረጃዎች ለማግኘት እንጠቀምበዋለን።

✝️✝️የጥበብ ዕይታ✝️✝️

10 Sep, 21:57


የተወደዳችሁ የጌታ ተወዳጆች እንዴት ናችሁልኝ በጌታ ሠላም ሠላም  እያልኳችሁ

አዲሱን ዓመት ፦ዝማሬያችን ፤ፀሎታችን፤ አገልግሎታችን፤ ህይወታችን፤ በመንፈስ ቅዱስ ሙላት ተቃኝቶ የምናከናውንበት ይሁንልን።
ዓመቱ ከጌታ ጋር ጌታን የምንመስልበት ይሁንልን።

ኢየሱስ ለኔ፦

ለእራሴ አክሊል .. ለዓይኔ ብርሃን
፤ለአፍንጫዬ በጎ መዓዛ...  ፤ለአፌ የማር ወለላ ፤
ለአንገቴ የወርቅ ድሪ፤...  ለእጄ አምባር ፤
ለጎኔ እረፍት ፤...... ለማንነቴ ክብር፤
ከፍ ያልኩበት ከፍታዬ. ፤.... የታየሁበት ሰገነቴ
መጠሪያ ስሜ.... ፤.... ድምቀት ማህረጌ
የልቤ ንጉስ.... ፤... የህይወቴ ፋና
እየሱስ መንገድ እወነቴ..... ፤... የጽድቃ ማህተሜ
ድፍረት መተማመኛዬ.. ፤...  የንግግሬ መልክት
የቀራንዮ በግ.... ፤...  የስንኜ ውበት
የመስቀሉ ሙሽራ... ፤.. የልቤ ናፍቆት
የእራቤ ጥጋብ... ፤... የጥማቴ እርካታ
የፍላጎቴ ወደብ.. ፤.. አንተ ነህ ኢየሱስ ጌታ

🌼ኢየሱስ🌼 ኢየሱስ 🌼ኢየሱስ 🌼 ኢየሱስ🌼

🌼አንተን ቀምሶ ወዴት አለ ጎዞ🌼



🌼መልካም የጌታ ኢየሱስ ዓመት ይሁንላችሁ🌼

✝️✝️የጥበብ ዕይታ✝️✝️

05 Sep, 16:14


#መልክ (አርአያ) ማለት ምን ማለት ነው?


መልክ (አርአያ) ማለት ሰው እግዚአብሔር አምላኩን ይመስል ዘንድ በተፈጥሮ የተሰጡት ባሕርያት ናቸው፡፡ እነዚህ ባሕርያት ከሰው ፈጽሞ የሚወሰዱ አይደሉም፡፡ ብዙ ቅዱሳን አባቶች መልክ (አርአያ) ለሚለው ቃል ትርጉም ሲሰጡ ሲለያዩ ይታያሉ፡፡ ለምሳሌ:-
#ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዘፍጥረትን በተረጎመበት ድርሳኑ ላይ መልክ (አርአያ) ማለት ለሰው በተፈጥሮ ፍጥረታትን ለሚገዛበት ባሕርይው የተሰጠው ስያሜ ነው ይላል እርሱ (ሙሴ) በእግዚአብሔር መልክ ሲል በምድር ያሉትን ሁሉ ሰው የሚገዛቸው መሆኑን የሚያመለክተን ነው፡፡ በምድር ላይ ከሰው በላይ የሆነ ፍጥረት የለውም ይላል፡፡ እንዲሁም ይህ ቅዱስ ስለ ሰው ተፈጥሮ ሲያስተምር ሰው ከሚታዩት ፍጥረታት በላይ የሆነ ፍጥረት ሲሆን ለዚህ ፍጥረት ሲባል ሁሉም ፍጥረታት ተፈጠሩ ይላል፡፡ ያም ማለት ሰማይ፣ ምድር፣ ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት፣ ተሳቢና ተራማጅ እንዲሁም በምድር ላይ ያሉ ፍጥረታት ሁሉ ለእርሱ ተፈጠሩ


