በሸዋ ግንባር የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ባሉት ሁሉም ክፍለ ጦሮች ባለፉት ቀናቶች ተከታታይ አውደ ውጊያዎች እየተደረጉ ይገኛል።
በአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ አስቴጎማ ክፍለ ጦር 6ኛ ቀኑን በያዘ አውደ ውጊያ ተጋድሎ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን በቅርብ ርቀት ኤፍራታና ግድም ወረዳ 3ተኛ ቀኑን በያዘ አውደ ውጊያ 7ለ70 ክፍለ ጦር ከአገዛዙ ሠራዊት ጋር በመፋለም ላይ ይገኛል። ከዚህ በተጨማሪም ምኒልክ ክፍለ ጦር በመንዝ ቀጠና ተጋድሎ ሲያደርግ ፤ደጅ አዝማች ተሰማ እርገጤ ክፍለ ጦር ሸዋሮቢት ዙሪያ ተጋድሎ እያደረገ ይገኛል።
የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር 7ለ70 ክፍለ ጦር ከጠላት ብልፅግና ሠራዊት ጋር ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ የኦሮሞ ብሄረሰብን መደበቂያ አድርጎ ተደጋጋሚ ጥቃት ለማድረስ ሙከራ ከሚያደርገው ከስርዓቱ አረመኔ ሠራዊት ጋር ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ በርካታ ድሎችን በማስመዝገብ ላይ ነው።
ከትናንት በስቲያ ማምሻ የጀመረውና ማክሰኞ ረፋዱን የተቀጣጠለው አውደ ውጊያ በአጣዬ ከተማ በላይኛው አጣዬ ፈረደ ውሃ ላይ እየተደረገ ሲሆን ትንቅንቁ እስከዚህ ሰዓት ድረስ በከፍተኛ ተጋድሎ ቀጥሏል። በአውደ ውጊያው በርካታ የአገዛዙ ሠራዊት ተደምስሷል። በጀግንነት ከጠላት ሠራዊት ጋር ተናንቀው ከ30 በላይ የብልፅግናን ሠራዊት በእርሳስ ቀለበታቸው ሸኝተው ለወገን ክብር "2 ጀግኖች" በክብር ሰማዕት ሆነዋል። አውደ ውጊያው አሁንም የቀጠለ ሲሆን የጠላት ሀይል እየተገረፈ የወገን ሀይል በአስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል።
በሌላ ግንባር ወደ መንዝ አቅጣጫ ያቀናው የብልፅግና ሠራዊት አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ተመልሷል። ከትናንት ወዲያ ማምሻውን በደፈጣ የጀመረው አውደ ውጊያ በመንዝ ላሎ አጎ ላይ በምኒልክ ክፍለጦር አናብስቶች የጠላት ሠራዊት ተቀጥቅጧል። ከዚህ ባሻገር አገዛዙ በለብ ለብ አሰልጥኖ ደብረብርሃን ያዘጋጃቸውን የሠራዊት አባላት በሁሉም ግንባሮች በማሰማራት እና የአየር ጥቃት ለመፈፀም እያደረገ ባለው ጥረት ከፍተኛ ውጥረቶች ያሉ ሲሆን የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 8ቱ ክፍለጦሮች በሁሉም ግንባር ዝግጁነታቸውን ጨርሰው በተጠንቀቅ ላይ ቆመዋል ሲል የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በገጹ ሰፍሯል።