የትጥቅ ትግል ባልታሰበበት ማንም ባልነቃበት ሁሉም በተኛበት የትጥቅ ትግል ባልተለመደበት በዚያ ጨለማ ጊዜ የአማራን ሕዝብ ከጭቆና ለማላቀቅ ሞጣና አካባቢዋ ወጣቶችን አንቅቶና አደራጅቶ አሰልጥኖ የትጥቅ ትግል በማስጀመር የካቲት 27 _ 2014 አመተ ምህረት የመጀመረያዋን ጥይት ወደ ካድሪ በመተኮስ አርበኛ መዝገቡ ዋለልኝ የትግላችን ችቦ ለኳሽ ጀግና አርበኛ ነበር። የመጀመሪያው የትጥቅ ትግል የጀመርን ዕለት በዚያች ቀን አርበኛ መዝገቡ ዋለልኝ ቢሰዋም 4 ባንዳዎችን በመቀንደሽ 9 ክላሽ 1 ጂም ስሪ በመማረክ ነበር በሞጣ ቀጠና የትጥቅ ትግሉን አሐዱ ብለን የጀመርን። ልክ በዛሬዋ ዕለት የካቲት 27-2014 የትጥቅ ትግሉን በይፋ የጀመርን ዕለት አርበኛ መዝገቡ ዋለልኝ ከእኛ ቢለይም ትግል ቅብብሎሽ በመሆኑ የእሱን አደራ ተቀብለን ከ እነ ተፈራ ዳምጤና ከሌሎች ከተሰው ጀግኖች ጋር ትግሉ ቀጣይነት እንዲኖረው ትግሉ ከሞጣ ቀጠና አልፎ በመላ ጎጃም የትጥቅ ትግሉ እንዲቀጣጠል አድርገናል።
የትጥቅ ትግሉን ስንጀምረው የብልጽግና ካድሬዎች አጥተው ቸግሯቸው ይሉን ነበር። አርበኛ መዝገቡ ዋለልኝም" እኛ የምንታገለው አጥተን አይደለም ለነጻነት ነው" ሲል ነበር ።
ዛሬም የምንታገለው አጥተን ቸግሮን ገንዘብ ለማግኘት የሚመስላቸው አሉ። ገንዘብ ሳይሆን ነጻነት አጥተን ነጻነትን ፍለጋ ወደ ጫካ ከወጣን እነሆ 3 ዓመታትን አስቆጠርን።
ጓድ ቀዳሚ ሰማዕት መዝገቡ ዋለልኝ ለአማራ ነጻነትና ለአማራ አንድነት ሲል ሞጣ ከብት ገበያ ከጎናችን ወድቋል። ጓዳችን ከተሰዋ በበነጋው ጀምረን የተሰዋለትን ለአማራ ነጻነትና አንድነት ለማምጣት እየታገልን እንገኛለን።
በትግላችንም መጠነ ሰፊ ውጊያ በመክፈት የብልጽግና ሰራዊት ተቆጣጥሯቸው የነበሩ ሰፊ ቀጠናዎችን ተቆጣጥረናል። የተቆጣጠርናቸውን ቀጠናዎችንም ከውጊያ ጎን ለጎን የሲቪል አስተዳደር በማዋቀር ሕዝብ እያስተዳደርን እንገኛለን።
ወቅቱ በጠየቀው ትግል ከጋንታ እስከ ክፍለጦር እየተዋጋን እስከዛሬ ያለውን አመርቂ ድል አግኝተናል። አሁን ላይ ግን ከጠላት አሰላለፍ አኳያ ይህ በአውራጃ የተመሰረተ የፋኖ አደረጃጀት ወደ አንድ የአማራ ፋኖ ወታደራዊ ተቋም በማሳደግ በወታደራዊ አንድነትና ቅንጅት ጠላቶቻችንን ደምስሰን ለሕዝባችን የመጨረሻዋን ድል ልናበስረው ይገባል እላለሁ።
አንድነት ኃይል ነው” እንደሚባለው። የመጨረሻውን ድልና ግብ ለሕዝባችን ለማብሰር አንድነት ፈጥሮ ተቀናጅቶ መዋጋት የደረስንበት የትግል ደረጃ ይጠይቃል። ደካማ አገርና ትውልድ የሚወለደው አንድነትን በማጣት በመሆኑ እንደ አማራ አንድ የአማራ ፋኖ ወታደራዊ ተቋም ያስፈልጋል።
ጠላቶቻችን እኛን ለማጥፋት ለእኩይ ግብር ሕብረት ፈጥረው አማራን ለማጥፋት ወደ ሰፈራችን ሲመጡ እኛ ለቅዱስ ዓላማ ለአማራ ፋኖ አንድነት ሲባል የግል ፍላጎትን ገርቶ ወደ አንድነት መምጣት አሸናፊነት እንጂ ውርደት አይደለም ።
እንደ መብረቁ የትጥቅ ትግል ከጀመርንበት ከየካቲት 27- 2014 ዓ.ም ጀምሮ ከአርበኛ መዝገቡ ዋለልኝ መስዋዕትነት በኋላ የትግሉ አስቀጣይና የመብረቁ ፊታውራሪ የነበሩትን እነ ሻለቃ ተፈራ ዳምጤንና ብዙ ጓዶችን በትግሉ ገብረናል። ጓዶቻችን የተሰ_ውት ደግሞ ለአማራ ነጻነትና ለአማራ አንድነት ሲሉ ነው። ጓዶቻችን የተሰውለትን ለአማራ ሕዝብ ነጻነትና አንድነት የሚከፈለውን መስዋዕትነት ሁሉ እየከፈልን የምናስፈጽም ይሆናል።
አዲስ ትውልድ
አዲስ አስተሳሰብ
አዲስ ተስፋ
(የአማራ ፋኖ በጎጃም )