አንዳንድ ቅዱሳን ሰው በእግዚአብሔር መልክ መፈጠሩን መንፈሳዊ ከሆነው ተፈጥሮው ጋር አገናኝተው ያስተምራሉ፡፡ ለምሳሌ:-
#ቅዱስ ኤፍሬም በእግዚአብሐር መልክ የተፈጠረችው ነፍሳችን ናት ብሎ ሲያስተምር አንተ መንፈሳዊ ተፈጥሮ አለህ፤ ነፍስ የእግዚአብሔር አርዓያና አምሳል ናት ይላል፡፡ ሰው በነፍስ ተፈጥሮው ነጻ ፈቃድ፣ ነገሮችን የማገናዘብ ችሎታ እንዲሁም ሓላፊነት የሚሰማው ሆኖ የተፈጠረ ፍጥረት ነው፡፡ በእነዚህ ሰው እግዚአብሔር አምላኩን ይመስላል፡፡
#ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ ግን ነፍሳችንም ሥጋችንም በእግዚአብሔር አርዓያ እንደተፈጠሩ ግልጽ በሆነ መልኩ ሲያስረዳ በአዳምና በሔዋን አስቀድሞ ያሳየን ምሳሌ ይፈጸም ዘንድ የሙሽራው ጎን በጦር ተወጋ፤ ከጎኑም (በፈሰሰው ደሙ) ቤተክርስቲያን ተመሠረተች፤ እግዚአብሔር ይህን ባወቀ አዳምንና ሔዋንን በብቸኛ ልጁ አርአያና አምሳል ፈጠራቸው፡፡ይለናል፡፡


ሰው ሰማያዊት አካል ስላለችው ረቂቁን ዓለም የመረዳት ችሎታ ሲኖረው ምድራዊውም አካል ስላለው ምድራዊውም እውቀት አለው፡፡ ሰውን ከሰማያውያን መላእክትና ከምድራውያን መላእክት ጋር ስናስተያየው ለሁለቱም ዓለማት እንግዳ እንዳልሆነ በሁለቱም ዓለማት እኩል የመኖር ተፈጥሮአዊ ባሕርይ እንዳለው፣ የሰማያውያንንም የምድራውያንንም እውቀት ገንዘቡ ያደረገ ፍጥረት መሆኑን ስናስተውል በእግዚአብሔር መልክና ምሳሌ መፈጠሩን እንገነዘባለን ፡፡


እግዚአብሔር አምላክ የሰማያውያንም የምድራውያንም ፍጥረታት እውቀት ባለቤት ነው፡፡ ሰውም በጸጋ ለሰማያውያን መላእክት ለምድራውያን ፍጥረታት እውቀት ባይተዋር አይደለም፡፡ እግዚአብሔር በላይ በሰማይ በታች በምድር ከሰማይም በላይ ከሰማይም በታች ይኖራል፡፡ ሰው ሙሉ ለሙሉ አይሁን እንጂ በታች በምድር ግዙፋን ፍጥረታትን ሲገዛ በላይ በሰማይ ደግሞ ከሰማያውያን መላእክት ጋር እኩል በምስጋና ይሳተፋል፡፡ ከዚህም ተነሥተን ሰው በሁለት ዓለማት እኩል የመኖር ተፈጥሮ እንዳለው ማስተዋል እንችላለን፡፡


#ቅዱስ ጎርጎርዮስ ሰው በእግዚአብሔር መልክ ተፈጠረ ስንል  በነፍሱም በሥጋውም እንደሆነ ሲያስረዳ እንዲህ ብሎ ጽፎልን እናገኛለን፡፡ ሰው ምድራዊና መንፈሳዊ አካል ያለው ፍጥረት ሆኖ በመፈጠሩ ከመላእክት በተለየ በእግዚአብሔር አርዓያና አምሳል ተፈጠረ ተባለለት፡፡ ሰው ምድራዊ ተፈጥሮ ባይኖረው ኖሮ በእግዚአብሔር አርአያ ተፈጠረ ባላልነው ነበር፡፡ ስለዚህም ሰው በምድራዊው ተፈጥሮውም የእግዚአብሔርን መልክ ይዟል፡፡ ብሎ ያስተምራል፡፡


በእርግጥ ይህ እውነት ነው፡፡ ለምሳሌ እግዚአብሔር ፍጥረትን ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ ፈጥሮአቸዋል፡፡ ወደ መኖርም ባመጣቸው ፍጥረታትም ሌሎችንም ፍጥረታትን ፈጥሮአል፡፡ ለምሳሌ ብንወስድ የሰው ተፈጥሮ አንዱ ነው፡፡ እግዚአብሔር አስቀድሞ ምድርን ፈጠራት፡፡ ከምድርም አፈር ሰውን አበጀው፡፡ ይህ ዓይነት ባሕርይ እንደ እግዚአብሔር አይሁን እንጂ በሰውም ላይ ይታያል፡፡ ሰው ምንም እንኳ ነገሮችን ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ እንደ አምላኩ አይፍጠር አንጂ የተፈጠሩ ፍጥረታትን በመጠቀም ምድራዊው አኗኗሩ ቀላልና ምቹ አንዲሆንለት ሲል ከመላእክት በተለየ እጅግ ድንቅና ሊታመኑ የማይችሉ ተግባራትን ሲከውን ይታያል፡፡ በዚህም አምላኩን ይመስላል፡፡

✝️✝️የጥበብ ዕይታ✝️✝️

05 Sep, 16:14


“ሰው ማለት ምን ማለት ነው?”

ሰው ማለት ነፋሳዊነት፣ እሳታዊነት፣ ውኃዊነት፣ መሬታዊነት ባሕርያት ያሉት በነፍስ ተፈጥሮውም ነባቢት ለባዊትና ሕያዊት የሆነች ነፍስ ያለችው ፍጥረት ነው፡፡ እንዲህ ብለን ግን የሰውን ተፈጥሮ ጠቅልለን መናገር አይቻለንም፡፡ ምክንያቱም ሰውን ከሌሎች ፍጥረታት ይልቅ እጅግ ልዩ በሆነ መልኩ በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል ተፈጥሮአልና፡፡ ስለዚህም ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ብለው ሰው ለሚለው ስያሜ ትርጓሜ ይሰጡታል፡፡

ቅዱስ ባስልዮስ ዘቄሳርያ:-
ከትምህርቶች ሁሉ ታላቁ ትምህርት ራሰን ማወቅ ነው፡፡ አንድ ሰው ራሱን ካወቀ እግዚአብሔርን ያውቀዋል፡፡ እግዚአብሔርን ካወቀ ደግሞ እግዚአብሔር አምላኩን ይመስላል ብሏል።
ቅዱስ ይስሐቅም:-
አንተ በልብህ ንጹሕ ከሆንህ ሰማይ በውስጥህ ነው፡፡ በውስጥህም መላእክትንና የመላእክትን ጌታ ትመለከታቸዋለህ (The Orthodox Church by Timothy Ware) ቅዱስ ይስሐቅ እንዲህ ማለቱ ያለ ምክንያት ሆኖ አይደለም፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ቃሉን በተግባር መልሰው ለሚተገብሩ ሰዎች የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል አባቴም ይወደዋል ወደ እርሱም እንመጣለን በእርሱም ዘንድ ማደሪያ እናደርጋለን፡፡(ዮሐ.14፡23) የሚለውን ይዞ ነው፡፡ አካላችን በሰማይ የሚኖረው አባታችን ማደሪያ ከሆነ እኛም ሰማይ ሆንን ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ በእኛ ሰውነት ውስጥ ካለ ደግሞ ቅዱሳን መላእክትም መገኘታቸው እርግጥ ነው፡፡


ከዚህ ጠንከር ባለ መልኩ ደግሞ የአሌክሳንደሪያው ቅዱስ ቀሌምንጦስ ወንድምህን አስተውለህ ስትመለከተው እግዚአብሔርን ትመለከተዋለህ ይላል፡፡ ቅዱስ ኤፍሬምም በሰው ላይ በአመፃ የምትነሣሣ ከሆነ በእግዚአብሔር ላይ እንደተነሣሣህ ቁጥር ነው፡፡ ለባልንጀራህ አክብሮትን የቸርከው ከሆነ እነሆ እግዚአብሔርን አከበርኽ፡፡ይላል፡፡


ቅዱስ ሄሬኔዎስ፣ ቅዱስ አትናቴዎስ፣ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ እንዲሁም ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ በአንድነት ሰው በጸጋ አምላክ ይሆን ዘንድ ከሦስቱ አካላት አንዱ እግዚአብሔር ቃል ሰው ሆነ ብለው ያስተምራሉ፡፡ (The Image and likeness of God by Vladimir Lossky) በእርግጥ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም የማቴዎስን ወንጌል በተረጎመበት በሁለተኛ ድርሳኑ ገጽ 9 ላይ He suffered Himself of to be called also the Son of David, that He might make thee Son of God. አንተን የእግዚአብሔር ልጅ ያደርግህ ዘንድ የዳዊት ልጅ መባልን መረጠ፡፡ ቅዱስ ኤፍሬምም ሙሴ በነዝር እባብ የተነደፉት እስራኤላውያን ከፍ ተብሎ በተሰቀለው የነሐስ እባብ እንደ ተፈወሱ አስተዋለ፡፡ በእርሱም በጥንቱ እባብ የተነደፉትን የሚያድነውን(ክርስቶስን) ከሩቅ ተመለከተው፡፡ ሙሴ እርሱ ብቻ ከእግዚአብሔር የጸጋው ብርሃን ተካፋይ እንደሆነ አስተዋለ፡፡ በእርሱም እግዚአብሔር ቃል ወደ እዚህ ዓለም በመምጣት አማልክት ዘበጸጋን በትምህርቱ እንደሚያበዛቸው ተመለከተ፡፡ ይላል፡፡


እኚሁ አባቶች ሰው ገና ሲፈጠር በጸጋ አምላክ እንዲሆን ተደርጎ መፈጠሩንም ያስረዳሉ፡፡ ለምሳሌ ቅዱስ ኤፍሬም ጌታ ሆይ ሠዓሊ ቀለማትን አዋሕዶ ሥዕሉን እንዲሥል አንተም አርአያህንና አምሳልህን እንዲመስሉ ሁለቱን አካላት አዋሕደህ አንድ አካል በማድረግ በራስህ መልክ ፈጠርካቸው፡፡ ወደ ራስህ አርአያ ተመለከትኽ የራስህን አርአያና አምሳል በእጆችህ ሣልኸው፡፡ ጌታ ሆይ እነሆ የሣልኸውን ሥዕል አንተው ሰው በመሆን ገለጥኸልን፡፡ሲል ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ ሰው ገና ከአፈጣጠሩ በእግዚአብሔር መልክና ምሳሌ ስለመፈጠሩ ሲያስረዳ በአዳምና በሔዋን አስቀድሞ ያሳየን ምሳሌ ይፈጸም ዘንድ የሙሽራው ጎን በጦር ተወጋ፤ ከጎኑም ቤተክርስቲያን በፈሰሰው ደሙ መሠረታት(በደሙ የዋጃትን ቤተክርስቲያን አንዲል የሐዋ.20፡28)፤ እግዚአብሔር ይህን ባወቀ አዳምንና ሔዋንን በብቸኛ ልጁ አርዓያና አምሳል ፈጠራቸው፡፡ብሎ ጽፎልን እናገኛለን ፡፡ (Spirituality in Syrian Tradition by Sebastian brock) ስለዚህም ወደ ድምዳሜው ስንመጣ ሰው ማለት በጸጋ አምላክ ሆኖ የተፈጠረ ፍጥረት መሆኑን በእነዚህ ሁሉ ቅዱሳን አባቶች አስተምህሮ መረዳት እንችላለን፡፡ በእግዚአብሔር መልክና ምሳሌ ተፈጠረም ስንል የጸጋ እውቀት የተሰጠው ክፉውን ከበጎ መለየት የሚችል ፍጡር መሆኑን ያስረዳናል፡፡ ከላይ ከሰጠናቸው ትንታኔዎች ተነሥተን ሰው ለሚለው ስያሜ ትርጉም ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋ ከሦስቱ ባሕርያተ ነፍስ ተፈጠረ ብለን ብቻ የምንቋጨው እንዳልሆነ መረዳት እንችላለን፤ እጅግ ሰፊ ትርጉም ያለውና በውስጡም ታላቅ የሆነ መልእክትን እንደያዘ እንገነዘባለን፡፡ ይህን እጅግ ሰፊና ጥልቅ የሆነ ትርጉም የያዘው ሰው የሚለው ስያሜ ለመረዳት መልክና ምሳሌ ወይም አርአያና አምሳል የሚሉትን ቃላት አስቀድሞ መረዳት ይገባናል፡፡

✝️✝️የጥበብ ዕይታ✝️✝️

05 Dec, 12:29


​​በመንፈሳዊ ሕይወትህ/ሽ ለውጥ እንዲኖሮት ከፈለጉ

1 የፀሎትን ህይወት ተለማመድ ተጠቀምበትም፣
2 ከመንፈሳዊ አባቶችና ሊቃውንት መ/ራን ምክርና ትምህርት አትራቅ
3 ከቅዱሳት መፃህፍት ጋር ያለህን ግንኙነት አዘውትር፣
4 የምትውልባቸውን ቦታዎች ፥የምታነባቸውን መፃህፍት፥ የምትመርጣቸውን ባልጀሮችህን ምረጥ፤ለመንፈሳዊ ህይወትህና ለሌሎች ወንድሞችህና እህቶችህ የሚያሰናክሉ እንዳይሆኑ ተጠንቀቅ፣
5 የእግዚአብሄር ቤተመቅደስ መሆንህን ዘወትር አትዘንጋ፣
6 ሃፍረትንና ፍርሃትን አስወግድ፥በራስህ ማስተዋልም አትደገፍ፣
7 አላዋቂነትህን ተቀበል 'እኔ ብቻ'፦ አትበል ውዳሴ ከንቱንም አትፈልግ፣
8 ለሰራሃው ሃጢአት ሳትዘገይ ንስሃ ግባ፣
9 ልበ ደንዳናነትንና አመፀኛነትን ከአንተ አርቃቸው፣
10 እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ ለመኖርና የቃሉ ሙላት በውስጥህ ኖሮ ከክርስቶስ ጋር መኖርን ተለማመድ በቃሉም ፀንተህ ተገኝ፣
11 የቅዱሳንን ተጋድሎና ፍቅር በመመልከት እነርሱን ለመምሰል ትጋ፣
12 ከዚህ በፊት የነበርክበትን የሃጢአት ህይወት ኮንነው
13 ሰዎችን/ባልንጀራህን አፍቅር ከጥላቻም ራቅ፣
14 ነገርን ሁሉ ለበጎ ነው ብለህ ተቀበል።


ጌታ ሆይ ይህን እንድናደርግ እርዳን አሜን ይቆየን።

✝️✝️የጥበብ ዕይታ✝️✝️

05 Oct, 08:20


+✝️ አባቶቻችን እንዲህ አሉ ✝️+

"እሳትና ውኃን ማዋሐድ እንደማይቻል በሌሎች ኃጢአት መፍረድም በራስ ኃጢአት ከመጸጸት ጋር አብሮ አይሔድም" ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው

"የማያማትብ እጅ ቀኙም ግራውም አንድ ነው" አባ ፓስዮስ ዘደብረ አቶስ

"እግዚአብሔር ለኃጢአተኛ ሰው ያለው ፍቅር
ጻድቅ ሰው ለእግዚአብሔር ካለው ፍቅር ይበልጣል"
አባ አርሳኒ

"ሕፃን ልጅ እናቱ ስታጥበው ያለቅሳል:: ሕፃን እምነት (ትንሽ እምነት) ያላቸው ሰዎችም ነፍሳቸውን የሚያጥብ መከራ ሲመጣባቸው እግዚአብሔርን ያማርራሉ"  አባ ስምዖን

"ዕለትን የሠጠህ እርሱ ለእለት የሚበቃህንም ይሠጥሃል"  ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

"እጅግ ምርጡ ጸሎት "ጌታ ሆይ አንተ ሁሉን ታውቃለህ የፈቀድከውን አድርግልኝ" ማለት ነው"
ባሕታዊ ቴዎፋን

"ሲያመነዝር ያየኸውን ሰው አንተ ንጹሕ ብትሆንም አትናቀው:: ምክንያቱም አታመንዝር ያለው ጌታ አትፍረድም ብሏል"  አባ ቴዎዶር

"አንድ ሰው ኃጢአት ሲሠራ ብታይ እንኳን አትፍረድበት:: አንዳንዴ ዓይንህም ሊሳሳት ይችላል"
ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው

"ለኃጢአተኛው ክንፍህን ዘርጋለት:: ኃጢአቱን ልትሸከምለት ባትችል እንኳን ሸፍንለት"
ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ

ከአበው አንዱን ትሕትና ምንድርን ነው? ብለው ጠየቁት:: እርሱም "ትሕትና ማለት ወንድምህ በበደለህ ጊዜ እርሱ ይቅርታ ሳይጠይቅህ በፊት ቀድመህ ይቅር ማለት ነው" አለ::

"ይቅር ካላልክ ገነትም ይቅርብህ" አባ ኤፍሬም አረጋዊ [ If you don’t forgive, forget heaven]

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

መልካም ቀን ይሁንላችሁ።

✝️✝️የጥበብ ዕይታ✝️✝️

22 Sep, 09:46


#አመሰግን #ዘንድ #ምክኒያቴ #ብዙ #ነው ✝️✝️
አምላኬ ሆይ፣ ያልገቡኝ ነገሮች ቢኖሩም አንተ ግን መልሴ🤝 ነህ ። ዝም ያሰኙኝ ነገሮች አያሌ ቢሆኑም ህይወት❤️ የማታስፈራ የአንተ ቀመር ናትና አልፈራም።ንፁህ ምንጮች ሲደፈርሱ ምንድነው ምክንያቱ ብልም አንተ ግን ነፍሴን🙏 መልሰህ ታሳርፋታለህ። እውነተኞች ሲደናቀፉ የፃድቃን✝️ መከራ ሲበዛ ምን ዓይነት ዓለም ነው ብልም አንተ ግን እራሴን መልሼ እንዳይ ታደርገኛለህ።ለጥያቄ መልስ፤ ለሁሉም ችግሮቼ  ፈውስ አንተ ነህና ሁሉን አልፋለሁ።ስለገቡኝ እና ስላልገቡኝ ነገሮች ሁሌም  አመሰግንሃለሁ ።አንተን ለማመስገን ምክኒያቴ እጅግ ብዙ ነውና ዛሬም ነገም ሁሌም አመሰግንሃለሁ ።

✝️✝️የጥበብ ዕይታ✝️✝️

21 Sep, 10:03


Channel name was changed to «✝️✝️የጥበብ ዕይታ✝️✝️»

✝️✝️የጥበብ ዕይታ✝️✝️

21 Sep, 09:55


Channel created

2,445

subscribers

0

photos

0

videos